ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ
Open in Telegram
ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።
Show more603
Subscribers
No data24 hours
-87 days
-1630 days
Posts Archive
የሰማዕቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሚካኤል የምስክርነት ሐውልት ግንቦት 14 ቀን 2008 ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት፣ ማኅበረ ካህናት እና ማኅበረ ምእመናን በተገኙበት ሰማዕትነትን በተቀበሉበት በጎሬ ከተማ ተመርቋል፡፡
የሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ረድኤትና በረከት ይደርብን::
ትውልድ እና ጵጵስናን ስለመቀበል
ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል፣ ከአባታቸው ከቄስ ገብረ ክርስቶስ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ትኩዬ በ1874 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ የተወለዱበት ስፍራም በቀድሞው አጠራር በጎንደር ጠቅላይ ግዛት በደብረ ታቦር አውራጃ፤ አፈረዋናት ድምበር ወረዳ፣ ልጨ መስቀለ ክርስቶስ ተብሎ ይጠራል፡፡ የጥንት ስማቸው ኃይለ ሚካኤል ይባላል፡፡ ግንድ አጠመም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን፤ ክርስትና ተነሥተውና በዚያው አድገው፣ እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ ወላጆቻቸው መምህር ዋሴ ለሚባሉ አስተማሪ እንዲያስተምሯቸው ሰጧቸው፡፡ ፊደል ከቆጠሩበት ቀን አንስቶ እንደ ልጅ አንድም ቀን ጥፋት ሳይኖርባቸው ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለማዕረገ ዲቁና እንደበቁ፤ መምህራቸው፣ የዜማ ትምህርት እንዲቀጥሉ መካነ ሰማዕት ገላውዴዎስ ለነበሩት መምህር ተድላ ከሰጧቸው በኋላ ጾመ ድጓ እና ምዕራፍ በሚገባ አደላደሉ፡፡ ዝማሬና መዋስዕት፣ ድጓ፣ መዝገብ ቅዳሴ ከነትርጓሜው፣ አቋቋም እና ቅኔ በተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር ከታላላቅ መምህራን ተምረዋል፡፡ ማዕረገ ዲቁና እና ማዕረገ ቅስና ከግብፃዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ከተቀበሉ በኋላ ቤተ ክርስቲያንን በንጽሕና እና በድንግልና በጥሩ ሕይወት አገልግለዋል፡፡ ግንቦት 25 ቀን 1921 ዓ.ም ከአራት አባቶች ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ግብፅ በማቅናት ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ተብለው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል፡፡ ከብፁዕነታቸው ጋር ጵጵስናን ከተቀበሉት ሌሎች ብፁዐን አባቶች መካከል፤ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ እና ብፁዕ አቡነ አብርሃም ይገኙበታል፡፡
ከወራሪው ፋሽስት ኢጣሊያ ጋር የፈጸሙት ተጋድሎ
ግፈኛው ፋሺስት የኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ ሀገራቸውን በአጥንታቸው እሾኽነት አስከብበው፣ በደማቸው የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖትን ክብር አስጠብቀዋል፡፡ በሀገረ ስብከታቸው፣ ሕዝቡን ሰብስበው ለጠላት እንዳይገዛ በማስተባበር፣ የቤተ ክርስቲያኑን ክብር እንዲጠብቅ በማደፋፈር የአርበኝነት ተግባር ፈጽመዋል፡፡ ከብዙ አርበኛ ወንድሞቻቸው ጋር ከሀገር ወደ ሀገር በመዞር ቃለ ወንጌል በማስተላለፍ ሲፋጠኑ፣ የፋሽስት ጦር ሰቢ ከሚባል ጫካ ደርሶ ከበባቸው፡፡ በዚኹ ቦታ አድረው በማግሥቱ በጠላት ጦር ተያዙ፡፡
