cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የትምህርት መረጃዎች

በትምህርት ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገ ገፅ

Show more
Advertising posts
249
Subscribers
+124 hours
No data7 days
+930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " ፈተናው በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል " - የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በአዲስ አበባ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ከተማ አቀፍ ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል፡፡ ከተማ አቀፍ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና ትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት በዚህ ዓመት በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልጿል። በዚህም በአዲስ አበባ ለ6ኛ ክፍል 86,691 ተማሪዎች እንዲሁም ለ8ኛ ክፍል 88,028 ተማሪዎች በከተማ አቀፍ ፈተናው ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አሳውቋል። #ኢዜአ @tikvahuniversity
Show all...
" ብሔራዊ መውጫ ፈተናውን ሁሉም በላቀ ውጤት አልፈዋል። ... 70% የማዕረግ ምሩቃን ናቸው " - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በነገው እለት የካቲት 9 ቀን 2016 ዓ/ም 249 #የህክምና_ዶክተሮችን እንደሚያስመርቅ አሳውቋል። ከነዚህ ተመራቂዎች መካከል 70 በመቶ የማዕረግ ምሩቃን ናቸው። የብሔራዊ የመውጫ ፈተናውን ደግሞ ሁሉም ተመራቂዎች (100%) በላቀ ውጤት አልፈዋል። ከዚህ በተጨማሪ ነገ 22 ተማሪዎች በአንስቴዥያ የህክምና ዘርፍ የሚመረቁ ይሆናል። ትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️ https://t.me/Tmhrt_Minister https://t.me/Tmhrt_Minister
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ዛሬ መግለጫ አውጥተዋል። መግለጫቸው ፤ በአውሮፓ ኅብረት እና በአፍሪካ፣ በካሪቢያንና በፓስፊክ ሀገራት መካከል የተፈረመውንና የሳሞአ ስምምነት በመባል የሚታወቀውን የንግድና የኢኮኖሚ አጋርነት ስምምነት የተመለከተ ነው። ጉባኤው ስምምነቱ ተካተውበታል ያላቸውን ጎጂ ሀሳቦች በዝርዝር አስፍሯል። ከነዚህም መካከል ፦ - በስምምነቱ አንቀፅ 36.2 ላይ የተጠቀሰው የወሲብና የተዋልዶ ጤናና መብቶች" ("Sexual and Reproductive Health and Rights") የሚለው ሐረግ በቀጥታ ፦ * #ከግብረሰዶም መብቶች፤ * ከፆታ መቀየር፤ * ከውርጃ፤ * ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርትና ግልሙትናን ሕጋዊ ከማድረግ በቀጥታ የተያያዘ መሆኑ በአውሮፓ ፓርላማና በዓለም የጤና ድርጅት የመረጃ ምንጮች ላይ በግልፅ መቀመጡ፤ - በስምምነቱ የአፍሪካ ፕሮቶኮል አንቀፅ 40.6 ላይ በአህጉሪቱ ለሚገኙ ልጆችና ታዳጊዎች ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት (Comprehensive Sexuality