en
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Open in Telegram

📈 Analytical overview of Telegram channel EEP Communication

Channel EEP Communication (@eepcommuication) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 15 686 subscribers, ranking 8 039 in the Technologies & Applications category and 2 170 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 15 686 subscribers.

According to the latest data from 04 September, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 132 over the last 30 days and by -4 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 26.82%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 15.99% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 4 208 views. Within the first day, a publication typically gains 2 509 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 9.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
EEP Communication

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 05 September, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Technologies & Applications category.

15 686
Subscribers
-424 hours
+57 days
+13230 days
Posts Archive
የህብረተሰቡን የኃይል ጥያቄ የሚመልስ የጋራ አሰራር መዘርጋት ይገባል …….///…….. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በጋራ የሚተገብሯቸው አሰራሮች የኃይል ተጠቃሚ ደንበኞችን ጥያቄ የሚመልሱ እንዲሆን የማከፋፈያ ጣቢያዎችና ማስተላለፊያ መስመሮች ኦፕሬሽን ዘርፍ አሳሰበ፡፡ በዘርፉ የማዕከላዊ 3 ሪጅን እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአዲስ አባባና የሸገር ከተማ የዲስትሪዩቢሽን ኃላፊዎች የ100 ቀናት ዕቅዶቻቸዉ ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡ የሪጅኑ የጥገና ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ  ታደሰ  ገብሬ  እንደገለፁት የውይይቱ ዓላማ በኦፕሬሽን እና ጥገና ሥራዎች የአፈፃፀም መሥፈርት /SOP/ ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ፣ ደንበኞችን ማዕከል ያደረገ የተቀላጠፈ ሥራ ለመስራት እና የኃይል  ጭነትን ለማሻሻል ነው፡፡ በውይይቱ ላይ በሪጅኑ ውስጥ በሚገኙ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች በ15 እና በ33 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች በአዲስ አባባና በሸገር ከተማ ላይ የሚታዩ የኃይል መቆራረጥ ችግሮችን በጋራ መፍታት እና የጋራ አሰራሮችን ማበልፀግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሃሳቦች ቀርበዋል፡፡ በ100 ቀናት ዕቅዱ ላይ የተካተቱ ችግሮችን ለመቅረፍ የጋራ መግባባት ፈጥሮ መንቀሳቀስ እንደሚገባ አቶ ታደሰ አሳስበዋል፡፡ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የምዕራብ አዲስ አበባ ሪጅን የፕላኒንግ ኃላፊ የሆኑት አቶ አለነ ወልዴ በበኩላቸው የመለዋወጫ ዕቃዎች እጥረትና ከአቅም በላይ ጭነት ያለባቸው መስመሮች መኖራቸውን ለሥራቸው እክል እንደሆነ ተናግረዋል። የውይይት መድረከ  ፈጣን የማስተካከያ እርምጃዎችን ለመውሰድ እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡      እንደ አቶ አለነ ገለፃ ተቋማቱ በጋራ የሚሰሯቸዉን ሥራዎች ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር ሊዘረጉ ይገባል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 16 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+4

የማከፋፈያ ጣቢያው የማስፋፊያ ሥራ 63 በመቶ ደርሷል …......///…...... የብሔራዊ ኤሌክትሪክ ደቡባዊ ግሪድ ማስፋፊያ ፕሮጀክት አካል የሆነው የወላይታ ሶዶ ሁለተኛ ማከፋፈያ ጣቢያ የማስፋፊያ ሥራ 63 በመቶ መድረሱን ፕሮጀክቱ አስታወቀ። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የወላይታ ሶዶ ሁለተኛ ማከፋፈያ ጣቢያ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሲቪል መሐንዲስ አቶ አበበ ሚጀና እንደገለጹት የእሳት መከላከያ ግድግዳን ጨምሮ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎችን ለማስቀመጥ የሚያግዙ የመሰረት ሥራዎች ተጠናቀዋል። በአሁኑ ሰዓት የትራንስፎርመር ዘይት የማጣራት ስራ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል። የፍሳሽ ማስወገጃ እና ገመዶች የሚዘረጉበት ቦይ (ኬብል ትሬንች) ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኙ ገልጸው የውስጥ ለውስጥ መንገድ፣ የአጥር ግንባታ እና መሬቱን ጠጠር የማልበስ ተግባራት ደግሞ በቀጣይ እንደሚከናወኑ ጠቁመዋል። ቀሪ ሥራዎችን ክረምት ከመግባቱ በፊት ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነም ተናግረዋል። በሥራ ተቋራጩ ሃዮሰንግ ሄቪይ ኢንደስትሪስ ኮርፖሬሽን የማስፋፊያው የሳይት ኢንጂነር አቶ ቁምላቸው ግርማ እንደተናገሩት የማከፋፈያ ጣቢያው የማስፋፊያ ሥራ እያንዳንዳቸው ባለ 250 ሜጋ ቮልት አምፔር የመጫን አቅም ያላቸው ሁለት ባለ400/230 ኪሎ ቮልት ትራንስፎርመሮች ተከላ ሥራን ያካትታል፡፡ ሥራውን በተያዘለት የጊዜ ገደብ እስከ ህዳር 2018 ዓ.ም ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውንም አብራርተዋል። የፕሮጀክቱ ምዕራፍ አንድ የሳይት ሥራ አስኪያጅ አቶ አንዷለም መላኩ በበኩላቸው ከ14 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ በሆነ በጀት የተጀመረው የወላይታ-ሶዶ ሁለተኛ ማከፋፈያ ጣቢያ የማስፋፊያ ሥራ ሲጠናቀቅ ለአርባምንጭ እና ለኦሞ ኩራዝ አካባቢ አስተማማኝ ኃይል ለማስተላለፍ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። የፕሮጀክቱ የሲቪል ሥራ 69 በመቶ እንዲሁም የኤሌክትሮሜካኒካል ሥራው ደግሞ 25 በመቶ መድረሱን የጠቆሙት ሥራ አስኪያጁ አጠቃላይ አፈጻጸሙ 63 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል። ለማስፋፊያ ሥራው አስፈላጊ የሆኑ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች በአብዛኛው ሳይት በመድረሳቸው ሥራውን በታቀደለት ጊዜ ለማጠናቀቅ የሳይት ሥራ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+8

photo content

የተቋረጠው ከቀናት በኋላ ኃይል መልሶ ተገናኝቷል .......///...... የቆቃ ሁርሶ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች በዘራፊዎች በመውደቃቸው ም
የተቋረጠው ከቀናት በኋላ ኃይል መልሶ  ተገናኝቷል .......///...... የቆቃ ሁርሶ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች በዘራፊዎች በመውደቃቸው ምክንያት በምስራቅ ኢትዮጵያ ተቋርጦ የቆየውን ኃይል መልሶ ማገናኘት መቻሉን  በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ 2 ሪጅን አስታወቀ። የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ዘበርጋ እንደገለፁት ምሽት 2፡19 ሰዓት ላይ የወደቁትን ታወሮች መልሶ የመትከልና የተበጠሰውን የኃይል ማስተላለፊያ የማገናኘት ሥራ ተጠናቆ በአንደኛው ሰርኪዩት የተቋረጠው ኃይል ማገናኘት ተችሏል፡፡ በተከናወነው ሥራ ኃይል ተቋርጦባቸው የቆዩት የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞች በሙሉ ኃይል ማግኘታቸውን አስታውቀዋል፡፡ የተቋረጠው ኃይል መልሶ እስኪገናኝ ድረስ በትዕግስት የጠበቁ  ደንበኞችን ዳይሬክተሩ አመስግነው ህብረተሰቡ የመሰረተ ልማቱን ከስርቆት እንዲከላከል ጥሪ አቅርበዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም

የተቋረጠውን ኃይል መልሶ ለማገናኘት ርብርብ እየተደረገ ነው .......///...... በአፋር ክልል አዋሽ 7 ከተማ አቅራቢያ በዘራፊዎች ተቆርጠው የወደቁትን የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብ
የተቋረጠውን ኃይል መልሶ ለማገናኘት ርብርብ እየተደረገ ነው .......///...... በአፋር ክልል አዋሽ 7 ከተማ አቅራቢያ በዘራፊዎች ተቆርጠው የወደቁትን የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች መልሶ ለመትከል ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ 2 ሪጅን አስታወቀ። የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ዘበርጋ እንደገለፁት የወደቁትን ታወሮች የማለያየት እና የጎደሉትን ብረቶች በመተካት ታወሮቹን መልሶ የማቆም ሥራ ተጀምሯል። በነገው ዕለት ታወሩን መልሶ የማቆም ሥራ በማጠናቀቅ የማስተላለፊያ መስመሩን የማገናኘት እና ኃይል መልሶ የማስተላለፍ ሥራ ሊጀመር እንደሚችል ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። ኃይል በተቋረጠባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ኃይል በትዕግስት እንዲጠብቁ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

ጣቢያው ቀጣናዊ የኃይል ትስስርን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው ........///........ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢትዮ-ኬኒያ ባለ 500 ኪሎ ቮልት ኮንቨርተር ጣቢያ ምስራቅ አፍሪካን በኃይል ለማስተሳሰር ከፍተኛ ሚና እየተጨወተ መሆኑ ተገለጸ። በጣቢያው የጥገናና የኦፕሬሽን ባለሙያ አቶ መኮንን ካሴ እንደተናገሩት የኮንቨርተር ጣቢያው በዲዛይን፣ በቴክኖሎጂ እና በዓይነቱ በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው በመሆን በ2014 ዓ.ም ነው ሥራ የጀመረው። ኮንቨርተር ጣቢያው ከወላይታ ሶዶ ቁጥር ሁለት የማከፋፈያ ጣቢያ በአራት ባለ 400 ኪሎ ቮልት ገቢ መስመሮች ተቀብሎ፣ 12 ኮንቨርተር ትራንስፎርመሮችን እና 1 ሺ 680 ታሪስተሮች(thyristors) ተጠቅሞ ኃይል የሚያስተላልፍ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ ጣቢያው 2 ሺ ሜጋ ዋት ኃይል የመሸከም አቅም ባላቸው በሁለት ፖሎች  እና ከኢትዮጵያ እስከ ኬኒያ በተዘረጋ 1 ሺ 60 ኪሎ ሜትር የማስተላለፊያ መስመር አማካይነት ኃይል እያስተላለፍ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ከኬኒያ ጋር ባለው የኃይል ሽያጭ ስምምነት መሰረት በአሁኑ ወቅት በቀን 18 ስዓት ማለትም እስከ ምሽት 6 ስዓት ድረስ በሰዓት 200 ሜጋ ዋት እንዲሁም ከዚያ በኋላ በሚኖረው ቀሪ 6 ስዓት ደግሞ በሰዓት 65 ሜጋ ዋት ኃይል እየቀረበ ይገኛል ብለዋል። ጣቢያው በስምምነቱ መሠረት እየጨመረ የሚሄደውን የኃይል አቅርቦት እና ወደ ታንዛኒያ ኃይል ለማስተላለፍ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት የሚያስችል አቅም እንዳለውም ገልጸዋል፡፡ በቀጣይ ከሌሎች ሀገራት ጋር የሚደረጉ የኃይል ሽያጭ ስምምነቶችን ተከትሎ አስተማማኝና ኃይል በማስተላለፍ ለአህጉራዊ የኃይል ትስስር መሳለጥ የሚያደርገውን አስተዋጽዖ ለማስቀጠል እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ጣቢያው የኃይል ኤክስፖርቱን ለማሳደግ የተያዘውን ጥረት ለመደገፍ ተለዋጭ ዥረት (Alternative Current) ወደ ቀጥተኛ ዥረት (Direct current) የቴክኖሎጅ ዓይነት ለመለወጥ የተገነባ ማከፋፈያ ጣቢያ በመሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው አስታውሰዋል። ቀጥተኛ ዥረት መሆኑ ከ1 ሺ ኪሎ ሜትር በላይ ያለምንም ተጨማሪ ማከፋፈያ ጣቢያ በሁለት መስመር ብቻ ኃይል ለማስተላለፍ ማስቻሉን የተናገሩት ባለሙያው መስመሩ በተለዋጭ ዥረት ዘዴ የተገነባ ቢሆን ኖሮ ምንአልባትም አራት አካባቢ ማከፋፈያ ጣቢያዎችን መገንባት ያስገድድ ነበር ብለዋል።   በተጨማሪም በፍሪኩየንሲ ልዩነት ምክንያት ግሪድ እንዳይረበሽ፣ የኃይል ብክነት እንዳይኖር፣ ከስምምነት ውጭ ኃይል ከግሪድ እንዳይሄድ እንዲሁም ኃይል መላክ ብቻ ሳይሆን ከኬኒያ ኃይል መቀበል ካስፈለገ ለመቀበል የሚያስችል መሆኑንም አብራርተዋል። የኃይል ሽያጩን ላይ መተማመን እንዲኖር ለማድረግም በኮንቨርተር ጣቢያው እና ሱስዋ ናሮክ ግዛት በሚገኘው የኬንያው ኬትራኮ ኮንቨርተር ጣቢያ ላይ የሁለቱ ተቋማት የኢነርጂ ሜትሮች መተከላቸውንም ጠቁመዋል። ተቋሙ የጣቢያውን የኦፕሬሽንና የጥገና ሥራውን አስተማማኝ ለማድረግ ወደ 20 የሚደርሱ መሐንዲሶችን ሕንድ አገር ድረስ በመላክ ሥልጠና እንዲወስዱ ማድረጉን የጠቆሙት ባለሞያው ማስተላለፊያ መስመሩ ላይ ችግር እንዳያጋጥም የደቡብ 1 እና 2 ሪጅኖች በሚያዋስኑት አከባቢ መሰረት ተከፋፍለው የጥገና ቡድን በማዋቀር ክትትል እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+7

