en
Feedback
𝖊-𝖘𝖆𝖋𝖊

𝖊-𝖘𝖆𝖋𝖊

Open in Telegram

This channel is mainly focused on - Programming tutorial - Technology news - Technology tips & - job opportunities our market channel @esafemarket contact @esafeSupport

Show more
1 115
Subscribers
No data24 hours
-97 days
-1830 days
Posts Archive
#G12 #student " ተፈታኞች የቅሬታቸውን ምላሽ ከዛሬ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ነገ አርብ ጥር 26/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት እንደሚያበቃ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል። አገልግሎቱ ፤ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያው ቀን ነገ 11:30 እንደሚያበቃ አውቀው በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ አለን የሚሉትን ቅሬታ እንዲያቀርቡ መልዕክት አስተላልፏል። በሌላ በኩል ፤ ቀድመው ቅሬታ ያቀረቡ ተፈታኞች የቅሬታቸውን መልስ www.neaea.gov.et:8081 ድረ ገጽ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን (Registration Number/ID) ብቻ በማስገባት ከዛሬ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ ቅሬታዎች ሁሉም ተጣርተው ሲጠናቀቁ በቀጣይ ቀናት የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጾ የቅሬታ ምላሽ ያልደረሳቸው ተፈታኞች በትዕግስት እንዲትጠባበቁ አሳስቧል። በተጨማሪ ባልተሟላ ወይም በተሳሳተ ወይም በሌላ ሰው መለያ ቁጥር ያመለከቱ የስም ዝርዝራቸው ዛሬ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ከላይ በተጠቀሰው ድረ ገጽ አድራሻ ላይ እንደሚያሳውቅ የገለፀው አገልግሎቱ ተፈታኞች ቅሬታቸውን በድጋሚ በተስተካከለ መለያ ቁጥራቸው ማመልከት እንደሚችሉ ገልጿል። https://t.me/matter_of_facts

ሰሞኑን 12 ውጤት ቀረ ብላችሁ የምታዝኑ ወይንም በቅርቡ ፈተና የምትፈተኑ ይችን ደብዳቤ እንድታነቧት ጋበዝኳችሁ። 🎖ለሌሎችም አጋሩ ✅ @esafeSoftwareSolution
ሰሞኑን 12 ውጤት ቀረ ብላችሁ የምታዝኑ ወይንም በቅርቡ ፈተና የምትፈተኑ ይችን ደብዳቤ እንድታነቧት ጋበዝኳችሁ። 🎖ለሌሎችም አጋሩ ✅ @esafeSoftwareSolution

ግዙፎቹ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በዚህ አመት ስንተኛ አመታቸውን ያከብራሉ?
ግዙፎቹ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በዚህ አመት ስንተኛ አመታቸውን ያከብራሉ?

#MoE ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አሰራር ለመከተል ማቀዱን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል። በዚህም መሰረት ከግማሽ በላይ ያመጡት 30 ሺህ ገደማዎቹ ተማሪዎች በሚቀጥለው ዓመት በቀጥታ ወደ ዩኒቨርስቲ ገብተው የአንደኛ ዓመት ተማሪ ይሆናሉ። ቀሪዎቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም መሰረት በማድረግ፤ የተሻለ ያመጡት ተመርጠው ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡ እንደሚደረግ አስረድተዋል። ይሁንና እነዚህ ተማሪዎች በቀጥታ የዩኒቨርስቲ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንደማይሆኑ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠቁመዋል። ተማሪዎቹ " የደከሙባቸው ትምህርቶችን” ለአንድ ዓመት በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እየተማሩ ከቆዩ በኋላ፤ በዓመቱ መጨረሻ ፈተና ወስደው ካለፉ በዩኒቨርስቲዎች የአንደኛ ዓመት ተማሪ ሆነው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል። #ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር https://t.me/esafeSoftwareSolution

