cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ) ✍

የጠራ እውቀት ከተቃና አቐምና ተግባር ጋር የተረዘቀ ታድሏል !!

Show more
Advertising posts
9 659
Subscribers
+124 hours
+707 days
+22830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ወሳኝ ሙሓዶራ “በእውቀት መስራት ያለው ቱሩፋት እና አውቆ ያለመስራት ያለው አደጋ‼️” 🎙 በታላቁ ዓሊም ሸይኽ አብዱልሐሚድ   አል–ለተሚይ(ﺣﻔﻈﻪ ﺍﻟﻠﻪ) https://t.me/Abdurhman_oumer/8475
Show all...
በ_እውቀት_መስራት_አና_አውቀትን_አውቆ_ያለመስራት_ያለው_አደጋ.mp311.53 MB
4_5958588672986057167.mp32.70 MB
አማነቱል ዒልም.mp36.89 MB
👉 የነብዩላሂ ኢብራሂም ታሪክ ክፍል አንድ የነብዩላሂ ኢብራሂም ታሪክ ቁርኣን ላይ ቱክረት ከተሰጣቸው የነብያት ታሪክ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ይመደባል ። ታሪካቸው ቁርኣን ውስጥ በ17 ምእራፍ ወደ 69 ጊዜ ተጠቅሷል ። ይህ የሚያሳየው ታሪካቸው ምን ያክል አስፈላጊና ቁም ነገር አዘል መሆኑ ነው ። ነብዩላሂ ኢብራሂም ዒራቅ ውስጥ ባቢል በሚባል ቦታ በጣኦት አምላኪ ማህበረሰብ ውስጥ ተወለዱ ። ከህብረተሰቡ ውስጥ ኮከብ የሚያመልክ ፣ ጨረቃ የሚያመልክና ፀሀይ የሚያመልክ እንዲሁም ከእንጨት የተሰራ ጣኦት የሚያመልክ ነበር ። አባታቸው ኣዘር ከእንጨት ጣኦት እየሰራ ይሸጥ ነበር ። እሳቸው በልጅነታቸው እርሻ ይሰሩ ነበር ። አባታቸው ጣኦት እያዞሩ እንዲሸጡላቸው ሲያዙዋቸው ተቀብለው መሬት ለመሬት እየጎተቱ የማይጠቅምና የማይጎዳ የሚገዛ እያሉ ያዞሩ ነበር ። በዚህም ምክንያት ማንም የሚገዛ ስለማያገኙ ይዘውት ይመለሳሉ ። እድሜያቸው 13 አመት ሲሞላቸው ፈጣሪዬ ማን ነው ብለው ማሰብ ጀመሩ ። ቤተሰቦቻቸውና ማህበረሰቡ በሚያመልኩት ነገር ደስተኛ አልነበሩም ። ለብቻቸው ሲሆኑ ማን ነው የፈጠረኝ እያሉ ይብሰለሰላሉ ። በዚህ ስሜት ውስጥ ሆነው ከቤት ወጥተው ወደ ሰማይ በሚያዩበት ጊዜ የተከሰተውን አላህ ሲነግረን በአል አንዓም ምእራፍ ከ75 – 79 ድረስ እንዲህ ይለናል : – وَكَذَٰلِكَ نُرِي إِبْرَاهِيمَ مَلَكُوتَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَلِيَكُونَ مِنَ الْمُوقِنِينَ እንደዚሁም ኢብራሂምን (እንዲያውቅና) ከአረጋጋጮቹም ይኾን ዘንድ የሰማያትንና የምድርን መለኮት አሳየነው ፡፡ فَلَمَّا جَنَّ عَلَيْهِ اللَّيْلُ رَأَىٰ كَوْكَبًا ۖ قَالَ هَٰذَا رَبِّي ۖ فَلَمَّا أَفَلَ قَالَ لَا أُحِبُّ الْآفِلِينَ ሌሊቱም በእርሱ ላይ ባጨለመ ጊዜ ኮከብን አየ ፡፡ «ይህ ጌታዬ ነው» አለ ፡፡ በጠለቀም ጊዜ ፡- «ጠላቂዎችን አልወድም» አለ ፡፡ فَلَمَّا رَأَى الْقَمَرَ بَازِغًا