cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Nehnu Tube ◈ ነህኑ ቲዩብ_||ኢስላማዊ ጥበብ||

Nehnu Tube ✧ ነህኑ ቲዩብ || #ኢስላማዊ_ጥብብ || #በመነባንብ ፤ #በግጥም ፤ #በታሪኮች እና የስነ - ፅሁፍ ውጤቶችን እንዲሁም ደግሞ ሌሎች ኢስላማዊ ትምህርቶችን በመሳጭ አቀራረብ ከ #Nehnu_Tube ያገኛሉ። ቻናላችንን #ሰብስክራይብ በማድረግ ጠቃሚ እውቀቶችን ይቅሰሙ። ሀሳብ አስተያየት ካሎት @Nehnu_Tube_bot 👆እዚህ ላይ ይስጡን👆

Show more
Advertising posts
329
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አስቂኝ ክስተት ፈገግ በሉበት‼️ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ✍የመን ውስጥ ዘማር የተባለ ቦታ ላይ አንድ መስጂድ ውስጥ የተከሰተ በጣም አስቂኝ ክስተት ነው አንብበው ሳይጨርሱ በሳቅ ሟቋረጥ ግን አይቻልም¡ || ይህ ክስተት እዚያው መስጂዱ ውስጥ ሶ'ፈል አወል (የመጀመሪያው ሰፍ) ላይ ቆሞ ሲሰግድ የነበረ አንድ ሰጋጅ ነው የሚያስተላልፍልን... * እናም ይህ ሰው እንዲህ ይለናል:- «አንድ ሰው ይሞትና ተሰግዶበት ተቀበረ ከዚያም ከኢሻ ሶላት በኋላ ነእሹ (ጀናዛ መሸከሚያው) ሊመልሱት ይዘውት ወደ መስጂድ ሲመጡ ሰአት ሄዶ ስለነበር መስጂዱ ተዘግቷል። ስለዚህ ኻዲሞች ለፈጅር ሶላት ሲመጡ እንዲያነሱት በሚል ጀናዛ መሸከሚያው ከመስጂዱ በር ከደረጃ ላይ ያስቀምጡታል። : ነገር ግን ሌሊት 9:30 ሰአት አካባቢ አንድ ሰውዬ ወደ መስጂድ ሲመጣ መስጂዱ ዝግ ሆኖ እና በረንዳው ተከፍቶ አገኘው የተወሰነ ቢጠብቅም መስጂዱን የሚከፍተው አጣ  ብርዱ በጣም ሲበረታበት ዞር ብሎ ሲያይ ጀናዛ መሸከሚያው ከአጠገቡ አገኘ በውስጡም ብርድልብስ ነገር አለ። : እና ይህ ሰው አገኘሁ ብሎ ጀናዛ መሸከሚያው ውስጥ ብርድ-ልብሱን ለብሶ ለጥ ብሎ እንቅልፉን ተኛ አባቴ! በብርድ ደንዝዞ የነበረው ሰውነቱ ትንሽ ምቾት ሲያገኝ ነፍሱንም አያውቅ ለጥ ብሎ ተኝቶልሀል... ሃሃሃ! ትንሽ እንደቆየ የመስጂዱ ኻዲም መጥቶ መሲጂዱ ሊከፍት ሲል በረንዳ ላይ ከነእሹ (ጀናዛ መሸከሚያው) ላይ የተኛ ሰውዬ ይመለከታል ከፈጅር በኋላ ሊሰገድበት ያመጡት ጀናዛ መሰለው... : ከኋላውም ሌሎች ሰዎች መጥቶ ግማሹ ሽንት ቤት ሌላው ውዱእ ሊያደርግ ይሄዳሉ ይህ በረንዳ ላይ ተኝቶ የሚያዩት ሰውዬ (ጀናዛ) ደግሞ ሁሉም ቀድመውኝ የመጡ ሰዎች ሊሰገድበት ያመጡት ጀናዛ ነው ብሎ ያስባል በውስጡ... (ያዝ እንግዲህ¡) በዚያ ላይ ፈጅር ነው ሰው ከእንቅልፉ ተነስቶ እየመጣ ነው ያለው ገና በደንብ ያልነቃ ህዝብ ነው። ሊሰገድበት የመጣ ጀናዛ ይሆናል በማለት ተጋግዘው ወደ መስጂድ ኢማሙ ጋር ወደ ሚህራብ አስገቡት። ሃሃ! : ብ ር ድ የቀጠቀጠው ሰውዬ ሲሸከሙት አያውቅ ተኝቷል¡ ህእ! ሰዎቹም የማን ይሁን ብለው አይጠይቁ ገና ከእንቅልፋቸው በደንብ አልነቁም