en
Feedback
የስንኝ ቋጠሮ

የስንኝ ቋጠሮ

Open in Telegram

የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው። ግጥሞችን ለመላክ @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!

Show more
2 046
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
...../የገፋሽው /..... አፈር መስሎ የወደቀ ትቢያ ሆኖ የደቀቀ ከጭቃ ጋር ተለውሶ ብናኝ አመድ ተወራርሶ ደጅ ጠንቶ የቀረበሽ ነበር መስሎት የወደድሽው የወደደሽ ለካስ የጨርቃም ልጅ ቡቱቷም ሰው የራብ ጠኔ ሆድ እምብርቱን ለወጠረው እድፍ ጉድፍ እከክ ቅማጭ ለወረሰው እንኳን ለሱ ለሰውም ሰው ፍቅር የለው ....ተፃፈ........፪/፭/፳፻፱ዓ.ም 8:12 ማታ በ tehal (Teddy+he'll.......) @gitmv @gitmv @gitmv

ግጥም በ TD ተዘጋጅቶ በ ሞገስ ሎታ የቀረበ

ውድ የስንኝ ቋጠሮ አባሎች ግጥሞቻችሁን እየላካችሁልን ስላለ እናመሰግናለን። የተመረጡ ግጥሞችን በድምፅ ስለምንለቅ ምርጥ ግጥሞቻችሁን ላኩልን ግጥም ለመላክ 👉 @mogea ይጠቀሙ @gitmv @gitmv

"ሠውና ዘመኑ" በረከሰው ገላ ትቢያ በወረሰው እንኳን ተደርቦ እንዲያውም እንዲያው ነው እፍኝ በማትሞላው በሲሶዋ ዘመን ተካፍላ ተባዝታ ለማትደፋው ሚዛን ጊዚያዊ ስሜትን እልባችን ቀርጸን አይነ ልቦናችን እንዳያይ አውረን እንደሠው ተፈጥረን እንደንስሣ ኖርን አስበን አስበን ዓለምን አሰስን ውቂያኖሥ ሠጠምን ሸለቆ ዘለቅን ጫካ መነጠርን ምድር ገለበጥን ወጣን ወረድን አልን አልንና ድንበሩን ተራምደን ሠማይ ሸነቆርን ጥፋትን አብዝተን ቁጣን አወረድን ጥላቻን በትነን እንክርዳድ አጨድን ሰውነትን ጥለን ቁሥን ሠበሠብን ደግመንም ደጋግመን ገንዘብ አመለክን ጣኦት አቆምንና በግንባር ሰገድን ዘመርን ዘፈንን ደነስን አበድን ሠከርን ጨፈርን ሥቀን አለቀስን በእንቅርት ያህል ነገር ጆሮ ተደግፎን ብዙ እየተመኘን ለመኖር አቅደን ከነግሣንግሧ ሥጋን አፀደቅን በምድራዊ በደል ሠማይ ቤት ወረስን ዳሩ ግን የነብስናሥጋ ሥራ ለየቅልነው አንጋሹም ፈራጁም አፅዳቂው ከላይ ነው ያቺ ሲሶ እድሜ ጊዜዋን ጨርሳ የቀጠሮዋን ቀን ጥሪዋን ሳትረሳ ትጠልቃለች ድንገት እንደማታ ጀንበር ይዘጋል ፋይሉ የተከፈተው በር 😭🙏🙏🙏😭 @TD @Tehal 24/05/13 @gitmv @gitmv @gitmv

😍😍 ለ እናቴ 😍😍 ፍቅርሽ አፌ ላይ ሳይሆን ልቤ ላይ ታትሞአል በየሰከንዶቹ አንቺን ይጠራሻል ከ አጠገቡ ሲያጣሽ በጣም ይጨንቀዋል ውሀ ምግብ አይደል አየርም ያንቀዋል ሚያደርገው ጠፍቶት ግራ ይገባዋል አንቺ የኔ ቅመም ለኔ አስፈላጊ ነሽ ሚየስፈልግሽን ፈጣሪ ይሙላልሽ☺️ ከአጠገብሽ ሆኜ እኔም ላቀማጥልሽ😉😉😍 M.D

ስላንተ ልናገር ቃላቶች ያጥሩኛል በምን እንደምገልፅ ግራ ይገባኛል በየትኛው ቋንቋ ብገልፅ ያምርብሃል?? እኔ ማውቀው ቋንቋ አቅም አጥሮቸዋል!! አልደምቅ አልታይ ብሎ በጅጉ አንሶብኛል አንተዬ አንተ ሆይ አንተዬ በምን ቃል ልግለፅህ ቃላት አጣሁልህ ውድድ ምታደርገኝ አንተኮ ልዩ ነህ ስም እንኳን ባጣልህ አንተን የሚገልፅህ ለመጠሪያም ቢሆን ፍቅር ነህ ልበልህ!! M.D ✍ @gitmv @gitmv

