cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

መንፈሳዊ ትምህርት | eotc theology

Eotc theology... ዘውትር ከሰኞ - አርብ በመርሐግብሩ #ተከታታይ ትምህርት በፅሁፍ #live ትምህርት #መዝሙር #ወቅታዊ ጉዳዮችን እንዳስሳለን

Show more
Advertising posts
5 418
Subscribers
No data24 hours
+307 days
+12330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

መንፈሳዊ የውይይት ግሩፕ ይቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/kidanameherat16
Show all...
"ኢየሱስም እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም " አለ ዮሐ 14:6 #_ይህን_ለምን_አለ ? ጌታችን እኔ መንገድ ነኝ ማለቱ የአንድነትና የሶስትነት መገለጫ እኔ ነኝ ማለቱ ነበር ። ምክንያቱም ጌታችን በስጋ ከመወለዱ በፊት እግዚአብሔርን አንድ እግዚአብሔር ከማለት ውጪ የአካል ሶስትነት ማለትም አብ፣ ወልድ ፣ መንፈስቅዱስ አይታወቅም ነበርና ጌታችን በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ያለው ታዲያ ለምንድነው ? ያልን እንደሆነ *፦ የወልድን ልጅነት ያላመነ የአብን አባትነት አያምንም ፤ የላከውን ልጁን ያልተቀበለ አብን አያውቅምና የአባትነት ማንነት በልጅ ስለሚታወቅ የእኔን ወልድነት "#ተወላዲነት" ካላመነ አብ በደመና የምወደው ልጄ ይህ ነውና በእርሱ እመኑ ብሎ ሲመሰክር ሰምቶ ካላመነ አይድንም ሲል ነው *።ዮሐ 14:7፣ 14:1 ፣14:21 ይመልከቱ ።  በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብዙ ቦታ ላይ ስለ #*መንገድ* ተጠቅሷል ። መናፍቃን ስለሌላው መንገድ በሚገባ ለምን እንደተባለ ሳያብራሩ ጌታ የተናገረውን በመጥቀስ ብቻ እኔ መንገድ ነኝ ማለቱ አማላጅ ነኝ ማለቱ ነው ይላሉ። እስቲ ከመጽሐፍ ቅዱስ ስለመንገድ ከተጠቀሱት ጥቂቱን እንመልከት፦ #1."እግዚአብሔር እንዲህ ይላል #*በመንገድ* ላይ ቁሙ ተመልከቱም የቀደመችውንም #*መንገድ* ጠይቁ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደሆነች እወቁ በእርሷም ላይ ሂዱ ለነፍሳችሁም እረፍት ታገኛላቹ " ት.ኤር 6:16 #2."ሀሳቤ እንደ ሀሳባችሁ #*መንገዳችሁም* እንደ #*መንገዴ* አይደለምና ይላል እግዚአብሔር " ኢሳ 55:8 #3."ካዘዝኀቸው #*መንገድ* ፈጥነው ፈቀቅ አሉ "ዘዳ 32:8 #4."በሕይወት እንድትኖሩ መልካምም እንዲሆንላችሁ በምትወርሷትም ምድር እድሜአችሁ እንዲረዝም አምላካችሁ ባዘዛችሁ #*መንገድ* ሁሉ ሂዱ " ዘዳ 5:33 #5."ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ  #*መንገዱም* ትልቅ ነውና ወደ እርሱ የሚገቡ ብዙዎች ናቸው " ማቴ 7:13 እንግዲህ #*መንገድ* የሚለው በጥሬው አገላለጽ በርካታ ትርጉሞችን ይዞ እናገኘዋለን መናፍቃን እንደሚሉት ግን በዚህ ጥቅስ ውስጥ ስለ አማላጅነት የተነገረ አንዳችም ነገር የለም ይልቅ በወልድ ልጅነት በማመን ወደ አብ መድረስ እንደሚቻል የተነገረ የሕይወት ቃል ነው ። ከላይ ባየናቸው ጥቅሶች መንገድ ሃይማኖት ነው ፣ መንገድ ትዕዛዘ  እግዚአብሔር ነው ፣ መንገድ ፍቃደ እግዚአብሔር ነው ፣ መንገድ ወንጌል ነው *ደግሞም ምልጃ የሚያስፈልገው ምህረትን ለማግኘት ነው ምሕረት ደግሞ ለመዳን ሲሆን መዳን ማለት ደግሞ የዘላለም ሕይወት ማለት ከሆነ* ጌታችን ደግሞ "እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ "እያለ "በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም " የሚለው ቃል እንዴት አማላጅ ተብሎ ይተረጓማል ? መናፍቃን እንደሚሉት አማላጅ ተብሎ የሚተረጎም ከሆነ ግን *ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወትን የሚሰጥ  ሕይወት  መሆኑ  ቀርቶ ሕይወት አሰጪ መሆኑ ነው* ይሄ ደግሞ የክህደት ክህደት ነው *ጌታችን መንገድ ነኝ ያለበት ሌላው ም/ት*፦ መንገድ ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ስፍራ የሚያደርስ ፣ የሚወስድ ማለት ነው ። ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለኛ በመገረፋ ፣ በመቁሰሉ ፣ በመመታቱ ፣ መስቀል ላይ ስለኛ ሀጢአት በመሰቀሉ ፣ በደላችንን ሁሉ ተሸክሞ በፍቅሩ እኛን ወደ እርሱ በመጥራቱ ከነበርንበት የዘላለም ሞት አውጥቶ ወደ ዘላለም ሕይወት አሻገረን አደረሰን ይህም እውነተኛውና ብቸኛው የመዳናችን መንገድ እርሱ በመሆኑ ነው ።