ru
Feedback
Halal memory🫀

Halal memory🫀

Открыть в Telegram

#ǫᴜʀᴀɴ & ʜᴀᴅɪs #ғᴜɴ ɪsʟᴀᴍɪᴄ ᴄᴏɴᴛᴇɴᴛ #вєѕт ɪsʟᴀᴍɪᴄ 𝑣𝑖𝑏𝑒 #ᴇᴠʀʏ ᴍᴜsʟɪᴍ ᴄᴏɴᴛᴇɴᴛ ╱◥██████◣. │∩│🪟▤│🪟│. ▓▆▇█▓🚪▓█▇. Cross @Usre_aviailabele

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала Halal memory🫀

Канал Halal memory🫀 (@halal_memory) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 10 079 подписчиков, занимая 9 220 место в категории Религия и духовность и 3 295 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 10 079 подписчиков.

Согласно последним данным от 04 июля, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило -259, а за последние 24 часа — -13, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 9.01%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 2.85% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 0 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 287 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 0.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
#ǫᴜʀᴀɴ & ʜᴀᴅɪs #ғᴜɴ ɪsʟᴀᴍɪᴄ ᴄᴏɴᴛᴇɴᴛ #вєѕт ɪsʟᴀᴍɪᴄ 𝑣𝑖𝑏𝑒 #ᴇᴠʀʏ ᴍᴜsʟɪᴍ ᴄᴏɴᴛᴇɴᴛ ╱◥██████◣. │∩│🪟▤│🪟│. ▓▆▇█▓🚪▓█▇. Cross @Usre_aviailabele

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 05 июля, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Религия и духовность.

10 079
Подписчики
-1324 часа
-457 дней
-25930 день
Архив постов
ደግነት ደንቆሮ የሚሰማው ዕውሮችም የሚያዩት ቋንቋ ነው።

...አንድ ቀን አላህ በምትጠብቀው መልካም ነገር ያበስርሃል... እርሱ ዕጣ ፈንታን በቅጽበት ቀያያሪ የሆነ ጌታ ነው .... ምቾትንም መከራ ካደከመው ልብ ውስጥ ሊከስት ዘንድ ቻይ ነውና....በአላህ
...አንድ ቀን አላህ በምትጠብቀው መልካም ነገር ያበስርሃል... እርሱ ዕጣ ፈንታን በቅጽበት ቀያያሪ የሆነ ጌታ ነው .... ምቾትንም መከራ ካደከመው ልብ ውስጥ ሊከስት ዘንድ ቻይ ነውና....በአላህ ላይ መልካምን እንጅ አትጠርጥር... [..وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ..] «.. አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡...»

«....ባሪያው ጌታውን እስከሚረሳው ድረስ ከርሱ ይዘናጋል....ጌታውም ይናፍቀውና ከፍቅሩ የተነሳ እርሱን እንዲያወሳ ሚያደርገው መከራን ይልክበታል.....ባሪያውም ይመለስና አላህን ማፍቀር ይጀምራል.
«....ባሪያው ጌታውን እስከሚረሳው ድረስ ከርሱ ይዘናጋል....ጌታውም ይናፍቀውና ከፍቅሩ የተነሳ እርሱን እንዲያወሳ ሚያደርገው መከራን ይልክበታል.....ባሪያውም ይመለስና አላህን ማፍቀር ይጀምራል.... አላህም ፍቅሩን ይሰጠዋል.....መከራውንም ያነሳለትና ጥሩ የሆነ ሲሳይን ይለግሰዋል..» ሰይዲ ሙተወሊ ሸዕራዊ 💙

Repost from Halal Fkr
አቡ ነውፈል “ፍቅር የማይዘው ሊኖር ይችላል?” ወይ ተብሎ ተጠየቁ፡ ‹‹አዎ! ደረቅና ደደብ ሰው ፍቅር ላይዘው ይችላል›› አሉ፤ ዓሊይ ቢን ዓብዳም ‹‹ፍቅር የማያጠቃው ሰው የለም፤ ተፈጥሮው ደረቅ፤
አቡ ነውፈል “ፍቅር የማይዘው ሊኖር ይችላል?” ወይ ተብሎ ተጠየቁ፡ ‹‹አዎ! ደረቅና ደደብ ሰው ፍቅር ላይዘው ይችላል›› አሉ፤ ዓሊይ ቢን ዓብዳም ‹‹ፍቅር የማያጠቃው ሰው የለም፤ ተፈጥሮው ደረቅ፤ ወኔው ጎደሎ ወይም የተዛባ ተፈጥሮ ያለው ሰው ሲቀር›› ብለዋል፡፡ ©️baledaw         𝓗𝓪𝓵𝓪𝓵 𝓕𝓴𝓻 ™

