Halal memory🫀
Open in Telegram
#ǫᴜʀᴀɴ & ʜᴀᴅɪs #ғᴜɴ ɪsʟᴀᴍɪᴄ ᴄᴏɴᴛᴇɴᴛ #вєѕт ɪsʟᴀᴍɪᴄ 𝑣𝑖𝑏𝑒 #ᴇᴠʀʏ ᴍᴜsʟɪᴍ ᴄᴏɴᴛᴇɴᴛ ╱◥██████◣. │∩│🪟▤│🪟│. ▓▆▇█▓🚪▓█▇.
Show more9 523
Subscribers
-1024 hours
-627 days
-27130 days
Posts Archive
9 521
ጦርነቱ ጀምሮዋል🖤
አሁን እንግሊዝ እና አርጀንቲና የሚያደርጉት ጨዋታ አይደለም ጦርነት ነው።
የሁለቱ ሀገራት ብሔራዊ ቡድኖች ሁልጊዜም ሲገናኙ ውጥረቱ እጅግ ይበረታል። ከእግርኳስ ይልቅ ፖለቲካዊው ሽኩቻ አይሎ የፎክላንድ ጦርነት ዳግም በእግርኳስ ሜዳ ይስተናገዳል።
ከዛሬ 40 አመት በፊት በማራዶና የሚመራው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን እንግሊዝን አሸንፎ የአለም ዋንጫን ሲበላ አርጀንቲናዊያን ከ ዚያ ጨዋታ 4 አመት በፊት በእንግሊዝ የደረሰባቸውን ሽንፈት የተበቀሉ ነበር የመሰላቸው።
ፎክላንድ ከአርጀንቲና አጠገብ የምትገኝ ደሴት ነች። አርጀንቲና ደሴቷን ግዛቴ ናት ስትል እንግሊዝ በበኩሏ ሺህ ኪሎሜትር ርቃ አርጀንቲና አጠገብ ሂዳ ፎክላንድን የኔ ነው አለች።
በዚህ ጊዜ አርጀንቲና ፎክላንድን በሀይል ተቆጣጠረች። የአርጀንቲናው መሪ ጄኔራል ሊዮፖልዶ ጋልታየሪ ፎክላንድ ሲይዝ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርጋሬት ታቼር 127 የጦር መርከብና በርካታ የጦር አይሮፕላኖችን ወደ አርጀንቲና በመላክ ከአርጀንቲና ጋር ከባድ ጦርነት ገጠሙ።
በ 1982 እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር የተካሔደው ይህ ጦርነት ለ 74 ቀናት ያለማቋረጥ ተደረገ ። በጦርነቱ እንግሊዝ 6 የጦር መርከቦችን ጨምሮ 10 የጦር አይሮፕላኖችን 24 ሄሊኮፕተሮችን ፣ በርካታ ታንኮችን ስታጣ አርጀንቲና ከ 6 በላይ መርከቦችን ከ 50 በላይ የጦር አይሮፕላኖችን 24 ሄሊኮፕተሮችን ጨምሮ በርካታ ኪሳራዎችን አስተናገደች።
በጦርነቱ 649 የአርጀንቲና ወታደሮች ሲገደሉ 255 የእንግሊዝ ወታደሮችም ተገደሉ። ጦርነቱም በእንግሊዝ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።
እናም አርጀንቲና እና እንግሊዝ ያደረጉት ያ ከባድ ጦርነት ዛሬ ላይ ላላቸው የእግርኳስ ባላንጣነት ዳርጓቸዋል።
ሁለቱ ሀገራት ዛሬም ሲገናኙ ድባቡ በዚህ የጦርነት ቁጭት ተሞልቶ ነው።
9 521
ለፍልስጥኤም ያለውን አጋርነት ለማሳየት አደጋ በሞላበት በፍልስጤም ምድር ሂዶ መጫወት የቻለው ብቸኛው ታላቅ ክለብ ባርሴሎና ሲሆን ይሄንን ቡድን በፊት አውራሪነት የመሩት ሊዮነል ሜሲ ፤ ኔይማር ጁኒየርና ሌሎችም የባርሳ ከዋክብቶችም ያኔ ላደረጉት ነገር ትልቅ ክብር ይገባቸዋል።
ክለቡ ፍልስጤም ከተጫወተ በሗላ ወደ እስራኤል ተጉዞ የወዳጅነት ጨዋታ በመጫወት ጦርነት እንዲቆም ሰላም እንዲሰፍን ጠይቄ ጉዞውን አጠናቆ ተመልሷል።
ከዚያ በሗላ ጦርነቱ ሲቀጥል እስራኤል የአርጀንቲናን ብሔራዊ ቡድን ለወዳጅነት ጨዋታ የጋበዘች ቢሆንም በሜሲ የሚመራው የአርጀንቲና ቡድን የእስራኤልን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ይታወቃል።
በዚህም ፍልስጤም ሜሲና ሀገሩን በዚህ መልኩ አመስግነዋቸው ነበር።
አሁን ላይ የኢኮኖሚ ቀውስ ወደ ስልጣን ያመጣው የአርጀንቲናው ፅዮናዊ መሪ ዣቪየር ሜሊዩ ከእስራኤል ጋር ሳይጣበቅ በፊት አርጀንቲና ለፍልስጤም ወዳጅ ከሚባሉ ሀገሮች ናት።
ይህ መሪ ሲወድቅም ልክ እንደ ብራዚል እንደምትመለስ ተስፋ አደርጋለሁ።
ቴሌግራም
JOIN US: ❯❯𝐇𝐀𝐋𝑨𝐋 _𝚖𝚎𝚖𝚘𝚛𝚢
9 521
ከ ''ብላልኝ'' ቡሃላ ''በላብኝ'' እንዳይመጣ ብላ ብለው ያቀረቡልህ ማዕድ ላይ በጎረስከው ልክ ማጉረስ እንዳትረሳ ፣በጥጋብ የተከፈተ ደግነት እረሃብን አብዝቶ ይፈታተነዋልና.......
