ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
Open in Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
Show more613
Subscribers
+124 hours
-37 days
-1130 days
Posts Archive
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ እንኳን #ለጾመ_ፍልሰት_የመጀመሪያ_ሳምንት ለዕለት እሑድ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዚህ_ሳምንት_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፪ "ዮም ንወድሳ ለማርያም በእንተ ዘተወልደ እምኔሃ መንክር ግርማ ኀይለ ልዑል ጸለላ ፆረቶ በከርሣ ውእቱኒ ቀደሳ አዝ (መ) እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት መንክር ግርማ ኀይለ ልዑል ጸለላ አማን መላእክት ይኬልልዋ"። ትርጉም፦ አምላክ ከርሷ ስለተወለደ ማርያምን ኑ ዛሬ እናወድሳት፤ በድንቅ ግርማ የልዑል ኀይል ጋረዳት፤ የምሕረት አባት በድንቅ ግርማ በታላቅ ኀይል ጋረዳት፤ የምሕረትን አባት በማኅፀኗ ወሰነችው፤ እርሱም ቀደሳት፣ ለያት፣ ከፍ ከፍ አደረጋት፣ አጸናት ልዩ አደረጋት፤ የሰንበት ጌታ የምሕረት አባት በድንቅ ግርማ በታላቅ ኀይል ጋረዳት፤ በእውነት መላእክት አመሰገኗት። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዚህ_ሳምንት_የዕለቱ_ምስባክ፦ "እመነ ጽዮን ይብል ሰብእ። ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ። ወውእቱ ልዑል ሣረራ"። መዝ 86፥5። የሚነበቡ መልክታት 1ኛ ቆሮ 8፥1-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 4፥1-6 እና የሐዋ ሥራ 26፥1-24። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥39-46። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም ዕለተ ሰንበትና የሱባዔ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ነሐሴ ፫ (3) ቀን።
❤ እንኳን #በገድል_ለተጠመዱ ስልሳ ክንድ የድንጋይ ምሰሶ ላይ ወጥተው በዚያም ሳይቀመጡ ቆመው እያስተማሩና እየጸለዩ #ለ42_ዓመታት ለተጋደሉ ለታላቁ አባት #ለአባ_ስምዖን_ዘዓምድ_ሶርያዊ ለዕረፍት በዐልና ከመንግሥት ወገን ለሆነች #ለቅድስት_ሶፍያ_ዘሮምና_ለሦስት_ሴት_ደናግል ልጆቿ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዐል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ስምዖን_ዘዓምድ_ሶርያዊ፦ ለዚህም ቅዱስ ስድስት ዓመት በሆነው ጊዜ አባቱ የበጎቹ ጠባቂ አደረገው። ወደ ቤተ ክርስቲያንም በመሔድ ሁል ጊዜ ቅዱሳት መጻሕፍትን ይሰማ ነበር የእግዚአብሔርም ቸርነት አነሳሥቶት ወደ አንድ ገዳም ሒዶ መነኰሰ ብዙ ዘመናትም በገድል ተጠምዶ ሲጋደልና ሰውነቱን ሲያስጨንቅ ኖረ።
❤ ከዚህም በኋላ ገመዱ ሥጋውን ቆርጦ እስቲገባ ድረስ በወገቡ ላይ ገመድን አሠረ። ሥጋውም ተልቶ ከእርሱ ክፉ ሽታ ይወጣ ነበር ስለ ክፉ ሽታውም መነኰሳቱ አዘኑ ተጸየፉትም ወደ አበ ምኔቱም ተሰብስበው "ይህን መነኰስ ስምዖንን ከእኛ ዘንድ ካላወጣኸው አለዚያ አንተን ትተን ወደሌላ እንሔዳለን" አሉት እርሱም "ምን አደረገ" አላቸው እነርሱም "ጥራውና አንተ ራስህ እይ" አሉት። ጠርቶትም መጥቶ በፊቱ በቆመ ጊዜ ደም ከመግል ጋራ በእግሮቹ ላይ ሲፈስ አየ አበ ምኔቱንም እጅግ አስጨነቀው። ልብሶቹንም ገልጦ በሥጋው ውስጥ የገባውን ያንን ገመድ አየው አበ ምኔቱም በእርሱ ላይ ተቆጥቶ "ይህን ታደርግ ዘንድ እንዴት ደፈርክ" አለው በታላቅ ድካምም ያንን ገመድ ከሥጋው ውስጥ አወጡት ቍስሉም እስከሚድን መድኃኒት እያደረጉለት ኃምሳ ቀኖች ያህል ኖረ።
❤ ከዚህም በኋላ አበ ምኔቱ እንዲህ አለው "ልጄ ስምዖን ሆይ እንግዲህስ ወደ ፈለግኸው ቦታ ሒድ" ከዚያም ወጥቶ ሔደ በደረቅ ጕድጓድ ውስጥም ገብቶ ከእባቦችና ከጊንጦች ጋራ ኖረ።
❤ ከዚህም በኋላ "አገልጋዩ ስምዖንን ለምን ሰደድከው አሁንም ፈልገህ መልሰው በፍርድ ቀን እርሱ ከአንተ ይሻላልና" ብሎ ሲገሥጸው አበ ምኔቱ ራእይን አየ። አባ ስምዖንንም ከገዳሙ ስለመውጣቱ ገሠጸው። በነጋም ጊዜ አበ ምኔቱ ራእይን እንዳየ ስለ አባ ስምዖንም እንደገሠጸው ለመነኰሳቱ ነገራቸው ወንድሞችም ደንግጠው እጅግ አዘኑ "እስከምታገኙትም ሔዳችሁ በቦታው ሁሉ ፈልጉት" አላቸው ሔደውም ፈለጉት ግን አላገኙትም። ከዚህም በኋላ መብራትን አብርተው ወደ ጕድጓድ ውስጥ ገቡ ያለ መብልና መጠጥም ከእባቦችና ከጊንጦች ጋራ ተቀምጦ አዩት።
❤ ገመድም አውረዱለትና ከዚያ አወጡት በፊቱም ሰግደው "በአንተ ላይ ያደረግነውን በደላችንን ይቅር በለን" አሉት "እኔንም ስለ አሳዘንኳችሁ ይቅር በሉኝ" አላቸው። ከዚህም በኋላ ወደ ገዳማቸው ወሰዱት በብዙ ገድልም ተጠምዶ ሲያገለግል ኖረ።
❤ ከዚህም በኋላ ከዚያ ገዳም በሥውር ወጥቶ ወደ አንዲት ዐለት ቋጥኝ ደረሰ። በእርስዋም ላይ ሳያረፍና ሳይተኛ ስልሳ ቀን ቆመ። ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ስለ ብዙ ሰዎች ድኅነት እግዚአብሔር እንደ ጠራው ነገረው። ከዚያም ሔዶ ቁመቱ ሠላሳ ክንድ የሚሆን የድንጋይ ምሰሶ አገኘ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ በሽተኞችንም እየፈወሰ ወደርሱ የሚመጡትንም እያስተማረ ዐሥራ ሁለት ዓመት በድንጋይ ምሰሶው ላይ ቆመ።
❤ አባቱም ፍልጎት ነበር ግን ሳያየው ሞተ እናቱ ግን ወሬውን ሰምታ ከብዙ ዘመናት በኋላ ወደርሱ መጣች በድንጋይ ምሰሶውም ላይ ቁሞ አገኘችው አይታውም አለቀሰች ከድንጋይ ምሰሶውም በታች ተኛች። ቅዱስ ስምዖንም ጌታችን በጎ ነገርን ያደርግላት ዘንድ ስለርሷ ለመነ ያን ጊዜም እንደተኛች ዐረፈችና ከደንጊያው ምሰሶ በታች ቀበሩዋት።
❤ ሰይጣንም በእርሱ ላይ ቀንቶ እግሩን መታው ከእግሩ ትል እየወደቀ በአንዲት እግሩ ብዙ ዓመታት ኖረ። ከዚህም በኋላ የሽፍቶች አለቃ ወደርሱ መጥቶ ንስሐ ገባ ጥቂት ቀኖችም ኑሮ ዐረፈ በጸሎቱም ሕይወትን ወረሰ። ወደርሱ ስለሚመጡ ብዙ ሕዝቦችም የውኃ ጥማት እንዳያስጨንቃቸው ወደ እግዚአብሔር ለምኖ ከድንጋይ ምሰሶው በታች ውኃን አፈለቀላቸው።
❤ ዳግመኛም ወደ ሌላ ምሰሶ ተዛወረ በእርሱም ላይ እየተጋደለ ሠላሳ ዓመት ኖረ። ብዙዎች አረማውያንንና ከሀድያንን ካስተማራቸውና ወደ ፈጠራቸው እግዚአብሔር ከመለሳቸው በኋላ ክብር ይግባውና ወደ ወደደው ክርስቶስ ሔደ በሰላምም ዐርፎ የዘላለም ሕይወትን ወረሰ።
❤ ከዚህም በኋላ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባ ስምዖን እንዳረፈ በሰማ ጊዜ ካህናትን ዲያቆናትንና የአገሩን መኳንንቶች ከእርሱ ጋራ ይዞ የቅዱስ አባ ስምዖን ሥጋው ወዳለበት ደረሰ በታላቅ ክብርም ተሸክመው እየዘመሩና እያመሰገኑ ወደ እስክንድርያ አድርሰው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖሩት ከሥጋውም ድንቆችና ተአምራቶች ታላቅ ፈውስም ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በመስተጋድል በአባ ስምዖን ዘአምድ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅድስት_ሶፍያ_ሦስቱ_ደናግል_ልጆቿ፦ ለዚችም ቅድስት ብዙ ሀብትና ብዙ ጥሪት ነበራት ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ ፍቅር የክርስቶስን መከራ መስቀል አንሥታ ትሸከም ዘንድ ከሦስት ሴቶች ልጆቿ ጋራ ወደ ሮም ከተማ ሔደች።
❤ ንጉሥ እንድርያሰኖስም ክርስቲያን እንደ ሆነች አውቆ ከልጆቹ ጋራ ወደ አደባባይ አስቀረባትና ስለ ሀገርዋና ስለ ስሟ ጠየቃት እርሷም "የሚቀደመው ስሜ ክርስቲያን ነኝ ወላጆቼ ያውጡልኝ ስም ሶፊያ ነው እኔም በኢጣልያ ባለ ብዙ ወገን ነኝ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ፈቃድም ልጆቼን መሥዋዕት አድርጌ ላቀርብ ወደ አገርህ መጣሁ" አለችው። ከዚህም በኋላ የከዳተኛው ንጉሥ ሥቃዩ እንዳያስፈራቸው ልጆቿን አበረታቻቸው።