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና 50%  እና በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት እንደሚገቡ ተገለፀ፡፡ ………………………………………… ጥር19/2015ዓም. (ትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም 12ኛ ከፍል የዉጤት ትንታኔ፣ወደ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤትና ተያያዥ ጉዳዮች  አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ መግለጫውን የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ  የተገኘው የፈተና ውጤት ከስርቆትና ከኩረጃ በፀዳ መልኩ በትክክል የተመዘገበ መሆኑን  ገልፀዋል፡፡ በ2014 ዓ.ም በተሰጠው ፈተና በሁለቱም የትምህርት መስክ ፈተናውን ከወሰዱት 896 ሺህ 520 ተማሪዎች ውስጥ 29 ሺህ 909 የሚሆኑት ተማሪዎች 50% እና በላይ ያስመዘገቡ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ከፍተኛ ውጤት የተበዘገበበት የትምህርት መስክ በተፈጥሮ ሳይንስ  666 ከ700 ከፍተኛ ውጤት ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ  524 ከ600 ከፍተኛ ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በክልሎች ደረጃ በዉጤት ደረጃ የጎላ ልዩነት እንደሌለ ገልፀው አዲስ አበባ፣ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም የሃረሪ ክልል የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ በሃገር አቀፍ ደረጃ ፈተናውን ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች ውስጥ  ሰባት ትምህርት ቤቶች ያስፈተኑትን ተማሪዎች 100% አሳልፈዋል ተብሏል፡፡ ሙሉ ዜናው👇 https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid074RJqnxxik7HZkHsim7DLkdnmE3PDTtTvsS9hQqFZanyH1nEHg29ifYCARbs59nPl&id=100064682287722&mibextid=Nif5oz https://t.me/esafeSoftwareSolution

key-logger-malicious-software ስልካችን እና ኮምፒውተራችንን በስውር የሚሰልለው ”ኪሎገር” ኪሎገር የምንለዋወጣቸውን መልዕክቶች፣ የምንከፍታቸውን ድረገጾች፣ የመተግበሪያዎች እና የባንኮች የይልፍ ቃላትን መዝግቦ ለጠላፊዎች ያስተላልፋል በሳይበሩ አለም የተጠቃሚዎችን ደህንነት ጥያቄ ውስጥ ከሚከቱ የኮምፒውተር ፕሮግራሞች ወይም ሶፍትዊሮች ውስጥ ኪሎገር አንዱ ነው። ኪሎገር በኮምፒውተር ወይም ስልካችን ላይ የምናስገባቸውን ቃላት እየመዘገበ ለመረጃ ጠላፊዎች ያቀብላል። በሁለት መልኩም የሰዎችን መረጃ እያነፈነፈ ለመዝባሪዎቹ ያስተላልፋል፤ ኮምፒውተር ላይ በሚደረግ ፍላሽ መሳይ መሳሪያ እና በተለያየ መልኩ በሚላኩ ቫይረሶች አማካኝነት እያንዳንዱን እንቅስቃሴ በጽሁፍ እየመዘገበ ይልካል። ፋይሎችን ስናወርድ በትሮጃን መልክ አልያም ከማናውቃቸው ምንጮች የሚላኩ አጠራጣሪ ሊንኮችን ስንከፍት ኪይሎገር ወደ ስልክ እና ኮምፒውተራችን ገብቶ በስውር ስለላውን ያካሂዳል ነው የተባለው። ደህንነቱ ያልተጠበቀ ፍለጋን ማድረግም ለዚሁ የስለላ ፕሮግራሙ ተጋላጭ ያደርጋል። በኪሎገር የተጠቃ ሰው ምንም አይነት ሚስጢር የሚባል ነገር አይኖረውም፤ ምን ጻፍን፣ ምን አይነት ድረገጾችን ጎበኘን፣ ወደተለያዩ መተግበሪያዎች ስንገባ የምንጠቀማቸው የይለፍ ቃላት ሁሉ በኪይሎገር ይመዘገባል። በዚህ ሶፍትዌር ጥቃት የሚደርሰው ከማይታወቁ የመረጃ መንታፊዎች ብቻ አይደለም፤ የቅርብ ጓደኞቻችንም ጥቃቱን ሊያደርሱ ይችላሉ። ስልካችን በአጋጣሚ እጁ የገባ ሰው መተግበሪያውን አውርዶ ሊሰልለን ይችላል። መተግበሪያው ለሚጠይቃቸው ቅድመ ሁኔታዎች አዎንታ በመስጠትም የተላላክናቸውን መልዕክቶችን፣ የባንክ የገንዘብ ዝውውር ሲደረግ የይለፍ ቃላትን ማየት፣ ያለበትን ስፍራ መለየት፣ ፎቶዎችን መመልከት ጨምሮ አጠቃላይ የስልካችን ስክሪን እንቅስቃሴ ኪሎገር እንዲመዘግብና እንዲሰልል ማድረግ ይቻላል። የተከማቸውን መረጃም የሚሰለለውን ሰው ስልክ ዳግም በማግኘት ሙሉ በሙሉ መመንተፍ እንደሚቻል ነው ሜክ ዩዝ ኦፍ ኢት ድረገጽ ያስነበበው። ኪሎገርን ለመልካም አላማ የሚጠቀሙበት እንዳሉ ተነግሯል። በተለይ ወላጆች ልጆቻቸውን ለመቆጣጠር እንዲሁም መስሪያ ቤቶች ሰራተኞቻቸው ከስራ ውጭ የሆኑና የተከለከሉ ድረገጾችን እንዳይከፍቱ ለመከታተል ጥቅም ላይ ያውሉታል። ባለሙያዎች ከኪሎገር ጥቃት ለማምለጥ ስልክን ወይም ኮምፒውተርን ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ አለመስጠት፣ የጸረ ቫይረስ መተግበሪያዎችን መጫን እና ቫይረሶችን ለማጥፋት ሁሌም ስካን ማድረግን ይመክራሉ። https://t.me/esafeSoftwareSolution

