የግጥም ቃና በ መክሊት የ16ቷ
Open in Telegram
እንኳን ደና መጡ🙏 በዚህ ቻናል የግጥም ቃና እንዲሁም ሀገርኛ ወጎችን በለዛ እናገኛለን ለማንኛውም አስተያየት እንዲሁም ስራዎን ማቅረብ ከፈለጉ በዚህ @yuliyana16 ያናግሩኝ እዚህ ላይ ደግሞ @meklitlema 👈 join በማድረግ ትምህርት ይቅሰሙ የ🇪🇹ሰላምን ያብዛልን
Show more1 432
Subscribers
No data24 hours
-77 days
-1830 days
Posts Archive
1 432
Repost from ከምድር ማህፀን With TinA
የቅድሙ ተመልሷል "ግራጫ ቃጭሎች" መዝገቡ ። ቢሆንም የተሰጠው ሰአት ካለቀ ከ20 ደቂቃ በኋላ በመመለሱ አይቆጠርም !
አሁን ሌላ ጥያቄ ልጠይቅ ሽልማት ያለው? በ 1 ደቂቃ የሚመለስ?
በReaction ግለፁ ...25 ሪአክሽን ሲደርስ ጥያቄው ይለቀቃል !!!
https://t.me/danutell
1 432
በምስሉ ላይ የምትመለከቱት አማዞን ደን አልያም ደግሞ ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ አይደለም !
በህንድ የሚገኝ አንድ ዛፍ ነው፤ ማለትም ብዙ ዛፎች ሳይሆኑ ለብቻው ያለ ታላቁ ባንያን እያሉ የሚጠሩት ግንዲላ ዛፍ ነውደ
ስፋቱ 4.67 ስኩዌር ያርድ፣ 80 ጫማ እርዝመት ያለው እና ደግሞ 250 አመት እድሜን የጠገበ...የእድሜ ባለጸጋ ዛፍ ነው።
1 432
ብዙ ቦይንግ 747 አውሮፕላኖች still ለሶፍትዌር አፕዴት የሚጠቀሙት 3.5 ኢንች የሆኑ ፍሎፒ ዲስኮችን ነው።
እኒ ኋላ ቀሮች 😏
1 432
ለን____ደን
የታላቋ ብሪታንያ ከተማ የሆነችው ሎንዶን (ለንደንም ይሏታል🤷♂️ ፀሀይ አትጠልቅም ይሉም ነበር....ነበር ነው! አሁን መላው የአፍሪካ ጥቁር ህዝብ፣ ኤዢያው፣ አሜሪካኖች-ደቡብም፣ ሰሜንም ኢቭን አውስትራሊያ፣ አንታርቲካ ሳይቀር ነቄ ቶሎ ተቄ አሉባቸውና ጠቅለው ሀገራቸው ገብተው ጸሀይ ትጠልቅ ጀምሯል።
ለምን? የኢትዮጵያ ፒፕል አፍሪቃውያንን አስተባብሮ ፓን-ከፍሪካኒዝም በአንድ አቀነቀነ one love!። እንደገናም ደግሞ "ጥሊያንን በካልቾ እንዳልን እናንተንም ኦንዳንደግማችሁ" ሲሏቸው ነበር..አሉ። እናም ባርነት በቃኝ አለ። እንደገናም ደሞ እንደናንተው ሁሉ እኛም ጸሀይ እንዳትጠልቅብን እንፈልጋለን አሉ። ብለውም አልቀሩ የጥቁር፣ ጭቁን ህዝብ ነፃ ሆነ። ግን እንዳለመው ፀሀይ ለመሪዎቹ ብቻ ነው የማትጠልቀው። እስካሁን !!!!!! ፀሀይ ለመሞቅ እንደተመኘ አለ! )
ወደ ነገሬ ልመለስና በአለም ትልቁ፣ ሰፊው የከተማ ውስጥ ደን (urban forest) እስከ 21% የሚሆን የደን ሽፋን ያለው በለንደን ነው። (ይሄ ነበር አይደለም! አሁን ነው )
እንዲያውም በቅርቡ በከተማዋ ውስጥ ያለው የዛፍ ብዛት ለንደን ከተማዋ ውስጥ ካለው የህዝብ ቁጥር ጋር እኩል ሳይሆን አይቀርም።
1 432
+1
🐍ሁለት ጭንቅላት ያለው አንድ እባብ እንዳለ ያውቁ ኖሯል? ይግረማችሁና አንድ ሆነው ሁለት ጭንቅላት ያላየቸው ምግብ ለማግኘት እርስ በርስ የሚራኮቱ፣ የሚሻኮቱ፣ የሚፎካከሩ አንድ ሆነው ሁለት የሆኑ።
ነገሩ እንደዚህ ነው....