❤ ምስክርነታቸውንም ፈጽመው ከሞቱ በኋላ ገንዛ ከሮሜ ከተማ ውጭ ቀበረቻቸው። በሦስተኛውም ቀን መታሰቢያቸውን ታደርግ ዘንድ ልጆቿ ወደ ተቀበሩበት ከብዙዎች ከከተማው ሴቶች ጋራ ሔደች እንዲህ ብላም ጸለየች "አክሊላትን የተቀዳጃችሁ የምታምሩ ፍጹማት የሆናችሁ ልጆቼ ሆይ እኔንም ከእናንተ ጋራ ውሰዱኝ" ይህንንም እንዳለች ወዲያውኑ ዐረፈች ከልጆቿም ጋር ተቀበረች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ሶፍያና በሦስቱ ደናግል ልጆቿ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ "#ሰላም_ለስምዖን_እንተ_ለሐቌሁ_አድንዖ። በኀብለ በቀልት ይቡስ ዘይገምዶ ወይበልዖ። በእንተ ዝንቱ እምደብር ሶበ አበምኔት አውጽኦ። በቃለ ተግሣጽ እግዚአብሔር አውሥኦ። ለገብርየ ስምዖን እንዘ ይብል አግብኦ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የነሐሴ_3።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ነሐሴ ፪ (2) ቀን።
❤ እንኳን #በአባ_ዮሐንስ_ሐጺር ምክር ለንስሐ በቅታ ከዘማዊነት ለተመለሰች #ለቅድስት_አትናስያና ከነገሥታት ወገን ለሆነች #ለቅድስት_ኢዮጰራቅስያ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከዲያቆናዊት_ኢዮኤልያና ዕረፍት፣ #ከሰማዕቱ_ደሚናና ሰማዕታት ከሆኑ ወንድሞቹ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅድስት_አትናስያ፦ የዚችም ቅድስት ወላጆቿ ባለጸጎች ነበሩ እነርሱም በሞቱ ጊዜ ቤቷን ለእንግዳ ማደሪያ ታደርግ ዘንድ በጎ ኃሳብ አሰበች ወደርሷም የሚመጡትን እንግዶች ሁሉ ትቀበላቸው ነበር። በገዳም ለሚኖሩ መነኰሳትም የሚያስፈልጓቸውን ትሰጣቸው ነበር ስለ በጎ ሥራዋም ይወዷት ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ ግብራቸው የከፋ ክፉዎች ሰዎች ወደርሷ ተሰብስበው ኃሳቧን ወደ ኃጢአት ሥራ መለሱትና ኃጢአትን አብዝታ ትሠራ ጀመር። በአስቄጥስ ገዳም በሚኖሩ አረጋውያን ቅዱሳን ዘንድም ወሬዋ ተሰማ ስለእርሷም እጅግ አዘኑ አባ ዮሐንስ ሐጺርንም ጠርተው ስለርሷ የሆነውን ነገሩት አስቀድማም ከእነርሱ ጋራ በጎ ስለ ሠራች ወደ እርስዋ ይሔድ ዘንድ ነፍስዋንም ለማዳን ይወድ ዘንድ ለመኑት።
❤ እርሱም ትእዛዛቸውን ተቀበለ በጸሎታቸውም እንዲረዱት ለመናቸው ያን ጊዜም አባ ዮሐንስ ሐጺር ተነሥቶ ሔደ አትናስያ ወዳለችበት ቦታ ደረሰ ለበረኛዋም "ለእመቤትሽ ስለእኔ ንገሪ" አላት። በነገረቻትም ጊዜ ለረከሰ ሥራ እንደሚፈልጓት ሰዎች ሁሉ የመጣ መሰላትና አጊጣ በዐልጋዋ ላይ ሁና ጠራችው። ወደርሷም ገባ እርሱም እንዲህ እያለ ይዘምር ነበር "በሞት ጥላ ውስጥ ብሔድም እንኳ ክፉን አልፈራውም አንተ ከእኔ ጋራ ነህና"። ከእርሷ ጋራም አስቀመጠችው ያን ጊዜም ራሱን ዘንበል አድርጎ አለቀሰ "ለምን ታለቅሳለህ" አለችው እርሱም "ሰይጣናትን በላይሽ ሲጫወቱ አየኋቸው ክብር ይግባውና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ለምን አሳዘንሺው የቀድሞ በጎ ሥራሽን ትተሽ ወደ ጥፋት ሥራ ተመልሰሻልና" አላት።
❤ ቃሉንም ሰምታ ደነገጠችና ተንቀጠቀጠች "ምን ይሻለኛል" አለችው "ንስሐ ግቢ" አላት እርሷም "እግዚአብሔር ይቀበለኛልን" አለችው እርሱም "አዎን" አላት እርሷም "ወደምትሔድበት ከአንተ ጋራ ውሰደኝ" አለችው እርሱም "ነዪ ተከተይኝ" አላት። ያን ጊዜም ፈጥና ተነሥታ በኋላው ተከተለችው ከገንዘቧም ምንም ምን አልያዘችም። በመሸም ጊዜ ለማደር ወደ ጫካ ውስጥ ገቡ በዚያም ለእርስዋ ቦታ አዘጋጅቶ "እስኪነጋ በዚህ አረፍ ብለሽ ተኚ እኔም ወደዚያ እሆናለሁ" አላት። ይህንንም ብሎ ከእርሷ ጥቂት ተገልሎ እየጸለየ ብቻውን ተቀመጠ።
❤ በሌሊቱ እኩሌታም ሊጸልይ ተነሣ ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ የብርሃን ምሰሶ አየ የእግዚአብሔርም መላእክት የከበረች ነፍስን ተሸክመው ሲወጡ አይቶ አደነቀ። በነጋም ጊዜ ወደ ርሷ ሔደ ሙታም አገኛት እጅግም አዘነ ስለ ርሷም ያስረዳው ዘንድ እየሰገደ ወደ እግዚአብሔር ለመነ።
❤ ወደርሱም እንዲህ የሚል ቃል መጣ ከቤቷ በወጣች ጊዜ እግዚአብሔር ንስሓዋን ተቀብሎ ኃጢአትሽ ተሠረየልሽ ብሎአታል። ከዚህም በኋላ ሒዶ ለአረጋውያን የሆነውን ሁሉ ነገራቸው እነርሱም እርሱ እንዳያት ማየታቸውን ነገሩት የኃጢአተኛን ወደ ንስሐ መመለሱን እንጂ ሞቱን የማይሻ እግዚአብሔርን አመሰገኑት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አትናስያ በጸሎቷ ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ድንግሊቱ_ቅድስት_ኢዮጰራቅስያ፦ የእርስዋም የአባቷ ስም ኢጣጎኖስ ነው የንጉሥም አማካሪ ነበር የእናቷም ስም ኢዮጰራቅስያ ነው እነርሱም ደጎች ነበሩ ጾምና ጸሎትንም ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡ ነበሩ። ይችንም ቅድስት በወለዷት ጊዜ በእናቷ ስም ኢዮጰራቅስያ ብለዉ ጠሩዋት።
❤ ከጥቂት ጊዜ በኋላም አባቷ ዐረፈ ዕድሜዋም ስድስት ዓመት በሆነ ጊዜ እናቷ ወደ ደናግል ገዳም ከእርሷ ጋር ወሰደቻት ይህችም ቅድስት ደናግሉ ሲያገለግሉ አይታ "ስለ ምን እንዲህ ደክማችሁ ትሠራላችሁ" አለቻቸው እነርሱም ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ ነው ብለው መለሱላት ወደ ዲያቆናዊትም ሒዳ ያመነኲሷት ዘንድ ለመነች እነርሱም ለእናቷ ነገሩዋት እናቷም ለዲያቆናዊተዋ ሰጠቻት በደናግሉም ሁሉ ዘንድ አደራ ሰጠቻት ከጥቂትም ቀኖች በኋላ እናቷ ዐረፈችና ቀበሩዋት።
❤ ከዚህም በኋላ ቅድስት ኢዮጰራቅስያ የምንኲስና ልብስን ለበሰች በጾም በጸሎትና በሰጊድ ተጋድሎ ጀመረች በየሰባት ቀንም ትጾም ነበር ሰይጣንም በእርሷ ላይ ቀንቶ ሊፈትናት ጀመረ ወደ ውኃ ውስጥ እርስዋን የሚጥልበት ጊዜ ነበር እንጨትም ስትፈልጥ በምሳር የሚአቊስልበት ጊዜ ነበር። የፈላ ውኃም በላይዋ የሚያፈሰበት ጊዜ ነበር ነገር ግን ምንም ምን የጐዳት የለም።
❤ ለደነግሎችም ስታገለግል ብዙ ዘመናት ኖረች ምንም አትታክትም ነበር በምድርም ላይ አትተኛም መላዋን ሌሊት ቁማ በጸሎት ታድር ነበር እንጂ ከገድሏ ጽናትም የተነሣ ደናግሉ እስከሚያደንቁ ድረስ አርባ ቀን ቁማ ትፈጽም ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ ጌታችን በሽተኞችን በማዳን አጋንንትን በማስወጣት የዕውሮችን ዐይን በመግለጥ የአንካሶችንም እግር በማስተካከል ድንቆችንና ተአምራቶችን በእጆቿ ገለጠ። ዲያቆናዊት ኢዮኤልያም ለኢዮጰራቅስያ መጸሐፍትንና የምንኵስናንም ሥርዓት አስተማረቻት በሥራም ሁሉ ትሳተፋት ነበር እጅግም ይፋቀሩ ነበር እርሷም ሰማያዊ ሙሽራ ወደአለበት የመንግሥት አዳራሽ የማያልቅ ተድላ ደስታም ወደአለበት ኢዮጵራቅስያን ሲያወጧት ራእይን አየች።
❤ በነቃችም ጊዜ ለደናግል ነገረቻቸው ወደርሷ ሲሔዱም በትኩሳት በሽታ ታማ አገኟት ስለእነርሱም እንድትጸልይ ለመኑዋት እርሷም ደግሞ በጸሎታቸው እንዲአስቧት ለመነቻቸው ያን ጊዜም ጸሎት አድርጋ መረቀቻቸውና ነሐሴ 2 ቀን በሰላም ዐረፈች በእናቷም መቃብር ውስጥ ቀበሩዋት።
❤ ወዳጅዋ ኢዮኤልያም ወደ መቃብርዋ ሒዳ ጸለየችና በሦስተኛው ቀን ዐረፈች ከእርሷም ጋር ተቀበረች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ደናግል በቅዱሳት ኢዮጰራቅስያና ኢዮኤልያ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 2 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለአትናስያ_ለተሊወ_ክርስቶስ_ፌማ። በምክረ ዮሐንስ ሐጺር ወአኮ ከማ። ሶበ መነነት ዓለም ወገደፈት ትርሲተ ዘማ። ነፍሳ ወሰዱ መላእክት እንዘ የኀልዩ በዜማ በዕለተ አዕረፈት ዮም እምሕማም ወፃማ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የነሐሴ 2።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወይወስዱ ለንጉሥ ደናግል ድኅሬሃ። ወቢጻሂ ይወስዱ ለከ። ወይወስድዎን በትፍሥሕት ወበኃሤት"። መዝ 44፥14-15 ወይም መዝ 86፥5። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ጢሞ 2፥8-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 3፥1-7 እና የሐዋ ሥራ 16፥13-19። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 8፥1-12 ወይም ማቴ 12፥38-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ነሐሴ ፪ (2) ቀን።