key-logger-malicious-software ኪሎገር የምንለዋወጣቸውን መልዕክቶች፣ የምንከፍታቸውን ድረገጾች፣ የመተግበሪያዎች እና የባንኮች የይልፍ ቃላትን መዝግቦ ለጠላፊዎች ያስተላልፋል በሳይበሩ አለም የተጠቃሚዎችን ደህንነት ጥያቄ ውስጥ ከሚከቱ የኮምፒውተር ፕሮግራሞች ወይም ሶፍትዊሮች ውስጥ ኪሎገር አንዱ ነው። ኪሎገር በኮምፒውተር ወይም ስልካችን ላይ የምናስገባቸውን ቃላት እየመዘገበ ለመረጃ ጠላፊዎች ያቀብላል። በሁለት መልኩም የሰዎችን መረጃ እያነፈነፈ ለመዝባሪዎቹ ያስተላልፋል፤ ኮምፒውተር ላይ በሚደረግ ፍላሽ መሳይ መሳሪያ እና በተለያየ መልኩ በሚላኩ ቫይረሶች አማካኝነት እያንዳንዱን እንቅስቃሴ በጽሁፍ እየመዘገበ ይልካል። ፋይሎችን ስናወርድ በትሮጃን መልክ አልያም ከማናውቃቸው ምንጮች የሚላኩ አጠራጣሪ ሊንኮችን ስንከፍት ኪይሎገር ወደ ስልክ እና ኮምፒውተራችን ገብቶ በስውር ስለላውን ያካሂዳል ነው የተባለው። ደህንነቱ ያልተጠበቀ ፍለጋን ማድረግም ለዚሁ የስለላ ፕሮግራሙ ተጋላጭ ያደርጋል። በኪሎገር የተጠቃ ሰው ምንም አይነት ሚስጢር የሚባል ነገር አይኖረውም፤ ምን ጻፍን፣ ምን አይነት ድረገጾችን ጎበኘን፣ ወደተለያዩ መተግበሪያዎች ስንገባ የምንጠቀማቸው የይለፍ ቃላት ሁሉ በኪይሎገር ይመዘገባል። በዚህ ሶፍትዌር ጥቃት የሚደርሰው ከማይታወቁ የመረጃ መንታፊዎች ብቻ አይደለም፤ የቅርብ ጓደኞቻችንም ጥቃቱን ሊያደርሱ ይችላሉ። ስልካችን በአጋጣሚ እጁ የገባ ሰው መተግበሪያውን አውርዶ ሊሰልለን ይችላል። መተግበሪያው ለሚጠይቃቸው ቅድመ ሁኔታዎች አዎንታ በመስጠትም የተላላክናቸውን መልዕክቶችን፣ የባንክ የገንዘብ ዝውውር ሲደረግ የይለፍ ቃላትን ማየት፣ ያለበትን ስፍራ መለየት፣ ፎቶዎችን መመልከት ጨምሮ አጠቃላይ የስልካችን ስክሪን እንቅስቃሴ ኪሎገር እንዲመዘግብና እንዲሰልል ማድረግ ይቻላል። የተከማቸውን መረጃም የሚሰለለውን ሰው ስልክ ዳግም በማግኘት ሙሉ በሙሉ መመንተፍ እንደሚቻል ነው ሜክ ዩዝ ኦፍ ኢት ድረገጽ ያስነበበው። ኪሎገርን ለመልካም አላማ የሚጠቀሙበት እንዳሉ ተነግሯል። በተለይ ወላጆች ልጆቻቸውን ለመቆጣጠር እንዲሁም መስሪያ ቤቶች ሰራተኞቻቸው ከስራ ውጭ የሆኑና የተከለከሉ ድረገጾችን እንዳይከፍቱ ለመከታተል ጥቅም ላይ ያውሉታል። ባለሙያዎች ከኪሎገር ጥቃት ለማምለጥ ስልክን ወይም ኮምፒውተርን ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ አለመስጠት፣ የጸረ ቫይረስ መተግበሪያዎችን መጫን እና ቫይረሶችን ለማጥፋት ሁሌም ስካን ማድረግን ይመክራሉ። https://t.me/esafeSoftwareSolution

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን ተማሪዎች ከዛሬ ለሊት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል። ተፈታኞች ከዛሬ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም #ከሌሊቱ 5፡30 ጀምሮ ፡- • በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ወይም • በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም • በቴሌግራም ላይ https://t.me/eaesbot ማየት የሚችሉ መሆኑን ተገልጿል። ማሳሰቢያ፡- • ማንኛውም ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልግ እስከ ጥር 26/2015 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ላይ Compliant የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል። • ተማሪዎች ፤ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አድራሻ ላይ ብቻ እንዲጠቀሙ #ከተመሳሳይ እና #የተዛባ_መረጃ ለማሰራጫት ከሚሞክሩ አካላት እራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት ተላልፏል። ምንጭ ፦ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት https://t.me/esafeSoftwareSolution

  በአንድሮይድ ስልኮች ላይ የሚገኙ ሚስጢራዊ ኮዶች በአንድሮይድ ስልኮች ላይ የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት የሚረዱ በርካታ ኮዶች አሉ ሚስጢራዊ ኮዶቹ በአንድሮይድ ስማርት ስልኮች ውስጥ የተደበቁ አገልግሎቶችን ለማግኘት ያስችላሉ። በስልኮቹ ላይ የተቀመጡ መረጃዎችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የሚያግዙ ኮዶችም አሉ። እነዚህን ሚስጢራዊ ኮዶች በአግባቡ ጽፎ በመደውል የሚፈለገውን ግልጋሎት ማግኘት እንደሚቻል የሚገልጹ ባለሙያዎች ፥ አንዳንዶቹ ኮዶች ሁለት ጊዜ ማሰብን ሊጠይቁ እንደሚችሉ ያሳስባሉ። በተለይም የስልክን ሙሉ በሙሉ የሚያጠፉ ኮዶችን አስፈላጊ ካልሆነ መጠቀም አይገባም ነው የሚሉት። በቀጣይ የተዘረዘሩት ሚስጢራዊ ኮዶችም አንድሮይድ ስልኮች ላይ የሚገኙ በቀላሉ የሳይበር ደህንነት ተጋላጭነትን ለማረጋገጥ እና የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት የሚያስችሉ ናቸው። 1. *#06# - የስልክን አለም አቀፍ መለያ (አይ ኤም ኢ አይ) ቁጥር ለማወቅ 2. *#61# ፣ *#62# ወይም #004# - የስልክ ጥሪ ወደሌላ ሰው ስልክ መተላለፉን (call forwarding) ለማረጋገጥ 3. ##61# ወይም ##67# - ያላነሳናቸው የስልክ ጥሪዎች በሌሎች ተነስቷል ብለን ስናምን፣ ስልካችን ሲዘጋ ጥሪው ወደ ሌላ ስልክ ሲያመራ( call forwarding) ወይም ስልካችን መጠለፉን ስንጠረጥር ለማጥፋት 4. *#21# - የስልክ ጥሪያችን በሌሎች አለመጠለፉን ለማረጋገጥ 5. ##21# - ስልካችን ተጠልፏል ብለን ስናምን ለማቋረጥ 6. #0# - የስማርት ስልኮች ስክሪን፣ ካሜራ፣ ንዝረት፣ ሴንሰርን ጨምሮ ሌሎች ነገሮች ለመሞከር 7. *31# - የደዋዩን ማንነት ለመደበቅ (Disable Caller ID) 8. #31# - የደዋዩን ማንነት መደበቅ ለማቋረጥ 9. *43# - ተጨማሪ የስልክ ጥሪን ለማስተናገድ (Enable Call Waiting) 10. #43# - ተጨማሪ የስልክ ጥሪን ለማስተናገድ የሚያስችለውን እድል ለማቋረጥ (Disable Call Waiting) 11. *#1234# - የስልክ ሞዴልና የተመረተበትን አመት ለማወቅ 12. *#0228# - የስማርት ስልኮችን ባትሪ መረጃ ለማየት  13. ##7780## - የስልክ መረጃዎችን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት (በተለይ የግል መረጃዎች እና መተግበሪያዎች በማጥፋት ስልኩን ለመሸጥ) https://t.me/esafeSoftwareSolution

