cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ተዋሕዶን እንጠብቃት

"ህዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቷል" ት. ሆሴዕ 4:6 አንብቡ ቤተ ክርስቲያንን እወቋት ከዛ እንጠብቃለን አለማወቅ እያጠፋን ነውና እንወቅ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር። ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ : https://t.me/joinchat/Ii5a8JeFvxA3NTJk

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
179Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

​​እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ #መዝ. 86፥1 “መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፡- መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮችናቸው” ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም በእመቤታችን ልደት ምክንያትዛሬ ደስ ሆነ፡፡ በግንቦት 1 ቀን 5ሺ ከ5መቶ የመከራው ዘመን ሊያልቅ 15 ዓመታት ሲቀሩት/ ሊባኖስ በሚባል ተራራ ከፀሐይ  የምታበራ ሴት ልጅ ተወለደች፡፡ ይህቺውም ፍጥረት ሁሉ ደቂቀ አዳም ሁላቸው ተስፋ ሲያደርጓትና ሲጠባበቋት የነበረች የድኅነታቸው ምልክት እመቤታችን ናት፡፡ ሶሪያዊው ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬምም  “አክሊለ ምክሕነ ወቀዳሚተ መድኀኒትነ፡፡ወመሠረተ ንጽሕነ ኮነ በማርያም ድንግል:- የመመኪያችን ዘውድ የደኅንነታችን መጀመሪያ የንጽሕናችንም መሠረት በድንግል ማርያም ሆነልን” በማለት መናገሩ ስለዚህ ነው፡፡ አክሊል ምክሐነ አላት ይህም አክሊል የወዲህኛው፣ ምክሕ የወዲያኛው ነው። ከነገሥታት መካከል እንደ ዳዊት የከበረ የለም። ምንም እንኳን ቅዱስ ዳዊት የከበረ ቢሆን የመመኪያችንን ዘውድ ማምጣት አልተቻለውም፡፡ ወቀዳሚተ መድኀኒትነ አላት፡- ቀዳሚተ የወዲህኛው መድኀኒት የወዲያኛው ነው፡፡ከመሳፍንት ወገን የሚሆን ኢያሱ ምንም የስሙ ትርጓሜ መድኃኒት ቢሆን የደኅንነታ መሆን አልተቻለውም፡፡ ወመሠረተ ንጽሕነ አላት:- መሠረት የወዲህኛው፤ ንጽሕ የወዲያኛው ከነቢያተ እግዚአብሔር ወገን የሚሆን ኤልያስ በድንግልና በንጽሕና መኖሩ የሚታወቅ ነው፡፡  ነገር ግን ምንም ንጹሕ ድንግል ቢባል የንጽሕናችንመሠረት መሆን አልተቻለው። የመመኪያችን ዘውድ፣ የደኅንነታችን መጀመሪያ፤ የንጽሕናችን መሠረት ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፤” በማለት ተናግሯል። በእርሷ ምክንያትነት መድኀኒዓለም  የሚፈጽምልንን ካሳነቢያትና የቀደሙ አበው ሁሉ  የእርሷን መወለድ በናፍቆት ሲጠባበቁ ነበር። ከነቢያት አንዱ የሆነ  ኢሳይያስም “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርዘርን ባያስቀርልን  ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንነ  እንደ ጎሞራም በመሰልነ ነበር፡፡” በማለት መናገሩ በእርሷ መገኘት  ከጥፋት መዳናችንን ሲገልጽ ነው፡፡ 
Show all...
የታላቁ የመድኃኔዓለም ልጆች በሙሉ እንካን ለጌታችን እና ለአምላካችን ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ እንኳን አደረሳችሁ መልካም በአል ለሁሏችሁም ክርስቶስ ተንስዓ እሙታን በአቢይ ሀይል ወስልጣን አሰሮ ለሰይጣን ወአገዓዞ ለአዳም ሰላም እምይዕዜሰ ኮነ ፍስሀ ወሰላም ዲያቆን ኤፍሬም የመድኃኔዓለም ልጆች
Show all...