በጣቢያው በራስ አቅም የሚከናወኑ የጥገና ሥራዎች እያደጉ ነው …….///…….. በጊቤ ሦስት ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በራስ አቅም የሚከናወኑ የጥገና ሥራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ገለጹ። ሥራ አስኪያጁ አቶ ሀብታሙ ሰሙ እንደገለጹት ማመንጫ ጣቢያው ሥራ በጀመረበት የመጀመሪያው ዓመት ቻይኖችን በማስገባት የዕውቀት ሽግግር ከተደረገ በኋላ ርክክብ በመፈጸም የጥገና ሥራዎችን በራስ አቅም ማከናወን ጀምሯል። የኃይል ማመንጫ ጣቢያው 1 ሺ 870 ሜጋ ዋት በማመንጨት ለብሔራዊ የኃይል ቋት ከፍተኛውን ድርሻ የሚያበረክት መሆኑን የተናገሩት አቶ ሀብታሙ ይኼን ከግምት ያስገባ የቅድመ መከላከል፣ የትንበያ እና የፍተሻ ጥገና ሥራዎች በጣቢያው ባለሙያዎች እንደሚከናወኑ ገልጸዋል፡፡ በጣቢያው የሚከናወኑ የጥገና ሥራዎችን በራስ አቅም በአግባቡ ለማከናወን ለባለሙያዎቹ አጫጭርና የሥራ ላይ ሥልጠናዎችን እንደሚሰጡ እና እርስ በእርስ የሚማማሩበት ሥርዓት መዘርጋቱንም ጠቁመዋል፡፡ ተርባይኖች እንዳይቆሙ የተበላሹ ዕቃዎች ላይ ማሻሽያ በመስራት ጭምር በርካታ የጥገና ሥራዎችን በራስ አቅም የመስራቱ ልምምድ እያደገ መምጣቱን አብራርተዋል፡፡ ይህም የባለሙያዎችን አቅም በመጠቀም ወጪና ጊዜን በቆጠበ መልኩ አስተማማኝ ኃይል ለማምረት ምቹ መደላድል መፍጠሩን አብራርተዋል። ከኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራ ተቋራጩ የቻይናው ዶንግፋንግ ኤሌክትሪክ ጋር በተደረገ ስምምነት መሰረት የመለዋወጫ ዕቃዎች በወቅቱ እየቀረቡ ነው ያሉት ሥራ አስኪያጁ በስምምነቱ ያልተካተቱት ዕቃዎች ደግሞ በግልጽ ጨረታ እየተገዙ ነው ብለዋል። የጣቢያው የጥገና ባለሙያ አቶ እሸቱ አበራ በበኩላቸው የኃይል ምርቱን በአስተማማኝነት ለመጨመር የሚያስችሉ የጥገና ሥራዎች በራስ አቅም በጣቢያው የጥገና ወርክሾፕ እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ብሬከሮችን ጨምሮ የማቀዝቀዣ ፓምፖች እና ሌሎች የጥገና ሥራዎች በራስ አቅም እንደሚከናወኑ ተናግረዋል። የማቀዝቀዣ ፓምፖች የጥገና ሥራ በውጭ ባለሙያ ቢከናወን ኖሮ ጥገና የሚያስፈልጋቸውን ዕቃዎች ከመጠገን ይልቅ ወደ መቀየር በመግባት ተቋሙን ለተጨማሪ ወጪ ይዳርገው እንደነበር ገልፀዋል። ዕቃዎቹን በጣቢያው ባለሙያዎች በመስራት ወደ አገልግሎት እንዲገቡ መደረጉ ወጪና ጊዜን ከመቆጠቡም በላይ የጣቢያውን የኦፕሬሽን ሥራ የሚያቀላጥፍ ነው ብለዋል። ሠራተኛው አቅሙን አሟጦ እንዲጠቀም እና ሙያዊ ክህሎቱን በማሳደግ ትልልቅ የጥገና ሥራዎችን መስራት እንችላለን የሚል የራስ መተማመን እንዲኖራቸው ዕድል የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል። አቶ እሸቱ የሠራተኛውን አቅም ቀጣይነት ባለው መልኩ የመገንባት፣ የመልዋወጫ እቃ አቅርቦት እና  የክትትልና ድጋፍ ሥራዎች ትኩረት ሊሰጥባቸው እንደሚገባ አሳስበዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+7