check current latest Samsung phones price list. 👇 1, M13 64GB/4GB 14,000 2, A13 4Ram with 64GB 15,500 3, A13 4RAM with 128GB 17500 4, M13 6RAM with 128GB 17500 5, M33 5G 6Ram with 128GB 21000 6, A33 5G 6RAM with 128GB 28000 7, A53 5G 8RAM with 128GB 36000 8, A73 5G 8RAM with 128GB 43500 ✅You can ask any model ከ 1 በላይ ለሚገዛ ልዩ ቅናሽ አለ contact 👇👇 @esafeSupport +251710545439 https://t.me/esafemarket

ቀጥለው የተዘረዘሩ መተግበሪያዎች በስልኮቻችን ላይ ካሉ ልናጠፋቸው ይገባል በስማርት ስልካችን ላይ የምንጭናቸው መተግበሪያዎች (አፕሊኬሽኖች) በርካታ ነገሮችን በሚያቀሉለን ቢሆኑን አንዳንዶች ግን መረጃዎቻችን ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ ከመስጠት ጀምሮ ለሳይበር ጠላፊዎች እንድንጋለጥ ሊያደርጉን ይችላሉ። በውስጣቸው አጥፊ ቫይረሶችን የያዙ ነገር ግን አገልግሎት የሚሰጡ በመመስል የተሰሩ መተግበሪያዎች አሉ የሚለን ፎን አሬና ድረ ገጽ፤ እንዚህን መተግበሪያዎች (አፕሊክሽኖች) ውለን ሳናድር ዛሬውኑ ከስልካችን ላይ እናጥፋቸው ሲልም ምክረ ቢጤ አክሏል። ቀጥለው የተዘረዘሩ አፕሊኬሽኖች በስልካችን ላይ ተጭነው ካሉ በፍጥነት ልናጠፋቸው ይገባል ዋለስ ላይት (Walls light - Wallpapers Pack ቢግ ኢሞጂ (Big Emoji – Keyboard) ግራድ ዋል ፔፐርስ (Grad Wallpapers - 3D Backdrops) ኢንጂን ዋል ፔፐርስ (Engine Wallpapers - Live & 3D) ኢፌክት ሚና (EffectMania - Photo Editor) አርት ፊልተር (Art Filter - Deep Photoeffect) ፋስት ኢሞጂ ኪቦርድ (Fast Emoji Keyboard) ከርኤት ስቲከር (Create Sticker for Whatsapp) ማትስ ሶልቨር (Math Solver - Camera Helper) ፎቶ ፊክስ ኢፌክት (Photopix Effects - Art Filter) ሊድ ቲም (Led Theme - Colorful Keyboard) ኪይ ቦርድ (Keyboard - Fun Emoji, Sticker) ስማር ዋይ ፋይ (Smart Wifi) ማይ ጂ.ፒ..ኤስ ሎኬሽን (My GPS Location) ኢሜጅ ወራፐ ካሜራ (Image Warp Camera) ስማርት ኪው.አር ክሬቶር (Smart QR Creator) ከለራይዝ ኦልድ ፎቶ (Colorize Old Photo) ጂ.ፒ.ኤስ ሎኬሽን ፋይነደር (GPS Location Finder) ስማርት ኪው.አር ስካነር (QR Scanner) ጂ.ፒ.ኤስ ሎኬሽን ማፕስ (GPS Location Maps) ቮልዩም ኮንትሮን (Volume Control) ሰክሪት ሆርስኮፕ (Secret Horoscope) ስማርት ጂ.ፒ.ኤስ ሎኬሽን (Smart GPS Location) አኒሜትድ ስቲከር ማስተር (Animated Sticker Master) ስሊፕ ሳውንድ (Sleep Sounds) አይ ሎቭ ፊልተር (I love Filter) ቤስት ካሜራ (Best camera) ቢዩቲፉል ካራ (Beautiful camera) ቻርሚንግ ካሜራ (Charming Camera) ታይድ ካሜራ (Tide Camera) ኬል ዴስክቶፕ (Cool Desktop) ዋይ ፋይ ቡስተር (Wifi Booster) ሲምፕል ካሜራ (Simple Camera) https://t.me/esafeSoftwareSolution