ሁሉም ነገር መስተካከል ያለበት አይደለም....ምናልባት አንዳንድ ህመሞች የሚሽሩት እንደነበረው ሲተው ነው...የሚያገግሙት ባለመነካታቸው ውስጥ ነው ...ምናልባት ባለመስተካከል ውስጥ ነው ሰላሙ ያለው
ሁሉም ነገር መስተካከል ያለበት አይደለም....ምናልባት አንዳንድ ህመሞች የሚሽሩት እንደነበረው ሲተው ነው...የሚያገግሙት ባለመነካታቸው ውስጥ ነው ...ምናልባት ባለመስተካከል ውስጥ ነው ሰላሙ ያለው ....ምናልባትም ትላንታችን ባለመታወሱ ውስጥ ነው መረጋጋት ያለው ...ይህ ሽሽት አይደለም..አላህ ልቦችን ከሚያክምባቸው መንገዶች አንዱ እንጂ...ስለዚህ .. ሰው ሲያዝን ..ሲከፋው ..ድባቴ ውስጥ ሲገባ ከዛ ሰው ጎን መሆን ...ማባሸር ችግሩን መጋራት.. ህመሙን መታመም ..መፍትሄውን ማፈላለግ የወዳጅነት ማዕረጉ እና ደንቡ ቢሆንም ...አንዳንዴ ግን እነዚህ ነገሮች በዝምታ የሚከናወኑ እና ፋታ በመስጠት ውስጥ የሚፈፀሙ ናቸው...በዛ መልኩ ወዳጅነታችን ሚገለፅባቸው ቀናቶች አሉ...!

Story

አፍሪካ ቲቪ ለወንዶች ብቻ የወጣ ማስታወቂያ

ከባድ ነው በዚህ ዝናብ፣ታክሲ ግፊያ፣እና ላጤነት🥲

"..ሁሌም ቢሆን ችግርህን ለማንም ሳትናገር ለመፍታት ጣር.." "..ላንቺም ቢሆን..?" "..መች ነው እኔ 'ማንም' የሆንኩት?!.." "አይ እኔኮ ከአንተ ውጪ ከማንም ጋር እንዳታወራው ስትዪኝ..." "..እኮ መች ነው እኔ ካንተ ውጪ የሆንኩት?.." "..አፍ አፌን አትበዪኛ ላስረዳሽ.." "..ተወው አታስረዳኝ እንደውም እኔ ነኝ ጥፋተኛ.." "..ካልሽ..እሺ .." "..አየህ ብትወደኝ ኖሮ ልታስረዳኝ ትሞክር ነበር.." "..ላስረዳሽ የምችለው ነገር እንዳለ ካወቅሽ እኮ.." "..ተወኝ.. ምንም አታብራራልኝ.." "..እሺ ይቅርታ.." "..የልብህን ከተናገርክ በኋላ ይቅርታ?!..ቀልደኛ.." "..አንድ ነገር ልንገርሽ.." (ዝምም) "..ለማንም የማልናገረው ችግሬ አንቺ ነሽ.." (ሳቀች) "..ሂዛ..ሞዛዛ.." (ፈገግኩላት) የምሬን እንደሆነ ማን በነገራት .. (..የሰው ዕጢ..)

ሴቶች ግን ተለክታችሁ የገዛችሁት የሚበቃቹህ ሂጃብ ስራ ስትጀምሩ ወይም ወጣ ወጣ ስንሉ ወደ  ታች የሚለው ለምንድነው ?ከሂጃቡ ነው ወይስ ከመንገዱ እና ስራ ቦታው ?💔