❤ እንኳን #በአባ_ዮሐንስ_ሐጺር ምክር ለንስሐ በቅታ ከዘማዊነት ለተመለሰች #ለቅድስት_አትናስያና ከነገሥታት ወገን ለሆነች #ለቅድስት_ኢዮጰራቅስያ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከዲያቆናዊት_ኢዮኤልያና ዕረፍት፣ #ከሰማዕቱ_ደሚናና ሰማዕታት ከሆኑ ወንድሞቹ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅድስት_አትናስያ፦ የዚችም ቅድስት ወላጆቿ ባለጸጎች ነበሩ እነርሱም በሞቱ ጊዜ ቤቷን ለእንግዳ ማደሪያ ታደርግ ዘንድ በጎ ኃሳብ አሰበች ወደርሷም የሚመጡትን እንግዶች ሁሉ ትቀበላቸው ነበር። በገዳም ለሚኖሩ መነኰሳትም የሚያስፈልጓቸውን ትሰጣቸው ነበር ስለ በጎ ሥራዋም ይወዷት ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ ግብራቸው የከፋ ክፉዎች ሰዎች ወደርሷ ተሰብስበው ኃሳቧን ወደ ኃጢአት ሥራ መለሱትና ኃጢአትን አብዝታ ትሠራ ጀመር። በአስቄጥስ ገዳም በሚኖሩ አረጋውያን ቅዱሳን ዘንድም ወሬዋ ተሰማ ስለእርሷም እጅግ አዘኑ አባ ዮሐንስ ሐጺርንም ጠርተው ስለርሷ የሆነውን ነገሩት አስቀድማም ከእነርሱ ጋራ በጎ ስለ ሠራች ወደ እርስዋ ይሔድ ዘንድ ነፍስዋንም ለማዳን ይወድ ዘንድ ለመኑት።
❤ እርሱም ትእዛዛቸውን ተቀበለ በጸሎታቸውም እንዲረዱት ለመናቸው ያን ጊዜም አባ ዮሐንስ ሐጺር ተነሥቶ ሔደ አትናስያ ወዳለችበት ቦታ ደረሰ ለበረኛዋም "ለእመቤትሽ ስለእኔ ንገሪ" አላት። በነገረቻትም ጊዜ ለረከሰ ሥራ እንደሚፈልጓት ሰዎች ሁሉ የመጣ መሰላትና አጊጣ በዐልጋዋ ላይ ሁና ጠራችው። ወደርሷም ገባ እርሱም እንዲህ እያለ ይዘምር ነበር "በሞት ጥላ ውስጥ ብሔድም እንኳ ክፉን አልፈራውም አንተ ከእኔ ጋራ ነህና"። ከእርሷ ጋራም አስቀመጠችው ያን ጊዜም ራሱን ዘንበል አድርጎ አለቀሰ "ለምን ታለቅሳለህ" አለችው እርሱም "ሰይጣናትን በላይሽ ሲጫወቱ አየኋቸው ክብር ይግባውና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ለምን አሳዘንሺው የቀድሞ በጎ ሥራሽን ትተሽ ወደ ጥፋት ሥራ ተመልሰሻልና" አላት።
❤ ቃሉንም ሰምታ ደነገጠችና ተንቀጠቀጠች "ምን ይሻለኛል" አለችው "ንስሐ ግቢ" አላት እርሷም "እግዚአብሔር ይቀበለኛልን" አለችው እርሱም "አዎን" አላት እርሷም "ወደምትሔድበት ከአንተ ጋራ ውሰደኝ" አለችው እርሱም "ነዪ ተከተይኝ" አላት። ያን ጊዜም ፈጥና ተነሥታ በኋላው ተከተለችው ከገንዘቧም ምንም ምን አልያዘችም። በመሸም ጊዜ ለማደር ወደ ጫካ ውስጥ ገቡ በዚያም ለእርስዋ ቦታ አዘጋጅቶ "እስኪነጋ በዚህ አረፍ ብለሽ ተኚ እኔም ወደዚያ እሆናለሁ" አላት። ይህንንም ብሎ ከእርሷ ጥቂት ተገልሎ እየጸለየ ብቻውን ተቀመጠ።
❤ በሌሊቱ እኩሌታም ሊጸልይ ተነሣ ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ የብርሃን ምሰሶ አየ የእግዚአብሔርም መላእክት የከበረች ነፍስን ተሸክመው ሲወጡ አይቶ አደነቀ። በነጋም ጊዜ ወደ ርሷ ሔደ ሙታም አገኛት እጅግም አዘነ ስለ ርሷም ያስረዳው ዘንድ እየሰገደ ወደ እግዚአብሔር ለመነ።
❤ ወደርሱም እንዲህ የሚል ቃል መጣ ከቤቷ በወጣች ጊዜ እግዚአብሔር ንስሓዋን ተቀብሎ ኃጢአትሽ ተሠረየልሽ ብሎአታል። ከዚህም በኋላ ሒዶ ለአረጋውያን የሆነውን ሁሉ ነገራቸው እነርሱም እርሱ እንዳያት ማየታቸውን ነገሩት የኃጢአተኛን ወደ ንስሐ መመለሱን እንጂ ሞቱን የማይሻ እግዚአብሔርን አመሰገኑት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አትናስያ በጸሎቷ ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ድንግሊቱ_ቅድስት_ኢዮጰራቅስያ፦ የእርስዋም የአባቷ ስም ኢጣጎኖስ ነው የንጉሥም አማካሪ ነበር የእናቷም ስም ኢዮጰራቅስያ ነው እነርሱም ደጎች ነበሩ ጾምና ጸሎትንም ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡ ነበሩ። ይችንም ቅድስት በወለዷት ጊዜ በእናቷ ስም ኢዮጰራቅስያ ብለዉ ጠሩዋት።
❤ ከጥቂት ጊዜ በኋላም አባቷ ዐረፈ ዕድሜዋም ስድስት ዓመት በሆነ ጊዜ እናቷ ወደ ደናግል ገዳም ከእርሷ ጋር ወሰደቻት ይህችም ቅድስት ደናግሉ ሲያገለግሉ አይታ "ስለ ምን እንዲህ ደክማችሁ ትሠራላችሁ" አለቻቸው እነርሱም ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ ነው ብለው መለሱላት ወደ ዲያቆናዊትም ሒዳ ያመነኲሷት ዘንድ ለመነች እነርሱም ለእናቷ ነገሩዋት እናቷም ለዲያቆናዊተዋ ሰጠቻት በደናግሉም ሁሉ ዘንድ አደራ ሰጠቻት ከጥቂትም ቀኖች በኋላ እናቷ ዐረፈችና ቀበሩዋት።
❤ ከዚህም በኋላ ቅድስት ኢዮጰራቅስያ የምንኲስና ልብስን ለበሰች በጾም በጸሎትና በሰጊድ ተጋድሎ ጀመረች በየሰባት ቀንም ትጾም ነበር ሰይጣንም በእርሷ ላይ ቀንቶ ሊፈትናት ጀመረ ወደ ውኃ ውስጥ እርስዋን የሚጥልበት ጊዜ ነበር እንጨትም ስትፈልጥ በምሳር የሚአቊስልበት ጊዜ ነበር። የፈላ ውኃም በላይዋ የሚያፈሰበት ጊዜ ነበር ነገር ግን ምንም ምን የጐዳት የለም።
❤ ለደነግሎችም ስታገለግል ብዙ ዘመናት ኖረች ምንም አትታክትም ነበር በምድርም ላይ አትተኛም መላዋን ሌሊት ቁማ በጸሎት ታድር ነበር እንጂ ከገድሏ ጽናትም የተነሣ ደናግሉ እስከሚያደንቁ ድረስ አርባ ቀን ቁማ ትፈጽም ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ ጌታችን በሽተኞችን በማዳን አጋንንትን በማስወጣት የዕውሮችን ዐይን በመግለጥ የአንካሶችንም እግር በማስተካከል ድንቆችንና ተአምራቶችን በእጆቿ ገለጠ። ዲያቆናዊት ኢዮኤልያም ለኢዮጰራቅስያ መጸሐፍትንና የምንኵስናንም ሥርዓት አስተማረቻት በሥራም ሁሉ ትሳተፋት ነበር እጅግም ይፋቀሩ ነበር እርሷም ሰማያዊ ሙሽራ ወደአለበት የመንግሥት አዳራሽ የማያልቅ ተድላ ደስታም ወደአለበት ኢዮጵራቅስያን ሲያወጧት ራእይን አየች።
❤ በነቃችም ጊዜ ለደናግል ነገረቻቸው ወደርሷ ሲሔዱም በትኩሳት በሽታ ታማ አገኟት ስለእነርሱም እንድትጸልይ ለመኑዋት እርሷም ደግሞ በጸሎታቸው እንዲአስቧት ለመነቻቸው ያን ጊዜም ጸሎት አድርጋ መረቀቻቸውና ነሐሴ 2 ቀን በሰላም ዐረፈች በእናቷም መቃብር ውስጥ ቀበሩዋት።
❤ ወዳጅዋ ኢዮኤልያም ወደ መቃብርዋ ሒዳ ጸለየችና በሦስተኛው ቀን ዐረፈች ከእርሷም ጋር ተቀበረች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ደናግል በቅዱሳት ኢዮጰራቅስያና ኢዮኤልያ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 2 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለአትናስያ_ለተሊወ_ክርስቶስ_ፌማ። በምክረ ዮሐንስ ሐጺር ወአኮ ከማ። ሶበ መነነት ዓለም ወገደፈት ትርሲተ ዘማ። ነፍሳ ወሰዱ መላእክት እንዘ የኀልዩ በዜማ በዕለተ አዕረፈት ዮም እምሕማም ወፃማ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የነሐሴ 2።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወይወስዱ ለንጉሥ ደናግል ድኅሬሃ። ወቢጻሂ ይወስዱ ለከ። ወይወስድዎን በትፍሥሕት ወበኃሤት"። መዝ 44፥14-15 ወይም መዝ 86፥5። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ጢሞ 2፥8-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 3፥1-7 እና የሐዋ ሥራ 16፥13-19። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 8፥1-12 ወይም ማቴ 12፥38-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታች የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ እንኳን #ለጾመ_ፍልሰታ_ለማርያም እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ "#በጾም_ወበጸሎት_ወበምጽዋት ወበተፋቅሮ ይሰረይ ኃጢአት ይእዜኒ ወዘልፈኒ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም"። ትርጉም፦ #በጾምና_በጸሎት_በምጽዋት በመፋቀርም ኃጢአት ይወገዳል ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለም።#ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በጾመ_ድጓው_ላይ።