#ሕማማት_ሐሙስ ከስቅለት በፊት ያለው ሐሙስ በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል፡፡ 1. # ጸሎተ_ሐሙስ_ይባላል ምክንያቱም - ጌታ ኅብስቱን በባረከ ጊዜ ስለጸለየ - በጌቴ ሴማኒ በዚህ ዕለት ስለጸለየ ነው 2. # የትእዛዝ_ሐሙስ_ይባላል ምክንያቱም - ከኅጽበተ እግር በኋላ ጌታችን ደቀመዛሙርቱን እናንተም እንዲሁ አድርጉ ብሎ ስላዘዘ - በጌቴሴማኒ ‹‹ወደፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ ›› ብሎ ያዘዘበት ዕለት በመሆኑ - ሥርዓተ ቁርባንን ከሠራ በኋላ ‹‹ከመዝግበሩ›› መታሰብያን አድርጉ በማለት በዚህ ዕለት ያዘዘበት በመሆኑ ነው፡፡ 3. # የነፃነት_ሐሙስ ፡- ይኸውም ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ወዳጆች ግን ብያችኋላሁ ያለውን የነፃነት ቃል ለማስታወስ 4. # ኅጽበተ_እግር ፡- ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር ማጠቡን የምናስብበት እና ዛሬም ጌታችን አብነት አድርገው ጳጳሳት ኢጴስ ቆጶሳት ቀሳውስት ከበታች ያሉትን ዝቅ ብለው እግር የሚያጥቡበት ዕለት ነው፡፡ 5. # አረንጓዴው_ሐሙስ_ይባላል ፡፡ በዚህ ዕለት ጌታችን በአትክልት ቦታ መጸለዩን የሚያስታውስ ስያሜ ነው፡፡ 6. # የሐድስ_ኪዳን__ሐሙስ ፡- ጌታችን በዚህ ዕለት ምሽት ‹‹ይህ የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው›› በማለት የሰጠንን ዘላዓለማዊ ኪዳን የሚያስታውስ ስያሜ ነው፡፡ ኪዳን ማለት በሁለት ወገን የሚደረግ ውል፣ ስምምነት መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓለማዊ የቃል ኪዳኑ ፈጻሚዎች ጠባቂዎች መሆናችንን ማጠየቅ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡፡ 7. # የምሥጢር_ቀን_ይባላል ፡፡ ከሰባቱ ምሥጢራተ አንዱ የሆነው ምሥጢረ ቁርባን በዚህ ምሽት የተመሠረተ በመሆኑ ነው፡፡ 8. # ፋሲካ_በአልዓዛር_ቤት_ይባላል ፡፡ ጌታችን የአይሁድን የፋሲካ በዓል ያከበረበት ታላላቅ ምሥጢራትን የፈጸመበት በአልዓዛር ቤት በመሆኑ ነው፡: በጠቅላላው በዚህ ሐሙስ ዕለት ቅዳሴ በለሆሳስ ይቀደሳል፣ እንደ ቃጭል ሆኖ የሚያገለግለው ጸናጽል ነው፡፡ ይህም 1.አይሁድ ጌታን ለመያዝ ሲመጡ በለሆሳስ እየተገጋገሩ መምጣታቸውን ለማሰብ 2. በዘመነ ብሉይ ጸሎት ዋጋው ምድራዊ እንደነበር ለማጠየቅ ነው፡፡ በቅዳሴው ጸሎት ኑዛዜ አይደረግም ሥርዓተ ቁርባን ግን ይፈጸምበታል፡፡
Show all...