አንዳንድ እባቦች ሲወለዱ ከሁለት ራስ ጋር ነው። ችግሩ ግን አንዱ የሚሰራው ራሱን ሊመግብ ነው፤ ሌላኛውም ደግሞ የሚሰራው ራሱን ሊመግብ ነው። እና በዚህ መሃል ምን ይፈጠራል? ምግብ ለማግኘት ፉክክር ውስጥ ይገባሉ።
1 432
🍇ቀይ ወይን የካንሰር ሴልን ይገድላል👊
ሪዝቬሬቶል የተባለው ከቀይ ወይን የሽፋን ቆዳ ላይ የሚገኝ ውህድ በሚገባ ካንሰርን አንገት ለአንገት ተናንቆ ይዋጋዋል።
ተፈጭቶ፣metabolized ሆኖም እንኳ ወደ ሌላ ውህድ ራሱን ቀይሮ አይፋታውም! ይዋጋዋል።
1 432
የምትመለከቱት ናትሮን ሀይቅ እንስሳትን ወደ አለትነት ይለውጣቸዋል።
ከፍተኛ አልካላይነት ባህሪ እና የሙቀት መጠን
ስላለው ወደ ሀይቁ ውስጥ ለዋናም ይሁን እንዲሁ ሞቋቸው አሊያም ፓርቲ አዘጋጅተው ለመፈታታት ቢገቡ immediately ይሞታሉ።
ቀጥሎም ደግሞ መገነዣ ምናምን ሳያስፈልግ ራሱ በሚንራል/ ማዕድናት ይገንዛቸዋል፣ አካላቸው ወደ አለትነት ይቀየራል።
ተፈጥሯዊ የሃውልት አሰራር ይሉሃል። እና አንድ ወደዚ ሀይቅ ገብቶ የሞተ አካል ቤተሰቦቹ ለለቅሶ ሳይሆን ለሐውልቱ ምርቃት ብቻ መምጣት ነው የሚጠበቅባቸው።
1 432
🌍 ከአሜዚንግ አለም
የአለማችን ረጅሙ፣ ቁመታም፣ ሎጋ ተራራ ማነው ብንባል ኤቨረስት አልያም ኪሊማንጃሮ ነው ምላሹ።
ነገርግን ውቅያኖስን ጠለቅ ብለን አልያም ውስጥ ለውስ ማሰስ ሳያሻን አይቀርም። ብሔራዊ የውቅያኖስ አገልግሎት(NOS) በሪፖርቱ እንዳሳወቀው ከሆነ 40,389 ማይሎች ርዝመት ያለው ተራራ የሚገኘው ከውቅያኖስ በታች 90%ቱ በውሃ ተውጦ ነው የሚገኘው።
(ልብ በሉ ኤቨረስት 8,500km ነው ርዝመቱ። ይሄ ከውሃ በታች የሚገኘው ተራራ ደግሞ 10 ወይም 20 እጥፍ እንደሚበልጠው ልብ ይሏል🤗)
1 432
+1
በ2017 G.c በአሜሪካዋ ኮሎራዶ ምን ሆነ መሰላችሁ?