ስላንተ ልናገር ቃላቶች ያጥሩኛል በምን እንደምገልፅ ግራ ይገባኛል በየትኛው ቋንቋ ብገልፅ ያምርብሃል?? እኔ ማውቀው ቋንቋ አቅም አጥሮቸዋል!! አልደምቅ አልታይ ብሎ በጅጉ አንሶብኛል አንተዬ አንተ ሆይ አንተዬ በምን ቃል ልግለፅህ ቃላት አጣሁልህ ውድድ ምታደርገኝ አንተኮ ልዩ ነህ ስም እንኳን ባጣልህ አንተን የሚገልፅህ ለመጠሪያም ቢሆን ፍቅር ነህ ልበልህ!! M.D ✍ @gitmv @gitmv

የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው። ግጥሞችን ለመላክ @mogea ፡ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!! https://t.me/joinchat/TjuxVoUSZHWw_xfo

🍆🍆ጉድ ኣረገኝ ዱቄት🍍🍍 ፎቶዋን ለጥፋ : በፌስቡክ አየኋት ውበቷን አይቼ : ጓደኛዬ አረኳት በውስጥ መስመርም ማዋራት ጀመርኳት ብዙ አዋራችኝ :እኔም አወራኋት ፎቶ ላከችልኝ :ፎቶዬንም ላኩላት ብዙ ተቀራረብን :እኔም ወደድኳት ከዛማ..... ፈለግኩኝ....በአካል ላገኛት እሷም እሺ ኣለች : እካፌ ቀጠርኳት በ አካል ሳገኛት.... ለካስ አክስቴ ናት ወይኔ ጉድ ኣረገኝ ዱቄት። 🍍🍍seif @gitmv @gitmv @gitmv

sticker.webp0.16 KB

መንገዱን ሰው ሞላው ኑሮው ሰለጠነ ስጋችን ስብ ከቦት ነፍሳችን ቀጠነ ገበሬው ቀረና ምሁሩ ዘር ያዘ ሳያርስ እየዘራ አረም ተመዘዘ። @gitmv @gitmv @gitmv

#""ያልተፈታው ቅኔ"" አንድ ቀን ቁጭ ብዬ ከሊቃውንቱ ጋር፣ ቅኔ ከሚቀኙት ከጉባኤው መንደር፣ ተማሪው ተነስቶ በተራው ሲናገር፣ ቅኔ እየዘረፈ ቅኔ ሲደረድር። ውስጡን ያቀበለውን፣ አዕምሮው ያለውን፤ አንዱ ሲጀምረው፣ ሌላው እየቀማው፣ ሌላ ሲጨርሰው። መምህሩም ሲመሩት፣ የጠፋበት ካለፈው በፍቅር ሲያርሙት። እኔም... እኔም ቁጭ ብዬ ሁሉን ሰማሁና ልቀኘው ተነሳሁ ተራዬ ሆነና። ልቤ የሚለኝን ከውስጤ እያወጣሁ፣ በቃላት ድርድር ቅኔ እየተቀኘሁ። ሳለ ድንገት... ያልታሰበ ነገር ድንገት ብቅ አለና፣ ቅኔዬን አቁሜ መንገዴን ጀመርኩኝ በሀሳብ ጎዳና። ገና ስጀምረው እንደ ጓደኞቼ፣ ልናገር እልባት የውስጤን አውጥቼ፣ ሁሉ ቢምታታብኝ እተወዋለሁኝ መምህሬን ፈርቼ። ለምን አትበይኝ፣ ምንም አትጠይቂኝ እንኳንስ በቅኔው ስሜት በሚነካው፣ ሁሉ ይጠፋብኛል ካሰብኩሽ በወሬው። እንዲህ እየሆነ ብዙ ጊዜ ሄደ፣ ቅኔው ይቀርና እንባ እየወረደ። አንድ ቀን ጨኬኜ... የሆዴን በሆዴ በውስጤ አፍኜ፤ ዕድሌን ልጠቀም ብዬ አሰብኩና፣ ቅኔውን ጀመርኩ ሁሉንም ተውኩና። ያው... ያው የተለመደ አይደል፣ ስላንቺ ማሰቡ በጉባኤው መሐል። እናም... እናም አቋረጥኩት ያው እንደልማዴ፣ ሐሳቤን ቢወስንም አልችል ቢለኝ ሆዴ። ከዛማ... የቅኔው መምህሬ ግራ ቢገባቸው፣ የእኔ እንደዚህ መሆን አልገባም ቢላቸው። ቁጭ አርገው ጠየቁኝ፣ መፅሐፍ ቅዱስ ጠቅሰው እንደዚህ መከሩኝ። "ልጄ... እውነቱን ልንገርህ...? ከሁሉ ተማሪዎች አንተ እድለኛ ነህ፤ ይመስልሀል እንጅ ያልተቀኘህ ቅኔ፣ ከሁሉም በላይ ነው ያንተ ቅኔ ለእኔ። በተግባር ተቀኘህ.........፣ የፍቅርን ጉልበት በተግባር አሳየህ።" ብለውኝ ሲሄዱ... እዛው ቁጭ እንዳልኩኝ፣ እኔም በተራዬ ስለተቀኘሁት ቅኔ እያሰብኩኝ፤ ለአንድ ሰዓት ያህል በተቀመጥኩበት ቁጭ ብዬ ቀረሁኝ። መምህሬ..... መከሩኝ እውነቱን፣ የፍቅር ጉልበቱን። አዎ... ለካስ የለም ኑሯል ከፍቅር በላይ፣ በርባኖስ ብትወርጂ ብትወጪ ሰማይ። እናማ... እናማ ልክ ነው ቅኔዬ፣ ፍቅር ነው መዝሙሬ፤ ግን የእኔ ፍቅር ቅኔ.... እስኪ ልጠይቅሽ፣ እንዲያው ምናልባት መልስ እንኳን ቢኖርሽ። "መምህሬ እንዳሉት ፍቅርሽ ቅኔ ቢሆን፣ ሰሙ እና ወርቁ ሕብረቃል የሚሉት ኧረ የቱ ይሆን?" ቅኔዬ..ፍቅርሽ..ሰምና ወርቅ የለው አልታየኝ ብሏል፣ ግን... ፍቅርሽ ቅኔ ሆኖ ከእኔ ጋራ ኑሯል። ታዲያ ፍቅሬ!!!... ምኑን ተቀኘሁት? ምኑን ተረዳሁት? ምኑን ተመከርሁት? ማፍቀሬን ነው እንጅ ቅኔ መቀኘቴን እኔ መች አወቅሁት። ቅኔዬ... ለካስ ፍቅርሽን ነው ቅኔ ያልኩት እኔ፣ በጉባኤው መሐል የሚያልፈሰፍሰኝ እያሳጣ ወኔ፤ ደግሜ ልንገርሽ ፍቅርሽ ሆኖብኛል ያልተፈታ ቅኔ። እና... ወይ ቅኔሽን ፍችው ወይ ትምህርቱ ይቅርብኝ፣ ብቻ ግን ፍቅሬዋ አንድ ነገር በይኝ።