Education) የተባለ እጅግ አደገኛ ኢግብረገባዊና ልቅ የወሲብ ትምህርት እንዲማሩ አስገዳጅ መሆኑ ለዚህም በዩኔስኮ የተዘጋጀውና እጅግ አደገኛ ይዘት እንዳለው የተረጋገጠው መተግበርያ "International Technical Guidance on Sexuality Education” በስም ተጠቅሶ መቀመጡ፤ - የፆታ ትንኮሳን (gender based violence) ማስቀረት በሚል በጣም አሻሚ የሆነ ግብረሰዶማዊ አስተሳሰቦችን ለማስረፅ እንዲረዳው በሰነዱ በበርካታ ክፍሎች ውስጥ " አካታች " (inclusive) በሚሉ ቃላት ተሸፍኖ እንዲገባ የተደረገ መሆኑ፤ - በበርካታ ሥፍራዎች የተጠቀሰው "Gender" የሚለው ቃል ወንድና ሴት ተብሎ እንደሚተረጎም በስምምነቱ በግልጽ ባለመቀመጡ ይልቁንም በርካታ ጾታዎች እንዳሉ በማስመሰል ሀገራትን የሚያደናግሩባቸው እንደ (sexual orientation እና gender identity)ን የመሳስሉ ግብረሰዶማዊ አስተሳሰቦችን የያዙ ዶክመንቶች በስም ተጠቅሰው በስምምነቱ ውስጥ መካተታቸው፤ - ስምምነቱ የወላጆችን መብት የሚጥስና የኢትዮጵያዊ ቤተሰብ እሴቶችን አደጋ ላይ የሚጥሉ አንቀፆችን የያዘ ስለመሆኑ በሰነዱ ላይ ከተደረገ የኤክስፐርቶች ጥልቅ ጥናት ተረድተናል...  የሚሉት ይገኙበታል። ጉባኤው በነዚህ እና ሌሎች ጎጂ ምክንያቶች ፦ ➡ መንግስት የሳሞአ የንግድና የኢኮኖሚ የአጋርነት ስምምነትን በርካታ ጎጂ ጎኖች እንዳሉት በማመን ከዚህ ስምምነት #ኢትዮጵያ ራሷን እንድታገልል በማድረግ መንግስታዊ ኃላፊነቱንና አደራውን በተግባር እንዲወጣ በአጽንኦት ጠይቋል። ➡ የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና በሥሩ ያሉ የሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች የስምምነት ሰነዱ ውስጥ በዝርዝር የቀረቡትን በተለይም ፦ ° ከሰብኣዊ መብቶች፣ ° ከወሲባዊና የተዋልዶ ጤናና መብቶች፣ ° ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት፤ ° አካታችነት እና መሰል በሰነዱ የተካተቱ አንቀጾች ወይም ይዘቶች ከግብረሰዶማዊነትና ጾታን ከመቀየር እንዲሁም ከልቅ ወሲብና ከውርጃ ጋራ በቀጥታ ተያያዥነት ያላቸው ጽንስ ሃሳቦች መሆናቸውን በመረዳት ይህንን እጅግ አደገኛ ስምምነት ባለማጽደቅ ህዝባዊና ታሪካዊ አደራውን እንዲወጣ በአጽንኦት ጠይቋል። (ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል) ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ስለ " ሳሞአ ስምምነት " ያዘጋጀው ሰፊ እና ዝርዝር ዘገባ በዚህ ይገኛል ፦ https://t.me/tikvahethiopia/84172 @tikvahethiopia
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
20 ሚሊዮን የሁለተኛ ደረጃ የመማሪያ መጻሕፍት ከሁለት ወራት በኋላ ለስርጭት ይደርሳሉ፡፡ - የትምህርት ሚኒስትሩ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አንድ መጻሕህፍ ለሁለት ተማሪ በሚል የዘንድሮ ዕቅድ ለማሳተም 40 ሚሊዮን ዶላር ወጪ መደረጉን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡ መጻሕፍቱን ለማሳተም አገራዊ አቅም ባለመኖሩ ምክንያት ከተለያዩ ፕሮጀክቶች ድጋፍ በመጠየቅ የህትምት ሥራው እንደተከናወነ ገልፀዋል፡፡ ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር በመነጋገር በኢትዮጵያ በህትመት ዘርፍ ለመሰማራት መስማማቱንም የገለፁት ሚኒስትሩ፤ ድርጅቱ በቀጣይ ዓመት በኢትዮጵያ ሥራ ይጀምራል ብለዋል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን https://t.me/Tmhrt_Minister https://t.me/Tmhrt_Minister
