en
Feedback
የስንኝ ቋጠሮ

የስንኝ ቋጠሮ

Open in Telegram

የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው። ግጥሞችን ለመላክ @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!

Show more
2 046
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
ስውር ማንነቴ በሚያበራው ፊቴ በጥርሴ ፈግጌ በኮምታራ 'ኔነት በውስጤ ጨፍግጌ ገነት ፖስታለው እውነታው በረሃ ስፈፈልግ ኖራለው ጥሜን ሚቆርጥ ውሃ ሲያውቀኝ አያውቀኝም ማንነቴን ዘልቆ ፈገግታዬን ሲያየ
ስውር ማንነቴ በሚያበራው ፊቴ በጥርሴ ፈግጌ በኮምታራ 'ኔነት በውስጤ ጨፍግጌ ገነት ፖስታለው እውነታው በረሃ ስፈፈልግ ኖራለው ጥሜን ሚቆርጥ ውሃ ሲያውቀኝ አያውቀኝም ማንነቴን ዘልቆ ፈገግታዬን ሲያየው ፊቴ አሸብርቆ ማስመሰሌ እንኳን እንዲሁ ያታልላል እንደ ጥርስ ልማም እያደር ይሸታል!! Moge ✍ @gitmv

እንቆጳዝዮን አንችነትሽን ሸሽተው ከፍቅርሽ ቢርቁ ፣ እንደሌዊ ልጆች በክብር ሳይበቁ ፣ ውድ እንቁ ሃገሬን ለጥል የነኩሽ 'ለት ከዙፋንሽ በታች በሞታቸው ይንቁ ። ሙሌ @gitmv

ብዕር አለቀሰ ፍልስፍና ቢሉ መላቅጡን ያጣ ዝቃጭ አስተሳሰብ ሀገር ካገረጣ የፈሰሰው እምባ ከአይን ካልደረቀ ፍትህ ተገማድሎ ከሀገር ከራቀ በሟች ቤተሰብ ፊት ገዳይ መሳለቁ ያንገበግበናል ፍትህ ማዘቅዘቁ። ገድለው ሲያበቁ ተፈቱ ሳይቀጡ ፍትህ ድምፁን ሲያጣ ተበዳይ ተቆጡ የ እንባችን ወዙ በፊታችን ደርቋል የመንግሥትም ጆሮ ከድምፃችን ርቋል እኛ ዝም ስንል ብእራችን አልቅሷል @gitmv . ✍

Coming Soon!! @gitmv
Coming Soon!! @gitmv

📚 በዓልን ከእኛ ጋር ያሳልፉ 🤗🤗🤗 የገና ፋቡላ 📚 “ነገ ዓመት በዓላቸው ነው:: ዓመት በዓል ማለት የሰው ልጆች በቀንድ ከብቶች ላይ… ” ------------------------------------------------ ✍🏽 በዕውቀቱ ስዩም 🎙ትረካ በዕውቀቱ ስዩም ------------------------------------------------ 📚 በዓልን ከእኛ ጋር !!🎄🎄🎄 Join @gitmv🎄 Share @gitmv🎄

"እኮ ለምን?????" ሴት እኮ እናት ናት፣ ሴት እኮ ሀገር ናት፣ ሰሴት እህት ናት፣ ወልዳ ተሸክማ ጡቶቿን አጥብታ ፣ ልጇ እንዲኖር ብላ እሷ ተሰቃይታ፣ እኮ ለምን.... በሁለት ሶስት ወንድ ተገዳ መደፈር፣ ለምንድነው ካለፍላጎቷ አፏ የሚታሰር፣ ህይወትን በሰጠች ነፍገው ምስጋናን፣ ሀገር አያድግም ካላገዝን ሴትን፣ የወላድ መካን እሷን ሊያደርጉ፣ እምነት አርክሰው ለስሜት ሊዋጉ፣ ምናለ ፈጣሪ ቢሰማኝ ጸሎቴን፣ ክብር ለማያውቁ ፈጽመው ክህደትን፣ ሊመራ ኢትዬጵያን አብዝቶ ስቃይን፣ እንዲእያደረገ ሳይወቅሰው ህሊናው፣ የተናቀ እንጂ አይደለም ይሄ ሠው። ገጣሚ" ጽዮን ግርማ (ቃል)" @gitmv

ተወዳዳሪዎችን ሸልመናቸዋል ስለተወዳደራችሁ እእናመሰግናለን!! @gitmv

ከላይ ከ አንድ እስከ ሶስት ድረስ የወጣችሁ ስልካችሁን በውስጥ መስመር ላኩልኝ @mogea ስለተወዳደራችሁ እናመሰግናለን

ሶስተኛ

Huletegnaaaaa🏆🏆🏆👍🏆🏆

Andegna🏆🏆🏆🏆🏆

https://t.me/yelbenlenante ወደ ቻናላችን ጎራ ብትል🙏😊

https://t.me/yelbenlenante ወደ ቻናላችን ጎራ ብትል🙏😊

የገሀነም መዝገብ አንድ ጦማር አንድ መዝገብ፣ አምልጦ ወድቆ ከሰማይ፣ ወደ ገሀነም የሚገቡ፣ ሰዎችን ዝርዝር የሚያሳይ፣ አነሳሁትና ስበር፣ ከራሴ ስም አስቀድሜ የፈለኩት ያንቺን ነበር። Firmaye Addisu

ቅጠረኝ 'መጣለው ቅጠረኝ 'መጣለው በተመቸህ ጊዜ ወዴት እሄዳለሁ ሁንልኝ አዛዤ ዝናቡ ቢዘንብም ቢሆንም በጭቃ ሆነሃልኮ የልቤ አለቃ ያለህበት ስፍራ ቢሆንም ዳገት አልቀርም እመጣለሁ በጠራኸኝ ሰአት yoyo✍

#ግራዋ_በቀለ የኒም ዛፍ ላይ ግራዋ በቀለ፣ በግርዛት ሰበብ ከደጅ የተነቀለ፣ በፍየል ምልማሎ ከደጅ የተሰቀለ፣ የት ታውቆ ከምን እንደታደቀለ። #ማክ

ያ ያ የተረገመ የክፉ ቀን ክስተት የሰይጣን ምርኮኛ የሰላም እንቅፋት የጠንቋዮች ፍሬ የባእዳውያን ብስራት የፈጣሪ ቁጣ ያ ነው የኛ ቅጣት ያ ያ ነዋ ያ የፈረንጆች ባርያ እኔ አላልኩም

#ለሰው ሞት አነሰው ብላለች ቀበሮ የሰው ልጅን ጥፋት ያየች ጊዜ ድሮ እውነትም በጥፋት እንዲህ ለሚረክሰው ለዚህ አጥፊ ፍጡር ፣ አይደለም ሌላውን ይሄው ሞት አነሰው! ሮቤል

ሳቅ የጋረደው እንባ ለሰው ከሚታየው ከፈገግታህ ጀርባ ብሶት የወለደው ይታየኛል እንባ ለማውራት ያልቻልከው የከበደ ህመም ልታሳካው ስትጥር የከሸፈብህ ህልም ውልብ ሲልብህ ውስጥህ ሲርመሰመስ ምንም ያህል ብትስቅ አያለሁ ስታለቅስ