የመዲናውን ባየነው አይኑን፣ በኑር አረንጓዴ የተኳለውን፣ ፊቱ ከጨረቃ የሚያበራውን፤ ሰሉ አለ ረሱል ﷺ💚

الصلاة والسلام عليك يا سيدي يا رسول الله ♥

~ከኢብሊስጋ የተደረገ ምናባዊ ኢንተርቪው ~~ ¤ጋዜጠኛው ÷ከስምህ እንጀምር። ዓለም የሚያውቅህ በብዙ አስፈሪ መጠሪያዎች ነው። ሸይጧን፣ ኢብሊስ፣ ሰይጣን... እነዚህ ግን ትክክለኛ ስሞችህ ናቸው? ኢብሊስ: "ሸይጧን ወይም ኢብሊስ ትክክለኛ ስሜ ሳይሆን ተግባሬን የሚገልፁ ቅጽሎች ናቸው ።ሸይጧን' ማለት እኮ 'ከእዝነት የራቀ' ወይም 'ባላንጣ' ማለት ነው። 'ኢብሊስ' ደግሞ 'ተስፋ የቆረጠ' ማለት ነው። እነዚህ በአላህ እዝነት ተስፋ ቆረጬ ከነበረኝ ክብር ስባረር የተሰጡኝ የውድቀት ማዕረጎች ናቸው። ዛሬ የምታውቀኝ በእነዚህ ስሞች ነው። ነገር ግን... ከመውደቄ በፊት... እኔ ግን በአንድ ወቅት የራሴ ስም ነበረኝ... አዛዚል! ያ ስም የክብር ነበር። ያ ስም የአምልኮ ነበር። ዛሬ ግን ያ ስም በሰማያት መዝገብ ላይ ተፍቋል።" ¤∞∞ ጋዜጠኛው፡ "አዛዚል... ደስ የሚል ስም ነው ! ግን ይህ የክብር ስም ወደ 'ኢብሊስ' የተቀየረው በአንድ ጀንበር አልነበረም። እስኪ እናንተ ጂኖች ከምን ተፈጠራችሁ? አደም ከመፈጠሩ በፊት ምን ትሰሩ ነበር? ኢብሊስ÷እኛ የተፈጠርነው እናንተ ከመፈጠራችሁ በብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ነው።እናንተ ከጭቃ አፈር ስትፈጠሩ እኔና ወገኖቼ ጂኖች ግን የተፈጠርነው ከሚንቀለቀል፣ ከማይጨስ ንጹህ የእሳት ነበልባል (ማሪጅ) ነው። እንደ ነፋስ ፈጣን፣ እንደ ብርሃን ረቂቅ፣ እንደ እሳት የሚንቀለቀል ተፈጥሮ ተሰጠን። እኔ የዚህ ተፈጥሮ ውጤት ነኝ። የጥንታዊው ነበልባል ልጅ ነን። እየውልህ እኛ ጂኖች ከተፈጠርን በኋላ ከሰው ልጅ በብዙ ሺህ ዓመታት ቀድመን ምድርን እንኖርባት ነበር። እኛ በባህሪያችን የረቀቅን፣ ከቦታ ቦታ በፍጥነት የምንወነጨፍ ኃያላን ነበርን።ወገኖቼ ጂኖች በምድር ላይ እንደ ልባቸው ይኖሩ ነበር። ∞ ግን ወገኖቼ... ጂኖች... ስሜታቸውን መቆጣጠር አቃታቸው። ተፈጥሯችን እንደ ነበልባሉ ስለነበር፣ ቶሎ እንቀጣጠል ነበር። እሳትነታቸው ፈተናቸው። ስልጣን ሲበዛባቸው አመፁ። ምድርን በደም አጨቀዩዋት። እርስ በርስ ተላለቁ።ምድሪቱን በጥፋትና በክፋት አደፏት። ምድር በጂኖች ጩኸትና ግጭት ታወከች። ያኔ ነበር አላህ መላእክትን ልኮ ምድርን እንዲያጸዱ ያዘዘው። ብዙዎቹ ጂኖች ጠፉ፣ የተረፉትም ወደ ተራራዎችና ደሴቶች ተሰደዱ።" ​ጋዜጠኛው፡ "አንተስ በዚያን ጊዜ ከእነርሱ ጋር ነበርክ? እንዴት ነው ከጥፋቱ ተርፈህ ወደ ሰማያት ከፍ ያልከው? አመፅ ውስጥ አልነበርክም?" ​ኢብሊስ፡ እኔ ከወገኖቼ የተለየሁ ነበርኩ። እነርሱ በምኞት ሲታወሩ፣ እኔ በዚያን ጊዜ የአምልኮ ጥማት ነበረኝ። ወገኖቼ ሲያምፁ እኔ እሰግድ ነበር። እነሱ ሲያጠፉ እኔ አላህን አመሰግን ነበር።በአምልኮቴና በንጽህናዬ ምክንያት መላእክት ወደ ሰማይ ይዘውኝ ወጡ። የአምልኮቴ ጽናት ከመላእክት ጋር እንድቀላቀል አደረገኝ። የጂን ዘር ሆኜ ሳለ፣ በመላእክት መሃል እንደ አንዱ ሆኜ ተቆጠርኩ።በሰማያት ውስጥ እኔ አላህን ያላወደስኩበት ሱጁድ ያላረግኩበት አንድም ኢንች ስፍራ የለም።መላእክት ያከብሩኝ ነበር። በጋራ ለአላህ ምስጋና እናቀርብ ነበር። ዓለሙ ንጹህ ነበር። እኔም ንጹህ ነበርኩ... ወይም ቢያንስ፣ ንጹህ እንደሆንኩ አስብ ነበር። ጋዜጠኛው፡ "ታዲያ ያ ሁሉ ክብር፣ ያ ሁሉ እውቀትና አምልኮ... እንዴት በአንድ አፍታ ሊፈርስ ቻለ? የውድቀትህ ዘር የተዘራው መቼ ነበር? አዳም ሲፈጠር ነው ወይስ ከዚያ በፊትም በውስጥህ የሆነ ነገር ነበር?" ​ኢብሊስ፡ ውድቀት በአንድ ሌሊት አይመጣም።