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" ወይ የሆነ መፍትሄ ተወስዶ እንዲቆዩ አልተደረጉ ፤ ከሄዱ ደግሞ በስነሥርዓት እንዲሸኙ ማድርግ ይገባ ነበር " - ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ዶክተር (በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሌክቸረር) በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፤ ትላንት ምሽት 2:45 ሰዓት ገደማ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው እንደነበር አንድ በተቋሙ ውስጥ በመምህርነት የሚሰራና ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ዶክተር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል። " ከሰሞኑን በዩኒቨርሲቲው ጥሪ ተማሪዎች ገብተው ነበር " ያለው ይኸው ዶክተር ፤ ትላንት ምሽት በተማሪዎች ዶርም አካባቢ ታጣቂዎች ገብተው ከባድ ተኩስ ከፍተው ነበር ብሏል። " የተማሪዎች ዶርም አካባቢ ነው ከባድ ተኩስ እና ፍንዳታ የነበረው ፤ እኔ በወቅቱ ለሪሰርች ስራ ላይብረሪ ነበርኩ ፤ ተኩሱና ፍንዳታው የተሰማበት ትክክለኛ ሰዓት ደግሞ ምሽት 2:45 ላይ ነው " ሲል ገልጿል። " በኃላ ላይ ስንጠይቅ ታጣቂዎቹ ተማሪዎቹን ' እኛ እናተን ልንጎዳ አይደለም ግን ከነገ ጀምሮ ግቢውን ለቃችሁ እንድትወጡ ስለምንፈልግ ነው ' ብለዋቸዋል " ያለው ዶክተሩ ፤ " የነበረው ተኩስ ከ10 ደቂቃ በኃላ ከቆመ በኃላ እኛም ከላይብረሪ ወጥተን ወደየቤታችን ገባን " በማለት የትላንት ምሽቱን ሁኔታ አስረድቷል። " ዛሬ ከጥዋት ጀምሮ ተማሪዎች ሲሄዱ ነበር ፤ ይሄን መረጃ ለእናተ በምሰጥበት ወቅት (ከሰዓት ላይ) ብዙ ተማሪ ሻንጣውን ጭኖ ፣ እየጎተተ እየወጣ ነው " ሲል የገለፀው ዶክተሩ ፤ " እኔ እንዳየሁት አስተዳደር አካባቢ ያሉ ሰዎችም አላነጋገሯቸውም ፤ ተማሪዎቹ ሰብሰብ ብለው ነው በራሳቸው ሲሄዱ የነበሩት፤ ከስንት ጊዜ በኃላ እድሜያቸው እንዳይሄድ ብለው ለመማር የመጡ ተማሪዎች ወይ የሆነ መፍትሄ ተወስዶ እንዲቆዩ አልተደረጉ ፤ ከሄዱ ደግሞ በስነሥርዓት እንዲሸኙ ማደርግ ይገባ ነበር " ብሏል። " ተማሪዎች በዚህ መንገድ ከግቢ መውጣታቸው በጣም ስላሳሰበኝ ነው ይሄን ለናተ የምናገረው ፤ ትላንት ማታ ላይብረሪ ውስጥ የነበሩበት ሁኔታ አሳዛኝ ነበር ፣ ሲያልቅሱ ነበር ፤ አንዳንዶቹ ድምፅም ሰምተው የሚያውቁ አይደሉም ብቻ ያሳዝናል " ሲል ገልጿል። በህክምና ኮሌጁ ሌክቸረር የሆኑት እኚህ ዶክተር ፤ " ለተማሪዎች ስነልቦና የሚያነጋግራቸው አካል ሊኖር ይገባ ነበር ፣ ተረጋጉ የሚላቸው አካልም መኖር ነበረበት ፤ ከጥዋት ጀምሮ ይሄን መረጅ እስከሰጠሁበት ሰዓት ያነጋገራቸው አካል የለም ፤ የግቢ ጥበቃዎችም መሳሪያ ተነጥቀናል ምንም ማድረግ አልቻልንም ነው የሚሉት ፤ ብቻ ተማሪዎቹ መፍትሄ ቢፈልጋላቸው " ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዩኒቨርሲቲው በኩል ስለጉዳዩ ምን አይነት ምላሽ እንዳለ ለማወቅ ጥረት አድርጓል፤ ነገ ጥዋት ይቀርባል። @tikvahethiopia
Show all...
