cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት | የመ/ሕ/ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ንዑስ ክፍል

ይኽ የፈረንሳይ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን መካነ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ቻናል ነው። በዚኽ ቻናል በመንፈሳዊ ሕይወትዎ የሚበረቱባቸውን መንፈሳዊ ጽሑፎችና መልእክቶች ባሉበት ሆነው መከታተል ይችላሉ።

Show more
Advertising posts
1 020
Subscribers
No data24 hours
+47 days
+2830 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
የወርሐ ግንቦት ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት መጽሔትን ያውርዱት ..........ያንብቡት..........ያጋሩት የመካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የመካነ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት ንዑስ ክፍል
1 3674Loading...
02
"ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡ ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡ ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡ ተፈጥሮ እንደ መጽሐፍ ፍጥረታት እንደ ጽላት ይሁኑህ። ከእነሱ ሕግጋትን ተማር፤ በተመስጦ ሆነህ በመጽሐፍ ያልሰፈሩትን ምስጢራት ተረዳ፡፡ እግዚአብሔርን ከሚፈራ በቀር ባለጸጋ የሆነ ሰው ማነው? የእውነት እውቀት ከጎደለው ሰው በላይ ፍጹም ደሃ የሆነ ማን ነው? ሁል ጊዜም እውነተኛ ፍቅራችን ጸንቶ ይቀጥል ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ፡፡ እርሱን ለምነው፡፡ ስለ ቸርነቱ ምስጋና አቅርብ፤ ምክሬን ፈጽሞ ቸል አትበል፡፡" (ምክር ወተግሳጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም)
1040Loading...
03
Media files
1320Loading...
04
†✝† እንኩዋን ለጥንተ በዓለ ዸራቅሊጦስ (መንፈስ ቅዱስ) እና ለጻድቁ አባ ገዐርጊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †✝† †✝† በዓለ ዸራቅሊጦስ †✝† ✝✞✝ ከዚሕ በፊት እንደተመለከትነው የጌታችን ዓበይት በዓላቱ 2 ጊዜ (ማለትም ጥንተ በዓልና የቀመር በዓል ተብለው) ይከበራሉ:: ዛሬም ከ1,978 ዓመታት በፊት አምላካችን መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ መውረዱን እናስባለን:: ††† ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- +ቸር አምላክ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሲል *ከልዑል ማዕርጉ ወርዶ: *በማሕጸነ ድንግል ተጸንሶ: *በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: *ከኃጢአት በቀር በግዕዘ ሕጻናት አድጐ: *በ30 ዘመኑ ተጠምቆ: *ቅድስት ሕግ ወንጌልን አስተምሮ: *በፈቃዱ ሙቶ: *በባሕርይ ስልጣኑ ተነስቶ: *በአርባኛው ቀን ያርጋል:: +ታዲያ ደቀ መዛሙርቱን የቅዱስ መንፈሱን ጸጋ ተስፋ እንዲያደርጉ ነግሯቸው ነበርና በተነሳ በ50ኛው ቀን: በዐረገ በ10 ቀን ተስፋውን ፈጸመላቸው:: +እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ እንድትይዝ በአንድ ላይ ሰብስባ ለክብረ መንፈስ ቅዱስ አብቅታቸዋለች:: 120ው ቤተሰብ ከጌታችን እናት ጋር ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ በአውሎ ንፋስ አርአያ ወርዶ በአምሳለ እሳት አደረባቸው:: +ቅዱሳን ሐዋርያት ፈሪዎች የነበሩ ደፋሮች: አሮጌ ሕሊና የነበራቸው ሐዲሶች ሆኑ:: በአዕምሮ ጐለመሱ: ቁዋንቁዋ ተናገሩ: ምሥጢርም ተረጐሙ:: በቅጽበትም ብሉይ ከሐዲስ በልቡናቸው ውስጥ ተሞላ:: +ሐዋርያቱ ቅዱስ መንፈስን ተቀብለው ዓለምን በወንጌል ዕርፈ መስቀል አርሰዋል:: አልጫውን ዓለም ጨው ሆነው አጣፍጠዋል:: ሳይሳሱም አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተዋል:: "ኪያሁ መንፈሰ ነሢኦሙ ለለአሐዱ: ሐዋርያት ለሰቢክ አሕጉራተ ዓለም ዖዱ: ሰማዕትኒ ለሕማም ነገዱ::" እንዳለ ደራሲ:: +በዚህ ቀን 2 ነገሮች በትኩረት ይነገራሉ:- 1."የመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክነት:-" *እርሱ ከአብ የሠረጸ: ቅድመ ዓለም የነበረ: በባሕርይ ስልጣኑ ከአብና ከወልድ ጋር እኩል የሆነ: የራሱ ፍጹም አካል ያለው ፍጹም አምላካችን ነውና:: 2."ቅድስት ቤተ ክርስቲያን:-" *አብ ያሰባት: ወልድ በደሙ የቀደሳት: መንፈስ ቅዱስ በጸጋው ያጸናት የክርስቲያኖች አማናዊት አንድነት: አንድም ቤት ናትና:: ዛሬ በጉባዔ ተመስርታለች:: ††† አባ ገዐርጊ ††† =>በዚችም ዕለት የአባ አብርሃም ጓደኛ የከበረ አባ ገዐርጊ አረፈ።ይህም ቅዱስ የክርስቲያን ወገን ነው ወላጆቹ ደጎች ጻድቃን ናቸው።በአደገም ጊዜ የወላጆቹን ከብቶች የሚጠብቅ እረኛ ሆነ።ሁል ጊዜም የምንኵስና ልብስ ይለብስ ዘንድ በልቡ ይመኝ ነበር። ዐሥራ አራት ዓመትም በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ አነሣሳችው በጎቹንም ትቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ።እየተጓዘም ሳለ ከሩቅ የብርሃን ምሰሶ አየ ወደ ወንዝ እስከ ደረሰ ድረስ ወደ ርሱ ሔደ ከዚህም በኃላ ያ የብርሃን ምሰሶ ከእርሱ ተሰወረ። ያንንም ወንዝ በተሻገረ ጊዜ በሽማግሌ አምሳል ሰይጣን ተገለጠለትና ልጄ ሆይ ዕወቅ ስለ አንተ ልብሱን ቀዶ አባትህን አየሁት እርሱም ያዝናል ያለቅሳል ተመልሰህ የአባትህን ልብ ልትአጽናና ይገባሃል።የዱር አውሬ ነጥቆ የበላህ መስሎታልና አለው። አባ ገዐርጊም ደንግጦ አንድ ሰዓት ያህል ቆመ ከዚህም በኃላ የከበረ ወንጌል ከእኔ ሊሆን አይገባውም ደቀ መዝሙሬም ሊሆን አይችልም ብሏል ብሎ አሰበ።ይህንንም በአለ ጊዜ ሰይጣን እንደ ጢስ ሆኖ ተበተነ።አባ ገዐርጊም ሰይጣን እንደ ሆነ አወቀ በዚያን ጊዜም ያ የብርሃን ምሰሶ ደግሞ ተገለጠለት የእግዚአብሔርም መልአክ በመነኵሴ አምሳል አብሮት ተጓዘ ቅዱሱም መልአኩን ተከተለው እርሱም ከአባ አርዮን ገዳም አደረሰው።አባ ገዐርጊም ከአንድ ጻድቅ ሰው መነኵሴ ጋራ በዚያ ዐሥራ አራት ዓመት ወጥሳይቀምስ ወይን ሳይጠጣ የአትክልት ፍሬም ቢሆን በዚህ በዐሥራ አራት ዓመት ያህል ከሚቀመጥ በቀር አልተኛም። ተጋድሎውንም በጨመረ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና እንዲህ አለው ሥጋህ እንዳይደክም በመካከለኛ ገድል ተጋደል ብሎሃል ጌታ።ከዚህም በኃላ ሊሠራው የሚገባውን ሥርዓት ሠራለት ።ሁል ጊዜም እስከሚመሽ እንዲጾም ትንሽም እንጀራን እንዲበላ ከአራት ሰዓት እስከ መንፈቀ ሌሊት ስለ ሥጋው ዕረፍት እንዲተኛ በቀረው ሌሊት እስቲነጋ ተግቶ እንዲጸልይ። በዚህም ተጋድሎ ብዙ ዘመናት እየተጋደለ በኖረ ጊዜ በበረሀ ውስጥ ብቻውን ሊኖር ወዶ በጫካ ውስጥ እየተመላለሰ ሁለት ዓመት ኖረ።ከዚህም በኃላ ጌታ ተገለጾለት ወደ ቦታው እንዲመለስ አዘዘው።ያን ጊዜም አምላካዊት ኃይል ከከበሩ መክሲሞስና ደማቴዎስ ገዳም አደረሰችው እርሷም ለደብሩ አቅራቢያ ናት። ወደ ደብሩም በተመለሰ ጊዜ በዚያን ወቅት አብርሃም ከዓለም ወደዚያ ገዳም መጥቶ ሁለቱም ተገናኙና በአንድነት ተስማምተው የአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ወደ ሆነ ወደ አባ ዮሐንስ ደረሱ።እርሱም ቦታ ሰጥቷቸው በውስጡ ኖሩ ያ ቦታም እስከ ዛሬ ታውቆ ይኖራል ። ያቺም ዋሻ በግቢግ ትባላለች የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዐለት የሆነ ጣሪያዋን ሠንጥቆ ወደ እነርሱ የወረዳበት ናት ።እነርሱም ሰገዱለት ሰላምታም ሰጥቷቸው አጽናንቷቸው ከእርሳቸው ዘንድ ዐረገ።በዚያችም ጌታችን በወረደበት መስኮት ብርሃንን አዩ እስከ ዛሬም የተከፈተች ሁና ትኖራለች። እሊህ ቅድሳንም ለመነኰሰኘሳት የሚሆን ብዙ ድርሳናትንና ብዙ ተግሣጻትን ደረሱ።ለአባቶቹ የሚታዘዘውንና የሚገዛውን አመሰገኑት።ከዚህም በኃላ አባ አብርሃም ጥር ሁለት ቀን አረፈ።ከእርሱ በኃላም የከበረ አባ ገዐርጊ በዚች በግንቦት ወር በዐሥራ ስምንት ቀን አረፈ።መላ ዕድሜውም ሰባ ሁለት ዓመት ሆነ።በዓለም ዐሥራ አራት ዓመት በምንኩስና ኃምሳ ስምንት ዓመት ነው።ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትሁን አሜን። =>በዚችም ዕለት የሰማዕት ሲኖዳ መታሰቢያው ነው በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። =>አምላከ ገዐርጊ ከቅዱስ መንፈሱ ጸጋ ለኃጥአን ባሮቹ ያድለን:: =>ግንቦት 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱሳን ሐዋርያት ወአርድእት 2.አባ ገዐርጊ ገዳማዊ 3.ቅዱስ ሲኖዳ ሰማዕት =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ 2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን) 3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ 4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ =>+"+ በዓለ ሃምሳም የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ:: ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው:: እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው:: በእያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው:: በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው:: መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር:: +"+ (ሐዋ. 2:1-4) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/zikirekdusn
1080Loading...
05
Photo
1050Loading...
