en
Feedback
HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

Open in Telegram

❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️ 👇👇👇 http://www.youtube.com/@haileG2239

Show more
2 280
Subscribers
No data24 hours
+57 days
+3230 days
Posts Archive
=> ይህ ጥያቄ በወንጌል ቃልና በቤተክርስቲያን ትምህርት መሠረት ጥልቅ ምላሽ የሚያስፈልገው ነው። በምስሉ ላይ ላለው ጥያቄ ኦርቶዶክሳዊ ምላሽ እንደሚከተለው ይቀርባል፦ በመጀመሪያ፣ አንድ መሠረታዊ ነጥብ ማረም ያስፈልጋል፦ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ "መለኮት" አይደለም፤ መለኮትነት የባሕርይ ገንዘቡ የሆነው እግዚአብሔር (አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ) ብቻ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ ግን ከሰው ልጆች መካከል የተመረጠ ሰው፣ ነቢይ እና ሐዋርያ ነው። ጥያቄውን "ዮሐንስ መጥምቅ ይህን የመሰለ ታላቅ ብርሃንና ቃል ከየት አገኘው?" በሚል መልኩ ለጠየቀው ሰው የሚከተሉት ነጥቦች ምላሽ ይሆናሉ፦ => ምንጩ እግዚአብሔር ነው (መለኮታዊ ተልእኮ)፦ ዮሐንስ መጥምቅ ቃሉንና ስልጣኑን ያገኘው ከራሱ ሳይሆን ከላከው ከእግዚአብሔር ነው። ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ ይላል፦ "ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ" (ዮሐ 1፡6)። ስለዚህ የዮሐንስ ብርሃን "የባሕርይ" ሳይሆን "የጸጋ" ብርሃን ነው፤ ምንጩም እግዚአብሔር ነው። => ከመጸነሱ ጀምሮ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ነው፦ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለአባቱ ለዘካርያስ ሲያበስረው፦ "ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል" ብሎ ነበር (ሉቃ 1፡15)። ዮሐንስ ወንጌልን የሰበከውና ዓለምን ያበራው በውስጡ በነበረው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንጂ በራሱ ጥበብ አይደለም። => እርሱ "ለብርሃኑ" ምስክር እንጂ ብርሃኑ አይደለም፦ መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር፦ "ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ እርሱ ብርሃን አልነበረም" ይላል (ዮሐ 1፡8)። ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ "የእግዚአብሔር በግ" የተባለውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለዓለም ለማስተዋወቅ የመጣ "አዋጅ ነጋሪ" ነው። ጌታችንም ስለ ዮሐንስ ሲመሰክር "እርሱ የሚነድና የሚያበራ መብራት ነበረ" ብሎታል (ዮሐ 5፡35)። => የመንገድ ጠራጊነት (የቀዳሚነት) ጸጋ፦ ዮሐንስ መጥምቅ ከእግዚአብሔር የተሰጠው ልዩ ስልጣን "መንገዱን ማስተካከል" ነው። ነቢዩ ኢሳይያስ "የአዋጅ ነጋሪ ቃል" (ኢሳ 40፡3) እንዳለው፣ ዮሐንስ የብሉይ ኪዳን መጨረሻና የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ በመሆን የክርስቶስን ወንጌል መንገድ ጠርጓል። => ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ዓለምን ያበራው፦ ከእግዚአብሔር ስለተላከ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስለተመራ፣ ለእውነተኛው ብርሃን (ለክርስቶስ) ምስክር በመሆኑ ነው። ዮሐንስ ራሱ እንደተናገረው "እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባኛል" (ዮሐ 3፡30) በማለት የክብር ምንጩ ክርስቶስ መሆኑን መስክሯል። ስለዚህ ዮሐንስ መጥምቅ የብርሃን ምንጭ ሳይሆን፣ የብርሃን ምንጭ የሆነውን አምላክ ያሳየ መለኮታዊ "መብራት" ነው።