Repost from Tikvah-University
Photo unavailableShow in Telegram
#MondayMotivation ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የኮግኒቲቭ ሳይንቲስት አበባ ብርሃን (ዶ/ር) በቅርቡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰው ሰራሽ አሰተውሎት አማካሪ ሆና ተመርጣለች። አየርላንድ በሚገኘው የትሪኒቲ ኮሌጅ የኮምፒውተር ሳይንስ እና ስታስቲክስ ትምህርት ክፍል መምህር እና ረዳት ፕሮፌሰር የሆነችው አበባ ብርሃን (ዶ/ር)፤ የሞዚላ ፋውንዴሽን ከፍተኛ አማካሪ በመሆን እያገለገለች ትገኛለች፡፡ ሳይንቲስቷ የቋንቋ፣ ሥነ-ልቦና፣ ፍልስፍና፣ ኮምፒውተር ሳይንስ፣ ሥነ-ሰብ እና ሰው ሠራሽ አስተውሎትን አጣምሮ የሚይዘው የኮግኒትቭ ሳይንስ ምሁር ብትሆንም በርካታ ምርምሮቿ በሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI) ላይ ትኩረት የደረጉ ናቸው፡፡ አበባ ብርሃን (ዶ/ር) ባለፈው መስከረም የታይም መፅሔት የ2023 100 ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ዝርዝር ውስጥ መካተቷ ይታወሳል፡፡ ረዳት ፕ/ር አበባ ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪዋን በፊዚክስ ያገኘች ሲሆን፤ በሳይኮሎጂ እና በፍልስፍና የትምህርት ዘርፍ ሁለት የመጀመሪያ ዲግሪዎችን ከኦፕን ዩኒቨርሲቲ አግኝታለች። ሁለተኛ እና ሦስተኛ ዲግሪዋን በአየርላንድ በኮግኒቲቭ ሳይንስ ተከታትላለች። በትውልድ ሀገሯ ኢትዮጵያ በሙያዋ አስተዋፅኦ የማበርከት ዕቅድ እንዳላት የምትገልፀው ሳይንቲስቷ፤ ለዚህም ከአዲስ አበባ እና ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ጋር አብራ መስራት መጀመሯን የዶቸቬለ ዘገባ ያሳያል። @tikvahuniversity
Show all...
የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መሠረት ያደረገ የአሠልጣኞች ምዘና መስጠት ጀመረ፡፡ (ጥር 27/2016 ዓ.ም) የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መሠረት ያደረገ የአሠልጣኞች ምዘና በተለያዩ ሙያዎችና የምዘና ጣቢያዎች እየሰጠ መሆኑ ታውቋል፡፡ በተለያዩ የምዘና ጣቢያዎች እየተካሄደ ያለውን ምዘና አስመልክቶ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የምዘና ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት አቶ ጋትዌች ቱት የምዘናውን ሂደት አስመልከቶ እንደገለጹት ምዘናው የሚካሄደው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የተከለሠበት ሁኔታ በመኖሩ እና የሙያ ብቃት ላይ መመዘን ተገቢ በመሆኑ ምዘናው ለአሠልጣኞች እየተሰጠ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡ የሙያ ብቃት ፓሊሲ ሲቀየር እና የሙያ ደረጃ ሲከለስ አሰልጣኞች ሁሌም በምዘናው ስርዓት የሚያልፋበት አግባብ ቀድሞም የነበረ አሰራር መኖሩን ጠቅሰው ተመዛኞች በምዘናው ብቁ ካልሆኑ ክፍተታቸውን በስልጠና እያሻሻሉ በድጋሚ ምዘናው እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል፡፡ እየተካሄደ ያለው የምዘና ሂደትም ጥሩ እንደነበረ እና ለተመዛኞች ቀድሞ ገለፃ በማድረግ ዝግጁ እንዲሆኑ ጥረት መደረጉን ተናግረዋል፡፡ የባለስልጣኑ የቴ/ሙ/ብ/ዝ/አ/አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ራሔል ማሞ በበኩላቸው እንደገለጹት በቴክኒክና ሙያ ስልጠና የሚሰለጥኑ ሠልጣኞች በአዲሱ የሙያ ደረጃ መሰረት ስልጠና እየተሰጣቸው በመሆኑ በተመሳሳይም የአዲሱን የሙያ ደረጃ መሠረት አድርገው ስልጠና የሚያሰለጥኑ አሠልጣኞች በአዲሱ የሙያ ደረጃ ምን ያህል ብቁ እንደሆኑ ምዘናው እየተሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር https://t.me/Tmhrt_Minister https://t.me/Tmhrt_Minister