እና ተሸክመው መስጂድ ውስጥ አስገቡት። ፈጅር አዛን ብሎ ለመስገድ ወደ 50 የሚሆኑ ሰዎች ተሰበሰቡ። ይህንን ታሪክ የሚያስተላልፍልን ሰው እኔም ከሰጋጆቹ አንዱ ነኝ የመጀመሪያው ሶፍ ላይ ነበርኩ ይላል። ከፈርድ በኋላ ልንሰግድበት ጀናዛው ከፊት ተደርጎ የፈጅር ሶላት እየሰገድን ነው። እህእ! : ልክ ለሁለተኛው ረከአ ስንነሳ ጂናዛው ሲንቀሳቀስ አየሁ እንዴዴዴ አይኔ ነው ወይስ ምንድ ነው¿ ብዬ አይኔን አበስኩ ጨፍኜም ገለጥኩ መንቀሳቀሱን ግን አልተወም በቃ እንቅልፍ አለቀቀኝም ይሆናል ብዬ አሰብኩ። ነገር ግን ነእሹ በደንብ መንቀሳቀስ ጀመረ ያኔ መረባበሽና መፍራት ጀመርኩ። ይህ የተኛው ሰውዬ ከብርድ ልብሱ ውስጥ ድንገት አንገቱ  አውጥቶ ሰገዳችሁ? ብሎ ጠየቀ። : ያኔ! ሁሉም ሰጋጆች ደንግጦ መተረማመስና መሮጥ ጀመሩ  እኔም አጠገቤ ከነበረው በር ወጥቼ በባዶ እግሬ ሮጥኩኝ ወደ 1 ኪ.ሜ ያክል የሚርቀውን ቤቴን በትንሽ ደቂቃዎች ደረስኩ ደግሞ ባዶ እግሬ መሆኔም የማውቀው ነገር የለም። ኢማሙ (አሰጋጁም) ሲያየው ደንግጦ መሬት ላይ ይወድቋል ሌሎች ሰዎች ግማሹ ከግድግዳ ጋር ይጋጫል ሌላው ደግሞ ልክ እንደኔው በባዶ እግሩ ይሮጣል መስጂድ ውስጥ አንድ ሰው አልቀረም። : አሁንም ሌላኛው በጣጣጣም የሚያስቀው ክስተት ተከሰተ ያ ከሬሳ መሸከሚያ(ከነእሹ) ላይ ተኝቶ የነበረው ሰውዬ ሲነሳ ሰዎች ሲሸሹ ሲሮጡ ሲያይ ከኋላቸው ተከትሎ መሮጥ ጀመረ። እናንተ ምን ሆናችሁ ነው ? ቂያማ ቆሞ ነው እንዴ? እያለ ከኋላ ኋላቸው መሮጥ ጀመረ። ሃሃሃ! : ሰዎቹ ደግሞ ወደ ኋላቸው ሲዞሩ ይህ ሰውዬ እየተከተላቸው  መሆኑ ያያሉ ያኔ ይብስባቸዋል ባለ በሌለ ሀይላቸው ይሮጣሉ። በዚህ መልኩ ሁሉም  ሰላታቸውን አቋርጠው ሮጡ...» ይለናል ቦታው ላይ የነበረ አንዱ ሰጋጅ። : መቼም ይህንን አንብቦ ያልሳቀ ካለ እኔንጃ¡ |━━━━⊱☆🧕ዘ¡k☆⊰━━━| 👇 #Share.... #join 👇 ┈┈•••✿❒☆❒✿•••┈┈    ➯@WeeMuslims ☆▬▬▬▬▬▬▬▬▬☆
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
#"አለመታገል ከመታገል በላይ ዋጋ ያስከፍላል!" #ሼር_ማድረግ_እንዳይረሱ ▽▽▽◊◊◊ለመ🀄️ላ🀄️ል◊◊◊▽▽▽ t.me/NehnuTube ኢስላማዊ ጥበብ ሀሳብ አስተያየት 👉 @Nehnu_Tube_bot የዩቲብ ቻናላችንን #ሰብስክራይብ_ያድርጉ https://www.youtube.com/channel/UCBQvGAsLudI4X5U3pHYBgtw
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
"ንስርን ሚወጋት ከራሷ ላባ የተሰራ ቀስት ነው" #ሼር_ማድረግ_እንዳይረሱ ▽▽▽◊◊◊ለመ🀄️ላ🀄️ል◊◊◊▽▽▽ t.me/NehnuTube ኢስላማዊ ጥበብ ሀሳብ አስተያየት 👉 @Nehnu_Tube_bot የዩቲብ ቻናላችንን #ሰብስክራይብ_ያድርጉ https://www.youtube.com/channel/UCBQvGAsLudI4X5U3pHYBgtw