“በዐቢይ ጾም መጀመሪያ ሱባኤ ፀሐይ እስኪገባ ይጹሙ፣ ሌሎቹን ሳምንታት እስከ 11 ሰዓት ይጹሙ፥ በሰሙነ ሕማማት ግን ኮከብ እስኪወጣ ይጹሙ” ብለዋል። (ፍት.ነገ.አን 15፥595)። ፍትሐ ነገሥት ቁጥር 578 ላይ ደግሞ “(የሰሙነ ሕማማትን) ዓርብንና ቅዳሜን ግን ሁለቱንም በአንድነት ይጹሟቸው፣ የሚችል እስከ ሌሊት ዶሮ ጩኸት ድረስ ምንም ምን አይቅመስባቸው፣ ሁለቱን በአንድነት መጾም የማይቻለው ግን ቅዳሜን ይጹም” ተብሎ ህግ ተሠርቷል።
Show all...
#በሰሙነ_ሕማማት_የሚፈጸ_ሥርዓቶች 1, #ስግደት :- በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል። 2, #ጸሎት :- በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው። በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ። 3, #ጾም :- በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት / አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ #አንድ_ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል። 4, #አለመሳሳም :- አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም። መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ.3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29 5. #አክፍሎት :- እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው። 6, #ጉልባን :- ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው። 7, #ጥብጠባ :- ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው። ይህም የጌታ ምሳሌ ነው። 8, #ቄጠማ :- ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን። እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም። #ሼር Join @ortodoxslijoch
Show all...
ሚያዚያ 5 ልደቱ ለቅዱስ ያሬድ ልደት ꔰ ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ #ሚያዚያ 5 ቀን በ505 ዓ.ም. ከአባቱ ይስሐቅ(አብድዩ) ከእናቱ ክርስቲና (ታውክልያ) በአኵሱም ከተማ ተወለደ፡፡ (አንዳንዶች ልደቱን 493 ዓ.ም. ነው ይላሉ፤ እንዲሁም አባቱ ኖኅ ነው ይሉና መሪጌታ ይስሐቅ የቀለም አባቱ /መምህሩ/ ነው ይላሉ፡፡) ꔰ የስሙም ትርጓሜም ያሬድ ማለት #እንዚራ፣ በገና፣ መሰንቆ ማለት ነው ፡፡ እነዚህ መሣሪያዎች በስልት በስልት ሲመቱ ለሚሰማቸው ደስ እንዲያሰኙ የያሬድም ዜማ በንጉሠ ነገሥቱ ክርስቶስ አደባባይ በቤተ ክርስቲያን ሲሰማ መላእክትን፥ ሰውንና እንስሳትን ደስ ያሰኛልና፡፡ አንድም ያሬድ ርደት፣ ወሪድ፤ መውረድ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ሰማያዊውን ልዩ ጣዕመ ዜማ ወደ #ኢትዮጵያ አውርዷልና፡፡ / ፍኖተ ሕይወት ሰ. ት. ቤት/ * አንድም ያሬድ ማለት ንብ ማለት ነው፤ ንብ የማይቀስመው አበባ እንደሌለ ሁሉ ቅዱስ ያሬድም ከመጻሕፍት የማይጠቅሰው የማይቀሰመው የለም፤ አንድም ያሬድ ማለት ረአዬ ምሥጢር፥ ነጻሬ ኅቡአት ማለት ነው፤ የመላእክት ምሥጢራት የነበሩትን ጸዋትወ ዜማ አምልቶ አስፍቶ ተናግሯልና፣ ነጻሬ ኅቡአት አለ፥ ኅቡእ (ስውር) የሆነ የጻድቃን፣ የሰማዕታት የነቢያት የሐዋርያትን ገድል አምልቶ አስፍቶም ይናገራልና፡፡ * አፄ ካሌብ ቤተ እስራኤል፣ ገብረክርስቶስና ገብረ መስቀል የሚባሉ ልጆች ነበሩት፤ ቅዱስ ያሬድ የተነሳው ከእነዚህ ውስጥ በአፄ #ገብረመስቀል ዘመን ነው፡፡ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇 •➢ ሼር // SHARE ✧┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✧ @DNZEMA 🤏 @DNZEMA 🤏 @DNZEMA 🤏
Show all...
እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን የአብይ ፆም ሰባተኛው ሳምንት "ኒቆዲሞስ" ይባላል። ◄◉►ኒቆዲሞስ◄◉► ኒቆዲሞስ ማለት :- በቤተክርስቲያን ሰባተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ኒቆዲሞስ ይባላል። ◾ትርጓሜው የአይሁድ መምህር ወይም ደሞ የጌታችን ደቀ መዝሙር የሌሊቱ ተማሪ ማለት ነው። ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ነው።ዮሐ 3:1 ኒቆዲሞስ የአይሁድ አለቃ ነው።ዮሐ 3: 1 ኒቆዲሞስ መምህረ እስራኤል ነው።ዮሐ 3:10 ኒቆዲሞስ ምሁረ ኦሪት ነው።የሐ 7:51 ◾ኒቆዲሞስ በኢየሩስ አሌም በሀብት በእውቀት ዝና በስልጣን የታወቀ ነው።ኒቆዲሞስ ስለ ሶስት ነገር ሌሊት ሌሊት እየሄደ ከጌታ እግር ስር ይማር ነበር። 1 አይሁድ ፈርቶ:-በዛን ሰአት በአይሁድ ህግ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር የሆነ ሀብት ንብረቱ ስለ ሚቀማ ከነሱ ለመሸሽ ሌሊትን መረጠ። 2,ውዳሴ ከንቱን ሽቶ:-በወቅቱ የነበረ እውቅ ሊቅ ነበርና እንዴት ከመምህር ስር ይማራል እንዳይሉት። 3 ልቡናው እንዲሰበሰብ:-ከቀን ይልቅ ሌሊት የአይምሮ እረፍ ስላላት እሱን ሽቶ ነው። ◾ኒቆዲሞስ ከጌታ እግር ስር ቁጭ ብሎ ስለ ምስጢረ ጥምቀትና ዳግመኛ ልጅነት የፅድቅ ስራ በሰፊው ተምሮአል።ዮሐ ም 3፡ 1-12 ወስብሐት ለ እግዚአብሔር
Show all...
እሳት ቅኔ አማረው?! የተወለደበትን ቀዬ ትቶ ቃሉን ሊማር የወጣው ከርታታ ተማሪ! "በእንተ ስማ ለማርያም ስለ እመብርሃን" ከሚል ቃል በቀር ሌላ ስንቅ ያልያዘው ምስኪን ተማሪ! ከወላጆቹ እቅፍ ተነጥሎ ቤተክርስቲያንን ቤቴ ብሎ የወጣው የጽድቅ ስደተኛ ተማሪ! ምቾቱን ሳይፈልግ መሬት ላይ እየተኛ ስንቁን ለምኖ በጎስቋላ ጎጆ የሚያድረው ተማሪ! ሥጋውን አስርቦ ነፍሱን የሚያጠግበው በቃለ እግዚአብሔር ማዕበል ውስጥ እየዋኘ የሚያድረው ተማሪ! ጎጆውም ከቤት ተቆጥራ እሳት ነደደባት ሲባል መስማት ምንኛ ያቆስላል? የወላጆቹን ቤት ተሰናብቶ ወጥቶ ቤቱ ያደረጋት የሳር ጎጆ : ለምኖ የሚያመጣትን ስንቅና በስስት የሚያነባቸውን መጻሕፍቱን የሚያስቀምጥባት ምቾት አልባዋ ጎን ማሳረፊያው ተቃጥላ ስትጠብቀው ምን ተሰምቶት ይሆን? ምስኪኑ ተማሪ ዛሬ የት አድረህ ይሆን? አንተ ባለ ቅኔ ዛሬ ለጎጆህ ምን ተቀኝተህላት ይሆን? መቼም ቅኔ የማይጠራው የለም! እሳትም ቅኔ አምሮት ከቅኔ ቤት ገባ? የሚቻለንን ሁሉ አድርገን ስደተኛውን ቅኔ ወደ ቤቱ እንመልሰው:: ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ መጋቢት 2014 ዓ.ም.