🎄🎅 እንኳን አደረሳችሁ ለገና አዲስ ስልክ መግዛት ወይንም ስልክ ስጦታ መስጠት ካሰቡ። check current latest Samsung phones list. 👇 1, M13 64GB/4GB 13,000 2, A13 4Ram with 64GB 15500 3, A13 4RAM with 128GB 17500 4, M33 5G 6Ram with 128GB 20500 5, A33 5G 6RAM with 128GB 27000 6, A53 5G 8RAM with 128GB 35000 7, A73 5G 8RAM with 128GB 43500 ✅You can ask any model ከ 1 በላይ ለሚገዛ ልዩ ቅናሽ አለ contact 👇👇 @esafeSupport +251710545439 https://t.me/esafemarket

Repost from N/a
Samsung Galaxy M33 5G camera: 50MP storage: 128GB/6GB battery: 6000mAh price 20,500 birr በግሩፕ ሁናችሁ ብታዙ እንመክራለን ከ 1 በላይ ለሚገዛ ል
Samsung Galaxy M33 5G camera: 50MP storage: 128GB/6GB battery: 6000mAh price 20,500 birr በግሩፕ ሁናችሁ ብታዙ እንመክራለን ከ 1 በላይ ለሚገዛ ልዩ ቅናሽ አለ contact👇 @esafeSupport https://t.me/esafemarket

1, M13 64GB/4GB 13,500 2, A13 4Ram with 64GB  15500 3, A13  4RAM with 128GB  17500 4, M33 5G 6Ram with 128GB  20500 5, A33 5G 6RAM with 128GB 27000 6, A53 5G 8RAM with 128GB 35000 7, A73 5G 8RAM with 128GB  43500 ✅You can ask any model contact 👇👇 @esafeSupport https://t.me/esafemarket

Repost from N/a
1, A13 4Ram with 64GB  15500 2, A13  4RAM with 128GB  17500 3, M33 5G 6Ram with 128GB  20500 4, A33 5G 6RAM with 128GB 27000 5, A53 5G 8RAM with 128GB 35000 6, A73 5G 8RAM with 128GB  43500 ✅You can ask any model contact 👇👇 @esafeSupport https://t.me/esafemarket

ለመጀመሪያ ደንበኞች ተብሎ በጣም በቅናሽ ዋጋ የቀረበ ነው ይሄ እድል አያምልጣችሁ። ሱቅ ወይንም ሌላ ቻናል ላይ ማየት ትችላላችሁ ከ 1000 ብር በላይ በሆነ የዋጋ ልዩነት የቀረብ ነው። ለሌሎች ሼር አድርጉ ከ 2 በላይ ለሚገዛ 500 ብር ይቀንሳል። Samsung Galaxy M13 64GB/4GB contact 👇👇 @esafeSupport https://t.me/esafemarket

Repost from N/a
Samsung Galaxy M13 64GB/4GB Price: 13,500 @Esafebot https://t.me/esafemarket
Samsung Galaxy M13 64GB/4GB Price: 13,500 @Esafebot https://t.me/esafemarket

Repost from N/a
Samsung Galaxy M13 64GB/4GB Price: 13,000 @Esafebot https://t.me/esafemarket
Samsung Galaxy M13 64GB/4GB Price: 13,000 @Esafebot https://t.me/esafemarket

