en
Feedback
የስንኝ ቋጠሮ

የስንኝ ቋጠሮ

Open in Telegram

የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው። ግጥሞችን ለመላክ @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!

Show more
2 046
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
💔አላፈቀርኩሽም❣️ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ እጅግ ልብ አንጠልጣይ ምርጥ የፍቅር ታሪክ💚ታሪኩ ሴት ልጅ❣️ካፈቀረች የቱንም ያክል መስዎትነት የምትከፍል እና ፍቅሯን ለመግለፅ የምታደርገው.
💔አላፈቀርኩሽም❣️ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ እጅግ ልብ አንጠልጣይ ምርጥ የፍቅር ታሪክ💚ታሪኩ ሴት ልጅ❣️ካፈቀረች የቱንም ያክል መስዎትነት የምትከፍል እና ፍቅሯን ለመግለፅ የምታደርገው. ሙሉ ታሪኩ በየቀኑ በኛ ቻናል ያገኛ

ጣይ እና አንሽ ################# ደመወዙን ሲጥል አንስተዉ ጠጡበት ባርኔጣዉን ቢጥል ወስደዉ ደመቁበት ከዘራዉን ቢጥል ተመረኮሩበት በሄደበት ሁሉ እየተከተሉ በጣለዉ ሲያጌጡ በጣለዉ ሲያተርፉ ራሱን ሲጥል ግን አይተዉት አለፋ። በእውቀቱ ስዩም✍ @gitmv

አዳምና ሚስቱ በዕዉቀቱ ስዩም *********************** አዳም የትላንቱ የጥንቱ የጧቱ ሳይለፋ ሳይታክት ተኝቶ ባደረ ዉኃ አጣጭ አቻዉን ከጎኑ ተቸረ ይብላኝ ላሁኑ አዳም ለታካች ሚስኪኑ ምነዉ በተኛና በሸሸሁ ከጎኑ ለምትል ሔዋኑ። @gitmv

​​.......... 👩ሄ ዋ ን 👩‍.......... ​​​​​​​​ 🌺🌷ክፍል 1⃣ ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 ገና በልጅነቴ ነበር አባቴ ለሀብታም ጓደኛው እኔን እንደሚድረው ቃል የገባለት እኔ ባባቴ ሀሳብ ባልስማማ አማራጭ አልነበረኝምና ባልፈልገውም ሁለተኛ ጀረጃ ትምህርቴን እንደጨረስኩ ያባቴ ጓደኛ ከዚህ በኃላ እንድማር ባለመፍቀዱና ካባቴ ጋር በመስማማታቸው እንዳገባ ተወሰነ ..... ድል ያለ ሰርግ ተደግሶ አለሜን ሳላይ አለምሽ ተብሎልኝ ተጋባን...ለመጀመሪያ ቀን ባሌ ቤት ስገባ የእስር ቤት ህይወት አንድ ብዬ መጀመሬን ለራሴ አሰብኩት... መረረኝም ጣፈጠኝም አማራጭ አልነበረኝምና የቤት እመቤትነት ኑሮ ሳልፈልግ አንድ ብዬ ጀመርኩት.. .. ቀናቶች ተቆጥረው ወራትን ወለዱ ባሌ ትልቅ ሰው ከመሆኑ ባሻገር ለኔ መልካም ለመሆንና ካለሀብት የሀዘን ኑሮ ሊያወጣኝ ይጥራል... እውነት ለመናገር ክፋ የሚባል አይነት ሰው አይደለም አንዳንዴ ፈገግ ብዬ ካየኝ በደስታ የሚሆነውን ነው የሚያጣው...... የሚጎድልብኝ አንድም ነገር የለም ባዶ የሚባል አይነት ኑሮ ልኑር እንጂ ማንኛዋም ሴት የምትመኘው አይነት የድሎት ህይወት ነው የምኖረው፡፡ ያልኩትንም ነገር በመፈፀም ሆነ የሚያስፈልጉኝን ነገሮች በማሟላት ወደኋላ አይልም ግን እኔ ከአባቴ እኩያ ጋር በፍቅር አብሮ መክነፍ የማላስበው ሆነ...በቃ ጭራሽ የሚሆንልኝን ነገሮች አባት ለልጁ የሚያደረገው እንክብካቤ አድርጌ እስከመቁጠር ደርሻለሁ ..... ከባለቤቴ አቶ ሽፈራው ጋር እስካሁን አንሶላ አልተጋፈፍንም ለየብቻ ነው የምናድረው እንዲህ ፍላጎቴን ማሟላት ከዚህ ከባድ መስዕዋትነት ይጀምራል እኔ ፍቃደኛ ባለመሆኔና ለዚህ ነገር ዝግጁ እስከምሆን እንዲታገሰኝ ስነግረው ቅር ቢለውም ፍላጎቴን አልተቃወመም ለዛም ነው ጥሩ ሰው መሆኑን ባንደበቴ የምመሰክረው ..... ግን አንድ ነገር እርግጠኛ ሆኜ አውቃለሁ እንደሚወደኝ... አንድ ቀን አባቴ ሊጠይቀኝ ሲመጣ እኔ ሌላ ክፍል እንደምተኛ አውቆ በጣም ተበሳጨ..... ይህን አይነት ወርቅ ህይወት ሰጥቼሽ ምን ፈልገሽ ነው እንደዚህ የምትሆኚው አለኝ...... ያባቴ እንደዛ መበሳጨት አልገባኝም...... #ሌሎች_ክፍል_ከፈለጉ_ሊንኩ_ተጭነው_ይቀላቀሉን 👇👇👇👇👇 @yederasiyanbet @yederasiyanbet @yederasiyanbet