በመላእክት መካከል ስኖር አንድ ነገር አስተዋልኩ። እነርሱ የታዘዙትን ብቻ የሚያደርጉ፣ የራሳቸው ፍላጎት የሌላቸው ፍጡራን ናቸው። እኔ ግን ጂን ስለሆንኩ ምርጫ ነበረኝ። ምርጫ ኖሮኝ መታዘዜ ከእነርሱ የተሻልኩ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ አደረገኝ።ይህ ልዩነት በውስጤ ስውር ኩራት ፈጠረ። እኔ ከጂን ተፈጥሬ በመላእክት ጉባኤ ከተቀመጥኩ፣ ታዲያ ከእኔ በላይ ማን አለ?' ብዬ ማሰብ ጀምሬ ነበረ። ትህትና የመሰለ ትዕቢት ነበር የያዝኩት። አምልኮዬ ለራሴ ክብር ምንጭ ሆነብኝ። ራሴን እንደ ልዩ ፍጡር ማየት ጀመርኩ። ይህ ሁሉ የሆነው ገና ያ የሸክላ ሰው ከመምጣቱ በፊት ነው። እናም አላህ ... 'በምድር ላይ ምትክን (ከሊፋ) አደርጋለሁ' ብሎ ያንን አስደንጋጭ ዜና ሲናገር... በውስጤ የነበረው እሳት በቅናት ነደደ።መላእክት ስለ ደም መፋሰስ ፈሩ። እኔ ግን ለምን?' አልኩ። 'እኔ እያለሁ ለምን ሌላ ያስፈልጋል?'የሚለው ስሜት አንገበገበኝ። ጋዜጠኛ: ከዚያ አዳም ተፈጠረ። ገና ነፍስ ያልተዘራበት፣ የተጋደመ የሸክላ ምስል ሆኖ ስታየው... ለመጀመሪያ ጊዜ ምን ተሰማህ?" " ኢብሊስ:ንቀት። ንጹህ ንቀት። አዳም ከጭቃ ተቦክቶ፣ ገና ነፍስ ሳይዘራበት አርባ ቀን (ወይም ዓመታት) ተቀምጦ ነበር። በዛን ጊዜ ነበር የእኔ ክፋት የጀመረው። ገና ነፍስ ሳይዘራበት፣ እንደ ደረቅ ሸክላ ተጋድሞ ሳለ ወደ እሱ ሄድኩ።ሆዱን መታሁት፤ እንደ ባዶ ጋን ድምጽ አሰማ።ባዶ ነው' አልኩ። ውስጡ ክፍት መሆኑን አየሁ። 'ውስጡ ክፍት ከሆነ ራሱን መቆጣጠር አይችልም፣ በምኞት ይሞላል' ብዬ ተረዳሁ። ውስጡን ሳይ ባዶነት፣ ሆድ፣ እና ፍላጎት ብቻ አየሁበት።ለአላህ ክብር የሚመጥን አልነበረም። ያኔ በራሴ እንዲህ አልኩ፦ "ይህ ፍጡር በእኔ ላይ ከተሾመ አልታዘዘውም፤ እኔ በእርሱ ላይ ከተሾምኩ ግን አጠፋዋለሁ።" በልቤ ውስጥ ያለው ኩራት ገና ነፍስ ሳይነፋበት ዘላለማዊ ጠላቴ አደረገው። ጌታዬ ለአለም ሚስጥር አድርጎ ያቀረበውን እኔ እንደ ተራ ቆሻሻ አየሁት። ጋዜጠኛው፡ "በኋላ ላይ ነፍስ ተዘራበት። ተነሳ። እና አላህ ስሞችን አስተማረው። አንተ የማታውቃቸውን ስሞች። በዚህ ጊዜ ምን ተሰማህ? ኢብሊስ: እውቀት በነጻ ሲሰጥ ማየት ያማል።እኔ ለሺህ ዘመናት የለፋሁ ተማሪ ነኝ። አዳም ግን ገና ትናንት ተፈጠሮ፣ ምንም ሳይለፋ፣በአንድ ጀምበር ሁሉንም ስሞች አወቀ።እውቀቱ የተሰጠው ነው እንጂ ያገኘው አልነበረም።ዕውቀቱ እንደኔ ጥረት ውጤት ሳይሆን የፈጣሪ ስጦታ ነበር። ይሄ አድሎ ነው ብዬ አሰብኩ ።ይህ ፍጡር የተከበረው በራሱ ጥንካሬ ሳይሆን፣ በተሰጠው ሚስጥር ነው። ያ ደግሞ የበለጠ አናደደኝ። ጋዜጠኛው፡ "አሁን ወደ ወሳኙ ቀን እንምጣ። ፡ 'ለአዳም ስገዱ የሚለው ትዕዛዙ ተላለፈ፣ ሁሉም ወደቁ። ሁሉም ግንባራቸውን መሬት አስነኩ። አንተ ግን ቀጥ ብለህ ቆምክ። በዛች ቅጽበት... በዛች ሰከንድ ምን እያሰብክ ነበር? የምር፣ እምቢ ማለት የሚያስከትለውን መዘዝ አላወቅክም ነበር? ኢብሊስ: ያቺ ቅጽበት...ትዕዛዙ እንደ ነጎድጓድ ሲያስተጋባ መላእክቱ ሁሉ ጅብሪል፣ ሚካኤል፣ እስራፊል እንደ ተራራ ናዱ። ታላቅ የሱጁድ ማዕበል ሆነ።‎እኔ ግን ቀጥ ብዬ ቆምኩ።ፊት ለፊቴ ያ ከጭቃ የተሰራ ሰው አለ። ትዕዛዙ ከጌታዬ እንደሆነ፣ አውቃለሁ... ይቀጥላል~~~