አንዲት አጋዘን ወደ አንድ ስቶር ቀጥ ብላ ቀጭ ቋ...ቀጭ ቋ እያለች ትገባለች።
(በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱትም ወገቧን ይዛ "ምን ታፈጣለህ አስተናግደኝ እንጂ" አይነት እይታ ታየዋለች 🤗 )
የሱፐርማርኬቱ አስተናጋጅም
በይ ይሄን ያዢና ሂጂ በሚል አይነት የለውዝ ቅቤ/ ፒኗት/ እጅ ከምን ይላታል። (ከፍቶ ይሰጣል ) አጋዘኗ በርግጥ ለቃ ትወጣለች፤ ክፍያም ሳትከፍል።
በሌላ ጊዜ ግን ስትመለስ ከነሙሉ ቤተሰቧ ከች አለች ከዛው ስቶር።
(የራት ግብዣ አለን ዛሬ ማታ ቤተሰብ ብላ 😂 እንደ ዘንድሮ አንዳንድ ሴቶቻችን ወንዱ ልጋብዝሽ ሲላት ሙሉ ጓደኞቿን አግተልትላ የትውውቅ መሰናዶ እንደማድረግ በሉት 🤗)
1 432
በ2017 G.c በአሜሪካዋ ኮሎራዶ ምን ሆነ መሰላችሁ?
አንዲት አጋዘን ወደ አንድ ስቶር ቀጥ ብላ ቀጭ ቋ...ቀጭ ቋ እያለች ትገባለች።
(በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱትም ወገቧን ይዛ "ምን ታፈጣለህ አስተናግደኝ እንጂ" አይነት እይታ ታየዋለች 🤗 )
የሱፐርማርኬቱ አስተናጋጅም
በይ ይሄን ያዢና ሂጂ በሚል አይነት የለውዝ ቅቤ/ ፒኗት/ እጅ ከምን ይላታል። (ከፍቶ ይሰጣል ) አጋዘኗ በርግጥ ለቃ ትወጣለች፤ ክፍያም ሳትከፍል።
በሌላ ጊዜ ግን ስትመለስ ከነሙሉ ቤተሰቧ ከች አለች ከዛው ስቶር።
(የራት ግብዣ አለን ዛሬ ማታ ቤተሰብ ብላ 😂 እንደ ዘንድሮ አንዳንድ ሴቶቻችን ወንዱ ልጋብዝሽ ሲላት ሙሉ ጓደኞቿን አግተልትላ የትውውቅ መሰናዶ እንደማድረግ በሉት 🤗)
1 432
ኢክሩን የማያውቃት አለ?
በተለይ የምትፅፋቸው አጫጭር በራሪ ፅሁፎች ከልብ የሚደርሱ ናቸው።
ገጣሚና አሰላሳይ ሰሎሞን አዱኛ እንዳለው "ትንሽዬ ነበልባል 🔥" ናት።
እንዲሁም ገጣሚት ዳጊ አሰፍም ጨምራ እንዳለችው "ሀያል ማዕበል" ነች።
ደራሲ ዮዳAም እንዳለው "ፊያሜታ .!" ናት።
እኔ ግን እላለሁ "አንቺ የሰውነት ከፍታ ያለሽ፣ የመንፈስሽ ርዝመቱ አርያምን ጠቅሶ በርባሮስ ይረብባል። አንቺን በማወቄ እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ። የምር ካየኋቸው ሰዎች ሚዛን ያጣሁልሽ ለወደፊቱ ከዚህም በላይ ካንቺ የምጠብቅ ነኝ 🙏
"
🕹 በሉ አሁን ቶሎ በሉና ☝️ ቻናሏን ተቀላቀሉ። እኛ መቼ ጻፍን??? መቼ አሰብን???