06
📝ታላቁ ቅዱስ ሐዋርያ ዕድሜው 90 ዓመት በሆነው ጊዜ ተሰውሯል። ከዚያ አስቀድሞም የዓለምን ፍጻሜ ተመልክቷል። ዛሬ ያለበትን የየሚያውቅ ቸር ፈጣሪው ነው። 📝ይሕች ዕለት ለሐዋርያው ቅዳሴ ቤቱ ናት። 📝እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲሕ ነው፦ 1. ወንጌላዊ 2. ሐዋርያ 3. ሰማዕት ዘእንበለ ደም 4. አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ) 5. ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት) 6. ወልደ ነጐድጓድ 7. ደቀ መለኮት ወምሥጢር 8. ፍቁረ እግዚእ 9. ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ) 10. ቁጹረ ገጽ 11. ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ) 12. ንስር ሠራሪ 13. ልዑለ ስብከት 14. ምድራዊው መልዐክ 15. ዓምደ ብርሃን 16. ሐዋርያ ትንቢት 17. ቀርነ ቤተ ክርስቲያን 18. ኮከበ ከዋክብት 🤲 በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር። ቅዱስ ዮሐንስን የወደደ ጌታ በፍቅሩ ይጠግነን። ከእናቱ ፍቅር አድርሶ በሐዋርያው በረከት ያስጊጠን። 🤲 🗓 ግንቦት 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ስብከቱና ቅዳሴ ቤቱ) 2.ቅዱስ ኢያሱ ሲራክ ነቢይና ጠቢብ (መጽሐፈ ሲራክን የጻፈ) 3.ቅድስት እናታችን ዐስበ ሚካኤል (ኢትዮዽያዊት) 🗓 ወርኀዊ በዓላት 1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም) 2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት) 3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ   (የቅዱስ ላሊበላ ወንድም) 4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ 5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ 6.አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ 7.አባ ዳንኤል ጻድቅ 📖"በጌታ ኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፡ የእናቱም እህት፡ የቀለዮዻም ሚስት ማርያም፡ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር። ጌታ ኢየሱስም እናቱን፡ ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን 'አንቺ ሆይ! እነሆ ልጅሽ' አላት። ከዚህ በሁዋላ ደቀ መዝሙሩን 'እናትህ እነሁዋት' አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።" (ዮሐ. 19:25) ✨ወስብሐት ለእግዚአብሔር✨ 🔗https://t.me/zikirekdusn
1320Loading...
07
✝ በስመ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ ቅዱስ፡ አሐዱ አምላክ 🗓 ግንቦት 16 የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 🌕 ቅዱስ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ 📝 አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው። ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ፡ በገሊላ አካባቢ አድጐ፡ ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል። 💡ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር። ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው ሕጻን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው። ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል። 📝 ከእርሷ ጋር ለ15 ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ። ስንኩዋን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላዕክትም ማዕረጉ ከፍ አለ። ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል። ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል። ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው። 📝 ቅዱስ ዮሐንስ በታናሽ እስያ ለ7ቱ አብያተ ክርስቲያናት መስበኩ ይታሰባል። ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በሁዋላ ለ70 ዓመታት በዚህ ምድር ሲኖር አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው በኤፌሶን አካባቢ ነው። ሕዝቡን ወደ ክርስትና ለማምጣት በአፍም በመጽሐፍም ደክሟል። 📝3 መልዕክታት፡ ራዕዩንና ወንጌልን ጽፎላቸዋል። ሕይወትን ስለ ሰበከላቸው በፈንታው ብዙ አሰቃይተውታል። ከእሳት እስከ ስለት፡ እስከ መጋዝም በስተእርጅና ደርሶበታል። እርሱ ግን በትእግስቱ ገንዘብ አድርጉዋቸዋል።      ቅዱሱ በኤፌሶን 📝ይህቺ ኤፌሶን የሚሏት ሃገር መገኛዋ በቀድሞው ታናሽ እስያ (አሁን ቱርክ አካባቢ) ሲሆን ብዙ ሐዋርያት አስተምረውባታል። ያም ሆኖ የሚፈለገውን ያህል ለውጥ ያመጣች አልነበረችምና ቅዱስ ዮሐንስ ሊሔድ ተነሳ። 📝ከደቀ መዛሙርቱ መካከልም ቅዱስ አብሮኮሮስን (ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው) አስከትሎ እየጸለዩ በመርከብ ላይ ተሳፈሩ። ሐዋርያት አበው መከረኞች ናቸውና ማዕበል ተነሳባቸው። በጥቂት አፍታም መርከባቸው በማዕበሉ ተበታተነች። ቅዱስ አብሮኮሮስ በስባሪ ላይ ተሳፍሮ ወደ አንዲት ደሴት ደረሰ። ከንጹሑ መምሕሩ ቅዱስ ዮሐንስ ተለይቷልና አለቀሰ። 💡ፍቁረ እግዚእ ግን ያለ ምግብና ውሃ ማዕበለ ባሕር እያማታው ለ40 ቀናት ቆየ። እርሱ በፈጣሪው ፍቅር የተመሰጠ ነበርና አለመመገቡ አልጐዳውም። በ40ኛው ቀን ግን ደቀ መዝሙሩ ወዳለበት ደሴት ማዕበሉ አደረሰው። 2ቱ ቅዱሳን ተፈላልገው ተገናኙ። እጅግም ደስ ብሏቸው ፈጣሪን አመሰገኑ። 📝አምላካቸው ወደዚህች ደሴት ያመጣቸው በጥበቡ ነውና ሲዘዋወሩ 2 ነገርን አስተዋሉ። 1ኛ የደሴቷ ሁሉም ነዋሪ የሚያመልኩት ጣዖትን ነው። 2ኛ አብዛኞቹ የቤተ መንግስት ውላጆች ናቸው። ሮምና የሚሏት አንዲት ሴት ደግሞ እነዚህን ሁሉ እየመገበች ታስተዳድራለች። 📝ቅዱሳኑ በቦታው በቀጥታ ትምሕርተ ወንጌልን ቢናገሩ እንደ ማይቀበሏቸው ስለ ተረዱ ሌላ ፈሊጥን አሰቡ። እንዳሰቡትም ወደ እመቤት ሮምና ቤት ሒደው በባርነት ተቀጠሩ። ለእርሷም "ድሮ የአባትሽ ባሮች የነበርን ሰዎች ነን" ስላሏት 2ቱን ቅዱሳን እሳት አንዳጅና ገንዳ አጣቢ አደረገቻቸው። ለሰማይ ለምድሩ የከበዱ እነዚህ ቅዱሳን የካዱትን ይመልሱ ዘንድ በባርነት ግፍን ተቀበሉ። 📝የመከር (የማሳመኛ) ጊዜ ሲደርስም አንዳች አጋጣሚ ተፈጠረ። ቅዱሳኑ ዮሐንስና አብሮኮሮስ ወደ መታጠቢያ ቤቱ ሲገቡ ሰይጣን በውስጥ ኖሮ ደንግጧልና እወጣለሁ ብሎ ሲሮጥ የንጉሡን ልጅ ረግጦ ገደለው። 📝ሮምናና የአካባቢው ሰዎች ከበው ሲላቀሱ ቅዱሳኑ ቀረቡ። ሮምና ግን በቁጣ "ልትሣለቁ ነው የመጣችሁ?" በሚል ቅዱስ ዮሐንስን በጥፊ መታችው። መላእክት እንኩዋ ቀና ብለው ሊያዩት የሚከብዳቸው ሐዋርያ ይህንን ታገሰ። በጥፊ ወደ መታችው ሴት ቀረብ ብሎም "አትዘኚ! ልጁ ይነሳል" አላትና ጸለየ። ወደ ሞተውም ቀረብ ብሎ በጌታችን ስም አስነሳው። 💡በዚህ ጊዜም ሮምናን ጨምሮ በሥፍራው የነበሩ ሰዎች ለቅዱስ ዮሐንስ ሰገዱ። እርሱ ግን ሁሉንም አስነስቶ ትምሕርተ ሃይማኖትን፡ ፍቅረ ክርስቶስን ሰበከላቸው። በስመ ሥላሴ አጥምቆ፡ ካህናትን ሹሞ፡ ቤተ ክርስቲያንም አንጾላቸው ወጥቷል። በሁዋላም ለሮምናና ለደሴቷ ሰዎች ክታብ (መልዕክትን) ጽፎላቸዋል። ይህች መልዕክት ዛሬ 2ኛዋ የዮሐንስ መልዕክት ተብላ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ትታወቃለች። 📝ቅዱስ ዮሐንስ ቀጥሎ የተጉዋዘው ወደ ኤፌሶን ነው። በዚህች ከተማ የምትመለክ አርጤምስ (አርጢሞስ) የሚሏት ጣዖት ነበረች። አርጤምስ ማለት መልክ የነበራት ትዕቢተኛ ሴት ስትሆን አስማተኛ ባሏ ነው እንድትመለክ ያደረጋት። 📝ቅዱስ ዻውሎስ ብዙ ምዕመናን ከእርሷ እንዲርቁ ማድረግ ችሏል። ጨርሶ ያጠፋት ግን ቅዱስ ዮሐንስ ነው። በቦታውም ብዙ ግፍ ደርሶበት፡ በርካታ ተአምራትን አድርጉዋል። ቤተ ጣዖቱንም በተአምራት አፍርሶታል። የፍቅር ሐዋርያ 📝ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን 'የፍቅር ሐዋርያ' ትለዋለች። ለ70 ዘመናት በቆየ ስብከቱ ስለ ፍቅር ብዙ አስተምሯል። ፍቅርንም በተግባር አስተምሯል።  በየደቂቃውም "ደቂቅየ ተፋቀሩ በበይናቲክሙ - ልጆቼ ሆይ! እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ" እያለ ይሰብክ ነበር። 💡በተለይ ደግሞ ከፈጣሪው ክርስቶስ ጋር የነበረው ፍቅር ፍጹም የተለየ ነበር። በዚህ ምክንያትም ጌታ ባረገ ጊዜ እንዲህ ብሎታል፦ "ለፍጡር ከሚገለጥ ምሥጢር ከአንተ የምሠውረው የለኝም" ብሎታል:: ቀጥሎም በንጹሕ አፉ ስሞታል። ሊቁ፦ "ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዓሞ፡ ንጽሐ ኅሊናሁ ወልቡ ለዐይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ" እንዳለው። (መልክዐ ኢየሱስ) 📝ቅዱስ ዮሐንስ ከእመቤታችንም ጋር ልዩ ፍቅር ነበረው። እርሷ እንደ ልጇ ስትወደው፡ እርሱ ደግሞ እንደ እናቱ ልቡ እስኪነድ ድረስ ይወዳት ነበር። እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ ተከትሎ ያገኛት እመቤቱ ናትና። 📝ከዚያ ሁሉ ጸጋና ማዕረግ የመድረሱ ምሥጢርም ድንግል ናት። ለ15 ዓመታት በጽላሎተ ረድኤቷ (በረዳትነቷ ጥላ) ተደግፎ አብሯት ሲኖር ብዙ ተምሯል። ከመላእክትም በላይ ከብሯል። ከንጽሕናዋ በረከትም ተካፍሏል። 📝ስለ ድንግል ማርያምም "ነገረ ማርያም" የሚል ድርሰት ሲኖረው "የሰኔ ጐልጐታንም" የጻፈው እርሱ ነው። ድንግል ባረፈችበት ቀንም ልክ እንደ ልጇ ክርስቶስ እርሷም ስማው፡ ታቅፋው ዐርፋለች። ሊቃውንቱ ለዚህ አይደል በንጹሕ ከንፈሮቿ መሳምን (መባረክን) ሲሹ፦ "በከመ ሰዓምኪ ርዕሰ ዮሐንስ ቀዳሚ፡ ስዒሞትየ ማርያም ድግሚ" ያሉት።
1281Loading...
08
በቅርብ ቀን ...
1640Loading...
09
ስለ ሥራው ሁሉ እግዚአብሔርን አመሥግኑ ፩ኛ ተሰሎንቄ ፭፥፲፰ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በቅድሚያ የከበረ መንፈሳዊ ሰላምታችንን እያቀረብን በሰንበት ትምህርት ቤታችን ዘውትር ሐሙስ እንዲሁም በልዩ ልዩ አጋጣሚዎች ወደ አምላካችን የምንጸልያቸውን የጸሎት ክፍሎች በአንድ ላይ ያካተተ የጸሎት ጥራዝ በህትመት ላይ ይገኛል። ☘☘☘☘☘☘☘ በዚህ የበረከት ሥራ ውስጥ ለመሳተፋ የምትፈልጉ እንዲሁም ቃል የገባችሁ አባላትና የገብረ መንፈስ ቅዱስ ወዳጆች ......... አንድ ጥራዝ በግላችሁ በማሳተም ከጸሎት በረከት ተካፋይ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ✨✨✨✨✨✨✨ በዚህ ሥራ ውስጥ የሚሳተፉ አባላት ሥመ ክርስትና ዘወትር በሰንበት ት/ቤቱ የጸሎት መርሐ ግብር ላይ የሚታሰብ ይሆናል። ለበለጠ መረጃ +251940252987                                       +251973406517 ሥነ-ሥርዓትና ግንኙነት ክፍል
1660Loading...
