cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ANRS public prosecutors

Show more
Advertising posts
282
Subscribers
No data24 hours
-17 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በዋስትና ጉዳይ ዋሱ በሚከሰስበት ጊዜ ዋስ የሆነን ሰው ሊያነሳቸው የሚችሉ መከራከሪያዎች ፡- የዋስትና ውል ማለት ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ሰዎች ባደረጉት ውል ግዴታ የገባው ሰው እንደውሉ ግዴታውን ባይፈጽም እኔ በባለእዳው ፈንታ ሆኜ ግዴታውን እፈጽማለው ብሎ ለባለገንዘቡ የጽሁፍ ማረጋገጫ የሚሰጥበት የውል አይነት ሲሆን በውሉ ላይ በግልጽ ዋስትናው የአንድነት እና የነጠላ ዋስ ነው ተብሎ ካልተገጸ በስተቀር ማንኛውም ዋስትና ተራ የዋስተና አይነት እንደሆነ እንደሚገመት የፍትሀብሄር ህጉ ቁጥር 1934 የሚደነግግ ሲሆን በዚህም የዋስትና አይነት(ተራ ዋስትና) ዋስ የሆነ ሰው በሚከሰስበት ጊዜ የሚከተሉት መከራከሪያዎችን በማቅረብ ከሳን ወይም ባለገንዘቡን ሊሞግተው ይችላል፡- 1ኛ.ከዋናው ባለእዳ ጋር ተከራከር (benefit of discussion) የማለት መብት ይህ ማለት ባለገንዘቡ ዋናውን ባለእዳ አስቀድሞ ሳይከሰው ዋሱን በከሰሰው ጊዜ ዋሱ ባለገንዘቡን ‹‹‹ከዋናው ባለእዳ ጋር ተከራከር›› የማለት መብት ያለው ሲሆን ዋሱ ይህንን የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ሳያቀርብ ቀርቶ ክርክሩ ቢቀጥል ዋናው ባለእዳ ግዴታውን የመፈጸም አቅም ኖሮት ቢሆን እንኳን ዋሱ ባለገንዘቡ ለሚያቀርብበት ጥያቄ ሁሉ ሀላፊ እንደሚሆን የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 1934፤1935፤1939 እና የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 244 ያስገነዝባል፡፡ ሆኖም ግን ዋሱ ይህንን መከራከሪያ ሲያቀርብ ዋናው ባለእዳ የገባበትን ግዴታ የመፈጸም አቅም ያለው መሆኑን የማስረዳት፤ የባለእዳው ንብረት የመምራት እንዲሁም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ለክርክሩ የሚያስፈልገውን ወጪ የማስያዝ ሀላፊነት ያለበት ሲሆን ዋሱ ይህንን ግዴታውን ተወጥቶ በባለገንዘቡ ቸልተኝነት ባለእዳው ንብረት ያሸሸ እንዲሆም ባለእዳው ኪሳራ ቢደርስደበት ዋሱ በመራው ወይም ባስያዘው ንብረት ልክ ሀላፊነቱን በሙሉ ወይም በከፊል ይወርድለታል፡፡ በዘህ ገዳይ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥሩ 25115 ተራ ዋስ እዳው ለመክፈል የሚገደደው ዋናው ባለእዳ ግዴታውን መወጣት የማይችል መሆኑን ሲረጋገጥ ነው በማለት አብራርቶታል፡፡ 2ኛ. እዳን የመከፋፈል መብት (benefit of divission) ዋሱ የባለእዳው እዳ እንዲከፍል በባለገንዘቡ ክስ ሲቀርብበት ሌላው ሊያነሳው የሚችለው መከራከሪያ እዳን የመከከፋፈል መብት ሲሆን ይህም ሊሆን የሚችለው ቁጥራቸው ከአንድ በላይ የሆኑ ዋሶች በተመሳሳይ ጉዳይ በአንድ ሰነድ ላይ ዋስ ቢሆኑ እና ባለገንዘቡ አንዱን ዋስ ብቻ ነጥሎ ሙሉ እዳውን ክፈለኝ ብሎ ቢከሰው የተከሰሰው ዋስ በቅድሚያ እኔ የምከፍለው የእዳ መጠን ከቀሪ ዋሶች ይለይልኝ እንዲሁም እኔ መክፈል ያለብኝ የእኔ ድርሻ እንጂ ሁሉንም እዳ አይደለም ብሎ ክርክር ማቅረብ የሚችል መሆኑን የፍትሀብሄር ህግ ቁጥር 1951 ይደነግጋል ፡፡ ሆኖም ግን በዋሶቹ መካከል አንዱ የመክፈል አቅም ባኖረው እዳው ቀሪው ዋሶች ይከፋፈሉታል፡፡ 3ኛ በዋናው ባለእዳ ላይ ክስ መስርት የማለት መብት(summons to proceed) ህይ ማለት የዋናው ባለእዳ የእዳው መክፈያ ጊዜ ወይም ውል መፈጸሚያ ጊዜው የደረሰ ከሆነ ግዴታውን እንዲወጣ ባለገንዘቡ ባለእዳውን እንዲከሰው ዋሱ ባለገንዘቡን የሚያሳውቅበት የህግ ሂደት ሲሆን በፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 1938 እንደተደነገገው ባለገንዘቡ በስድስት ሳምንታት ውስጥ ከባለእዳው መብቱን እንዲጠይቅ ዋሱ ሊያስገድድ የሚችል ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ባለገንዘቡ ባለእዳን ሳይከሰው ቢቀር ዋሱ ሀለፊነት እንደሚውርድለት የሚደነግግ ሲሆን ከዚህ በኋላ ዋሱ ይህን እንደ ክስ መቃወሚያ ማንሳት ይችላል Join 👇🛑 t.me/ethiolawtips
Show all...