የሆነች ልጅ ጂኒ ይዟት ኡስታዝ ተጠራና እየቀራባት ጂኒው " ሊያገባት ፈልጎ ነውኮ የሚቀራብኝ "  አለ😶 ፣ ኡስታዝየውም " አንተ ውሸታም ዝምበል አሉት " ። የሚገርመው  ጂኒው እንደ ድንገት ገጥሞለት ልጅቷ ተሽሏት ያንኑ ኡስታዝ አገባች 👐

ተው ባካችሁ ጂኒዎች እኛ ውስጥ የሚገቡት እኮ 'ወደውት' አይመስለኝም ፣ ባይሆን በጂኒዎች ዓለም ክፉኛ ያጠፉ፣ ስርዓት የጣሱ ወይም አመፅ የቀሰቀሱ "ወንጀለኛ ጂኒዎችን" ለመቅጣት እንደ    'High Security Prison' ነው ሚጠቀሙብን እንጂ እንዴት ነው እንደፈለገ መብረር የሚችል ፍጥረት ከኔጋ ሆኖ ሜክሲኮ ታክሲ ሚጋፋው?

ጂኖች ባናያቸውም በራሳቸው ዳይሜንሽን ሚገርም ስልጣኔ መስርተው ነው ሚኖሩት ይላሉ ሙአሪኾቹ እና ያው እነሱምጋ በስልጣንና በሀብት የናጠጡ የጅን መኳንንት እንዳሉ ሁሉ፣ የዕለት ጉርሳቸውን ለማግኘት የሚኳትኑ "ደሃ ጅኖችም" ይኖራሉ ማለነው። so እኛ ጋር መጥተው ከጠንቋይጋ ተሻርከው ምናምን ሰላም የሚነሱንና አዛ ሚያረጉን፣ በጅኖች ዓለም በየኢኮኖሚ ቀውስ የገጠማቸው፣ ቤትና ንብረት የሌላቸው እና ስራ ፈትተው የሚንከራተቱት የጂን ወገኖች ብቻ ቢሆኑስ? i mean ደሃ ሚባለው ጅን የሚበላውና የሚጠጣው ሲያጣ፣ አማራጭ ፍለጋ ወደ ሰዎች ዓለም መጥቶ "ይህችን ምስኪን ሰው ላስፈራራትና ቃሊቻ ቤት ወስጄ ላስገብራት ብሎ አቅዶ ቢሆንስ 🤲 መቼስ ቢሊየነሩ ጅን እዛ ቢዝነሱን ሲያራውጥ ለኛ ግዜ አይኖረውም ብዬኮነው