Show all...
​​የቀጠለ 👆 በመሆኑም የባለ አምስትና የባለ ሁለት መክሊት ባለቤቶች የሆኑት ወጥተው ወርደው ደክመው፣ መከራ መስቀልን ሳይሳቀቁና ሳይፈሩ፤ ወድደው ፈቅደው የጀመሩትን አገልግሎት በማክበር ሕይወታቸውን ለታመነው አምላክ አደራ በመስጠት የተማሩትን ፍጹም ትምህርት ለሌላው አስተምረው፣ ሠርተው ያገኙትን ለሌላው አካፍለው ወገናቸውን እንደራሳቸው አድርገው ሲመለከቱ ባለ አንድ መክሊት የተባለው ግን ዓላውያን እሳት ስለት አሳይተው ሃይማኖቴን ሲያስክዱኝ መናፍቃን ተከራክረው ምላሽ ቢያሳጡኝ ብሎ ፈርቶ ሃይማኖቱን በልቡ ከመደበቅና ከመሠወር በቀር የተማረውን ትምህርት ሠርቶ ያገኘውን ሀብት ንብረት ለሌላው ሊያካፍልና የተሰጠውን አደራም ሊወጣ አልወደደም፡፡ ይህ የመክሊቱ ባለቤት የተባለው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን የተሰጣቸውን ሓላፊነት በአግባቡና በጽንአት ለተወጡት ሁሉ እርሱ ፍጹም ዋጋን የሚሰጣቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡ ይህም ሁኔታ “አንተ በጎ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ። ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” በሚል ታላቅ የምስጋና ቃል ተገልጧል፡፡ ይህ ቃል በሃይማኖትና በበጎ ምግባር ለእግዚአብሔር የታመኑ ሁሉ ዘለዓለማዊና ፍጹም ደስታ ወደሚገኝበት መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ለሚያደርጉት የእምነት ጉዞ እጅግ ተስፋ የሆነ ቃል ነው፡፡ በዚህ ምንባብ ላይ እንደተገለጸው እግዚአብሔር አምላክ ለሁላችንም እርሱን የምናገለግልበትንና ለእርሱ በመታመን ዘለዓለማዊ ክብርን የምናገኝበትን ዕውቀትን፣ ማስተዋልን፣ እምነትን፣ ተስፋን፣ የሥነ ምግባር ሀብትን፣ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን እንጠቀምባቸው ዘንድ ለእኛ ለሰው ልጆች እንደየዓቅማችን መጠን ሰጥቶናል፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች የሥጋችንን ምኞት ለማስፈጸም የተሰጡ ሳይሆኑ ነፍሳችን የምትከብርበትን መልካም ሥራን የምንሠራባቸው መሣሪያዎቻችን ናቸው። በመሆኑም እርሱ በሰጠን የአገልግሎት በር ጸጋ በታማኝነት በማገልገል በሕይወት ዘመናችን ሁሉ መንፈሳዊውን ሀብት የምናተርፍ እንሆን ዘንድ የተላለፈልን አምላካዊ ምክር ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ የተጠራነው ፍሬ ልናፈራና ሌላውንም ልናተርፍ መልካም ሥራን ልንሠራ እንጂ የሥጋችንን ፈቃድ በመከተል የኃጢአት