en
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Open in Telegram

📈 Analytical overview of Telegram channel EEP Communication

Channel EEP Communication (@eepcommuication) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 15 559 subscribers, ranking 8 384 in the Technologies & Applications category and 2 165 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 15 559 subscribers.

According to the latest data from 23 June, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 0 over the last 30 days and by -2 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 25.89%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 15.48% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 4 026 views. Within the first day, a publication typically gains 2 408 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 9.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
EEP Communication

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 24 June, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Technologies & Applications category.

15 559
Subscribers
-224 hours
-37 days
No data30 days
Posts Archive
photo content
+4

በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት የፈፀሙ አካላት በቁጥጥር ሥር ውለዋል ……///…. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከኮምቦልቻ 2 ወደ ኮምቦልቻ 1 ማከፋፈያ ጣቢያ በተዘረጋው ባለ 132 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ ስርቆት የፈፀሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን በደቡብ ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡ የተፈፀመው ስርቆት ለአንድ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶ መውደቅና በኮምቦልቻ፣ በደሴ አቀስታ እና ዓለም ከተሞች እና አካባቢያቸው ለመብራት መቋረጥ ምክንያት ሆኖ ነነበር፡፡ በስርቆቱ የተሳተፉ አራት ግለሰቦችን ማለትም ሁለቱ በስርቆቱ በቀጥታ የተሳተፉ፣ አንድ ገዥ እና ቀሪው የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያካሄደ እንደሚገኝ የገለፀው ፖሊስ ፅ/ቤቱ ምርመራውን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለፍርድ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ የሚፈፀም ስርቆት የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል መሆኑን በመረዳት በመሰል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካልት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡም ፖሊስ አሳስቧል፡፡ በቀጣይም በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ የሚፈፀም ስርቆትን ለመከላከል ከማህበረሰቡና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀራርቦ እንደሚሰራ ገልጿል፡፡ የኢነርጂ አዋጅ 810/2006 አንቀጽ 26 በኃይል ማመንጫ፣ ማስተላለፊያ ወይም ማከፋፈያ ተቋማት ላይ ጉዳት ያደረሰ ማንኛውም ሰው ከ5 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ወይም እስከ 50 ሺህ ብር በሚደርስ ገንዘብ ወይም በሁለቱም እንደሚቀጣ ይደነግጋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+2

የህፃናት ማቆያ ማዕከሉ የሠራተኞችን ጫና እያቃለለ ነው ……….///……….. የአዋሽ ሁለት እና ሶስት የኃይል ማመንጫ ጣቢያ የህፃናት ማቆያ ማዕከል በመከፈቱ በሥራ ላይ የሚገጥማቸውን ጫና እያቃለለ መሆኑን የጣቢያው ሠራተኞች ተናገሩ፡፡ በማዕከሉ ልጆቻቸውን በማቆየት ተጠቃሚ የሆኑ የጣቢያው ሰራተኞች እንደተናገሩት ጣቢያው ከሰኞ እስከ አርብ  ልጆቻቸውን ተቀብሎ በመንከባከቡ የሥራ ጊዜያቸውን ለሥራ ለማዋል አስችሏቸዋል፡፡ ማዕከሉ በጣቢያው ውስጥ መከፈቱ ልጆቻቸውን ያለስጋት እንዲቆዩ እና በቅርበት እንዲንከባከቡ ማስቻሉን ተናግረዋል፡፡ በጣቢያው የንብረት አስተዳደርና አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ኮከቤ ተመስገን በበኩላቸው ሁሉም የጣቢያው ሠራተኞች በእውቀት፣ በቁሳቁስ እና በጉልበታቸው በማገዝ ሥራ እንዲጀምር ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡ ማዕከሉ ለጊዜው ስድስት ህፃናት ተቀብሎ በአንድ ተንከባካቢ ሰራተኛ ስራውን መጀመሩን አስረድተዋል፡፡ 💡"ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር↠ https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+6