ጊዜ ልክ እንደ ወንዝ ነው። ሁለት ጊዜ ተመሳሳይ ውሃ መንካት አትችልም ምክኒያቱም አንዴ ያለፈው ድጋሚ አያልፍም። "በህይወትህ እያንዳንዷን ቅፅበት አጣጥማት!" Join & share us 🙏 ~የኛ ሳይኮሎጂ~ @yegna_psychology @yegna_psychology

sticker.webp0.16 KB

በዚህ ሳምንት ግጥም የላኩልን ስም ዝርዝር 1…ሞገስ 3 ግጥም 2…ኤፍራታ 2 ግጥም 3…አብዱ 4 ግጥም 4…ዮሴፍ 2 ግጥም 5…Abe 1 ግጥም ልከውልናል!! ሌሎቻችሁም ለ አንድ ወር poem Challenge ላይ ግጥሞቻችሁን ላኩልን!! 🏆poem Challenge🏆 በስንኝ ቋጠሮ ብቻ!! @gitmv @gitmv @gitmv

ውብ Arts Here you will get a variety of arts which satisfied your feeling and you can order and buy any arts. @yeabkal27 https://telegram.me/yabkal27

🙏ሰላም እንዴት ናችሁ የስንኝ ቋጠሮ አባሎቻችን!!🙏 Poem እየላካችሁልን በመሆኑ ምስጋናችን ከፍተኛ ነው!! እስከ ነገ እሁድ ድረስ የመጀመሪያ ሳምንት ግጥሞቻችሁን ያ ማለት ሶስት ግጥም እና ከዚያ በላይ በዚህ ሳምንት የተፃፉትን በታማኝነት ላኩልን!! ማሳሰቢያ 👉ሽልማት ለማኘት ብቻ ጥራት የሌላቸውን ግጥሞች አግበስብሶ መላክ ውጤት አያስገኝም 👉ከጊዜው እጥረት አንፃር በጣም ረጅም ግጥም ባይሆን ይመረጣል። ግጥሙ አቅም ካለው ግን አይከለከልም። 👉ግጥሞቻችሁን ስትልኩ ስም፣ ስልክ፣ አድራሻ ፣ብታስቀምጡ ይመረጣል። 👉ነገ ማለትም እሁድ ማታ ስም ዝርዝራችሁን እናስቀምጣለን። 🏆Poem Challenge🏆 ግጥም ለመላክ @mogea እና @SphinxEBS ይጠቀሙ!! 🏆Poem Challenge🏆 በስንኝ ቋጠሮ ቻናል ብቻ!! ችሎታው ያላቸውን ጓደኞቻችሁን ወደቻናሉ ጋብዟቸው!! @gitmv @gitmv @gitmv

የግጥም አፃፃፍ ትምህርት ክፍል አንድ ከአቤል k.m 28/05/09 ዓ.ም ግጥም በዚ ምድር ላይ ካሉ የምድር ጥበቦች ግንባር ቀደሙ ነው። ካልሆነ ግጥም ሲፅፉ አይቶ ወይም ፍቅሩ ስላለው ብቻ አልያም በትምህርት አዳብሮ ግጥም መፃፍ በአስፋልት ላይ ሳር ለማግኘት እንደመፈለግ ነው አይሆንም። ስለዚህ ለዛሬ ግጥም ላይ ብቻ መሰረት አድርገን እንማማር። 1፦ ግጥም ለመፃፍ ተሰጥኦ ( Gift) እንዳለን እና እንደሌለን ማረጋገጥ። ይህን ለማረጋገጥ በተለይ ተመስጦ ( ሙድ) ውስጥ ስንገባ ከአራት መስመር ያላነሱ የተለያዮ ስሜት ሊሰጡን በሚችሉ ( በምንወደው ወይም አጥብቀን በምንጠላው) ነገር ርእስ መርጠን ደጋግመን ለመፃፍ መሞከር። የግጥሙ ስርዓት እና ስሜት የተበላሸ ቢሆንም በትምህርት እና በልምድ ሊስተካከል ይችላል። እሄን ካደረግን ቀስበቀስ ሊያድግ የሚችል የመፃፍ ተሰጥኦ እንዳለን ፍንጭ አገኘን ማለት ነው። 2፦ ገጣሚ መሆን የሚፈልግ ሰው በጣም አንባቢ መሆን አለበት። በሌሎች የተገጠሙ ግጥሞችን ስናነብ ገጣሚዎቹ የተጠቀሙት የአፃፃፍ ዘይቤ እና ክብደት ያላቸውና ቅደም ተከተላቸውን የጠበቁ የቃላት አመራረጥ እንማርባቿለን።ከኛ ጋር ሊሄድ የሚችልለውን አፃፃፍ እናገኘዋለን። 3፦ ግጥም ለመፃፍ ትልቁና ዋናው ነገር መማር ይጠይቃል። የአብዛኛዎቻችን ችግር ተሰጥኦ ካለን በቂ ነው በማለት ምንም ትምህርት ሳንማር ነው የምንፅፈው።እሄ ደግሞ ስነ ፅሑፉን ከማበላሸታችንም በላይ ግምታዊ የሆነ እና እውቀት እና ብስለት የሌለው እኛን የማያሳድግ ግጥም ነው የምንፅፈው። ዝም ብለን በጓደኞቻችን ዝም ብሎ ማስተዋል የሌለው comment ለማግኘት ነው የምንፅፈው። ስለዚህ አለመማር ስነ_ፅሑፉን ይጎዳል። 4፦ ጥቂት እና ጉልበት ያላቸው ቃላቶችን መጠቀም።ለመግለፅ የምንፈልገውን እያንዳንዱን ሃሳብ ለመግለፅ ብለን ለእያንዳንዱ ሐሳብ አንዳንድ ቃላት መጠቀም ፈፅሞ አይገባም። ግጥሙን ያንዛዛዋል።ስሜቱንም ያበላሸዋል። ስለዚህ ሃሳባችንን በአንድ ጊዜ ጠቅለል አድርገው ሊገልፁ የሚችሉ በጣም ውስን እና ክብደትያላቸው ቃላቶችን መጠቀም። 5፦ አሰልቺ የሆኑ እና ማንም ሰው የሚያውቃቸው ተራ ቃላትቶችን አለመጠቀም። 6፦ ግጥም ስንፅፍ አብዛኞቻችን የሚስተዋለው ስህተት የግጥማችን የሐረግ ቁጥር (number of phrases) አለማመጣጠን ነው።ግጥሙን ከመግጠማችን በፊት የግጥማችን የሐረግ ቁጥር ማወቅ አስፈላጊ ነው።ሐረጋቱ ባለ1 ሐረግ; ባለ 2 ሐረግ; ባለ 3 ሐረግ እየተባሉ ይጠራሉ። እነዚህ በምሳሌ እንያቸው፦ ባለ 1 ሐረግ ለምሳሌ፦ አንቺን ያየሁ 'ለታ፡ ስንገናኝ ማታ፡ ልቤ እየመታ፡ ተሞላሁ በደስታ። ይህ ግጥም ለአሁን እንደምሳሌ የተጠቀምኩበት ነው እንጂ በስርአቱ የተገጠመ አይደለም። ግን በሁለት ቃላት የተሰራ ባለአንድ ሐረግ ነው። ስናነበውም አንድ አይነት ድምፅ አለው። ባለ2 ሐረግ ግጥም ለምሳሌ፦ አንቺ ስትበይ(1):እኔ እጠግባለሁ፡(2) አንቺ ስትጠጪ፡ እኔ እረካለሁ፡ ደስ ሲልሽ ሲደላሽ፡ አኔ እፋፋለሁ፡ እማ ፍቀጂልኝ፡ ከሆድሽ አልውጣ፡ እዚሁ ልለፈው፡ የዚህ አለም ጣጣ። ይህ የግጥም አይነት በአንድ ስንኝ ሁለት ሐረጋት አሉበት። ስለዚህም ባለሁለት ሐረግ ነው ማለት ነው።ሲነበብም አንድ አይነት ድምፅ አለው። አንባቢው በቀላሉ ራሱ የገጠመው መስሎ እስኪሰማው ድረስ በቀላሉ ያነቧልም ይገባዋልም። የምንወደውና የምናከብረው ገጣሚ ታገል ሰይፉ ባለ 1 እና 2 ሐረጋት በአብዛኛው ይስተዋልበታል። እሄ ደግሞ አንባቢው በቀላሉ የግጥሙ ሁሳብ እንዲረዳው ያደርጋል። ባለ 3 ሐረግ ግጥም ለሞሳሌ፦ ውዴ የኔ ቆንጆ፡ ሞናሊዛን አየኋት፡ ውበቷ ቀለም ነው፡ ካንቺ ጋር ስትታይ፡ የውበት ሚዛኗ፡ አረ ምኗ ላይ ነው? አንቺን ተመልክቼ፡ ተመልሼ ሳያት፡ ከቶ አላደንቃትም፡ ሊዮናርዶ ይመስክር፡ ውዴ አንቺን የሚያክል፡ ድምቀትም የላትም። ይህ ግጥም በአንድ ስንኝ 3 ሐረጋት ያሉት ስለሆነ ባለ 3 የግጥም ሐረግ እንለዋለን። ሲነበብም እያንዳንዱ ስንኝ ተመሳሳይ ድምፅ አላቸው። ከላይ የፃፍኳቸው ግጥሞች ለምሳሌ ብዬ ነው እንጂ በአግባቡ አይደሉም። 7፦ ቤት መምቻ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ። ብዙ ሰዎች ቤት መምቻውን አንድአይነት ለማምጣት ሲሉ የግጥሙን ቅደም ተከተል( order of the poim) ያበላሹታል። ቅደምተከተሉን መጠበቅ ይኖርብናል። ሌላው ደግሞ የግጥማችን ቤት መምቻ በሳድስ ፊደል ባንጠቀም ይመከራል።ብዙ ጊዜ ለጀማሪ ገጣምያን በሳድስ ፊደላት ለመጨረስ ይቀላቿል። ሳድስ ፊደላት ማለት ት…ች…ል…የመሳሰሉ ናቸው።አንድ ግጥም ችችች…ትትት…ስለተፃፈ ግጥም ነው ማለት አይደለም።በሳድስ ፊደል ቤት መምታት የግጥሙን ጉልበት ይቀንሷል። 8፦ ትልቁ እና ዋናው ነገር ግጥም ለመፃፍ በቂ ቋንቋ ፤ባህል ፣ የህብረተሰቡ የአኗኗር ዘይቤ ፣ ደግነቱን ክፋቱን ፡ፍቅሩን ጥላቻውን ማወቅ ይኖርብናል።ተረትና ምሳሌ ፣ ፈሊጣዊ ንግግሮችን በተቻለ አቅም ማወቅ ግድ ይለናል። ለዛሬ ይብቃን በክፍል ሁለት በጥልቀት እንገናኝ። ከ አቤል k.M የተቀነጨበ @gitmv @gitmv

