cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Abu mahir lbnu kedir

የዚህ ቻናል አላማው ኢስላማወዊ ትምህርቶችን በቁርኣንና በሀዲስ ማስረጃ ተደግፎ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ስለዚህ ሙስሊም ወንድሞችና እህቶቻቹን አድ በማድረግ ተባበሩን ጀዛኩም አሏሁ ኸይር

Show more
Advertising posts
1 490
Subscribers
-124 hours
+17 days
+130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

✅ #አዲስ_ሙሐደራ  ✅ #محاضرة_جديدة ➡️ ርዕስ፦ ↪️ «ነብያቶች እና ሰለፎችቻን ህዝቦቻቸውን፣ ልጆቻቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ከሽርክ ያስጠነቅቁ እንደነበር እና ወደ ተውሂድ ያዙዋቸው እንደነበር እንዲሁም በነፍሳቸው፣ በህዝቦቻቸው እና በቤተሰቦቻቸው ላይ ሽርክን ይፈሩ እንደነበር ዳሰሳ።» 🚦🚥 ክ ፍ ል አንድ 🚥🚦 🎙 للشيخ أبي طلحة أبي ذر بن حسن الولوي «حَفِظَهُ اللَّهُ» 🎙 በሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን አቡ ጦልሃ አላህ ይጠብቃቸው! 🗒 የጊራና ሰለፍዮች የመስጅድ ቦታ መግዢያ የገቢ ማሰባሰቢያ ግሩፕ የተደረገ ሙሐደራ ➴➘➴➘ https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha
Show all...
👆👆👆👆👆 ዳር አስ–ሱንና የሸሪዓ እውቀት መዕከል
Show all...
ቀጣይ ደርስ በያኑ ማፊ ነሲሀቲ ኢብራሂም ተጀምሯል ገባ ገባ በሉ! https://t.me/DarASSunnah1444?livestream=62929fc6dd6d5f07c7
Show all...
ዳር አስ-ሱንና Dar As-sunnah Channel

ይህ የዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ነው مركز دار السنة لتعليم الشريعة الإسلامية Dar As-Sunnah Sharia Knowledge Center አድራሻ:- አዲስ አበባ ኮ/ቀ ክ/ከተማ አለምባንክ ከኦርዶፎ ህንፃ ፊት ለፊት ባለው ቂያስ ወደ ቤተል በሚወስደው ኮብልስቶን ከድልዲዩ በስተቀኝ እንገኛለን። ለተጨማሪ መረጃ:- +251920908031