➽ broo...ከዚህ ቡኃላ DM ምታወራቸው ናቸው መጥፊያህ ..እባክህ ስማኝና ደናደር 🤳

የጭንቅላትህን "Overtime" ክፍያ ማነው የሚከፍለው? ∞ ​አንዳንድ ጊዜ Overthinking ማለት ጭንቅላትህ ውስጥ ያለ ነፃ የፊልም ፕሮዳክሽን ነው፤ ዳይሬክተሩም፣ ተዋናዩም፣ ተጎጂውም አንተ ነህ። ገና ያልተከሰተን ችግር 10 ጊዜ ተለማምደህ ስትጨርስ እውነታው ሲመጣ ግን አቅም ታጣለህ። ∞ ​Let’s be real... Overthinking is not a superpower, it’s a silent thief of your inner peace.💔 አእምሯችን መፍትሄ ለማግኘት ሲጥር "መፍትሄው ራሱ መጨነቅ ነው" ብሎ ያምናል። ግን እውነታው Overthinking ችግርን አይፈታም፣ ይልቁንም ያለህን ሰላም ይበላዋል። This is a mental pattern, not your identity. ​ በዝምታ የምታለቅሱ፣ ምሽት ላይ እንቅልፍ አጥታችሁ ከራሳችሁ ጋር የምትሟገቱ ዛሬ ይሄንን ማንም ካልነገራቹህ ይህ ለናንተ ነው እንተ "እብድ" ወይም "ደካማ" አይደለህም። አእምሮህ አንተን ለመጠበቅ በጣም እየሞከረ ነው! ግን በተሳሳተ መንገድ። ሁሌም ደግነት ለራስህ በመስጠት ጀምር።🤍 ​ በነጻ ለምትሰራው የጭንቅላትህ "Overtime" ስራ ማንም አይከፍልህም። So, stop being a prisoner of your own thoughts.