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ስንቱን ጀግና እየጣለ! ያ ተራራ ዛሬም አለ... #ሼር_ማድረግ_እንዳይረሱ ▽▽▽◊◊◊ለመ🀄️ላ🀄️ል◊◊◊▽▽▽ t.me/NehnuTube ኢስላማዊ ጥበብ ሀሳብ አስተያየት 👉 @Nehnu_Tube_bot የዩቲብ ቻናላችንን #ሰብስክራይብ_ያድርጉ https://www.youtube.com/channel/UCBQvGAsLudI4X5U3pHYBgtw
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም ያ ጀመዓህ! እንደሚታወቀው ሚሽነሪዎች ለማክፈር ተፍ ተፍ የሚሉት ከተማ ላይ ሳይሆን ገጠሩ ክፍል ነው፥ ያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ የሃይማኖት ንጽጽር ፈር ቀዳጅ እና ፋና ወጊ የሆነው ኡሥታዙና ሳዲቅ ሙሐመድ(አቡ ሃይደር) በገጠር መሣጂድ ማስገንባት፣ መድረሣዎች ማሠራት፣ ታዳጊ ሕፃናት በዱኑል ኢሥላም ዒልም መኮትኮት መርሐ ግብር ጉልኅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። አሏህ ሥራውን በኢኽላስ ይቀበለው! በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ይህንን መርሐ ግብር ገጠር ውስጥ የሚያደርገው በክራይ ሞተር ሳይክል ነው፥ ከወንድሞች እና ከእኅቶች በመጣው የተቀደሰ አሳብ ከፍ ያለ መኪና ለመግዛት ታስቧል። ይህም ከፍ ያለ መኪና ለቅንጦት ሳይሆን ገጠር ውስጥ ለደዕዋህ ነው። በዚህ ኸይር ሥራ መሳተፍ የምትፈልጉ ከታች ባለው የራሱ የአካውንት ቁጥር የቻላችሁትን ማስገባት ትችላላችሁ! Commercial Bank of Ethiopia 1000329226712 0911 10 32 31 ሼር በማድረግ አላፍትናችንን እንወጣ። ወጀዛኩሙሏህ ኸይራ! ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ደስ አለዎት 🎉 ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሳሪብርን ተደራሽነት ለማስፋት ያዘጋጀውን 5,000 ብር የሚያሸልም ቀላል ውድድር እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል ‼️ 💢እንዴት #መሳተፍ እችላለሁ ? 1. በመጀመሪያ ይሄን ሊንክ ተጭነው ቡቱን start ብለው ያስጀምሩ 👇👇 https://t.me/SafariBirr_bot?start=r05351668210 2. በመቀጠል "👤 ሰው ለመጋበዝ " የሚለውን MENU ይጫኑ። 3. ከዚያ ለእርሶ የሚላክሎትን የራሶ መለያ 🔗ሊንክ ለሌሎች #ሼር ( Forward ) በማድረግ ይጋብዙ። 4. በእርስዎ ግብዣ አማካኝነት የተቀላቀሉ ሰዎች ቁጥር 50 ሲደርስ የባንክ ሂሳብ ቁጥርና ስልክዎን ይላኩልን። በተከታታይ 5 የስራ ቀናት ውስጥ 5000 ብር ገቢ ይደረግሎታል። ✅ የ አሸናፊ ተሸላሚዎችን ዝርዝር ለማየት ሊንኩን በመጫን በቴሌግራም ገፃችን ይመልከቱ።👇👇 https://t.me/+zjqhof7wpENmZjNk መልካም እድል ❕
Show all...