قَالَ هَٰذَا رَبِّي ۖ فَلَمَّا أَفَلَ قَالَ لَئِن لَّمْ يَهْدِنِي رَبِّي لَأَكُونَنَّ مِنَ الْقَوْمِ الضَّالِّينَ ጨረቃንም ወጪ ኾኖ ባየ ጊዜ፡- «ይህ ጌታዬ ነው» አለ፡፡ በገባም ጊዜ፡- «ጌታዬ (ቅኑን መንገድ) ባይመራኝ በእርግጥ ከተሳሳቱት ሕዝቦች እኾናለሁ» አለ ፡፡ فَلَمَّا رَأَى الشَّمْسَ بَازِغَةً قَالَ هَٰذَا رَبِّي هَٰذَا أَكْبَرُ ۖ فَلَمَّا أَفَلَتْ قَالَ يَا قَوْمِ إِنِّي بَرِيءٌ مِّمَّا تُشْرِكُونَ ፀሐይንም ጮራዋን ዘርግታ ባየ ጊዜ፡- «ይህ ጌታዬ ነው ፡፡ ይህ በጣም ትልቅ ነው» አለ ፡፡ በገባችም ጊዜ፡- «ወገኖቼ ሆይ! እኔ ከምታጋሩት ሁሉ ንጹሕ ነኝ» አለ ፡፡ إِنِّي وَجَّهْتُ وَجْهِيَ لِلَّذِي فَطَرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ حَنِيفًا ۖ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ «እኔ ለዚያ ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው (አምላክ) ቀጥተኛ ስኾን ፊቴን አዞርኩ ፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» (አለ) ፡፡ በዚህ መልኩ ካስተነተኑ በኋላ አላህ የማይታይ የማይዳሰስ አምሳያ የሌለው ብቸኛ አምላክ መሆኑን አሰቡ አላህም በጅብሪል አማካይነት ለአላህ ትእዛዝ እጅ እንዲሰጡ አዘዛቸው ። እሳቸውም ለጌታቸው ትእዛዝ ፍፁም ታዛዥ መሆናቸውን አረጋገጡ ። ይህን እውነታ አላህ በተከበረው ቃሉ በላሚቷ ምእራፍ ( ሱረቱል በቀራ ) 131ኛው አንቀፅ ላይ እንዲህ ብሎ ይነግረናል : – إِذْ قَالَ لَهُ رَبُّهُ أَسْلِمْ ۖ قَالَ أَسْلَمْتُ لِرَبِّ الْعَالَمِينَ ጌታው ለርሱ ታዘዝ ባለው ጊዜ (መረጠው) ፡፡ ለዓለማት ጌታ ታዘዝኩ አለ ፡፡ አላህ ካለ ይቀጥላል ። http://t.me/bahruteka
Show all...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👉 የነብዩላሂ ኢብራሂም ታሪክ ክፍል ሁለት ነብዩላሂ ኢብራሂም አላህ ለትእዛዙ እጅ እንዲሰጡ ካዘዛቸው በኋላ ፍፁም ታዛዥነታቸውን ገልፀው ዳዕዋ ጀመሩ ። ማህበረሰባቸው አላህን አያውቅም ። ቤተሰቦቻቸው ጣኦት ያመልካሉ ያለባቸው ሀላፊነት ክብደት እረፍት አልሰጣቸውም ። ወደ አላህ መንገድ የመጣራቱን ሂደት ከጣኦት ቸርቻሪው አባታቸው መጀመር እንዳለባቸው ወሰኑ ። ወደ አባታቸውም ሄደው አባቴ ሆይ አላህ ሰዎች እሱን ብቻ እንዲያመልኩ ልጣራ አዞኛል ። ዳዕዋዬን ካንተ መጀመር መረጥኩኝ እነዚህ የማይጠቅሙና የማይጎዱ የማይሰሙና የማያዩ ጣኦታትን ትተህ አላህን ብቻ ተገዛ እያሉ ወደ አላህ አምልኮት መጣራታቸውን አላህ በሱረቱል መርየም ከ41 – 45 ድረስ በሚከተለው መልኩ ይነግረናል : – وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ إِبْرَاهِيمَ ۚ إِنَّهُ كَانَ صِدِّيقًا نَّبِيًّا በመጽሐፉ ውስጥ ኢብራሂምንም አውሳ ፡፡ እርሱ በጣም እውነተኛ ነቢይ ነበርና ፡፡ إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ يَا أَبَتِ لِمَ تَعْبُدُ مَا لَا يَسْمَعُ وَلَا يُبْصِرُ وَلَا يُغْنِي عَنكَ شَيْئًا ለአባቱ ባለ ጊዜ (አስታውስ) «አባቴ ሆይ! የማይሰማንና የማያይን ከአንተም ምንንም የማይጠቅምህን (ጣዖት) ለምን ትግገዛለህ يَا أَبَتِ إِنِّي قَدْ جَاءَنِي مِنَ الْعِلْمِ مَا لَمْ يَأْتِكَ فَاتَّبِعْنِي أَهْدِكَ صِرَاطًا سَوِيًّا «አባቴ ሆይ! እኔ ከዕውቀት ያልመጣልህ ነገር በእርግጥ መጥቶልኛልና ተከተለኝ ፡፡ ቀጥተኛውን መንገድ እመራሃለሁና ፡፡ يَا أَبَتِ لَا تَعْبُدِ الشَّيْطَانَ ۖ إِنَّ الشَّيْطَانَ كَانَ لِلرَّحْمَٰنِ عَصِيًّا «አባቴ ሆይ! ሰይጣንን አትግገዛ ፡፡ ሰይጣን ለአልረሕማን አመጸኛ ነውና ፡፡ يَا أَبَتِ إِنِّي أَخَافُ أَن يَمَسَّكَ عَذَابٌ مِّنَ الرَّحْمَٰنِ فَتَكُونَ لِلشَّيْطَانِ وَلِيًّا «አባቴ ሆይ ! እኔ ከአልረሕማን ቅጣት ሊያገኝህ ለሰይጣንም ጓደኛ ልትኾን እፈራለሁ ፡፡» ነብዩላሂ ኢብራሂ በጣም አስደናቂና አስተማሪ በሆነ መልኩ ክብር በተሞላበትና እኔ አዋቂ ነኝ የሚል የኩራት ስሜት በሌለበት የሚገርም አካሄድ አባቴ ሆይ እያሉ ላደረጉት ለዚህ ጥሪ ከአባታቸው የተቸሩት ምላሽ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነበር ። የአባታቸው ምላሽ ምን እንደነበረ አላህ ሲነግረን እዛው በሱረቱል መርየም 46ኛው አንቀፅ እንዲህ ይለናል : – قَالَ أَرَاغِبٌ أَنتَ عَنْ آلِهَتِي يَا إِبْرَاهِيمُ ۖ لَئِن لَّمْ تَنتَهِ لَأَرْجُمَنَّكَ ۖ وَاهْجُرْنِي مَلِيًّا (አባቱም) «ኢብራሂም ሆይ! አንተ አምላኮቼን ትተህ የምትዞር ነህን ባትከለከል በእርግጥ እወግርሃለሁ ፡፡ ረዥም ጊዜንም ተወኝ» አለ ፡፡ ይሁን እንጂ ነብዩላሂ ኢብራሂም በአባታቸው መልስ ተስፋ ቢቆርጡም ሳይበሳጩ የሰጡት መልስ በዛው ምእራፍ 47 ኛው አንቀፅ እንዲህ የሚል መሆኑ ተነግሮናል : – قَالَ سَلَامٌ عَلَيْكَ ۖ سَأَسْتَغْفِرُ لَكَ رَبِّي ۖ إِنَّهُ كَانَ بِي حَفِيًّا «ደህና ኹን ፡፡ ወደፊት ከጌታዬ ምሕረትን እለምንልሃለሁ ፡፡ እርሱ ለኔ በጣም ርኅሩኅ ነውና» አለ ፡፡ ነብዩላሂ ኢብራሂም ዳዕዋቸው አባታቸው ዘንድ ፍሬ ባለማፍራቱ ስሜታቸው ቢጎዳም የዳዕዋ ጉዞዋቸውን ከመቀጠል አላገዳቸውም ። በዘመኑ ወደ ነበረው ነምሩድ ወደ ሚባለው ንጉስ ሄደው ዳዕዋ ማድረግ ጀመሩ የነመምሩድ ባለሟሎች ጌታችን ነምሩድ ነው የሚል መልስ ሲሰጡ ነብዩላሂ ኢብራሂም በቆራጥነትና በአላህ ላይ በመመካት ነምሩድ ጌታ እንዳልሆነና የሁላቸውም ፈጣሪ አላህ መሆኑን አስመልክቶ ያደረጉትን ዳዕዋ አላህ ሲነግረን እንዲህ ይለናል : – قَالَ بَل رَّبُّكُمْ رَبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ الَّذِي فَطَرَهُنَّ وَأَنَا عَلَىٰ ذَٰلِكُم مِّنَ الشَّاهِدِينَ «አይደለም ጌታችሁ የሰማያትና የምድር ጌታ ያ የፈጠራቸው ነው ፡፡ እኔም በዚህ ላይ ከመስካሪዎቹ ነኝ» አለ ፡፡ የዚህን ጊዜ ነምሩድ ጌታ መሆኑን ሞገተ ። ነብዩላሂ ኢብራሂምም አላህ ማለት ምን አይነት ጌታ እንደሆነና የነምሩድን ደካማነት ያስመሰከሩበትን መረጃ አላህ በሱረቱል በቀራ 258 ኛው አንቀፅ ላይ ይነግረናል : – أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِي حَاجَّ إِبْرَاهِيمَ فِي رَبِّهِ أَنْ آتَاهُ اللَّهُ الْمُلْكَ إِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ رَبِّيَ الَّذِي يُحْيِي وَيُمِيتُ قَالَ أَنَا أُحْيِي وَأُمِيتُ ۖ قَالَ إِبْرَاهِيمُ فَإِنَّ اللَّهَ يَأْتِي بِالشَّمْسِ مِنَ الْمَشْرِقِ فَأْتِ بِهَا مِنَ الْمَغْرِبِ فَبُهِتَ الَّذِي كَفَرَ ۗ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ ወደዚያ አላህ ንግሥናን ስለሰጠው ኢብራሂምን በጌታው ነገር ወደ ተከራከረው ሰው አላየህምን ኢብራሂም «ጌታዬ ያ ሕያው የሚያደርግና የሚገድል ነው» ባለ ጊዜ «እኔ ሕያው አደርጋለሁ እገድላለሁም» አለ፡፡ ኢብራሂም፡- «አላህ ፀሐይን ከምሥራቅ በኩል ያመጣል (አንተ) ከምዕራብ በኩል አምጣት» አለው ፡፡ ያም የካደው ሰው ዋለለ ፤ (መልስ አጣ) አላህም በዳዮች ሕዝቦችን አይመራም ፡፡ ነምሩድ በዚህ መልኩ ማላገጥ ሲጀምር አላህ አዋርዶት ነብዩላሂ ኢብራምን በሐቅ ላይ የበላይ አድርጎ ተአምረኛው ጌታ ያ እኔ አምላክ ነኝ ሲል የነበረውን ነምሩድ አንድ ትንኝ በአፍንጫው ገብታ እራሱን እንኳን ከመከራ ማዳን እንደማይችል በማሳየት ለዘመናት ስታሰቃየው ቆይታ በዛው ፍፃሜው እንዲሆን አደረገው ። አላህ ካለ ይቀጥላል ። http://t.me/bahruteka
Show all...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

🔷 የነብዩላሂ ኢብራሂም ታሪክ ክፍል ሶስት ነብዩላሂ ኢብራሂም ዳዕዋቸውን ከንግግር ወደ ተግባር ለመቀየር ወሰኑ ። ለጣኦት አምላኪያን የሚያመልኩዋቸው ጣኦታት ያልተገዛቸውን መጎዳትም ሆነ የተገዛቸውን መጥቀም እንደማይችሉ ከዚህም በላይ ራሳቸውንም ከጥቃት የማይከላከሉ መሆናቸውን ማሳየት እንዳለባቸው አመኑ ። የባአላቸው ቀን ጠብቀው ሁሉም ተሰባስበው ወደ በአሉ ሲሄዱ ነብዩላሂ ኢብራሂም መጥረጢያቸውን ተሸክመው ወደ ጣኦቶቻቸው