10
🕊መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስኅ ግቡ🕊 (ማቴ ፫:፫) ✨በአማን ተንሥአ መድኃኒነ!✨ 🌿ብፁዕ አባ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘኤለ ገዳማተ እምኀበ እግዚኡ ይነሣእ እሴተ ቦአ ሀገረ ደብረ ሊባኖስ በፍሥሐ ወበሰላም። ⚜ሰአል ለነ ጊዮርጊስ ኀበ እግዚአብሔር ወጸሊ በእንቲአነ ሐረድዎ ወገመድዎ ወዘረዉ ሥጋሁ ከመ ሐመድ ወወሰድዎ ኀበ ሰብአ ነገሥት ረገጸ ምድረ አንሥአ ሙታነ አባ ጊዮርጊስ በሰላም ዐደወ መንግሥተ ክብር ወረሰ። 🌿ወልደ እግዚአብሔር አምላክነ ወመድኃኒነ ዕቀብ  ሕይወተነ እም ገሀነመ እሳት ወእምኵሉ መንሱት በእንተ ቅዱስ ስምከ ወበእንተ ማርያም እምከ ወበእንተ ቅዱስ መስቀል ወበእንተ ዮሐንስ ወንጌላዊ ወበእንተ ዮሐንስ መጥምቅከ ወበእንተ ኵሎሙ ቅዱሳን ወሀባ ሰላመ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ ወለቅድስት ቤተክርስቲያን። ⚜ሰላም ለክሙ ጻድቃን ወሰማዕት እለ አዕረፍክሙ በዛቲ ዕለት መዋዕያነ ዓለም አንትሙ በብዙኅ ትዕግሥት። ሰአሉ ቅድመ ፈጣሪ በኩሉ ሰዓት እንበለ ንስሐ ኪያነ ኢይንሣእ ሞት። 🌿አንቅሐኒ በጽባሕ ክሥተኒ ዕዝንየ በዘአጸምእ አምላኪየ አምላኪየ እገይሥ ኀቤከ ዘይሰማዕ ግበር ሊተ ምሕረተከ በጽባሕ" ⚜ነቢያት ወሐዋርያት፥ ጻድቃን ወሰማዕት፤ ደናግል ወመነኮሳት፥ አዕሩግ ወሕጻናት፤ ገዳማውያን ወሊቃውንት፤ ሰአሉ ለነ ኲልክሙ፥ ቅድመ መንበሩ ለጸባኦት። 🌿እግዝእትየ ፍትሕኒ እማዕሠሩ ለሰይጣን፤ እሙ ለመድኅን ወለተ ብርሃን። ✝ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር 🌿ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ታሪክ እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል) 🌿አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር) 🔗https://t.me/zikirekdusn ▶️https://www.youtube.com/@ZikereKedusan 🔰🛑ግእዝ ለመማር  https://t.me/lisanegeez5
1600Loading...
11
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ከቅዱሳን_ባሕታውያ_ጋር በአንድ ወቅት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፡-ከዕለታት አንድ ቀን በሀገረ ስብከቴ ሥር በነበሩ በሜዲትራኒያን ባሕር በሚገኙ ደሴቶች ውስጥ የሚኖሩ ምእመናንን ለመጎብኘት አሰብሁ፡፡ ከእኔ ጋር ቀሳውስትንና ዲያቆናትን አስከትዬ በጀልባ ተሳፍሬ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ተጓዝሁ፡፡ በደሴቱ ውስጥ ስንዘዋወር የሰው ዱካ ብንመለከትም ምንም ሰው ማየት አልቻልንም ነበር፡፡ በአሸዋው ላይ ታትሞ የነበረውን የሰው ዱካ ተከትለን ስንጓዝ ካልተፈለፈሉ ዐለቶች የተሠራ ቤተ ክርስቲያን የሚመስል ዋሻ ላይ ደረስን፡፡ ዋሻው በርም ሆነ መስኮት የለውም፡፡ ወደ ውስጥ ስንገባ ልክ እንደ ሰባቱ ደማቅ ከዋክብት እጅግ በጣም አንጸባራቂ ብርሃን ቆመው ከሚጸልዩ ሰባት አባቶች ዘንድ ሲወጣ ተመለከትን፡፡ እኛም ከእነርሱ ጋር ለመጸለይ ባለንበት ቆምን። አባቶች ጸሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ ወደ እኛ ዞሩና በፊቴ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰገዱ። በመቀጠልም ሰላምታ ሰጡን፡፡ እኔ ዮሐንስም ‘እኔ አባታችሁና ፓትርያርካችሁ ዮሐንስ ነኝ’ አልኳቸው፡፡ ቅዱሳኑ እንደገና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በፊቴ ሰገዱ እና እኔን ደካማውን እንዲህ አሉኝ፡- “የምንወደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትባርከንና እኛም አንተን በማየት እንድንበረታ ወደዚህ አመጣህ” አሉ። እኔም “እባካችሁ ታሪካችሁን ንገሩኝ” አልኋቸው፡፡ ሰባቱ አባቶችም “ከብዙ ዓመታት በፊት ሰባታችንም ከቍስጥንጥንያ ወጥተን በአንድነት ተሰባስበን ሕይወታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና በአምልኮ ብቻ ለማሳለፍ ወደዚህ ደሴት መጣን፡፡ ከዚህ ደሴት በደረስንበት ዕለት ከባሕሩ ከሚመጣው አስቸጋሪ ነፋስ ራሳችንን ለመከላከል ዋሻዎችን ለመገንባት ዐለቶችን ሰበሰብን፤ በሁለተኛው ቀን ደግሞ ይህን ቤተ ክርስቲያን መሥራት ጀመርን፡፡ በዐለቶች መካከል ከሚበቅለው ሣር እንበላለን፤ ውኃም ከባሕሩ እንጠጣለን፡፡ ቤተ ክርስቲያኑን የከበቡትን እነዚህን የአሸዋ ክምሮች ለማስወገድ ፈልገን ነበር፤ ግን አእምሯችንና አሳባችን ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ስለተያዘ ጊዜ አጣን” በማለት ታሪካቸውን ነገሩኝ። እኔም “መንፈሳዊ አባታችሁ የት ነው?” ብዬ ጠየቅኋቸው፡፡ ይህን ጥያቄ ከመጠየቄ ወዲያውኑ አንድ ሽማግሌ በትሩን ተደግፎ ወደ እኔ ቀረብ አለና “እኔ የአንተ አገልጋይ ነኝ” አለኝ፡፡ አረጋዊው ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ ራቁቱን ነበረና “ሰውነትህን የምትሸፍንበት ትንሽ ልብስ ትፈልጋለህ?” ስለው እሱም “ጌታ ከክረምቱ ቅዝቃዜ፣ ከበጋው ሙቀት ይከላከልልናል፤ ይጠብቀናልም” በማለት መለሰልኝ፡፡ “ምግብ ያስፈልጋችኋል?” ብዬ ስጠይቀው እርሱም “የሚበቃንን ያህል ከእነዚህ ዕፅዋት እንመገባለን ከዓለም የሆነ ምንም ነገር አያስፈልገንም” በማለት መለሰልኝ፡፡ እኔም “አባቶቼ እባካችሁ ለእኔ እና ስለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ጸልዩ” አልሁት። የእነዚያን ቅዱሳን ባሕታውያን አባቶች በረከት ከተቀበልን በኋላ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለም ምሥጋና የሚገባውን የምንወደውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እያመሰገንን ወደ መጣንበት ተመለስን” ይለናል ቅዱሱ አባታችን ዮሐንስ አፈ ወርቅ። ምንጭ፦ ግሑሣን አበው
2570Loading...
12
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ግንቦት 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +°✝ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ✝°+ =>ለቤተ ክርስቲያን የብርሃን ምሰሶ ስለሆነላት ስለ ታላቁ ሐዋርያዊ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? እንደ እኔ ያለ ኃጥእ: ለባሴ ሥጋና ገባሬ ንስሃ ስለሱ ሊናገር አይቻለውምና:: አባቶቻችን እንደ ነገሩን ስለ አፈ ወርቅ ለመናገር አፈ ወርቅ መሆን ያስፈልጋል:: ግን እስኪ በቅዱሱ አባት ምልጃ ጥቂት ልሞክር:: << ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው? >> +ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ:: እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ አደገ:: ገና በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና) ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል:: +ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮችም አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ በመንፈሳዊ ትምሕርት ይህ ቀረህ የማይሉት ሊቅ የሆነው ገና በ15 ዓመቱ ነበር:: በ2 ወገን የተሳለ ሰይፍ በመሆኑ ስንኳን በሕይወተ ሥጋ እያለ ዛሬም ለንፉቃን ትልቅ የራስ ምታት ነው:: +ቅዱሱ ገና በ16 ዓመቱ ሃብት: ንብረት: ውበት: ክብርና እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበርሃ ሲኖር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጡ:: ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት:: +ከዚህች እለት በኋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራዕየ ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጉዋሜ ተነተናቸው:: በተለይ ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው ሳይታክት: ንጹሕ እጆቹ ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት: መልዕክታትና ትርጉዋሜያት ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ አንክሮ ይገባል! የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና ለጋ: ማዕርጉም ዲቁና ነበር:: +ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው ወደውታልና የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: አፈ ወርቅ ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኳን የሚያወራ ኮሽ የሚል የለም:: ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ በተደሞ ይሰሙት ነበር:: +ሲያስተምር ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር:: አንዴም እመቤታችን በሕዝብ መካከል " አፈ-ወርቅ" ብላ ጠርታዋለች:: ለዛም ነው አፈ-ወርቅ የሚባለው:: ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ 10 ዓመት አቁሞታል:: +ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: +በተሰደደበት ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ/ ም አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ:: +አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ አርቃድዮስ ግብር አገባ (ግብዣ አዘጋጀ):: በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ ታጥቆ ሲጸልይ ሳለ: አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ ከሰማይ 12ቱ ሊቃነ መላእክት (እነ ቅዱስ ሚካኤል) በግርማ ሲወርዱ ተመለከተ:: +ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ: ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንገለጥልኝ መርቁኝ" አላቸው:: ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን ቀጠሉ:: +በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ: መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ ነበር እንጂ አልበላም:: ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ" ብሎ በጉባኤ መካከል ጠየቀው:: +"ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ አመ ወለደት ወለደ ዘበኩራ-የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም' ማለቱ (ማቴ. 1:25) ስለ ምን ነው?" ቢለው ቅዱሱ ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ይተረጉምለት ጀመር:: +"ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ ይቀያየራል:: እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ መለኮቱ ሲለዋወጥ መልኳ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር:: +'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው' እያለ ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በኋላ ግን አንድ ሕብረ መልክ ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች አላወቀም:: +አሁን ግን እርሷም ወላዲተ አምላክ: ልጇም አምላክ ዘበአማን መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም ሰምተው ሁሉም ሲያደንቁ: በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ "አፈ ወርቅ! ልሳነ ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች:: +ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ! እሰግድ ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት:: ይህንን ምስጋናም ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው እያደነቁ ወደ ሰማይ ወጥተዋል:: +ሊቁ ባረፈ በ35 ዓመቱ: በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን: ሥጋው ፈልሷል:: ወደ ቁስጥንጥንያ ሲደርስም ከናፍቆት የተነሳ ታላቅ ዝማሬና እንባ ተደርጓል:: አፈ ወርቅም ቀና ብሎ ሕዝቡን ባርኳል:: ✔ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው:- *ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ *አፈ በረከት *አፈ መዐር (ማር) *አፈ ሶከር (ስኳር) *አፈ አፈው (ሽቱ) *ልሳነ ወርቅ *የዓለም ሁሉ መምሕር *ርዕሰ ሊቃውንት *ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ) *ሐዲስ ዳንኤል *ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው) *መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ *ጥዑመ ቃል - - - +እግዚአብሔር ከቅዱሱ በረከት አብዝቶ: አብዝቶ: አብዝቶ ይክፈለን:: +ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥጋቸው ፈልሷል:: ይሕ የተደረገው ጻድቁ ከረፉ ከ56 ዓመታት በኋላ ነው:: በዕለቱም ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተፈጽመዋል:: +እናታችን ርሕርሕቷ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ደግሞ በዚሕ ቀን ስሟን ለጠራና መታሠቢያዋን ላደረገ የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች:: ❖ቸር አምላካቸው ከሁለቱም ብሩሃን ቅዱሳኑ ክብር ያድለን::
2412Loading...