~masterbation part 2 ~ አዕምሯችን የፀነሰውን ፅንስ ለመግለጥ የተለያዩ አማራጮችን ይጠቀማል ..ከዛም ውስጥ ምቹ እና ቀላሉ ማስተርቤሽን ይሆናል ። ይህን ተግባር በእርካታ ውስጥ ቅጣት ይሉታል ። የፅንሱ ሴሎች የምንላቸው በስልኮቻችን ስክሪን ውስጥ የምናገኛቸው ምስሎች እና ከውጪው አለም የሚንፀባረቁ ምስሎች እንደሆኑት ሁሉ በወሲብ አለም ውስጥ የተዘፈቁ ቀልዶች እና ፅሁፎች የራሳቸው ድርሻ አላቸው ። እንዲሁም ልቅ የሆነ የተቃራኒ ፆታ ፍላጎት የራሱ ተፅዕኖ አለው ። ምናልባት የነፍስን ምንነን በደንብ አልተረዳንም ...ነፍስ ደስታን ስቃይ በሚያስከትልባት ነገር ውስጥ ስቃዩን ችላ በማለት ደስታን የምታሳድድ ሀይልም ናት ! የቂያም ለት የሰውነት አካሎች ሁሉ ሲመሰክሩ ነፍስ በድንጋጤ የምትዋልል የተለየች ነገር አይደለች ? ከላይ እንዳልኳቹ ማስተርቤሽን በእርካታ ውስጥ ቅጣት ነው ....አይን እና ሌሎች አካላቶቻችን ተባብረው ለሰሩት ቅጣቱን ነፍስ ላይ የመጫኛ መንገድ ነው ! ይህ ስራ የደስታ መንገድ ሳይሆን አንድ ራሱን የቻለ የቅጣት አይነት ነው ። ልክ ቁስሉ ያሳከከው ሰው በቻለው ልክ አኮ ቁስሉን ቢመለከት አጥንት እንደሚያየው ሁሉ በዚህ መንገድ በብዙ የተመላለሰ ሰው ነብሱን ሲመለከት እጅግ ደካማ ፣ ተስፋ የቆረጠች....የባከነች እና ራሷን የምትጠላ ነፍስ ያያል ። ራስን በራስ ማርካት ከነፍስ ላይ ተስፋን...ህልምን...ጥንካሬን ...ደስታን መገንጠያ መሳርያ ነው ። በዚህ አጭር ሂደት ውስጥ የሚከሰተው ራስን የመጥላት እና ራስን የመናቅ ዝንባሌ በመኖር ውስጥ ከሚከሰቱ ትላልቅ ስህተቶች ከሚመነጨው የበለጠ ነው ። በዚህ ጨለማ አለም ውስጥ የተዘፈቀ ሰው ድንጉጥ ነው ...ጥንካሬውን በተሳሳተ ሜዳ የጨረሰ ጦረኛ ነው ። ልፍስፍስ ነው ....ድፍረቱን ያባከነ ነውና ። እይታው ያጠረ ነው ....እይታውን በራሱ ላይ በመተኮስ አባክኗልና ። ይህ ስራ ነፍስን ከማድከም እና ራስን ከመጥላት ባሻገር አካላዊ ጉዳቱም ከባድ ነው ....መኪና በረጅም መንገድ ላይ ሳለ በየሰዓቱ ነዳጁን እየደፋ ቢሄድ ምን ይሆናል ? በዚህ ተግባር ውስጥ ያለም ሰው ምሳሌው ይህ ነው ! ጉልበት ነው ያለአግባብ እየተደፋ ያለው..የ testestrone hormone እጥረት የጸጉር መሳሳት ፤እውነተኛ ወሲባዊ ግንኙነት የማድረግ ችግር ቶሎ መሰልቸት, የሰውነት መዛል አይነ ስውርነት ራስ ምታት ፤ለግብረ-ሰዶማዊነት ፍላጎት መጨመር.. ይሄ ብቻ አይደለም በሚገርም ሁኔታ ለማይታየው አለምም ተጋላጭ ያደርጋል ...ጀናባ የሆነ አካል ነፍሱ ደካማ ትሆናለች እንደ አኸላለቃችን ጂኒዎች ለሰው ልጅ ፍራቻ ያላቸው ሲሆን በዛ ርክሰት ውስጥ እና ጀናባነት ውስጥ ያለን አካል አይፈሩም ....ይህም ማለት ለጂኒ ጥቃት ተጋላጭነታችንን ይጨምራል ! ይህ አሊሞች የተናገሩት ንግግር ነው ። ማስተርቤሽን አለም ላይ ካመጣው ጉዳት በጣም ትልቁ የፆታ አመለካከትን ማዛባት ይመስለኛል ። በዚህ የጨለማ አለም ውስጥ ያለ ሰው አጠገቡ ያሉ ተቃራኒ ፆታዎችን ሰው ከሚል ፍቺ የፋቀ ይመስለኛል ። ወንዱ ሴቱን ሲመለከት የሚያየው አንድ የወሲብ መፈፀሚያ እቃ  ...ሴቷም ወንድ ስትመለከት የሚታያት በተመሳሳይ ከሆነ ከዚህ በበለጠ ምን አይነት ጉዳት ሊያስከትል ይችላል ?.. ለቅፅበታዊ ደስታ አሁንም ራስህን ትገብራለህ? አረፈደም ከዚህ ቀውስ ለመውጣት ቀላሉ መፍትሄ sport መስራት በመንፈሳዊ ህይወትህ በዲንህ ወደአላህ መቃረብ.. ወደዚህ የሚገፋፉ s.media content ከስልክህ ጥርቅም ማድረግ ..ወደ sexchat ወደ hot content የሚገፋፉ ሁኔታና ሚድያዎችን ጥርቅም ማድረግ ከዛ በአጭር ቀን ሌላ ህይወት ሌላ ሰው ትሆናለህ።