አመሩ ። የተለያየ ስለት እንዲሁም ምግብም አጠገባቸው ተቀምጦ አዩ ‼ አትበሉም እንዴ እያሉ ያናግሯቸው ጀመር መልስ የለም ። ትልቁን ብቻ አስቀርተው ጣኦታቱን ፈላልጠው ጨረሱ ። ከዛም መጠረቢያውን በትልቁ ጣኦት ላይ አስቀምጠው ጥለው ሄዱ ። ጣኦትአምላኪያኖቹ ከባአል ማክበሪያ ሲመለሱ በጣኦቶቻቸው ላይ የተሰራውን ጉድ አዩ ። ስለጣኦቶቻቸው ደካማነትና ስለራሳቸው ዐቅለቢስነት ከማሰብ ይልቅ በአማልክቶቻችን ላይ ማነው ይህን የሰራው እያሉ መጠያየቅ ጀመሩ ። ኢብራሂም የሚባል ነው ተባለ ፈልገው ጠየቋቸው ። እሷቸውም ትልቁን ጠይቁት የሚናገር ከሆነ ብለው መለሱ ። ይህን ክስተት ቁርኣን በሚቀጥለው የአል ንቢያ ምእራፍ ከ59 – 67 በዝርዝር ያስቀምጥልናል : – قَالُوا مَن فَعَلَ هَٰذَا بِآلِهَتِنَا إِنَّهُ لَمِنَ الظَّالِمِينَ «በአማልክቶቻችን ይህንን የሠራ ማነው እርሱ በእርግጥ ከበደለኞች ነው» አሉ፡፡ قَالُوا سَمِعْنَا فَتًى يَذْكُرُهُمْ يُقَالُ لَهُ إِبْرَاهِيمُ «ኢብራሂም የሚባል ጎበዝ (በመጥፎ) ሲያነሳቸው ሰምተናል» ተባባሉ፡፡ قَالُوا فَأْتُوا بِهِ عَلَىٰ أَعْيُنِ النَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَشْهَدُونَ «ይመሰክሩበት ዘንድ በሰዎቹ ዓይን (ፊት) ላይ አምጡት» አሉ፡፡ قَالُوا أَأَنتَ فَعَلْتَ هَٰذَا بِآلِهَتِنَا يَا إِبْرَاهِيمُ «ኢብራሂም ሆይ! በአማልክቶቻችን ይህንን የሠራህ አንተ ነህን» አሉት፡፡ قَالَ بَلْ فَعَلَهُ كَبِيرُهُمْ هَٰذَا فَاسْأَلُوهُمْ إِن كَانُوا يَنطِقُونَ «አይደለም ይህ ታላቃቸው ሠራው፡፡ ይናገሩም እንደ ኾነ ጠይቋቸው» አለ፡፡ فَرَجَعُوا إِلَىٰ أَنفُسِهِمْ فَقَالُوا إِنَّكُمْ أَنتُمُ الظَّالِمُونَ ወደ ነፍሶቻቸውም ተመለሱ፡፡ «እናንተ (በመጠየቃችሁ) በዳዮቹ እናንተው ናችሁም» ተባባሉ፡፡ ثُمَّ نُكِسُوا عَلَىٰ رُءُوسِهِمْ لَقَدْ عَلِمْتَ مَا هَٰؤُلَاءِ يَنطِقُونَ ከዚያም በራሶቻቸው ላይ ተገለበጡ፡፡ «እነዚህ የሚናገሩ አለመኾናቸውን በእርግጥ ዐውቀሃል፤» (አሉ)፡፡ የዚህን ጊዜ ጥሩ መግቢያ አገኙ ። ጠንከር ባለ ሁኔታ ዳዕዋ አደረጉላቸው ። ይህንንም ቁርኣን በዛው ምእራፍ በሚቀጥሉት አንቀፆች ላይ ይነግረናል :– قَالَ أَفَتَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَنفَعُكُمْ شَيْئًا وَلَا يَضُرُّكُمْ «ታዲያ ለእናንተ ምንም የማይጠቅማችሁንና የማይጎዳችሁን ነገር ከአላህ ሌላ ትገዛላችሁን» አላቸው፡፡ أُفٍّ لَّكُمْ وَلِمَا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ ۖ أَفَلَا تَعْقِلُونَ «ፎህ! ለእናንተ ከአላህ ሌላ ለምትገዙትም ነገር፤ አታውቁምን» (አለ)፡፡ ጣኦት አምላኪያኑም በመረጃ ሲሸነፉ ሐቅን ከመቀበል ይልቅ ወደ ሀይል ተሸጋገሩ ። ይህ የሁሉም የባጢል ተከታዮች ባህርይ ነው ። መረጃ ሲያጡ ጡንቻን መረጃ ያደርጋሉ ‼ ። ኢብራሂምንም አቃጥሉ ጣኦቶቻችሁንም እርዱ አሉ ። ይህም እውነታ ቁርኣ በሚቀጥለው አንቀፅ ያስቀምጠዋል : – قَالُوا حَرِّقُوهُ وَانصُرُوا آلِهَتَكُمْ إِن كُنتُمْ فَاعِلِينَ «ሠሪዎች እንደ ኾናችሁ አቃጥሉት፡፡ አማልክቶቻችሁንም እርዱ» አሉ፡፡ (በእሳት ላይ ጣሉትም)፡፡ ዐቅለ ቢሶቹም ነብዩላሂ ኢብራሂምን ለማቃጠል ወሰኑ ። ጥፋታቸው ጣኦታትን ራቁ አላህን ብቻ ተገዙ ማለታቸው ነው ። በወቅቱ የነበረው መንግስት ግንብ ገንቡና እሳት አቀጣጥላችሁ እዛ ውስጥ ጣሉት ብሎ አዘዘ ። ይህን ክስተት ቁርኣን እንዲህ ብሎ ይነግረናል : – قَالُوا ابْنُوا لَهُ بُنْيَانًا فَأَلْقُوهُ فِي الْجَحِيمِ «ለእርሱም ግንብን ገንቡ በእሳት ነበልባል ውስጥ ጣሉትም» አሉ ፡፡ በመንግስት ትእዛዝ ከፍታው 30 ሜትር ጎኑ የተራራ ጫፍ የሚሆን ምሽግ ተገነባ ። ማንኛውም ህዝብ እንጨት እንዲሰበስብ ታዘዘ ። ሴት ወንድ ፣ አዋቂ ልጅ ሁሉም ወደ 40 ቀን አካባቢ ስራውን ትቶ መሰብሰብ ጀመረ ። በዚህ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ክምር እሳት ተለኮሰበት ። ነበልባሉ ከሰማይ አሞራ ይጠልፍ ነበር ይባላል ። ጣኦት አምላኪያን ጉድ ተሰሩ ‼ ። ኢብራሂምን እንዴት በዚህ እሳት ይወርውሩ ? የሰው ሸይጣን መጥቶ ወስፈንጥር ( ምንጀኒቅ ) ዛሬ በዘመናዊ መልኩ መድፍ የሚባለው አይነት ማለት ነው እንዲሰሩና እዛ ላይ አድርገው እንዲወረውሩዋቸው ሐሳብ አቀረበ ። እንደተባሉት አደረጉ ። በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ጅብሪል መጣ ምን ትፈልጋለህ አላቸው ? ነብዩላሂ ኢብራሂምም ካንተ ምንም አልፈልግም ። አላህ በቂዬ ነው ምን ያማረ መጠጊያ ነው አሉ ። ወዲያውም የአላህ እርዳታ መጣ ። አላህ እሳትን አናገረ ። ይንንም ቁርኣን እንዲህ ብሎ አረጋገጠው : – قُلْنَا يَا نَارُ كُونِي بَرْدًا وَسَلَامًا عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ الأنبياء ( 69 ) «እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛ፤ ሰላምም ሁኚ» አልን፡፡ فَأَرَادُوا بِهِ كَيْدًا فَجَعَلْنَاهُمُ الْأَسْفَلِينَ الصافات ( 98 ) በእርሱም ተንኮልን አሰቡ፡፡ ዝቅተኞችም አደረግናቸው ፡፡ አላህ ካለ ይቀጥላል ። http://t.me/bahruteka