ባሮች ልንሆን አይደለም፡፡ መጽሐፍ እንዲህ አለ “ወኲሉ ዘከመ ተጸውአ ከማሁ ለየሀሉ፤ ሁሉ እንደተጠራ እንዲሁ ይኑር” /፩ኛ ቆሮ. ፯፥፳/ ከላይ እንደተመለከትነው በልዑል አምላክ በእግዚአብሔር አንደበት አንተ በጎ ታማኝ አገልጋይ በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ መባልን የመሰለ አስደሳችና አስደናቂ ነገር የለም፡፡ ይህ ደግሞ የሚገኘው ሃይማኖትን በሥራ በመግለጥ እንጂ ሃይማኖትን በልቡና በመያዝ ብቻ /ሙያ በልብ ነው/ በማለት ብቻ የሚገኝ አይደለም፡፡ ከእነዚህ እንደ አቅማቸው መጠን መክሊት ተሰጥቷቸው በትጋታቸውና በቅንነታቸው ሌላ መክሊት ካተረፉት በጎና ታማኝ አገልጋዮች የምንማረው እውነታም ይህ ነው፡፡ በብዙ ለመሾም ለማደግ ለመጽደቅ በጥቂቱ መታመን መፈተን መጋደል ግድ ነው፡፡ አንድ መክሊት የተሰጠውን ሰው ስንመለከተው ጌታውን ጨካኝና ፈራጅ አድርጎ ከመቁጠር ውጪ በተሰጠው መክሊት ወጥቶ ወርዶ ሊያተርፍ አልወደደም፡፡ መክሊቱንም ባስረከበ ጊዜ በጌታው ላይ የተናገራቸው ቃላት የእርሱን አለመታዘዝና አመጸኝነት ይገልጡ ነበር፡፡ በመሆኑም ይህ ሰው በጥቂቱ መታመን ያቃተውና በአስተሳሰቡ ደካማነት እጅግ የተጎሳቆለ ሰው ነው፡፡ በዚህ ምሳሌ መሠረት ይህ ባለ አንድ መክሊት የተባለው ሰው ዓላውያን ነገሥታት እሳት ስለት አሳይተው ቢያስክዱኝ መናፍቃን ተከራክረው መልስ ቢያሳጡኝ በማለት ሃይማኖቱን በልቡ ሸሽጎና ቀብሮ በተቀደሰ ተግባር ሳይገልጠው ከመያዙ ባሻገር በጌታ ፊት በድፍረት ቆሞ አንተ ሕግ ሳትሠራ በአእምሮ ጠባይዕ አውቃችሁ፤ መምህራንንም ሳትመድብ በሥነ ፍጥረት ተመራምራችሁ በሠራችሁ ብለህ የምትፈርድ ጽኑ ጨካኝ መሆንክን አውቃለሁና ፈርቼ ሃይማኖቴን በልቡናዬ ይዠዋለው በአዕምሮዬ ጠብቄዋለሁ የሚል ሃይማኖቱን ግን በሥራ የማይገልጥ ሰነፍ ሰውን ያመለክታል፡፡ ለዚህ ዓይነት ሰው የጌታ መልስ ደግሞ በምሳሌው መሠረት የሚከተለው ነው። እኔ ሕግ ሳልሠራ በአእምሮ ጠባይዕ አውቃችሁ ፤ መምህር ሳልሰጥ በሥነ ፍጥረት ተመራምራችሁ አውቃችሁ በሠራችሁት ብዬ የምፈርድ ጽኑ ጨካኝ መሆኔን ታውቃለህን? እንዲህስ ካወቅህ ሹመትክን ልትመልስልኝ ይገባኝ ነበር፡፡ ወጥቶ ወርዶ ለሚያስተምር በሰጠሁት ነበር፡፡ አሁንም የእርሱን መምህርነት ሹመት ነሥታችሁ (ወስዳችሁ) ለዚያ ለባለ ዐራቱና ለባለ ዐሥሩ ደርቡለት! እርሱን ግን አውጡት የሚል ነው። ምክንያቱም ከበጎ ምግባር የተለየች እምነት የሞተች እንደሆነ ተጽፏልና። ዛሬም እያንዳንዳችን በዓቅማችን መጠን መክሊት ተሰጥቶናል፡፡ ነገር ግን መክሊቱን እንደቀበረው እንደዚያ ሰው የተሰጠንን ቀብረን ለወቀሳና ለፍርድ እንዳንሰጥ በአገልግሎታችን ልንተጋ ይገባናል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህንኑ ሲገልጥ “ወዘሂ ይትለአክ በመልእክቱ፤ ወዘሂ ይሜህር በትምህርቱ. . .