❤ ጾም ለአገራችን ኢትዮጵያና ለሕዝቧቿ ፍቅር፣ሰላም አንድነትን፤ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን አማኞች ላይ እየሆነ ያለው ስደት፣ እንግልት፣ መካራና ሞት የሚያበቃ ያድርግል። በሰላም ጀምረን በሰላም ለመጨረስ ያብቃን ለሁላችንም የበረከት ጾምና መልካም ሱባኤ ይሁንልን።
❤ ያን ጊዜም ቅዱስ አቦሊ ተነሣ እንዲህ ብሎ ጸለየ "ስለ ቅዱስ ስምህ መከራን እቀበል ዘንድ የመረጥከኝ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በእኒህ በሞቱ ሰዎች ላይ ኃይልህን ግለጥ። እኒህ ሰዎች ሁሉ እንዲአምኑ ያለ አንተም ሌላ አምላክ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ ከሞት አንሣቸው። ላንተም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን"።
❤ ከዚህም በኋላ የተገፈፈ ቆዳውን ወስዶ በሞቱት ሰዎች ላይም ዘረጋውና "በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከሞት ተነሡ" አለ። ወዲያውም ሁሉም ድነው ተነሡ በዚያ ያሉ ሕዝብም ይህን ድንቅ ሥራ በአዩ ጊዜ "የክርስቲያን አምላክ የቅዱስ አቦሊም አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ነው እኛም እናምንበታለን ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለምና" እያሉ ጮኹ።
❤ ባለ ጸጋው አብስኪሮንም መጥቶ ለቅዱስ አቦሊ እንዲህ እያለ ሰገደ "ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ይግባውና እውነተኛ አምላክ እንደሆነ ዛሬ አወቅሁ እኔም አምንበታለሁ። ከቤተሰቦቹም ሁሉ ጋር አመኑ መኰንኑም" ዐፈረ።
❤ ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ አቦሊ ተገለጠለት እንዲህም ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው። "በመከራ ውስጥ ያለ ሰው በስምህ ርዳታ ቢለምን እኔ እሰማዋለሁ ልመናውን ፍላጎቱንም እፈጽምለታለሁ። በስምህ ቤተ ክርስቲያን ለሠራም እኔ በሰማያት ብርሃናዊ ማደሪያ ቤት እሠራለታለሁ የገድልህን መጽሐፍ የሚጽፈውን ወይም የሚያነበውን ወይም የሚሰማውን እኔ በኪሩቤል ክንፎች ላይ ስሙን እጽፉለሁ በአብርሃም በይስሐቅና በያዕቆብ እቅፍም አሳርፈዋለሁ ተድላ ደስታ ካለባት ከገነት ፍሬዎችም እመግበዋለሁ። ብዙ ኃጢአትን ሠርቶ የበደለውንም በስምህ ወደኔ እየለመነ ንስሐ ቢገባ በደሉን ሁሉ ይቅር እለዋለሁ። ከጻድቃንም ጋርም እቈጥረዋለሁ ሰላሜም ካንተ ጋራ ይሁን" ይህንንም ብሎ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ።
❤ መኰንኑም ከማሠቃየቱ የተነሣ በደከመ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ የከበረች ራሱን ቆረጡት የሕይወት አክሊልንም ተቀበለ። ሥጋውም ከምስር ከተማ ውጭ ሕንቅ በሚባል ገዳም ይኖራል ከእርሱም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ አቦሊ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 1 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወእነግር ስምዐከ በቅድመ ነገሥት ወኢይትኃፈር። ወአነብብ ትእዛዘከ ዘአፍቀርኩ ጥቀ። ወአነሥእ እደውየ ኀበ ትእዛዝከ ዘአፍቀርኩ"። መዝ 118፥46-47 ወይም 131፥13-14 ። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ጢሞ 5፥1-11፣ 1ኛ ዮሐ 5፥1-6፣ የሐዋ ሥራ 5፥26-34። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 19፥38-ፍ.ም ወይም ሉቃ 1፥39፥47። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ወይም የዮሐንስ አፈወርቅ ቅዳሴ ነው። መልካም የፆም ጊዜና በዓል ለሁላችን ይሁንልን።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ የተባረከው #የነሐሴ ወር የቀኑ ሰዓት ዐሥራ ሦስት ነው ከዚህም በኋላ ይጎድላል።
❤ #ነሐሴ ፩ (1) ቀን።
❤ እንኳን #ጌታችንን_ለገነዙ ለአምላካዊ ምሥጢር አገልጋዮች ለሆኑ ለተገባቸው ለከበሩ #ለቅዱስ_ዮሴፍና_ለቅዱስ_ኒቆዲሞስ_ለመታሰቢያ በዐላቸውና ለታላቁ ሰማዕት ለቅዱስ ዮስጦስ ልጅ #ለቅዱስ_አቦሊ_ለዕረፍት_በዐል_በሰላም_አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ አምላክን ከወለደች ከእመቤታች ከድንግል ማርያም እናት #ከቅድስት_ሐና ከመታሰቢያዋ፣ #ከፋኑኤል_ልጅ_ከነቢይት_ሐና ከመታሰቢያዋና #ከንግሥት_ሶፍያ_ልጆች #ከቅዱሳን_ደናግል ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቅዱሳን_ዮሴፍና_ኒቆዲሞስ፦ በፈቃዱ መከራ ተቀብሎ ስለ ደኅንነታችን በሞተ ጊዜ የደኅንነታችንንም ምሥጢር በፈጸመ ጊዜ የሕያው እግዚአብሔርን ልጅ የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ እነርሱ ከመስቀል ላይ አውርደዋልና። የአይሁድም መገርመም ከጲላጦስ ዘንድ የመድኃኒታችንን ሥጋ እስከ ለመኑ ድረስ አላስፈራቸውም።
❤ ጲላጦስም በፈቀደላቸው ጊዜ የእጆቹንና የእግሮቹን ችንካሮች ነቅለው ከመስቀል አውርደው በትክሻቸው ተሸከሙት ሲገንዙትም እንዲህ የሚል ቃል ከበድኑ ሰሙ። "ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደ አቤቱ ይቅር በለን። ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት በዮርዳኖስ የተጠመቀ በእንጨት መስቀልም የተሰቀለ አቤቱ ይቅር በለን። ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ የተነሣ በክብር ወደ ሰማያት ያረገ በአባቱም ቀኝ የተቀመጠ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ የሚመጣ አቤቱ ይቅር በለን። ለአብ ምስጋና ይገባል ለወልድ ምስጋና ይገባል ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን አሜን ይሁን ይሁን። ልዩ ሦስት ሕያው እግዚአብሔር ይቅር በለን"።
❤ ይህንንም በሰሙ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖታቸው ጸናች። ዮሴፍም በፍታ ኒቆዲሞስም ሽቶዎችን አምጥተው ጌታችንን ገነዙት በአዲስ መቃብር ውስጥም ቀበሩት።
❤ ይህ ዮሴፍም ለሰማዕታት መጀመሪያ ለእስጢፋኖስ ዘመድ ለሆነው ለቀለዮጳ ወንድሙ ለኒቆዲሞስ ዘመዱ ነው ኒቆዲሞስም የአይሁድ አለቃ ፈሪሳዊ ነበር እርሱም ወደ ጌታ ኢየሱስ አስቀድሞ በሌሊት የሔደና ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣ ያመነ ነበር። ጌታችንም ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንደማይችል የነገረው ነው።
❤ ይህ ኒቆዲሞስም የጌታችንን ቃል በሚአቃልሉ ጊዜ አይሁድን ይገሥጻቸው ነበር። ከተነሣ በኋላም በኢማሁስ መንገድ ሲሔድ ጌታችን ኢየሱስ የተገናኛቸው እሊህ ኒቆዲሞስና ቀለዮጳ ናቸው። እነርሱም ሳያውቁት በእርሱ ላይ የሆነውን ሁሉ ነገሩት። እርሱም ስለ ሞቱና ስለ ትንሣኤው ነቢያት ትንቢት እንደ ተናገሩ አስተማራቸው።
