en
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Open in Telegram

📈 Analytical overview of Telegram channel EEP Communication

Channel EEP Communication (@eepcommuication) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 15 555 subscribers, ranking 8 397 in the Technologies & Applications category and 2 165 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 15 555 subscribers.

According to the latest data from 21 June, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 10 over the last 30 days and by 1 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 25.74%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 14.94% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 4 003 views. Within the first day, a publication typically gains 2 323 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 9.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
EEP Communication

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 22 June, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Technologies & Applications category.

15 555
Subscribers
+124 hours
+87 days
+1030 days
Posts Archive
photo content
+9

photo content

photo content
+9

የተሽከርካሪ ስምሪት እና ቁጥጥርን ለማዘመን እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ውጤት እየተገኘባቸው ነው ………///………. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተሸከርካሪ ስምሪት እና ቁጥጥርን ለማዘመን የተገበራቸው የአሰራር ስርዓቶች ውጤት እየተገኘባቸው መሆኑን በተቋሙ የተሽከርካሪ አስተዳደር ቢሮ ገለፀ። የቢሮው ሥራ አስኪያጅ አቶ ዋለ ታምሬ እንደገለፁት ተቋሙ የተሸከርካሪዎችን ስምሪት ለማሳለጥ እና የቁጥጥር ስርዓቱን ለማዘመን የጂ.ፒ.ኤስ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡ የጂ.ፒ.ኤስ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ተሽከርካሪዎች የመስክ ሥራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ያለ ሥራ የሚቀመጡበት ጊዜ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ ይህም የተሸከርካሪ እጥረት እንዲከሰት በማድረግ የሥራ ክፍሎች  ሥራቸውን በዕቅዳቸው መሰረት እንዳያከናውኑ እንቅፋት ሆኖ እንደነበር አቶ ዋለ ተናግረዋል፡፡ በተሸከርካሪ ስምሪት እና ቁጥጥርን ላይ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በአሁኑ ወቅት በተቋሙ ካሉ 1 ሺህ 40 ተሸከርካሪዎች መካከል 500 በሚሆኑት ላይ ጂ.ፒ.ኤስ መገጠሙንም ነው ያስታወቁት፡፡ ተሸከርካሪዎችን በቴክኖሎጂ በመከታተል ሥራቸውን ጨርሰው ሲመለሱ ለሌላ ስምሪት ዝግጁ በማድረግ እና የተቋሙን ሥራ ውጤታማ ለማድረግ የራሱ የሆና አስተዋጽዖ እንዳለው አስረድተዋል፡፡ የጂፒኤስ ቴክኖሎጂው ሥራን ከማቀላጠፍ በተጨማሪ ከዚህ በፊት ከነዳጅ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የነበሩ ችግሮችን በማቃለል ተቋሙን ከተጨማሪ ወጭ እየታደገው ይገኛል ብለዋል፡፡ እንደ አቶ ዋለ ገለፃ ማሻሻያው በአሃዝ የተደገፈ ግልጽ መረጃ ለማግኘት ከማስቻሉም ባለፈ ተሸከርካሪዎች ከተመደቡበት መስመር ሲወጡና ከፍጥነት ወሰን በላይ ሲጓዙ መልዕክት ወደ ማዕከል ያደርሳል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication to 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መስከረም 7 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content

#vacancy የፈተና ውጤት ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በጀማሪ ኤሌክትሪካል መሐንዲስ እና በጀማሪ መካኒካል መሐንዲስ የስራ መደብ ለመቅጠር ነሐሴ 07 እና ነሐሴ 08 ቀን 2017 ዓ.ም
+2
#vacancy የፈተና ውጤት ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በጀማሪ ኤሌክትሪካል መሐንዲስ እና በጀማሪ መካኒካል መሐንዲስ የስራ መደብ ለመቅጠር ነሐሴ 07 እና ነሐሴ 08 ቀን 2017 ዓ.ም የጽሁፍ ፈተና መስጠቱ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም በጀማሪ ኤሌክትሪካል መሐንዲስ የስራ መደብ የጽሁፍ ፈተና ተፈትናችሁ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 15 እንዲሁም በጀማሪ መካኒካል መሐንዲስ የስራ መደብ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 ስማችሁ የተገለጸው አመልካቾች በተሰጠው የፅሁፍ ፈተና አብላጫ ውጤት ያመጣችሁ በመሆኑ ከመስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 (አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ ኮተቤ በሚገኘው በዋናው መ/ቤት የሰው ኃይል ቅጥርና ምደባ ቢሮ በመገኘት የትምህርት ማስረጃ ዋናውን እና ኮፒ በመያዝ ቀርባችሁ የቅጥር ሂደት እንድትፈጽሙ እያሳወቅን፤ ስማችሁ ያልተገለጸው አመልካቾች የማለፊያ ውጤት ያላመጣችሁ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication to 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et መስከረም 5 ቀን 2017 ዓ.ም

