649
Subscribers
+224 hours
+107 days
+2730 days
Posts Archive
የፎቶግራፈሩ ማስታወሻ ፦ እነዚህ ምስሎች በዋናነት በትዳር ውስጥ በሚፈጠር የተካረረ ጸብ እና መለያየት ወቅት ጎጆ ሲፈርስ ልብ ባይባሉም ከማንም በላይ የስነ ልቡና ተጎጂ ሊሆኑ የሚችሉ ሕፃናትን በማሰብ ያነሣኋቸው ፎቶግራፎች ናቸው።
Repost from B e t h e l 🌻
🎙 Song title - B a t i
🎼 Artist - C h e l i n a
🎧 Cover Music - B e t h e l 🌻
🕸 https://t.me/BethelGSong"ብዙ ተኛሁ፡፡ ከትናንት ማታ አንድ ሰዓት እስከ ዛሬ ጠዋት ሁለት ሰዓት ነው የተኛሁት፡፡ ስባንን፣ ድንገተኛ የመሰለች ነገ መሃል ተጠናቅቄ ወድቄአለሁ፡፡ ደክሞኛል፡፡ ብዙ ስተኛ ይደክመኛል፡፡ ብርድ ልብሴ ከአልጋ ላይ ተንሸራቶ ወርዶ በከፊል መሬት ላይ ነው። ትራሴ አንደኛው ጎኑ አልጋ ላይ፣ ሌላው ጎኑ ደሞ ከአልጋው ጠርዝ ወጥቶ አየር ላይ ነው፡፡ ከአፌ በሚወጣ ለሃጭ የትራስ ልብሴ ተዥጎርጉሯል። ትራሴ ደሞ ከቀረጢቱ እየተንሸራተተ ወጥቶ ጣፊያ መስሎ ብቅ ብሎአል።"
ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ|
የመንግሥቱ ነዋይ ጊዜ|Adam Reta
Self_portrait | Gebrela Shewakena
ማለት በጊዜ ኺደት ኹሉም ነገር የበለጠ ይመሰቃቀላል። ያለፍናቸውን ቀናት እንናፍቃለን። “ያ ደጉ ዘመን” ይባላል። “ልጅነቴ ልጅነቴ ማርና ወተቴ” ይባላል። ቀላል የሃይ ስኩል ፊዚካ ነው። entropy ይባላል። ማለት እየፈረስን ይሁን እየተሰራን በጊዜ ኺደት ግን ቅርፅ እየቀየርን እንመጣለን፡፡ እና ትናንቶቻችን ያምራሉ። ከዛሬዎቻችን የበለጠ ያልተዘበራረቁ ናቸው፡፡
ስለ ትናንሽ አለላዎች በዮናስ አ. Yo Na
ሜክሲኮ ጃዕፈር መፅሐፍ መደብር ያገኙታል Jafer Shifa Book
እማዬ ሁልጊዜ እኔ እና ብሩክን ይዛ ስትወጣ "አይ ወይዘሮ ኤልሳቤጥ !ሴቷን ልጅ አጥቁረሽ ቅላትሽን ሁሉ ወንዱ ልጅ ላይ አባከንሽው! መልክ ለወንድ ልጅ ምን ያደርጋል አሁን ? አሄሄ! ይላሉ...
እኔ እንዲህ እና እንዲያ ሳስብ ቴሌቪዥኑ ላይ ጓድ መንግሥቱ ኃይለማርያም የዛምቢያውን ፕሬዝዳንት ኬኔት ካውንድን ሲቀበሉ የሚያሳይ ምስል መጣ።
መንግሰቱ ሀይለማርያም በመጣ ቁጥር የሚቀለድብኝ ቀልድ እስኪጀምር ጠበቅኩ፤"መንጌ እኮ አባትሽ ነው"ሊሉኝ ነው።ጠበቅኳቸው።እህቴ ቀደመችና "ይሄውልሽ ሜሮን! አጎትሽ አባትሽን ሊጠይቅ አዲስ አበባ መጣ!" ሁሉም ሣቁ። እኔ ግን ነጭ መሃረብ እያርገበገበ ከአውሮፕላን ደረጃ ላይ የሚወርደውን "አጎቴን" ኬኔት ካውንድን እያየው እግዚአብሔር ከ ነነጭ መሃረቡ በአውሎ ንፋስ ጥ...ር...ግ አድርጎ ወደመጣበት ቢመልሰው እየተመኘው ከእንባዬ ተናነቅኩ።ደግሞ በዚህ ጥቁረቱ ላይ ነጭ መሃረብ የሚይዘው አማረብኝ ብሎ ነው ?...ወይስ ከሩቅ እንዲታይ ?አንጀቴን አሳረረው።
"ዕያት..ዕያት ...በሸቀች! በሸቀች!" ይላሉ እየተቀባበሉ
"አትናደጂ ይባስ ያጠቁርሻል"አለ ብሩክ ፣ አጠገቤ መጥቶ እየሳቀ ...
ከባርቾ መፅሐፍ