Show all...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👉   ፋሽኑ ያለፈበት ሹብሃ     የዛሬ 20 አመት አካባቢ ሱሩርዮች ሸይኽ ሙሐመድ ሳሊሕ አል ዑሰይሚን " ፊርቃ በበዛበት ጊዜ ወደየትኛውም አትጠጋ በትክክለኛ ኢስላም ላይ ቀጥበል ። ከድሮ ጀምሮ ብዙ ፊርቃዎች ተከስተዋል እንደ ራፊዳ ፣ ጀህሚያ ፣ ሙዕተዚላ … … ኢኽዋን ፣ ሰለፍያ ፣ ተብሊጝ የሚባሉ ፊርቃዎች አሉ እነዚህን ሁሉ ወደ ግራህ ትተህ ቁርኣንና ሐዲስን ያዝ ። በርግጥ አንድ ሰው መከተል ያለበት የሰለፎችን መንገድ ነው ። ሰለፍይ የሚባልን ፊርቃን አይደለም ……… "     ብለው ተናግረው ነበርና ይህን ይዘው እንደ ጉድ አራገቡት ። አብዛኛዎችንም ግራ አጋብተው ነበር ። አሁን ደግሞ አንዳንድ እንጭጮች ደንቆሮ የተሰማው ጊዜ ይዘፍናል እንደሚባለው ይህችን ሹብሃ ማራገብ ይዘዋል ። ለእንደነዚህ አይነት እንጭጮች የሚሰጠው ምላሽ የሸይኹ ንግግር ራሱ የሰለፎችን መዝሀብ መከተል ግዴታ መሆኑ ያስቀምጣል ። ከሳቸው በፊት የሰለፍ ሊቃውንቶች አረጋግጠውታል ። ንግግራቸውን መዘርዘር ከብዛቱ የተነሳ ከጭብጡ ያወጣናል ብዬ እሰጋለሁ ። ሌላው ቁርኣንና ሐዲስን በሰለፎች መንገድ የሚከተል ሰለፍይ የጥመት አንጃ ማለት በኢስላም ላይ ወሰን ማለፍ ከዚህም በላይ በሰለፍች ላይ መቅጠፍ ነው ። በተረፈ የሀገራችን ሰለፍይ መሻኢኾችና ኡስታዞች በአማርኛ በዚህ ዙሪያ የተናገሩዋቸው ራሱ ቁጥር ስፍር የለውም ።      ሸይኽ ዑሰይሚን እየተናገሩ ያሉት የማሕሙድ አል ሐዳድ ፊትና በተነሳበት ጊዜ የነበረውን ነው ። ራሳቸው የነበሩበት ጊዜ ስለነበረና ጅዳ ላይ የማሕሙድ ሙሪዶች ዐብዱል ለጢፍ ባሽሚልና ጓደኞቹ ሸይኽ ረቢዕንና ሸይኽ አልባኒን ሙብተዲዕ ያላለ ሙብተዲዕ ነው እያሉ ሰለፍይ ነኝ የሚለውን በዚህ እየፈተኑ በነበረበት ጊዜ ነው የተናገሩት ። እነዚህ አካላት ቢዳዓ ላይ ወድቋል ያሉትን ሁሉ ሙብተዲዕ ሲሉ የነበሩ ፈትሑል ባሪ ሽርሑል ሙስሊም የነወዊ ፈትሑል ቀዲር የሸውካኒ ተፍስርና የኢማሙል ቁርጡብይ ኪታቦች መቃጠል አለባቸው ሲሉ የነበሩ አካላት ናቸው ። ቁርኣንና ሐዲስን ሳይሆን እነርሱን ያልተከተለን በሙሉ ሙብተዲዕ ሲሉ የነበሩ ናቸው ። ታዲያ ሰለፍዮች ከእነዚህ ጋር ምን አገናኛቸው ? የጥመት አንጃ ብለው ረድ ከሚያደርጉባቸውና ከእነርሱ ከሚያስጠነቅቋቸው ውስጥ አንዱ ሆነው ሳሉ የኢኽዋን ርዝራዦች አሁንም ሰለፍያን ለመዋጋት እንዲህ አይነት ውዳቂዮችን እየለቃቀሙ ያሰራጫሉና ሰለፍዮች የሸይኹን ንግግር ምክንያትና በማን ላይ እንደሆነ አውቃችሁ መልስ ስጡ ። http://t.me/bahruteka
Show all...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

ሸይኽን ተከታለቱ ➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/WCUMSJ2015?livestreamበተወሰኑ ሙስሊሞች ላይ ችግር (ስህተት ) አለ ማለት በኢስላም  ላይ ስህተት አለ ማለት አይደለም፤ እስልምና ላይ ቅንጣት ያክል ስህተት የለም። 🎙 ሸይኽ አብዱልሐሚድ አላህ ይጠብቃቸው አሁን ሸይኹ ስለ ተመዪዕ  ቫይረስ  በሰፊው እያብራሩ ነው። ➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/WCUMSJ2015?livestream
Show all...