❤ ከዘህም በኋላ እርሱ መሆኑን ባወቁት ጊዜ ተሠወራቸው እነርሱም ተመልሰው ለደቀ መዛሙርቱ ነገሩ። ክብር ይግባውና የጌታችንን ሥጋ ስለ ቀበረ ሊገድሉት ፈልገው አይሁድ ዮሴፍን በወህኒ ቤት አሠሩት። የወህኒ ቤቱም በር በሊቃነ ካህናቱና በጲላጦስ ማኅተም ተቆልፎ ሳለ ጌታችን በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጦ ዮሴፍ ወደ አለበት ገባ ከእርሱ ጋርም እልፍ አእላፋት መላእክት ነበሩ። ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው በፊቱ ያጥናሉ በቀኝ በኩል ተሰቅሎ የነበረ ወንበዴውም ብሩህ ልብስ ለብሶ በቀኝ ቁሞአል ባለሟልነትን በልዑል ፊት አግኝቶአልና ስለ ኃጢአተኞች ይማልድ ነበር።
❤ የወህኒ ቤት ጠባቂዎችም በአዩ ጊዜ ደነገጡ ፈርተውም መንቀጥቀጥ ያዛቸው ጌታችንም ዮሴፍን ጠርቶ እንዲህ አለው "ከአይሁድ ግርማ የተነሣ አትፍራ ከማሠሪያህ ልፈታሕ እኔ መጣሁ አንተ መከራዬን የተሳተፍከኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ እኔ ነኝ አኔ ጌታህና የዓለሙ ሁሉ ጌታ እንደሆንሁ ፈጽመህ ታውቅ ዘንድ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን የተወጋ ጐኔንም እይ"።
❤ ከዚያም ዮሴፍን ነጥቆ ወደ አገሩ አርማትያስ ወሰደው። የወህኒ ቤቱ ጠባቂዎችም ሔደው ጌታችን ያደረገውን ሁሉ ዮሴፍንም ይዞ ከእርሱ ጋር እንደወሰደው ለካህናት አለቆች ነገሩ። የካህናት አለቆችም በሔዱ ጊዜ የወህኒ ቤቱ በር ተቆልፎ አገኙ እሽጉም አልተለወጠም ነበር። እሊህ ቅዱሳንም ከሐዋርያት ጋር ወንጌልን እየሰበኩ ኖሩ ብዙ መከራም አገኛቸው። ከዚህም በኋላ በሰላም ዐረፉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
❤ የዮስጦስ ልጅ ሰማዕቱ ቅዱስ አቦሊ፦ ይህም ቅዱስ አቦሊ ከመንግሥት ልጆች ውስጥ ነበር ዐላውያንን ወግቶ በተመለሰ ጊዜ ዲዮቅልጥያኖስን ክብር ይግባውና ክርስቶስን ክዶ አገኘው። ያም አቦሊና አባቱ ዮስጦስ ሌሎችም የመንግሥት ልጆች ሁሉ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስን ሊያጠፉትና መንግሥትን ከእርሱ ሊወስዱ ችሎታ ሲኖራቸው የማታልፍ ሰማያዊት መንግሥትን አሰቡ።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ አቦሊ ወደ ንጉሡ ቀርቦ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም አብዝቶ አባበለው። እንዲሁም አባቱ ዮስጦስንና የከበረች እናቱ ታውክልያን አባበላቸው እነርሱ ግን አልሰሙትም ልባቸው በመድኅን ክርስቶስ ፍቅር ተነድፏልና። ንጉሡም እነርሱን በዚያ ማሠቃየትን ፈራ ስለዚህም ከመልእክት ደብዳቤ ጋር ወደግብጽ ስሙ ኄርሜኔዎስ ወደሚባል የእስክንድርያ ገዥ ላካቸው በመልእክቱም እንዲህ አለው "ዮስጦስና ሚስቱ ታውክልያ ልጃቸው አቦሊም ወደአንተ በሚደርሱ ጊዜ አባብላቸው አለዚያም እየአንዳንዳቸውን ለያያቸው"።
❤ በዚያችም ሌሊት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዮስጦስና ለሚስቱ ታውክልያ ለልጃቸው አቦሊም ተገልጦላቸው አጽናናቸው ከእነርሱም የሚሆነውን ነገራቸው የጸና ቃል ኪዳንም ሰጣቸው።
ወደ መኰንኑ ኄርሜኔዎስም በደረሱ ጊዜ ስለእነርሱ እጅግ አደነቀ እነርሱ መንግሥታቸውን ትተዋልና ክፋ ነገርንም ሊናገራቸው አልደፈረም ከምክራቸው ይመለሱ ዘንድ በለሰለሰ ቃል ሸነገላቸው እንጂ ነገር ግን አልሰሙትም።
❤ ከዚህም በኋላ በእነርሱ ላይ ተቆጥቶ ለእየብቻቸው ለያያቸው ቅዱስ ዮስጦስን ወደ እንዴናው ከተማ ሚስቱን ታውክሊያን ፃ ወደ ሚባል አገር ልጃቸው አቦሊንም ብስጣ ወደ ሚባል አገር ሰደዳቸው ለእያንዳንዳቸውም የሚአገለግላቸው አንዳንድ አገልጋይ ሰጣቸው። ቅዱስ አቦሊም ወደ ሀገር ብስጣ በደረሰ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመኰንኑ ፉት ታመነ። መኰንኑም ጽኑ ሥቃይን በእሳት ቃጠሎና በመንኰራኵር አሰቃየው ሕዋሳቱንም ቆራርጦ ለአንበሶች ጣለው ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስም ከሥቃዩ ሁሉ አድኖ ያለ ጉዳት በጤና አነሣው።
❤ ብዙዎች ሰዎችም ስቃዩንና ዳግመኛ መዳኑን በአዩ ጊዜ እጅግ አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አምነው ሰማዕታት ሆኑ። መኰንኑ ግን እጅግ ተቆጥቶ የቅዱስ አቦሊን ቆዳውን እንዲገፍፉትና ጨውና መጻጻን በማቅ አምጥጠው ቍስሉን እንዲያሹ አዘዘ ይህንንም ሁሉ አደረጉበት።
በኃላ
ለሚነሡ ልጆቻችሁም አስተምሯቸው።
❤ ከዚህም በኃላ የአራዊትን ጠባይ ከእነርሱ ያርቅ ዘንድ እግዚአብሔርን ለመኑት ክብር ይግባውና ጌታችንም ይህን የአራዊት ጠባይ አራቀላቸው። ሰዎች የሚመገቡትንም የሚመገቡ የዋሆች ሆኑ። አባቶቻችን ሐዋርያትም ብዙ ተአምራትን አደረጉ በሽተኞችን ሁሉ ፈወሱ ከዚህም በኃላ እንድርያስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ወደ ግሪክ አገር ተመለሰ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁንእኛንም በአባቶቻችን ሐዋርያት ቅዱስ እንድርያስና በቅዱስ ማትያስ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእርሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን ከአባ መርቆሬዎስና ከአባ ማትያስ ከሁሉም ኤጲስ ቆጶሳት ከክርስቲያን ወገኖችም ሁሉ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ብልጽግናን_ንቆ_የተወ_አባ_ጳውሎስ፡- ይህም ቅዱስ ባለ ጸጋ ነበር። ደግ የሆነች ሚስትና የተባረኩ ልጆችንም ነበሩት፡፡ መነኰስ ሊሆን ወደደ ሚስቱንና ልጆቹንም ጠርቶ "እነሆ ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ ፍቅር እሸጣችሁ ዘንድ ወደድኩ" አላቸው እነርሱም "አሳዳሪያቸን ነህና የወደድከውን አድርግ" አሉት።
❤ ከዚያም በኋላ ገንዘቡን ሁሉ ወስዶ ለድኆችና ለችግረኞች በተነ ሚስቱንም ወደ ደናግል ገዳም ወሰዳት አመ ምኔቱንም ጠራትና እንዲህ አላት "ለገዳምሽ አገልጋይ ትሆን ዘንድ ሚስቴን ልሸጥልሽ አወዳለሁ" እርሷም "እሺ" አለችው የመሸጫዋንም ደብዳቤ ጻፈ የሺያጭዋን ዋጋ ተቀብሎ ለድኆች ሰጠ ልጆቹንም ወደ አበ ምኔቱ ወስዶ እንደ እናታቸው ሸጣቸው ለአበ ምኔቱም አሳልፎ ሰጣቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ ሌላ ቦታ ሔደ ራሱንም ለገዳሙ አለቃ ሸጠ አለቃውንም "ወደ ቤተ ክርስቲያን ልገባ እሻለሁ" አለው፡፡ በገባም ጊዜ በሩን በላዩ ዘጋ። እጆቹን ዘርግቶ ቆመ በታላቅ ድምፅም እንዲህ ብሎ ጮኸ "አቤቱ በፍጹም ልቡናዬ ወዳንተ እንደ መጣሁ፣ አንተ ታውቃለህ" ወደርሱም እንዲህ የሚል ቃል መጣ "ሀሳብህን ሁሉ አወቅሁ በፍጹም ልቤም ተቀበልሁህ"
❤ ከዚህም በኋላ ከመነኵሶ አስጨናቂ የሆኑ የገዳሙን ሥራዎች ሁሉ እንደ ባሪያ እየሠራ ኖረ ራሱንም ከሁሉ እጅግ አዋረደ ነገር ግን ስለ መዋረዱ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አደረገው። ከእርሱም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ ከዚህም በኋላ ሐምሌ 30 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጳውሎስ ጸሎት ይማሰን ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሰማዕታት_ቅዱሳን_መርቆሬዎስና_ኤፍሬም፡- እሊህም ከአክሚም ከተማ የመጡ የሚዋደዱ በመንፈስ ቅዱስ ወንድማማቾች በሥጋም ዘመዳሞች ነበሩ መንፈሳዊ ስምምነትንም ተስማምተው በላይኛው ግብጽ ካሉ ገዳማት በአንዱ ገዳም መነኰሱ፡፡ በጾም በጸሎትና በስግደት በታላቅ እየተጋደሉ በገዳሙ ውስት ሃያ ዓመት ዓመት ያህል ኖሩ፡፡
❤ ከዚህም በኋላ ጠላት ሰይጣን በአብያተ ክርስቲያናት ላይ ከአርዮሳውያን ችግርን በአመጣ ጊዜ አርዮሳውያኑ በአርዮሳዊ ንጉሥ ትእዛዝ መሥዋዕት ሊሠው ወደ ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያን ሊሠዉ ወደ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገቡ፡፡ እኒህ ቅዱሳንም አምላካዊ ቅንአትን ቀንተው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገቡና አርዮሳውያን ያኖሩትን መሥዋዕት በተነኑት። እንዲህም አሏቸው "በሥሉስ ቅዱስ ስም ያልተጠመቀ መሥዋዕትን ያሳርግ ዘንድ አይገባውም"።