ሪጅኑ ለኦዲት ግኝቶች ፈጣን ምላሽ መስጠት እንዳለበት ተገለፀ፤ ….///…. ሪጅኑ ለኦዲት ግኝቶች ፈጣን ምላሽ በመስጠት ለተቋማዊ ለውጡ ስኬት የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የውስጥ ኦዲት ዘርፍ አሳሰበ፡፡ ዘርፉ ከምስራቅ ሪጅን አንድ ለተውጣጡ ባለሙያዎችና የሥራ ኃላፊዎች በተቋማዊ ለውጡ እና በውስጥ ኦዲት ሥራዎች ዙሪያ በድሬድዋ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ የዘርፉ ሥራ አስፈፃሚ አቶ መርጋ ተረፈ እንደገለጹት ስልጠናው ሪጅኑ ሥራውን ግልፅነትንና ተጠያቂነትን ባሰፈነ መልኩ በማከናወን ተቋሙ እየተገበረ ያለውን ተቋማዊ ለውጥ ለማሳካት የሚችሉበትን ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡ የውስጥ ኦዲት ሥራ የተቋሙን የመልካም አስተዳደር፣ የሥራ ቅልጥፍናና የፋይናንስ ጤንነት እንዲሁም የቁጥጥር ሥርዓቱን በመገምገምና በማሻሻል ተቋማዊ ስኬትን ለማምጣት እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡ ኦዲትን ከፋይናንሽያል ምርመራ ጋር ብቻ የማያያዝ አመለካከት መኖሩን የጠቆሙት አቶ መርጋ ዘርፉ ይሄን አመለካከት ለማስተካከል ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራትን ለማከናወን አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡ ሪጅኑ የሚያከናውኗቸው ሥራዎች በተቋሙ የተቀመጡ ፖሊሲዎችና ደንቦችን የተከተለ እና ከብክነት የፀዱ መሆናቸውን በማረጋገጥ እንዲሁም ለኦዲት ግኝቶች ፈጣን ምላሽ በመስጠት በኩል ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡ የውስጥ ቁጥጥርን በማጠናከር፣ የስጋት አስተዳደርን በማሻሻል፣ የሕግና ደንብ ተገዢነትን በማረጋገጥ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን ማስፈን ለአንድ አካል ብቻ የሚተው ባለመሆኑ የውስጥ ኦዲት ሥራውን በተሳካ ሁኔታ ለማከናወን ሁሉም በእኔነት ስሜት እንዲሰራ አሳስበዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+5

