en
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Open in Telegram

📈 Analytical overview of Telegram channel EEP Communication

Channel EEP Communication (@eepcommuication) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 15 679 subscribers, ranking 8 043 in the Technologies & Applications category and 2 176 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 15 679 subscribers.

According to the latest data from 06 September, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 111 over the last 30 days and by -1 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 25.35%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 15.94% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 3 974 views. Within the first day, a publication typically gains 2 500 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 10.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
EEP Communication

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 08 September, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Technologies & Applications category.

15 679
Subscribers
-124 hours
-157 days
+11130 days
Posts Archive
photo content
+9

ኢትዮ - ኤሌክትሪክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ሽንፈት ገጥሞታል ……..///………. በ2ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂው ጨዋታ በሐዋሳ ከነማ አሸናፊነት ተጠናቋል። ከረፋዱ 4 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስቴዲየም በተከናወነው የኢትዮ-ኤሌክትሪክ እና ሐዋሳ ከነማ ጨዋታ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ አንድ ለባዶ ተረቷል። የሐዋሳን ብቸኛ የማሸነፊያ ጎል እፀገነት ግርማ በ26ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፋለች። ከጎሉ መቆጠር በኋላ ተጭኖ የተጫወተው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ያገኛቸውን በርካታ የጎል ዕድሎች አባክኗል። በአንፃሩ ሐዋሳ ከነማ ውጤቱን ለማስጠበቅ በመከላከል ላይ የተመሰረተ የአጨዋወት ስልት ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን ተጫዋጮቹ ሰዓት ለማባከንም በርካታ ጊዜ ሜዳ ላይ ሲወድቁ ተስተውሏል። በ3ኛ ሳምንት መርሃግብር ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከልደታ ክፍለ ከተማ በመጪው አርብ ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስቴዲየም ጨዋታቸውን የሚያከናውኑ ይሆናል። "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+4

የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከላይ ለተዘረዘሩት ክፍት የሥራ መደቦች ሥራ ፈላጊዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከላይ የተዘረዘሩ መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች ከ
የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከላይ ለተዘረዘሩት ክፍት የሥራ መደቦች ሥራ ፈላጊዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከላይ የተዘረዘሩ መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች ከታች በተገለፁት አማራጭ ሊንኮች በመጠቀም የተዘጋጀው ቅጽ የሚጠይቀውን መረጃዎች በሙሉ ሞልቶ በመላክ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ Link 1: https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSf2CT-PMEIAJS7eb2e-4UcDvlUFTTmkaMpQ9RFIJgTqyqgeyw/viewform?usp=sf_link Link 1: https://forms.gle/brmiQnKWc8wQChH38 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም

ማህበሩ ከ48 ሚሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ አግኝቷል .......///......... በ2016 የበጀት  ዓመት ከ48 ነጥብ 21 ሚሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ሥራ ማህበር አስታወቀ። የህብረት ሥራ ማህበሩ የጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የስብሰባ አዳራሽ አካሂዷል። የማህበሩ የሥራ አመራር ቦርድ ሠብሳቢ አቶ አንበሴ ግዛቸው እንደገለፁት ማህበሩ በ2016 በጀት ዓመት 49 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ለማግኘት አቅዶ ከ48 ነጥብ 21 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ በማግኘት የዕቅዱን 98 በመቶ ማሳካት ችሏል። በበጀት ዓመቱ የተገኘው ትርፍ ከቀዳሚው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ወይም የ6 በመቶ ብልጫ እንዳለውም ጠቁመዋል። እንደ አቶ አንበሴ ገለፃ ማህበሩ በበጀት ዓመቱ ከተለያዩ ምንጮች ከ129 ነጥብ 46 ሚሊዮን በላይ ብር ገቢ ማግኘቱንና ይህም ከ2015 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ ያለው ነው። የማህበሩ አጠቃላይ ካፒታል ከ1 ነጥብ 53 ቢሊዮን ብር በላይ እንደደረሰ እና ከ2015  በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ21 በመቶ እድገት እንዳለውም አመልክተዋል። ማህበሩ ለአባላቱ እስከ አሁን 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ብድር  መስጠቱንም ሠብሳቢው አስታውሰዋል። በ2017 በጀት ዓመት አባላቱ በማህበሩ ላይ ያላቸውን የገንዘብ እንቅስቃሴና የብድር መረጃዎችን በቀላሉ በስልካቸው የሚያገኙበትን አሰራር ለመዘርጋት፣ ተጨማሪ የሠው ኃይል ቅጥር ለመፈፀም፣ የህንፃና ተሽከርካሪ ግዥ ለመፈፀም ማቀዱንም አቶ አንበሴ አስረድተዋል። የማህበሩ የቁጥጥር ኮሚቴ ሠብሳቢ አቶ ደረጀ አጥናፌ በበኩላቸው የቁጥጥር ኮሚቴው በጠቅላላ ጉባኤው ላይ የሚሰጡ ውሳኔዎች ተፈፃሚ እንዲሆኑ እየሰራ ይገኛል ብለዋል። ኮሚቴው ከአባላቱ  የሚነሱ ጥያቄዎች እልባት እንዲሰጣቸው በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ አንስተው የአባላቱን እርካታ ለማሳደግ በቀጣይ  ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም አረጋግጠዋል። የማህበሩን የ2016 የሂሳብ ኦዲት ሪፖርት  ያቀረቡት ወ/ሮ አስናቀች መንገሻ በበኩላቸው የኦዲት ሪፖርቱ በማህበሩ የሚቀርቡ የተለያዩ ማስረጃዎችን በማረጋገጥ እንደተከናወነ ተናግረዋል። ማህበሩ በበጀት ዓመቱ ከተለያዩ ምንጮች ከ129 ነጥብ  46 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን እና ከዚህ ውስጥ ከ77 ነጥብ 46 ሚሊዮን ብር በላዩ ለተለያዩ አገልግሎቶች ወጪ መደረጉን በሂሳብ ሪፖርቱ ላይ ቀርቧል። በበጀት ዓመቱ ከተገኘው የተጣራ ትርፍ ውስጥ 33 ነጥብ 75 ሚሊዮኑ ለትርፍ ክፍፍል ድልድል የሚውል ሲሆን ቀሪው 14 ነጥብ 46 ሚሊዮን ብሩ ደግሞ ለመጠባበቂያነት እንደሚቀመጥ  ተመላክቷል። በጉባኤው ላይ የተገኙት በአራዳ ክፍለ ከተማ የህብረት ሥራ ማህበራት ማደራጃ ቢሮ የኢንስፔክሽን ቡድን መሪ አቶ ዳኜ ከበደ እና የማህበራት አስተባባሪ አቶ አስናቀ ጫላ በበኩላቸው ማህበሩ በክፍለ ከተማው ሥር ከሚገኙ አራት ማህበራት መካከል በአባላት ብዛትና የካፒታል መጠን  ቀደሚ ነው ብለዋል። ህብረት ሥራ ማህበሩ ያለውን ዝና ለማስቀጠል የማህበሩ አባላት ከሥራ አመራር ቦርዱ ጋር በትብብር መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል። ክፍለ ከተማው በማህበሩ ላይ ከዚህ በፊት ያጋጠመው ችግር መፍትሔ እንዲሠጠው በትኩረት እየሠራ እንደነበር አውስተው በቀጣይ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚያደርገውን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል  አረጋግጠዋል። በጉባኤው ላይ የማህበሩ የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም፣ የቁጥጥር ኮሚቴና የሂሳብ ኦዲት ሪፖርት እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድና በጀት ጨምሮ ከማህበሩ አባላት መተዳደሪያ ደንብ ጋር በተያያዘ መሻሻል የሚገባቸው የተለያዩ  ድንጋጌዎች ቀርበው በጠቅላላ ጉባኤው አባላት ፀድቀዋል። የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ  ማህበሩ ከ13 ሺ 300 በላይ አባላት አሉት። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ; ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com:/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+2