❤ ያን ጊዜም አርዮሳውያን ይዘው ደበደቧቸው ታላቅ ግርፋትንም ገረፏቸው ዐጥንቶቻቸውም እስኪሰበሩ ድረስ በምድር ላይ ጥለው ረገጧቸው ነፍሶቻቸውንም በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ሰጡ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ ምእመናንም መጥተው ሥጋቸውን ወሰዱ በአማሩ ልብሶችም ገንዘው በመልካም ቦታ አኖርዋቸው ከእነርሱም ለበሽተኞች ታላቅ ፈውስ ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን መርቆሬዎስ ኤፍሬም ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
❤ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ጳውሎስ በሁሉም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት እንዲሁም በሁላችን በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ ይደር ለዘላለሙ አሜን። በሐምሌ ወር የሚነገበብ ንባብ ደረሰ ተፈጸ። እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 30 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ዕብል_ለቤትከ_ቅዳሴሃ። ድኅረ ፈጸመ በቊስጥንጥንያ ሕንፄሃ። ሱርያል ገሀደ ተአምሪከ አሜሃ። እምዘይት ማኅቶት ዘሥዕልከ ተቀቢዖ ሶቤሃ። ዐይነ ዕውረሰ በቅጽበት በርህ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የሐምሌ_30።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ይቤ ወመጽአ መንፈስ አውሎ። ወተለዓለ ማዕበል። የዐርጉ እስከ ሰማይ"። መዝ 106፥25-26። የሚነበበው ወንጌል ማር 6፥47-53።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "እምውኂዝ እምሰጠት ነፍስነ። እምሰጠት ነፍስነ እማየ ሀከክ። ይትባረክ እግዚአብሔር አምላክነ ዘኢያግብአነ ውስተ መሥገርተ ማዕገቶሙ"። መዝ 123፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 2፥1-9፣ 2ኛ ጴጥ 1፥12-17፣ የሐዋ ሥራ 3፥1-10። የሚነበበው ወንጌል ማር 4፥35-41። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
:
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ሐምሌ ፴ (30) ቀን።
❤ እንኳን #ለሊቀ_መላእክት_ለቅዱስ_ሱርያል (እስራልዩ) ቤተ ክርስቲያኑ ለከበረችበት (ለቅዳሴ ቤቱ) በዐል፣ #ለሐዋርያው_ቅዱስ_እንድርያስ አስገራሚ ተአምር በማድረግ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ማትያስን ከእስር አስፈትቶ ሰውን ከሚበሉ ሰዎች እጅ ላዳነበት፣ ክብርንና ብልጽግናን ንቆ ለተወ ራሱን ስለ ጽድቅ ለሸጠ #ለቅዱስ_ጳውሎስ_ለዕረፍት በዐል፣ ለቅዱሳን ለገሊላ ሰዎች #ለመርቆሬዎስና_ለኤፍሬም ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከእስክድርያው ሊቀ ጳጳሳት #ከአባ_ጢሞቴዎስ ከምስር በአስቄጥስ ወደ አለወደ አባ መቃረስ ገዳም ከሥጋው ፍልሰት፣ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትን በረከት ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚችም ቀን #የእስራልዩ_ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ይኸውም #ቅዱስ_ሱርያል መልአክ ነው። የቅዱስ ሱርያል አማላጅነቱና ረድኤቱ ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚችም ቀን #ሐዋርያው_ቅዱስ_እንድርያስ ተአምራትን አደረገ። እንድርያስ በጽርዕ አገር እያለ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ተገልጦ እንዲህ አለው "ማትያስን ከእሥር ቤት ታወጣው ዘንድ ሰውን ወደሚበሉ ሰዎች አገር ሒድ የዚያች አገር ሰዎች ከሦስት ቀን በኃላ ሊበሉት ያወጡታልና"። እንድርያስም ጌታችንን እንዲህ አለው "የቀረው ሦስት ቀን ከሆነ እንዴት እደርሳለሁ ነገር ግን ፈጥኖ የሚያወጣውን ከመላእክት አንድ ላክ እንጂ"።
❤ ጌታችንም ለእንድርያስ እንዲህ ብሎ መለሰለት "ስማ ሀገሪቱን ወደዚህ ነዪ ከልዃት በውስጧ ከሚኖሩ ሁሉ ጋር ትመጣለች አንተና ደቀ መዘሙሮችህ ግን ጠዋት በሆነ ጊዜ ተነሥታችሁ ወደ ባሕር ሒዱ የተዘጋጀ መርከብንም ታገኛላችሁ እርሱም ያደርስሃል" ይህንንም ብሎ ከእርሱ ዘንድ በክብር ዐረገ። በነጋ ጊዜም እንድርያስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ተነሥቶ ወደ ወደብ ደረሰ ጥሩ መርከብንም አየ ጌታችንንም በሊቀ ሐመር አምሳል አየው ጌታችን እንደሆነ አላወቀም "ሊቀ ሐመር ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን" አለው ጌታም "የእግዚእብሔር ሰላም ይደርብህ" አለው እንድርያስም ደግሞ "በዚህ መርከብ ወዴት ትሔዳለህ" አለው "ሰውን ወደ ሚበሉ ሰዎች አገር እሔዳለሁ" አለው እንድርያስም ሊቀ ሐመሩን "ወንድሜ ሆይ ከአንተ ጋር ትጭነኝ ዘንድ እለምንሃለሁ" አለው ሊቀ ሐመሩም "እሺ" ብሎ ወደ መርከቡ አወጣቸው። በባሕሩ ላይም ሲጎዙ ጌታችን እንድርያስን እንዲህ ብሎ ጠየቀው "ጌታህ ምን ኃይል አደረገ" እንድርያስም ጌታችን ከአደረጋቸው ተአምራቶች ይነግረው ጀመረ ጌታችን እንደሆነ አላወቀም ነበርና።
❤ ከዚህም በኋላ ሊቀ ሐመሩ እነደሚአንቀላፋ ሰው ሆነ ያንጊዜም እንድርያስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ተኛ በዚያን ጊዜም ጌታችን እንድርያስንና ሁለቱን አርድእቱን ይሸክሙአቸው ዘንድ መላእክትን አዘዛቸውና ወስደው በባሕሩ ዳርቻ አኖሩዋቸው። እንድርያስም ከእነቅልፍ በነቃ ጊዜ መረከብን አላገኘም እጅግም አደገቀ ለደቀ መዛሙርቱም እንድህ አላቸው "ልጆቼ ሆይ በመርከብ ውስጥ ከጌታችን ጋር ነበርን ግን አላወቅንም"።
❤ ከዚህም በኋላ እንድርያስ ተነስቶ ጸለየ ክብር ይግባውና ጌታችንም በመልካም ጎልማሳ አምሳል ተገለጸለት እንዲህም አለው "ወዳጄ እንድርያስ አትፍራ እኔ ይህን አድርጌአለሁና አንተ በሦስት ቀን አልደርስም ብለህ ነበር ስለዚህ በፍጥረት ሁሉ ላይ ኃይል እንዳለኝ የሚሳነኝምእንደሌለ ታውቅ ዘንድ እንግዲህም ወደ ከተማው ገብተህ ማትያስን ከእሥር ቤት አውጣው ከእርሱ ጋር ያሉትንም ሁሉ"።
❤ ከዚህም በኋላ እንድርያስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተነሥቶ ወደ ከተማ ገባ ማትያስ ወዳለበትም እስር ቤት ሔደ። በደረሰም ጊዜ የወሀኒ ቤቱ ደጀ ራስዋ ተከፈተች በገባ ጊዜም ማትያስን ተቀምጦ ሲዘምር አገኘው እርስ በርሳቸውም ሰላምታ ተሳጣጡ እንድርያስም ማትያስን "ከሁለት ቀን በኋላ አውጥተው እንደ እንስሳ አርደው ይበሉኛል አልክ አንተ በጌታችን ዘንድ ያየናትን ያቺን ምሥጢር ረሰሃትን በምንናገርበት ጊዜ ሰማይና ምድርን ይናወጣሉ" አለው። ማትያስም "ወንድሜ ሆይ እንሆ ይህን አወቅሁ ነገር ግን በዚች ከተማ ውስጥ ሥራዬን እንድፈጽም የጌታችን ፍቃድ እንደ ሆነ እኔ እናገራለሁ እርሱ ራሱ "እንሆ እኔ እንደ በጎች በተኲላዎች መካከል እንኳችኋለሁ" ብሏልና ወደ ዚህም እሥር ቤት በጨመሩኝ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችንን ጠራሁት እርሱም ሃያ ሰባት ቀን ሲፈጸም ወንድምህ እንድርያስን ወዳንተ እልከዋለሁ እርሱም ከእሥር ቤት ያወጣሃል ከአንተ ጋራ ያሉትን ሁሉ ያወጣችዋል ብሎ ገለጠልኝ እንሆም ደርሰሃል የምትሠራውን አስተውል" አለው።
❤ እንድርያስም ወደ እስረኞች በተመለከተ ጊዜ እንደ እንስሳ ሣር ሲበሉ አይቶ አዘነ አለቀሰም ሰይጣንንም ከሠራዊቱ ጋር አሠረው ከዚህ በኃላ አንድርያስና ማትያስ ተነሥተው ወደ እግዚአብሔር ማለዱ እጆቻቸውንም በእሥረኞች ሁሉ ላይ ጫኑ አእምሮአቸውም ተመለሰ ከከተማው ውጭ ወጥተው በዚያ በአንድነት እንድቀመጡ አዘዙአቸው።