🟢አንዱን መምረጥ አይቀሬ ነው ❗️ يقول ابن القيم رحمه الله: "فهي النفس إن لم تشغلها بالحق شغلتك بالباطل، وهو القلب إن لم تسكنه محبة الله عز وجل سكنه محبة المخلوقين ولابد، وهو اللسان إن لم تشغله بالذكر شغلك باللغو وما هو عليك ولابد، فاختر لنفسك إحدى الخطتين، وأنزلها في إحدى المنزلتين" ( الوابل الصيب  80) "እርሷ ነፍስ እኮ በሀቅ ካልያዝካት ( ቢዚ ካላደረከት) በሀሰት ትይዘሃለች። እርሱም ቀልብ ያአላህን ውዴታ ካላኖርክበት የፍጥረታት ውዴታ መኖሪያ ይሆናል።አይቀሬ ነው።እርሱም ምላስ እኮ በዚክር ካልያዝከው በዛዛታና በወንጀል ቢዚ ያደርገሃል።አይቀሬ ነው። ከሁለቱ መንገዶች ለነፍስህ አንዱን ምረጥላት። ከሁለቱ ደረጃዎች አንዱን ምረጥላት።" የአላህን ቃል እናስተውል: ﴿وَمَنْ يَعْشُ عَنْ ذِكْرِ الرَّحْمَنِ نُقَيِّضْ لَهُ شَيْطَانًا فَهُوَ لَهُ قَرِينٌ (٣٦) وَإِنَّهُمْ لَيَصُدُّونَهُمْ عَنِ السَّبِيلِ وَيَحْسَبُونَ أَنَّهُمْ مُهْتَدُونَ﴾ [الزخرف ٣٦-٣٧] {አረህማንን ከማስታወስ የታወረ ሁሉ ለእርሱ ሸይጣንን እንመድብለታለን። እርሱም ለእርሱ የተቆረኛ ጓደኛው ነው።እነርሱም (ሸይጣኖቹ) ከመንገድ በእርግጥ ያግዷቸዋል።እነርሱም የተመሩ እንደሆነ ያስባሉ።} 👉ጥቆማ قال الشيخ ابن عثيمين- رحمه الله- فالصواب أن المراد بـ ﴿ذِكْرِ الرَّحْمَنِ﴾ ليس القرآن، بل المراد بـ ﴿ذِكْرِ الرَّحْمَنِ﴾ ذكر الله نفسه ኢብኑ ዑሰይሚን ሲፈስሩ እንዲህ ይላሉ "ትክክለኛው ተፍሲር {ذِكْرِ الرَّحْمَنِ} የተፈለገበት ቁርኣን አይደለም።ይልቁንም አላህን ራሱን ማስታወስ (ዚክር) ነው።" https://t.me/Abuhemewiya
Show all...
የሰው አይን (ቡዳ) የበላው ሰው እንዴት ይፈወሳል? የሰው አይን (ቡዳ) ያለና የሚያጋጥም ነው።  የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ( ﺍﻟْﻌَﻴْﻦُ ﺣَﻖٌّ )  «በአይን (መጎዳት) ያለ እውነታ ነው» (ቡኻሪና (5740) ሙስሊም (2187)ዘግበውታል) ይህ ሰው የሚታወቅ ከሆነና ፍቃደኛ ከሆነ ውዱእ እንዲያደርግ ወይም ገላውን እንዲታጠብ ተደርጎ ውሀውን ለፈውስ መጠቀም ይቻላል።  ማንኛውም ሰው እይታው የጎዳውን ሰው ካወቀ ወይም ከጠረጠረ ውዱእ እንዲያደርግለት የመጠየቅ መብት አለው። ሸይኽ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፤ «የሰው አይን ለጉዳት የዳረገው ሰው ሊወስድ የሚገባውን እርምጃ ምንድነው? ቁርአን በመቅራት ይታከማል፤ በእይታው የጎዳው ሰው ከታወቀ ውዱእ እንዲያደርግ ይጠየቅና ውዱእ ሲያደርግ የተንጠባጠበውን ውሀ ለበሽተኛው ይሰጣል። ጀርባውና ራሱ ላይ ይደፋበታል። እንዲጠጣም ይደረጋል። በአላህ ፍቃድ በዚህ ይፈወሳል። ለኪታቡ ተውሂድ በሰጡት ማብራሪያ ላይም እንዲህ ብለዋል፤ «ሌላም መንገድ አለ እሱንም ከመጠቀም ምንም የሚከለክል ነገር የለም። እሱም፤ እንደ ኮፍያ ከነቴራና የውስጥ ሱሪ ያሉ ከሰውነት ጋር የሚነካኩ የውስጥ ልብሶችን ወይም በባዶ እግሩ የሄደበትን ንፁህ አፈር ተወስዶ ዉሀ ይነከርና በዛ ውሀ የታመመው ሰው ላይ ይረጫል ወይም ይጠጣዋል፤ ይህም የተሞከረ ነው።» መጅሙእ ሙአለፋት ኢብኑ ኡሰይሚን 9/88 ይህ የመጨረሻው መፍትሄ ይበልጥ ጠቃሚ የሚሆነው ይህ ሰው ውዱእ ለማድረግ ወይም ለመታጠብ ዝግጁ ካልሆነ ወይም ካፊር ከሆነ ወይም ደግሞ ከዚህ ሰው ጋር ያለንን ግንኙነት የሚያበላሽ መስሎ ከተሰማን ሰውየው በማያውቅበት መልኩ መፈፀም ስለሚችል ጥሩ አማራጭ ነው። ─────────── ቴሌግራም ቻናላችንን Join⤵️ ብለው ይቀላቀሉ! https://t.me/Abumahiraselefiy https://t.me/Abumahiraselefiy
Show all...
Abu mahir lbnu kedir

የዚህ ቻናል አላማው ኢስላማወዊ ትምህርቶችን በቁርኣንና በሀዲስ ማስረጃ ተደግፎ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ስለዚህ ሙስሊም ወንድሞችና እህቶቻቹን አድ በማድረግ ተባበሩን ጀዛኩም አሏሁ ኸይር

Show all...
ዳር አስ-ሱንና Dar As-sunnah Channel

ይህ የዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ነው مركز دار السنة لتعليم الشريعة الإسلامية Dar As-Sunnah Sharia Knowledge Center አድራሻ:- አዲስ አበባ ኮ/ቀ ክ/ከተማ አለምባንክ ከኦርዶፎ ህንፃ ፊት ለፊት ባለው ቂያስ ወደ ቤተል በሚወስደው ኮብልስቶን ከድልዲዩ በስተቀኝ እንገኛለን። ለተጨማሪ መረጃ:- +251920908031