photo content
+9

photo content
+1

photo content
+9

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በቁጥር ኢኤ.ኃ/8.4/23/16 ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በሹፌር 2ኛ የስራ መደብ ለውጭ አመልካቾች ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በላይ ስማችሁ የተገለጸው አመልካቾች በሙሉ ህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መንጃ ፈቃድ በመያዝ ኮተቤ ብረታብረት በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ የጽሁፍ ፈተና የሚሰጥ በመሆኑ ለፈተና እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ ማሳሰቢያ፡- ለፈተና በምትመጡበት ወቅት ስማችሁ የተገለጸበትን ተራ ቁጥር ማወቅ አስፈላጊ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ; ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com:/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም

የማከፋፈያ ጣቢያው የመንገድ ኮንክሪት ሙሌት ስራ ተጠናቀቀ ........///....... ለገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ኃይል ለማቅረብ እየተገነባ ለሚገኘው ባለ 230 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ የሠራተኞች መኖሪያ ቤት የውስጥ ለውስጥ መንገድ የኮንክሪት ሙሌት ሥራን ዛሬ መከናወኑን የፕሮጀክቱ የሳይት ሥራ አስኪያጅ ገለጹ። ሥራ አስኪያጁ አቶ ቴዎድሮስ ጋሻው እንደገለጹት የማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት አካል የሆነው የሠራተኞች የመኖሪያ ቤት የውስጥ ለውስጥ መንገዱ ለተሸከርካሪ አራት ሜትር እንዲሁም ለእግረኛ ሁለት ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ እየተገነባ ነው፡፡ የውስጥ ለውስጥ መንገዱ ከ100 ሜትር በላይ ርዝመት ሲኖረው ለግንባታው የሚያስፈልገውን 140 ሜትር ኪዩብ ኮንክሪት እና ሥራውን ለማከናወን የሚያስፈልገውን ፓምፕ የመከላክያ ግንባታ ግብዓቶች ማምረቻ ድርጅት እንዳቀረበ ተናግረዋል፡፡ አቶ ቴዎድሮስ እንዳሉት የውስጥ ለውስጥ መንገዱ የኮንክሪት ሙሌት መጠናቀቅ ለፕሮጀክቱ አፈጻፀም ውጤታማነት የራሱ የሆነ አስተዋፅዖ ይኖረዋል፡፡   ከጥቂት ከማጠናቀቁያ ሥራዎች ውጪ የሠራተኞች መኖሪያ ቤት ግንባታ መጠናቀቁን ያወሱት አቶ ቴዎድሮስ የማከፋፈያ ጣቢያውን የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች ለመትከል የሚያስፈልገው የመሠረት ሙሊት ሥራ 80 በመቶ መጠናቀቁንም ጠቁመዋል፡፡ ለኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች መትከያ ከሚያስፈልጉት 314 የመሰረት ሙሊት ሥራዎች መካከል የ243ቱ ሙሌት ሥራ መጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡ የሁለት ትራንስፎርመሮች ማስቀመጫ የኮንክሬት ሙሊት ሥራ ቀደም ብሎ መጠናቀቁን ሥራ አስኪያጁ አስታውሰዋል፡፡ የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክት የግንባታ ሥራ አጠቃላይ አፈፃፀሙ 41 በመቶ መድረሱን አቶ ቴዎድሮስ ተናግረዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ; ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com:/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+3

