en
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Open in Telegram

📈 Analytical overview of Telegram channel EEP Communication

Channel EEP Communication (@eepcommuication) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 15 533 subscribers, ranking 8 368 in the Technologies & Applications category and 2 174 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 15 533 subscribers.

According to the latest data from 30 June, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 10 over the last 30 days and by -6 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 24.86%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 16.87% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 3 862 views. Within the first day, a publication typically gains 2 620 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 9.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
EEP Communication

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 01 July, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Technologies & Applications category.

15 533
Subscribers
-624 hours
-207 days
+1030 days
Posts Archive
photo content
+1

photo content
+9

በማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ ላይ የስርቆት ወንጀል እየተፈፀመ ነው ………///……… 82 በመቶ የደረሰው የአዋሽ- ወልዲያ- ሀራ ገበያ የባቡር መስመር የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ፕሮጀክት ተደጋጋሚ ስርቆት እየተፈፀመበት መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታ ዘርፍ የፕሮጀክቱ የሳይት ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ። ሥራ አስኪያጁ አቶ ተክለወይኒ ብርሃነ እንዳስታወቁት በፕሮጀክቱ ላይ እስከ አሁን ከተተከሉ 175 የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሶሶዎች መካከል በ37ቱ ላይ ስርቆት ተፈፅሞባቸዋል። ከመስከረም 2 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተፈፀመው ስርቆት 6 ሺህ የሚሆኑ የምሰሶ ብረቶች ተፈተው የተወሰዱ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 262 የሚሆኑት በፖሊስ በኤግዚቢትነት ተይዘው እንደሚገኙ ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል። በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ዱብዱብ በሚባል ቀበሌ በፕሮጀክቱ ላይ የተፈፀመው ስርቆት የግንባታ ሥራውን በተያዘለት ጊዜና በጀት ለማጠናቀቅ እንቅፋት እንደሚሆንም አመልክተዋል። አቶ ተክለወይኒ እንዳሉት ስርቆቱ ከተፈፀመ ጀምሮ ችግሩ በስፋት በሚስተዋልበት አካባቢ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የቁጥጥርና የጥበቃ ሥራ በመጀመሩ የስርቆት ወንጀሉ የመቀነስ አዝማሚያ አሳይቷል፡፡ ስርቆቱን በተቋሙ፣ በሥራ ተቋራጩ እና በፀጥታ አካላት ብቻ ማስቆም ስለማይቻል ህዝቡ በአካባቢው የተተከሉ የመስመር ተሸካሚ ምሶሶዎችን በእኔነትና በኃላፊነት ስሜት እንዲጠብቅ ለማድረግ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሆነም አስረድተዋል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ፕሮግራም-2 የፕሮጀክት አስተዳደር-1 ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮናስ አባዲ በበኩላቸው በፕሮጀክቱ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የስርቆት ወንጀል ለመከላከል ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ በስርቆቱ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል እና ህዝቡ ንብረቱን በሚጠብቅበት መንገድ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር፤ በየደረጃው ካሉ የዞን፣ የወረዳና የከተማ የፀጥታ አካላት የተውጣጣ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ መገባቱን ተናግረዋል። የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ የግንባታ ሥራ ተቋራጭ ፒንጋኦ ግሩፕ የሳይት ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ዣይ በበኩላቸው በፕሮጀክቱ ላይ በተፈፀመው ስርቆት ምክንያት በአሁኑ ሰዓት የግንባታ ሥራውን በአግባቡ ማከናወን አልተቻለም ብለዋል። ከአንድ ምሶሶ ከ150 እስከ 200 የሚጠጉ ብረቶች ተፈተው እንደተወሰዱ የጠቆሙት ሥራ አስኪያጁ ተሰርቀው የተወሰዱትን ብረቶች ለመተካት 12 ነጥብ 5 ማሊዮን ብር እንደሚጠይቅ ተናግረዋል። በፕሮጀክቱ ላይ እየተፈፀመ ያለው ስርቆት በወቅቱ መፍትሄ ካልተሰጠው ግንባታውን በተያዘለት በጀት እና ጊዜ አጠናቆ ለማስረከብ ፈታኝ እንደሚያደርገው እና የግንባታ እንቅስቃሴውን አደጋ ላይ እንደሚጥለውም የሥራ ኃላፊዎች አስገንዝበዋል። እስከ አሁን ከስርቆት ወንጀሉ ጋር በተገናኘ ሰባት ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ እና ከዚህ ውስጥ አራቱ ከንብረቱ ጋር እጅ ከፈንጅ የተያዙ መሆናቸውን ከአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል። የአዋሽ - ወልዲያ - ሀራ ገበያ የባቡር መስመር የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ፕሮጀክት በመቶ ደርሷል፡፡ "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 06 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content
+4