አዳምና ሔዋን ዕፀ በለስን እንደበሉ ከተፈረደባቸው ቡሃላ "እግዚአብሔር አምላክም አለ ...እጁን እንዳይዘረጋ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ ...ከገነት አስወጣው ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም #*መንገድ* ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔደን ገነት ምስራቅ አስቀመጠ። " ዘፍ 3:22 *እንግዲህ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደው #መንገድ* *ስለተዘጋ ወደ ሕይወት የሚያደርሰን #መንገድ* *ያስፈልገን ነበር * ስለዚህም እርሱ ሕይወት ነውና #*መንገድ* በመሆኑ ተዘግታ የነበረችውን ገነት አስከፈተልን  መከፈቱንም ሊያረጋግጥልን በቀኙ ተሰቅሎ የነበው ወንበዴ " በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ " ሲለው "ኢየሱስ እውነት እልሃለው ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ "አለው ሉቃ 23:42 ሌላው መንገድ ነኝ ያለበት ፦ "*ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው *" ዮሐ6:5 ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ እኛን ከኀጢአት ሞት ወደ ዘልዓለማዊ ሕይወት የሚያሻግረን ስለሆነ *እኔ መንገድ ነኝ* አለ እንጂ መናፍቃን እንደሚሉት ለምልጃ የተጠቀሰ ቃል አይደለም ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE ✧┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✧ @dnzema @dnzema @dnzema ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
Show all...
3
ክርስቶስ ሕያው ነው ክርስቶስ ሕያው ነው ሞት ይዞ ያላስቀረው የለም ከመቃብር ተነሰቷል በክብር /2/ በገዛ ፈቃዱ ነፍሱን ስለሰጠ የጨለመው ዓለም በብርሃን ተዋጠ ሲኦል ድል መንሳቱ መውጊያውም ታጠፈ የሞት ስልጣን በሞት ስለተሸነፈ የጥሉ ግድግዳ በሞቱ ፈረሰ የነፍሳችን ቁስል በእርሱ ተፈወሰ ከቶ አላስቀረውም የመቃብር ድንጋይ ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ኤልሻዳይ ዓለሙን እንዲሁ እግዚአብሔር ወዶ የሰው ልጅ ከበረ ዲያብሎስ ተዋርዶ ይገዛን ይነዳን ያስጨንቀን ነበር በሞት ላይ ተራመድን አምላካችን ይክበር ሕይወት ይሰጠን ዘንድ ስለኛ የሞተው ቤዛችን ክርስቶስ ሞትን ድል አረገው የሞተው ተነስቷል በመቃብር የለም ዳግመኛም ይመጣል ሊፈርድ በዓለም 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
ሼር ያድርጉ 🔺
ክብርህ ገነነ ክብርህ ገነነ ቅዱስ ስምህ አልተከደነም መልካም ስራህ መቃብር ድንጋይ ያላስቀረህ ኃያል ጌታ ነህ ሞት ማይገዛህ የወይን ስካር እንደለቀቀው እንደ ኃያል ሰው እንደታጠቀው በዝግ መቃብር ጌታ ተነሳ ጠላትን ጥሎ እኛን አነሳ አዝ የሞተልንን እንሰብካለን የተነሳውን እናመልካለን ኃያል ነው በእውነት ታላቅ ነው ጌታ በራሱ ስልጣን ሞትን የረታ አዝ በኩር ነውና የትንሳኤያችን ልባችን ጸና ሞላ ተስፋችን ሞተን አንቀርም እንነሳለን ጥልቁን ተሻግረን እንዘምራለን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
Show all...
2
ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ ✥ ● ሰኞ - ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡ ● ማክሰኞ - ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29 ● ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡ ● ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ ● አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡ ● ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡ ● እሁድ- ዳግም ትንሳኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡ ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 🔴• ለኦርቶዶክሳውያን ሼር // SHARE በማድረግ ለማያውቁት እናሳውቅ ‼️ ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ቻናላችንን ተቀላቀሉ 👇 ◽  •✥• @DNZEMA •✥•🔺 ◽  •✥• @DNZEMA •✥•🔺 ◽  •✥• @DNZEMA •✥•🔺
Show all...
👍 3🙏 3 2😍 1
ጌታ ተነስቷል ጌታ ተነስቷል እልል እልል በሉ አምላክ ተነስቷል የምስራች በሉ ሙስና መቃብር በኃይሉ አጥፍቶ ሁላችን አየነው ክርስቶስ ተነስቶ /አዝ ===== አዳምን ለማዳን ቃልኪዳን ገብቶለት ዘመኑን ጠብቆ ካሳ ሊከፍልለት ከሰማያት ወርዶ የተሰቀለው ሞትን በሞት ሽሮ ይኸው አየነው /አዝ ===== ደቀ መዛሙርቱ እጅጉን ተጨንቀው በጌታቸው መሞት በኀዘን ተመተው በተዘጋ ደጃፍ ተሰብስበው ሳለ እጆቹን ዘርግቶ ሰላም ለእናንተ አለ /አዝ ===== ማርያም መግደላዊት እየገሰገሰች በለሊት ተነስታ ወደ አምላኳ ሄደች አይሁድ አንገላተው የሰቀሉት ጌታ ተነስቶ አግኝታው ተመላች በደስታ •➢ ሼር // SHARE ✧┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✧ •✥•🍁 @Z_TEWODROS 🍁•✥• @Z_TEWODROS •✥•🍁 @Z_TEWODROS 🍁•✥• ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
Show all...
ሂዱ ንገሩ አውሩ ለአለም ተነሥቷል በዚህ የለም/2/ መድኃኔ አለም ሞት የማይችለው የበረታ ኃያል ነው የማይረታ ማኅተሙን የፈታ የትንሳኤው ጌታ ገዳዩ ሞት በእርሱ ድል መንሳት ተዋጠና ሰንሰለቴን ቀንበሬን ተካው በበገና ሞት ሆይ መውጊያህ የታል እያልን እምንዘምረው መስቀልህ ጦር ስምህ ጋሻችን ሆኖልን ነው ዳንን የምንለው ተሻግረናል ስላሻገርከን ለዘላለም በመቃብር ሞት ይይዘህ ዘንድ ከቶ አልቻለም ኃይለኛውን በኃይል አስረኸው ላይፈታ መመርንልህ አሸናፊ ነህ የእኛ ጌታ ከፍ በል በእልልታ ማቶ ማዳን ለማን ተችሏል ካንተ በቀር ጌትነትህ ስራህ ይኖራል ሲመሰከር ወዳጄ ሆይ ውበትህ ውብ ነው የሚያበራ ተጨነቀ ተንቀጠቀጠ ጥላት ፈራ ዕጹብ ያንተ ስራ መስክሩለት የምስራች ነው ታላቅ ዜና መላዕክቱ ነጭ ለብሰዋል ድል ነውና ከተማዋ አንዳች ሁናለች በሌሊቱ በዝማሬ ተንቀጠቀጠ ወኅኒ ቤቱ ከበረውን ምቱ ━━━━━━━━━━━━ አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል። 1ኛ ቆሮ 15፥20 ━━━━━━━━━━━━ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇 •➢ ሼር // SHARE ✧┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✧ •✥•🍁 @Z_TEWODROS 🍁•✥• @Z_TEWODROS •✥•🍁 @Z_TEWODROS 🍁•✥• ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
Show all...
እንቋዕ አብጽሐክሙ ለእግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ በሰላም በፍቅር ወበጥዒና። ሠናይ በዓል ይኩን ለኲልክሙ ሕዝበ ክርስቲያን!
BAGA AYYAANA DU'AA KA'UU GOOFTAA KENYAA IYAASUS KIRISTOOSIN NAGAAN ISINIIN GAHE
"ኢሀሎ ፡ ዝየ ፡ ተንሥአ ፡ በከመ ፡ ይቤ ፤ እንደተናገረ ተነስቷልና በዚህ የለም" ''AKKA JEDHEETI KA'EERA ASI HIN JIRU'' ማቴ ፳፰ ፥ ፮ "እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም በፍቅርና በጤና አደረሳችሁ።" ✝️ ለሁሉም የክርስቲያን ሕዝብ መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁን ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE         ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇         •➢ ሼር // SHARE ╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮           @dnzema           @dnzema           @dnzema ╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯
Show all...
መንፈሳዊ ትምህርት | eotc theology

Eotc theology... ዘውትር ከሰኞ - አርብ በመርሐግብሩ #ተከታታይ ትምህርት በፅሁፍ #live ትምህርት #መዝሙር #ወቅታዊ ጉዳዮችን እንዳስሳለን

1