ችግሮቻችሁ በጠንቋይና በጸበል ካልተፈታ እኛ ሳይኮሎጂስቶች እንፈታላችኋለን!! ከአጋንንትና እስራትና ከደዌ ለመፈወስ የሚረዳ ጬሌና አቴቴ! ሱፍ የለበሱ እብዶች! https://youtu.be/dKTt4WiCXmc?si=oUvt4DiVSo1XH_K1

መምህር ግርማ ወንድሙ ያስተማሩን እጅግ አስገራሚ ትምህርት!! መንፈሳዊ ቤት ለመሆን እንዴት እንሰራ? የዲያብሎስን ሴራ በመረዳት መንፈሳዊ ህይወትን መገንባት!! https://youtu.be/3mTnavPH6UE

የሰሎሞን ጥበብ እያላችሁ የተጃጃላችሁ ይኼንን ጉድ ተመልከቱ!! ማንያዘዋል እሸቱ ዛሬም ደገመው የመተቱ ጉዳይ!! እግዚአብሔር አጥብቆ የሚጠላቸው 6 ነገሮች!! https://youtu.be/GOhPL-Z9bbA

ጥያቄ፡ በበዓለ ኀምሳ ስግደት እንደማይፈቀድ ያዝዛል። የጸሎት ስግደትንም ጨምሮ ነው? ጸሎት አድረስን መስገድ አይቻልም? መልስ፦ የጸሎት ስግደት በማንኛውም ቀን የሚሰገድ ነው። እሑድ ቀንም ወደ ቤተክርስቲያን ስንገባ ሦስት ጊዜ ሰግደን እንገባለን። ጸሎት ስንጀምርም ሦስት ጊዜ ሰግደን እንገባለን። የተከለከለው ንስሓ ተቀብለን የምንሰግደው የቀኖና ስግደት ነው።

ጥያቄ፡ ከትንሣኤ በኋላ በበዓለ ኀምሳ ጊዜ አርብም፣ ረቡዕም በማንኛውም ጊዜ የፍስክ ምግቦች ይበላሉ። ምክንያቱ ምንድን ነው? መልስ፦ ዘመነ ትንሣኤ (በዓለ ኀምሳ) በመንግሥተ ሰማያት ለምንኖረው ኑሮ ምሳሌ ነው። በመንግሥተ ሰማያት ደግሞ ድካም፣ ኀዘንና የመሳሰሉት ነገሮች የሉም። ፍጹም ዕረፍት፣ ፍጹም ደስታ አለ እንጂ። ፋሲካ ደግሞ በግ አርዶ ከመብላት ጋር የተያያዘ ነው (ዘፀ.12፥21)። ይህም በሀገራችን የደስታ መግለጫ ሆኖ የኋላውን ፍጹም ዕረፍት እናስብበት ዘንድ ይደረጋል።

ጥያቄ፡ እንደየ አካባቢው የተለያየ ባህል ይኖራል። በመሆኑም ባህሉን እንደ ሃይማኖት በመቁጠር የሚከናወን ድርጊት ስለሚኖር መለኪያችን ምን ይሁን? መልስ፦ የባህል መለኪያው ሃይማኖት (ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ) ነው። አንድ ባህል ሃይማኖታዊ አስተምህሮን እስካልተቃወመ ድረስ ሊነቀፍ አይችልም። በሀገራችን ያሉ ባህሎች ብዙዎች ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ጋር የሚመሳሰሉ ደጎች ናቸው። አንዳንድ ባህሎች ግን ከሃይማኖት የሚቃረኑ ሆነው ሲገኙ መቃወም ይገባል።