የህፃናት ማቆያ ማዕከሉ 34 ህፃናትን ተቀብሎ እስተናገደ ነው ……..///……. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የህፃናት ማቆያ ማዕከል 34 የሰራተኞች ህፃናትን ተቀብሎ በማዋል ሴት ሰራተኞች በተረጋጋ ስሜት ሥራቸውን እንዲያከናዉኑ እያገዘ መሆኑን የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች መምሪያ አስታወቀ፡፡ የመምሪያው ዳይሬክተር ወ/ሮ ሌንሲ ኢደኤ እንደተናገሩት ማዕከሉ የተቋሙን ሴት ሰራተኞች ህፃናት ልጆች ተቀብሎ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ስዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ስዓት ድረስ በመንከባከብ ላይ ይገኛል፡፡ ማዕከሉ በመቋቋሙ ሠራተኞቹ የስራ ጊዜያቸውን ሳያባክኑ እና ለልጆቻቸው ደህንነት ስጋት ሳይሰማቸው ስራቸውን በአግባቡ እንዲያከናውኑ እያገዘ ነው ብለዋል፡፡ የህፃናት ማቆያ ማዕከሉ ከ6 ወር እስከ 4 ኣመት ድረስ ላሉ የተቋሙ ሴት ሰራተኞች ልጆች የመኝታ፣ የመጫወቻ፣ የምግብና ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶችን የሚሰጥ መሆኑ ደረጃውን የጠበቀ ማቆያ እንደሚያደርገው ወ/ሮ ሌንሴ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የህፃናት ማቆያ ማዕከል 1 ነርስ እና ስድስት ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚሰጡ ሠራተኞችን አሉት፡፡ ኮተቤ በሚገኘው አዲሱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገነባው የህፃናት ማቆያ ማዕከል ሜክሲኮ ከነበረው የማቆያ ማዕከል ጋር ሲነፃፀር በዘመናዊ መልክ ከመገንባቱ ባሻገር ተቋሙ ለሰራተኖቹ የሰጠውን ትኩረት ያሳያል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ህይወታቸውን በኤች አይ ቪ/ኤድስ ላጡ የተቋሙ ሠራተኞች ልጆች የገንዘብ እገዛ እየተደረገ መሆኑን በመምሪያው የስርዓተ ፆታ ባለሙያ አቶ ተስፋዬ ዮሐንስ ገልፀዋል፡፡ እንደ ባለሙያው ገለፃ ከ 18 ዓመት በታች ለሆኑ የተቋሙ ሰራተኞች ልጆች በየወሩ 500 ብር ገንዘብ ድጋፍ እየተደረገ ነው፡፡ በዋናው መ/ቤትና በተለያዩ የተቋሙ የስራ አካባቢዎች የውይይት መድረኮችን በመፍጠር ሠራተኞች ስለ ቫይረሱ የተሻለ ግንዛቤ እያገኙ መሆናቸውን እና እያንዳንዱ የተቋሙ ሠራተኞች ከደመወዙ ላይ ተቆራጭ በማድረግ ኤች አይ ቪ በደማቸው የሚገኝ ሠራተኞችና ቤተሰቦታቸውን እንደሚደጉም ባለሙያው አስታውቀዋል፡፡ "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@Ethiopianelectricpower ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 06 ቀን 2016 ዓ.ም

photo content