13
ያሬድ ነጎድጓድን ..ከደመናት ተውሶ ዜማን ....ከመላዕክቱ ማዕድ ቆርሶ ብስራትን ...ከገብርኤል ቀንሶ የሚካኤልን ሰይፍ... ተንተርሶ ያሬድ በልሳኑ እያዜመ ...በልቡ እየተቀኘ የድጓውን ባህር ቀዝፎ...በቅኔው ማዕበል እየዋኘ ከላይ....ከመላዕክቱ ነጥቆ ምድርን ..በዜማ ሰንጥቆ በመወድሱ ጎርፍ ...አጥለቅልቆ በዝማሬው ሰረገላ ...አምጥቆ መሬት ላይ አንስቶ...ከሰማይ ያደረሰን ከመላዕክቱ ጋር አቁሙ...ግዕዝና ዕዝል ያዘመረን አራራይ ብሎ በርህራሔ...በዝማሬ ሲቃ ያስለቀሰን ያሬድ ዋይ ዜማ እያለ....ዋይታን አጥፍቶ ዋይታ ልቅሶአችን ቀይሮ...ዋይ ዜማ ዝማሬን ተክቶ እንደ መላእክቱ አርቅቆ እንደ ሰውም አድምቆ ሰማይና መሬት አስተባብሮ ከመላእክቱ ጋር ደምሮ "ሃሌ ሉያ" ብሎ አዘምሮ በዜማ ቁልፉ ከፍቶ...በቅኔው በትር ገልጦ አሳየን ከላይ እግዜርን...ከዜማ ወንበር ላይ አስቀምጦ ያሬድ ኢትዮጵያ ላይ... የቆመ የዜማ ብርሃን ሻማ ጥበብን ያገኘንበት ...የመስፈሪያው አውድማ ይህ ነው ብርሃን የአለሙ...ኢትዮጵያዊ ነው ቀለሙ ከያሬድ በተጨማሪ..."ምድራዊ መልአክ" ነው ስሙ Moges Hunyalew
2143Loading...
14
ኢትዮጵያ ከመላእክት ጋር የሚዘምር ማሕሌታዊ ከካህናተ ሰማይ ጋር የሚያጥን ካህን የምታፈራ ሀገር ናት። ለሰማይ አገልጋዮችን ገና ሳይሞቱ የምትልክ፣ ከተዋጊዎች መካከል ወደ ድል ነሺዎች መልእክተኛ የምትልክ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ያለች ናት? ቅዱስ ያሬድ በትሕትናው ከትል ተማረ። ትሑታንን ከፍ የሚያደርግ ፈጣሪም ከፍ አደረገውና ከመላእክት ጋር ዘመረ። ትልዋን ከዛፍ አውርዶ ቢጨፈልቃት ኖሮ ለአንድ ሺህ አምስት መቶ ዓመታት ያልነጠፈው የምስጋና ጅረት በሀገራችን ባልፈሰሰ ነበር። ኃይል አለኝ ብለህ የምትጨፈልቃቸው ትሎች ሰማይ የሚያደርሱህ መምህራኖችህ እንዳይሆኑ ተጠንቀቅ ይላል የታሪኩ ተግሣፅ። ቅዱስ ያሬድ እግሩን በጦር እየተወጋ እንኩዋን ዝማሬው ሰማያት ወስዶት አልተሰማውም ነበር። የእኛው ሲላስ የእኛው ጳውሎስ ቅዱስ ያሬድ ሆይ በዘመርክባት ሀገርህ ዛሬ ብዙ ጦር ተሰክቶባታል። ከአንተ ዜማ በቀር ዛሬም መጽናኛ የለንምና በምልጃህ አስበን። ጥዑመ ልሳን ያሬድ: ሊቀ ጠበብት ያሬድ: ሊቀ ሊቃውንት ያሬድ የቤተ ክርስቲያን ጌጥ!! (Deacon Henok Haile)
2693Loading...
15
#ግንቦት_11 #ቅዱስ_ያሬድ_ካህን_ወማኅሌታይ ግንቦት ዐሥራ አንድ በዚህች ዕለት የሱራፌል አምሳላቸው የሆነ ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ ያሬድ የተሰወረበት ነው። ይህም ቅድስ ከአባ ጌዴዎን ዘመዶች ወገን ነው እርሱም በኢትዮጵያ አገር ከታነፁ አብያተ ክርስቲያን ለምትቀድም ከአክሱም ካህናት ውስጥ ነው እርሷም አስቀድሞ የክብር ባለቤት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት በውስጥዋ የተሰበከና አምላክን በወለደች በእመቤታችን በከበረች ድንግል ማርያም ስም የከበረች ናት። ይህም አባ ጌዴዎን ትምህርትን ሊአስተምረው በጀመረ ጊዜ መቀበልም ማጥናትም እስከ ብዙ ዘመን ተሳነው። በአንዲት ዕለትም መምህሩ በእርሱ ላይ ተበሳጭቶ መትቶ አሳመመው። ያሬድም ሸሽቶ ከዱር ውስጥ ገባ ከኀዘኑም ብዛት የተነሣ ከዛፍ ሥር ተጠለለ። ወደ ዛፉ ላይም ትል ሲወጣ አየ ትሉም ከዛፉ እኩሌታ ደርሶ ይወድቅ ነበረ እንዲሁም ብዙ ጊዜ ከአደረገ በኋላ በጭንቅ ከዛፉ ላይ ወጣ። ቅዱስ ያሬድም የትሉን ትጋት በአየ ጊዜ ወደ መንፈሳዊ መምህሩ ተመልሶ አባቴ ሆይ ይቅርታ አድርግልኝና እንደ ወደድክ አድርገኝ አለው መምህሩም ተቀበለው። ከዚህ በኋላ በብዙ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር በለመነ ጊዜ ልቡናው ብሩህ ሆኖለት በአጭር ጊዜ የብሉይና የሐዲስ መጻሕፍትን ተምሮ ፈጸመ ዲቁናም ተሾመ። በዚያም ወራት እንደ ዛሬ በከፍተኛ ቃል የመዝሙር ማኅሌት የለም ነበር በትሑት እንጂ። እግዚአብሔርም መታሰቢያ ሊአቆምለት በወደደ ጊዜ ከኤዶም ገነት ሦስት አዕዋፍን ላከለት እነርሱም በሰው አንደበት ተናግረውት ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ከእሳቸው ጋራ አወጡት በዚያም ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የሚያመሰግኑበትን ማኅሌታቸውን ተማረ። ወደ አነዋወሩ ወደ ምድርም በተመለሰ ጊዜ በአክሱም ዳር ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን በሦስት ሰዓት ገባ በታላቅም ቃል ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ የጽዮንም ደገኛዋ ሰማይን ፈጠረ። ዳግመኛም እንዴት እንደሚሠራት የድንኳንን አሠራር ለሙሴ አሳየው አስተማረው አለ። ይቺንም ምስጋና አርያም ብሎ ጠራት። የቃሉንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ንጉሡም ንግሥቲቱም ጳጳሱም ከካህናቱ ሁሉ ጋራ የመንግሥት ታላቆችና ሕዝቡ ሁሉ ወደርሱ ሮጡ ሲሰሙትም ዋሉ። ከዚያም በኋላ ከዓመት እስከ ዓመት በየክፈለ ዘመኑ በክረምትና በበጋ በመጸውና በጸደይ በአጽዋማትና በበዓላት በሰንበታትም እንዲሁም በመላእክት በዓል በነቢያትና በሐዋርያት በጻድቃንና በሰማዕታት በደናግልም በዓል የሚሆን አድርጎ በሦስቱ ዜማው ሠራ ይኸውም ግዕዝ ዕዝል አራራይ ነው። የሰው ንግግር የአዕዋፍ የእንስሳትና የአራዊት ጩኸት ከዚህ ከሦስቱ ዜማው አይወጣም። በአንዲት ዕለትም ቅዱስ ያሬድ ከንጉሥ ገብረ መስቀል እግር በታች ቁሞ ሲዘምር ንጉሡም የያሬድን ድምፅ እያዳመጠ ልቡ ተመሥጦ የብረት ዘንጉን በያሬድ እግር ላይ ተከለው ከእርሱም ደምና ውኃ ፈሰሰ። ያሬድም ማኅሌቱን እስከ ሚፈጽም አልተሰማውም። ንጉሡም አይቶ ደነገጠ በትሩንም ከእግሩ ላይ ነቀለ ስለ ፈሰሰው የደምህ ዋጋ የፈለግኸውን ለምነኝ ብሎ ለያሬድ ተናገረው ያሬድም ላትከለክለኝ ማልልኝ አለው። ንጉሥም በማለለት ጊዜ ወደገዳም ሔጄ እመነኲስ ዘንድ አሰናብተኝ አለው ንጉሡም ሰምቶ ከመኳንንቱ ጋራ እጅግ አዘነ ተከዘም እንዳይከለክለውም መሐላውን ፈራ እያዘነም አሰናበተው። ከዚህ በኋላም ቅዱስ ያሬድ ወደ ቤተክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት ቆሞ ፈጽሞ የከበረሽና የተመሰገንሽ ከፍ ከፍም ያልሽ የብርሃን መውጫ የሕይወት ማዕረግ የሆንሽ የሚለውን ምስጋና እስከ መጨረሻው በተናገረ ጊዜ ክንድ ያህል ከምድር ከፍ ከፍ አለ። ከዚህ በኋላ ወደ ሰሜን አገር ሒዶ በጾም በጸሎት ተወስኖ ሥጋውን እጅግ እያደከመ ኖሮ ገድሉን በዚያ ፈጸመ። እግዚአብሔር ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጥቶታል። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባታችን ያሬድ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት)
1962Loading...
16
ሰላመ እግዚአብሄር ከናንተ ጋር ይሁን ከላይ 👆ይተለቀቁትን መዝሙሮችህ ለ ዝክረ ያሬድ የዝማሬ ምሽት 🙏🏼እንዘጋጅባቸው
2221Loading...
17
Media files
2883Loading...
18
Media files
2886Loading...
19
Media files
2375Loading...
20
Media files
2145Loading...
21
Media files
1935Loading...
22
Media files
2156Loading...
23
Media files
2165Loading...
24
Media files
2216Loading...
25
@kaletsidkizm
2376Loading...
26
††† እንኳን ለእናታችን ቅድስት እሌኒ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† እሌኒ ንግሥት ††† ††† ቅድስት እሌኒ የታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ እናቱና እግዚአብሔር ለበጐ አገልግሎት የጠራት ቡርክት ሴት (ንግሥት) ናት:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- የቅድስቲቱ ሃገረ ሙላዷ ሮሃ (ሶርያ) አካባቢ ነው:: ነገዷ ከእሥራኤል ዝርዋን እንደሆነም ይነገራል:: ጣልያኖች "Helena" : በእንግሊዝኛው "Helen" ይሏታል:: እኛ ደግሞ "እሌኒ" እንላታለን:: ትርጓሜው "ጥሩ ምንጭ" : አንድም "ውብና ደግ ሴት" ማለት ነው:: ቅድስት እሌኒ በመልካም ክርስትና አድጋ እንደ ቤተ ክርስቲያን መተርጉማን ተርቢኖስ የሚባል ነጋዴ አግብታ ነበር:: ወቅቱም ዘመነ ሰማዕታት ነበር:: በማይሆን ነገር ጠርጥሮ ባሕር ላይ ጥሏት ንጉሥ ቁንስጣ አግኝቷታል:: እርሱም የበራንጥያ (የኋላዋ ቁስጥንጥንያ) ንጉሥ ነበር:: ቅድስት እሌኒ ከቁንስጣ የተባረከ ልጅን ወለደች:: ቆስጠንጢኖስ አለችው:: በልቡናው ፍቅርን : ርሕራሄን : መልካምነትን እየዘራች አሳደገችው:: ቅዱሱ አባቱ በሞተ ጊዜ ተተክቶ ነገሠ:: ቅድስት እሌኒንም ንግሥት አደረጋት:: ያንን የአርባ ዓመት ግፍ በአዋጅ አስቀርቶ ለክርስቲያኖች ነፃነትን : ክብርን በይፋ ሰጠ:: አንድ : ሁለት ብለን የማንቆጥረውን ውለታ ለምዕመናን ዋለ:: ከነዚህ መልካም ምግባራቱ ጀርባ ታዲያ ቅድስት እናቱ ነበረች:: ቅድስት እሌኒ ጾምን : ጸሎትን ከማዘውተሯ ባሻገር አጽመ ሰማዕታትን ትሰበስብ : አብያተ ክርስቲያንን ታሳንጽ : ለነዳያንም ትራራ ነበር:: በኢየሩሳሌምና አካባቢው ብቻ ከሰማንያ በላይ አብያተ መቃድስ አሳንጻለች:: እነዚህንም በወርቅና በእንቁ ለብጣቸዋለች:: በዘመኗ መጨረሻም የጌታችንን ቅዱስ ዕፀ መስቀል ከተቀበረበት አውጥታ ለዓለም በረከትን አስገኝታለች:: እናታችን ቅድስት እሌኒ እንዲህ በቅድስና ተመላልሳ በሰማንያ ዓመቷ በ330ዎቹ አካባቢ ዐርፋለች:: ቤተ ክርስቲያናችንም ስለ ቅድስናዋና ውለታዋ በዓል ሠርታ : ታቦት ቀርፃ ስታከብራት ትኖራለች:: ††† ከቅድስት እናታችን ምልጃና በረከት አምላካችን ያድለን:: ††† ግንቦት 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅድስት እሌኒ ንግሥት 2.ቅዱስ ስልዋኖስ ††† ወርኀዊ በዓላት 1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት) 2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮጵያዊ) 3.ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ) 4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን 5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮጵያዊ) 6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት) ††† "ነገር ግን ለበጐ ነገር ጥበበኞች : ለክፉትም የዋሆች እንድትሆኑ እወዳለሁ:: የሰላምም አምላክ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል:: የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን::" ††† (ሮሜ. ፲፮፥፲፱) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† https://t.me/zikirekdusn
2142Loading...