ጥያቄ፡ እግዚአብሔር የነጻነት አምላክ ነው እንላለን። ነጻነት ራሱ ምንድን ነው ከምርጫ በምን ይለያል? ፍጹም ነጻነትስ አለወይ? እና እንደዚህ ከሆነ ሰው በነጻነቱ ውጤት ለምን ይጠየቃል? መልስ፦ ነጻነት ማለት አንድን ነገር የማድረግና ያለማድረግ ሙሉ ሥልጣን መኖር ማለት ነው። ይህ ሲሆን ግን በማድረጉና ባለማድረጉ ምክንያት የሚገኘው ውጤት ኀላፊነትንም ያካተተ ነው። አንድ ሰው የመብላት ነጻነት አለኝ ብሎ አብዝቶ ቢበላና ቁንጣን ቢይዘው ተጠያቂው ራሱ ነው። "ጽጋብ ያመጽእ ግብረ ድንጻዌ፣ ወድንጻዌ ያፈደፍድ ደዌ" እንዳለ ባለቅኔ። የሰው የነጻነቱ ውጤት ባለቤቱ ራሱ ስለሆነ መጥጠየቁ አግባብ ነው። ሰው የፈለገውን የማድረግ ሙሉ ነጻነት አለው። ሁሉንም ለማድረግ የሚያስችል ባሕርይ ግን የለውም። በተፈጥሮው ወሰን ያለበት ነውና።

ጥያቄ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሳትን ሲያወጣ በሲኦል የቀሩ ነፍሳት አሉ ወይስ የሉም? እነ ፈርኦን እና እነ ሄሮድስ የት ናቸው? ገነት ወይስ ሲኦል? መልስ፦ በዚህ ዙሪያ ሁለት እይታዎች ይነገራሉ። እነዚህ ሰዎች አልወጡም የሚሉ አሉ። መነሻቸው በመቅድመ ወንጌል ወኀደጎሙ ለእኩያን የሚለው ቃል ነው። በብዙዎች ዘንድ የሚታመነው ግን ማንም ሰው አልቀረም ሁሉም ሰው ከሲኦል ወደገነት ተመልሷል የሚለው ነው። ወኀደጎሙ ለእኩያን የሚለውንም በስመ ኀዳሪ ይጼዋዕ ማኅደር በሚለው አግባብ በነፈርዖን አድረው ክፉ ያሠሯቸው አጋንንት አልወጡም ለማለት እንጂ ራሳቸው እነፈርዖን አልወጡም ማለት አይደለም ብለዋል።

ጥያቄ፡ ንስሐ ድንግል ያልሆነችውን ወደ ድንግልና ትመልሳለች ተብሎ ተጽፏል። ስለዚህ አንድ ካህን ቢሳሳት እንዴት በንስሓ ወደ ክብሩ አይመለስም? መልስ፦ ንስሓ ድንግል ያልሆነውን ወደ ድንግልና ትመልሳለች የሚለው ስለነፍስ ድንግልና የተነገረ ነው እንጂ ስለሥጋ ድንግልና የተነገረ አይደለም። ነፍስ ኃጢአት ስትሠራ ድንግልናዋን አጣች ትባላለች። ንስሓ ስትገባ ደግሞ ድንግልናዋ ተመለሰ ይባላል። አንድ ካህን ከሌላ ሴት ቢደርስ ክህነቱ ይፈርሳል። ንስሓ ገብቶ ኃጢአቱ ይቅር ስለሚባል ነፍሳዊ ክብሩን መመለስ ይችላል። ክህነታዊ ክብሩ ግን በንስሓ አይመለስም።

ጉድ! በመገናኛ በድብቅ ሰው የሚገበርበት ትልቁ ሕንጻና አስከፊ ምስጥሮቹ!! መተት አይነካኝም እያልኩ ስኩራራ ይኼው ጉድ ሆንኩኝ!! መቁጠሪያ ያጋለጠው ምስጥር! https://youtu.be/Ymdod1QaM_o

ማንያዘዋል እሸቱ የመተት ጉዳይ ከአቅሜ በላይ ሆነብኝ እያለን ነው ወገን!! ጡቷን በመተት ከተፈጥሮና ከተለመደው ውጭ አደረጉት እጅግ ያሳዝናል!! https://youtu.be/llgw5Ge81rw

እግዚአብሔር ከፍ ሊያደርጋችሁ ሲል የሚታዩ 5 አስገራሚ ህልሞችና ትርጉማቸው!! ይኼንን ነገር በህልም ካያችሁ እባካችሁ ተጠንቀቁ!! #ህልም #ሕልሞች #ጸሎት https://youtu.be/a95iFM7fMlQ

ወለተ ሰንበትና ገብረ ኪዳን ለቅዱስ ሩፋኤል 1100 ብር አስገብተዋል! እግዚአብሔር ይስጥልኝ። በወጣ ይተካ በርቱልኝ ቤተሰቦቼ። ሌሎቻችሁም ከላይ በተጠቀሰው አካውንት ማስገባታችሁን እንዳትረሱ። የቅዱ
ወለተ ሰንበትና ገብረ ኪዳን ለቅዱስ ሩፋኤል 1100 ብር አስገብተዋል! እግዚአብሔር ይስጥልኝ። በወጣ ይተካ በርቱልኝ ቤተሰቦቼ። ሌሎቻችሁም ከላይ በተጠቀሰው አካውንት ማስገባታችሁን እንዳትረሱ። የቅዱስ ሩፋኤል ረድኤት በረከቱ በሁላችን ላይ ይሁን።

"ዳግም ትንሣኤ" ስላልን ክርስቶስ ዳግም ተነሣ አያሰኝም። ለሁለተኛ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ መገለጡን መናገር ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሣኤ ዕለት ሐዋርያት ባሉበት በዝግ ቤት ገብቶ በመካከላቸው ተገኝቶ <<ሰላም ለሁላችሁ ይሁን>> በማለት ትንሣኤውን ገልጾላቸዋል። <<አስታረቅኋችሁ>> ሲል ነው። ቅዱሳን ሐዋርያት የትንሣኤውን የምሥራች ለቅዱስ ቶማስ ሲነግሩት አላመነም ነበር። "ትንሣኤ ሙታን የለም" ከሚሉ ከሰዱቃውያን ወገን ስለነበር ነው። <<በእርግጥም እናንተ ትንሣኤውን 'ዐየን' ብላችሁ ስትሰብኩ እኔ ግን 'ሰምቻለሁ' ብዬ ልመስክር ላስተምር ነውን?>> ብሎ <<ካላየሁ አላምንም"µ>> አለ። ይልቊንም <<የችንካሩን ምልክት በእጆቹ ዳስሼ ካላየሁ፥ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ላይ ካላገባሁ እጄንም በጐኑ ካላገባሁ፤>> አላምንም አላቸው። ከስምንት ቀን በኋላ (በሳምንቱ) ደቀ መዛሙርቱ በድጋሜ በዝግ ቤት ውስጥ ነበሩ። ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበር። (ዮሐ ፳፥፳፮) ደጁ ተዘግቶ ሳለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መጣ። ማንም ሳይከፍትለት ገብቶ በመካከላቸውም ቆመና <<ሰላም ለእናንተ ይሁን>> አላቸው። ጌታችንም ሐዋርያ ቶማስን <<ጣትህን በጎንህ አስገባው ያመንህ እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን>> ብሎም ገሠፀው። ቶማስም እጆቹን ከሰደደ በኋላ <<እግዚእየ ወአምላኪየ - ጌታዬና አምላኬ>> ብሎ መለሰ። መለኮት ነውና ቢዳስሰው እጁ ከእሳት እንደገባ ጅማት እርር ኩምትር አለ። መዳሰሱን ሲያይ <<እግዚእየ>> ማቃጠሉን ሲያይ <<አምላኪየ>> አለ። ይህንንም ሊቁ <<አንተ ዘቀዳሚ ወአንተ ዘይእዜ>> ብሎ ተርጐሞታል። የሚገርመው ነገር መለኮትን የዳሰሰች የቅዱስ ቶማስ እጅ በሕያውነት ትኖራለች። በሕንድ ሀገር ከመንበር ላይ ከታቦቱ ጋር የሚያኖሯት ሲሆን በዓመት አንድ ቀን (የአስተርእዮ ማርያም) እየወጣች የሚሾመውን አገልጋይ ቀኝ እጁን ትይዘዋለች። አንድ ዓመት አገልግሎ ያርፋል። በዓመቱ ወጥታ ከሚተካው አገልጋይ እጅ ላይ ታርፍና ተተኪውን ተሿሚ ታመላክታለች። እንዲህ እያለች ግብረ መንፈስ ቅዱስን እየገለጠች ትኖራለች። ከበዓሉ ረድኤት ይክፈለን።