እንኳን ለ2018 አዲስ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ! አዲስ ዓመት ሁሌም ተስፋ ይዞ የሚመጣ የበዓላት ሁሉ በኩር ነው፡፡ የዘመን መቀየር ተስፋችንን የሚያለመልም እና ወደፊት እንድናስብ የሚያደርግ ከመሆኑ
እንኳን ለ2018 አዲስ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ! አዲስ ዓመት ሁሌም ተስፋ ይዞ የሚመጣ የበዓላት ሁሉ በኩር ነው፡፡ የዘመን መቀየር ተስፋችንን የሚያለመልም እና ወደፊት እንድናስብ የሚያደርግ ከመሆኑም ባሻገር በአዲስ ዓመት ዋዜማ ለምርቃት የበቃው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ደግሞ ተስፋችንን ምሉዕ ያደርገዋል፡፡ እንደ ተቋም ብቻ ሳይሆን እንደሀገር ለምናቅዳቸው ሥራዎች መሳካት ትልቅ አቅም እንደሚሆን እምነቴ የፀና ነው፡፡ ስለሆነም በአዲሱ ዓመት "የአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ማዕከል" የመሆን ራዕያችንን እውን ለማድረግ የምንሠራበት፣ ሁለንተናዊ ተቋማዊ ስኬት የምናስመዘግብበት እንዲሁም በግል ያቀድናቸውን ውጥኖች ከግብ የምናደርስበት የሠላም፣ የደስታና የስኬት ዘመን እንዲሆን እመኛለሁ!! መልካም አዲስ ዓመት! አሸብር ባልቻ (ኢንጂነር) ዋና ሥራ አስፈፃሚ

በቅርቡ የኃይል ትስስር ሊፈረም ይችላል ........///....... ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመውሰድ የሚያስችላትን ስምምነት በቅርቡ እንደምትፈጽም ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት አስታወቁ ፡፡ ፕሬዚዳንቱ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት ግድቡ ከኢትዮጵያ አልፎ የቀጣናውን ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት የሚያስችላትን ስምምነት በቅርቡ እንደምትፈፅም ገልፀዋል፡፡ ሁለቱ ሀገራት የኃይል ሽያጭ ለማከናወን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውና ባለሙያዎቻቸው አስፈላጊውን ጥናት እያካሄዱ መቆየታቸው ይታወሳል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content