ደብረ ዲቦራ (በእውቀቱ ስዩም) ከለታት አንድ ቀን ፥ ከሶስት ጓደኞቼ ጋራ ካፌ ውስጥ ቡን እየጠጣን እናወራለን፤ አንዱ ገና ፍልስፍና ማንበብ የጀመረ ጎረምሳ “ የስነ ውበት ፍርድ እና የስነ ምግባር ፍርድ በሚባሉት ጽንሰ ሀሳቦች መሀል ያለው ልዩነት ምንድነው? የሚል ጥያቄ አነሳ፤ ሁለተኛው ወዳጃችን ፥ የምእራብን እና የምስራቅን ፈላስፎች ሀሳብ እየጠቀሰ በሰፊው ምላሽ ለመስጠት ሞከረ፤ ውይይቱን ቡና የማይመክተው የእንቅልፍ ክኒን አደረገብን:: በዚህ መሀል፥ ሶስተኛው፥ ምኡዝ ፥ “ ያንን ዘናጭ ቂጥ እዩልኝማ “ ብሎ ጮኸ፥ ሁላችንም ወደ ተጠቆመው ቂጥ ዞርን፤ ባጠገባችን ቡና እየጠጡ የነበሩ ሁለት ጠና ጠና ያሉ ሴቶች ምኡዝን ክፉኛ ገላመጡት:: ምኡዝ እንዲህ አለ; “ ዘናጭ ቂጥ” የሚለው አነጋገሬ የስነ-ውበት ፍርድ ሲሆን፥ የኒህ ሴቶች ግልምጫ ደግሞ የስነ-ምግባር ፍርድ ነው፤ ገባህ?” ከካፌው ማዶ ቡቲክ አለ፤ የቡቲኩ ባለቤት የዘናጬ መቀመጫ ተሸካሚ ናት፤ ዲቦራ ትባላለች፤ ከእሷ ጋር ሲነጻጸር የሌሎች ሴቶች መቀመጫ ፥ መቆሚያ እንጂ መቀመጫ ነው ማለት አይቻልም፤ ከሰገጥሁባቸው ቀኖች ባንዱ እለት፥ ካልነካሁት ብየ አስቸገርኩ፤ ምኡዝን” በሁለት መቶ ብር እንወራረድ የዲቦራን ቂጥ በመዳፌ እተመትመዋለሁ አልሁት፤ “ውድድሩ በአምስት መቶ ብር ቢሆን ደስ ይለኛል፤ አምስት መቶ ብር አምሮኛል “ አለኝ፤ ተስማማሁ፤ አንድ ቀን ዲቦራ ከቡቲኩ ወጥታ ወደ ካፌው ለመሄድ በፊታችን ስታልፍ እጄን ወደ ሁዋላዋ ሰደድሁት፤ አሰነዛዘሬ በዝግታ እንዲሆን አስቤ ነበር፤ ዝንብ እንደሚያባርር ሰው ጣቶቼን ገፋ አድርጌ ለመመለስ ተዘጋጀሁ፤ ግን እንደ ሀሳቡ የኖረ ማን ነው? ድንገት እጄ፥ የምድርን መአዘን ነክቶ ተመለሰና መቀመጫዋ ላይ አረፈ፤ ጡዋዋዋዋዋ! የልደት ፊኛ ራሱ እንደዚያ አይጮህም! “ ትልቅ ሰው አይደለህም እንዴ?” አለችኝ እሳት ለብሳ፤ እሳት ጎርሳ፤ እሳት ተንተርሳ፤ “ ለትልቅ ሰው ትልቅ ቂጥ አይወድለትም? “ የሚል ምላሽ መስጠቴን አስታውሳለሁ፤ ለህዝብ ማስተማርያ ይሆናል ብየ ነው እንጂ ከዚያ ቀጥሎ የተከተለውን ባልናዘዘው እመርጥ ነበር፤ መዳፏ ፊቴ ግድም ውልብ ሲል ትዝ ይለኛል፤ አቀርቅረህ ፤ቴክስት እያደረግህ ስትሄድ ከመብራት ምሶሶ ጋራ ተጋጨተህ ታውቃለህ? የደረሰብኝ አደጋ ከዚያ አይተናነስም፤ ከጥቂት ደቂቃ በሁዋላ፤ ባቅራቢያው ወደሚገኝ ፋርማሲ ጎራ ብየ፥ ከምኡዝ በበላሁት አምስት መቶብር የነስር ማስቆሚያ መድሀኒት ገዛሁ:: ካንድ ሳምንት በሁዋላ ብስጭቴ አልቀነሰም፤ ከዲቦራ መዳፍ በላይ የምኡዝ ሳቅ እያደር አመመኝ፤ ምኡዝ ተመሳሳይ ነገር ካልደረሰበት በቀር እንደማልጽናና ገባኝ፤ “አንተ የዲቦራን ቂጥ ከነካህ አንድ ሺህ ብር እሰጥሀለሁ “ አልሁት፥ ምኡዝ ተስማማ፤ ተያይዘን ወደ ቡቲኳ ሄድን፤ ዲቦራ ረስታኛለች፤ የጠፈጠፈ ቢረሳ የተጠፈጠፈ አይረሳም፤ ኩርፍያየን ለማሳየት ያክል ፈንጠር ብየ ቆምሁ፤ ምኡዝ አንድ ሸሚዝ ገዛትና ትንሽ ሲያሳስቃት ከቆየ በሁዋላ፤ ወደ መቀሜዋ እየጠቆመ “ ሲያዩት በጣም ደስ ይላል፤ ስፖንጅ አይመስልም “ አላት፡ : “ ስፖንጅ አይደለም፤ “ ብላ ቀወጠችው፥ ከዚያ፥ ትንሽ ስታመነታ ከቆየች በሁዋላ እንዲህ ስትል ሰማሁዋት፥ “ ካላመነከኝ ነክተህ ማረጋገጥ ትችላለህ” ምኡዝ ወደኔ ዞሮ “ምንም ማድርግ አይቻልም በሚል ፈገግ አለ:: ከዚህ የተሻሉ ወጎችን ማዳመጥ ከፈለጉ የዩቲዩብ ቻናሌን ሰብስክራይብ ያድርጉ🙂 https://t.me/esafeSoftwareSolution