ለኢንዱስትሪው ፍላጉት በቂ የኃይል አቅርቦት መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፁ ........///......... በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚፈልገውን የኃይል አቅርቦት ለማሟላት የሚያስችል በቂ ኃይል መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ የፌደራል መንግስት የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምን አስመልክቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ ሰጥተዋል። ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሲሰጡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለፁት በፋብሪካዎችና ኢንዱስትሪዎች በተደረገ ጥናት ቀደም ሲል ሲነሳ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር ሙሉ በሙሉ ተፈቷል፡፡ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ በበጀት ዓመቱ 8 ወራት ለኢንዱስትሪ ሴክተሩ የቀረበው የኤሌክትሪክ ኃይል ምርት 50 በመቶ ዕድገት ሲያሳይ በሀገር ደረጃ ደግሞ 47 በመቶ የኃይል ፍላጎት ዕድገት ተመዝግቧል፡፡ የሚታየው የፍላጎት ዕድገት ከፍተኛ ዝግጅት እንደሚጠይቅ ያሳየ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ታሳቢ ያደረገ የኤሌክትሪከ መሰረተ ልማት ግንባታ አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+1

የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በቅርቡ ሙሉ በሙሉ እንደጠናቀቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ ….///…. የኢትዮጵያ የአንድነት ተምሳሌት የሆነውና ብዙ ውጣ ውረድ የታየበት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት በቅርቡ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በቅርቡ አገልግሎት እንደሚጀመር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ በሚቀጥሉት 6 ወራት የግንባታውን ቀሪ ሥራዎች በማጠናቀቅ የፕሮጀክቱን ፍፃሜ ለኢትዮጵያ ህዝብ እናበስራለን ብለዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአፍሪካ ኩራት ከመሆኑም ባሻገር መቻልን ያሳየንበት፣ በውስጣችን ያለውን ውድቀት ያረምንበት እና 74 ቢሊዮን ሜትር ኩዩብ ውሃ ይዘን ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል የምናመርትበት ሀብት ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፃ የህዳሴ ግድብ አፍሪካውያን የፋይናንስና ዲፕሎማሲያዊ ጫና ቢደረግባቸው እንኳ የራሳቸውን ሀብት በገዛ ዜጎቻቸው አልምተው መቀየር እንደሚችሉ በተግባር የሚያሳይ ነው፡፡ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ከታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ጋር ስላለው ዲፕሎማሲ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ማምረት እንጂ ማንኛውንም ሀገር የመጉዳት ፍላጎት የላትም ብለዋል፡፡ ስለሆነም ግድቡ ግብፅን ጨምሮ በታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ምንም ዓይነት ጉዳት እንደማያመጣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡ ከግብፅ ጋር በተደረጉ ተደጋጋሚ ውይይቶች የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት በአስዋን ግድብ ምንም ዓይነት ተጽዕኖ እንደሌለው ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር ለውይይት፣ ለድርድር እና  በትብብር አብሮ ለመስራት ሁል ጊዜም በሯ ክፍት መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+5