27
ለዝክረ ቅዱስ ያሬድ የሚዘመሩ መዝሙራት
2130Loading...
28
Media files
2273Loading...
29
Media files
2041Loading...
30
Media files
1891Loading...
31
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ግንቦት 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✝✞✝ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ✝✞✝ =>በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሐዋርያት ቀጥሎ የቅዱስ አትናቴዎስን ያሕል ስለ ሃይማኖት የተዋጋ ቅዱስ ፈልጐ ማግኘት አይቻልም:: ❖ቅዱስ አትናቴዎስ ማን ነው? +ቅዱስ አትናቴዎስ በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት በዘመነ ሰማዕታት መጠናቀቂያ በ300 አካባቢ(296) እስክንድርያ ግብፅ ውስጥ ነው የተወለደው:: ወላጆቹ አረማውያን በመሆናቸው ክርስትናን አልተማረም ነበር:: +ሕጻን እያለ ለጭዋታ ከቤቱ ሲወጣ የክርስቲያን ልጆች ሃይማኖታዊ ጨዋታ ሲጫወቱ ተመለከተ:: ሊቀላቀላቸው ቢፈልግም ክርስቲያን ባለመሆኑ ከለከሉት:: አትናቴዎስም ክርስቲያን ልሁንና አጫውቱኝ ብሏቸው እሺ ስላሉት ሕጻናቱ ዕጣ ተጣጣሉ:: +ላንዱ ቄስ: ላንዱም ዲያቆን መሆን ሲደርሳቸው ለአትናቴዎስ ፓትርያርክ መሆን ስለ ደረሰው ሌሎቹ ሕጻናት ይሰግዱለት ጀመር:: በአጋጣሚ ሕጻናቱ ይሕንን ሁሉ ሲያደርጉ የወቅቱ ፓትርያርክ ቅዱስ እለ እስክንድሮስ በመገረም ያያቸው ነበርና ለሕጻኑ አትናቴዎስ ትንቢት ተናገረለት:: +ከዚያም የአትናቴዎስ አባቱ ሲሞት ሊቀ ዻዻሳቱ ከእናቱ ወስዶ አጥምቆ: የሚገባውን መንፈሳዊ ትምሕርት ሁሉ በልቡናው ላይ ቀረጸበት:: ከዚሕ በኋላ ዲቁናን ሹሞ አስተምር አለው:: ምንም ሕጻን ቢሆንም ከሊቅነቱ: ከአመላለሱና ከአንደበቱ ጣፋጭነት የተነሳ የሰማው ሁሉ ይደነቅ ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ አድራለችና:: +ቅዱስ አትናቴዎስ ሊቀ ዲቁና በተሾመ ወራት አርዮስ ቤተ ክርስቲያንን በመረበሹ ኒቅያ ላይ 318ቱ ሊቃውንት ሲሰበሰቡ ጸሐፊ አድርገው ሾሙት:: በጊዜውም በዕድሜ የስንት ጊዜ ትልቁ የሚሆነውን አርዮስን ተከራክሮ ምላሽ አሳጣው:: ✝ቅዱስ አትናቴዎስ ከሊቃውንቱ ጋር ሆኖ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: እግዚአብሔር መሆኑን በአደባባይ መሠከረ:: ጸሎተ ሃይማኖትንም ያረቀቀው እርሱ ነው:: +ከዚሕ በኋላ የእስክንድርያ (የግብፅ) 20ኛ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ:: ቤተ ክርስቲያንን በመልካም እረኝነት ለ48 ዓመታት ሲመግብ ብዙ መከራዎችን ተቀበለ:: ለ5 ጊዜ ከመንበሩ አፈናቅለው ወደ በርሃ ሲያግዙት በስደት ከ15 ዓመታት በላይ አሳልፏል:: +በተሰደደባቸው ቦታዎች መከራን እየተቀበለ ያላመኑትን አሳምኗል:: በጎቹ እንዳይባዝኑበት ደግሞ በጦማር (በደብዳቤ) ይጠብቃቸው ነበር:: ዛሬ በሃይማኖተ አበው የምናገኘው ቃለ ሃይማኖት በዚሕ ዘመን የተጻፈ ነው:: +በወቅቱ የነበረው ንጉሥ (ትንሹ ቆስጠንጢኖስ) የአባቱን (ታላቁ ቆስጠንጢኖስን) ዕረፍት ተከትሎ ነገሠ:: +ወዲያውም አርዮሳዊ መናፍቅ ሆነ:: ሃይማኖታቸው የቀና አባቶችንም ያሳድድ ገባ:: ከአበው ቅዱሳን መካከል ግን የዚህ መከራ ቀዳሚው ገፈት ቀማሽ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ አንትናቴዎስ ነበር:: +በተለይ አንድ ጊዜ ንጉሡ ቅዱሱን ወደ በርሃ አግዞ: መናፍቅ ዻዻስ በግብጽ ሹሞ: ብዙ ክርስቲያኖችን በግፍ ሲያስገድል: ቅዱሱን ለ6 ዓመታት አሰቃየው:: የወገኖቹ (የልጆቹን) ስቃይ የሰማው ቅዱስ አትናቴዎስ ግን በድፍረት ወደ ቤተ መንግስት ገብቶ ተናገረው:: +2 አማራጭን አቅርቦ "ወይ ግደለኝና እንደ አባቶቼ ሰማዕት ልሁን: ካልሆነ ግን ወደ መንጐቼ (ምዕመናን) መልሰኝ" አለው:: መናፍቁ ንጉሥም ቢገድለው ብጥብጥ እንደሚነሳ ስለሚያውቅ በስልት ሊያጠፋው ወሰነ:: +ቀዛፊ: መቅዘፊያ: ምግብና ውሃ በሌላት ጀልባ ውስጥ ከቶም ሜዲትራኒያን ባሕር ውስጥ ጣለው:: ድንገት ግን ከሰማይ ጌታችን መላእክቱን አስከትሎ ወረደ:: +ሚካኤልና ገብርኤል ባሕሩን እየቀዘፍ: ሌሎች መላእክት እየመገቡት በዚህች ቀን እስክንድርያ (ግብጽ) አድርሰውት ተሠውረዋል:: ሕዝቡም በታላቅ ሐሴት እየዘመሩ አባታቸውን ተቀብለውታል:: +ሐዋርያዊው ቅዱስ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋግቶ: ብዙ ስቃይንም ተቀብሎ በ373 ዓ/ም አካባቢ አርፏል:: ቤተ ክስርቲያን ☞"ሊቀ ሊቃውንት: ☞ርዕሰ ሊቃውንት: ☞የቤተ ክርስቲያን (የምዕመናን) ሐኪም (Doctor of the Church): ☞ሐዋርያዊ" ብላ ታከብረዋለች:: =>አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሊቁ በረከት አይለየን:: በምልጃውም ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን:: =>ግንቦት 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ 2.የባሕታውያን አለቃ ታላቁ አባ ሲኖዳ (ጽንሰቱ) 3.ቅዱስ ዮሐንስ ጻድቅ (ሃብቱን: ንብረቱን: ልብሱን ሳይቀር መጽውቶ ራቁቱን የተገኘ ደግ ሰው ነው) 4.አባ ሐርስዮስ ገዳማዊ =>ወርሐዊ በዓላት 1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ) 2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ 3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ) 4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት 5.አባ ባውላ ገዳማዊ 6.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ) =>+"+ ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዐን ናቸው:: መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና:: ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብጹዓን ናችሁ:: ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ:: ሐሴትም አድርጉ:: ከእናንተ በፊት የነበሩ ነቢያትን እንዲሁ አሳደዋቸዋልና:: +"+ (ማቴ. 5:10) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/zikirekdusn
1650Loading...
32
«ወደ እግዚአብሔር የምንጸልየው፥ መረጃ ወይም መመሪያ ልንሰጠው ሳይሆን፥ ወደ እርሱ እንድንቀርብና ከእርሱ ጋር ኅብረት ያለን እንድንሆን ነው።» ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
2394Loading...
33
Media files
3 2285Loading...