ብፁዕነታቸው በጾም፣ በፀሎት እና በምህላ ወደ እግዚአብሔር እየማለዱ ሕዝቡን በማፅናናት ቆይተዋል። የፋሽስት ኢጣሊያ ጦር አዲስ አበባ ከገባ በኋላ ቆራጡ የልብ ጓደኛቸው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ለሃይማኖታቸው እና ለአገራቸው ነፃነት መሥዋዕት ለመሆን መዘጋጀታቸውን እንዲሁም ከነፃነት አርበኞች ጎን በመሰለፍ ሕዝቡ ስለ ሃይማኖቱ እና ስለ ሀገሩ ነፃነት እንዲዋጋ በመቀስቀስ ላይ መሆናቸውን ሲሰሙ በጣም ተደሰቱ።
የብፁዕ አቡነ ሚካኤል በጠላት እጅ መውደቅ
በኅዳር ወር 1929 ዓ.ም በፋሽስቱ የጦር አዛዥ በኮሎኔል ማልታ የሚመራው የፋሺስት ኢጣሊያን ጦር የጎሬን ከተማ ተቆጣጠረ። አቡነ ሚካኤል ደግሞ በጎሬ ከተማ አጠገብ ‘ሳንቤ ቀበሌ’ በምትባል ስፍራ ሆነው ሕዝቡ ጠላትን እንዲከላከል በመቀስቀስ ላይ ነበሩ። ብፁዕነታቸው ከብዙ አርበኛ ወንድሞቻቸው ጋር ከሀገር ወደ ሀገር በመዟዟር ቃለ ወንጌል በማስተላለፍ ላይ እንዳሉ ከሁለት አርበኞች ማለትም፤ ከግራዝማች ተክለሐይማኖት እና ከቀኛአዝማች ይነሱ ጋር በመሆን ከጎሬ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ወረድ ብሎ በሚገኝ ሰቢ ከሚባል ጫካ ሲደርሱ ይህን የሰማው የፋሽስት ጦር በአፋጣኝ ወታደር ልኮ አስከበባቸው። ከብፁዕነታቸው ጋር የነበሩት አርበኞች ከከበቧቸው የኢጣሊያ ጦር ጋር ተኩስ ከተለዋወጡ በኋላ የጠላት ጦር ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ እያፈገፈጉ ሳለ፤ አቡነ ሚካኤል በቅሎዋቸው ላይ ተቀምጠው መንገድ እንደ ጀመሩ በኢጣሊያ ወታደሮች ተያዙ።
የአቡነ ሚካኤልን ጠንካራ አቋም ከተረዳው ጠላት ተልከው ወደ እርሳቸው ጋ መጡ።
ተልከው የመጡት መልዕክተኞችም አቡነ ሚካኤል ከጣሊያን ጋር እንዲስማሙ፤ ሕዝቡን እንዲያባብሉ፤ “ለኃያሉ የኢጣሊያ መንግሥት ለመገዛት ቃል ይግቡና ሕዝቡም እንዲገዛልን ይስበኩልን። ይህንን ካደረጉ እንለቅዎታለን።” በማለት በልዩ ልዩ መደለያ ጭምር አባበሏቸው። ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ግን ከሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጠላት ጋር እንደማይተባበሩ በፅናት ሲገልጹ፤ “እኔ የማምነው በአንድ እግዚአብሔር ነው። የምቀበለው የነፃነታችን ምልክት የሆነውን የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ብቻ ነው። ኢጣሊያ የሚባል ገዥ አላውቅም። ለፋሺስት ኢጣሊያ የተገዛ እንደ አርዮስ የተረገመ ይሁን። እንኳንስ ሕዝቡ ምድሪቱም እንዳትገዛላቸው አውግዣለሁ።” በማለት በዚያ ለተሰበሰበው ሰው ሁሉ ውግዘታቸውን አሰሙ።
ሰማዕትነትን መቀበል
የጠላት ጦር አዛዥ ኮሎኔል ማልታ እሥረኛውን ጳጳስ ከእሥር ቤት አስመጥቶ ሕዝቡ በተሰበሰበበት አደባባይ አቀረባቸው። ከጎሬ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በታች አሮጌው ቄራ አጠገብ ጉድጓድ ተቆፈረ።
በጉድጓዱ ዳር በሁለት ስመጥር አርበኞች በቀኛዝማች ይነሱ እና በግራዝማች ተክለ ሐይማኖት መካከል ጳጳሱ እንዲቆሙ ተደረገ። በዚህን ጊዜ አቡነ ሚካኤል ለጥቂት ደቂቃዎች ፀሎት እንዲያደርጉ ጠይቀው ተፈቀደላቸው። ፀሎታቸውን አድርሰው ሲያበቁ መስቀላቸውን በግንባራቸው አድርገው፤ “በል እንግዲህ የፈለከውን አድርግ” በማለት ተናገሩ። ወዲያውኑ የወታደሮቹ አዛዥ የተኩስ ትዕዛዝ ሰጠ። ከእነ አቡነ ሚካኤል እና ከአርበኞች ፊት ለፊት በተርታ ተደርድረው ጠመንጃቸውን ያነጣጠሩት የጠላት ወታደሮች የእሩምታ ተኩስ ተኮሱ። ብፁዕነታቸውና ሁለቱ አርበኞች በተተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ወደቁ። ብፁዕነታቸው ኅዳር 24 ቀን 1929 ዓ.ም. በፋሽስቱ እጅ በመትረየስ ጥይት ተደብድበው ለእናት ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የነፃነት ታጋይ አርበኛ መሆናቸውን አስመስክረው ሰማዕትነትን በመቀበል
ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጡ፡፡