በአዋሽ 7 ኪሎ አካባቢ የተፈፀመው ስርቆት ለምስራቅ ከተሞች ኃይል መቋረጥ ምክንያት ሆኗል .......///...... በአፋር ክልል አዋሽ 7 ኪሎ ከተማ አቅራቢያ በ3 የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ  የብረት ምሰሶዎች ላይ ሥርቆት መፈፀሙን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ 2 ሪጅን አስታወቀ። የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ዘበርጋ እንደገለፁት ከለሊቱ 6:05 አካባቢ ከቆቃ ወደ ሁርሶ በተዘረጋው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተፈፀመው ሥርቆት ድሬዳዋ፣ ሐረር እና ጅግጅጋን ጨምሮ በምስራቅ ኢትዮጵያ በሚገኙ ከተሞች ኃይል ተቋርጧል። የምስራቅ ረጅን 1 ዳይሬክተር አቶ ወርዲ መሀመድ በበኩላቸው ኃይል ለተቋረጠባቸው አካባቢዎች በሌላ አማራጭ ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሰራ ነው። በተቋሙ የትራንስሚሽን ቢዝነስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አንዱዓለም ሲዓ ሥርቆቱ በከተማ አቅራቢያ መፈፀሙ የችግሩን አሳሳቢነት የሚያሳይ በመሆኑ የፀጥታና የመስተዳድር አካላት ድርጊቱን ለመከላከል ትኩረት እንዲሰጡት ጠይቀዋል። ኃይል የተቋረጠባቸው አካባቢዎች በተቻለ ፍጥነት በሌላ አማራጭ ኃይል እንዲያገኙ እየተደረገ ቢሆንም በጊዜያዊነት በቂ ኃይል ላይኖር ስለሚችል ከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚዎች አጠቃቀማቸውን እንዲያስተካክሉ አሳስበዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+6

ማዕከሉ በጣቢያው ያሉ ችግሮችን በመለየት የመፍትሔ ኃሳብ ለማቅረብ እየሰራ ነው .......///....... በጊቤ ሦስት የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የተቋቋመው የጥናት፣ ምርምርና ሥልጠና ማዕከል በጣቢያው ያሉ ችግሮችን በመለየት የመፍትሔ ሀሳቦችን ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። በጣቢያው የኮሙዩኒኬሽን ኢንጅነርና የማዕከሉ አስተባባሪ አቶ ይስሃቅ ወልደየስ እንዳስታወቁት የማመንጫ ጣቢያው የሚያጋጥሙትን ችግሮች በጥናት ላይ ተመስርቶ ለመፍታት ከሦስት ዓመታት በፊት ማዕከሉን አቋቁሟል። ማዕከሉ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ጥናትና ምርምሮችን በመስራት የጣቢያውን የኦፕሬሽንና የጥገና ሥራዎችን ለማቀለጠፍ የሚያግዙ ዘመናዊ አሰራሮችን ለመተግበር ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ማዕከሉ ለጣቢያው የኮሙዩኒኬሽን ሥርዓትና የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን  ተናግረዋል። የወረቀት ሥራዎችን በዘመናዊ የአሠራር ሥርዓት ለመተካት በጣቢያው ኔትወርክ የሚሰራ "ጊቤ ፕላስ" የተሰኘ መተግበሪያ በልጽጎ ወደ ሥራ መግባቱን ገልጸዋል። እንደ አቶ ይስሐቅ ገለፃ መተግበሪያው የእያንዳንዱን የማሽን ታሪክ፣ የንብረት አያያዝ፣ የሰው ኃይሉንና የሚጠቀምባቸውን መሣሪያዎች ኮምፒውተራይዝድ በማድረግ በቀላሉ ታሪካቸውን ለማወቅ የሚያስችል ነው። መተግበሪያው በወረቀት የነበሩ አሰራሮችን በማዘመን ችግሮችን የቀረፈ ቢሆንም አገልግሎቱን ከዚህ የተሻለ ለማድረግ መተግበሪያውን ለማሻሻል ዕቅድ ተይዞ በመስራት ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል። ማዕከሉ በተለይም በጣቢያው የኮሙዩኒኬሽንና የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ የአሰራር ሥርዓቶች ላይ የሚያስፈልጉ ሥልጠናዎችን በመለየት እንደሚሰጥም ጠቁመዋል። የጥናት፣ ምርምርና ሥልጠና ማዕከላት  በማመንጫ ጣቢያዎች ያሉ ችግሮችን በመቅረፍ በኩል ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን የተናገሩት አቶ ይስሃቅ ይኼን ከግምት በማስገባት በተቋሙ መዋቅር ተፈጥሮለት በሰው ኃይልና በግብዓት የሚደራጅበት መንገድ መታሰብ አለበት ብለዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+3