🙏ሰላም እንዴት ናችሁ የስንኝ ቋጠሮ አባሎቻችን!!🙏 Poem እየላካችሁልን በመሆኑ ምስጋናችን ከፍተኛ ነው!! እስከ ነገ እሁድ ድረስ የመጀመሪያ ሳምንት ግጥሞቻችሁን ያ ማለት ሶስት ግጥም እና ከዚያ በላይ በዚህ ሳምንት የተፃፉትን በታማኝነት ላኩልን!! ማሳሰቢያ 👉ሽልማት ለማኘት ብቻ ጥራት የሌላቸውን ግጥሞች አግበስብሶ መላክ ውጤት አያስገኝም 👉ከጊዜው እጥረት አንፃር በጣም ረጅም ግጥም ባይሆን ይመረጣል። ግጥሙ አቅም ካለው ግን አይከለከልም። 👉ግጥሞቻችሁን ስትልኩ ስም፣ ስልክ፣ አድራሻ ፣ብታስቀምጡ ይመረጣል። 👉ነገ ማለትም እሁድ ማታ ስም ዝርዝራችሁን እናስቀምጣለን። 🏆Poem Challenge🏆 ግጥም ለመላክ @mogea እና @SphinxEBS ይጠቀሙ!! 🏆Poem Challenge🏆 በስንኝ ቋጠሮ ቻናል ብቻ!! ችሎታው ያላቸውን ጓደኞቻችሁን ወደቻናሉ ጋብዟቸው!! @gitmv @gitmv @gitmv

🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋 ከዋክብቶች ዘንበዉ መሬት ላይ ቢፈሱ ሰማያት ሊያፈሩ እልፍ ቢታረሱ * ጨረቃ ሽ ብትሆን ፀሀይም ብትጠፋ አሁን ካለችበት ዓለም ብትሰፋ * ምድር ተደርምሳ ገሞራ ቢሞላት ሰይጣኖች ቢሆኑ የሚያበራ መላዕክት * ዉሃ ሽቅብ ቢሄድ ቁልቁል በቃኝ ብሎ በሬ አምጦ ቢወልድ በላም ተተክቶ * ብቸገር ብነጣ ህይወቴ ባይደላ ተወስኖ ሞቴ ቢዘንብብኝ ዱላ * እሳት ባያቃጥል ለነፍስ ለስጋ አንተምብ ትመጣ እኔኑ ፍለጋ * መልካም ንጉስ ሆነህ አለምን ብትመራ እንደ ሙሴ በትር ታምርን ብትሰራ * እንደ ሳሩ ጉዝጓዝ ከግሬ ብትነጠፍ ብትፆም ብትፀልይ ሰርክ ብትለፈልፍ በረጅም ምላስህ ቅኔህን ብትዘርፍ * ለፈጠረን ታምነህ ዘማሪ ብትሆንም እኔስ ተመልሸ መቼም ያንተ አልሆንም። ✍✍EBS @SphinxEBS Join👉👉👉👉 @gitmv

ቅጠሪኝ_አልቀርም . ቅጠሪኝ አልቀርም በተመቸሽ ግዜ እንዴት እቀራለው በፍቅርሽ ተይዤ ዝናብ እንኳን ቢዘንብ መብረቁ ቢያጓራ ያለሽበት ስፍራ ቢሆንም ተራራ ቁልቁለትን መውረድ ቢጠበቅብኝም ሰው ሁሉ ተኝቶ እንስሳት ቢጮሁም ቅጠሪኝ ብቻ አንቺ በፍፁም አልቀርም፡፡ @SphinxEBS Join👉👉👉👉 @gitmv

ለምን…? በለምለሙ ገነት ፍሬ በሞላበት በነፋሻው እርሻ ሳይዙ ማረሻ እንዲኖሩ ፈቅዶ እንዲበሉ ወዶ ሁሉን ለግሶአቸው አንዳች ሳያንሳቸው እውቅ መምህር እግዜር ማእቀብ ጣለባቸው የበለሷን ፍሬ አሳይቶ ነሳቸው ለምንስ ነሳቸው ለምን ብዬ ጠየኩ ልረዳ ፈልጌ መዛግብትን ገለጥኩ ዳክሬ ብፈጋ አጥጋቢ መልስ ባጣ (ለምን) ርዕስ ሆኖ በግጥም እ (ላይ) ወጣ ✍ Moge @gitmv @mogea

https://t.me/giximochi Moge ብቻ ቅኔ ያውቃል ያለ ማነው😜

ሰላም እንዴት ናችሁ የስንኝ ቋጠሮ አባሎቻችን!! በዚህ ቻናል 👉"POEM CHALLENGE"👈 የተሰኘ event ለማዘጋጀት አስበናል። 👉የዚህ event ጥቅም ብዙ ሰው ግጥም ለመፃፍ እየፈለገ የሚያነሳሳውን ምቹ ሁኔታ በማጣት ብቻ ችሎታ እና ፍላጎት እያለው መፃፍ ላቃታቸው የተዘጋጀ ሲሆን የግጥም መድብል ለመፃፍ ለሚያስብ ሰው ትልቅ ሚና አለው። በመሆኑም በሳምንት ቢያንስ 3 ግጥም እና ከዛ በላይ ለመፃፍ ቃል የሚገባ ሰው በውስጥ መስመር ቢያናግረኝ ደስ ይለኛል ይህን poem challenge መቀላቀል ይችላል። 👉ሶስት ግጥም በሳምንት ግዴታ ስለሆነ በ አንድ ወር ውስጥ ከ 12 በላይ ግጥም እየፃፈ ብዙ ግጥም ለፃፉ ሶስት ሰዎች ሽልማት እናዘጋጃለን!! በዚህ ሃሳብ ማንኛውንም ገንቢ አስተያየት በ 👉 @mogea ላይ ላኩልን !! @gitmv @gitmv

፨እናት አለም፨ ከደበዘዘው ደስታሽ ስር፤የሚፈካ ብርሃን ይመጣል ካዘመመው ምሰሶሽ ግርጌ፤በረከትሽ ይትረፈረፋል ፅልመት ከከበው ቅጥርሽ ላይ፤ውብ የንጋት ፀሃይ ይወጣል ከመጣሽበት ከባድ መንገድ ይልቅ፤የነገው ቀና ይሆናል ዘመንሽ እንደጠቆረ አይቆይም ሀዘን እንደወረሰው አይቀርም ከከበሽ የጽልመት ህይወት፤ከተቃጣብሽ መከራ ከደረሰብሽ የክፋት ሸክም፤ከሆንብሽም ግራ የሚያድንሽ ተስፋ ይኖራል የሚረዳሽም ፍሬ ይመጣል እናትነትሽ ገብቶት ባዳ ያረገሽ ይዞራል አንቺንው ሲል ኖሮ አንቺን እያለ ያልፋል። ✍Ab

👩‍🦰ለውበትዎ ወይም ለቆዳዎ አብዝተው ይጨነቃሉ እንግዲያውስ እኛ ጋር መፍትሔ አለን ምርጥ ምርጥ Brand የሆኑ ኮስሞቲክሶችን💅በቀላሉ ሚያገኙበት ምርጥ ቻናል Join በማለት የፈለጉትን መርጠው
👩‍🦰ለውበትዎ ወይም ለቆዳዎ አብዝተው ይጨነቃሉ እንግዲያውስ እኛ ጋር መፍትሔ አለን ምርጥ ምርጥ Brand የሆኑ ኮስሞቲክሶችን💅በቀላሉ ሚያገኙበት ምርጥ ቻናል Join በማለት የፈለጉትን መርጠው ይዘዙን🧝‍♂። https://t.me/joinchat/IMzEOwsenLthYzY0

👩‍🦰ለውበትዎ ወይም ለቆዳዎ አብዝተው ይጨነቃሉ እንግዲያውስ እኛ ጋር መፍትሔ አለን ምርጥ ምርጥ Brand የሆኑ ኮስሞቲክሶችን💅በቀላሉ ሚያገኙበት ምርጥ ቻናል Join በማለት የፈለጉትን መርጠው
👩‍🦰ለውበትዎ ወይም ለቆዳዎ አብዝተው ይጨነቃሉ እንግዲያውስ እኛ ጋር መፍትሔ አለን ምርጥ ምርጥ Brand የሆኑ ኮስሞቲክሶችን💅በቀላሉ ሚያገኙበት ምርጥ ቻናል Join በማለት የፈለጉትን መርጠው ይዘዙን🧝‍♂። https://t.me/joinchat/IMzEOwsenLthYzY0

👩‍🦰ለውበትዎ ወይም ለቆዳዎ አብዝተው ይጨነቃሉ እንግዲያውስ እኛ ጋር መፍትሔ አለን ምርጥ ምርጥ Brand የሆኑ ኮስሞቲክሶችን💅በቀላሉ ሚያገኙበት ምርጥ ቻናል Join በማለት የፈለጉትን መርጠው
👩‍🦰ለውበትዎ ወይም ለቆዳዎ አብዝተው ይጨነቃሉ እንግዲያውስ እኛ ጋር መፍትሔ አለን ምርጥ ምርጥ Brand የሆኑ ኮስሞቲክሶችን💅በቀላሉ ሚያገኙበት ምርጥ ቻናል Join በማለት የፈለጉትን መርጠው ይዘዙን🧝‍♂። https://t.me/joinchat/IMzEOwsenLthYzY0