ግድቡ አፍሪካዊ አጀንዳዎችን ለማሳካትና ቀጣናዊ ትስስርን ለማሳደግ የሚያስችል ነው …....///…...... ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አፍሪካዊ አጀንዳዎችን ለማሳካት እና ቀጣናዊ ትስስርን ለማሳደግ እንደሚያስችል የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ገለፁ፡፡ ሊቀመንበሩ ሙሐሙድ አሊ ዩሱፍ በግድቡ ምርቃት ላይ ባደረጉት ንግግር ግድቡ በትውልድ ቅብብሎሽ ተገንብቶ ለምረቃ በመብቃቱ ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። ግድቡ የሀገር ውስጥን ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር ቀጣናውን በኃይል ልማት ዘርፍ ለማስተሳሰር የጎላ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ በመገንባት ኢትዮጵያንና ቀጣናውን ተጠቃሚ የሚያደርግና ከአህጉራዊ አጀንዳዎች ጋር የሚጣጣም መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ ኢትዮጵያ ግድቡን በራስ አቅም ገንብታ ማጠናቀቋ ለአህጉሩ መነሳሳትን የሚፈጥርና የሕብረቱን 2063 አጀንዳን ለማሳካት የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ከሴኔጋል ወንዝ ጋር በተያያዘ በሴኔጋል፣ ማሊ እና ሞሪታኒያ መካከል የተደረገውን የሦስትዮሽ ትብብር የጠቀሱት ሊቀመንበሩ ድንበር ተሸጋሪ ወንዞችን በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በተመሰረተ መርህ በሰላማዊ መንገድ የመጠቀም ልምምድ መጎልበት እንደሚገባው ገልፀዋል፡፡ የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትጵያውያን ብቻ ሳይሆን የዓለምን ሕዝብ ያስደነቀ የመላ አፍሪካውያን የጋራ ፕሮጀክት ነው ብለዋል፡፡ የግድቡ መሳካት ለኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ ድል በመሆኑ የከበረ አድናቆት አለን ያሉት ፕሬዝዳንቱ የግድቡ ግንባታ በኢትዮጵያውያን ሙያተኞች ለፍጻሜ በመብቃቱ እጅግ የተለየ አድናቆት የሚቸረው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ የግድብ ግንባታውን በራስ አቅም በማጠናቀቅ ኢትዮጵያውያን እንደገና አፍሪካን የሚያኮራ ሥራ መስራታቸውን የተናገሩት ደግሞ የኢስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ሩሴል ሚሶ ድላሚኒ ናቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ሀገራቸው ኢስዋቲኒን ጨምሮ በርካታ የምዕራብ አፍሪካና በጥቅሉ አፍሪካውያን መሪዎች ህዳሴን መሰል ትውልድ ተሸጋሪ ሥራዎችን እንዴት መስራት እንደሚቻል የሚያስተምር ነው ብለዋል፡፡ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐመድ በበኩላቸው የግድቡ መመረቅ ለቀጣናው ኩራት እንዲሁም ለጋራ ዕድገትና ቀጣናዊ ትብብር ወሳኝ ስለመሆኑም ገልፀዋል፡፡ የግድቡ መጠናቀቅ ኢትዮጵያ በራሷ አቅም ያከናወነችው ትልቅ ታሪክ እና የብልጽግናዋ ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑንም አንስተዋል። ፕሮጀክቱ ከአንድ ግድብነት ያለፈ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ በትብብር ለመልማትና ለማደግ የሶማሊያ ሕዝብና መንግስት ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+2

የግድቡ ግንባታ ጠንካራ የሥራ ባህል እና ጽናት የታየበት ነው- ፔትሮ ሳሊኒ …....///….. የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ጠንካራ የሥራ ባህል እና ጽናት የታየበት እንደሆነ የፕሮጀክቱ ሥራ ተቋራጭ የጣሊያኑ ዊ ቢውልድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፔትሮ ሳሊኒ ተናገሩ፡፡ ሥራ አስፈጻሚው በግድቡ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት ላይ የግድብ ግንባታው ተጠናቆ ሲታይ ቀላል ቢመስልም በርካታ ፈተናዎችን እና ውጣ ውረዶችን በጽናት ማለፉን ተናግረዋል፡፡ ግድቡ አሁን ላይ የሚያስፈልገውን ውሃ መያዙን እና የሀገሪቱን የማመንጨት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ በማሳደግ በርካታ ኢትዮጵያውያን የኃይል ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለጎረቤቶቿ በመሸጥ ትብብሯን ለማጠናከር ጉልህ ሚና እንደሚጫወት አስገንዝበዋል:: የህዳሴ ግድብ በዓለማችን ደህንነታቸው ከተጠበቁ ፕሮጀክቶች አንዱ ነው ያሉት ሥራ አስፈጻሚው በግንባታው ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በጽናትና በቁርጠኝነት የተሳተፉበት እንዲሁም የእውቀት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ያገኙበት መሆኑንም አብራርተዋል፡፡ የግድብ ግንባታው መጠናቀቅ የኔ እና የኢትዮጵያ ህልም እውን የሆነበት ነውም ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን በፈተናዎችና በችግሮች ሳይበገሩ ግድቡ እንዲጠናቀቅ ትልቅ ሚና መጫወታቸውን የጠቆሙት ፔትሮ ሳሊኒ ለግድብ ግንባታው እውን መሆን አሻራቸውን ላሳረፉ ሠራተኞችም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በግድቡ ግንባታ ሥራ ላይ እየተሳተፉ በነበረበት ወቅት በተለያዩ አደጋዎች ሕይወታቸውን ላጡ ሠራተኞች ክብር እንደሚሰጡ እና በኅሊና እንደሚያስቧቸው ተናግረዋል። የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ለመንግሥታቸው የላኩትን የደስታ መግለጫ መልዕክትም አቅርበዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content