ሪጅኑ የፕላንት ሜንቴናንስ ሞጁል የተጠቃሚዎች ስልጠና እየሰጠ ነው ………//………... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማዕከላዊ ሪጅን 3 ሥር ለሚገኙ የማከፋፈያ ጣቢያ እና ማስተላለፊያ መስመር የጥገና እና ኦፕሬሽን ባለሙያዎች የሳፕ ፕላንት ሜንቴናንስ ሞጁል የተጠቃሚዎች ስልጠና መሰጠት ተጀመረ። የሳፕ ትግበራ ኮሚቴ አባልና አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ወልዳይ ገ/ትንሳኤ እንደገለጹት ሥልጠናው በሪጅኑ የማከፋፈያ ጣቢያዎች እና ማስተላለፊያ መስመሮች የአሰራር ሥርዓት ለማዘመን፣ ጠንካራ የሀብት ቁጥጥር ሥርዓት ለመዘርጋት፣ ወጭ ለመቀነስ እና ሥራን ለማቀላጠፍ አስተዋፅኦው ከፍ ያለ ነው። የፕላንት ሜንቴናንስ ሞጁል የማስተላለፊያና ማከፋፈያ ጣቢያዎችን ንብረቶች የሚመዘግብ ከመሆኑም ባሻገር የጥገና ሥራዎችን በዕቅድ ላይ ተመስርቶ ለማከናወን ፋይዳው የጎላ መሆኑን አስረድተዋል። እንደ አቶ ወልዳይ ገለፃ የሞጁሉ መተግበር የጥገና መረጃዎችን በመሰብሰብና በመተንተን የተሻለ ውሳኔ አሰጣጥ እና ትንበያ እንዲኖር ከማስቻሉም በተጨማሪ  የጥገና ሂደቱን  ሙሉ ለሙሉ በማዘመንና በማቀላጠፍ በኩል ጉልህ ሚና ይጫወታል። ሥልጠናው የማከፋፈያ ጣቢያዎች እና ማስተላለፊያ መስመሮችን ንብረቶች አያያዝና አጠቃቀም ለመከታተልና አስተማማኝነታቸውን ለማረጋገጥ ያስችላል፡፡ በሪጅኑ መደበኛ የፍተሻ እና የጥገና ሥራዎችን  ለመከታተልና የቁጥጥር ሥርዓቱን ለማዘመን እንዲሁም  የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ እንደሚረዳ አቶ ወልዳይ አብራርተዋል። ሥልጠናው በጥገና አሰራር ሥርዓት፣ በመለዋወጫ ዕቃዎች አቅርቦት፣ አስተዳደር እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች የሚያተኩር ሲሆን በሪጀኑ በሚተዳደሩ 20 ማከፋፋያ ጣቢያዎች ውስጥ  ለሚገኙ  ለጥገና  እና ለኦፕሬሽን ባለሙያዎች በአንድ  ወር ቆይታዎች በአራት ዙር እንደሚሰጥ አመልክተዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም