ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
Open in Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
Show more603
Subscribers
-324 hours
-87 days
-1730 days
Posts Archive
✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #የተባረከ_የታኅሣሥ_ወር_የቀኑ_ሰዓት_ዘጠኝ ሲሆን ከእንግዲህም ይጨምራል።
✝ #ታኅሣሥ ፩ (1) ቀን
✝ እንኳን #ለርእሰ_ባሕታዊ_ለታላቁ_ነቢይ ለቴስብያዊ #ለቅዱስ_ኤልያስ በእስራኤል ፊት ለተገለጠበት ለልደቱ ዓመታዊ በዓል፣ ለእስራኤላዊ #ለቅዱስ_ናቡቴ ለዕረፍት በዓል፣ ለጋዛ አገር ኤጲስቆጶስ ለቅዱስ አባት #ለአባ_ጴጥሮስ_ለዕረፍት_በዓል፣ ለእስክንድርያ አገር ሠላሳኛ ሊቀ ጳጳሳት ለቅዱስ አባት #ለአባ_ዮሐንስና ሰባ ስድስተኛ ሊቀ ጳጳሳት #ለአባ_አትናቴዎስ_ለዕረፍታቸው_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ጴጥሮስ_ከያዕቆብ_ከመነኰስ_ኤልያስ #ከንጉሥ_ሰሎሞን_እናት_ከቤርሳቤህ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
ዜና እረፍት
የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በኩረ ትጉኃን ዘርዓዳዊት ኃይሉ ባልታወቁ ኃይሎች በደረሰባቸው ጥቃት አረፉ !
ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም
+++
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በኩረ ትጉኃን ዘርዓ ዳዊት ኃይሉ ባልታወቁ ኃይሎች በደረሰባቸው ጥቃት አረፉ !
ዝርዝር መረጃው እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ኅዳር ፴ (30) ቀን።
✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ለጻድቁ_ንጉሥ_ለዐፄ_ገብረ መስቀል_ለዕረፍት_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
✝ #ጻድቁ_ንጉሥ_ዐፄ_ገብረ_መስቀል፦ ይኸውም ንጉሥ ታላቁ ጻድቅ አቡነ አረጋዊ ከሰማይ በወረደላቸው ኅብስት ቀድሰው ያቆረቡትና መንግሥቱን የባረኩለት ነው። ዐፄ ካሌብ የናግራንን ሰማዕታት ደም ተበቅሎ በድል ከተመለሰ በኋላ ከአቡነ ጰንጠሎዎን እጅ መንኰሶ ገዳም ከገባ በኋላ ልጁ ገብረ መስቀል ነገሠ። ዐፄ ገብረ መስቀል በእውነትና በቅንነት ከነገሠ በኋላ አመራሩ ከአህጉሪቷ ጽንፍ እስከ ጽንፍ ደረሰ። በዘመኑም ሁሉ መንግሥቱን የሚቃወም አልተነሣም፤ እርሱም ቤተክርስቲያንን ከመሥራት በቀር ወደ ጦርነት የሄደበት ጊዜ የለም።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
በሲነርጂ ሀበሻ ፊልምና ኮሚኒኬሽን በመዘጋጀት ላይ የሚገኘው የሰማዕቱ ሊቀ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ፊልም ጽሑፍ በሊቃውንት ጉባኤ እንዲመረመር ታዘዘ።
***
ኅዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም
"""""""""""""""""""""""""
አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ
==============
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሲነርጂ ፊልምና ኮሚኒኬሽን በኢትዮጵያዊው ሰማዕት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሊቀ ጳጳስ የስማዕትነት ተጋድሎ ዙሪያ የሚያጠነጥን ፊልም ለመስራት የሚያደርገው እንቅስቃሴ
ታሪክን የሚያጎድፍ ሆኖ ስለተገኘ ሊቆም እንደሚገባ በመግለጽ ኅዳር 25 ቀን 2016ዓ.ም በቁጥር 1673/2789/2016 በተጻፈ ደብዳቤ መግለጹ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎ የፊልሙ ጸሐፊ እና ዳይሬክተር ሞገስ ታፈሰ ዶ/ር እየተዘጋጀ የሚገኘውን ፊልም ቤተክርስቲያናችን በሊቃውንቶቿ አማካኝነት መርምራ፣ የሚታረም ካለ አርማና የሚቃናውን አቅንታ በምትሰጠን አስተያየትና ማስተካከያ መሠረት ፊልሙን የምንሠራ መሆኑ ታውቆ አስፈላጊው ትብብር ሁሉ ይደረግልን። በማለት በጽሑፍና በአካል ጠቅላይ ቤተ ክህነት በመገኘት በፊልሙ ዝግጅት ዙሪያ ማብራሪያ በመስጠት ለተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ይቅርታ ጠይቀዋል።
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስም ዶ/ርሞገስ ታፈሰ ያቀረቡትን ይቅርታ በመቀበል በአካልና በጽሑፍ በፊልሙ ጽሑፍ ዝግጅት ዙሪያ መረጃ ከመስጠት ባለፈ በቤተ ክርስቲያናችን በኩል የፊልሙ ጽሑፍ እንዲመረመርላቸውና እርማት በሚያስፈልገው ጉዳይ ዙሪያ እርማት እንዲደረግበት መጠየቃቸው የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ ኅዳር ፳፱ (29) ቀን።
✝ እንኳን #ለኢትዮጵያኑ_ጻድቃን በጸሎታቸው የተከዜን ባሕር ለሁለት ለከፈሉ #ለአቡነ_ገብረ_መስቀል_ዘለጋሶ ለመታሰቢያቸው በዓል፣ የአየር አጋንንት ከእናቱ ጋራ ተገናግቶ የተወለደው መጥቆራ ተብሎ ይጠራ የነበረው #አቡነ_ተክለሃይማኖትና_አቡነ_ዜና_ማርቆስም_በጸሎታቸው ወደ እግዚአብሔር ለምነው በመስቀሉ ኃይል ድል ካደረጉት በኋላ ወደ ሰው አርአያነት እንዲለወጥ አድገውት ሥሙን ለውጠው አመንኵሰው ለታላቅ የቅድስና ደረጃ ለአበቁቱ #ለአቡነ_ፄዋለ_ጽጽቅ ለዕረፍት በዓል፣ ለታላቁ አባት በፀሐይ ላይ 50 ዓመት፣ በጨረቃ ላይ 50 ዓመት፣ በደመና ላይ 50 እንዲሁም ዓለምን በክንፋቸው በመዞር በደመና ላይ 50 ለኖሩ ከሰው ተወልደው ከመላእክት ለተደመሩ ጻድቅ #ለእጨጌ (እጨ) #ለአቡነ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ ለልደታቸው በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BI
tiktok
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ኅዳር ፳፰ (28) ቀን።
✝ እንኳን #ከዘጠኙ_ቅዱሳን ለአንዱ ለሆኑት በጸሎት ጊዜ የእጆቻቸው ጣቶች እንደ መብራት ያበራ ለነበሩት በአክሱም ከተማ አካባቢ የሚገኘውን ደብረ ቊንጽል ገዳም ለመሰረቱት #ለአባ_ሊቃኖስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
✝ "#ሰላም_ለአባ_ሊቃኖስ ዘኮነ ማኅደሮ ለመንፈስ ቅዱስ"። ትርጉም፦ ለመንፈስ ቅዱስ ማደሪያው ለኾነ #ለአባ_ሊቃኖስ_ሰላምታ_ይገባል። #ሊቀ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ_በተአምኆ_ቅዱሳን_ላይ።
✝ ✝ ✝
✝ #አባ_ሊቃኖስ፦ ቊጥራቸው ከዘጠኙ ቅዱሳን ሲኾን የመጡት ከቊስጥንጥንያ (ሮም) አገር ሲኾን በአክሱም ከተማ አካባቢ ደብረ ቊናጽል የሚል ገዳምን ገድመዋል፤ በዓለ ዕረፍታቸውም ኅዳር 28 ቀን ነው፤ በጸሎት እጃቸውን በዘረጉ ጊዜ ዐሥሩ ጣቶቻቸው እንደ መብራት ይበራ እንደነበር ዜና ገድላቸው ያስረዳል።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ኅዳር ፳፯ (27) ቀን።
✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ስለ ጌታችን ሥጋና ደም ክብር ሲሉ ቅዱስ ቊርባን የተቀበለ ሰው ያስታወከው የጠጡ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ተክለ_ሐዋርያት_ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
✝ #አቡነ_ተክለ_ሐዋርያት፦ አባታቸው የእናርዕት አገረ ገዥ የነበሩት እድርያስ ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ እሌኒ ይባላሉ። የትውልድ አገራቸው ሸዋ ሲሆን በዚሁ የምትገኘውን ታላቋን ደብረ ጽሙናን ገዳም የመሠረቱ ሲሆን በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን የነበሩ ታላቅ አባት ናቸው። ገና በእናታቸው ማኅፀን ሳሉ አጋንንትን እያቃጠሉ ያጠፏቸው ነበር። የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ተምረው ከጨረሱ በኋላ ገና በድቁና እያገለገሉ ሳለ 40 ቀን በማክፈል ይጾሙና ይጸልዩ ነበር። አባታችን የመነኰሱትና ብዙ ተጋድሏቸውን ፈጽመው ወደ ሰማይ ተነጥቀው ሥላሴን እስከማየት የደረሱት በደብረ ሊባኖስ ነው። ያመነኰሷቸውም ሁሉን በስውር ያለውን የሚያውቁት አቡነ ዮሐንስ ከማ ናቸው።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ህዳር 24 ቀን 2016 ዓ/ም ባወጣችው መግለጫ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ፣ መነሃም በመባል በሚታወቀው ቀበሌ “ቶኩማ መነሃም” በተሰኘው የመካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናን ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ/ም ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት ላይ በቤተ ክርስቲን በጸሎት ላይ ከነበሩት 17 ሰዎች መካከል ማንነታቸው ተጣርቶ ባልታወቁ ታጣቂዎች 9 የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት ላይ የጅምላ ግድያ እንደተፈጸመ ከቤተ ክርስቲኒቱ የወጣው መግለጫ ይገልፃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ባለፈው ዓመት በተለያዩ ቦታዎች ላይ የቤተ ክርስቲኒቱ አማኞች ላይ ግድያ መፈጸሙን መግለጫው ያትታል፡፡
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ይህ አይነቱ የወንጀል ድርጊት በእጅጉ እያወገዘ የሚመለከተው የመንግስት አካልም የዜጎችንና የሃይማኖት ተቋማትን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅና የማስጠበቅ ሕገ መንግስታዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጉባኤው በአጽንኦት ያሳስባል፡፡ በንጹሐን ላይ የግድያ ወንጀል የፈጸሙትንም ወንጀለኞች በአፋጣኝ በሕግ ተጠያቂ እንዲያደርግና ፍትህን አንዲያስከብር ይጠይቃል፡፡
ከዚህም ባለፈ በሀገራችን የሚታየው ማንኛውንም ዓይነት ሕገ ወጥ ድርጊት እንዲታረም፣ የዜጎች ሕገ መንግስታዊ መብት ሳይሸራረፍ የመጠበቅ መንግስታዊ ሃላፊነተን ሕግንና መመሪን መሠረት በማድረግ ሊሠራ ይገባል፡፡
ጉባኤያችን በንፁሀን ላይ ስለተፈጸመው ጥቃትና ግድያ በድጋሚ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጆች ዘመዶች እንዲሁም ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና ለኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢያሱስ አባቶችና መሪዎች ልባዊ መጽናናትን እንመኛለን፡፡
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ!
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸመውን ግድያ አወገዘ
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ንጹሐን አማኞች ላይ የተፈጸመውን ግድያ በእጅጉ ያወግዛል
“በንጹሐን ላይ የሚፈጸም ግድያ፣ ኢሰብአዊ ድርጊትና አያያዝ በሁሉም ሃይማኖቶች የሚወገዝ ወንጀል ነው”
ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ንፁሐን አማኞች ላይ ግድያ መፈጸሙን የሚገልጽ ከሁለቱ አባል ቤተ እምነቶች ካወጡት መግለጫ ተገንዝበናል፡፡ ድርጊቱ በእጅጉ የሚያሳዝን ከመሆኑም በላይ በሃይማኖት አገልግሎት ላይ የነበሩ ንፁሐን አማኞችን መግደል ደረቅ የወንጀል ተግባር በመሆኑ በእጅጉ የሚወገዝ ድርጊት ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን “በአርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች ላይ በኦርቶዶክሳዊያን ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በእጅጉ እናወግዛለን፣ የፀጥታ ተቋማትም ጥቃቱን እንዲከላከሉ እንጠይቃለን፡፡” የሚል መግለጫ በቤተ ክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የፌስቡክ ገጽ ያወጣች ሲሆን በአርሲ ዞን በሹርካ ወረዳ ሶቤ ሚካኤል፣ በዲገሎ ማርያም፣ በሮቤ አንዲቶ ደብረ ምጥማቅ ማርያም አብያተ ክርስቲያናት ላይ በተለያዩ ጊዜያት 36 ኦርቶዶክሳውያን በደረሰባቸው ጥቃት ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ከሀገረ ስብከቱ የደረሰውን መረጃ ዋቢ በማድረግ መምሪያው ገልጿል፡፡ በተጨማሪም የአማኖች ቤትም ስለመቃጠሉ ዘገባው ይጠቁማል፡፡
✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ኅዳር ፳፮ (26) ቀን።
✝ እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን ታላቁን ገዳም ሐይቅ እስጢፍኖስ ላቀኑት #ለአቡነ_ኢየሱስ_ሞዐና ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ሀብተ_ማርያም_ለዕረፍታቸው በዓል፣ #ለኢትዮጵያ_የመጀመርያው_ሊቀ_ጳጳስ ለነበሩት #ለአቡነ_ሰላማ_ከሣቴ_ብርሃን_ለልደት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✨ጻድቁ አቡነ ሃብተ ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ:: ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን?" እያሉ ይሰግዱ ነበር::
✨የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል:: ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ:: ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:: የፈጣሪውን ስም ያቃለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል::
✨ከዚያ ግን ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው: መጻሕፍትንም አጥንተው መንነዋል:: በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኮሱ በሁዋላ የሠሩትን ትሩፋትና የነበራቸውን ተጋድሎ ግን የኔ ብጤ ደካማ ሰው ሊዘረዝረው አይችልም::
✨ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ::በየቀኑ 4ቱን ወንጌልና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ:: (መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ታላቅ ጸሎት ነው)በ40 ቀናት: ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ::
ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው::
✨በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ:: (ካህን ናቸውና)ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ: ክቡር ደሙን ይጠጣሉ::በፍጹም በልባቸው ውስጥ ቂምን: መከፋትን አላሳደሩም::
✨በእነዚህና በሌሎች ትሩፋቶቻቸው ደስ የተሰኘ ጌታም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ኢየሩሳሌም ይሔዱ ነበር:: ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በሁዋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ አላቸው::