ኢትዮጵያ ውስጥ 85% የሚሆነው ወጣት የ Masterbation [ ሴጋ ] ሱስ ተጠቂ ነው። ወጣቱ ተዘፍቋል። ∞ አንድ ጥናት ባወጣው መረጃ መሰረት ከ 17 አመት እስከ 35 አመት እድሜ ክልል ላይ የሚገኙ 85% ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች አዘውትረው አልያም አልፎ አልፎ ግለ ወሲብ ይፈፅማሉ። ሴቶቹም ጭምር። ∞ የሆነ ጊዜ መንግስት የ Porn ሳይቶችን በሙሉ አጠፋፍቶ ገላግሎን ነበር። ነገር ግን በ VPN የተለያዩ ሳይቶችን የሚመለከቱ ወጣቶች በርካታ ናቸው። በነገራችን ላይ.. እነዚህ የ Pornography ሳይቶች በአብዛኛዎቹ የሚሰሩት Sex Trafficked ተደርገው በሚመጡ ሴት ተዋንያን ነው። The Actors are in drug influence. ይሄ የ Porn Addiction ችግር አለምአቀፋዊ ነው። በአሜሪካ ራሱ 40 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች የወሲብ ፊልም ሱሰኛ ናቸው። እነዚህን የወሲብ ሳይቶች በየእለቱ የሚጎበኙ አሜሪካዊያን ቁጥር 40 ሚሊየን ደርሷል። ∞ የእኛ ሀገር ደግሞ ይብሳል ነው የምላችሁ በአለም አቀፍ ደረጃ Google ራሱ ባወጣው ጥናት Sex የሚለውን ቃል ደጋግሞ search በማድረግ ኢትዮጵያ ከአለም 2ኛ ናት።የአለም የ Porn Industry ከ 100 ቢሊየን ዶላር በላይ የሚያንቀሳቅስ ሰፊ ኢንዱስትሪ ነው። Porn sites get more visitors each month than Netflix, Amazon and Twitter combined. ከዚህ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ የሚወስደው የ Porn site ደግሞ p.**.h ነው። ∞. P**h ባለፈው አመት በ 2024 ብቻ 41 ቢሊየን ጊዜ search ተደርጓል። በነገራችን ላይ.. ለመጀመርያ ጊዜ የተሰራው የ Porn ፊልም የተሰራው በ 1908 ዓ.ም ነበር ከ Internet በፊት ራሱ porn ነበር። ኢትዮጵያ በህግ Pornographyን መከልከል ይገባታል ብዬ አስባለሁ ፤ ካልተከለከለ sex የሚለውን ቃል Google ላይ Search በማድረግ 2ኛ የነበርነው በቅርቡ ደግሞ 1ኛ መሆናችንና ወርቁን መብላታችን አይቀርም። ∞∞ በአለማችን ላይ ከሚገኙ 204 ሀገራት ውስጥ በ 17 ሀገሮች የ Porn ፊልሞችን ማየት በህግ ያስቀጣል። በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ 70% የሚሆኑ በየትኛውም እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወንዶች ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ Porn ያያሉ። ጉዳዩ እጅግ በጣም ሲሪየስ ነው። ማንም ሰው በግልፅ ስለማያወራው ነው እንጂ የወሲብ ፊልም ሱስ- ስነ ልቦናን የሚያዳክም፣ የፀፀት ስሜት ውስጥ የሚከት፣ የአእምሮን የማሰብ ደረጃ የሚያዛባ ነገር ነው። ∞ ወላጆች --- ልጆቻችሁ ስልክ ላይ ያለውን ነገር ተከታተሉ። ከ 15 አመት ጀምሮ ያሉ ልጆቻችሁን ስልኮቻቸውን በደንብ ተከታተሉ። የብዙ ሰው Google History ቼክ ቢደረግ ብዙ ጉድ ነበር የሚወጣው። የማትጠብቋቸው ሰዎች Porn Addicted ናቸው ወይም በወሲብ ፊልም ሱስ የተጠቁ ናቸው። ወጣቱ ደንዝዟል። ይሄ ነገር አእምሮውን ተቆጣጥሮታል። አብዛኛው ወጣት ጠዋት፣ ቀን፣ ማታ በዚህ ሱስ ውስጥ ተዘፍቆ ነው ያለው። በነገራችን ላይ ከሱሶች በጣም የከፋ መጥፎ ሱስ ነው ወጣቶችን ህልማቸውን እንዳይኖሩ ፈጣሪህን እንዳትገዛ+ እራስህን እንዳትለውጥ እና እንዳትሻሻል፥ ኮንፊደንስ እንዳይሰማህ፥ ከሰው በታች ነኝ ብለህ እንድታስብ የበታችነት እንዲሰማ አድርጎ ጠፍሮ አስሮ! የሚያስቀምጥህ መጥፎ መንፈስ ነው ! ግን ማንም ስለዚህ ጉዳይ አያወራም። part 2 ይቀጥላል~~~