34
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ ግንቦት 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ አባ መቃርስ ካልዕ +"+ +ይህ ቅዱስ "መቃርዮስ: መቃርስ: መቃሬም" ይባላል:: ትርጉሙ በ3ቱም መንገድ አይለወጥም:: ምክንያቱም ሥርወ ቃሉ በዮናኒ ልሳን "ብጹዕ: ንዑድ: ክቡር" ማለት ነውና:: +ከስሙ ቀጥሎ "ካልዕ-2ኛው": አንዳንዴ ደግሞ "እስክንድርያዊ" እየተባለ ይጠራል:: "ካልዕ-2ኛው" የሚባለው ከቀዳሚው (ታላቁ መቃርስ) ለመለየት ሲሆን "እስክንድርያ" ደግሞ ተወልዶ ያደገባት ሃገር ናት:: +አባ መቃርስ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ ገዳማዊ: ጻድቅና ትሩፈ-ምግባር ነው:: በዓለም ለ40 ዓመት ሲኖር እንደ ሕጉ ፈጣሪውን ደስ ያሰኘ ሰው ነው:: ጻድቃን እንደ ከዋክብት በበዙበት በዚያ ዘመን የታላቁ መቃርስን ዜና ሰምቷልና ይህቺን ክፉ ዓለም ከነግሳንግሷ ንቋት በርሃ ገብቷል:: +እንደሚገባ ሥርዓተ ገዳምን ጠብቆ: ለአበው ታዞ: በጾም: በጸሎት: በትሕትናና በስግደት ተጠምዶ ቢያገኘው ፈጣሪ አከበረው:: በዚያ ጊዜም ለታላቁ ገዳመ አስቄጥስ መናንያን አበ ምኔት ሊሆን መረጡት:: +እርሱም እረኝነትን ያውቃልና በጐቹን (መነኮሳትን) ከተኩላ (ሰይጣናት) ይጠብቅ ዘንድ ብዙ ተጋ:: ከብቃቱ የተነሳም ሳያስታጉል: ሳይበላ: ሳይጠጣና ሳይቀመጥ እስከ 40 ቀን ይጸልይ ነበር:: ሲጸልይ ደግሞ በልቡ እየተቃጠለ በፍቅረ ክርስቶስ ነበርና አጋንንት ይርዱለት ነበር:: +እርሱ ጸሎት ሲጀምርም በገዳሙ ዙሪያ ያሉ አጋንንት እየጮሁ ይሸሹ ነበር:: ከተጋድሎው ጽናትና ከትሕትናው ብዛት የተነሳ ያዩት ትዕቢተኞች ሁሉ ይገሠጹ ነበር:: በዘመኑም ብዙ ተአምራትን ሠርቷል:: +አንድ ቀን በበዓቱ ሳለ ጅብ መጥታ ተማጸነችው:: አብሯት ወደ ዋሻዋ ቢሔድ ልጆቿ በሙሉ ዓይነ ሥውራን ሆነው አገኛቸው:: እርሱም ወደ መሬት ምራቁን እትፍ ብሎ በጭቃ ለውሶ ቢቀባቸው የሁሉም ዐይናቸው በርቷል:: +ስለ ውለታውም ጅቢቱ የበግ ቆዳ እየጐተተች አምጥታ ሰጥታዋለች:: (ከሰው ልጅ በቀር እንስሳት ውለታን አይረሱምና) ቅዱስ መቃርስም ለወትሮው ባዶው መሬት (አፈር) ላይ ይተኛ የነበረው ከዚያ ቀን በኋላ በአጐዛው ላይ የሚተኛ ሁኗል:: +በሃገሩ እስክንድርያም ለ2 ዓመታት ዝናብ በመጥፋቱ ሕዝቡ ተጨንቆ ነበርና "ናልን" ሲሉ መልዕክት ላኩበት:: እርሱ መጥቶ ሲጸልይም መብረቅ የቀላቀለ ዝናብ ጣለ:: ዝናቡም ያለ ማቆም ለ2 ቀናት በመዝነቡ ሕዝቡ ፈርተው "አባታችን ስለ ኃጢአታችን እንዳንጠፋ ለምንልን?" አሉት:: እርሱም በጸሎቱ (በፈጣሪው ኃይል) እንደ ወደዱት ዝናቡን አቁሞላቸዋል:: +የአባ መቃርስን ዜና ሕይወትና ተአምራት ተናግሬ አልፈጽመውም:: ግን አንዲት ብቻ ላክል:: ሁሌ ሳስበው ስለሚገርመኝም ነው:: +ብዙዎቻችን የጌታችን ሥጋና ደም አንቀበልም:: ለምን ያከበርነውና የፈራነው አስመስለን ኃጢአትን ለመጥገብ ቦታን ( አጋጣሚን) ስለምንፈልግ:: በተቃራኒው ደግሞ አንዳንዶቻችን መለኮት የተዋሐደውን የጌታ ሥጋና ደም እንደ ተርታ ነገር (ያለ ጥንቃቄ) ስንቀበል ይታያል:: 2ቱም ግን ስሕተት ነው:: +ፈርተን (ፍርሃቱ ጤነኛ ባይሆንም) ስለ ራቅን በፍርድ ቀን ማምለጥ አንችልም:: "ሥጋየን ያልበላ: ደሜንም ያልጠጣ የዘለዓለም ሕይወት የለውም" ይለናልና:: (ዮሐ. 6:52) +በድፍረት ለምንቀበልም ሥጋው እሳት ሁኖ እንዳይበላን: ደሙም ባሕር ሆኖ እንዳያሰጥመን ልናከብረው ይገባናል:: "ሳይገባው ከጌታ ሥጋና ደም የተቀበለ የጌታ ሥጋ ዕዳ አለበት" ይለናልና:: (1ቆሮ. 11:27) << ታዲያ የሚሻለው ለሁላችንም ንስሃ ገብቶ: በፍርሃት ሆኖ መቅረቡ ነው:: >> +ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና አባ መቃርስ ወደ በርሃ እንደ ገባ ሥጋ ወደሙን ተቀብሎ ነበር:: ቅዱሱ ይህንን እያሰበ ለ60 ዓመታት ምራቁን ሳይተፋ ኑሯል:: ለዚያ አይደል አበው "ብታከብሩት ያከብራቹሃል" ያሉት:: +ሊቃውንቱም ይህንን ሲያደንቁ:- "ኢታስተማስልዎ ለቁርባን ከመ ሕብስት ዕራቆ:: አኮኑ ሥጋ መለኮት ዘይትላጸቆ:: መቃርዮስ አብ ዕበየ ቁርባን ለአጠይቆ:: ድኅረ ተወክፈ በአሚን እንበለ ያብዕ ናፍቆ:: መጠነ ዓመታት ስሳ ኢተፍአ ምራቆ::" ብለዋል:: +ቅዱስ መቃርስም በ100 ዓመቱ በ5ኛው ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢ በዚህች ቀን ዐርፏል:: ❖ጌታችን ከክብሩ: ከበረከቱ አይለየን:: =>ግንቦት 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱስ አባ መቃርስ ገዳማዊ 2.እናታችን ቅድስት ሰሎሜ ኢትዮዽያዊት 3.አባ ይስሐቅ ጻድቅ 4.ቅድስት ዲላጊና 4 ሴት ልጆቿ (ሰማዕታት) 5.ቅዱስ ዳናስዮስ ሰማዕት 6.ቅዱስ በንደላዖስ ሰማዕት (የታላቁ ኤስድሮስ አባት) 7.አባ አሞን ጻድቅ (ዽዽስናን አልፈልግም ብሎ የሸሸ አባት) =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም 2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን 3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል 4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ 5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ 6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ 7.ቅድስት ሰሎሜ 8.አባ አርከ ሥሉስ 9.አባ ጽጌ ድንግል 10.ቅድስት አርሴማ ድንግል =>+"+ ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው:: እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለሁ:: ሥጋዬ እውነተኛ መብል: ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና:: ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል:: እኔም በርሱ እኖራለሁ:: +"+ (ዮሐ. 6:53-56)    <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
2671Loading...
35
🔔 ✥✥✥ ፱ ሰዓት ✥ተንስኡ ለጸሎት✥ #መዝሙረ ዳዊት 118_25 አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና። #በዚህ ሰዓት ይህንን የምታዩ የምታደርጉትን ለ2 ደቂቃም ብትሆን ተውና ልዑል እግዚአብሔርን እያሰብን አንድ አባታችን ሆይ እንጸልይ ✥የእግዚሐብሔር ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ማረን ✥የእግዚሐብሔር ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ማረን ✥የእግዚሐብሔር ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ማረን
2472Loading...
36
Photo
2 5914Loading...
37
#እንደ_ወሮቻችን_ኑ_በእርሷ_እንጀምር (ዲ/ን ሕሊና በለጠ) የወር መጀመሪያ የእርሷ ልደት ነው። ወሮቻችን ኹሉ በእርሷ ልደት ጀምረው በመጨረሻው የብሉይ ኪዳን ነቢይና የሐዲስ ኪዳን መንገድ ጠራጊ በመጥምቁ ዮሐንስ ያበቃሉ። እርሱ የብሉይን ማለፍና የሐዲስን መምጣት በማብሰር መንገድ እንደ ጠረገ ፣ የብሉይ ምሳሌ የኾነውን የአሮጌውን ዓመት ማለፍና የሐዲስ ምሳሌ የሚሆነውን የአዲሱን ዓመት መምጣት ያበሥር ዘንድ መስከረም አንድ ቅዱስ ዮሐንስ እንዲባል ኾነ። ልክ እንዲሁ ደግሞ የአሮጌው ወር መጨረሻ ላይ ወርኀዊው መታሰቢያው በመሆኑ በእርሱ ትምህርት ላይ ቆመው፣ እርሱ መንገድ ጠርጎላቸው ሐዲስን እንዳዩት የብሉይ ኪዳን ሰዎች፣ እኛም በእርሱ መታሰቢያ በዓል ላይ (በ30) ላይ ቆመን ሐዲስ ወርን እናያለን። እነርሱ በእርሱ ትምህርት ጸንተው የአሮጌውን ኪዳን መጨረሻነት ተረድተው የሐዲስ ኪዳንን ሐዲስ ሕይወት "1" ብለው እንደ ጀመሩ፣ እኛም 30 ላይ ቆመን የአሮጌው ወር ብልየታችንን መጨረሻነት ተረድተን የአዲሱን ወር ሐዲስ ሕይወት "1" ብለን እንጀምራለን። "1" ደግሞ ልደታ ለእግዝእትነ ነው - የኹሉ ነገር ጅማሬ የኾነችው የእመቤታችን ልደት። ወሮቻችን ኹሉ በእርሷ ልደት ስለሚጀምሩ ቀና ናቸው። ወሩን እርሷን አክብሮ፣ ዘክሮ ስሟን ጠርቶ የሚጀምር ሰው መንገዱ የቀና ነው። በእርሷ ጀምሮ ያፈረ የለም። የአዳም የመዳን ተስፋ "እምወለተ ወለትከ" በሚለው እርሷን በሚያነሣው ቃል ኪዳን ተጀምሮ ፍጻሜው ያማረ ሆነ። ኖሕ ከጥፋት ውኃ መዳኑን ለእርሷ ምሳሌ በሚሆን መርከቡ ጀምሮ አላፈረም። ሙሴ እስራኤልን ከፈርዖን የማዳን ሥራውን የጀመረው ሐመልማሉ እሳቱን ሳያጠፋው እሳቱም ሐመልማሉን ሳያቃጥለው ባየው ድንቅ ምሥጢር ነው፤ ይህ ደግሞ እሳተ መለኮት ሐመልማል የሆነች እርሷን ላለማቃጠሉና ላለመዋጡ፣ በእርሷ የተፈጸመውን ተዋሕዶ የሚያሳይ ነው። ሠለስቱ ዮሐንሶችም እንዲሁ ናቸው። ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ የፍቅር እናትን ተቀብሎ የጀመረው ሕይወት "ነባቤ መለኮት" አስብሎታል። ዮሐንስ መጥምቅ በእናቱ ማህጸን ሳለ ለእርሷ ሰግዶ የጀመረው ሕይወት "ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከእርሱ የሚበልጥ አልተነሣም" አስብሎታል። (ማቴ.11:11)። አፈ በረከት ዮሐንስ ስለ እርሷ አመሥጥሮ የጀመረው ሕይወቱ "አፈ ወርቅ" አስብሎታል። (ግንቦት 1 ዓመታዊ በዓሏ እንደ ሆነው ግንቦት 12 የሊቁ ፣ ግንቦት 16ም የሐዋርያው በዓል መሆኑን ልብ ይሏል) እርሷ የወራችን ብቻ ሳይሆን የሰማይና የምድርም መጀመሪያ ናት። (ሰማይና ምድር በውስጣቸውም ያሉት ስላንቺ ተፈጠሩ እንዲል ድርሳነ ማርያም)። ሰማይና ምድር ሳይጋፉ ፣ ሳይራበሹ "ይህ የኔ ክልል ነው፣ ይህ የኔ ወሰን ነው" ሳይባባሉ ሺህ ዘመናትን በፍቅር የጸኑት እርሷን መጀመሪያቸው ስላደረጉ ይሆን? እርሷ የአዳምና ሔዋን መጀመሪያ ናት። ስለ እርሷ አዳምና ሔዋን ተፈጥረዋል። (መላእክትን ከፈጠረ በኋላ በጸፍጸፈ ሰማይ ቀጥሎ ማንን እንደሚፈጥር ያሳያቸው ነበር። ቀጥሎ የሚፈጠረው ሰው: አምላኩን እንደሚክድ ሲያዩ መላእክቱ "አትፍጠረው" አሉ። ድንግልን አሳያቸው፤ ሊያዩት የሚጓጉለትን አምላክን መውለዷን ሲያዩ "ይህችን ፍጠርልን" ብለው ተማጸኑ። "ካለ እርሱ (አዳም) እርሷ አትገኝም" ቢላቸው "እንግዲያውስ ስለ እርሷ እርሱን ፍጠርልን" አሉ። \ትርጓሜ. ኢዮብ? ኩፋሌ?)። ነገረ ልደቱ በእርሷ የጀመረለት አዳም ነገረ ልደቱ በእርሷ እንዳልጀመረለት ሳጥናኤል ወድቆ አልቀረም - ተነሣ እንጂ። በእርሷ የሚጀምር ቢወድቅ እንኳን ይነሣል። መጽሐፍ ቅዱስ ካምና ያፌትን ትቶ የሴም የትውልድ ሐረግን ለምን ተረከ? እመቤታችን ከሴም ዘር ስለምትወለድ ነው። ከሌሎች ሕዝቦች መኻል እስራኤልን መርጦ ለምን ቀጠለ? እመቤታችን ከእስራኤል ስለምትወለድ ነው። የካም ዘር የሆነውን መልከጼዴቅን ትቶ የሴም ዘር ስለ ሆነው ስለ አብርሃም እየተረከ ለምን ቀጠለ? አብርሃም ስለሚበልጥ ነውን? አይደለም። መልከጼዴቅ ታላቅ አብርሃም ታናሽ እንደ ሆነ ቅዱስ ጳውሎስ ነግሮናል። (ዕብ.7)። ታዲያ ምክንያቱ ምንድን ነው? እርሷ ከአብርሃም ዘር ስለምትወለድና ጌታችንና አምላካችንም ወልደ ዳዊት ወልደ አብርሃም ስለሚሆን ነው። መጽሐፍ ቅዱሳችን እንኳን እርሷን በሩቅ ዐይቶና በእርሷ ላይ ተመሥርቶ የተጻፈ ነው። ድኅነታችን በእርሷ ምክንያትነት የተገኘ ነው። "አንዲት ዘር" የሆነች እርሷን ባያስቀርልን ኖሮ ከምድር በታች መውደቃችን ለመቀበር እንጂ ተዘርቶ ለማበብ አይሆንም ነበር። ኢትዮጵያውያን በእርሷ በመጀመር አንታማም። በእርሷ እየጀመርን ከብዙ ውድቀትም ተርፈናል፣ ተነሥተናል። እርስ በእርስ የመባላታችንም ሆነ የመጠላላታችን ነገር ምናልባት የፍቅር እናት የሆነች እርሷን ዘንግተን የመጡብን ይሆኑ ይሆን? ምናልባትም እርሷን የማይጠሩ ዜጎች በርክተው እኛም በዚህ ደክመን ይሆን? ኑ ልክ እንደ ወሮቻችን በእርሷ እንጀምር። ያለፈውን ብልየት ኹሉ በመጥምቁ ትምህርት ላይ ቆመን እንሻገርና እርሷን ይዘን እንጀምር። ባለፈው ወር ያለቀስን፣ ያዘንን፣ የወደቅን፣ የከፋን፣ ያቄምን፣ የሞትን፣ የዘረፍን፣ የገደልን፣ የዘሞትን በክፋትና በሥጋ ሥራ ያረጀን ኹሉ በመጥምቁ ትምህርት ላይ እንቁምና ብሉዩን እንሰናበተው፤ ሐዲሱን ሕይወት ልክ እንደ ወሮቻችን "1" ብለን በእርሷ እንጀምር።
3080Loading...