፤ አገልግሎት ቢሆን በአገልግሎታችን እንትጋ የሚያስተምርም በማስተማሩ ይትጋ የሚሰጥም በልግሥና ይስጥ›› (ሮሜ. ፲፪፥፯) በማለት ተናግሯል፡፡ ለመሆኑ አሁን ባለንበት የስግብግብነት ወቅት ዛሬ ‹‹አንተ በጎ ታማኝ አገልጋይ…›› ተብሎ በእግዚአብሔር ሊመሰገን የሚችል ሰው ማን ይሆን? በእውነት እንዲህ ተብሎ የሚመሰገን በጎና ታማኝ ካህን በጎና ታማኝ መምህር በጎና ታማኝ ምእመን ታማኝ ሰባኪና ታማኝ ዘማሪ ማግኘት ይቻል ይሆንን? ነገር ግን መቼም አምላካችን ቸር ነውና በየዘመናቱ አንዳንድ ታማኝ አባቶችን እንደማያሳጣን ተስፋ አለን። ምክንያቱም ዛሬም ቢሆን እንደአባቶቻችን እንደቅዱሳን ሐዋርያት በእምነት፣ በትዕግሥት በፍቅር በተጋድሎ በየውሐት በትሕርምት በጸሊዓ ንዋይ በትሕትናና በትጋት በማገልገል የተሰጣቸውን መክሊት የሚያበዙ አገልጋዮች አሉ፡፡ የእነዚህ ክብራቸው በምድርም በሰማይም እጅግ የበዛና ራሳቸውን አስመስለው በትምህርት የወለዷቸው ልጆቻቸውም ለቤተ ክርስቲያን የተወደዱ የተከበሩ ልጆች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ነቢየ እግዚአብሔር ሙሴ ነቢየ እግዚአብሔር ኢያሱን ፤ ቅዱስ ጴጥሮስ ቀሌምንጦስን፣ ቅዱስ ጳውሎስም ቅዱስ ጢሞቴዎስን ለቤተ ክርስቲያን አበርክተዋል፡፡ ሌሎችም አበው ቅዱሳን በወንጌል ቃል መንፈሳውያንና ትጉሃን የሆኑ ምእመናንን በሚገባ አፍርተዋል፡፡ ያላመኑትንም አሳምነው ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመመለስ ለዘለዓለማዊ ክብር የበቁ እንዲሆኑ አስችለዋቸዋል። በተሰጣቸው ጸጋም አትርፈው አትረፍርፈው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሀብተ መንፈስ ቅዱስ እንድትጎበኝ አድርገዋል፡፡ የእነርሱም በረከታቸው ረድኤታቸው ቃል ኪዳናቸው ለሌሎች እንዲተርፍ ሆኖላቸዋል፡፡ በመሆኑም ክርስቶስ በደሙ የከፈለውን ወደር የሌለውን ዋጋ ዓለም አምኖና ተቀብሎ በክርስትና ሃይማኖት እንዲድንበትና እንዲጠቀምበት በማድረግ እንዲሁም በታማኝነትና በበጎነት አገልግሎታቸው ጥንትም ዛሬም ላለችዋና ወደፊትም ለምትኖረዋ ቅድስት ቤተክርስቲያን ድምቀትም ውበትም የሆኑት ቅዱሳን አበው ሊገኙ የቻሉት ከእግዚአብሔር ይልቅ ሰውን ደስ ለማሰኘት በመድከማቸው ሳይሆን የተጠሩበትን ዓላማና የጠራቸውን እርሱን በሚገባ አውቀውና ከልብ ተረድተው ለዘለዓለማዊ ሕይወት ተግተው በመሥራታቸው ነው። ወስብሐት ለእግዚአብሔር 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...