ስርቆት የአፋር ክልል መገለጫ ባለመሆኑ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ሊታገሉት ይገባል ........///.......... በአፋር ክልል እየተፈፀመ ያለውን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስርቆት ለማስቆም የአካባቢውን የጎሳ መሪዎችና ወጣቶች በማሳተፍ እንደሚሰሩ የገቢረሱ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ገለፁ። የስርቆት ችግሩን ለመከላከል ከገቢረሱ ዞንና አዋሽ 7 ኪሎ ከተማ እንዲሁም ከፈንታሌ ወረዳ ከተውጣጡ አመራሮች፣ የፀጥታ ኃላፊዎች እና የጎሳ መሪዎች ጋር  በተደረገ ውይይት ላይ የዞኑ ዋና  አስተዳዳሪ አቶ አብዱ አሊ እንደገለፁት ስርቆት የአፋር ክልል መገለጫ ባለመሆኑ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ሊታገሉት ይገባል። ማህበረሰቡ ነውር ነው ብሎ የተጠየፈው የስርቆት ድርጊት ለምን እንደተስፋፋ በመለየት ለችግሩ መፍትሔ ለመስጠት መስራት ይገባል ብለዋል። እንደ ዞን አስተዳዳሪው ገለፃ የስርቆት ወንጀሉ የተደራጀና በአቀባይና ተቀባይ ሰንሰለት የተሳሰረ በመሆኑ ድርጊቱን ለማስቆም አመራሩ በቁርጠኝነት መስራት አለበት። አመራሩና የፀጥታ አካሉ በኃላፊነት ስሜት ካልተንቀሳቀሰ በስተቀር በመሰረተ ልማቶቹ ላይ እየተፈፀመ የሚገኘውን የስርቆት ወንጀል ማስቆም አይቻልም ሲሉ ገልፀዋል። የገቢረሱ ዞን ብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባሃባ ሁሴን እንደተናገሩት ስርቆቱ በየትኛውም ወገን ይፈፀም በአፋር ክልል እስከተፈፀመ ጊዜ ድረስ የክልሉን ህዝብ ስም የሚነካ በመሆኑ እስከታችኛው የአስተዳደር መዋቅር ድረስ ግንዛቤ መፍጠርና በባለቤትነት ስሜት እንዲጠበቅ ማድረግ ያስፈልጋል። በኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ የስርቆት ወንጀሎችን ለመከላከል በየደረጃው ያለው የመንግስት መዋቅር፣ ህብረተሰቡና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እጅና ጓንት ሆነው እንዲሰሩ አሳስበዋል። የፈንታሌ ወረዳ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ባህሩ በበኩላቸው በየደረጃው የሚገኙ የዞንና የወረዳ አመራሮች የስርቆት ወንጀሉን ለማስቀረት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ብለዋል። ለህብረተሰቡ አገልግሎት በሚሰጡ የልማት አውታሮች ላይ የስርቆት ወንጀል የሚፈፅሙ አካላትን ለመከላከል የአጎራባች ወረዳዎች በትብብር እንዲሰሩ ነው ጥሪ ያቀረቡት። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን በበኩላቸው በአፋር ክልል በኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ አካላት ላይ የሚፈፀመውን ስርቆት ለማስቀረት በዳጉ ባህላዊ የመረጃ ልውውጥ ስርዓት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ያስፈልጋል ። በመሰረተ ልማቱ ላይ ዝርፊያ የሚፈፅሙ አካላት ብረቶቹን የፍተሻ ኬላዎች የሚያሳልፉት ቅርፃቸውን በመለውጥ በመሆኑ የፀጥታ አካላት የቁጥጥር ስርዓታቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል። በተቋሙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ክትትልና ቁጥጥር ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዋለ ታምሬ በበኩላቸው በመላ ሀገሪቱ በኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይ እየተፈፀመ ያለው የስርቆት ወንጀል ወረርሽኝ አየሆነ መምጣቱን ገልፀዋል። የዞንና የወረዳ አመራሮች ለህብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጡ የኃይል መሰረተ ልማቶችን የመጠበቅ ግዴታ እንዳለባቸውም ነው ያሳሰቡት። በተቋሙ የማዕከላዊ ሁለት ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ዘበርጋ በበኩላቸው ባለፉት ዓመታት በዞኑና በከተማ አስተዳደሮቹ ስለተፈፀሙ የማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ሞሰሶዎች ስርቆት መጠንና ስርቆቱ በየትኞቹ አካባቢዎች እንደሚፈፀም ለተወያዮቹ ገለፃ አድርገዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ; ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com:/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+6

