የስንኝ ቋጠሮ
Open in Telegram
የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው። ግጥሞችን ለመላክ @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!
Show more2 046
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
2 046
እንደው አንዳንድ ሰው
የሚገርመኝ እኮ
አራዳ ለነሱ
ቅመው ካላጬሱ
ጠጥተው ካልከሱ
ሴት ካላተራመሱ
ሀገር ካላሰሱ
እንደውም
እንደውም
ፀጉሩን ካልደረደ
ሱሪ ካልቀደደ
ጬሶ ካላበደ
በሰውነቱ ላይ ታቶ ካልተሰራ
ጆሮውን ያልተበሳ ከተባለ ፋራ
ሱሪ አስጠብቦ ካልተወጣጠረ
2 ሶስት ሰው ወግቶ ካልተኮሳተረ
እነዚን ሁሉ መስፈርቶች ካሟላ
ከሱ ውጪ አራዳ ማን ሊባልነው ሌላ
እነዚን ሁሉ ካሎነ በስተቀር
አራዳ አይመስልም የሚል ወሬ ነገር
ጉድ አድምጬ ነበር
ገረመኝ ገረመኝ
አይገርምም?
Getami ✍@AbeLaxu94
2 046
ሌላ ምን እላለሁ!!!
ሀሴት ደስታ መጣ ሄደ ተመልሶ፡
ወግና ምግባሩን ተልዕኮዉ ጨራርሶ፡፡
እረሀብ ችግር መጣ ሄደ ተመልሶ፡
ማንም ሰዉ ሳይለኝ ""ይማርህ ጨርሶ"""::
የመጣዉም ሲሄድ የሄደዉ ሲመጣ፡
ኦ አምላኬ!!!
ምድርና ሞላዋን ፀሀዩን ባወጣ፡
መገረም መደነቅ ነበር የኔ እጣ፡፡
2 046
.....👫ያኔ ልጅ እያለን👫.........
💖ያኔ በጨቅላ እድሜ💖
💖በጠዋቱ ጀንበር💖
💖ያለክፋት የኖርን💖
💖ከመጫወት በቀር💖
🙇አፈሩን አንሶላ🙇
መሬት ፍራሽ አርገን
በንፁህ ህሊና ወንድናሴት ሣንል
አብረን እንተኛለን
አብረን እንነቃለን
🙊ደግሞ እናቦካለን አፈሩን ሰባስበን🙊
ውሃና ምራቅን አንድ ላይ ቀላቅለን
ግዑዝ ሥነፍጥረት የሌለው እስትፋሥ
ሥንቀጥል ሥንሠራ መልሠን ሥናፈርሥ
ኮልኮሌ ሰብስበን እያልን እቃቃ
በዛች ትንሽ ድንቡል ዶቃ
እጅለጅ ተያይዘን በሙሉ ጨረቃ
መዘመር መጨፈር ጉሮሮ እሥኪነቃ
ጨዋታችን እሥኪያልቅ ዳቦ እሥኪቆረሥ
እቃቃ ፍርሥርሥ ውሃው እሥኪል ድፍርሥ
Tedy ✍
@gitmv
@gitmv
@gitmv
2 046
✍ ገዳይ ፍቅር
******
ሕይወት መግዣ የሌላት ፣ መናጢ ደሀ አለም
የተጨማለቀች ፣ በኃጢአት ሞት ቀለም
መሞቷን የማታውቅ ፣ ሕያው ነኝ የምትል
በደዌ ያቆሰላት ፣ ያዳም በደል በትር
መድህን አግኝታ ፣ ሞቷን የገደለ
ሕይወት እንኪ ሲላት ፣ ጆሮዋ ጭው አለ
ለመውደድ ለመጥላት ፣ ምክንያት የለመደች
እንዲያው ስትወደድ ፣ ካልሰቀልኩት አለች
ለፍቅሩ ምላሽ ፣ እየገረፈችው
እንደወጋት ሳታውቅ ፣ መስሏት የወጋችው
ሟች ገዳይ በመሆን ፣ ገዳይ ሟች አ'ረጋት
ያመነችው ጊዜ ፣ ሕይወት ሊሆንላት
ሰቀልኩት ባለችው ፣ መስቀል ላይ ሰቀላት
ልታጠፋው ገድላው ፣ ሊያድናት ገደላት
አዳኝ ፍቅር
#ሄኖክ_አሸብር
2 046
አንተ እኮ😘😘😘
ሳለቅስ ብታይ እኔ ላልቅስ😔
ስወድቅ ብታይ እኔ ልሰበር🙈
ሲያመኝ ብታይ እኔ ልሙትልሽ☺️
ይሁን እሺ ብዬ ብቀበልህ👍
ምን ይሉታል? 🤔
ስበላ ብታይ እኔ ልጥገብልሽ
ስጎርስ ብታይ እኔ ልዋጥልሽ
ስቀመጥ ብታይ እኔ ልረፍልሽ
ስስቅ ብታይ እኔ ልፈንድቅልሽ
ኧረ አቦ ተወኝ...ብዬ ሳልጨርሰው...
እኔን ይተወኝ ልትል መጣህልኝ
በምን አባቴ ነው ዝም የምትልልኝ
እሺ እስከመቼ ነው የምትጃጃለው
የኔን ሁሉ ላንተ የምታደርገው ልልህ ፈልጌ ይኽን አግኝቼው ነው?
አንተማ አንተማ
ስስቅ ጥርስሽ ይርገፍ😷
ስሄድ እዛው ተቀርቀሪ😩
ስመጣ ሞትሽ ይምጣ🙃
ሲያመኝ ይዞሽ ይሂድ🙌
ስሮጥ እግርሽ ይሰበር🏃♀
ስበላ አሁን ይውጣ 🍇🍓🍈
ስጠጣ ትን ይበልሽ እያልክ የምትፀልይ ጠላቴ ነህ ለካ 🙏
ብዬም እንዳላስብ
ትወደኛለህ አሉ እስትገግም💔
አንተ ሰው ማነህ ግን?😉
H.B
2 046
ሰላም የ ስንኝ ቋጠሮ ተከታዮች የግጥም ውድድር የምንጀምር መሆኑን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው!!
በዚህ ቻናል ለመወዳደር የምትፈልጉ ግጥሞቻችሁን 👉 @mogea ላይ ላኩልን።
መስፈርት:-
1, ግጥሙ የራሳችሁ መሆን አለበት
2, ከ ስምንት እስከ አስር ስንኝ ቢሆን ይመረጣል
3, በተሰጣችሁ የ ላይክ መጠን ከ አንድ እስከ ሶስት የወጡትን እንሸልማለን!!
ግጥሞቻችሁን ላኩልን @mogea ላይ ፖስት ካደረግንበት ሰአት ጀምሮ የ ላይክ መጠን ይቆጠራል። መልካም ውድድር!!
ሃሳብ አስተያየት ካሎት እንቀበላለን!!
@gitmv
@gitmv
@gitmv
መወዳደር የምትፈልጉ
2 046
❤️❤️
አይንህ ቦቃ ቦቃ ብይ የሚያህል
መልክህ ቸኮላታ ብሉኝ ብሉኝ የሚል
ጠረንህ ሚማግ ነው ሀሴትን የሚያድል
ደረቁን በሙሉ የሚያለመልም
ፈጣሪ የሰጠህን ልገልፅ ልሞክር
አየሁኝ አንድ ዕለት ከሀ እስከ ፐ ያሉትን አንድም ፊደል ሳይቀር
በየሆሄያቱ ሰባቱንም ፊደላት ብደረድር😌
በተመስጦ ሆኜ🤔 ላጤነው ብሞክር😉
አንድም ፊደል አጣሁ😢 አልገልፅ አለኝ አንተን😳
2 046
...................ትመጫለሽ ብዬ
አይኖቼን በሩ ላይ ተክዬ
ወጭ ወራጁን ስመለከት
ጀንበር ጠልቃ መጣ ጽልመት
ብርሃን ተጋረደ ×ተስፋ ዘቀዘቀ
እድሜ መሽቶ ×ፍቅር አለቀ
አይንም ያዘ ×መንገደኛ ጠፋ
የሄደም ቀረ ×የሚመጣም ከፋ
በጋ እየነጎደ ×ክረምት ገሰገሰ
አበባ ረገፋ ×ወንዙም ደፈረሰ
ነገር ተበላሸ ×ጨዋታው አለቀ
ቃልኪዳን ፈረስ ×መሃላ ወደቀ
ተስፋዬ ተናደ ×በነበር ቀረና
እኔ አንቺን ስጠብቅ ×አንቺም ቀረሽና
ኋለኞች ፊተኛ × ፊተኞች ኋለኛ
የተኛ ተነስቶ × የተነሳው ተኛ
ትመጫለሽ ብዬ ×መንገድሽን ሳይ
ቀጠሮ ተረስቶሽ×መቅረትሽ ነው ወይ
@gitmv
@gitmv
@gitmv