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ተራዘመ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአዲስ እና የሬሜዲያል ተማሪዎችን መግቢያ ቀን #ላልተወሰነ ጊዜ አራዘመ። ዩኒቨርሲቲው የተማሪዎችን የመግቢያ ቀን ያራዘመው የመግቢያ ቀኑ ሊደርስ 3 ቀን ሲቀረው ነው። ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም አዲስ ለተመደቡ የጀማሪ መርሐግብር (Freshman) ተማሪዎች እና ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) መርሐግብር ተማሪዎች እንዲሁም በ2015 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) መርሐግብር ወስደው የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ከጥር 21 እስከ 23/2016 ዓ.ም ምዝገባ እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፎ ነበር። ነገር ግን ምዝገባው ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙንና ወደፊት ጥሪ እስኪደረግ ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል። ተቋሙ ለምን የመግቢያ ቀኑ እንደተራዘመ የሰጠው ማብራሪያ የለም። በሌላ በኩል ፤ በዘንዘልማ ካምፓስ ሰሞኑን ማታ ማታ ሲቪል የለበሱ ሰዎች ተኩስ ከፍተው መስተዋላቸውን ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። አንድ የዘንዘልማ ካምፓስ ተማሪ ጥር 15 ቀን 2016 ዓ/ም ምሽት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ በግቢያቸው ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር ገልጿል። በአካባቢው የቦንብ ፍዳታም እንደነበር ጠቁሟል። ይኸው ተማሪ " በዘንዘልማ ካምፓስ ተኩስ አዲሳችን አልነበረም " ሲል ገልጾ ከትላንት በስቲያ በአጥር ዘለው የገቡ አካላት ጥይት እየተኮሱ እስከ ዋና መግቢያ በር መሄዳቸውን ጠቁሟል። " የገባነው ‘ግቡ’ ተብሎ ነው፤ ብዙ ተማሪ የለም። ወደ 100 ብንሆን ነው " ሲልም አክሏል። ተኩስን ኖርማል ሲቪል ልብስ የለበሱ ሰዎች መክፈታቸውን ነው የተናገረው። ጥር 16 ቀን 2016 ዓ/ም በተጨማሪ ማብራሪያ የሰጠ አንድ የግቢው ተማሪ ፤ በዘንዘልማ ያለው ሁኔታው ስለሚያሰጋ ወደ ዋናው ካምፓስ መሄዱንና የቀሩት ጓደኞቹ በሁኔታው መጨነቃቸውን እንደገለፁለት ተናግሯል። " እስከ 18 ድረስ ግቢውን ለቃችሁ ውጡ " የሚል ወረቀቶችም መበተኑን ከጓደኞቹ ዘንድ እንደሰማ በመግለፅ ያለንበትን ሁኔታ የሚመለከተው አካል ይወቅልን ብሏል። የዩኒቨርሲቲው ሁነኛ አካል ጉዳዩን በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ ጉዳዩን #እንዳልሰሙና አጣርተው ምላሽ እንደሚሰጡ ቢገልጹም፣ በድጋሚ ሲደወልና የፅሑፍ መልዕክት ቢላክላቸውም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው። @tikvahethiopia
Show all...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ዘንድሮ በመላ ሀገሪቱ የ " ኬጂ " ተማሪዎች እንግሊዝኛ ቋንቋ እየተማሩ አይደለም። የመዋዕለ ህጻናት ተማሪዎች " ኤ፣ ቢ፣ ሲ፣ ዲ… " ን በዜማ መቁጠር፣ " ኤ ፎር አፕል፣ ቢ ፎር ቦል… " እያሉ ቃላት መመሥረትም አቁመዋል። ከዚህ ዓመት ጀምሮ " ስፖክን ኢንግሊሽ " እና " ኢንግሊሽ ሊትሬቸር " ከ " ኬጂ " ተማሪዎች የትምህርት ዓይነቶች ውስጥ ተሰርዘዋል። እንደ ቀድሞው በአማርኛ ሂሳብ፤ በእንግሊዝኛ " ማትስ " እያሉ የቁጥሮችን አጠራር በሁለት ቋንቋ መሸምደድም ቀርቷል። የዘንድሮ የ " ኬጂ " ተማሪዎች ለአካባቢ ሳይንስ እና ለ " ጄኔራል ሳይንስ " ሁለት ደብተር አይዙም። በአራት ዓመታቸው " ነርሰሪ " የሚገቡት ህጻናት፣ በ6 ዓመታቸው ከ " ዩ ኬጂ " ሲመረቁ የሚያውቁት ብቸኛ የፊደል