ፕሮጀክቱ ከመተግበሩ በፊት ጥናት መካሄዱ ተቀባይነቱ እንዲጎላ አድርጎታል ………///……… የአርባ ምንጭ 2ኛ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ ከመጀመሩ በፊት የአካባቢያዊና ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ተፅእኖ ጥናት መከናወኑ ፕሮጀክቱ በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ማድረጉ ተገለፀ፡፡ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የካሳ ጉዳዮች አስተባባሪ አቶ ኢዘዲን ሸምሱ እንደገለፁት የፕሮጀክቱ ግንባታ ከመጀመሩ በፊት በአካባቢው ሥነ ምህዳርና በማህበረሰቡ ላይ ሊፈጥር የሚችለው አወንታዊና አሉታዊ ተፅዕኖ እና ተፅዕኖዎችን እንዴት ማስቀረት እንደሚቻል ከዞን እስከ ቀበሌ ካሉ የመስተዳድር አካላት እና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡ ግንባታው የሚካሄድበት ቦታ ለ140 ግለሰቦች ለቤት መስሪያነት በመመራቱና በውስጡም ስምንት መቃብሮች መኖራቸው በጥናቱ ስለተለየ ከዞን መስተዳደር፣  ቤት እንዲሰሩ ከተመሩ ግለሰቦች እና ከሟች ቤተሰቦች ጋር በመነጋገር መፍትሔ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የማስተላለፊያ መስመሩ ለማህበራዊ አገልግሎት በተሰጠ ቦታና በዞኑ አስተዳደር ህንፃ ላይ እንደሚያልፍ በጥናቱ በመረጋገጡ የሚዘረጋበት ቦታ እንዲቀየር መደረጉንም አቶ ኢዘዲን ጠቅሰዋል፡፡ በፕሮጀክቱ ላይ የተካሄደው ጥናት በኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ማረጋገጫ ተሰጥቶት እና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በማከናወን ወደ ትግበራ መገባቱንም ተናግረዋል፡፡ በፕሮጀክቱ ላይ ጥናትና ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት ሳይደረግ ወደ ሥራ ቢገባ ኖሮ በማህበረሰቡ ተቀባይነት ላያገኝ ይችል ነበር ያሉት አስተባባሪው ይህም በግንባታ ሥራው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ በፕሮጀክቱ አማካሪ ባዮሰን ፓወር ኩባንያ የአርባ ምንጭ 2ኛ ማከፋፈያ ጣቢያ የአካባቢና ማህበረሰባዊ ጉዳዮች እንዲሁም የጤናና የሥራ ላይ ደህንነት ባለሙያ አቶ ቤካን ዳምጠው በበኩላቸው ሥራ ተቋራጩ አካባቢውን የማይበክሉ ማሽነሪዎች እንዲጠቀም እና ለፕሮጀክቱ ግንባታ የዋሉ የተለያዩ ተረፈ ምርቶች በአግባቡ እንዲወገዱ ክትትል እየተደረገ ስለመሆኑም ገልፀዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር↠ https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክአካውንት↠ https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+5

photo content
+2

ለተቋረጠው ኃይል ጊዜያዊ መፍትሄ ተሰጥቷል .........///....... ትናንት በስርቆት ምክንያት የወደቀው የኮምቦልቻ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር  የብረት ምሰሶ በጊዜያዊነት በእንጨት ምሰሶ መተካቱን  በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ምስራቅ አንድ ሪጅን አስታወቀ። የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ በድሩ አህመድ እንደገለፁት በኮምቦልቻ ከተማ አቅራቢያ በተፈፀመው ዝርፊያ የወደቀውን የብረት ታወር በእንጨት ምሰሶ ሲተካ የተፈታታውን ታወር ደግሞ በማጥበቅና የጎደሉ አካሎችን በማሟላት አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጓል። ለጊዜው በተከናወነው ጥገና  በኮምቦልቻ ከተማና አካባቢው፣ በደሴ ከተማና አካባቢው፣ በአቀስታ ከተማና አካባቢው እንዲሁም በዓለም ከተማና አካባቢው የተቋረጠው ኃይል ማምሻውን መመለሱን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