JOIN US: ❯❯𝐇𝐀𝐋𝑨𝐋 _𝚖𝚎𝚖𝚘𝚛𝚢
9 521
"ሀኪሞች ፍቅርን ከነፍስ በሽታ ውስጥ ቆጥረውት መድሃኒቱንም ገልፀዋል። እኔ ግን ከፍቅር መዳንን አላህን ከለመንኩኝ አላህ አፊያ አያድርገኝ"
ሊሳኑዲን ኢብኑ ኸጢብ
ሁሉም ለለይላው ያለቅሳል ለይላም ለሌላው ታለቅሳለች
ቀኑ ይለፍ እንጂ ጊዜው ይለፍ እንጂ የሁሉ ለይላ ከደጅ ትጠናለች
#አብሽሩ
JOIN US: ❯❯𝐇𝐀𝐋𝑨𝐋 _𝚖𝚎𝚖𝚘𝚛𝚢
9 521
ጋሽ ስብሃት አንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፥
"በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ፤ ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ፤ ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ ፣ ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ፤ በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ፤ ሰዎች ሊጠሉህ ፣ ሊያሙህ ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ ይችላሉ።"በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል።አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው
አብዝተው ይፀየፉሀል። ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። ነፃ አውጭ
ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል።
"ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም። ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!" አንድ ነገር ልንገራችሁ፥ በህይወታችሁ ማንንም አትውቀሱ፤ ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጡልችሀል፤ መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኑችሁዋል። ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆናቹኋል፤ ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኑላችሁዋል።
ሊቅነት-የአስተሳሰብ ለውጥ -
share & like 🤜🤛
JOIN US: ❯❯𝐇𝐀𝐋𝑨𝐋 _𝚖𝚎𝚖𝚘𝚛𝚢
9 521
"ትዳር በጥብቅ የህግ አንቀጾች የሚመራ የፍርድ ቤት መድረክ ሳይሆን፣ አንዱ የሌላውን ድካም የሚጋራበት የፍቅርና የመተሳሰብ ጎጆ ነው።"
በእስልምና ሚስት ለቤቷ የምታበረክተው አስተዋጽኦ የደግነቷ መግለጫ ሲሆን፣ የባል እገዛ ደግሞ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና እና የወንድነት ልቅና ማሳያ ነው።
JOIN US: ❯❯𝐇𝐀𝐋𝑨𝐋 _𝚖𝚎𝚖𝚘𝚛𝚢
9 521
ስያቀብጠኝ የስልኬን password በድምፅ አደርጋለው ብዬ reccord ሳደርግ ዉሻችን አብሮ ጮሆ ይኸው አሁን አብረን ካልጮህን ስልኬ አልከፍት ብሏል😢
በደንብ ፊቸር ሚችል dm😭
9 521
Repost from Halal Fkr
እረ አላህ በአላህ 😑
----------------------------------------