✨ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ: *ስለ ምናኔሕ: ስለ ተባረከ ምንኩስናህ: ስለ ንጹሕ ድንግልናህ: ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ: ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ: ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ::"
✨"በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን: 500 የእንቁ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ: በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ! በርእስየ!' ብዬሃለሁ" አላቸው::
✨ቅዱሳን መላእክትም "ሃብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸው ይህንን የተመለከቱ የናግራን ክርስቲያኖች ግን ስለ መፍራት ፈንታ በፈቃዳቸው እየተሯሯጡ ወደ እሳትና ሰይፍ ተሽቀዳደሙ::
✨ከተማዋም እየነደደችና ደም እየፈሰሰባት ለ40 ቀናት ቆየች:: ይሕንን የሰማው ቅዱሱ አፄ ካሌብም ደርሶ የተረፉትን ሲታደግ ፊንሐስን ከነ ወታደሮቹ አጥፍቶታል::
አምላከ አበው ወሰማዕት ጣዕመ ፍቅራቸውን: ክብራቸውን: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን::
💥💥💥አሜን አሜን አሜን 💥💥💥
✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊
🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨✨🕊✨🕊✨🕊እንኳን ለፃዲቁ አባታችን አቡነ ሀብተማርያም በዓለ እረፍ በሰላም አደረሳችሁ (ህዳር 26)
✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊🕊✨🕊✨🕊✨✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨✨
🍋🍋 ኑ አብረን እናክብር 🍋🍋🍋
✨ኢትዮጵያዊው_ፃዲቅ_አቡነ_ሀብተማርያም
እኒህ ጻድቅ የሃገራችን ኮከበ ገዳም ናቸው:: "ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" እንዲሉ አበው:: ባሕር ከሆነ ጣዕመ ሕይወታቸው ጥቂቱን ለበረከት እንካፈል::
ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ (የራውዕይ) ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ: እናታቸውት ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች:: በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ: ምጽዋትን ወዳጅ: ቡርክት ሴት ነበረች:: እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር::
✨ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት "ከማሕጸንሽ ደግ የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ" ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች:: ጻድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች::
✝️ በንጉሡ በዑልያኖስ ዘመን ክርስቲያኖች መከራና ስቃይ በበዛባቸው ጊዜ ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስና ጎርጎርዮስ በቅዱስ መርቆሬዎስ #ሥዕል ፊት ሲጸልዩ ሳለ
" #አድነነ_ሥዕል_ከመ_ዘይብል_ኦሆ "
/ #ስዕሉም_እንደሚታዘዝ_ዘንበል_አለ።/
በስእሉ ላይ ቅዱስ መርቆሬዎስ ከሀዲውን ንጉስ ዑልያኖስን ሲገድለው ከጦሩም ጫፍ ትኩስ ደም ሲንጠባጠብ ታየ።
ባስልዮስና ጎርጎርዮስም ከክርስቲያን ወገኖቻቸው ጋር እጅግ ተደሰቱ ። ቅዱስ መርቆሬዎስ ከሐዲውን ንጉሥ ዑልያኖስን ስላጠፋላቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ ።
🙏 የቅዱስ መርቆሬዎስ ረድኤት በረከት አይለየን ከመከራ ከመከራ ነፍስ ይጠብቀን 🙏
🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊🕊📣🕊🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣
🕊📣🕊📣🕊📣🕊🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊🕊📣📣🕊📣🕊🕊📣
እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ_መርቆሬዎስ በዓለ ዕረፍቱ በሰላም አደረሳችሁ!!!
✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊🕊✨🕊🕊✨🕊🕊✨🕊🕊✨🕊✨🕊
✝️ ቅዱስ መርቆሬዎስ የነበረበት ዘመን በሶስተኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ንጉስ ዳክዮስ የሮም ገዥ ሆኖ የነገሰበት ዘመን እንደመሆኑ በዘመኑ የተከበረ የተባለ የውትድርናን ትምህርት ተምሮ ለንጉሱ አገልጋይ ሁኖ ነበር ።
✝️ አባቱ በአደን ላይ ሳለ ሊበሉት ከመጡ ገጸ ከለባት እግዚአብሔር ስላዳነውና እንዲያውም አገልጋዮች ስላደረጋቸው በዚህ ተአምር መነሻነት ቤተሰቡ ሁሉ በክርስትና ሐይማኖት አምነው ተጠምቀዋል ።
ከጥምቀት በኋላ
አባቱ ✝️ ኖኅ
እናቱ ✝️ ታቦት
ተብለው ተሰይመዋል
✝️ቅዱሱም ፕሉፓዴር ከሚባል ከቅድሞ ስሙ መርቆሬዎስ ተብሏል። ትርጓሜውም የአምላክ አገልጋይ ማለት ነው።
ባርባርያን በሮም ላይ በጠላትነት በተነሱ ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ የጦር አዛዥ ነበርና የእግዚአብሔር መልአክ በሰጠው ሰይፍ በመዋጋት ድልን ተቀዳጅቷል። የባርባርያንን ንጉሥም ገድሎታል።
ንጉስ ዳኬዎስ ግን " ድልን የሰጡን ጣዖታቴ ናቸው። " በማለት ለጣዖታቱ በዓል አደረገ ። ቅዱስ መርቆሬዎስ ይህንን ድርጊት በአደባባይ ተቃወመ በንጉሱም ፊት ትጥቁንና ልብሱን ማዕረጉንም አውልቆ ወረወረው።
በዚህ የተቆጣው ንጉሡም በወታደሮች አስይዞ መከራን ያደርሱበት ዘንድ ወደ ቂሳሪያ ( ቀጰዶቅያ ) ላከው ።በዚያም የሰማዕትነት ስቃይን ከተቀበለ በኋላ ፦
✝️ በኅዳር 25 ቀን አንገቱን ተሰይፎ የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ ።
✝️ ቅዱስ መርቆሬዎስ ከዕረፍቱ በኋላ ጸሊም (ጥቁር) የሆነ ፈረሱ ለሰባት ዓመታት በየሀገሩ እየዞረ ስለ ክርስቶስ መስክሯል።
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ኅዳር ፳፭ (25) ቀን።
✝ እንኳን #ለታላቁ_ሰማዕት_ለቅዱስ_መርቆሬዎስ (ፒሉፓዴር) በንጉሥ ዳኬዎስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእስላሞች ወገን ከነበረ #ቅዱስ_መርቆሬዎስ ተአምር አድርጎ ከመለሰው #ከቅዱስ_ዮሐንስ_ከአቃርዎስና #ከሮማኖስ ከመታሰቢያቸወ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ #የዕለቱ_አንገርጋሪ_ግእዝ_ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ፈጸመ ስምዓ #ቅዱስ_መርቆሬዎስ፤ በመዋዕሊሁ ለዳኬዎስ ንጉሥ፤ ወኮነ መድኃኒተ ለኲሉ ዘነፍስ፤ #ወተፈሥሑ_ባስልዮስ_ወጎርጎሬዎስ"። ትርጉም፦ #ቅዱስ_መርቆሬዎስ በንጉሥ ዳኬዎስ በዘመኑ ምስክርነቱን ፈጸመ፤ በዚህም ለነፍሳት ሁሉ መድኃኒት ሆናቸው፤ #ባስልዮስና_ጎርጎርዮስ_ተደሰቱ። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።
✝ #ቅዱስ_መርቆሬዎስ፦ መርቆሬዎስ ማለት የአብ ወዳጅ ማለት ነው። በሁለተኛ ትርጓሜ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
በአርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን
ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በማስመልከት ከኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ
ጽሕፈት ቤት የተሰጠ መግለጫ።
++++++++++++++++++++++++++++++++++++
"ወዳጆች ሆይ፥ በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፤ ነገር ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሐሤት እያደረጋችሁ ደስ እንዲላችሁ፥ በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁ።
" 1ኛ ጴጥርስ 4፥12:13
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ::
በአርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በጥብቅ እናወግዛለን፤የጸጥታ ተቋማትም ጥቃቱን እንዲከላለሉ እንጠይቃለን።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአርሲ ዞን በሹርካ ወረዳ ሶሌ ሚካኤል፣በዲገሎ ማርያም፣በሮቤ እንደቶ ደብረ ምጥማቅ ማርያም አብያተክርስቲያናት ላይ በተለያዩ ጊዜያት 36 ኦርቶዶክሳዊያን በደረሰባቸው ጥቃት ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ሀገረ ስብከቱ ባደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል።
በዚሁ ጥቃት በሶሌ ዲገሉ እና ጢጆ ለቡ በተባሉ ቀበሌዎች 28 ኦርቶዶክሳዊያን ከየቤታቸው ተለቅመው የተገደሉ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም 7ቱ ሴቶችና 21ዱ ወንዶች መሆናቸው ታውቋል።በዚህ ጥቃትም እድሜያቸው ከሰባ ዓመት አዛውንት እስከ ሃያ ስምንት ቀን ጨቅላ ሕጻናት ይገኙበታል። በዛሬው ዕለት ደግሞ በዲገሉ ማርያም ቤተክርስቲያን 5 ኦርቶዶክሳዊያን ከመገደላቸው በተጨማሪ የሦስት ኦርቶዶክሳውያን ቤት ደግሞ ተቃጥሏል።
ከዚህ ቀደም በሮቤ አንዲቶ ደብረ ምጥማቅ ማርያም ቤተክርስቲያን በዓለ ማርያምን አክብረው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ የነበሩ ሦስት ኦርቶዶክሳዊያን ጨለማን ተገን ባደረጉ ነፍሰ ገዳዮች መገደላቸው ይታወሳል።
የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ከመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር በተደጋጋሚና ሆን ተብሎ በሚፈጸመው የኦርቶዶክሳዊያን ጥቃት ዙሪያ በጋራ እየሠሩ የሚገኙ ሲሆን በዚህ ዐይነት የጥቃት ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ አንዳንድ አካላት ላይ በመንግሥት በኩል የማያዳግም ርምጃ እንደተወሰደባቸው ሀገረ ስብከቱ በላከው ሪፖርት አረጋግጠዋል።
ይህ ዐይነት ሃይማኖት ተኮር ጥቃት በምእመናን ላይ መድረሱ አግባብነት የሌለውና እምነትን በነጻነት የማራመድ መንግስታዊ መብትን የሚጥስ በመሆኑ መሰል ሕገ ወጥ ጥቃትን ለመከላከልና ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት መብቶቻቸውን ተቋማዊ በሆነ መንገድ ማስከበር እንዲችሉ ያቋቋሙት የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ድርጊቱን በማውገዝ ችግሩ ከመሠረቱ እንዲፈታ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር መፍትሔ መፈለግ ሲገባው በዝምታ በማለፉ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ቅሬታ ተሰምቷታል።
ይህ ዐይነቱ ኦርቶዶክሳዊያን ላይ ያነጣጠረ ግድያ እንዲቆምና የወንጀሉ ፈጻሚዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ በሀገረ ስብከቱ በኩል እየተደረገ ያለው ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤትም በድርጊቱ እጅጉን ማዘኑን እየገለጸ ጉዳዩን ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመሆን የሚከታተለው መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።
በሌሎች ስፍራዎች የሚያጋጥሙ ተመሳሳይ ጥቃቶችን በእንጭጩ ለመቅጨትና ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመነጋገር መፍትሔ ማበጀት ይቻል ዘንድ አህጉረ ስብከት ችግሮች በሚያጋጥሙ ወቅት ሪፖርት እንዲልኩ ቀደም ሲል በደብዳቤ በተላከላቸው የስልክና ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴዎች አማካኝነት በፍጥነት በማሳወቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እያሳሰብንና ለሞቱት ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ሁሉ ልዑል እግዚአብሔር መንግሥተ ሰማያትን እንዲያወርስልን በመጸለይ የፌዴራልም ሆነ የክልል መንግሥታት የሚደርሱ ሃይማኖት ተኮር ጥቃቶች እንዲቆሙና መሰል ጥቃት እንዳይፈጸም ለኦርቶዶክሳዊያን ወገኖቻችን ከለላ እንዲሰጡልን እንጠይቃለን።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
ኅዳር ፳፬ቀን ፳፻ ፲፮ዓ.ም
