የስንኝ ቋጠሮ
Kanalga Telegram’da o‘tish
የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው። ግጥሞችን ለመላክ @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!
Ko'proq ko'rsatish2 046
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kun
Ma'lumot yo'q30 kun
Postlar arxiv
2 046
"እኮ ለምን?????"
ሴት እኮ እናት ናት፣
ሴት እኮ ሀገር ናት፣
ሰሴት እህት ናት፣
ወልዳ ተሸክማ ጡቶቿን አጥብታ ፣
ልጇ እንዲኖር ብላ እሷ ተሰቃይታ፣
እኮ ለምን....
በሁለት ሶስት ወንድ ተገዳ መደፈር፣
ለምንድነው ካለፍላጎቷ አፏ የሚታሰር፣
ህይወትን በሰጠች ነፍገው ምስጋናን፣
ሀገር አያድግም ካላገዝን ሴትን፣
የወላድ መካን እሷን ሊያደርጉ፣
እምነት አርክሰው ለስሜት ሊዋጉ፣
ምናለ ፈጣሪ ቢሰማኝ ጸሎቴን፣
ክብር ለማያውቁ ፈጽመው ክህደትን፣
ሊመራ ኢትዬጵያን አብዝቶ ስቃይን፣
እንዲእያደረገ ሳይወቅሰው ህሊናው፣
የተናቀ እንጂ አይደለም ይሄ ሠው።
ገጣሚ" ጽዮን ግርማ (ቃል)"
@gitmv
2 046
የገሀነም መዝገብ
አንድ ጦማር አንድ መዝገብ፣ አምልጦ ወድቆ ከሰማይ፣
ወደ ገሀነም የሚገቡ፣ ሰዎችን ዝርዝር የሚያሳይ፣
አነሳሁትና ስበር፣
ከራሴ ስም አስቀድሜ የፈለኩት ያንቺን ነበር።
Firmaye Addisu
2 046
ቅጠረኝ 'መጣለው
ቅጠረኝ 'መጣለው በተመቸህ ጊዜ
ወዴት እሄዳለሁ ሁንልኝ አዛዤ
ዝናቡ ቢዘንብም ቢሆንም በጭቃ
ሆነሃልኮ የልቤ አለቃ
ያለህበት ስፍራ ቢሆንም ዳገት አልቀርም እመጣለሁ በጠራኸኝ ሰአት
yoyo✍
2 046
#ግራዋ_በቀለ
የኒም ዛፍ ላይ ግራዋ በቀለ፣
በግርዛት ሰበብ ከደጅ የተነቀለ፣
በፍየል ምልማሎ ከደጅ የተሰቀለ፣
የት ታውቆ ከምን እንደታደቀለ።
#ማክ
2 046
ያ
ያ የተረገመ የክፉ ቀን ክስተት
የሰይጣን ምርኮኛ የሰላም እንቅፋት
የጠንቋዮች ፍሬ የባእዳውያን ብስራት
የፈጣሪ ቁጣ ያ ነው የኛ ቅጣት
ያ ያ ነዋ ያ
የፈረንጆች ባርያ
እኔ አላልኩም
2 046
#ለሰው ሞት አነሰው ብላለች ቀበሮ
የሰው ልጅን ጥፋት ያየች ጊዜ ድሮ
እውነትም በጥፋት እንዲህ ለሚረክሰው
ለዚህ አጥፊ ፍጡር ፣
አይደለም ሌላውን ይሄው ሞት አነሰው!
ሮቤል
2 046
ሳቅ የጋረደው እንባ
ለሰው ከሚታየው ከፈገግታህ ጀርባ
ብሶት የወለደው ይታየኛል እንባ
ለማውራት ያልቻልከው የከበደ ህመም
ልታሳካው ስትጥር የከሸፈብህ ህልም
ውልብ ሲልብህ ውስጥህ ሲርመሰመስ
ምንም ያህል ብትስቅ አያለሁ ስታለቅስ