photo content
+9

በዞኑ 507 የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች አካላት ተሰርቀዋል .......///....... በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ባለፉት ሦስት ወራት 507 የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ አካላት መሰረቃቸውን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የምስራቅ አንድ ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን መምሪያ አስታወቀ። የተቋሙ እና የዞኑ አመራሮች ጋር በመሰረተ ልማት ላይ ስለሚፈፀሙ የስርቆት ወንጀሎች በተወያዩበት መድረክ ላይ የሪጅኑ የቴክኒክ ባለሙያ አቶ በሱፈቃድ ባዩ እንደገለፁት በሪጅኑ ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ ከ1 ሺህ 3 መቶ በላይ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶ አካላት ላይ የስርቆት ወንጀል ተፈፅሟል። ከዚህ ውስጥ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ቦርደዴ፣ መኤሶ፣ ቡሲን አርቤ እና ኪቶን ካራ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች 507 የማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ አካላት ተሰርቀዋል። ጉዳት የደረሰባቸውን የምሰሶ አካላት ዳግም ለመጠገን ከ2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ገልፀዋል። ከ2011 እስከ 2016 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን የተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች በሚያልፉ 119 የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ምሰሶዎች ላይ 744 ብረቶች ለስርቆት እንደተዳረጉ የጠቀሱት ባለሙያው ስርቆት የተፈፀመባቸውን የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ጠግኖ ወደ ሥራ ለማስገባት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉን አስታውሰዋል። እንደ አቶ በሱፈቃድ ገለፃ በዞኑ እና በከተማ አስተዳደሮቹ ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ በኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይ የተፈፀመው የስርቆት ወንጀል በአምስት ዓመታት ውስጥ ከተፈፀመው ዝርፊያ ጋር እጅግ ተቀራራቢ ነው። ይህም በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎችና ቀበሌዎች  የሚፈፀመው የስርቆት ወንጀል አሳሳቢነቱ እየጨመረ ለመምጣቱ ማሳያ ነው ብለዋል። በአካባቢው በተደራጀ መልኩ ስርቆት የሚፈፀም መሆኑ፣ የወሰን ማስከበር ጉዳይ፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች ቁርጠኝነት ማነስ እና የሥራ ትብብርን ከጥቅም ጋር የማያያዝ እንዲሁም ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት አፋጣኝ ጥቆማ አለመስጠቱ ለስርቆቱ መባባስ አስተዋጽኦ ማድረጉን ነው ባለሙያው ያብራሩት። በመሰረተ ልማቶቹ ላይ የሚፈፀሙ የስርቆት ወንጀሎችን ከምንጩ ለማድረቅ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የምዕራብ ሀረርጌ ዞን እና የጭሮ ከተማ አስተዳደር በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባም ነው ባለሙያው ያስገነዘቡት። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ; ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com:/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+8