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
9 521
Men's morning and afternoon status🥲
--------------------------------------
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
9 521
ውድ ደንበኛችን...እና ጓደኞቼ
እንኳን ለ1447 ዓ.ሒ. የዒድ አል- አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሰዎ እያልን፣ በዓሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሆንልን እንመኛለን።
©ከሆነ ባንክ
9 521
በቀደሙት ዓመታት፣ በተለይም ክርስቲያንና ሙስሊሙ ተቀላቅሎ በሚኖርባቸው ሰፈሮች ውስጥ፣ ለአንዳንዶች "ቂጣ አጣቢ" የሚለው ቃል ሙስሊሙን ወገን ለማሸማቀቅና ዝቅ አድርጎ ለመመልከት እንደ ጦር የሚመዘዝ ስድብ ነበር። አልፎ ተርፎም ትንሿን የዝናብ ጠብታ ተገን በማድረግ፣ በልጆች አንደበት "ዝናቡ አንጠበጠበ... ሙስጠፋ ቂጡን አጠበ" እየተባለ የሚዘፈነው ስላቅ፣ የብዙዎችን ትውስታ የሚያቆስል የታሪክ ጠባሳ ሆኖ አልፏል።
የጊዜ መለወጥና የእውነት መገለጥ
ግርም የሚለው ግን የጊዜ መሽከርከር ነው። ትላንት እንደ ነውር እና እንደ ድንቁርና ይታይ የነበረው በውሃ የመታጠብ ልማድ፣ ዛሬ የጤና እና የሥልጣኔ ምልክት ሆኖ ብቅ ብሏል። ትላንት ሲሳለቁ የነበሩ ወገኖች ዛሬ ውሃ ይዘው መጸዳጃ ቤት መግባት መጀመራቸው፣ አልፎ ተርፎም በየሆቴሉና በየሕዝብ መገልገያው ውሃ መዘጋጀቱ፣ እውነቱ ከሃይማኖታዊ ክርክር ባለፈ የሰው ልጅ የተፈጥሮ ፍላጎትና የንፅህና ጥግ መሆኑን አረጋግጧል።
ዛሬ ላይ ቆሞ ያንን የትላንት ስድብ የሚደግም ሰው ቢኖር፣ እርሱ ራሱ ከአለም የንፅህና ሳይንስና ከዘመኑ አስተሳሰብ የራቀ መሳቂያ መሆኑ አይቀሬ ነው።
የአስተሳሰብ ምጥቀትና የለውጥ ሂደት
አንዳንድ ማህበረሰባዊ ግጭቶችና አለመግባባቶች በጊዜ ሂደት፣ የሰው ልጅ የጭንቅላት ምጥቀት ሲያድግ በራሳቸው ጊዜ የሚፈቱ ናቸው። የእኛ ድርሻ፦
እውነትን ማድረስ፣
በጽናት መቆም፣
እና መልካም ስነ-ምግባርን ማሳየት ብቻ ነው።
ልብን የሚቀይርና ቅኑን መንገድ (ሂዳያን) የሚመራው ፈጣሪ ብቻ ነው። አንዳንዱ በጊዜ ይባንናል፣ ሌላው ደግሞ በጨለማው ውስጥ ይቆያል።
የነብርን ጭራ ከያዙ በኋላ መልቀቅ አይታሰብም። ጉዞው ተጀምሯል፣ ለውጡም አይቀሬ ነው። ትላንት በጨለማ የተወረወሩ ቃላት ዛሬ በብርሃን ተሸንፈዋል። ስለዚህ እውነትን ይዞ መገስገስ እንጂ ወደ ኋላ ለሚሉ ትንኮሳዎች ቦታ መስጠት ተገቢ አይደለም።
9 521
የምሽት ብርሀን
ክፍል ➊
በ @Halal_memory
ሁልጊዜ ማታ 12 ሰአት ላይ መጥቼ ምቀመጥባት ቦታ እዚህ ቦታ ሁል ጊዜ ስመጣ ግን ጥያቄዎች ይኖሩኛል ለምን እዚህ መጣው ግን መልስ የለም ከጨረቃ ጋር ቁጭ ብዬ ማውራት ስወድ ቆይ ትንሽ ስለ ቦታው ልንገራችሁ በትልቅ ዛፍ የተከበበች ድንጋይ አለ ፊት ለፊት ደሞ ጨረቃ ስትወጣ እና ስትገባ በደንብ ነው ሚታየው ለኔ ሆን ተብሎ የተሰራልኝ ይመስለኛል ወይኔ ረስቼው ራሴን አለስተዋወኳችሁም ለካ
ኢብቲሳም እባላለው የ 12ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ
ለቤተሰቤ 2ኛ እና የመጨረሻ ልጅ ነኝ እናቴ ወ/ሮ ሷሊሃ ትባላለች አባቴ አብዱ ይባላል ታላቅ ወንድሜ ደሞ
