አዶናይ
Open in Telegram
በዚህ ቻናል በኩል የታረደውን የእግዚአብሔር በግ እያከበርን ፣ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በውስጥ ሰውነታችንን በሀይል እንበረታለን። መንፈስ ቅዱስ ከኛ ጋር ነው 🥰 @AdonaiComments_bot
Show more7 310
Subscribers
-124 hours
-297 days
-8430 days
Posts Archive
7 310
ሰሞኑን ይህንን መዝሙር ሰምቼ ከማገለግለው አገልግሎት ያለፈ ፣ በአንደበቴ በየቀኑ ከምዘምርለት ብዙ መዝሙሮች በላይ ሰውነቴን ንፁህ እና ቅዱስ መሥዋዕት ሆኖ ጌታዬ እንዲያሸተው ፈለጉ 😭
ላምልክህ በህይወቴ 😭🙌🏼
7 310
ገና በለሊት ቤት መቀመጥ አላስችል ብሏት የህይወቷን መምህር ፍለጋ ምንም በሌለበት መቃብር ስፍራ ላይ ብቻዋን እያለቀሰች 😭 በአይኖቿ አስሬ የተከፈተውን መቃብር ታያለች የምትፈልገው መምህሯ ግን በቦታው የለም ፤ የኢየሱስን ከመቃብር መጥፋት ለማየት ከማርያም ጋር የመጡት ሌሎች ደቀ-መዛሙርት መቃብሩ መከፈቱንና የኢየሱስ ስጋ ከቦታው አለመኖሩን ከማየት ባለፈ እንደዚች ሴት የጌታ አለመኖር ጥያቄ አልሆነባቸውም መግደላዊት ማርያም ግን እርሱ እኮ ሞቷን ብለው የነገሯትን ረቡኒዋን ፍለጋ አይኖቿ እረፍት አጥተዋል በዚህ ሁሉ የጭንቅ ፍለጋ ውስጥ ግን አንድ ለማመን የሚከብዳትና የምታውቀውን ውብ ድምፅ ከበስተ ኃላዋ ሰማች " ማርያም " የሚል ድምጽ ፤
ይሄ ድምፅ ጥያቄዎቿን ሁሉ የሚመልስላት የምቶደው የመምህሯ ድምጽ ነበር... ማርያም በጣም በሚያስፈራ በመቃብር ስፍራ አጥብቃ የፈለገችው የህይወቷ መምህር በመጨረሻ ራሱን በትንሳኤ አካል ገለጠላት፤ ከዛም ይህ ቃል የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ብቻ ሳይሆን የሚሰራ ህያው ቃል እንደሆነ ለአለም ህዝብ በተግባር አሳየች !
"እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።" — Jeremiah 29:13
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost7 310
Dollar መግዛትና መሸጥ የምትፈልጉ ሰዎች በዚህ Username 👉@Beloved_ELA በኩል በታማኝነት ግብይት ማድረግ ትችላላችሁ፤
100% Trusted
@Beloved_ELA
7 310
🎙️ መሥዋዕት
ይህን መዝሙር ሁላቹም ትኩረታቹን ሰብስባቹ ከልባቹ ብትሰሙት ደስ ይለኛል፤
ጌታ በቃላችን ከምንዘምርለት መዝሙሮች በላይ ህይወታችን ለሱ ሲዘምርለት ማየት ይፈልጋል፤ያምልከው ሰው የማያውቀው ኑሯችን ፤ ይዘምርለት የጓዳ ህይወታችን ። @thedayofpentecost @thedayofpentecost
7 310
በመንፈሳዊ ህይወታቹ ማደግ የምትፈልጉ ከሆነ ከምንም ነገር በላይ በየቀኑ ከምትሰሟቸውና ከምታያቸው ነገሮች ራሳቹን ጠብቁ ፤ እንዲሁም በየማህበራዊ ሚዲያው በየቀኑ ከሚበተኑ ቀልዶች ፣ ፊልሞች እና ከሌሎችም የእናንተን መንፈሳዊነት ከማያንፁ ሀሳቦች ተቆጠቡ ።
ልቡን የሚጠብቅ ሰው ህይወቱን ይጠብቃል ፤ ልባቹን ጠብቁ !
7 310
ስልካቹን ለተወሰኑ ቀናት ዘግታቹት ፣ በአለም ከሚሰማው ጫጫታ ራሳቹን አግልላቹ በጌታ እግሮች ስር በህልውናው ውስጥ ብቻቹን ሆናቹ ስታለቅሱ ራሳቹን ማግኘት አልናፈቃቹም 🙌🏼 ?