WACHEMO UNIVERSTY MUSLIM STUDENTS JAMEA(WCUMSJ)

ይህ የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመአ ኦፊሲየል የቴሌግራም ቻናል ነው!! This is the official channel of Wachemo University Muslim Students jamea. በዚህ channel ላይ:- ① የሚቀሩ ቂርዓቶችን ② የሚደረጉ ሙሀደራዎችን ማዳረስ ፡፡ ③ እንድሁም ሌሎች ዲናዊ ምክሮች ይላኩበታል ሀሳብ ካለዎት መልዕክትዎን በዚህ ይላኩልን! @Wcumsj1_bot

ኘሮግራማችን እንደ ቀጠለ ነው።ስለ ኢድ አከባበር እየተብራራ ነው። ገባ ገባ ይበሉ https://t.me/medresetulislah
Show all...
مدرسة الإصلاح (አል ኢስላሕ መድረሳ)

ይህ ቻናል ከፉሪ ሕይወት ፋና ወደ ዑመር ኢብኑ ዓብዱልዐዚዝ መስጂድ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ ኑሪ ሜዳ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የአል ኢስላሕ መድረሳ ኦፊሺያል የቴሌግራም ቻናል ነው። በአላህ ፍቃድ በመድረሳው የሚሰጡና በተለያዩ የሰለፊያህ ዱዓቶች፣ ኡስታዞችና መሻኢኾች የሚተላለፉ መልዕክቶች (በድምፅም ይሁን በፅሑፍ) ይተላለፉበታል።

https://t.me/medresetulislah

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته. ዛሬ ማለትም ዕለተ እሁድ በቀን 2/10/2016 E.C በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ታላቅ የሙሓዶራ ፕሮግራም ስለተዘጋጀ እንዳያመልጦ፤ እንዲሁም በሆሳዕና ዙሪያ ለምትገኙ...ፎንቆ፣ላፍቶ ሌንቃ፣አጫሞ፣በሌሳ...ይህ እጅግ በጣም ውብና ማራኪ የሆነው ፕሮግራም እንዳያመልጦ። ከወዳጅ ዘመዶዎ ጋር በዚህ በተከበሩት እስርት የዙል-ሒጃ ቀን ውስጥ የፕሮግራሙ ተቋዳሽ ይሁኑ!፤ከበረከቱም ይቋደሱ!፤ ባረከላሁ ፊኩም!!!!!!!! https://t.me/abdulham/2296
Show all...
"የሸይኽ ዐብዱልሐሚድ አል–ለተሚይ" ትምህርቶች ቻናል [THE OFFICIAL CHANNEL OF SHAYKH ABDULHAMID LATAMO]

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته. ዛሬ ማለትም ዕለተ እሁድ በቀን 2/10/2016 E.C በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ታላቅ የሙሓዶራ ፕሮግራም ስለተዘጋጀ እንዳያመልጦ፤ እንዲሁም በሆሳዕና ዙሪያ ለምትገኙ... ፎንቆ፣ላፍቶ ሌንቃ፣አጫሞ፣በሌሳ...ይህ እጅግ በጣም ውብና ማራኪ የሆነው ፕሮግራም እንዳያመልጦ። ከወዳጅ ዘመዶዎ ጋር በዚህ በተከበሩት እስርት የዙል-ሒጃ ቀን ውስጥ የፕሮግራሙ ተቋዳሽ ይሁኑ!፤ከበረከቱም ይቋደሱ!፤ ባረከላሁ ፊኩም!!!!!!!!

https://t.me/abdulham/2296

🟢89 አልፈጅር وَالْفَجْرِ. وَلَيَالٍ عَشْرٍ. وَالشَّفْعِ وَالْوَتْرِ. وَاللَّيْلِ إِذَا يَسْرِ} የሱረቱል ፈጅር መልእክት 🟢 የአመፀኞች መጨረሻ 🟢ድሎትም ችግርም ፈተናዎች ናቸው 🟢በኣኸራ መመከር http://t.me/Abuhemewiya
Show all...
89 አልፈጅር.mp37.40 MB