ፕሮጀክቱ ከመተግበሩ በፊት ጥናት መካሄዱ ተቀባይነቱ እንዲጎላ አድርጎታል ………///……… የአርባ ምንጭ 2ኛ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ ከመጀመሩ በፊት የአካባቢያዊና ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ተፅእኖ ጥናት መከናወኑ ፕሮጀክቱ በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ማድረጉ ተገለፀ፡፡ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የካሳ ጉዳዮች አስተባባሪ አቶ ኢዘዲን ሸምሱ እንደገለፁት የፕሮጀክቱ ግንባታ ከመጀመሩ በፊት በአካባቢው ሥነ ምህዳርና በማህበረሰቡ ላይ ሊፈጥር የሚችለው አወንታዊና አሉታዊ ተፅዕኖ እና ተፅዕኖዎችን እንዴት ማስቀረት እንደሚቻል ከዞን እስከ ቀበሌ ካሉ የመስተዳድር አካላት እና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡ ግንባታው የሚካሄድበት ቦታ ለ140 ግለሰቦች ለቤት መስሪያነት በመመራቱና በውስጡም ስምንት መቃብሮች መኖራቸው በጥናቱ ስለተለየ ከዞን መስተዳደር፣  ቤት እንዲሰሩ ከተመሩ ግለሰቦች እና ከሟች ቤተሰቦች ጋር በመነጋገር መፍትሔ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የማስተላለፊያ መስመሩ ለማህበራዊ አገልግሎት በተሰጠ ቦታና በዞኑ አስተዳደር ህንፃ ላይ እንደሚያልፍ በጥናቱ በመረጋገጡ የሚዘረጋበት ቦታ እንዲቀየር መደረጉንም አቶ ኢዘዲን ጠቅሰዋል፡፡ በፕሮጀክቱ ላይ የተካሄደው ጥናት በኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ማረጋገጫ ተሰጥቶት እና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በማከናወን ወደ ትግበራ መገባቱንም ተናግረዋል፡፡ በፕሮጀክቱ ላይ ጥናትና ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት ሳይደረግ ወደ ሥራ ቢገባ ኖሮ በማህበረሰቡ ተቀባይነት ላያገኝ ይችል ነበር ያሉት አስተባባሪው ይህም በግንባታ ሥራው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ በፕሮጀክቱ አማካሪ ባዮሰን ፓወር ኩባንያ የአርባ ምንጭ 2ኛ ማከፋፈያ ጣቢያ የአካባቢና ማህበረሰባዊ ጉዳዮች እንዲሁም የጤናና የሥራ ላይ ደህንነት ባለሙያ አቶ ቤካን ዳምጠው በበኩላቸው ሥራ ተቋራጩ አካባቢውን የማይበክሉ ማሽነሪዎች እንዲጠቀም እና ለፕሮጀክቱ ግንባታ የዋሉ የተለያዩ ተረፈ ምርቶች በአግባቡ እንዲወገዱ ክትትል እየተደረገ ስለመሆኑም ገልፀዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር↠ https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክአካውንት↠ https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 6 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+4

ፕሮጀክቱ በጥናት ውጤቱ መሰረት እየተከናወነ ነው ……..///……… የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በአካባቢያዊና ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ተፅዕኖ ግምገማ ጥናት ውጤት መሰረት መከናወኑን በፕሮጀክቱ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያ አስታወቁ፡፡ ባለሙያው አቶ አዲሱ እጅጉ እንዳስታወቁት ፕሮጀክቱ በሚከናወንበት ወቅትና ወደ ኦፕሬሽን ሲገባ በአካባቢና በማህበረሰቡ ላይ ሊኖር የሚችለውን አሉታዊና አዎንታዊ ተፅእኖ ለመለየትና መፍትሔ ለማስቀመጥ የአካባቢያዊና ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ተፅዕኖ ግምገማ ጥናት ተካሂዷል፡፡ ጥናቱ ፕሮጀክቱ በአካባቢው መልከዓ ምድር፣ በአየር ንብረት፣ በውሃ አካላት፣ በእፅዋት፣ በእንስሳትና ማህበረሰቡ ላይ ጉዳት ማድረሱንና አለማድረሱን ለማወቅ ትኩረት ያደረገ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡ በጥናቱ ላይ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት መሳተፋቸው እና ጥናቱ በትክክለኛመረጃ ላይ ተመስርቶ መከናወኑ ፕሮጀክቱ ወደ ትግበራ ሲገባ በማህበረሰቡ ተቀባይነት እንዲኖረው ከማድረግ ባለፈ ከማህበረሰቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች በጥናቱ መሰረት ምላሽ መሰጠቱን ጠቅሰዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም መሬታቸው በፕሮጀክቱ ለተወሰደባቸው አካላት አስፈላጊውን የካሳ ክፍያ ለመፈፀም፣ ማህበረሰቡ በፕሮጀክቱ ላይ የባለቤትነት ስሜት እንዲኖረው እና ፕሮጀክቱን በተያዘለት ጊዜ እንዲከናወን ለማድረግ ማገዙንም አስረድተዋል፡፡ ፕሮጀክቱ አሁን ለደረሰበት አፈፃፀም የአካባቢያዊና ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ተፅዕኖ ግምገማ ጥናት ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ባለሙያው አመልክተዋል፡፡                                                                                                                     የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በአርሲ ዞን ሂጦሳ ወረዳ ከሚገኙ ቀበሌዎች አራቱን  ያካልላል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር↠ https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠  https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 6 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+3

በኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ስርቆት የተነሳ በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ኃይል ተቋርጧል .........///....... ከኮምቦልቻ 2 ወደ ኮምቦልቻ 1 ማከፋፈያ ጣቢያ በተዘረጋው ባለ 132 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ በተፈፀመ ዝርፊያ ዛሬ ከረፋዱ 5:30 ሰዓት አካባቢ በአንዳንድ አካባቢዎች ኃይል ተቋርጧል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ምስራቅ አንድ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ በድሩ አህመድ እንደገለፁት በኮምቦልቻ ከተማ አቅራቢያ በተፈፀመው ዝርፊያ አንድ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ሲወድቅ ሌላኛው ተፈታቶ ከመውደቁ በፊት ተደርሶበታል። በዚህ የተነሳ በኮምቦልቻ ከተማና አካባቢው፣ በደሴ ከተማና አካባቢው፣ በአቀስታ ከተማና አካባቢው እንዲሁም በዓለም ከተማና አካባቢው ኃይል መቋረጡን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል። የኮምቦልቻ ቁጥር አንድ ማከፋፈያ ጣቢያ ወደ ደሴ በ66 ኪሎ ቮልት፣ ወደ አቀስታ እና ዓለም ከተማ ማከፋፈያ ጣቢያዎች በ132  ኪሎ ቮልት እንዲሁም ለኮምቦልቻ ከተማ በ15 ኪሎ ቮልት ኃይል ሲሰጥ ነበር። የወደቀውን የብረት ምሰሶ መልሶ ለማቆምና የመውደቅ ስጋት ያጠላበት ሁለተኛውን ምሰሶ በሌሎች ድጋፎች መልሶ ለማቆም ጊዜ የሚፈልግ በመሆኑ ህብረተሰቡ ችግሩን ተገንዝቦ በትዕግስት እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 5 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+2

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ከባንያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚስተር ጋሲማ ኒያሞ ሀንጋ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል። ኒያሞ ሀንጋ የታንዛኒያን ብሎም የቀጣናውን ኢነርጂ ዘርፍ በምስራቅ አፍሪካ የኃይል ቋት በኩል ለማላቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ባለራዕይና ቁርጠኛ መሪ ሲሉ ዋና ሥራ አስፈፃሚው ገልፀዋቸዋል። በተሽከርካሪ ድንገተኛ አደጋ በደረሰባቸው ህልፈት በእጅጉ ማዘናቸውን ያስታወቁት ኢንጂነር አሸብር ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸውና ለታንዛኒያ ኤሌክትሪክ ኩባንያ መጸናናትን ተመኝተዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 5 ቀን 2017 ዓ.ም

Condolence Message from the CEO of Ethiopian Electric Power (EEP) It is with profound sorrow that I extend my heartfelt condolences on the sudden and tragic passing of Mr. Gissima Nyamo-Hanga, Managing Director of TANESCO, who lost his life in a road accident. Mr. Nyamo-Hanga was a committed and visionary leader whose efforts significantly contributed to advancing the power sector in Tanzania and the regional power trade through the Eastern Africa Power Pool (EAPP). His passing is a significant loss to TANESCO and the broader energy community in EAPP. I express our deepest sympathies to his family, colleagues, and the TANESCO family on behalf of EEP and myself. May you find strength during this difficult time, and may his soul rest in eternal peace. Eng. Ashebir Balcha Chief Executive Officer, EEP 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠https://twitter.com/EEPethiopia ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power ዩትዩብቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ሚያዝያ 5 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content