ገበታ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውን እንዲሆን ተደርጓል። ልጆችን እንግሊዝኛ በማስተማር ተመራጭ የሆኑት የግል መዋለ ህጻናት ከዚህ ዓመት ጀምሮ ሁሉንም ትምህርት የሚሰጡት በአካባቢው የአፍ መፍቻ ቋንቋ ብቻ ነው። በአዲሱ የትምህርት ሚኒስቴር አሠራር መሠረት ተማሪዎች እንግሊዝኛ ቋንቋን እንደ አንድ ትምህርት መማር የሚጀምሩት #አንደኛ_ክፍል ሲደርሱ ነው። ከዚህ ዓመት ጀምሮ መተግበር የጀመረው ሥርዓተ ትምህርት ህጻናት የሚማሩትን ትምህርት በተለያዩ የትምህርት ዓይነቶች (ሰብጀክት) አይከፋፍልም። የኬጂ ተማሪዎች እንደ ቀድሞው ሂሳብ፣ አማርኛ ወይም አካባቢ ሳይንስ የሚባሉ የትምህርት ዓይነቶች አይኖሯቸውም። በትምህርት አይነቶች ፋንታ ህጻናቱ የሚማሩት " ጭብጦችን " ነው። ለምሳሌ፤ የመጀመሪያ ዓመት የመዋለ ህጻናት ተማሪዎች ስድስት ጭብጦችን ይማራሉ። ከእነዚህ ጭብጦች ውስጥ፦ * ስለ እኔ፣ ስለ ቤቴ እና ስለ ቤተሰቦቼ * ትምህርት ቤቴ እና አካባቢዬ የሚሉት ይገኙበታል። የኬጂ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከሚማሯቸው ጭብጦች ውስጥ ደግሞ ፦ * ዋሊያ * ህዋ * ተክሎች እና መጓጓዣ ተጠቃሽ ናቸው። በአዲሱ ካሪኩለም መሠረት ህጻናቱ እንደ ቀድሞው አብዛኛውን ጊዜያቸውን ክፍል ውስጥ ቁጭ ብለው ከሰሌዳ እና ከደብተር ጋር እንዲፋጠጡ አይደረግም። ዘንድሮ የኬጂ ተማሪዎች የሚማሩባቸው ዋነኛ መንገዶች ጨዋታ፣ መዝሙር እና ተረት ናቸው። በአዲሱ ካሪኩለም የኬጂ ተማሪዎች እንግሊዝኛ እንዲማሩ አይደርግም። በእንግሊዝኛ ምንም ነገር የለም። ሁሉም ነገር በአፍ መፍቻ ቋንቋ ይሰጣል። የኬጂ ትምህርት ይዘት መቀነስ ያላስደሰታቸው ወላጆችም ያሉ ሲሆን ተማሪዎች ከአቅማቸው በታች እንዲማሩ እያደረገ ነው ብለዋል። በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶችም ከወላጆች ቅሬታ እየተቀበሉ መሆኑን የአዲስ አበባ የግል ትምህርት ቤቶች አሠሪዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ አበራ ጣሰው አሳውቀዋል። የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ካሪኩለሙ በዝግጅት ላይ በነበረበት ወቅት የትምህርት ይዘቱ መቀነሱን እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት መውጣቱን በተመለከተ ማኅበሩ ተቃውሞ አስተያየት መስጠቱንም አስታውሰዋል። የቅድመ አንደኛ ሥርዓተ ትምህርትን ካዘጋጁ ባለሙያዎች አንዱ የሆኑት ዶ/ር ታደሰ ጃለታ ፤ " ቤተሰብ ልጁ እንግሊዝኛ ከቻለ፣ ፊደል ከቆጠረ ወይም መደመር ከቻለ ተምሯል፣ አድጓል ብሎ ያስባል። በህጻናት ደረጃ ትምህርት እርሱ አይደለም " ብለዋል። ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/BBC-AMAHRIC-01-24 Credit - #BBCAMAHRIC @tikvahethiopia
Show all...
Repost from Tikvah-University
#WolaitaSodoUniversity በ2016 ዓ.ም ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ጥር 23 እና 24/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። አጠቃላይ ገለፃ ጥር 25/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን ትምህርት ጥር 27/2016 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል። ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፡- ➢ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➢ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ ➢ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣ ➢ ጉርድ ፎቶግራፍ፣ ➢ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ። @tikvahuniversity
Show all...