ህብረተሰቡን በማንቀሳቀስ በኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ የስርቆት ወንጀሎችን ማስቆም ይገባል .......///......... በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሀረርጌ ዞን ህብረተሰቡን በማንቀሳቀስ በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ የስርቆት ወንጀሎችን ማስቆም እንደሚገባ የዞኑ ጽ/ቤት ኃላፊ ገለፁ። የጽ/ቤት ኃላፊው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ከምዕራብ ሀረርጌ ዞን እና ከተለያዩ ወረዳዎች ከተውጣጡ አመራሮች፣ የፀጥታ እና ደህንነት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከጭሮ ከተማ አስተዳደር ጋር በኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ ስለሚፈፀሙ የስርቆት ወንጀሎች ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ ላይ በተቋሙ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ስለ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃላይ ገፅታና እንደ ተቋም በኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይ እየደረሱ ስላሉ ጉዳቶች አብራርተዋል። በተቋሙ የምስራቅ አንድ ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ወርዲ መሀመድ በበኩላቸው ከ2011 እስከ 2015 ዓ.ም ድረስ ባሉት ዓመታት በዞኑና በከተማ አስተዳደሩ ስለተፈፀሙ የማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ሞሰሶዎች ስርቆት መጠንና ስርቆቱ በየትኞቹ አካባቢዎች እንደሚፈፀም ለተወያዮቹ ገለፃ አድርገዋል። የጭሮ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መሀመድ ዑመር የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎቹ በተደራጀ መልኩ ከተሰረቁ በኋላ ፖሊሶች ቁጥጥር የሚያደርጉባቸውን የፍተሻ ጣቢያዎች አቋርጠው ስለሚያልፉ ችግሩም ሆነ መፍትሔ ያለው በእኛው እጅ ነው ብለዋል። በአካባቢው የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎችን የሚቆርጡ፣ የሚደልሉ፣ የሚሸጡና የሚገዙ ግለሰቦችንና ለእነርሱ ሽፋን የሚሰጡ የፀጥታ አካላት የሚፈፅሙትን ወንጀል ለመከላከል ተደጋጋሚ የምክክር መድረኮች በማዘጋጀት ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ ገልፀዋል። በምዕራብ ሀረርጌ ዞን የጉምቢ ወረዳ ቦርደዴ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ይርጋ ብሩ እንዳሉት በወረዳው በኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ እየተፈፀመ የሚገኘው የስርቆት ወንጀል እጅግ በጣም አስደንጋጭ ነው። የወረዳው ፀጥታ ዘርፍ የተሰረቁ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች መዳረሻቸውን የመለየትና የመፈተሽ ሥራዎችን መስራቱንም ጠቁመዋል። እንደ ኢንስፔክተር ይርጋ ገለፃ በአካባቢው ከማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ዝርፊያ በተጨማሪ በባቡር ሀዲድ ብረቶች ላይም መሰል ችግሮች እያጋጠሙ ይገኛሉ። የጭሮ ከተማ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዚያድ አማን በበኩላቸው  ከተማ አስተዳደሩ የመብራት መቋረጥን እንደ ፀጥታ ቾግር አድርጎ ይገነዘባል። የስርቆት ድርጊቱ የአካባቢው መገለጫ እንዳይሆን አበክረን እንሰራለን ብለዋል። እንደ አቶ ዚያድ ገለፃ ዝርፊያ ከሚፈፀምበት አካባቢ እስከ አዲስ አበባ ድረስ የተዘረጋ የስርቆት ሰንሰለት በመኖሩ ችግሩን ለማስቆም በጋራ መስራት ይገባል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮች ማስተባበሪያ አንድ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ መንግሥቱ እንደገለፁት የኃይል መሰረተ ልማት ስርቆትን ለማስቀረት የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀም እየተሰራ ነው። የምዕራብ ሀረርጌ ዞንና የጭሮ ከተማ አስተዳደርም የስርቆት ወንጀሉን ለመከላከል የቁጥጥር ሥርዓታቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል። የምዕራብ ሀረርጌ ዞን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቶፊቅ አህመድ በሰጡት የማጠቃለያ ሀሳብ ኤሌክትሪክ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ አመራሩ በኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይ የሚፈፀሙ ዝርፊያዎች ላይ ትኩረት አድርጎ ሊሰራ እንደሚገባው ተናግረዋል። የስርቆት ወንጀሉን በሚፈፅሙ ግለሰቦች ላይ ህጋዊና አስተማሪ  ርምጃ በመውሰድ ድርጊቱን ማስቆም እንደሚገባም ነው አቶ ቶፊቅ ያሳሰቡት። በውይይቱ ላይ የተሳተፉ አመራሮች ህብረተሰቡን በማንቃትና የስርቆት ወንጀሉን በመከላከል ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ; ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com:/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+5

photo content
+9