ለገጠር ልጆች ብቻ! (አሌክስ አብርሃም) በተለይ ቤተሰቦቻቸው በቂ እርሻ ያላቸው የገጠር ልጆች በስንት ችግር ከተማ ገብተው ፣ እየተሰቃዩ አካውንቲንግ ተምረው (የማውቃቸው ሁሉ ደግሞ አካውንቲንግ ወይም ነርሲንግ ነው የሚማሩት) ለምን እዚህ ግባ በማይባል ደመወዝ አመት ሙሉ ስራ ፍለጋ ከተማ ለከተማ እንደሚንከራተቱ አይገባኝም! የከተማ ልጅ መሄጃ የለውም! ምርጫው ተምሮ መቀጠር፣ ወይም ከቻለ የግል ስራ መፍጠር አልያም እንደምንም ከአገር መሰደድ ነው! እስቲ አሁን አርሶ አደር ቤተሰቦቹ ከበርበሬ እስከፍራፍሬ፣ ከጤፍ እስከማር ከዓመት ዓመት የሚያመርቱ አንድ የደቡብ ልጅ ...አራት ኪሎ የሀብታም ደረጃ ላይ ተኮራምቶ ጋዜጣ ላይ ስራ ሲፈልግ መዋል ምን ይባላል? ስንቱ መሰላችሁ በእርጅና አቅማቸው ደክሞ ማረስ ያቃታቸው ወላጆቹን ትቶ አዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች የሚንከራተተው! ገጠር ለአይኑ ያስጠለዋል በቃ! ብዙሀኑ ወላጅም "ልጀ ከተማ ገባ" ማለትን እንደልዩ ስኬት ያይዋል! አትማሩ አይደለም ተማሩ፣ ግን መሠረታችሁን ሳትለቁ አያት አባቶቻችሁ ያቆዩላችሁን ግብርና አንድ ስንዝር ወደፊት የሚያስኬድ ነገር ተማሩ ፣ ከተማ በቁሙ እየሞተ ነው! ዓለም ወደገጠር ወደግብርና ፊቱን እየመለሰ ነው! በአባቶቻችሁ መሬት ነገ አንዱ ባለሀብት እስኪቀጥራችሁ ከመዋተት እስቲ ጨክኑ! ከተማን ከአዕምሯችሁ አውጡት!ከተማው ወደእናተ ይመጣል ባላችሁበት ሞክሩ! ይገባኛል ገጠር ተነግሮ የማያልቅ ብዙ ችግር አለ! ውስብስብ ችግር! ግን ከችግር ወደሚዘገንን ሌላ ችግር ስትሸሹ መኖር እስከመቸ? ያንን ችግር ማን ይጋፈጥላችሁ? ኧረ ተው ካረጃችሁ በኋላ ከመባነን ዙሪያችሁን ተመልከቱ! ነገ ወደኋላ ስትዞር መሬቱም አይኖርም አንተም የተወዛገብክ ቅጥረኛ ሁነህ ትቀራለህ! https://t.me/esafeSoftwareSolution