የወርሐ ግንቦት ቃለ ጽድቅ ዘመካነ ሕይወት መጽሔትን ያውርዱት ..........ያንብቡት..........ያጋሩት የመካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን የመካነ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት ንዑስ ክፍል
Show all...
"ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡ ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡ ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡ ተፈጥሮ እንደ መጽሐፍ ፍጥረታት እንደ ጽላት ይሁኑህ። ከእነሱ ሕግጋትን ተማር፤ በተመስጦ ሆነህ በመጽሐፍ ያልሰፈሩትን ምስጢራት ተረዳ፡፡ እግዚአብሔርን ከሚፈራ በቀር ባለጸጋ የሆነ ሰው ማነው? የእውነት እውቀት ከጎደለው ሰው በላይ ፍጹም ደሃ የሆነ ማን ነው? ሁል ጊዜም እውነተኛ ፍቅራችን ጸንቶ ይቀጥል ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ፡፡ እርሱን ለምነው፡፡ ስለ ቸርነቱ ምስጋና አቅርብ፤ ምክሬን ፈጽሞ ቸል አትበል፡፡" (ምክር ወተግሳጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም)
Show all...
†✝† እንኩዋን ለጥንተ በዓለ ዸራቅሊጦስ (መንፈስ ቅዱስ) እና ለጻድቁ አባ ገዐርጊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †✝† †✝† በዓለ ዸራቅሊጦስ †✝† ✝✞✝ ከዚሕ በፊት እንደተመለከትነው የጌታችን ዓበይት በዓላቱ 2 ጊዜ (ማለትም ጥንተ በዓልና የቀመር በዓል ተብለው) ይከበራሉ:: ዛሬም ከ1,978 ዓመታት በፊት አምላካችን መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ መውረዱን እናስባለን:: ††† ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- +ቸር አምላክ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሲል *ከልዑል ማዕርጉ ወርዶ: *በማሕጸነ ድንግል ተጸንሶ: *በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: *ከኃጢአት በቀር በግዕዘ ሕጻናት አድጐ: *በ30 ዘመኑ ተጠምቆ: *ቅድስት ሕግ ወንጌልን አስተምሮ: *በፈቃዱ ሙቶ: *በባሕርይ ስልጣኑ ተነስቶ: *በአርባኛው ቀን ያርጋል:: +ታዲያ ደቀ መዛሙርቱን የቅዱስ መንፈሱን ጸጋ ተስፋ እንዲያደርጉ ነግሯቸው ነበርና በተነሳ በ50ኛው ቀን: በዐረገ በ10 ቀን ተስፋውን ፈጸመላቸው:: +እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ እንድትይዝ በአንድ ላይ ሰብስባ ለክብረ መንፈስ ቅዱስ አብቅታቸዋለች:: 120ው ቤተሰብ ከጌታችን እናት ጋር ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ በአውሎ ንፋስ አርአያ ወርዶ በአምሳለ እሳት አደረባቸው:: +ቅዱሳን ሐዋርያት ፈሪዎች የነበሩ ደፋሮች: አሮጌ ሕሊና የነበራቸው ሐዲሶች ሆኑ:: በአዕምሮ ጐለመሱ: ቁዋንቁዋ ተናገሩ: ምሥጢርም ተረጐሙ:: በቅጽበትም ብሉይ ከሐዲስ በልቡናቸው ውስጥ ተሞላ:: +ሐዋርያቱ ቅዱስ መንፈስን ተቀብለው ዓለምን በወንጌል ዕርፈ መስቀል አርሰዋል:: አልጫውን ዓለም ጨው ሆነው አጣፍጠዋል:: ሳይሳሱም አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተዋል:: "ኪያሁ መንፈሰ ነሢኦሙ ለለአሐዱ: ሐዋርያት ለሰቢክ አሕጉራተ ዓለም ዖዱ: ሰማዕትኒ ለሕማም ነገዱ::" እንዳለ ደራሲ:: +በዚህ ቀን 2 ነገሮች በትኩረት ይነገራሉ:- 1."የመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክነት:-" *እርሱ ከአብ የሠረጸ: ቅድመ ዓለም የነበረ: በባሕርይ ስልጣኑ ከአብና ከወልድ ጋር እኩል የሆነ: የራሱ ፍጹም አካል ያለው ፍጹም አምላካችን ነውና:: 2."ቅድስት ቤተ ክርስቲያን:-" *አብ ያሰባት: ወልድ በደሙ የቀደሳት: መንፈስ ቅዱስ በጸጋው ያጸናት የክርስቲያኖች አማናዊት አንድነት: አንድም ቤት ናትና:: ዛሬ በጉባዔ ተመስርታለች:: ††† አባ ገዐርጊ ††† =>በዚችም ዕለት የአባ አብርሃም ጓደኛ የከበረ አባ ገዐርጊ አረፈ።ይህም ቅዱስ የክርስቲያን ወገን ነው ወላጆቹ ደጎች ጻድቃን ናቸው።በአደገም ጊዜ የወላጆቹን ከብቶች የሚጠብቅ እረኛ ሆነ።ሁል ጊዜም የምንኵስና ልብስ ይለብስ ዘንድ በልቡ ይመኝ ነበር። ዐሥራ አራት ዓመትም በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ አነሣሳችው በጎቹንም ትቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ።እየተጓዘም ሳለ ከሩቅ የብርሃን ምሰሶ አየ ወደ ወንዝ እስከ ደረሰ ድረስ ወደ ርሱ ሔደ ከዚህም በኃላ ያ የብርሃን ምሰሶ ከእርሱ ተሰወረ። ያንንም ወንዝ በተሻገረ ጊዜ በሽማግሌ አምሳል ሰይጣን ተገለጠለትና ልጄ ሆይ ዕወቅ ስለ አንተ ልብሱን ቀዶ አባትህን አየሁት እርሱም ያዝናል ያለቅሳል ተመልሰህ የአባትህን ልብ ልትአጽናና ይገባሃል።የዱር አውሬ ነጥቆ የበላህ መስሎታልና አለው። አባ ገዐርጊም ደንግጦ አንድ ሰዓት ያህል ቆመ ከዚህም በኃላ የከበረ ወንጌል ከእኔ ሊሆን አይገባውም ደቀ መዝሙሬም ሊሆን አይችልም ብሏል ብሎ አሰበ።ይህንንም በአለ ጊዜ ሰይጣን እንደ ጢስ ሆኖ ተበተነ።አባ ገዐርጊም ሰይጣን እንደ ሆነ አወቀ በዚያን ጊዜም ያ የብርሃን ምሰሶ ደግሞ ተገለጠለት የእግዚአብሔርም መልአክ በመነኵሴ አምሳል አብሮት ተጓዘ ቅዱሱም መልአኩን ተከተለው እርሱም ከአባ አርዮን ገዳም አደረሰው።አባ ገዐርጊም ከአንድ ጻድቅ ሰው መነኵሴ ጋራ በዚያ ዐሥራ አራት ዓመት ወጥሳይቀምስ ወይን ሳይጠጣ የአትክልት ፍሬም ቢሆን በዚህ በዐሥራ አራት ዓመት ያህል ከሚቀመጥ በቀር አልተኛም። ተጋድሎውንም በጨመረ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና እንዲህ አለው ሥጋህ እንዳይደክም በመካከለኛ ገድል ተጋደል ብሎሃል ጌታ።ከዚህም በኃላ ሊሠራው የሚገባውን ሥርዓት ሠራለት ።ሁል ጊዜም እስከሚመሽ እንዲጾም ትንሽም እንጀራን እንዲበላ ከአራት ሰዓት እስከ መንፈቀ ሌሊት ስለ ሥጋው ዕረፍት እንዲተኛ በቀረው ሌሊት እስቲነጋ ተግቶ እንዲጸልይ። በዚህም ተጋድሎ ብዙ ዘመናት እየተጋደለ በኖረ ጊዜ በበረሀ ውስጥ ብቻውን ሊኖር ወዶ በጫካ ውስጥ እየተመላለሰ ሁለት ዓመት ኖረ።ከዚህም በኃላ ጌታ ተገለጾለት ወደ ቦታው እንዲመለስ አዘዘው።ያን ጊዜም አምላካዊት ኃይል ከከበሩ መክሲሞስና ደማቴዎስ ገዳም አደረሰችው እርሷም ለደብሩ አቅራቢያ ናት። ወደ ደብሩም በተመለሰ ጊዜ በዚያን ወቅት አብርሃም ከዓለም ወደዚያ ገዳም መጥቶ ሁለቱም ተገናኙና በአንድነት ተስማምተው የአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ወደ ሆነ ወደ አባ ዮሐንስ ደረሱ።እርሱም ቦታ ሰጥቷቸው በውስጡ ኖሩ ያ ቦታም እስከ ዛሬ ታውቆ ይኖራል ። ያቺም ዋሻ በግቢግ ትባላለች የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዐለት የሆነ ጣሪያዋን ሠንጥቆ ወደ እነርሱ የወረዳበት ናት ።እነርሱም ሰገዱለት ሰላምታም ሰጥቷቸው አጽናንቷቸው ከእርሳቸው ዘንድ ዐረገ።በዚያችም ጌታችን በወረደበት መስኮት ብርሃንን አዩ እስከ ዛሬም የተከፈተች ሁና ትኖራለች። እሊህ ቅድሳንም ለመነኰሰኘሳት የሚሆን ብዙ ድርሳናትንና ብዙ ተግሣጻትን ደረሱ።ለአባቶቹ የሚታዘዘውንና የሚገዛውን አመሰገኑት።ከዚህም በኃላ አባ አብርሃም ጥር ሁለት ቀን አረፈ።ከእርሱ በኃላም የከበረ አባ ገዐርጊ በዚች በግንቦት ወር በዐሥራ ስምንት ቀን አረፈ።መላ ዕድሜውም ሰባ ሁለት ዓመት ሆነ።በዓለም ዐሥራ አራት ዓመት በምንኩስና ኃምሳ ስምንት ዓመት ነው።ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትሁን አሜን። =>በዚችም ዕለት የሰማዕት ሲኖዳ መታሰቢያው ነው በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። =>አምላከ ገዐርጊ ከቅዱስ መንፈሱ ጸጋ ለኃጥአን ባሮቹ ያድለን:: =>ግንቦት 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱሳን ሐዋርያት ወአርድእት 2.አባ ገዐርጊ ገዳማዊ 3.ቅዱስ ሲኖዳ ሰማዕት =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ 2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን) 3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ 4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ =>+"+ በዓለ ሃምሳም የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ:: ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው:: እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው:: በእያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው:: በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው:: መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር:: +"+ (ሐዋ. 2:1-4) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> https://t.me/zikirekdusn
Show all...