ደስታ ማግኘት ቀላል ነው! 1, እውነትህን ኑር :- እውነትህን ተጋፈጥ አታስመስል ከራስህ አትደበቅ ምንም ቢሆን ልብህ እውነቱን ያውቃል ከላይ ከላይ ላስመስል ልሸውደው ብትልም አይቀበልህም ስለዚህ ደስታህን ይነፍግሀል መደሰት ከፈለክህ የእውነትህን ኑር እውነቱ ከባድ ቢሆንም ተጋፍጠህ ስታሸንፈው የምታገኘውን ደስታ እና እርካታ ማንም አይሰጥህም! 2 , በፍቅር ኑር :- ከሰዎች ጋር ከልብ በሆነ እውነተኛ ፍቅር ኑር ምንም ሳትጠብቅ ፍቅር ስጥ ለሰዎች ሰላም መስጠት የምትችል ሁን ብርቱ ሁን ከልብህ ተቀበላቸው ለመጠንከራቸው ለመሳቃቸው ለማሸነፋቸው ለሰላማቸው ምክንያት ሁን ፍቅር በመስጠትህ ብቻ ህይወቱን የምታተርፍለት አንድ ሰው መኖሩን እወቅ ፤ ሞቅ ያለ ፈገግታህን በማየት ከህይወቱ ጨለማ የሚወጣ የሆነ ሰው አለ ስለዚህ በሄድክበት ሁሉ ፍቅርን የምትሰጥ እና ፈገግታህ ተስፋን የሚፈነጥቅ መሆኑን እወቅ ያኔ ደስታ ሳትጠራው ራሱ ፈልጎህ ይከተልሀል ካንተ ርቆ መሄድ አይችልም! "እነዚህን ካደረግህ ደስታ ራሱ ካንተ ጋር መሆን ያስደስተዋል "
Show all...
መውሊድን በአል ብለው ለሚያስቡ የሙስሊሙ በአል አላህ ዘንድ እና መልክተኛው ዘንድ እውቅና የተሰጠው ሙስሊምን ህብረተሰብ በአንድነት በጋራ የሶላት አምልኮ ሸሪዓዊ ህግጋት የሚፈፀምበት አመታዊ በዓል ኢደል ፊጥር እና ኢደል አድሃ በዓል እንጂ አላህ ዘንድ እና መልክተኛው ዘንድም አንድም ተቀባይነት ያለው በዓል የለም ፦ዘይኑ ይማም
Show all...
ሳታልፍ በፊት ኑር! በዚህ አለም የሚያረጋጋ ቃል ቢኖር አንዱ "ሁሉም ያልፋል" የሚለው ነው፤ ሀዘኑም ያልፋል፣ደስታውም ያልፋል፣ ንዴቱም ያልፋል፣ እርካታውም ያልፋል፤ ሌላውን ተወው አንተም እኔም እናልፋለን! በፍጥረት አለም ፀንቶ የሚኖር ነገር ቢኖር አምላክ ብቻ ነው። ታዲያ ለሚያልፍ ችግር ለምን አብዝተህ ትጨነቃለህ? ለሚያልፍ ቀን ለምን ራስህን ትጎዳለህ? ህይወትህን ነብስ ዝራበት፤ የምትወደውን ስራ፣ የምትወዳትን የራስህ ለማድረግ ተዘጋጅ፣ መንፈሳዊነትህን ሳትለቅ የምድርን በረከት ሁሉ አጣጥም፤ ሳታልፍ በፊት ኑር ወዳጄ!
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.