ሰ.መ.ቁ 226490 ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም የወራሽነት ማስረጃ ከፍርድ ቤት የተሰጠው ሰው የመብት ጥያቄ ሲያቀርብ ሌላኛው ወራሽ የመውረስ መብት እንደሌለው ክርክር ለማቅረብ በቅድሚያ የወራሽነት ማስረጃውን ማሰረዝ አስፈላጊ አይደለም። ስለሆነም የወራሽነት ማስረጃ የተሰጠው ሰው የውርስ ድርሻውን ለማግኘት ባቀረበው ክስ ላይ የሟች ልጅ አይደለም ብሎ ለመቃወም በቅድሚያ የወራሽነት ማስረጃው እንዲሰረዝ አቤቱታ አቅርቦ ማሰረዝ አይጠበቅበትም። ወራሽነትን በማረጋግጥ የሚሰጥ የወራሽነት ማስረጃ በአመልካች ብቻ የቀረበውን የአንድ ወገን ማስረጃ በመቀበል የሚሰጥ ማስረጃ (Declaratory judgment) ለመክሰስ መብትና ጥቅም ያለው መሆኑን አሳይቶ የድርሻ ክፍፍል ጥያቄ ለማቅረብ በማስረጃነት የሚቀርብ፤ በማንኛውም ተዓማኒነት እና ክብደት ባለው ማስረጃ ሊስተባበል የሚችል ማስረጃ በመሆኑ ማስረጃው በተሰጠበት መዝገብ ላይ መብት ወይንም ጥቅሜን ይነካል በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሠረት የፍርድ መቃወሚያ የሚቀርብበት አይደለም። Join 🛑👇 t.me/ethiolawtips
Show all...
Extra Contractual liability law by mehari Redea. @AAU_Lawschool
Show all...
Property law short note! @AAU_Lawschool
Show all...
በሕግ አውጭው በኩል ለብዙ ዘመናት ያገለገለውን የኢትዮጵያ ከውል ውጭ ኃላፊነት ሕግ እንዲሁም የታክስ ሕግጋትን የማሻሻል ዕቅድ አለ፡፡ ለዚህም ይረዳ ዘንድ በUSAID ፍትሕ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ጥናት ተካሄዷል፡፡ በጥናቱ ከሕግ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተመራማሪዎች ተሳትፈዋል ፡፡ የጥናቱ ዉጤት ከውል ውጭ ኃላፊነት ሕግን እና የታክስ ሕግጋትን ለማሻሻል ለሕግ አውጭዎች እና ለፖሊሲ አርቃቂዎች ዐብይ ግብዓት ይሆናል፡፡ የእነዚህ ጥናቶች አጭርና ጥቅል የውጤት መግለጫ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕግ መጽሔት ቅጽ 13 ቁጥር 1 ታትሟል፡፡ የእነዚህን ጥናቶች ጥቅል የውጤት መግለጫ ከተያያዘው ፋይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
Show all...
የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በክልሉ ለ5ኛ ጊዜ የመደበኛ ቁርጥ ግብር ጥናት ማካሄዱ ይታወቃል፡፡ የክልሉ ገንዘብ ቢሮ በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 240/2008 አንቀፅ 39 ንዑስ አንቀፅ 2 በተሰጠው ስልጣን መሠረት የደረጃ "ሀ" ፣ "ለ" እና "ሐ" ንግድ ስራና ኪራይ ገቢ ግብር ከፋዮች የግብር አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 15/2015 ዓ/ም አውጥቷል፡፡ አውርደው ይጠቀሙ፡፡
Show all...