photo content
+2

ከፊታችን ለሚጠብቀን ከባድ ሥራ ታጥቀን ልንነሳ ይገባል .......///....... ኢትዮጵያዊያን በሰራነው ገድል ሳይሆን ከፊታችን ለሚጠብቀን ከባድ ሥራ ታጥቀን ልንነሳ እንደሚገባ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳስበዋል፡፡ ዶ/ር ዐቢይ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ ባደረጉት ንግግር ከዛሬ በኋላ ዳግም ዓድዋ ጉባ ላይ በመሰራቱ የኢትዮጵያ የልመና፣ የስንፍናና የእንጉርጉሮ ዘመን አብቅቶ እንደ ልኳ የምትመዘንበት ዘመን ከፊታችን መዘርጋቱን ገልፀዋል፡፡  ኢትዮጵያ ተረጅነቷ ቀርቶ ረጂ ትሆናለች ያሉት ዐቢይ አህመድ በኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን የመጀመሪያው ቀን የተገኙ ወዳጆች ኢትዮጵያ ወዳጅነት ብቻ ሳይሆን ከሀብቷ፣ ከብልጽግናዋ፣ ከተስፋዋ፣ ከእውቀቷ ከልምዷ የምታቋድሳቸው እንደምትሆን አረጋግጠዋል፡፡ "የኢትዮጵያ ብልጽግና የማይሳካ ለሚመስላቸው ለቅርብና ለሩቅ ጠላቶቻችን እኛ ኢትዮጵያዊያን የማይሞት ስም እንጅ የማይሞት አካል የለንም፤ አካላችን ሞቶ የማይሞት ስም ለማስቀረት፤ የማይሞት አሻራ ለማኖር የምንተጋ ህዝቦች ነን" ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ህዳሴ ጥቁሮች እንደምንችልና እንደምናሳካ በጥቁር ዘር ታሪክ የመጀመሪያው ታላቅ ሥራ  ነው ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ህዳሴን በንግግር፣ በፎቶና በተንቀሳቃሽ ምስል ብቻ መግለጽ ስለማይቻል የህዳሴን ልክ ለመገንዘብ መላው ኢትዮጵያዊያንና አፍሪካዊውያን ግድቡን በመጎብኘት የተሰራውን ገድል እንድገነዘቡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ከእንግዲህ የህዳሴ ፋይል ተዘግቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አምስትና ስድስት ዓመታት በአጠቃላይ ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሀብት የሚፈስባቸው የአፍሪካን ልጆች ቀና የሚያደርጉ እና የኢትዮጵያን ብልጽግና የሚያሰምሩ የተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት ዕቅድ እንዳላት አብስረዋል፡፡ የኢትዮጵያ የታሪክ እጥፋት፣ የብልጽግና መሰረት እና የማንሰራራት ዘመን ዛሬ በሁሉም አቅጣጫ መታወጁን በመጠቆም ኢትዮጵያን ለማቅናት ሁሉም በአንድ ልብና በአንድ መንፈስ በጋራ በመቆም የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ማድረግ እንደሚጠበቅበትም አሳስበዋል። የኢትዮጵያ ብልጽግና እውን መሆኑን ኢትዮጵያ ዳግም አደዋን ደጋግማ ለጥቁር ህዝቦች ማሳየቷ አይቀሬ ነው ያሉት ዶ/ር ዐቢይ የጥቁር ህዝቦች ከልመና በመውጣት ለመበልጸግ በአንድ ላይ ሊቆሙ እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም

ግድቡ ከብሔራዊ ፕሮጀክትነት ባለፈ የፓን አፍሪካ አቅምን በተግባር ያሳየ ነው -ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ….///…. የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከብሔራዊ ፕሮጀክትነት ባለፈ የፓን አፍሪካ አቅምን በተግባር ያሳየና የአፍሪካ መር መሰረተ ልማት ግንባታ መገለጫ መሆኑን የኬኒያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ተናገሩ፡፡ በዛሬው ዕለት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት ላይ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ (ዶ/ር)፣ የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌህ፤ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ (ዶ/ር)፣ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማየርዴት፣ የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞትሊ፣ የኢስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ሩሴል ሚሶ ድላሚኒ፣ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር መሀመድ አሊ ዩሱፍ፣ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ክላቨር ጋቴቴ እና ሌሎችም ተገኝተዋል። በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እንደተናገሩት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት ትልቅ ታሪካዊ አንድምታ ያለው መሆኑን እና አፍሪካ የራሷን እጣ ፈንታ በራሷ የመወሰን አቅም እንዳላት የሚያሳይ ታላቅ ፕሮጀክት ነው፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የምህንድስና ሥራ ሳይሆን አፍሪካ የራሷን መጻኢ እድል በራሷ መወሰን እንደምትችል የሚያሳይ በመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግስት ለዚህ ታሪካዊ ስኬት እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል። አፍሪካውያን የራሳቸውን የብልጽግና መሻት በራሳቸው ማካሳት እንደሚችሉም የሚያመላክት መሆኑን የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ ፕሮጀክቱ የአፍሪካ ቀንድ እና የናይል ተፋሰስ ሀገራት ለጋራ ትብብር ያለንን ቁርጠኝነት በግልጽ እያሳየን መሆኑንም በንግግራቸው አንስተዋል፡፡ ኢትዮጵያ በኢነርጂ ራሷን ለመቻል እና ኢኮኖሚዋን ለመለወጥ እያደረገች ያለውን ጥረትም አድንቀዋል። የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር  ማየርዲት በበኩላቸው ግድቡ ሕዝብ በተባበረ ክንድ ምን መስራት እንደሚችል ያሳየ የአንድነትና የመስዋዕትነት ምልክት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የደቡብ ሱዳን ሕዝብና መንግስት ከኢትዮጵያውያን ጋር የጋራ ታሪክ እና ሕልም ያላቸው መሆኑን ጠቅሰው ለግድቡ ግንባታ መጠናቀቅ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞትሊ በበኩላቸው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአድዋ ድል ተምሳሌት ሆኖ በኢንጅነሪንግ ጥበብ ዳግም የተገለጠበት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ግድቡ ኢትዮጵያውያ ለመላው አፍሪካውያን መቻላቸውን ያሳዩበት ፕሮጀክት መሆኑንም አብራርተዋል፡፡ ሌሎችም መሪዎችም የግድቡ ግንባታ መጠናቀቅ ለአፍሪካና ለቀጠናው የሚኖረውን በጎ ሚና በማውሳት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+3

ገደሉን ተሻግረን በሕዳሴ ገድል አትመናል   - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ….///….. የገጠሙንን ፈተናዎችና ችግሮች ተጋፍጠን ገደሉን ተሻግረን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን በማጠናቀቅ ገድል አትመናል ሲሉ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ይህን የተናገሩት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምርቃት ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡ ሕዳሴ የትላንት ቁጭት ማሰሪያ የመጭው ንጋት ማብሰሪያ እንዲሁም ለመላ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ ታሪክ ሆኖ የሚኖር ገድል ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ሕዳሴን የሰራችው የታችኛውን ተፋሰስ ሀገራት ጨምሮ አፍሪካውያንን በኃይል ለማስተሳሰር እንጂ የጎረቤት ሃቅን ለማስቀረትና ለመጉዳት አለመሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡ ስለሕዳሴ በመናገር ጊዜ አናባክንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዳሴን ግድብ የሚስተካከል ለሠላማዊ ዓላማ ብቻ የሚውል የኒኩሌር ኃይል ማመንጫን ጨምሮ የአየር ማረፊያ ግንባታ፣ የማዳበሪያ እና የጋዝ ፋብሪካዎችን ሥራ በቅርቡ እንደምታስጀምርም ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን በሁሉም አቅጣጫ በሕዳሴ መጀመሩንም አብስረዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+1

በግድብ ግንባታ ላይ አበርክቶ የነበራቸው አመራሮች ተሸለሙ፤ …....///…..... በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ምርቃት ላይ በግድብ ግንባታው ወቅት በአመራርነት አበርክቶ የነበራቸው አመራሮች በጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የክብር ኒሻን ተሸልመዋል፡፡ የክብር ኒሻን የተሸለሙት  ኢንጂነር ኤፍሬም ወልደኪዳን አማካለኝ  ከህዳር 2004 ዓ.ም ጀምሮ ጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የፕሮጀክቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ፣ ኢንጂነር ከማል አህመድ ሱለይማን ከሚያዚያ 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የፕሮጀክቱ የኦፕሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ በላቸው ካሳ ወልዴ በምክትል ሥራ አስኪያጅ ማዕረግ የፕሮጀክቱ ሳይት አስተባባሪ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም