የስንኝ ቋጠሮ
Open in Telegram
የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው። ግጥሞችን ለመላክ @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!
Show more2 046
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
2 046
#ያለባለቤቱ
ሳቂ አትበሏት ተነሽ ተጫወቺ፣
ፈገግታሽ መቼ ነው የሚታየው ያንቺ።
ኮራችም አትበሉ በንቀት ተዘባንና፣
ከኃጢአት ይወድቃል ሰው ይገባና።
ዲዳም አትበሏት አፏ ባይላወስ፣
በቃል አትውገሯት ከክብሯ ላይቀነስ።
አትሰኝም ሰነፍ አብራችሁ ባትቦርቅ፣
ደስታዋ ቢገደብ የጥርሷ ፍልቅልቅ።
የፊቷ ፀሐይ ቢከለል በደመና፣
ምክንያት አለው ከሰማይ በላይ የቆመና።
ይላሉ አበው ፍፁም ያለባለቤቱ፣
ቢራገብ አይነድም ነውና እሳቱ።
እናም ልንገራችሁ ማገዶ አትፍጁ፣
ለኔ ፈጥራቷል ተጠቦ በእጁ።
#መኮንን ዮሴፍ(ባቢ)
ይቀላቀሉን 👉 @gitmv
2 046
እንደስሙ ሽንት አስጨራሽ 😁
የዚህን ቻናል ኮሜንቶች አንብበህ ሽንትህ ካላመለጠህ
እመነኝ አለም ላይ ጀግና አንተ ብቻ ነህ
አልሸናም ካልክ/ሽ join ብለህ/ሸ ሞክረው/ሪው
2 046
ረጅም እቅዱ - ከዳር ሳይደርስለት፣
ባጭሩ ተቀጭቶ - ህዝብ ሲያለቅስለት፣
የቆመ ሲሸኘው - እየተሳለመ፣
እንግዲህ ይባላል፣
"የመኖር ግዳጁን - የሰው ልጅ ፈፀመ"
ሲሳይ ሳሙኤል ✍
2 046
ናርምም
ዛሬ ደሞ ድንገት ልቤ ተነሳና
ፊደልን ቀምሮ ቃላትን ሰፋና!
ሳላት ውድ ሀገሩን ካንጀቱ አወጣና
ሰአሊው ሲስላት : ሆኖ በጽሞና::
አርጓዴ ቀለም ነክሮ ይቀባና
ትርጉሙን ፍለጋ ትንሽ ያስስና
ቀዩን ይጀምራል ናርምም ይልና
ናርምም ! ናርምም ይላል ይደግምና
ሚስጥሩ ባይገባው ወርቁን ያጠፋና
ቢጫውን ይቀባል ይቀባል ቢጫውን
ትንሽ ይቆምና ያወራል ብቻውን
አሁንም ናርምም ! ናርምም ጸጥታ
ሀገር ስሯ ጠፍቷል በሴራው እሩምታ
ናርምም ይልና ቀለም ይነክርና
ናርምም ! ናርምም ናርምም በጌታ
ባለቤቱ ወርዶ ህልሜን እስኪፈታ
ተገድቦ እስካየው የሴራው ጋጋታ
ናርምም ! ናርምም ናርምም በጌታ ።
ጮሀን ካልጠቀምናት
ካልሆናት እፎይታ
እስኪ ዝም እንበል ናርምም ላንዳፍታ።
ያሬድ ብርሃነ
2 046
🍂🍁🍂Wow ዋው ፍቅር በጣም ደስ ይላል::🍃
🌹ፍቅረኛ አለህ/አለሽ?🌹
💐አንድ ጨዋታ ነው በጣም ተወዱት አላቹ🥀
🥀ፉቅረኛ ላላቹ #love ንኩ
ፍቅረኛ የለላቹ ደሞ #single ንኩ
🍁መልካም ጨዋታ🌿
2 046
Well come😊
✍ትኩረት ነጥቦች
፩ ፦ግጥም
፪፦ድርሰት
፫፦ፍልስፍና
፬፦ስሜት
~> በዚህ ቻናል አዳማጭ ያጡ ልቦችን እናኳኳለን
ለስሜት እጅግ ቅርብ የሆኑ ጹሁፎችን ያገኙበታል!!❤
2 046
የልቤ ፀሎት
¤¤¤¤¤¤¤¤¤
አቤቱ! አንተ ስም ሰጠኽን
እኛ ቅጽል ፈጠርን
አንተ ቤት ሰጠኽን
"እልፍኝ ሳሎን"ጨመርን
ፊትህ ቢገስፀን ፊትህን እንዳናይ
ከምድር አንሥተን ሰቀልህ ከሰማይ።
✍️✍️በዕዉቀቱ ስዩም
2 046
"ቃል እና ጠል"
ሰማይ ጠል ከጣለ ቁልቁል ከወረደ
ሃሩሩን ከቀጣ ብናኝ ካበረደ
ጠውላጋ ለምልሞ ስሩን ከሰደደ
እህልን ከ አፈር
ሰማይን ከምድር
አንድ ላይ አዋቅሮ በድል ካዋደደ
…
ድርቁን አረስርሶ አመዳም ካወዛ
ተል እኮ ፈፅሞ ካልሄደ እንደ ዋዛ
…
ቃልም እንደዚህ ነው እስኪተኛ በግርግ
ከላይ ተልኮልን ያሻውን እስኪያደርግ
ህይወት ካልቸረልን ሴኦልን ካልቀጣ
ለምንስ መነነ ለምን ከላይ መጣ
ቁልቁል በመውረዱ ሽቅብ ካላወጣ?
Moge✍