start

የተላኩልን ግጥሞች በጣም ጥቂት ስለሆኑ ለውድድር ማቅረብ አልተቻለም ስለዚህ የተወዳዳሪዎች ቁጥር ሲጨምር ግጥሞችን ፖስት እናደርጋለን፨ ግጥም የላካችሁልን አባሎች ለምን ውድድሩ እንዳልጀመረ እንድታውቁ ነው!!

ሰላም የ ስንኝ ቋጠሮ ተከታዮች የግጥም ውድድር የምንጀምር መሆኑን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው!! በዚህ ቻናል ለመወዳደር የምትፈልጉ ግጥሞቻችሁን 👉 @mogea ላይ ላኩልን። መስፈርት:- 1, ግጥሙ የራሳችሁ መሆን አለበት 2, ከ ስምንት እስከ አስር ስንኝ ቢሆን ይመረጣል 3, በተሰጣችሁ የ ላይክ መጠን ከ አንድ እስከ ሶስት የወጡትን እንሸልማለን!! ግጥሞቻችሁን ላኩልን @mogea ላይ ፖስት ካደረግንበት ሰአት ጀምሮ የ ላይክ መጠን ይቆጠራል። መልካም ውድድር!! ሃሳብ አስተያየት ካሎት እንቀበላለን!! @gitmv @gitmv @gitmv

የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው። ግጥሞችን ለመላክ @mogea ፡ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!

በውስጥ መስመር የተላከ ምርጥ ግጥም ጠላሁህ መሠለ 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ትዝ ይለኛል ያኔ ስላንተ ሲያወሩ ልቤ ይደነግጣል ለምን እንደሆን እንጃ ዝም ብሎ ይመታል ትዝ ይለኛል ያኔ ስሜን ስትጠራኝ በደስታ ብዛት አፌን የሚያስይዘኝ ትዝ ይለኛል ያኔ አይኖቼን ስታየኝ አይኖቼ ደንግጠው ድንብርብር ሚሉብኝ ፨ አሁን ግን ስላንተ ቢያወሩ ስምህን ቢጠሩልኝ ስሜን ብትጠራኝ አይኖቼን ብታየኝ ጠላሁህ መሠለኝ መስሎም አይታየኝ ከወደዱት share ያድርጉ ✍መሩ @gitmv @gitmv @gitmv

በውስጥ መስመር የተላከ ምርጥ ግጥም ጠላሁህ መሠለ ትዝ ይለኛል ያኔ ስላንተ ሲያወሩ ልቤ ይደነግጣል ለምን እንደሆነ እንጃ ዝም ብሎ ይመታል ትዝ ይለኛል ያኔ ስሜን ስትጠራኝ በደስታ ብዛት አፌን የሚይዘኝ ትዝ ይለኛል ያኔ አይኖቼን ስታየኝ አይኖቼ ደንግጠው ድንብርብር ሚሉብኝ አሁን ግን ስላንተ ቢያወሩ ስምርን ቢጠሩልኝ ስሜን ብትጠራኝ አይኖቼም ብታየኝ ጠላሁህ መሠለኝ መስሎም አይታየኝ ✍መሩ @gitmv @gitmv @gitmv