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

📝ታላቁ ቅዱስ ሐዋርያ ዕድሜው 90 ዓመት በሆነው ጊዜ ተሰውሯል። ከዚያ አስቀድሞም የዓለምን ፍጻሜ ተመልክቷል። ዛሬ ያለበትን የየሚያውቅ ቸር ፈጣሪው ነው። 📝ይሕች ዕለት ለሐዋርያው ቅዳሴ ቤቱ ናት። 📝እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲሕ ነው፦ 1. ወንጌላዊ 2. ሐዋርያ 3. ሰማዕት ዘእንበለ ደም 4. አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ) 5. ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት) 6. ወልደ ነጐድጓድ 7. ደቀ መለኮት ወምሥጢር 8. ፍቁረ እግዚእ 9. ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ) 10. ቁጹረ ገጽ 11. ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ) 12. ንስር ሠራሪ 13. ልዑለ ስብከት 14. ምድራዊው መልዐክ 15. ዓምደ ብርሃን 16. ሐዋርያ ትንቢት 17. ቀርነ ቤተ ክርስቲያን 18. ኮከበ ከዋክብት 🤲 በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር። ቅዱስ ዮሐንስን የወደደ ጌታ በፍቅሩ ይጠግነን። ከእናቱ ፍቅር አድርሶ በሐዋርያው በረከት ያስጊጠን። 🤲 🗓 ግንቦት 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ስብከቱና ቅዳሴ ቤቱ) 2.ቅዱስ ኢያሱ ሲራክ ነቢይና ጠቢብ (መጽሐፈ ሲራክን የጻፈ) 3.ቅድስት እናታችን ዐስበ ሚካኤል (ኢትዮዽያዊት) 🗓 ወርኀዊ በዓላት 1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም) 2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት) 3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ   (የቅዱስ ላሊበላ ወንድም) 4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ 5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ 6.አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ 7.አባ ዳንኤል ጻድቅ 📖"በጌታ ኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፡ የእናቱም እህት፡ የቀለዮዻም ሚስት ማርያም፡ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር። ጌታ ኢየሱስም እናቱን፡ ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን 'አንቺ ሆይ! እነሆ ልጅሽ' አላት። ከዚህ በሁዋላ ደቀ መዝሙሩን 'እናትህ እነሁዋት' አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።" (ዮሐ. 19:25) ✨ወስብሐት ለእግዚአብሔር✨ 🔗https://t.me/zikirekdusn
Show all...
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)

በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

✝ በስመ አብ፡ ወወልድ፡ ወመንፈስ ቅዱስ፡ አሐዱ አምላክ 🗓 ግንቦት 16 የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 🌕 ቅዱስ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ 📝 አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው። ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ፡ በገሊላ አካባቢ አድጐ፡ ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል። 💡ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር። ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው ሕጻን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው። ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል። 📝 ከእርሷ ጋር ለ15 ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ። ስንኩዋን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላዕክትም ማዕረጉ ከፍ አለ። ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል። ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል። ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው። 📝 ቅዱስ ዮሐንስ በታናሽ እስያ ለ7ቱ አብያተ ክርስቲያናት መስበኩ ይታሰባል። ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በሁዋላ ለ70 ዓመታት በዚህ ምድር ሲኖር አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው በኤፌሶን አካባቢ ነው። ሕዝቡን ወደ ክርስትና ለማምጣት በአፍም በመጽሐፍም ደክሟል። 📝3 መልዕክታት፡ ራዕዩንና ወንጌልን ጽፎላቸዋል። ሕይወትን ስለ ሰበከላቸው በፈንታው ብዙ አሰቃይተውታል። ከእሳት እስከ ስለት፡ እስከ መጋዝም በስተእርጅና ደርሶበታል። እርሱ ግን በትእግስቱ ገንዘብ አድርጉዋቸዋል።      ቅዱሱ በኤፌሶን 📝ይህቺ ኤፌሶን የሚሏት ሃገር መገኛዋ በቀድሞው ታናሽ እስያ (አሁን ቱርክ አካባቢ) ሲሆን ብዙ ሐዋርያት አስተምረውባታል። ያም ሆኖ የሚፈለገውን ያህል ለውጥ ያመጣች አልነበረችምና ቅዱስ ዮሐንስ ሊሔድ ተነሳ። 📝ከደቀ መዛሙርቱ መካከልም ቅዱስ አብሮኮሮስን (ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው) አስከትሎ እየጸለዩ በመርከብ ላይ ተሳፈሩ። ሐዋርያት አበው መከረኞች ናቸውና ማዕበል ተነሳባቸው። በጥቂት አፍታም መርከባቸው በማዕበሉ ተበታተነች። ቅዱስ አብሮኮሮስ በስባሪ ላይ ተሳፍሮ ወደ አንዲት ደሴት ደረሰ። ከንጹሑ መምሕሩ ቅዱስ ዮሐንስ ተለይቷልና አለቀሰ። 💡ፍቁረ እግዚእ ግን ያለ ምግብና ውሃ ማዕበለ ባሕር እያማታው ለ40 ቀናት ቆየ። እርሱ በፈጣሪው ፍቅር የተመሰጠ ነበርና አለመመገቡ አልጐዳውም። በ40ኛው ቀን ግን ደቀ መዝሙሩ ወዳለበት ደሴት ማዕበሉ አደረሰው። 2ቱ ቅዱሳን ተፈላልገው ተገናኙ። እጅግም ደስ ብሏቸው ፈጣሪን አመሰገኑ። 📝አምላካቸው ወደዚህች ደሴት ያመጣቸው በጥበቡ ነውና ሲዘዋወሩ 2 ነገርን አስተዋሉ። 1ኛ የደሴቷ ሁሉም ነዋሪ የሚያመልኩት ጣዖትን ነው። 2ኛ አብዛኞቹ የቤተ መንግስት ውላጆች ናቸው። ሮምና የሚሏት አንዲት ሴት ደግሞ እነዚህን ሁሉ እየመገበች ታስተዳድራለች። 📝ቅዱሳኑ በቦታው በቀጥታ ትምሕርተ ወንጌልን ቢናገሩ እንደ ማይቀበሏቸው ስለ ተረዱ ሌላ ፈሊጥን አሰቡ። እንዳሰቡትም ወደ እመቤት ሮምና ቤት ሒደው በባርነት ተቀጠሩ። ለእርሷም "ድሮ የአባትሽ ባሮች የነበርን ሰዎች ነን" ስላሏት 2ቱን ቅዱሳን እሳት አንዳጅና ገንዳ አጣቢ አደረገቻቸው። ለሰማይ ለምድሩ የከበዱ እነዚህ ቅዱሳን የካዱትን ይመልሱ ዘንድ በባርነት ግፍን ተቀበሉ። 📝የመከር (የማሳመኛ) ጊዜ ሲደርስም አንዳች አጋጣሚ ተፈጠረ። ቅዱሳኑ ዮሐንስና አብሮኮሮስ ወደ መታጠቢያ ቤቱ ሲገቡ ሰይጣን በውስጥ ኖሮ ደንግጧልና እወጣለሁ ብሎ ሲሮጥ የንጉሡን ልጅ ረግጦ ገደለው። 📝ሮምናና የአካባቢው ሰዎች ከበው ሲላቀሱ ቅዱሳኑ ቀረቡ። ሮምና ግን በቁጣ "ልትሣለቁ ነው የመጣችሁ?" በሚል ቅዱስ ዮሐንስን በጥፊ መታችው። መላእክት እንኩዋ ቀና ብለው ሊያዩት የሚከብዳቸው ሐዋርያ ይህንን ታገሰ። በጥፊ ወደ መታችው ሴት ቀረብ ብሎም "አትዘኚ! ልጁ ይነሳል" አላትና ጸለየ። ወደ ሞተውም ቀረብ ብሎ በጌታችን ስም አስነሳው። 💡በዚህ ጊዜም ሮምናን ጨምሮ በሥፍራው የነበሩ ሰዎች ለቅዱስ ዮሐንስ ሰገዱ። እርሱ ግን ሁሉንም አስነስቶ ትምሕርተ ሃይማኖትን፡ ፍቅረ ክርስቶስን ሰበከላቸው። በስመ ሥላሴ አጥምቆ፡ ካህናትን ሹሞ፡ ቤተ ክርስቲያንም አንጾላቸው ወጥቷል። በሁዋላም ለሮምናና ለደሴቷ ሰዎች ክታብ (መልዕክትን) ጽፎላቸዋል። ይህች መልዕክት ዛሬ 2ኛዋ የዮሐንስ መልዕክት ተብላ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ትታወቃለች። 📝ቅዱስ ዮሐንስ ቀጥሎ የተጉዋዘው ወደ ኤፌሶን ነው። በዚህች ከተማ የምትመለክ አርጤምስ (አርጢሞስ) የሚሏት ጣዖት ነበረች። አርጤምስ ማለት መልክ የነበራት ትዕቢተኛ ሴት ስትሆን አስማተኛ ባሏ ነው እንድትመለክ ያደረጋት። 📝ቅዱስ ዻውሎስ ብዙ ምዕመናን ከእርሷ እንዲርቁ ማድረግ ችሏል። ጨርሶ ያጠፋት ግን ቅዱስ ዮሐንስ ነው። በቦታውም ብዙ ግፍ ደርሶበት፡ በርካታ ተአምራትን አድርጉዋል። ቤተ ጣዖቱንም በተአምራት አፍርሶታል። የፍቅር ሐዋርያ 📝ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን 'የፍቅር ሐዋርያ' ትለዋለች። ለ70 ዘመናት በቆየ ስብከቱ ስለ ፍቅር ብዙ አስተምሯል። ፍቅርንም በተግባር አስተምሯል።  በየደቂቃውም "ደቂቅየ ተፋቀሩ በበይናቲክሙ - ልጆቼ ሆይ! እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ" እያለ ይሰብክ ነበር። 💡በተለይ ደግሞ ከፈጣሪው ክርስቶስ ጋር የነበረው ፍቅር ፍጹም የተለየ ነበር። በዚህ ምክንያትም ጌታ ባረገ ጊዜ እንዲህ ብሎታል፦ "ለፍጡር ከሚገለጥ ምሥጢር ከአንተ የምሠውረው የለኝም" ብሎታል:: ቀጥሎም በንጹሕ አፉ ስሞታል። ሊቁ፦ "ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዓሞ፡ ንጽሐ ኅሊናሁ ወልቡ ለዐይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ" እንዳለው። (መልክዐ ኢየሱስ) 📝ቅዱስ ዮሐንስ ከእመቤታችንም ጋር ልዩ ፍቅር ነበረው። እርሷ እንደ ልጇ ስትወደው፡ እርሱ ደግሞ እንደ እናቱ ልቡ እስኪነድ ድረስ ይወዳት ነበር። እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ ተከትሎ ያገኛት እመቤቱ ናትና። 📝ከዚያ ሁሉ ጸጋና ማዕረግ የመድረሱ ምሥጢርም ድንግል ናት። ለ15 ዓመታት በጽላሎተ ረድኤቷ (በረዳትነቷ ጥላ) ተደግፎ አብሯት ሲኖር ብዙ ተምሯል። ከመላእክትም በላይ ከብሯል። ከንጽሕናዋ በረከትም ተካፍሏል። 📝ስለ ድንግል ማርያምም "ነገረ ማርያም" የሚል ድርሰት ሲኖረው "የሰኔ ጐልጐታንም" የጻፈው እርሱ ነው። ድንግል ባረፈችበት ቀንም ልክ እንደ ልጇ ክርስቶስ እርሷም ስማው፡ ታቅፋው ዐርፋለች። ሊቃውንቱ ለዚህ አይደል በንጹሕ ከንፈሮቿ መሳምን (መባረክን) ሲሹ፦ "በከመ ሰዓምኪ ርዕሰ ዮሐንስ ቀዳሚ፡ ስዒሞትየ ማርያም ድግሚ" ያሉት።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram