cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች

ይህ ቻናል በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ፈቃድ ትምህርቶች የሚለቀቁበት ነው:: @deaconhenokhaile "ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን" 2ኛ ቆሮ. 2:14

Show more
Advertising posts
64 568Subscribers
-1524 hours
-367 days
-27730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ቅትለተ መነኮሳት ከዝቋላ ወደ ደቡብ አፍሪቃ አባ ተክለ ሃይማኖት (አባ ተክላ) ደቡብ አፍሪቃ ገጠር ውስጥ የሚያገለግሉ መነኩሴ ነበሩ:: ወላጆቻቸው ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ምልጃቸውን በመማጸን ተስለው ስለወለዱአቸው ስማቸውን በጻድቁ ስም ሰይመዋቸዋል:: ከባለጸጋ ቤተሰብ የተወለዱትና የሚተዳደሩበት የራሳቸው መርከብ የነበራቸው እኚህ ወጣት የእንጦንስ የመቃርስን መንገድ ተከትለው ሀብታቸውን ሸጠው ለድኆች ሠጥተው የቀረውን ለገዳም አውርሰው መነኮሱ:: ከዓመታት በፊት በገዳማቸው ተገኝቼ በረከት በተቀበልሁበት ወቅት እንዴት እንደመነኮሱ ፣ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ያላቸውን ፍቅርና አንዳንድ ነገሮችን አጫውተውኝ ነበር:: ለእኔም ያሳዩት ስስትና ፍቅር ከሕሊናዬ የማይጠፋ ነው:: ዛሬ በግፍ ሰማዕትነትን እንደተቀበሉ ቢቢሲ ዘግቦ አየሁ:: ሰይጣን የእውነተኛይቱን ቤተ ክርስቲያን አድራሻ መቼም አይሳሳትም:: በግብፃዊው ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስም በተሰየመ ገዳም የመነኮሱ ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት በሆኑ በሳምንቱ በኢትዮጵያዊው ጻድቅ ተክለ ሃይማኖት ስም የተሰየሙ መነኩሴ ከወንድሞቻቸው ጋር ሰማዕትነት ተቀበሉ:: ሰይጣን ከሃይማኖታችን እንጂ ከዘራችን ጠብ የለውም:: ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ እስመ በጸሎተ ጻድቅ ትድኅን ሀገር “በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ" ማቴ. 24:9 https://www.facebook.com/share/U25yhRDtJaBojkjB/?mibextid=WC7FNe
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

ምንኩስና የተጀመረው እንዴት ነበር? ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ መነሻዎቹ ባሻገር የምንኩስናን ታሪክ ስናጠና በ4ኛው ክፍለ ዘመን እንደተጀመረ ይታወቃል:: ለሦስት መቶ ዓመታት በአሰቃቂው ዘመነ ሰማዕታት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መከራ ስትቀበል ክርስቲያኖችም በየቀኑ ሲገደሉ የነበረበት ዘመን ድንገት አበቃ:: በደማቸው ለመጠመቅና በሞታቸው ክብር ለመቀዳጀት የተዘጋጁ ምእመናንን ድንገት "በቃ ከእንግዲህ አትሞቱም" የሚል አዋጅ ታወጀባቸው:: ዕረፍት አገኘን ብለው የተደሰቱ እንደነበሩ ሁሉ ለሰማዕትነት ቆርጠው ለክብር አክሊል ተዘጋጅተው የነበሩ ብዙዎች ግን ድንገት ሰማዕትነት ሲቆም አዘኑ:: ከሰማዕትነት ክብር ወርደው እንደማንኛውም ሰው መኖር ከበዳቸው:: ስለዚህም በሰይፍ ባይሞቱም በፈቃዳቸው ሞተው ለክርስቶስ ሕያው ሆነው ሊኖሩ ወደ ገዳማዊ ሕይወት ወደ ምንኩስና ጎረፉ:: ይህም ክስተት ለምንኩስናና ለገዳማዊ ሕይወት ምክንያት ሆነ:: ዝቋላን በመሳሰሉ ገዳማት የሚገኙ መነኮሳት በሥጋ የሚሞቱበት ቀን ሳይደርስ በክርስቶስ ፍቅር በፈቃዳቸው የሞቱ ሐዋርያው እንዳለው "ሥጋን ከክፉ ምኞቱና መሻቱ ጋር የሰቀሉት" ናቸው:: ሰማዕትነትም ቀድመው የተመኙት ክብር ነበር:: በእነርሱ መገደል የሞትነው በእነርሱ ጸሎት ብርሃንነት የምንኖር ፣ ስንጨነቅ ከእግራቸው ሥር የምናለቅስ ፣ በዓለም ማዕበል ስንላተም በመስቀላቸው መልሕቅ ወደ ጸጥታ ወደብ የምንደርስ እኛው ነን:: ባለቆቡ ሰማዕት አባቴ ሆይ እርስዎን የገደሉ የገደሉት የእኔን ተስፋ ነው:: ሰማዕቱ መነኩሴ ሆይ በእርስዎ ሞት የተቀደደው የዕንባዬ መሐረብ ነው:: አንጀታችን በኀዘን እርር የሚለው ለእናንተ ሳይሆን ለራሳችን ነው:: ከእናንተ ጸሎት በቀር ምርኩዝ የሌለን እኛ ይለቀስልን እንጂ ለእናንተ አናለቅስም:: ቀድማችሁ የጠላችኋት ዓለም ብትጠላችሁ አይገርምም:: በፍቅርዋ ለተሸነፍን ለእኛ ግን ዕንባ ያስፈልገናል:: እውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን የትኛዋ እንደሆነች ፣ ዘመነ ሰማዕታትን የምትደግመዋ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ማን እንደሆነች በደማችሁ ያሳያችሁ ምስክሮች ሆይ ለእኛ እንጂ ለእናንተ አናለቅስም:: የእኛን እግር ከማጠብ ፣ የእኛን ብሶት ከመስማት ፣ የእኛን የክርስትና ስም ዘወትር በጸሎት ከመጥራት ፣ እኛን ተቀብሎ ከማስተናገድ አረፍ ብላችሁ ከመነኮሳችሁለት አምላክ ዕቅፍ ስለገባችሁ አናዝንም:: የምናዝነው በተራራ ላይ ያለ መብራታችን ለጠፋብን ለእኛ ነው:: የእኛ ደብረ ታቦር ዝቋላ ሥሉስ ቅዱስ በደመና ይጋርድሽ እንጂ ምን እንላለን? ገዳምንና ገዳማውያንን መንካት የንቡን ቀፎ ማፍረስ ነው:: ቤተ ክርስቲያን ከቅዱስ ሲኖዶስ እስከ ዐቃቢት ያሉት ሁሉ በገዳም ቀፎነት የተሠሩ የማር እንጀራዎች ናቸው:: ማሩን የሚጋግሩት ንቦች ያሉት ከቀፎው ገዳም ውስጥ ነው:: የአቡየ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የቆብ ልጆች በአስኬማ ላይ የሰማዕትነት አክሊል የደረባችሁ ቅዱሳን መነኮሳት ጸልዩልን በዙፋኑ ፊት ቆማችሁ "ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?" ብላችሁ ስለ እኛ አማልዱ:: (ራእ. 6:10)
Show all...
"ይህችን ዓመት ተወኝ!" ከዓመት እስከ ዓመት - ፍሬን ሳላፈራ - ደረቅ እንደሆንኩኝ በራድ ወይም ትኩስ - ሁለቱንም ሳልሆን - እንዲያው ለብ እንዳልኩኝ አለሁኝ በቤትህ - ለሙን መሬትህን - እያጎሳቆልኩኝ አውቃለሁ አምላኬ - ፍሬዬን ለመልቀም - እንዳመላለስኩህ ዛሬም ሳላፈራ - እሾህን አብቅዬ - ደርቄ ጠበቅሁህ ያልተደረገልኝ - ያላፈሰሰክብኝ - ያልሰጠኸኝ የለም ነገር ግን ይህ ሁሉ - አላርምህ አለኝ - አልለየኝም ከዓለም የማትሰለቸኝ ሆይ - ተነሥቼ እስክቆም - እባክህ ታገሠኝ የእኔን ክፋት ተወው - መልአክህን ሰምተህ - ይህችን ዓመት ተወኝ! አውቃለሁ ታውቃለህ - ቀጠሮን ሰጥቼ - እንደማላከብር ብዙ ጊዜ አቅጄ - ብዙ ጊዜ ዝቼ - በወሬ እንደምቀር ‹ዘንድሮስ…!› እንዳልኩኝ - አምና ይሄን ጊዜ - ሰምተኸኝ ነበረ ምንም ሳልለወጥ - ‹ዘንድሮዬ› አልፎ - በአዲስ ተቀየረ ፍሬ የማይወጣኝ - እኔን በመኮትኮት - እጆችህ ደከሙ እኔ ግን አለሁኝ - ዛሬም አልበቃኝም - በኃጢአት መታመሙ የቃልህን ውኃ - በድንጋይ ልጅህ ላይ - ሳትታክት ስታፈስስ - ዘመን ተቆጠረ ወደ ልቤ ሳይሰርግ - ሕይወቴን ሳይለውጥ - እንዲያው ፈስሶ ቀረ ቃልህን ጠግቤ - እያገሳሁት ነው - ሌሎች እስኪሰሙ በቃልህ መኖር ግን - አልያዝህ አለኝ - ከበደኝ ቀለሙ ብዙ ጥቅስ አገኘሁ - ከቅዱስ መጽሐፍህ - ገልጬ አይቼ ከራሴ ላይ ብቻ - አንድ ጥቅስ አጣሁኝ - በበደል ተኝቼ ውጤቴ ደካማ - ትምህርት የማይሠርጸኝ - ተማሪ ብሆንም ይህችን ዓመት ተወኝ - ደግሞ ትንሽ ልማር - ታገሠኝ አሁንም! እባክህ አልቆረጥ - በቅዱስ መሬትህ - ልቆይ ፍቀድልኝ ያፈሩት ቅዱሳን - የፍሬያቸው ሽታ - መዓዛ እንዲደርሰኝ የተሸከምከኝ ሆይ - ዛሬም ተሸከመኝ - አትሰልቸኝ አደራ ማን ይታገሠኛል - ጠላት እየሆንኩት - አይሠሩ ስሠራ! አታውጣኝ ከቤትህ - ብዙ ቦታ አልይዝም - ፍሬ ስለሌለኝ ስፍራ የማያሻኝ - ቤት የማላጣብብ - ፍሬ አልባ በለስ ነኝ! ቦታስ የሚይዙት - ባለ ምግባሮቹ - ቅዱሳንህ ናቸው ልክ እንደ ዘንባባ - የተንዠረገገ - ተጋድሎ ጽድቃቸው! ከሊባኖስ ዝግባ - እጅጉን የበዛ - ገድል ትሩፋታቸው! እኔ አይደለሁም - ቦታስ የምትይዘው - የአንተው እናት ናት ሥሮቿ በምድር - ጫፎቿ በሰማይ - ሲደርሱ ያየናት ይሀችን ዓመት ተወኝ - ከሥርዋ እሆናለሁ - ባፈራ ምናልባት!.. ይህችን ዓመት ተወኝ - እባክህ አምላኬ - አንድ ዓመት ምንህ ናት ሺህ ዓመት አንድ ቀን - አይደለም ወይ ለአንተ - ዓመት ኢምንት ናት! ይሄ ዓመት አልፎ - ዳግም ‹ዓመት ሥጠኝ› - እስከምልህ ድረስ እባክህን ጌታ - ይህችን ዓመት ተወኝ - የወጉን እንዳደርስ! ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ---
Show all...
+ ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል + ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶአል:: ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጠይቀው መጣ:: ሆኖም እንደ ልማዱ እግዚአብሔር ይማርህ አላለውም:: ለጆሮ የሚከብድ ቃል ጥሎበት ወጣ:: "ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!" ነቢዩ ይህንን ብሎት ከወጣ በኁላ ሕዝቅያስ ወደ ግድግዳው ዞሮ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ:: አምላኩ በንግግር ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለምና ፊቱን ወደ መቅደሱ አቅጣጫ አዙሮ አለቀሰ:: ከጥቂት ደቂቃ በኁዋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ሌላ መልእክት ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :- ጸሎትህን ሰምቻለሁ ዕንባህን አይቻለሁ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ" (ኢሳ 38:5) ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም:: ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው? ለባሪያዎችህ መመሪያ ሳትሠጥ የምታስተካክለው ቤትስ እንዴት ያለ ነው? በደቂቃዎች ውስጥ ትሞታለህ ከተባልክ በኁዋላ ዐሥራ አምስት ዓመት ያስጨመረልህ ምን ዓይነት ማስተካከያ አድርገህ ነው? ለእኛም ንገረንና ዕድሜ እናስጨምር:: ሕዝቅያስ ከአልጋው ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ ልቡ ነበር:: ልብህን ካስተካከልህ ቤትህ ይስተካከላል:: እግዚአብሔር እንደሆን ትሞታለህ ቢልህም መሞትህን አይፈልግም:: እርሱ ካንተ ጋር ጸብ የለውም:: "በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን?" ይላል መሐሪው (ሕዝ 18:23) እርሱ ትሞታለህ የሚልህ መኖርህን ፈልጎ ነው:: አንዴ ብያለሁ ብሎ አይጨክንብህም:: በንስሓ ተመለስ እንጂ ምሬሃለሁ ለማለት ይቸኩላል:: አሁን ትሞታለህ ብዬው አሁን ትድናለህ ብለው ይንቀኛል ሳይል ተመልሶ ይምርሃል:: ኃጢአትህንም ወደ ጥልቁ ይጥለዋል:: በጎ እንድትሠራም ዕድሜ ይጨምርልሃል:: አንተ ብቻ ተመለስና አሁኑኑ ንስሓ ግባ:: ከበደል አልጋ ጋር ያጣበቀህን ፈተናም ድል መንሻው ጊዜ አሁን ነው:: ሕዝቅያስ በደቂቃ ዕንባ ምሕረት አግኝቶ ዕድሜ ካስጨመረ በዐቢይ ጾም ሙሉ የሚያለቅስ ምን ያህል ዕድሜ ያገኝ ይሆን? ወዳጄ አንተም ተነሣና በዚህ ወር ቤትህን አስተካክል:: እንደ ሕዝቅያስ ፈጣሪህ ይጠብቅሃል:: የተቀየምከውን ይቅር በል የበደልከውን ካስ የሚበቀልህን የማይተኛ ጠላትህን ዲያቢሎስ ተበቀለው:: የዐቢይ ጾም የወንጌል ምንባብ ስለ ዲያቢሎስ ፈተና ሦስቱ ወንጌላት የተናገሩትን ስናስተውል ሦስት ዓይነት ጥቅሶች እናገኛለን:: አርባ ቀን ከዲያብሎስ ተፈተነ። (ሉቃ 4:2) በምድረ በዳም ከሰይጣን እየተፈተነ አርባ ቀን ሰነበተ (ማር 1:13) የሚሉት ቃላት ጌታችን ዐርባውንም ቀን መፈተኑን ያሳያሉ:: አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ። ፈታኝም ቀርቦ እንዲህ አለው (ማቴ 4:2) የሚለው ደግሞ ከጾሙ በኁዋላ የቀረቡለትን ሦስት ፈተናዎች የሚያሳይ ነው:: ሦስተኛው ጥቅስ ደግሞ ከተፈተነ በኁዋላ ያለው ሲሆን ዲያቢሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ እስከ ጊዜው ከእርሱ ተለየ። (ሉቃ 4:13) ይላል:: ዲያቢሎስ ፈተናውን ቢጨርስም የሚተወው ለጊዜው እንጂ መፈተኑን አያቆምም:: የዲያቢሎስ ፈተና ስልቱ ይቀያየራል እንጂ ይቀጥላል:: ዐቢይ ጾም ዲያቢሎስ ድል የተደረገበት የጦር ዐውድማ ነው:: በዚህ ወራት ድል ያላደረግነውን ፈተና በሌላ ጊዜ አናደርገውም:: ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል እንደሚባለው በዐቢይ ጾም የተኛ ክርስቲያን መቼም አይነቃም:: ከነስሙ ሁዳዴ (ሰፊ እርሻዬ) የምንለው ይህ ጾም ለነፍሳችን ብዙ ዘር የምንዘራበት አጋንንት መድረሻ የሚያጡበት ጾም ነው:: በዐቢይ ጾም ያልተገራ አንደበት መቼም አይገራም:: በዐቢይ ጾም ያልተፈወሰ ቂም መቼም አይፈወስም:: ጌታችን በወንጌል አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥል ጋኔን ያለበትን ልጅ ሲፈውስ "ይህ ዓይነቱ ጋኔን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም" ብሎ ነበር:: ሀገራችንን አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥላት የጥላቻ ጋኔንም ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም:: ወዳጄ ከቁስልህ የምትፈወስበት ወር እንደደረሰ ዕወቅ:: አንተስ ብትሆን ልትላቀቀው እየፈለግህ ያቃተህ ክፉ ልማድ የለብህም:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "የምፈልገውን መልካም ነገር አላደርግም የማልፈልገውን ክፉ ነገር ግን አደርጋለሁ:: ምንኛ ጎስቋላ ለዚህ ለሞት ከተሠጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?" ብለህ ምርር እንድትል ያደረገህ ኃጢአት የለም? እንግዲያውስ እወቀው:: ይህ ዓይነቱ ወገን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም:: ይህ ጾም ቁስል የሚሽርበት ጾም ነው:: ይህ ጾም ሸክም ማራገፊያ ጾም ነው:: እንደ ሕዝቅያስ በዚህ ወር ቤትህን በንስሓ አስተካክል:: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የካቲት 15 2012 ዓ ም ዝዋይ ኢትዮጵያ
Show all...
+ ከሁሉ በኋላ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ታየኝ + ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ምእመናን ስለ ጌታ ትንሣኤ ማስረጃ እያቀረበ ነው:: በዚያን ዘመን ለጌታ ትንሣኤ ማስረጃ ስትጠቅስ በማቴዎስ ወንጌል እንዲህ ይላል ብለህ እንዳትጠቅስ ገና ወንጌላት አልተጻፉም:: ቢጻፉም ማቴዎስ በሕይወት እያለ በቃሉ መመስከር ሲችል ጽሑፉን ማስረጃ ማድረግ አያስፈልግህም:: ስለዚህ ለመነሣቱ ማስረጃዎች ከተነሣ በኋላ ያዩት ሰዎች ነበሩ:: በሕይወት ያሉትን የዓይን ምስክሮችን መጥቀስ ይቻላል:: የዓይን እማኞች ምስክርነት ከጽሑፍ በላይ የታሪክ ማስረጃ ነው:: ስለዚህ ጳውሎስ ስለ ጌታ ትንሣኤ "እነ እገሌ አይተውታል" እያለ መዘርዘርን መረጠ:: ጌታ ከተነሣ በኋላ እንደ ቀድሞው ለሁሉ አልታየም:: እርሱን ለማየት የተገባቸው ጥቂት ወደ ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ነበሩ:: በማኅበር ያዩት አሉ:: በግል ያዩት አሉ:: ያዩት ነገር ወንጌል የሆነላቸው ብፁዓን ዓይኖች ያሏቸው እንዴት የታደሉ ናቸው? የተሰቀለውን ተነሥቶ ያዩት! ዳግም በሚመጣበት አካል የተገለጠላቸው ምንኛ የታደሉ ናቸው? ከመድኃኔ ዓለም አፍ ተቀብለው ኪዳን ያደረሱ! የጌታን ቅዳሴ ተቀብለው ያስቀደሱ! የትንሣኤው ማግስት ምስክሮች እንዴት ዕድለኞች ናቸው? ቢሞቱም እንኳን መነሣታቸውን በጌታ ትንሣኤ አይተው ደስ ብሎአቸው ያንቀላፉ እነርሱ ምንኛ የታደሉ ናቸው? ቅዱስ ጳውሎስ በወንጌል ከተጠቀሱት ከነ ኬፋ በተጨማሪ ለይቶ ጌታ ለማን ለማን እንደታየ ገለጸ:: ለያዕቆብ ታየ ብሎ የእልፍዮስን ልጅ ለይቶ ጠቀሰው:: የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፍት እንደሚሉት ይህ ሐዋርያ ከሌሎች በተለየ የጌታን ትንሣኤ ሳላይ እህል አልቀምስም ብሎ የተሳለና አክፍሎትን የጀመረ ነበርና ጌታ ለይቶ ክብሩን አሳይቶታል:: ከዚያም ለዐሥራ ሁለቱ ታየ ብሎ የጌታን ድኅረ ትንሣኤ አስተርእዮ ዘረዘረ:: እኔ ማለትን የማይወደው ትሑት ቅዱስ ጳውሎስ "ከሁሉ በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ አለ:: ጭንጋፍ ምንድር ነው? ጭንጋፍ (ጸዕጻዕ/ ተውራድ) ለፅንስ የሚነገር ቃል ነው:: መወለድ ያለበትን ጊዜ ያልጠበቀ ያለ ጊዜው የተወለደ ፅንስ ነው:: በመጠኑ ከሌላው ጊዜውን ከጠበቀ ፅንስ የሚያንስ ሲሆን ዕድገቱን በተገቢው ጊዜ ከሚወለድ ልጅ ጋር ለማስተካከል ሲባል በሙቀት ማቆያ ክፍል እንዲቆይ ይደረጋል:: ይህ ፅንስ ሲወለድ በሕመም ውስጥ ሆኖ ተሰቃይቶ ተጨንቆ ነው:: ቅዱስ ጳውሎስ ራሱን ለመግለጽ የተጠቀመበት ይህ አንድ ቃል የሕይወት ታሪኩን ጠቅልሎ የያዘ ድንቅ ቃል ነበር:: ቅዱስ ጳውሎስ ምንም እንኳን የቤተ ክርስቲያን ብርሃን የሆነ ሐዋርያ ቢሆንም እንደ ዓሥራ ሁለቱ ሐዋርያት በጊዜው የተጠራ አልነበረም:: እርሱ ከሐዋርያት ጋር አብሮ በዳግም ልደት የተወለደ ሳይሆን ያለ ጊዜው ክርስቶስ ባረገ በስምንተኛው ዓመት የተጠራ ነበረና ራሱን ካለ ጊዜው ከተወለደው ፅንስ ጋር አመሳስሎ እንደ ጭንጋፍ የምሆን ብሎ ጠራ:: ጭንጋፍ ሲወለድ በመጠኑ ከሌላው ፅንስ ያነሰ ይሆናል:: ቅዱስ ጳውሎስም ራሱን ጭንጋፍ ካለ በኋላ "እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ስላሳደድሁ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ" ብሎ አብራርቶታል:: (1ቆሮ 15:9) ልጅ ጭንጋፍ ሆኖ ሲወለድ በሥቃይ ነው:: ጤና ያጣል ይታመማል:: እናቲቱም ትታወካለች በድብታ በጭንቀት ትቸገራለች:: ባለሙያዎቹ እንደሚሉት እናት ያለ ጊዜው ከተወለደ ልጅዋ ጋር እናታዊ ትስስር ለመፍጠርና የእናትነት ፍቅርዋን ለመሥጠት ባልጠበቀችው ጊዜ የመጣ በመሆኑ ምክንያት ለጥቂት ጊዜ ትቸገራለች:: በአጭሩ ጭንጋፍ ሆኖ ሲወለድ እሱም ይሰቃያል እናቱንም ያስጨንቃል:: ወዲያው እንደሌላ ሕፃን በሰው እጅ አይታቀፍም:: ከተፈጥሮአዊ እስከ ሰው ሠራሽ እንደየጊዜው እየዘመነ በሔደው የልጅ ሙቀት መስጫ መንገድ እየታገዘ የሰውነት አካሎቹ በአግባቡ መሥራት እስከሚችሉና በሽታ መቋቋም እስከሚችል ይቆያል:: ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ጭንጋፍ ነበርኩ ያለው ለዚህ ነው:: በዳግም ልደት የተወለደው በደማስቆ መንገድ ወድቆ ሊቋቋመው ባልቻለው ብርሃን ተመትቶ ነበር:: "ሳውል ሳውል ስለምን ታሳድደኛለህ?" የሚል ድምፅ ሲሰማ ፅንስ ነውና ዓይኑን እንኳን መግለጥ አልቻለም ነበር:: ከተወለደ በኋላም ወዲያው ወደ ቤተ ክርስቲያን እቅፍ ወደ ሐዋርያት ማኅበር አልገባም:: እንደ ጭንጋፍ የምሆን እንዳለ ሙቀት ያስፈልገው ነበርና የሰው እጅ ሳያቅፈው ሦስት ዓመት በሱባኤ ቆይቶ በመንፈስ ቅዱስ ተማወቀ:: "ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፥ ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም፥ ከእኔም በፊት ሐዋርያት ወደ ነበሩት ወደ ኢየሩሳሌም አልወጣሁም፥ ነገር ግን ወደ ዓረብ አገር ሄድሁ እንደ ገናም ወደ ደማስቆ ተመለስሁ። ከሦስት ዓመት በኁዋላ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣሁ" ብሎ ስለ መንፈሳዊ ኃይል መልበሱ ይናገራል:: (ገላ 1:15-18) ጭንጋፍ ሆኖ የተወለደ ልጅ የሚገጥመው ችግር ከወላጆቹ ጋር በሥነ ልቡና ለመተሳሰር መቸገሩ ነው:: ቅዱስ ጳውሎስን ለማመንና እንደ ልጅ ለመቀበል የቤተ ክርስቲያን ማኅበርም ተቸግራ ነበር:: "ሳውልም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከደቀ መዛሙርት ጋር ይተባበር ዘንድ ሞከረ፤ ሁሉም ደቀ መዝሙር እንደ ሆነ ስላላመኑ ፈሩት" ሐዋ 9:26 ስለዚህ ሐዋርያው እንደ ጭንጋፍ ነኝ አለ:: ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ጌታ መነሣት ምስክሮች ብሎ ሌሎችን ከዘረዘረ በኋላ "ከሁሉ በኋላ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ታየኝ" ብሎ ተናገረ:: ክርስቶስ ተነሥቶአል ወይ ብለው ሲጠይቁህ አዎ ተነሥቶአል እነ እገሌ አይተውታል ብለህ ዘርዝረህ "ከሁሉ በኁዋላ ለእኔም ታየኝ" ብለህ መናገር መቻል እንዴት መታደል ነው!? ወዳጄ ክርስቶስ መነሣቱን ታምናለህ:: ልክ ነህ ለብዙዎች ታይቶአል:: አንተስ ከሁሉ በኁዋላ ለእኔም ታየኝ ማለት ትችል ይሆን? ጌታ ከተነሣ በኁዋላ ላለፉት ሁለት ሺህ ዓመታት ለብዙዎች ታይቶአል:: ብዙዎቹ ቅዱሳን አይተውታል:: ቅዱስ እስጢፋኖስ አይቶታል : ቅድስት አርሴማ አይታዋለች : አቡነ ተክለ ሃይማኖት አይተውታል : አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ተመልክተውታል:: አባ ጳኩሚስ በዕንባ ተመልክቶታል : ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ አይታዋለች:: ሁሉም ቅዱሳን ብዕር ቢሠጣቸው ከዕንባ ጋር "ከሁሉ በኁዋላ ለእኔም ታየኝ" ብለው የትንሣኤውን ማስረጃ ዝርዝር ይቀጥላሉ:: ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በበረሃ ሲጸልይ አይቶት ነበርና ሰው ባገኘ ቁጥር ወቅቱ የፋሲካ ሰሞን ባይሆንም እንኳን በፈገግታ ተሞልቶ "ክርስቶስ ተነሥቶአል!" ብሎ ያበሥርና ሰላምታ ይሠጥ ነበር:: ጌታ ሆይ ለእኔ ለኃጢአተኛው የምትታየኝ መቼ ይሆን? ቸርነትህን አይቻለሁ! ፍቅርህን አይቻለሁ! ብሩሕ ገጽህን የማየው መቼ ይሆን? መች እደርሳለሁ የአምላኬንስ ፊት መቼ አየዋለሁ? እኔም እንደ ቅዱሳንህ "ከሁሉ በኁዋላ ለእኔ ታየኝ" ብዬ የተቀመጠውን ብዕር አንሥቼ የምጽፈው መቼ ይሆን? አቤቱ ፊትህን እሻለሁ! አቤቱ ፊትህን ከእኔ አትመልስ! አቤቱ ፊትህን እሻለሁ! "ኢየሱስ ክርስቶስ በግዕ ዘቀራንዮ ለላሕይከ ንትሜነይ ከመ ንርአዮ" "የቀራንዮው በግ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ውበትህን ልናየው እንመኛለን" ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
Show all...
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ FB: https://www.facebook.com/officialHenokhaile/ Telegram: https://t.me/deaconhenokhaile Instagram: https://www.instagram.com/p/CBnMF0nnhcQ/?igshid=549jvl607bv4 Youtube: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

Show all...
#New 🔴አንተ ሰው ነህ? ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ | እራሳችንን የምንፈትሽበት ድንቅ ስብከት | Kendil media - ቀንዲል ሚዲያ @Kendilmedia

Show all...
🛑ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ || ኢየሱስ የሚሉት አዲስ ንጉሥ@arganon #የአእላፋትዝማሬ @janderebaw_media

#እንኳንአደረስዎ #like #Share #Subscribe @arganon @janderebaw_media

https://youtube.com/@arganon

ይህንን ቻናል Subscribe በማድረግ አገልግሎቱን ይደግፉ።ለወዳጅዎም በማጋራት የእግዚአብሔር ቃል እንዲዳረስ የበኩልዎን ይወጡ። እግዚአብሔር ያክብርልን!! Any way of reproducing, reposting & reusing of this video is prohibited by ARGANON. ©አርጋኖን ሚድያ - Arganon Media -2016|2024

በከበረች ጸሎቱ ይቅር ይበለንና ራሱን በትሕትና "ከጌቶች ልጆች የሚወድቀውን ፍርፋሪ የሚለምን ውሻ" ብሎ የሚጠራው ሶርያዊው ኮከብ ቅዱስ ኤፍሬም በየድርሰቶቹ መካከል እንዲህ እንዲህ አለ:- "ጌታችን ከሣምራዊትዋ ሴት ጋር በተነጋገረ ጊዜ በንግግራቸው መጀመሪያ ማንነቱን አልገለጠላትም። መጀመሪያ ያየችው ውኃ የጠማውን ሰው ነበር ፣ ከዚያ አይሁዳዊ ፣ ከዚያ መምህር (ረቢ) ፣ ቀጥሎ ነቢይ ከሁሉም መጨረሻ መሲህ መሆኑን አየች። ውኃ የተጠማውን ሰው በንግግር ልትረታ ስትሞክር በአይሁዳዊ ላይ ያላትን ጥላቻ አሳየች። ከመምህሩ ጋርም ተከራከረች ፣ ከነቢዩ እግር ስር ተንበረከከች ፣ መሲሁንም ወደደችው" ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (ስለ ሣምራዊቷ ሴት ዮሐ 4:1) ★ ★ ★ "ጌታ ሆይ ለእኛ ፊት ክብርን የሠጠ እንደ አንተ ያለ ማን አለ? የዕውሩን ዓይን ባበራህለት ጊዜ ላድነው ነህ ብለህ በፊቱ ላይ አልተፋህበትም። ነገር ግን አርኣያችንን አክብረህ በመሬት ላይ እንትፍ ብለው ፈወስከው። ጌታዬ ሆይ በእኔ ላይ ግን በፊቴ ላይ እንትፍ በልብኝ ፣ በፈቃዴ ያጠፋሁትን ዓይኔን በፈቃድህ አብራልኝ" ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (ዕውር ሆኖ ስለተወለደው ዮሐ 9:30) ★ ★ ★ "ጌታ ሆይ ዕውሩን ሂድ ብለህ ወደላክህበት ወደ ሰሊሆም መጠመቂያ አሁን ልንሔድ አንችልም። ነገር ግን ሕይወትንና ብርሃንን የተሞላው የከበረ ደምህ ያለበት ጽዋ በእኛ ዘንድ አለ። ከእርሱ በተቀበልን ቁጥር እንነጻለን" ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ★ ★ ★ "ጌታዬ ሆይ በሔድኩበት ውጣውረድ የተሞላ መንገድ እምነቴ ደከመ ፣ መንገዱ የሚወስደኝም በግራ ወደሚቆሙት ፣ በደጅ ቆመው ክፈትልን ሲሉህ "አላውቃችሁም" ከምትላቸው ወገን ልሆን ነው። ጌታዬ ሆይ እኔ አውቅሃለሁ ፣ አንተ ግን አላውቅህም ትለኝ ይሆን? አቤቱ በአንተ ለማምን ለእኔ ለኃጢአተኛው ራራልኝ። ብበድልህም እንኳን አሁንም በርህን እያንኳኳሁ ነው። እየተጎተትኩም ቢሆን አሁንም የምጓዘው ወደ አንተ ለመምጣት ነው" ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (ማቴ 7:7) ★ ★ ★ "ጌታ ሆይ እነዚህን በዕድሜ ሕፃናት የሆኑ የመንፈስ ልጆቼን ይቅር በላቸው። ሕፃን የነበርከው ሆይ የሕፃንነትህን ጊዜ አስብ። ልጅነታቸው ያንተን ልጅነት እንዲመስል አድርግላቸውና በቸርነትህ አድናቸው" ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ከተለያዩ መዝሙራቱ (Hymns) በተርጓሚው ተለቃቅሞ የተሰበሰበ ኅዳር 26 2011 ዓ ም ክርስቲያን ሳንድ Deacon Henok Haile
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!