መሀመድ ይባላል ኦ የድሬ ልጅ ነኝ 😁
እብድ ናቸው እኔም ከነዛ ውስጥ ነኝ
የድሬ ልጆች ደሞ
ባህሪዬ ደሞ 🤔
ተግባቢ ተጨዋች እብድ ነገር ነኝ እኔ ግን በባህሪዬ ከሴት ጋር ማውራት መጫወት ምናምን አይመቸኝም ውሎዬ ሁሉ ከወንዶች ጋር ነው በዚ ጸባዬ የሰፈር ሰው አይወዱኝም ነበር ግን ደሞ ቤተሰቦቼ አይቃወሙኝም ነበር ለዛ ምንም አይመስለኝም ። እና ደሞ ቁጭ ብዬ በቁም ነገር ማስበው እንዴት ወንድ መሆን እንደምችል ነው ነገር ግን አንድ ቀን ህይወቴን ሙሉ ቀየረው እቤት ቁጭ ብዬ ነበር እና በቃ ወንድ ለመሆን ወስኜ ከወንድሜ ሱሪ ወስጄ ለራሴ በሚበቃኝ መልኩ ቁርጬ አስታካክይ ለቤሼ እንደዚሁም ጃኬቱን ለብሼ ጨርሼ ፀጉሬ ትዝ አለኝ በጣም ሚያናደው ፀጉሬ በጣም ትልቅ ነበር ግዴታ ፀጉር ቤት ሄጄ መቆረጥ ነበረብኝ እና ፀጉር ቤት ሄድኩ ወረፋ ብዙም ስላልነበረ ልቆረጥ ልክ ስቀመጥ ያየሁትን ማመን አቃተኝ 😬
አባቴ መጣ ደንግጦ ወደ ቤት እንዴት እንደወሰደኝ እና ደሞ በህይወቴ እንደዛ ቀን መቶኝ አያቅም ሱሪውን አሶልቆ ቀሚስ እና ሂጃብ በግድ አስለበሰኝ ከዛ ቡሃላ ግን ሂጃብ በራሱ ቀየረኝ ወደ እራሴ መመለስ ጀመርኩ ልክ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈትነን ስንጨርስ አባቴ ለ2 አመት መርከዝ አስገባኝ ከዛ ቡሀላ ህይወቴ ሙሉ ተቀየረ ከዛ የዲን ትምህርቴን ጨርሼ ስወጣ ዩኒቨርስቲ የተመደብኩበትን ሳይ አዲስ አበባ ነበር ደስ አለኝም ምክንያቱም ማየት ምፈልገው ከተማ ነበር እናም ቤተሰቦቼን ተሰናብቼ ሙሉ ዝግጅት አድርጌ ጉዞ ወደ አዲስ አበባ እየሄድኩ እያለ ታክሲው ውስጥ አጠገቤ .....
join @Halal_memory
9 521
ሀገር መመራት ያለበት በከተማ ልጅ ነው። ከተማ ስል ዝም ብሎ አስፓልት ላይ መኖር ማለቴ አይደለም፤ የከተማ ልጅነት የአስተሳሰብ ጉዳይ ነው።
¤
የከተማ ልጅ ካደገበት ሰፈር ጀምሮ የተለያየ ቋንቋ፣ ባህልና እምነት ካለው ሰው ጋር ተጠጋግቶ ስለሚያድግ Tolerance ልቡ ውስጥ አለ።
¤
የከተማ ልጅ በባህሪው Global Citizen ነው። ሰው ምን ይለኛል የሚል ስሜት አለው። ይሄ ደግሞ ለፖለቲካ መሪ በጣም አስፈላጊ ነው። ይሉኝታ ያለው መሪ ዝም ብሎ አይሰግጥም፤ ህዝቡ ፊት ሲቆም የሚያፍርበት ነገር እንዳይኖር ይጠነቀቃል።
¤
ገና በልጅነቱ ፒዛና እንጀራን፤ ኳስና ጌምን፤ ቸርችና መስጂድን ጎን ለጎን እያየ ስለሚያድግ እኔ ብቻ ልኑር አይልም።
¤
የከተማ ልጅ በብዙ ሰዎች መሃል ስለሚያድግ ነገሮችን በንግግር Diplomacy የመፍታት ብቃቱ ከፍተኛ ነው። Lee Kuan Yew ሲንጋፖርን ከአፈር ውስጥ አውጥቶ የአለም የንግድ ማዕከል ያደረገው Cosmopolitan አስተሳሰቡ ነው።
¤
ከተሜነት ማለት Style and Substance ነው። የከተማ ልጅ ስልጣን ላይ ሲወጣ ለራሱ ስም ለቤተሰቡ ክብር እና ለሰፈሩ ኩራት ሲል ታች አይወርድም። ተግባራቱ ሁሉ Standard ይኖረዋል።
¤
ሀገርን መምራት ማለት ከተማን ማስተዳደር ማለት ነው። ከተማን ደግሞ እንደ ከተማ ልጅ የሚያውቃት የለም።
9 521
{وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا لِي وَلْيُؤْمِنُوا بِي لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ}
