የስንኝ ቋጠሮ
Open in Telegram
የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው። ግጥሞችን ለመላክ @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!
Show more2 046
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
2 046
ፅልመት ነው ማፍቀሬ
ለመኖር ህላዌ መውደቅ አይል? ግዴ
ሰርክ እንኳን ቢመስል አንዴ ነው መውደዴ
እሱማ እንዳለን
እንደ ቅዱስ ቃሉ
ብርሀንን ነው
እንጂ ፅልመት አታፍቅሩ
የበደላችሁን አሜን
ይቅር በሉ
ነካሽ ጥርስም ቢሆን ማጉረስ አታቁሙ
ሆድ አምጣ ቢለው ነው ከ'ጅ' መፋለሙ
እርቦት ነውና እስኪጠግብ ድረስ ታጥቃችሁ? አልሙ
ከጠገበስ ወዲያ!??
ሊጥልህ የመጣ የ ከብት እንኳ መንጋ
ኢላማው አድርጎ ለመውጋት ቢንጋጋ
ቀጥ ብለህ ጠብቀው የትም ሳትጠጋ
ይሄ ምን ማለት ነው??
ቃል እየሰበኩ
ምስለት እያረዱ
ሰም እያሳመሩ ንፁህ እያፀዱ
ሰርክ ነው ትክክል
ምንድን ነው ዉደዱ
ቀን ያልፋል እያሉ
ፀደይ ተሰይሞ
ፅልመት እየኖሩ
ዘላለምን መግፋት
ዕድሜ እየገደሉ
ይሄ ነው እንግዲህ
እነ መልከ ጥፉ
በስም ይደገፉ
ነው አይደል ተረቱ
አባዉ ሲሟገቱ
ይሄ ነው እንግዲህ
ፀሀይ ተሰይሞ
ፅልመት ከወረሰኝ
ፅልመት ላፍቅርና
ፀሀይ እኔን ትራቀኝ
ወይ ዕምነቴን ልጣ?
ወይ ዕምነቴን ላግኝ።
@gitmv
@gitmv
✍✍ በብርቱካን
2 046
#ገና ሳገኛት ነው ።
ሳይሽ ግንባሬ ይፈካል
ሳስብሽ ልቤ ይተርካል
ስተኛ ህልሜ ይፈስካል
ስራመድ እግሬ ይደንሳል
ስቀመጥ ወገቤ ይነዝራል
ውዴ! የኔ! ...................ል
አካሌና ልቤ ግራ ሆነውብኝ
ሳስብሽ መሸና ሳስብሽ ነጋልኝ
ማን ነች እንዳትሉኝ
የት ነች እንዳትሉኝ
እኔም አላወኳት
ገና ሳገኛት ነው! እንደዚህ የምላት ።
በ ያሬድ.ብ
@yared_the_ethio
2 046
ቅጣትና ማጣት
ሀሳብ አኝካለሁ፤ነገር እፈትላለሁ
ስለ በደሎችሽ ሳስብ እውላለሁ
የተውሽኝ እንደሆን 'ምን እሆን?' እላለሁ?!
የተውኩሽ እንደሆን 'ምን ላጣ?' እችላለሁ?!
እያልኩ እብሰለሰላለሁ
ወትሮስ
ኖረሽ እንደሌለሽ ከማሰቤ በላይ ምን ማጣት ይኖራል፤ምን ቅጣት ይመጣል?!
ሄደሽ ረስቼሽ ህመሜን እስካክም ሌላስ ምን ያጓጓል፤ምንስ ይናፈቃል?!
ምንም!!!
✍Ab
2 046
A+ እናቴ
በስንኝ ቋጠሯ ተሰፍሮ ፍትል ሸማ መስሎ
ልቤን ከፈሎ ጥሎ ወርቁን አንጠልጥሎ
ሰሎ ግሎ መሮ አይኔን አሳውሮ
ሰላሜን አንግሎ ልቤን አስመርሮ
ያረገኝ ፍቅርሽ ነው በልብሽ ሰውሮ
ያ ጨካኙ ፍቅርሽ ሲጥለኝ ሲያነሳኝ
አልያዝ ብለሽኝ ሁሌም እንዳሳሳኝ
ልመረቅልሽ ነው ሳልስምሽ አቅፌ
A+ እናቴ ውዴ ሰቀቀኔ ሳትገቢ ከቅፌ
# በያሬድ . ብ
@yared_the_ethio
2 046
እንዴት ናችሁ የስንኝ ቋጠሮ ቤተሰቦች እስካሁን በነበረን ቆይታ ግጥሞችን ብቻ ፖስት ስናደርግ እንደነበር የሚታውቅ ነው፣ ከዚህ በኋላ ግጥሞች በዋናነት እንደነበሩ ሆነው ነገር ግን አንዳንድ አስተማሪ ፅሁፎች፣ ወጎች፣ እናም የተለያዩ የ ስነፅሁፍ ስራዎችንም እናቀርባለን፣ በመሆኑም በ እነዚህ ዘርፎች ላይ ችሎታው ያላችሁ ልጆች የ ጥበብ ስራዎቻችሁን በ 👉 @mgea ላይ እንድትልኩ ይሁን
2 046
መጀመሪያ እንባው ይድረቅ!
ላላገባችሁና ለተጎዳችሁ . . .
በጣም ከተጎዳችሁበትና ካስለቀሳችሁ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ወጥታችሁ ራሳችሁን እንዴት እንደዚያ አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳገኛችሁት ትክክለኛ የራስ-በራስ ምርመራ ሳታደርጉና ከራሳችሁ ጋር ሳትተማመኑ ወደሌላ ግንኙነት የምትገቡ አይነት ሰዎች ከሆናችሁ ችግሩ በአብዛኛው ያለው እናንተው ጋር እንደሆነ አትርሱ፡፡
ከስህተታችሁ ሳትማሩ፣ አደራረጋችሁን ሳትቀይሩና ካለፈው ቁስላችሁ በሚገባ ሳትድኑ ወደሌላ ግንኙነት ዘው ብላችሁ እየገባችሁ የቁስል ድግግሞሽ የምታተርፉ ወጣቶች ትንሽ ብትረጋጉ ምን ይመስላችኋል?
@Kibirenaw
@gitmv
@gitmv
2 046
ቂም እንዳልይዝ በሆዴ
እንዳይጎብጥ የህይወት መንገዴ
ሰው እንዳልዞልም በምላሴ
እንዳይጠፋ የህመም ፈውሴ
እንዳልሳሳት በሾይጧን ሴራ
በሰራኋት ትእምት ተግባር እንዳልኩራራ
#እማ በፀሎትሽ መሀል አትርሺኝ አደራ
#blue fish
#መልካም ጁማዕ❤❤ ተመኘሁ