ስዊድናዊው ኮሎኔል ካውንት ካርል ስለ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሚካኤል ሲናገር፤
“ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ከማልዘነጋቸው ቆራጥ ኢትዮጵያውያን አርበኞች አንዱ ናቸው፡፡
ጳጳሱ በሞት ፊት ያሳዩት ድፍረት እና የሀገር ፍቅር ስሜት ምንጊዜም አይረሳኝም፤”
በማለት ገልጿቸዋል፡፡ የቀብራቸውም ሥነ ሥርዓት በአግባቡ አልተፈፀመም ነበር። አቶ ወልደአብ የተባሉ የአገር ፍቅር ያደረባቸው የአካባቢው ነዋሪ በሌሊት ተነስተው ቀበሯቸው። ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ከተረሸኑ በኋላ አፅማቸው ከነበረበት አልባሌ ሥፍራ ተለቅሞ በሣጥን ተደርጎ፣ በጎሬ ደብረገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በክብር የተቀመጠው፤ ጠላት ከሀገር ተባሮ ነፃነት ከተመለሰ ከ1935 ዓ.ም. በኋላ ነው፡፡
የሰማዕትነት መታሰቢያ
ግንቦት 14 ቀን 2008 ዓ.ም. መስዋዕት በሆኑባት ጎሬ ከተማ በሚገኘው በደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደጀ ሰላም ውስጥ የቆመላቸው ሐውልት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለጎሬው አቡነ ሚካኤል ቅድስናን ሰጥቷል። መጎሬ ከተማ ውስጥ በ1960 ዓ.ም. በስማቸው የተቋቋመው አቡነ ሚካኤል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤ በማስታወሻነት ተገንብቷል። የኢሊባቡር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ የአቡነ ሚካኤልን ፎቶግራፍ ከግብፅ አሌክሳንድርያ አስመጥተው በጎሬ ከተማ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው አደባባይ ላይ ከ 1952 ዓ.ም እስከ 1967 ዓ.ም ድረስ በመስታወት ውስጥ አስቀምጠውት ነበር። በደርግ አስተዳደር ወቅትም በቦታው መንገድ አቋርጦ ያልፍበታል ተብሎ ፎቶግራፋቸው እንዲነሣ ተደረገ።
ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል (ዘጎሬ) ቀዳማይ
ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ኅዳር 24 ቀን 1929 ዓ.ም. በፋሺስቱ እጅ በመትረየስ ጥይት ተደብድበው ለእናት ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የነፃነት ታጋይ አርበኛ መሆናቸውን አስመስክረው ሰማዕትነት የተቀበሉባት ዕለት ናት፡፡ ሰማዕትነትን ከተቀበሉ ወርኃ ኅዳር 2016 ዓ.ም 87ኛ ዓመታቸው ነው፡፡ ይህን በማስመልከት ጥቂት ስለ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ታሪካቸውን እናስታውሳችሁ፡፡
በመምህር ጌታቸው በቀለ
EOTC TV
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣ሰማእታት የዚህችን ዓለም ጣዕም ስለ እዉነት ናቁ ደማቸውንም ስለ ክርስቶስ ክብር አፈሰሱ። 📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣
🎤ታላቅ የንግስ በዓል እና ጉባኤ የሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ የንግስ በዓል በደብራችን በደብረ ዓባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ (አየር ጤና ኪዳነምህረት ደብረ ዓባይ ሰፈር )
🎤የፊታችን ህዳር 25/03/2014ዓ.ም አዲስ አበባ በደመቀ ሁኔታ ይከበራል ።
በግራር ደብረ ዓባይ ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ዘማሪያን እና የተለያዩ መምህራን ዘማሪያን በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ይዉላል።ኑ ይህን ከመሰለ በዓል እና ጉባኤ እንዴት ይቀራል አብረን ከበረከቱ እንሳተፍ።
የቅዱስ መርቆሬዎስ ረድኤት በረከት አይለየን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይጠብቀን አሜን!!!