❤ እኒያ ሐዋርያትም የሚሆነውን ያዩ ዘንድ ወጥተው በሀገሩ ጎዳና ዳር ተቀመጡ የከተማው ሰዎችም እነደ ልማዳቸው የሚበሉትን ከእሥረኞቹ ውስጥ ሊአመጡ መጡ የእሥር ቤቱን ደጅ ክፍት ሆኖ አገኙ እሥረኞችም አልነበሩም ደነግጠውም "በእኛ የደረሰብን ምንድነው ወዮልን" አሉ ያን ጊዜም ሰይጣን በሰው መስሎ ሐዋርያት ይህን እንዳደረጉ ነገራቸው የአሉበትንም አመለከታቸው የከተማው ሰዎችም በመቀዳደም ሮጡ እንድርያስንና ማትያስንም ይዘው በከተማው ጥጋጥግ አስጎተቱአቸው በሌሊትም በእሥር ቤት ያሳድሩአቸው ነበር ሦስት ቀናትም እንዲህ አደረጉባቸው ደማቸውም እንደ ውኃ ፈሰሰ።
❤ ከዚህም በኋላ ሰለ ከተማዋ ሰዎች ድኀነት ወደ እግዚአብሔር ጸለዪ ጸሎታቸውንም በፈጸሙ ጊዜ በላዩ ምስል ወደአለበት የዕብነ በረድ ምሶሶ ቀርበው በመስቀልመ ምልክት አመተቡት እንዲህም አሉት "አንተ ምሶሶ ፍራ ከበታችህም እንደ ጥፋት ውኃ ያለ ብዙ ውኃን በዚች ከተማ ላይና በውስጧ የሚኖሩ ሁሉ ላይ አውጣ" ያን ጊዜም ከምሶሶው ሥር ብዙ ውኃ መነጨ የከተማው ሰዎችንም ያሠጥማቸው ዘንድ ገነፈለ ሰዎችም ከከተማው ወጥተው ሊሸሹ ወድደው ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ያዙ ውኃውም በዝቶ ከበባቸው ማምለጥም አልቻላቸውም ውኃውም እስከ እስከ አንገታቸው ደረሰ ያን ጊዜም አለቀሱ እንዲህም አሉ "ወዮልን ይህ ሁሉ በእኛ ላይ የመጣው በእነዚህ በተመረጡ ሰዎች በእግዚአብሔር አገልጋዮች ምክንያት ነው እኛም በአምላካቸው እናምናለን"።
❤ ቅዱስ እንድርያስም "የዕብነ በረደ ምሰሶ እንግዲህስ በቃህ እነሆ የጥፋት ጊዜ አለፈ" ያን ጊዜም ውኃው ተገታ ውኃውም እንደተገታ የከተማው ሰው አይተው ወደ ሐዋርያት ሔዱ ስለዚያች ከተማ ሰዎች ድኅነትም ቁመው እጆቻቸውን ዘርግተው ወደ እግዚአብሔር ሲጸልዩ አገኙአቸው ሐዋርያትን "ይቅር በሉን" ብለው ለመኑአቸው። ሐዋርያትም "በሕያው እግዚአብሔር እመኑ እንጂ አትፍሩ" አሏቸው ሐዋርያትም ሁለተኛ ጸለዩ በውኃ ስጥመት የሞቱትንም ሙታን አስነሡአቸው በዚያም ውኃ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው። ሥጋውንና ደሙንም አቀበሏቸው ቤተ ክርስቲያንንም ሠሩላቸው። ሕግንና ሥርዓትንም ሁሉ አስተምረው በቀናች ሃይማኖት አጸኑአቸው እንዲህም አሏቸው ያዘዝናችሁን ጠብቁ ከእናንተ
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ሐምሌ ፳፱ (29) ቀን።
❤ እንኳን #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ታዴዎስ ከሶርያ አገር ወደ ቁስጥንጥንያ ከተማ #ሥጋው_ለፍልሰት በዐልና #ለሰማዕቱ_ለቅዱስ_ወረስኖፋ_ለዕረፍት በዐል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታች ቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ ለተወለደበት #ከልደቱ_ከበዓለ ወልድ_ከወራዊ መታሰቢያ በዓል ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ በዚችም ቀን ከሶርያ አገር ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ #የቅዱስ_ሐዋርያ_ታዴዎስ_የሥጋ_ፍልሰት ሆነ። ይህ የሆነው ክርስቶስን የሚወድ ጻድቁ ንጉሥ ቊስጠንጢኖስ በነገሠ ጊዜ ነበር። በሱ ትእዛዝም የቅዱስ ሐዋርያ ታዴዎስን ሥጋ አፈለሱ ያማረች ቤተ ክርስቲያን ሥጋውን በውስጡ አኖሩ።
❤ በዚችም ቀን አከበሩዋት ከእርሱም ብዙ የሆኑ ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ። እግዚአብሔር ምስስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው በቅዱስ ታዴዎስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ዋርስኖፋ፦ ይህም ቅድስ አዋቂ ሃይማኖቱ የቀና የዋህና በገድል የተጠመደ ሰው ነበረ። ኤጲስቆጶስነት ሊሾሙት በፈለጉት ጊዜ ከእርሳቸው ሸሸ ወደ አንዲት አገርም ደርሶ እግዚአብሔርን በሚወዱ ሁለት መነኰሳት ዘንድ አደረ። በዚያቺም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለት ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲ ታመን የሰማዕትነትንም አክሊል እንዲቀበል አዘዘው። በነቃም ጊዜ ለእኒህ ለሁለቱ ወንድሞች ያየውን ነገራቸው። እነርሱም ከእርሱ ጋር በሰማዕትነት ይሞቱ ዘንድ ተስማሙ።
❤ ከዚህም በኃላ መኰንኑ ወደ አለበት ሔዱ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ታላቅ ሥቃይንም አሠቃያቸው ከዚያም ሰንዑር ወደሚባል አገር እስከሚሔድ ድረስ በወህኒ ቤት ጨመራቸው።
የሚሔድበትም ሰዓት በደረሰ ጊዜ ከእርሱ ጋራ ወሰዳቸው በዚያም ታላቅ ሥቃይን አሠቃያቸው በሚያሠቃያቸውም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ያጸናቸውና ቁስላቸውን ይፈውስ ነበር።
❤ ከዚህም በኃላ ፃ ወደሚባል አገር ወሰዳቸው። በዚያም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃያቸው ብዙዎች አማንያንንም ሰብስቦ ስለ አምልኮ ጣዖት የሚያዝዝ የከሃዲውን ንጉሥ ደብዳቤ አነበበላቸው። ይህም ቅዱስ ወርስኖፋ ተነሥቶ ያቺን ደብዳቤ ከአንባቢው እጅ ነጥቆ ቀደዳት መኰንኑም አይቶ እጅግ ተቆጣ እሳትንም እንዲያነዱና ቅዱስ ወርስኖፋን በውስጡ እንዲያነዱና ቅዱስ ወርስኖፋን በውስጡ እንዲጨምሩት አዘዘ። ሰማዕትነቱንና ተጋድሎውን በእሳቱ እቶን ውስጥ ፈጸመ።
❤ እነዚህንም ሁለት ወንድሞች ራሶቻቸውን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዝዞ ቆረጧቸው የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ቅዱስ ዋርስኖፋ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 29 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለልደትከ_በአፈ_ነቢያት_ዘተዜነወ። እንበ ያርኁ ፍጹመ ድንግልና እሙ ዕጸወ። እንዘ ይሰድድ ጽልመተ ወእንዘ ያቈርር ሐወ። ናሁ ተረክበ መድኃኒነ ህልወ።ወከመ ዝናም ከዊኖ ፍንወ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ_አርኬ_የሐምሌ 29።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ምስሌከ ቀዳማዊ በዕለ ኃይል። ወብርሃኖሙ ለቅዱሳን። ወለድኩከ እምከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ"። መዝ109፥3።የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 2፥1-8።
✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ወእምኵሉ ያድኅኖሙ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር የዐቅዐብ ኵሎ አዕፅምቲሆሙ። ወኢይትቀጠቀጥ አሐዱ እምውስቴቶሙ"። መዝ 33፥19-20። የሚነበቡት መልዕክታት ገላ 3፥15-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 4፥9-18 እና የሐዋ ሥራ 9፥20-32። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 12፥1-13። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ የዕረፍት በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።
ሃምሳ ሃምሳ ዓመት በጸሎት ኖረው በአጠቃላይ በ500 ዓመታቸው ነው ያረፉት፡፡ ዐፅማቸው መንዝ ከአርባ ሐራ መድኃኔዓለም አጠገብ ፍርኩታ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ውስጥ ይገኛል፡፡
ከአባታች ከእጨጌ አቡነ ዮሐንስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸውም ይማረን። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ።
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ሐምሌ ፳፱ (29) ቀን።