7 310
🎙️ፀሎቴ ጋ
ሽፍት ልበል ከግርግሩ ልራቅ ልረሳ፣ ከእግሮችህ ስር መድሃኒትን ይዜ እንድነሳ፤ ከዛም ባለፈ ባንተ በራስህ እደነቃለሁ፤ባወኩህ ቁጥር እወድህና እዛው ከርማለሁ።ነፍሴ ጌታዋን ስትናፍቅ የምከፍትላት መዝሙር ነው፤ ይሄን መዝሙር እየሰማቹ ከጌታ ጋር ጊዜ አሳልፉ። @thedayofpentecost @thedayofpentecost
7 310
ልጅ ያሰበው አልሆነም
ትዝ ይላቿል ሉቃስ 15 ላይ ያለው የጠፋው ልጅ ታሪክ ? እዚህ ታሪክ ውስጥ የጠፋው ልጅና የአባትዬው የሀሳብ ልዩነት ይገርመኛል፤ ልጅ ከአባቱ የድርሻውን ንብረት ከወሰደ በኃላ ወደ ሩቅ ሀገር ጠፍቶ የልቡን እያደረገ ገንዘቡን ያጠፋል ታዲያ በዚህ ጊዜ ትናንት ከአባቱ ይልቅ ያመነው ገንዘቡ ቀስ በቀስ ሲከዳውና የሚበላው ሲያጣ የግድ ህይወቱን ለማስቀጠል ሲል ትናንት ልጅ በነበረበት ቤት እንደ ባሪያ ለመኖር ይወስናል፤ ተበዳይ አባት ግን ያን ሁሉ ጥፍት ረስቶ ልጄ አንድ ቀን ሊመለስ ይችላል በሚል ተስፋ ለጠፋው ልጁ የእጅ ቀለበት እና ለሰውነቱ ጥሩ ልብስ እያዘጋጀ እንዴት ሮጦ እንደሚያቅፈው ያስባል
፤ ታዲያ በመጨረሻ ልጅ የትናንቱን ጥፍት እየሰበ ከወሰነው ባርነት ይልቅ አባት ልጅነቱን እያሰበ የወሰነው ክብር በልጦ ተገኘ።
የተወደዳቹ የአባቴ ልጆች እናንተ ትናንት ላይ ያጠፋቹትን ጥፍት እያሰባቹ ለራሳቹ ከሰጣቹት ስፍራ በላይ ጌታ ልጅነታቹን እያሰበ ያዘጋጀላቹ ያ የክብር ስፍራ ይበልጣል።
@thedayofPentecost
@thedayofPentecost7 310
ያላቹበትን ችግር ለሰዎች ከመናገራቹና ሰዎች ጋር መፍትሄ ከመፈለጋቹ በፊት መጀመሪያ የከበዳቹን ጉዳይ ምንም ሳታስቀሩ ለእግዚአብሔር ንገሩት ።
ለእግዚአብሔር የተነገረ ችግር መፍትሄ አያጣም !
7 310
ዛሬ ላይ ነፍሳችን ከደነዘዘችበት ፣ እኛም የግድ የኛ ካልሆነ ብለን ችክ ካልንበት እግዚአብሔር ግን ከማያውቀውና ከሚጠላው ጉዳይ ላይ ጨክነን ሮጠን የምሸሽበትን ፀጋ ጌታ ይስጠን🙏
7 310
የ 1 ቀን መጠጥ ለ 1 ቀን ብቻ ነው የሚያሰክረው
መጠጥ የሚጠጣ ሰው የሚሰክረው በጠጣው ልክ ነው፤ ለአንድ ቀን
የጠጣው መጠጥ ሳምንቱን ሙሉ አያሰክረውም በየቀኑ ለመስከር በየቀኑ መጠጣት ይኖርበታል፤ መንፈስ ቅዱስም ልክ እንዲሁ ነው አንዴ በመንፈስ ተሞልታቹ ሳምንቱ ሙሉ ሳትፀልዩ ሳምንቱን ሙሉ በመንፈስ መቀጣጠል አትችሉም ዘውትር በመንፈስ ለመስከር ዘውትር በፀሎት መትጋት ይኖርባቿል።
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost7 310
🎙️ አረስርሰኝ 🙌🏼
እንደ ልጅ ጌታን ፊት የምናቀርባቸው ብዙ የህይወት ጥያቄዎች ቢኖሩንም የቱም ጥያቄያችን ግን ከዚህ አንዱ ጥያቄያችን በላይ ግን አይደለም 😭
ናና አረስርሰን...
@thedayofpentecost
@thedayofpentecost