ሰዎችን በጭፍን አትከተል!! ————— ሰዎች በሐቅ ይመዘናሉ እንጂ ሐቅ በሰዎች አይመዘንም!! የሀቅ እንጂ የሰዎች ጭፍን ተከታይ አትሁን!። ምክንያቱም የታዘዝከው ሐቅን እንጂ ሰዎችን እንድትከተል አይደለም!። በጭፍን ውዴታ ጥግ መድረስ አደጋ አለው። ጭፍን ተከታይ መሆን ሐቅ ከመቀበል ያውርሃልና ተጠንቀቅ!። በህይወት ያለ ሰው ፈተና አይታመንለትም። አላህ ይጠብቀንና በጭፍን የተከተልከው ሰው ከተንሸራተተ አለያም ድንበር አላፊ ከሆነ አንተም አብረሀው ገደል ልትገባ ትችላለህና ጭፍን ተከታይ አትሁን!!። ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) “በህይወት ያለ ሰው ፈተና አይታመንለትም” ብለዋል። በመሆኑም የሰዎች ጭፍን ተከታይ መሆንን ተጠንቀቅ። ወደ ቁል ቁል ሲወርዱ እንዳያወርዱህ፣ ድንበር ሲያልፉም በጭፍን ተከትለሃቸው እንዳታልፍ። የሰዎች ንግግር ትክክል ካልሆነ ተመላሽ ነው። ፍፁም የሆነውና ሊመለስ የማይችለው የመልእክተኛው ንግግርና ተግባር ብቻና ብቻ ነው። ኢማሙ ማሊክ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ማለታቸውን አትዘንጋ:- "ሁላችንም ተመላሾችና የተናገርነውም የሚመለስ ነው የዚህ ቀብር ባለ ቤት ሲቀር።" አሉ። የቀብሩ ባለ ቤት በማለታቸው የፈለጉበት መልአክተኛውን ነው። ሐቅን እወቅ! ከዚያም ሰዎችን በሀቅ ትመዝናቸዋለህ። የሀቅ ሰዎችንም ታውቃለህ። ሰዎችን አውቀህ በጭፍን የምትከተላቸው ከሆነ ግን የሐቅ መመዘኛ መሰረትህ ትክክለኛ ማስረጃ ላይ የተገነባ ሳይሆን የሰዎች ጭፍን ውዴታና ጭፍን ተከታይነት ይሆንና ሲገለባበጡም አብሮ መገለባበጥ ይሆናል። ቆም ብለህ አስተውል! ቡድንተኝነትና ጭፍን ውዴታ አያውርህ!። ነገ አላህ ፊት ወዳጅህ ጠላት ሊሆንብህ ይችላል። አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:- الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِينَ «ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ነው፡፡ አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ፡፡» አዝ-ዙኽሩፍ 67 ታዲያ ስትወድም ሆነ ስትጠላ በጭፍን አይሁን!። የወደድከው አቅጣጫ ከሳተና ለየት ያሉ ነገሮችን ካስተዋልክበት ቆም በል።  በጭፍን መውደድም መጥላትም አደጋው የከፋ ነውና ተጠንቀቅ!!። ሳታስበው በሰለፊያ መንሀጅ ስም በተመሰረተ ልዩ በሆነ ቡድንተኝነትና ዘመናዊ ሙሪድነት አዘቅጥ ውስጥ እንዳትዘፈቅ!!። በጭፍን በውዴታው የከነፍከለት አካል መንገድ ከሳተ ተከትለሀው መሳትህ አይጠቅምህም! ከባድ አደጋ ነው። የሚጠቅምህ በየትኛውም ወቅት ሀቅን አጥብቀህ መያዝህ ነው!!። በተለይ በፊትና ጊዜ ምንም ያህል በአንዳንድ መልካም ስራዎቹ የምትወደው በዳዒነት የገነነ ነገር ግን እውቀቱ እዚህ ግባ የማይባል የምትወደው ሰው ቢኖር እንኳ ጠንካራ ነጥቦች ሲነሱ፣ የሆነ ጊዜ "እኔ እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን አንስቼ ለመናገር እውቀቴ አይፈቅድልኝም" እያለ በሌላ ጊዜ ደግሞ የእውቀት ደረጃው በማይፈቅደው አጀንዳ ውስጥ ገብቶ ሲዘባርቅ እያየሀው ስለ ወደድከው ብቻ በጭፍን መከተል የለብህም!። በየትኛውም ወቅት የጠንካራ እውቀት ባለ ቤቶችን እና በዳዒነት የገነኑ ያለ እውቀት ደረጃቸው ተከታይ ስላላቸው ብቻ በድፍረት የሚናገሩና ተከታዮቻቸውን ይዘው ወደፈለጉበት አቅጣጫ የሚዋዥቁ ያለ እውቀት ታዋቂ የሆኑ ሰዎችን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል። ሐቅ በጋጋታና ከተለያየ አቅጣጫ በሚጮሁ በተደራጁ ቲፎዞዎች ጩሀት አይለካም!። እውነትን ቆም ብሎ በማስረጃ መለየት ነው እንጂ ጭፍን ተከታይ መሆን አደጋው የከፋ ነው!። ትላንት በጥሩ አቋምና በትክክለኛው መንሀጅ እያለ ጠላቶቹ የነበሩ ኢኽዋንን ጨምሮ "አይንህ ላፈር" የሚሉት ሰዎች ዛሬ እንዴት ወዳጆቹ ሊሆኑና እሱን ሊያደንቁ፣ ሊያሞግሱ እንደቻሉ? ቆም ብለህ ፈትሽ!!። እሱ ተለሳልሶ ከአቋሙ ሸርተት ብሎ ነው ወይስ እነሱ ወደ ትክክለኛው አቋምና መንሀጅ ተመልሰው ነው? ብለህ እራስህን ጠይቅ። ያለፉ ሂደቶችንና በወቅቱ ያሉ ሂደቶችንም በተረጋጋና በገለልተኝነት መንፈስ ቃኝ!። እውነት ጭፍን ተከታይነትና ቡድንተኝነት ሳያውረው ከልቡ ለፈለጋት ሰው ግልፅ ትሆናለች!። ታላቁ ሸይኽ አሕመድ ኢብኑ የህያ አን-ነጅሚ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ: - “ወላሂ! በጌታዬ ይሁንብኝ አላህ ዘንድ እገሌና አገሌ አይጠቅሙህም!። የሚጠቅምህማ በሀቅ ላይ መቆምህና ለሀቅና ለተከታዮቹ ረዳት መሆንህ ነው።” ረዱል ጀዋብ 54 »» ሐቅን ተከተል!። ለሸይኽ አሕመድ ቢን የህያ አን-ነጅሚ (ረሂመሁላህ) ድንቅ ንግግር ትኩረት ስጠው!። ወገንተኝነት አያጥቃህ፣ ለሀቅ ብቻ ወግን! ሀቁ በበቂና በትክክለኛ ማስረጃ ከተነገረህ አንተም ሆንክ የምትወደው ዳዒ አለያም ከጎንህ ያሉ ወዳጆችህ መንገድ ስህተት እስከሆነ ወደ ሀቁ ለመመለስ አታንገራግር!! የተነገረህ እውነት እሰከሆነ ለመቀበል ቆራጥ አቋም ይኑርህ!። ምክንያቱም ወገንተኛ የምትሆንለት አካል ከአላህና ከመልእክተኛው በላይ የለምና ለአላህ እና ለመልእክተኛው እና ለሐቅ ብቻ ወገንተኛ ሁን!!። ሐቅ ከየትም ይምጣ ከማንም ሐቅ እስከሆነ መቀበል ነው። ሀቁ ካልተገለጠልህ ደግሞ እስኪገለጥልህ ከቡድንተኝነትና ጭፍን ተከታይነት ገለልተኛ ሆነህ በአደብ ፈልገው፣ በንፁህ ኒያ እስከፈለግከው ኢንሻአላህ ቢዘገይ እንኳ ፍንትው ብሎ ይታይሃል!!። ግን ግን አደራ ምን ጊዜም ለግለሰቦች ከወገንተኝነት፣ ከጭፍን ተከታይነትና ከቡድንተኝነት ራስህን አርቅ!!። ምን ጊዜም ወገንተኝነታችሁ ለሐቅ ከሆነ ሐቅን የሚከተልን ትወዱታላችሁ ታከብሩታላችሁ እንጂ ጭፍን ተከታይ አትሆኑለትም!!። አላህ ሐቁ ለተደበቀበት ግልፅ ያድርግለት!!  የሀቅ ተከታዮችና በሐቅ ላይ ከሚፀኑ ባሮቹም ያድርገን!! ✍🏻 ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa) #join ⤵️ የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
Show all...
[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]

እራስህን ሁል ጊዜ ለቁርኣንና ለሀዲስ ተጎታች አድርግ! በአንድ ነገር ላይ ከቁርኣንና ከሀዲስ ማስረጃ ሳታገኝ አቋም አትያዝ! ሁሌም ለሰዎች መልካምን ተመኝ! ለሀቅ እንጂ ለሰዎች ወጋኝ አትሁን

እህት ተጠንቀቂ በአሁን ግዜ እህቶች ለስራ ወይም ለጉዳይ በሚወጡበት ግዜ ሽቶ እንደ ሀላል እደተፈቀደ አድርውታል። ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿أيما امرأةٍ استعطرتْ فمرتْ على قومٍ ليجدوا من ريحِها فهي زانيةٌ﴾ “ሽቶ ተቀብታና መዓዛው እንዲያውዳቸው አስባ በሰዎች አጠገብ የተላለለፈች ማንኛዋም ሴት ዝሙተኛ ነች።” 📚 ነሳዒ ሶሂህ ብለውታል: 5141 በአሁን ግዜ የሚታየው ተቀባብተው እራስህ እስክትታመም ድረስ ይሸቱሃል ። ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ከዘይነብ አሰቅፊ ተይዞ: ከአብደላህ ቢን መስዑድ ሴቶች ውስጥ አንዷ ነች ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል ትላለች፦ ﴿إذا خرجتْ إحْداكنَّ إلى المسجدِ فلا تقْرَبنَّ طِيبًا.﴾ “አንዳችሁ ወደ መስጂድ በምትሄዱ ግዜ ሽቶ የተቀባችሁ እንደሆነ ወደ መስጂዱ አትቅረቡ።” 📚 ሶሂህ አልጃሚ: 501 እህቴ ሆይ! ሽቶ ተቀብተሽ እንደ ዙሙተኛ  ስትባዪና እንደ ዝሙተኛ ስትቆጠሪ  ማየት ያስጠላል። ዝሙተኞች በሚቀጡበት ቅጣት ሽትቀጪ ማየት ያስጠላል። እህቶች አለህን እንፍራ አላህን እንፍራ ቴሌግራም ቻናላችን ተቀላቀሉ! ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️ https://t.me/Abumahiraselefiy https://t.me/Abumahiraselefiy
Show all...
Abu mahir lbnu kedir

የዚህ ቻናል አላማው ኢስላማወዊ ትምህርቶችን በቁርኣንና በሀዲስ ማስረጃ ተደግፎ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ስለዚህ ሙስሊም ወንድሞችና እህቶቻቹን አድ በማድረግ ተባበሩን ጀዛኩም አሏሁ ኸይር

Photo unavailableShow in Telegram
ከጁመዓ ቀን ሱናዎች ↩️ ‏سنن يوم الجمعة ➊ الغسل ➋ الطيب ➌ السواك ➍ لبس الجميل ➎ قراءة سورة الكهف ➏ التبكير لصلاة الجمعة ➐الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي 〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️ 🔹ገላን መታጠብ 🔹ሽቶ መቀባት ለወንድ 🔹ሲዋክ መጠቀም 🔹ጥሩ ልብስ መልበስ 🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት 🔹በጠዋት ለጁመዓ ሶላት መጣድ 🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት ማብዛት ------------------------------------------------------------------------------------------------------------ ﷽ ዛሬ ጁመዐ ነው ሱረቱል ካፍ የቻለ ይቅራ ያልቻለ ያድምጥ 📌سورة الكهف 💎ሱረቱል ካህፍ 🖋 (بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَـٰنِ ٱلرَّحِیمِ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِیۤ أَنزَلَ عَلَىٰ عَبۡدِهِ ٱلۡكِتَـٰبَ وَلَمۡ یَجۡعَل لَّهُۥ عِوَجَاۜ) [Surah Al-Kahf 1] (قَیِّمࣰا لِّیُنذِرَ بَأۡسࣰا شَدِیدࣰا مِّن لَّدُنۡهُ وَیُبَشِّرَ ٱلۡمُؤۡمِنِینَ ٱلَّذِینَ یَعۡمَلُونَ ٱلصَّـٰلِحَـٰتِ أَنَّ لَهُمۡ أَجۡرًا حَسَنࣰا) [Surah Al-Kahf 2] የ ዛሬዉ ጁመአ   🤲🌺ወንጀላችን የሚማርበት   🤲🌺ስራችን ሚወደድበት   🤲 🌺የተቸገረ የሚያገኝበት   🤲🌺 የከፍው ሚደሰትበት   🤲 🌺የታመመ የሚሽርበት    🤲🌺ፍትህ ያጣ ፍትህ ሚያገኝበት   🤲 🌺ሰላም የሚሰፍንበት 🌺አላህ ይድርግልን #Join  & #share https://t.me/abumahiraselefiy/8146 https://t.me/abumahiraselefiy/8146
Show all...