❤ እንኳን #ለታላቁ_አባት በፀሐይ ላይ 50 ዓመት፣ በጨረቃ ላይ 50 ዓመት፣ በደመና ላይ 50 እንዲሁም ዓለምን በክንፋቸው በመዞር በደመና ላይ 50 ለኖሩ ከሰው ተወልደው ከመላእክት ለተደመሩ ጻድቅ #ለእጨጌ_እጨ_አቡነ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ_ለዕረፍት በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #እጨጌ_እጨ_አቡነ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ፦ ጻድቁ አባታችን የተወለዱት በኢየሩሳሌም አውራጃ ልዩ ስሙ ሳሬራ በሚባል ቦታ ነው፡፡ የካቲት 28 ቀን ተፀንሰው ህዳር 29 ተወለዱ፡፡ አባታቸው ድላሶር እናታቸው እምነ ጽዮን ይባላሉ፡፡ ሲወለዱ በወላጆቻቸው ቤት ውስጥ ብርሃን ወርዷል፡፡ ወላጆቻቸውም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ አባታችን ገና በተወለዱ በ5 ዓመታቸው ወላጆቻቸው ወደ እግዚአብሔር ቤት ይዘዋቸው የእመቤታችንን ሥዕል ተመልክተው በደስታ ተመልተው ሳቁ፡፡ አምላክን የወለደች የብርሃን እናቱ እመቤታችንም ከምሥሉ ወጥታ "በምን አውቀኸኝ ነው?" ብላ አቅፋ ሳመችውና "ከእንግዲ ወዲህ የልጄ አገልጋይ ትሆናለህ ኑሮህም እንደ መላእክት ይሆናል በአንተ ምክንያት ብዙ ሰዎች ይድናሉ በምድር ላይም 500 ዓመት ትኖራለህ…" ብላ ባርካው ተሰወረች፡፡
❤ ከዚያችም ቀን ጀምሮ አባ ዩሐንስ ለክርስቶስ ተላልፎ ተሰጠ፡፡ 50 ዓመትም በበረሃ ሲጋደል ኖሮ ከ50 ዓመት በኋላ በደመና ተጭኖ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል መሪነት ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መጡ፡፡ ጻድቁ አባታችን በአቡነ ተክለሃይማኖት ዘመን መጨረሻ የመጡ ሲሆን ምንኵስና ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተቀብለው በዚያው በድብረ ሊባኖስ ገዳም ለ50 ዓመት በጾምና በጸሎት በተጋድሎ ኖዋል፡፡ ከዚኽም በኋላ አባ ዮሐንስ ወደ ተዘጋጀላቸው ምድር በቅዱስ ገብርኤል አሳሳቢነት ወደ ጠገሮ መጡ፡፡ ይኽም ጠገሮ ያለው ገዳማቸው በሰሜን ሸዋ በመንዝና ይፋት ክልል መዘዞ በሚባል ቦታ ሲደርሱ በእግር አንድ ሰዓት ከተጓዙ በኃላ ይገኛል፡፡
❤ ሕዝቡ በተለምዶ እጨ ዮሐንስ እያለ ይጠራቸዋል እንጂ ስማቸው እጨጌ ዮሐንስ ነው፡፡ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ መስቀል ከሰማይ የወረደላቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡ መስቀሉም ሁልጊዜ ተአምር ይሠራል፡፡ በልደታቸው ቀን ኅዳር 29 ቀን መስቀሉ ከመቅደሱ ወጥቶ በካህናቱ ታጅቦ ወደ ጸበሉ ሲወርድ ከየት እንደመጣ ሳይታሰብ ደመና መጥቶ ከመስቀሉ ላይ ብቻ እረቦና እንደ ጃንጥላ ተዘርግቶ አብሮ ወደ ጸበሉ ይወርዳል፡፡ እዛው ቆይቶ መስቀሉ ሲመለስም አብሮ አጅቦ ይመለስና መስቀሉ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሲገባ ደመናው ወዴት እንደተበተነ ሳይታወቅ ይጠፋል፡፡ ይህ በዘመናችንም ጭምር እየታየ ያለ ታላቅ ተአምር ነው፡፡
❤ አባታችን በታላቀ ተጋድሎ ሣሉ ሰይጣን የሀገሩን ሰዎች በጠላትነት እንዲነሡባቸው አደረገ፡፡ ሰዎቹም አባታችንን እንዴት እንደሚያጠፏቸው ይማከሩ ጀመር፡፡ ሊገድሏቸው ፈልገው ቅድስናቸው በሁሉ ዘንድ የታወቀ ነውና ፈሩ፡፡ ከዚህም በኋላ "ለምን ከመንደራችን ከወንድ ያረገዘች ሴት ፈልገን እሳቸው አስረገዟት ብለን በሐሰት እንከሳቸው?" ብለው ተማከሩ፡፡ ብዙ ወርቅና ብርም ለአንዲት ሴት ሰጥተው በሐሰት ከእርሱ አርግዣለሁ ብላ እንድትመሰክር አደረጓት፡፡ አባታችንም በሕዝብ ፊት በሐሰት ተከሰሱ፡፡ ጻድቁም "አንቺ ሴት ከእኔ ነው ያረገሽው?" አሏት እርሷም "አዎ ከአንተ ነው ልትክድ ነው እንዴ?" አለቻቸው፡፡ አባታችንም በዚህ አዝነው "በአንቺና በእኔ መካከል እግዚአብሔር ይፍረድ" ሲሉ ያች ሴት ወዲያው ለሁለት ተሰንጥቃ ሞተች፡፡ የአገሩ ሰዎችም እጅግ ፈሩ፡፡ አባታችንም ምድሪቱን እረገሟት፡፡ "የተዘራው ዘር አይብቀልብሽ፣ የተተከለው አይፅደቅ፣ ብርድና ውርጭ ይፈራረቅብሽ" ብለው እረግመዋት በደመና ተጭነው ወደ ሰሜን ጎንደር እስቴ ጉንደ ተክለተሃማኖት ሔዱ፡፡
❤ አቡነ ዮሐንስ በመላው ኢትዮጵያ ወንጌልን እየተዘዋወሩ ያስተማሩ ሲሆን ከቅድስናቸው የተነሣ በፀሐይ ላይ 50 ዓመት፣ በጨረቃ ላይ 50 ዓመት፣ በደመና ላይ 50 እንዲሁም ዓለምን በክንፋቸው በመዞር በደመና ላይ 50 የኖሩ ከሰው ተወልደው ከመላእክት የተደመሩ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ በይፋት ጠግሮ በዓለወልድ፣ በአፋር አዘሎ፣ በመንዝ ፍርኩታ ኪዳነምሕረት፣ በደብረ ሊባኖስ፣ በጎንድ ተክለ ሃይማኖት በሌሎችም ቦታዎች በመዘዋወር በታላቅ ተጋድሎ ኖረዋል፡፡
❤ አባታችን ከሰማይ መስቀል የወረደላቸው ሲሆን ዛሬም በገዳማቸው የሔደ ሰው በወረደው በእጃቸው መስቀል እየተዳበሰ ቆመው በጸለዩበት ባሕር በጠበላቸው ይጠመቃል፡፡ በተጨማሪም ይይዙት በነበረውም መቋሚያቸው በመዳበስ በረከትን ማግኘት ይቻላል፡፡ ቆመው ከጸለዩበት ባሕር ውስጥ ደረቅ አሸዋ ይወጣል፡፡ አባ ዮሐንስ 500 ዓመት ከኖሩ በኋላ ዕረፍተ ዘመናቸው ሲደርስ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከ15 ነቢያት፣ ከ12 ሐዋርያት፣ ሄሮድስ ያስፈጃቸው ከመቶ አርባ አራት ሺ ሕፃናት፣ ከአብርሃም ከይስሐቅ፣ ከዕቆብ ጋር ሁሉንም ነገደ መላእክትን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን ሁሉ አስከትሎ መጥቶ ታላቅ ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ "ስምህን የጠራ ገዳምህን የረገጠ፣ መባ የሰጠ፣ ቤተ ክርስትያንህን የሠራ ያሠራ የረዳ፣ ገድልህን የሰማ ያሰማ ያስተረጎመ፣ መታሰቢያን ያደረገ እስከ 10 ትውልድ እምርልሀለው፤ ንስሀ ሳይገባ አይሞትም፣ ልጅ መውለድ ባይችል እኔ ልጅ እሰጠዋለሁ፤ ገድልህን በቤትህ ያስቀመጠ እርኩስ መንፈስ፣ ክፉ አጋንንት ቸነፈር ወባ መልአከ ጽልመት አይነካውም፡፡ በገዳምህ መነኵሴ ቢቀበር በሰማይ ክንፍ አበቅልለታለሁ፤ አይሁድም አረማዊም ያላመነ ያልተጠመቀ በገዳምህ መጥቶ ቢያርፍ ይቅር እልልሃለሁ፣ እንደ መቃብሬ ጉልጎታ እንደተቀበረ አድርጌ እቆጥርልሃለሁ…" የሚል ቃል ኪዳን ከሰጣቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡
❤ ቅዱስ አባታችንም በ 500 ዓመታቸው ሐምሌ 29 ቀን ዐርፈው በጎንድ ተክለ ሃይማኖት ተቀብረዋል፡፡ በሰሜን ጎንደር የሚገኘውን ይህንን ገዳም ጻድቁ ራሳቸው ናቸው የመሠረቱት፡፡ ነገር ግን የገዳሙን ስያሜ በአባታቸው በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ስም አድርገውታል፡፡ አቡነ ዮሐንስ ካረፉ በኋላ በእርግማናቸው መሠረት በመንዝና በይፋት ብርዱ ድርቁ ስለበዛባቸው አንድ ብቁ ባሕታዊ ከበዓታቸው ወጥተው "በሐሜታችሁ ምክንያት እጨ ዮሐንስ ስለረገማችሁ ነው የእርሱን ዐፅም ካላመጣችሁ ብርዱ ውርጩ ድርቁም አይጠፋላችሁም" አሏቸው፡፡ ሕዝቡም አባታችን በጉንድ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከተቀበሩ ከ 134 ዓመት በኋላ በቅዱሳን እየተመሩ ሄደው በሌሊት ግማሽ ዐፅማቸውን አምጥተው በሀገራቸው አምጥተው ስላስቀመጡ ብርዱና ውርጩ በመንዝ እየቀነሰላቸው መጥቷል፡፡
❤ ዛሬም በሀገሩ ብርዱና ውርጭ ሲበዛ የጻድቁን ታቦት ሲያወጡ ውርጩ ይጠፋል፡፡ ጠገሮ በሚባለው ገዳማቸው ውስጥ የሚገኘው ጠበላቸው እጅግ አስደናቂ ነው፡፡ ግማሽ ዐፅማቸውን ከጉንደ ተክለሃይማኖት አምጥተው አርባ ሐራ መድኃኔዓለም አጠገብ በላይ በፍሩክታ ኪዳነምሕረት መጋቢት 18 ፍልሰተ ዐፅማቸው ተከናወነ፡፡ ምድሪቷም ተባረከች፣ የዘሩትንም አበቀለች፣ ውርጩም ብርዱም ቀነሰ፣ ዝናብ አልዘንብ ሲል ወይም ሰብል የሚጨርስ አንበጣ ሲመጣ ታቦታቸው ወጥቶ ምህላ ይያዛል ወድያውም መቅሰፍት ይርቃል፣ ዝናብም ይዘንባል፡፡ ጻድቁ ደመናን፣ ጨረቃንና ፀሐይን በእጃቸው እየያዙ ይጸልዩ ነበር፡፡ በጠገሮ፣ በአዘሎ፣ በፍርኩታና በሌሎቹም ታላላቅ ቦታቦዎች ላይ በእያንዳንዱ ገዳም