ገብታችሁ እዩና የምለው ይገባችኋል ።
https://t.me/Demaq_Dukawech
1 432
Repost from ደማቅ ዱካዎች (ኢክራም ሰኢድ)
ምናለ ትንሽ አለመኖርን መኖር ቢፈቀድልን ግን? ..... ትንሽ ከራሳችንም ከሰወችም ብንጠፋ.... አለመኖራችን የሚፈጥረውን ቀዳዳ እኛም እነሱም ቢያዩት..... መኖር እስኪናፍቀን ህይወት እስኪያጓጓን ድረስ ባንኖር ......ምናለ በመኖር ውስጥ የአለመኖርም እድል ቢኖር?
@Demaq_Dukawech
1 432
🌎 ከአሜዚንግ አለም
ዶሮ
የዶሮን ጉድ ሹክ ልበላችሁማ !
ዶሮዎች የቀኝ አይናቸውን ምግብ/ ጥራጥሬ ለመመልከት አልያም ለመፈለግ ሲጠቀሙበት፤ የግራ አይናቸውን ክፍል ደግሞ አዳኛቸውን ወይም ጠላታቸውን ይመለከቱበታል
አጃኢብ !
1 432
🌍 ከአሜዚንግ አለም
ደም እንባ ማልቀስ ይቻላል?
ጨዋማ የሆነው እንባ በደም እንባ ሲተካ በሳይንስ መጠሪያው ሄሞላክሪያ ይሰኛል። ይህ ክስተት የመፈጠር እድሉ በጣም ጠባብ ነው።
በስሜት መጨናነቅ ወይም በሆርሞን መለዋወጥ፣ ጭንቅላት በሚደርስ ጉዳት፣ ቲውመር፣ በደም መርጋት፣ ኢንፌክሽን ወይም የእንባ ከረጢት/ እጢ መጎዳትና ሙሉ በሙሉ መውደም የደም እንባ ከአይን እንዲመነጭ ምክንያቶቹ ሊሆኑ ይችላሉ።
1 432
አባይ ለግብጽ ምኗ? 🤔
እየውላቹማ እኒህ ምስሮች (ጥንታዊ ስማቸው ነው..)፤ እነዚ ጥንታዊያን ግብፆች የአባይን ውሃ መሙላት ይለኩት ነበር!
ለክተውት ምን ያደርጉት ካላችሁ ...ይሸቅሉበታል ስላቹህ ! (ሰከላን ይንሳኝ! ጣናን እምቦጭ ይውረስብኝ የምሬን ነው። ቁምነገር...ህእ!!! እኛ ነን እንጂ አራስ ሆነን መሰረተ-ድንጋይ ተጣለ፣ አሁን መሠረቱን ሲሰሩ እንጂ ጠብ የሚል ነገርም ያላየን😒)
ከፍተኛ የውሃ ሙላት ወይም ጎርፍ ባለበት አከባቢ እየሄዱ እንደ ውሃው ብዛት ከበድ ያለ ታክስ ይጥሉበታል። ይህም ማለት ውሃው መጠኑ/ጎርፉ በዛ ካለ እዛ ስፍራ ያለ ነዋሪ በዛ ያለ አዝመራ ይሰበስባል፤ ታክሱም እንደዚያው ከበድድድ፣ ወደድድድ ይላል ።
ጥንት ነው ይህ!
አሁን ደግሞ አስቡት የአስዋንን ግድብ ታክኮ ያለው ኤኮኖሚና ካይሮ !
እኛስ?
1 432
🌍 ከአሜዚንግ አለም
ካርታ !
ለመዝናናት፣ ለቁማርና ለለቅሶ ማስተዛዘኛ የምንጫወትበት ካርታ ውስጥ ያሉ
አበባ
ጦር
ዳይመንድ
ልብ
(Spades, Clubs, Hearts &Diamonds )
እያንዳንዱ የቀድሞ ሃያል ነገስታትን ይወክላሉ።
📌 ይህም
ጦር-> ንጉሥ ዳዊትን
አበባ->ታላቁ እስክንድር
ልብ-> ቻርልማኝ
ዳይመንድ->ጁሊየስ ቄሳር