💥💥💥ፍኖተ ብርሃን💥💥💥
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
የደብረ ዕንቁ ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የጉልላት መስቀልን የማኖር ስነ ሥርዓት ተከናወነ ።
ኅዳር 23 ቀን 2016 ዓ.ም
በመሠራት ላይ የሚገኘውን የደብረ ዕንቁ ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የጉልላት መስቀል የማኖር ስነ ሥርዓት ብፁዕ አቡነ ቶማስ በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተከናውኗል ።
በመርሐ ግብሩ ላይ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣ ካህናት አባቶች እንዲሁም በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።
📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣ሰማእታት የዚህችን ዓለም ጣዕም ስለ እዉነት ናቁ ደማቸውንም ስለ ክርስቶስ ክብር አፈሰሱ። 📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣
🎤ታላቅ የንግስ በዓል እና ጉባኤ የሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ የንግስ በዓል በደብራችን በደብረ ዓባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ (አየር ጤና ኪዳነምህረት ደብረ ዓባይ ሰፈር )
🎤የፊታችን ህዳር 25/03/2014ዓ.ም አዲስ አበባ በደመቀ ሁኔታ ይከበራል ።
በግራር ደብረ ዓባይ ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ዘማሪያን እና የተለያዩ መምህራን ዘማሪያን በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ይዉላል።ኑ ይህን ከመሰለ በዓል እና ጉባኤ እንዴት ይቀራል አብረን ከበረከቱ እንሳተፍ።
የቅዱስ መርቆሬዎስ ረድኤት በረከት አይለየን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይጠብቀን አሜን!!!
💥💥💥ፍኖተ ብርሃን💥💥💥
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ✝
✝ #ኅዳር ፳፬ (24) ቀን።
✝ እንኳን #ለኢትዮጵያኑ_ጻድቃን ለታላቁ አባት #ለሐዲስ_ሐዋርያ_ለአቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ሃያ አምስተኛ ሆነው አብራው #ከሃያ_አራቱ_ካህናተ_ሰማይ_ጋር_የቅድስት_ሥላሴ_ዙፍን_ላጠኑበት በዓልና #ለአቡነ_ዜና_ማርቆስ #በቅዱስ_ማርቆስ_አብሳሪነት_ለተወለዱበት (ለልደታቸው) በዓላቸው በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
✝ #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖትም_ከሃያ_አራቱ_ካህናተ_ሰማይ_ጋር_የቅድስት_ሥላሴን_መንበር_እንዳጠኑ፡- አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ መጥተው በሐይቁ ዳር ቆመው ሳለ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦላቸው ነው በእግሩ በውኃው ላይ እየሄደ እያሳያቸው ተከትለውት እንዲሄዱ የነገራቸው። አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትም መልአኩን ተከትለው ሐይቁን በእግራቸው ተራምደው ተሻግረው አቡነ ኢየሱስ ሞዐን አገኟቸው፡፡ እርሳቸውም አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ እርሳቸው እየመጡ እንደሆነ በመንፈስ ዐውቀው ነበርና ሲያገኟቸው በጣም ተደስተው ከተቀበሏቸው በኋላ አመነኩሰዋቸዋል፡፡
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ አሐዱ አምላክ አሜን። ✝
✝ #ኅዳር ፳፫ (23) ቀን።
✝ እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት አንዱ ለሆነው በሐዋርያው #በቅዱስ_ጴጥሮስ_እጅ_ለተጠመቀ ለመቶ አለቃ ለነበረው #ለጻድቁ_ቅዱስ_ቆርኔሌዎስና የስሙ ትርጓሜ የእግዚአብሔር አገልጋይ ለሆነ #ለነቢዩ_ቅዱስ_አብድዩ_ለዕረፍታቸው_በዓል በሰላም አደረሰን። ከእነዚህ ቅዱሳን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊ሰማእታት የዚህችን ዓለም ጣዕም ስለ እዉነት ናቁ ደማቸውንም ስለ ክርስቶስ ክብር አፈሰሱ።🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣
🎤ታላቅ የንግስ በዓል እና ጉባኤ የሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ የንግስ በዓል በደብራችን በደብረ ዓባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ (አየር ጤና ኪዳነምህረት ደብረ ዓባይ ሰፈር )
🎤የፊታችን ህዳር 25/03/2014ዓ.ም አዲስ አበባ በደመቀ ሁኔታ ይከበራል ።
በግራር ደብረ ዓባይ ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት ዘማሪያን እና የተለያዩ መምህራን ዘማሪያን በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ይዉላል።ኑ ይህን ከመሰለ በዓል እና ጉባኤ እንዴት ይቀራል አብረን ከበረከቱ እንሳተፍ።
የቅዱስ መርቆሬዎስ ረድኤት በረከት አይለየን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይጠብቀን አሜን!!!
💥💥💥ፍኖተ ብርሃን💥💥💥
🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊📣🕊
✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝
✝ #ኅዳር ፳፪ (22) ቀን።
✝ እንኳን በንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበሉ በድዮማ ከተማ አረምያ ከምትባል አገር ለሆኑ #ለቅዱሳን_ለቆዝሞስና_ለድምያኖስ ለወንድሞቻቸው #ለአላድዮስ_ለአቢሞስ_ለአብራንዮስና ለእናታቸው #ለቅድስት_ቴውዳዳ_ለዕረፍታቸው_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_ቆዝሞስ ማኅበር #ሰማዕታት_ከሁለት_መቶ_ስልሳ_ሁለት ወንዶችን፣ #ከአርባ_ዘጠኝ_ሴቶችና_ከቀሌምንጦስ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
✝ #ቅዱሳን_ቆዝሞስና_ድምያኖስ ወንድሞቻቸው #አንቲቆስ_ዮንዲኖስና_አብራንዮስ እናታቸው #ቅድስት_ቴዌዳዳ፦ እሊህም ድዮማ ከምትባል ከተማ ስለ እግዚአብሔር ልጅ የታነፀች ግምብ ከአለችበት አረምያ ከምትባል አገር ናቸው።
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨
የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጽዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በደማቅ ተከብሮ ዋለ ።
**********
የቅድስት ድንግል ማርያም ጽዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በኮዬ ፈጬ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም የበላይ ኃላፊ በተገኙበት ተከብሯል::
ዘገባው የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ነው
የአማናዊት ጽዮን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና የታቦተ ጽዮን ክብረ በዓል በአስመራ ርዕሰ አድባራት ቅድስት ድንግል ማርያም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል !
ኅዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም
የአማናዊት ጽዮን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና የታቦተ ጽዮን ክብረ በዓል በጅማ ደብረ ኤፍራታ ቅድስት ማርያም ካቴድራል ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል !
ኅዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም
ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ጥንታዊት ጽዮን ሰማያዊት ብርብር ማርያም ገዳም የህዳር ጽዮንን ዓመታዊ ክብረ በዓል በእንዲህ መልኩ በታላቅ ድምቀት አክብራለች።
***
እግዚአብሔር ይመስገን
√ የዩቲዩብ ገጻችንን
https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared
√ ፌስቡክ ገጻች
https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema
√ የቴሌግራም ገጻችንን
https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN
√ የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA
√ የቲክ ቶክ ገጻችንን
tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema
✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨
ኅዳር ፳፩ ቀን የሚከበረው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ተከበረ።
እግዚአብሔር አምላክ በእናቱ በእመቤታችን አማላጅነት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይሠውረን፡፡ አሜን!🙏
ኅዳር ፳፩ ቀን የሚከበረው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ተከበረ።
እግዚአብሔር አምላክ በእናቱ በእመቤታችን አማላጅነት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይሠውረን፡፡ አሜን!🙏
