en
Feedback
የስንኝ ቋጠሮ

የስንኝ ቋጠሮ

Open in Telegram

የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው። ግጥሞችን ለመላክ @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!

Show more
2 046
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
Press The Join Button To Get and Play PC Games Like - GTA V -Assassin Creed Syndicate -Watch Dogs 2 -PUBG -Fortnite... and Ot
Press The Join Button To Get and Play PC Games Like - GTA V -Assassin Creed Syndicate -Watch Dogs 2 -PUBG -Fortnite... and Others Game PRESS THE "JOIN" BUTTON👇

"ማችን ላለመውቀስ" ሰው እየገደለ ዛፍ ላይ ሚሰቅለውን አስክሬን ጐትቶ ቤንዚን አርከፍክፎ የሚያቃጥለውን ቤት እያፈረሰ ሚያፈናቅለውን እሱን እያወደስን አርባ ሙት አመቱን በስሙ እየደገስን የሰላም ሰው ነበር ሰለላምን ፈላጊ ለሰዎች የሚያዝን እሩሩህ ታዳጊ እያልን እናልቅስ። ማችን ላለመውቀስ በእናቶች እንባ ላይ የተራመደውን ሴት እየደፈረ የብዙዋችን ህልም ባጭር የቀጨውን ትዳርን አፍርሶ ልጆች በመበተን ጎዳና ያወጣውን ተምሳሌት ነበሩ በጨዋነታቸው አይደል የሰፈር ሰው ሀገር ያወቃቸው እያልን እናልቅስ። ማችን ላለመውቀስ በእግዚአብሄር ስም ምሎ ደሀ እንደሚረዳ በዚ ሚነግድ በደሀ ሰው ፍዳ ደግ ቸር ነበረ ሰውን የሚረዳ አንጀቱ የማይችል የሰው ልጅ ሲጎዳ እያልን እናልቅስ። ሟችን ላለመውቀስ ቂቤን ከሙዝ ጋራ እንጀራን ከጀሶ ዘይት ከጪቃ አንድ ላይ ለውሶ ሲሸጥ የነበረን መልካም ሰው ነበረ የጥሩ ምሰሶ አይደል የሚያውቀው ሰው የማያውቀው እኳን አንድ ቀን ሲታመም የማይችል ጨርሶ እያልን እናልቅስ። ሟችን ላለመውቀስ ባልባሌ ምክንያት ትምርቱን አቋርጦ ግንጋይ ሚያጎደጉድ ተቀምጦ ተቀምጦ ከመሰሎቹ ጋር እየተቧደነ በቁማር በሀሺሽ ልቡ የደነደነ የስንቶችን እናት አንጀት ያደበነ በመንገድ ላይ ቆሞ ሴት ማያሳልፍን በመጠጥ ሱስ ምክንያት አይደለም ከሀገር ከሰፈሩ መውጣት ያቃተውን ባለ ምጡቅ ማይንድ ታታሪ ነበረ ተምሮ ተምሮ ኮሌጅ የሰበረ ከቤተሰብ አልፎ ሀገር ያስከበረ እስኮላር አጊኝቶ ሊወጣ ነበረ ግን ምንያደርጋል እንደመፋቃያ እንጨት ባጭር ተሰበረ እያልን እንልቅስ ሟችን ላለመውቀስ ዶክተር ኢንጅነሩን ታጋይ ወታደሩን ለሀገር ለሰው ብሎ ነፍሱን የሰዋውን ደራሲም አልቀረም ወይም ጋዜጠኛ ተማሪውም አለ እንደ ወንጀለኛ እነዚን ንፁሀን በሀሰት ወንጅሎ ሀገር ሚበድልን መልካም ቀንመስሎ ቅን አሳቢ ነበር እጅግ እውነተኛ ለተጎዳ ፈራጅ ለተበዳይ ዳኛ እያልን እናልቅስ ሟችን ላለመውቀስ። ✍AddisT @gutmv @gutmv

sticker.webp0.11 KB

* ዝም * ምንም ሳይናገር የ ቃላት ልውውጥ በ ዝምታ ብቻ ስሜቱን የሚሰጥ ፍቅርን ለ ማውጋት ዝምታ ነው ምርጫ ከ ሚቀባጥረው የ ሀሳብ ፍጥጫ ዝምታ ነዉ ደጉ ክፉም አይናገር መሃል መንገዱ ላይ በተናጠል ቢቀር ዝም በማለት ወስጥ ብዙ ትርጉም አለ ጊዜ በ ጣለህ ቀን ሰማይ ሲደፋብህ በ ዝግታ ቃላት ስንት መካሪ አለ ሌላው ሌላውማ😏 ደመ መራር ሆኖ አለሁልህ /ሽ ያለ ጥርሱን አግጥጦልህ ከንፈሩን ደብቆ ምላሱን ያሳለ🙆 አቤት ስንት አይነት ሰዉ አለ? ዝም ባለ አፍ ላይ ዝንብ አይገባበትም ወዳጁን ለመጣል ህሊናን አይሸጥም!! ዝምታ የ ግዚሀር ፀጋ በረከቱ ፍቅሩን ሚገልፅበት ሀያል መለኮቱ ፈጣሪ ሲሰቀል..... ለሰው ልጆች ብሎ ሲገረፍ ሊገደል በጌቴ ሰማኔ በ አትክልቱ ቦታ ለ እኛ ሃጥያት በሎ እግሩን እና እጁን በሚስማር ሲመታ 😔 እስኪ ራስህን አድን ብለው ሲፎክሩ ቃል ያልተነፈሰው የጌታ ሚሰጥሩ ምን ይሆን ነበረ? መውረድ አላቃተው ወይ እነሱን መግደል በዝምታው መሀል ትልቅ መልስ ነበር ☺️ እናም ወዳጆቼ ምላሱን አርዝሞ ክፋት ከቀመመው ጥሩ ወዳጅ መስሎ ነገህን ሊሸጠዉ እሱን ሰዉ እራቀው🤚 አርባ ክንድ አርቀው 😁 ሰይጣን ነው አምላክን መሆን ሚናፍቀው እናም ወገኔ . ሆይ..... ዝም ያለህን ልመድ በዝምታ ቋንቋ ከ ፍቅር ተዛመድ ነገር አቀናጅቶ ወሬ ከሚያወራዉ ዝም ያለዉን ዉደድ ዝም ያለውን ፍራው ✍✍N@ti ኢthio

ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! የስቅለት በዓል በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው የስቅለት በዓል በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ነው፡፡ በዓሉ በክርስትና እምነቶች በስግድት እና በፀሎት ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በስግደትና በየጾም የስቅለት በዓል የሚታወስ ሲሆን በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች ተከብሮ ይውላል፡፡ በዓሉ በተለያዩ ቤተክርስቲያኖች በሚካሄዱ መንፈሳዊ ዝግጅቶች የሚከበር ሲሆን፣ እየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጅን ለማዳን ሲል የተቀባላቸውን መከራዎች ለማስታወስ መንፈሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በዓሉ በሌላው አለም በሚገኙ የክርስቲያን ማህበረሰብ ዘንድ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡ @gitmv @gitmv

👉 ውሸት ነበር <<አንተ ከሀዲ ወረኛ እስኪ ዛሬ ልለምንህ ስለፍቅራችን አንድ በአንድ ንገረኝ እባክህ> የምትል ደብዳቤ ለኔ ፅፈሻል መልሱን ለማወቅም ጉጉትሽን ገልጠሻል ጎሽ ! ማሬ በይ ስሚኝ ዛሬ እዚህ ላይ የቆምኩት አንድ በአንድ ልተርክልሽ ከራሴው አንደበት 1በይ <ሴት በሞላበት ዘመን እኔን የመረጥከኝ ከቆንጆዎች መሀል ንግስት ነሽ ያልከኝ በሚያማምሩ ቃላት እኔኔቴን ያወድስከኝ እስኪ ምን ነክቶህ ነው እባክህ ንገረኝ > ባልሽኝ ወቅት እውነት ነው ሺህ ሴቶች ሞልተዋል ከፊሎች አግብተው ከፊሎች ቀርተዋል ታዲያ ከቀሩት መሀል አንችን ያስመረጠኝ የውስጥሽ ውበት ነው እኔን የማረከኝ ብየ ያልኩሽ ሁሉ ውሸት ነበር አንድም የለው እውነት ዝም ብለሽ አድምጪኝ ስሚው ከእኔ አንደበት 2በይ <ፍቅሬ አፍቃሪ እኮ ገጣሚ ነው ለኔ የማትገጥምልኝ ለምድነው >> ስትይኝ ለኣንቺ አይነቱ ቆንጆ'ማ መች ይገጠምለታል ሆሆያትም ቤት መምታት ይሳናቸዋል እገጥማለሁ ብሎ ጀግና ነኝ ባይ ቢመጣ በሱ ላይ ይወርዳል የፈጣሪ ቁጣ ብየ ያልኩሽ ሁሉ ውሸት ነበር አንድም የለው እውነት ዝም ብለሽ አድምጪኝ ስሚው ከእኔ አንደበት 3በይ አንቺ የመጀመሪያዬ ነሽ የብቻየ ማንም ሊያወጣሽ የማይችል ከጉኛየ ማንም የማይወዳደርሽ አንደኛየ የመኖሬ ትርጉም ሁለንተናየ ብየ ያልኩሽ ሁሉ ውሸት ነበር አንድም የለው እውነት ዝም ብለሽ አድምጪኝ ስሚው ከእኔ አንደበት 4 5 6......እያልሽ ብታዳምጪኝ ውሸት ነበር 'ንጂ እውነት ነው አታገኝ እሚገርምሽ ! ዝም ብለሽ አድምጪኝ እያልኩኝ የነገርኩሽ አንድ በአንድ ውሸት ነው ብየ ያስነበብኩሽ እራሱ ውሸት ነው እኔ ልሙት ስልሽ #blue fish @gitmv @gitmv

ተይው አትበሉኝ ከቶ አልሰለቸው ያን ዓለም በጭራሽ ለእኔ ለየት ይላል ለማን ብዬ ልዋሽ። የነፃነት ዓለሜ የደስታየ ቦታ ከማንም በላይ ልቤን የምረታ። ለዛ ነው ማልጠግበው ልዩ ነው የምለው እየደጋገምኩኝ ሺ ጊዜ ምነግረው የእኔ ልዩ ዓለም እያልኩ የማልደክመው ከሰው መራቀን ነው አብዝቸ ምወደው። በRicho @gitmv @gitmv

ቅኔ ቢጤ *************** ሲያሳሳቸው ጊዜ ነገውን ሊሰቅሉት ሮብ ርቧቸው አስቀድመው በሉት ስቀለው ስቀለው ስቀለው ይላሉ ጠርጴዛ ከበው ከጁ እንዳልበሉ አጠገበው ህብስት አሰከረው ወይኑ? በ3ተኛው ጩኸት ተገለጠን አይኑ የፋሲካ ቂጣ ስንዴው ምን ምን አለክ? ሰው ሰው ይላልን ወይስ አምላክ አምላክ? ከየት በላህ ስጋ ደምስ ከምኑላይ ከ'ኔ ትለፍ ብሎ በጽኑ ሲጸልይ ጽዋ ነበረ ወይ የተራራው ድንጋይ የወዝ ደም የሞላው የጠጣችሁት ማይ የፋሲካው ወይን ምን ምን አለክ ደሙ? የልጅ የልጅ ነውን? ያባት ያባት ጣ'ሙ ስትቀባበሉት ስትቆርሱ ያየች ለታ ልጄን ልጄን ነውን? አባቴን አባቴን የናቲቱ ዋይታ? ሃሙስ ጾሜን ልዋል አልፈልግም ንፍሮ አርብ ስጋ አለልኝ ህዝብ ያልበላው አፍሮ እጅ እጅ ይላል ምነ እማ ያነፈርሽው የአይሁድን ሞያ መቼ በቀመስሽው ምንአስቦ ይሆን በ ባዶ እሚለፋ ቅጭጭት ከግራቸው ባጠባ ላይጠፋ። አለም ለረገጣት እድፍ ነው ምንጣፏ ላዘላት ነው እንጂ የሚበራ ጧፏ። °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° መልካም ምሴተ ሃሙስ ይሁንልን ********************** ✍tomi (Toma's tigistu)✍

የአባትነት ወጉ አባት ማለት ክብር አባት ማለት ኩራት አባትነት ፍቅር አባትነት ፅናት በልጁ መደሰት በሀዘኑ ማዘን አይደል ወይ አባትነት የፍቅር ማዕዘን ምነው ታዲያ አሁን ትርጉሙን ቀየረ የአባትነት ወጉ ፍቅሩ መና ቀረ ማዘኑ ቀርቶበት እሱ ሀዘን ጨመረ ትርጉሙ ጠፍቶበት ልጁን ከደፈረ የመውደዱ ጥልቀት ፍቅሩ ተሰወረ ኧረ እናንተዬ የአባትነት ወጉ እንዲህ እስኪጠፋ የስሙ ማዕረጉ ብዬ መጠየቄ ምክኒያቱ ምንድን ነዉ እስቲ መልሱልኝ ጥያቄዬ ይህ ነው ግጥም በናታኒም @gitmv @gitmv @gitmv

።ወ<ግም> ነኝ። •••••••••••••••••••• እሰርጋለሁ እከንፋለሁ እሰምጣለሁ እዋኛለሁ •••••••••••••••••••••• አዎን በኔነት ውስጥ እኔን ባንተ ነት ውስጥ አንተን እሰርጋለሁ፤ ..... በራሴ ህላዌ፣በኔነት አቅጣጫ አንተን በመደረብ፣ለቆምኩት እሩጫ እከንፋለሁ፤.... እውነት በሆነ አክናፍ፣ከውሸት አለም መውጫ እሰምጣለሁ፤..... የለበስኩ ሲሚስለኝ፣ዋሾ ያንተን ካባ በራሴው እኔነት፣ወደ ማንነቴ ጠልቄ እንድገባ እዋኛለሁ...... ያልገጠምኩቢመስለኝ፣ያንተን ቅብ ልቀባ። አዎን በኔነት ውስጥ እኔን ባተነት ውስጥ አንተን ••••••••••••••••••••••• ሰርጌያለሁ- ከንፌያለሁ- ሰምጫለሁ- ዋኝቻለሁ- ••••••••••••••••••••••• የጥፊህን ሰንበር፣ለመዳፍህ ጸባይ የምራቅህን ጭርት፣እስስት መሰል ተባይ። እንደጫርከው ሁሉ፣የስክሪብቶ ምስል አንተን ተከትዬ፣አንተን የምመስል እኔ ማለት ያነኝ፣ያቆሰልከኝ ቁስል። ባንተነት ውስጥ ስዋኝ፣ከራሴ እንዳልጠፋ ነጠል ባልኩኝ ቁጥር፣መክነፌም አይከፋ ባንቺ ነት ውስጥ ስሰምጥ እኔነቴ እንዳይለቅ ገንጠል ባልኩኝ ቁጥር ስርገቴንም አለቅ ••••••••••••••••••••••• እሰርጋለሁ እከንፋለሁ እሰምጣለሁ እዋኛለሁ ••••••••••••••••••••••• አዎን በኔነት ውስጥ እኔን ባንተ ነት ውስጥ አንተን የምመስል........ የጣር ጦማር ለጦር የጣዝማ ማር ለፍቅር ለ3 እየጫንኩኝ ስኖር እንዳህያ ለእሾሁ እሾህ ነኝ ለ እኩዩ እኩያ ወ-ግም ነኝ ለወጉ ዳ(ደ)ግም ነኝ ለ ደጉ ስ(ት)ንኝ ነኝ ለግጥም ሰ(ያ)ው ነኝ ለሰዉም ቅን(2×) ነኝ ለሚቀና ፅ(ጎ)ኑ ነኝ ለሚጠና ለአንተ አ(እ)ንተ(ት)ን ነኝ አለቅም ቢፍቁኝ ብመስልም ከሁሉ..... >>>>>ልዩ ነኝ ለናቁኝ ____________ ✍tomi

አሻፈረኝ ካልሽማ ~ምን እላለሁ አላቆምሽ ሸንጎ~ አለከስሽ በዳኛ ግን ! ሁሌ እንዳይሽ~ ተውበሽ በሂጃብ ~ፈጣሪ ያድርገኝ የቤትሽ ዘበኛ #blue fish

🏆ዉድ የቻናል ቤተሰቦቻችን ሶስተኛው ዙር የግጥም ዉድድር ልናካሄድ ስለሆነ ከ አሁን ጀምሮ እስከ ምሽቱ 3:00 ድረስ ግጥሞቻችሁን📄 በዚህ ሊንክ👉 @mogea 📨 ይላኩልን 🥇ኛ የወጣ 145 mb 🥈ኛ የወጣ 75 mb 🥉ኛ የወጣ 30 mb ተወዳዳሪዎች አሸናፊ ለመሆን ከ30 Like በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል። ከተወዳዳሪዎቹ ምን ማድርግ ይጠበቅባቸዋል? 1.ተወዳዳሪዎች ግጥሞቻችሁን ለጓደኞቻቹሁ እና ግሩፖች ላይ ሼር በማድርግ Like አስደርጉ 2.አሸናፊ ለመሆን ከ30Like በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል 3. ከ 10 ስንኝ ያልበለጠ ግጥም ቢሆን ይመረጣል 4. ጓደኞቻችሁ like ለማድረግ የቻናሉ ቤተሰብ መሆን ይጠበቅበታል 5, ተወዳዳሪዎች ኮድ ይሰጣችኋል በዛ መሰረት ላይክ ማስደረግ ነው 6,ተወዳዳሪዎች የድምፅ ግጥሞቻችሁ 1mb ባይበልጥ ይመረጣል!! ልብ ይበሉ Like ማስደረጋቹሁን አትርሱ 👇👇 በዚህ ይላኩልን @mogea መልካም ዕድል 🖼 Join Us👉 @gitmv

ለውጥ የለም አትበሉ ''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''' ለውጥ የለም አትበሉ ሆደ ጩቤ ይሉት አፈ ቅቤ ነግሶ በየቀኑ ሰበር በየቀኑ ለቅሶ መልካም ዜና ናፍቆት ጆሮ ግንባር ላይ ነው ምንሰማው ይቀድማል ባይናችን ካየነው አ ዎ ለውጥማ... አለ መፈናቀል አለ መገዳደል አለ ሴራ ማሴር አለ ቤት ማቃጠል አለ ዘረኝነት አለ አድሎኝነት አለ ይህ ሁሉ ተደርጎም ማስተባበል አለ ለዚህ ስራ ስኬት ለትግላችን ሲባል ዓለም አጨብጭቦ አክብሮት ሰጥቶናል ስለዚህ... እንወጣለን ገና ከመሃሉ ይሄ ሁሉ እያለ ለውጥ አታጣጥሉ ከዚህ በላይ የለም ለውጥ የለም አትበሉ የኋሊትም ቢሆን ብዙ ለውጦች አሉ ✍️ ህሊና ደሳለኝ

ሲነጋ አይቼሽ ገና በጠዋቱ ጸሃይ ስትጣራ ተነሱ እያለች ብርሃን ስታበራ የወፎች ጫጫታ በዜማው አጅቦኝ በደስታዬ ብዛት ቀኑ ሕልም መስሎኝ ግን ለካ ስእል ነሽ የናፍቆቴ ማስታገሻ የፍቅር ሀ-ሁዬ ጅማሬ የክፉ ቀኔ ማርከሻ ትዝታዋ ሲመጣ ፍቅሬን ሳልኳት በብሩሼ ደስታ ሲርቀኝ ፈገግ እንድል ያንን ሳቅዋን አስታውሼ ፈገግ አልኩኝና.... የስንኝ ደብተሬን ላነብ ስገልጠው ድጋሜ አየሁሽ ነገሩ ምንድን ነው በቃላቶቼ ከትቤሽ በስንኞቼ አጅቤሽ የመውደዴን ጥግ ለመግለጽ ፍቅሬን በግጥም ጽፌልሽ ነበር ለካ ትናንትና ካንቺ በላይ ምን አለና አሁንም እንደገና ....ተነስቼ በበረንዳው ጽሃይዋን ላደንቅ ስወጣ እንዴት እንደሆነ ሳላውቀው ያ ውብ ጠረንሽ መጣ በጽጌረዳ ተመስለሽ ሃሳቤ ውስጥ ስእል ስለሽ እንደ ጽጌረዳ አበባ ሆነሽ የልቤ ካባ ሁሉ ቦታ አይሻለሁ ሁሉ ቦታ አንቺ አለሽ አንቺ ማለት እኮ የአምላኬ ስጦታ ነሽ ውዴ የቀኔ ድምቀት ፍቅሬ የግጥሜ እስትንፋስ ምን ብዬ ልሰይሽ ከማን የትኛውን ቃል ልዋስ እንደው ግን ፈጣሪ ብቻዬን አዝኖልኝ ከኔ ለተዋሰሽ ከሄዋኔ ውጪ ከሄዋኔ ውጪ ሌላ ምን ቃል አለሽ

ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች እንዴት ቆያችሁ? እስካሁን ሁለት ዙር የግጥም ውድድር እንዳደረግን ይታወቃል፣ አንዳኖቻችሁ ሶስተኛው ዙር መቼ እንደሚጀምርም እየጠየቃችሁ ትገኛላችሁ ውድድሩም ይቀጥላል በመሆኑም እስከ አምስተኛ ዙር ድረስ ብቻ ተወዳዳሪዎችን እናወዳድርና በመጨረሻም በአምስቱም ዙር ከ አንድ እስከ ሶስት የወጡትን ብቻ የግጥም ርዕስ ሰጥተናቸው በዛ ርዕስ የተፃፈውን ግጥም እናወዳድራለን ይህ ሲሆን የመጨረሻውን አሸናፊ እንለያለን ስለዚህ ተወዳዳሪዎች በትጋት እንድትወዳደሩ እናሳስባለን!! @gitmv @gitmv @gitmv

ምንድነው በየቀኑ ስምሽን ማነሳቴ አንቺ ላጠፋሽው ልቀጣ ማለቴ በለለሽበት ስምሽን መጥራቴ ካንቺ ጋር በሀሳብ ውየ ካንቺ ጋር ማደሩ ምን ሁኘ ነው ውዴ ምንድነው ነገሩ 😠 ? ምን ሁኘ ነው ምንድነው ምክንያቴ አንዴ ሳላገኝሽ እንዳላጠፋሽ መፍራቴ😠 ብርሃን በጠፋበት በድቅድቅ ጨለማ ታበራልኛለች ሁና ቀላጭ ሻማ ውዴ! የኔ ! ሱሴ ! እያልኩኝ እዘምራለሁ ወደድኳት አፈቀርኳት እላቸዋለሁ ግን እነሱ !😠 ምን ነካው ይሄ ልጅ ከምኔው አበደ 😂 ካልጠፋ ሴት እንዴት እሷን ወደደ እያሉ እንደሚያሙኝ ስሰማ በየቡና ቤቱ ምንም ያልመሰለኝ ምን ሁኘ ነው እቱ 😠 አ ፍ ቅ ሬ ሽ ባ ል ሆ ነ 😠😠😠 #blue fish

በበጎች መሃከል ትርምስ ተፈጥሮ ተደናብረው ሳይ ዛሬ ላይ ከወትሮ አውሬ ይሆን ብዬ በግርምት ሮጬ በ አፅንኦት ስቃኝ ብርሃኔን ገልጬ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ከበጎቼ መሃል አንደኛው ተነክሶ ወድቆ አገኘሁት በደም ተለውሶ ፨ ሁሉም በጎች ናቸው አውሬ የለም ከመሃል ምንስ ተገኝቶ ነው በጌን የሚገድል ብዬ ስደናገጥ ልቤ ተከላውሶ ተኩላን አገኘሁት የበግ ለምድ ለብሶ። ሞገስ (Moge) ✍ ከወደዱት ሼር ያድርጉ @gitmv @gitmv @gitmv

በበጎች መሃከል ትርምስ ተፈጥሮ ተደናብረው ሳይ ዛሬ ላይ ከወትሮ አውሬ ይሆን ብዬ በግርምት ሮጬ በ አፅንኦት ስቃኝ ብርሃኔን ገልጬ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ከበጎቼ መሃል አንደኛው ተነክሶ ወድቆ አገኘሁት በደም ተለውሶ ፨ ሁሉም በጎች ናቸው አውሬ የለም ከመሃል ምንስ ተገኝቶ ነው በጌን የሚገድል ብዬ ስደናገጥ ልቤ ተከላውሶ ተኩላን አገኘሁት የበግ ለምድ ለብሶ። ሞገስ (Moge) ✍ @gitmv @gitmv @gitmv

በዚህ ቻናል ከዚህም ከዚያም የተለያዩ ጠቃሚ እና አስደማሚ የሆኑ ➖የጠቅላላ እውቀት መረጃዎች ➖ የምሁራን አባባሎች ➖ ድንቃድንቅ ዜናዎች እና ሌሎችም ይቀርቡበታል።.

በዚህ ቻናል ከዚህም ከዚያም የተለያዩ ጠቃሚ እና አስደማሚ የሆኑ ➖የጠቅላላ እውቀት መረጃዎች ➖ የምሁራን አባባሎች ➖ ድንቃድንቅ ዜናዎች እና ሌሎችም ይቀርቡበታል።.