cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

الدعوة السلفیة بالأجبار

የአጅባርና እና አከባቢው የሰለፍያ ደዕዋ

Show more
Advertising posts
198
Subscribers
No data24 hours
-47 days
-1530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

3. የአህለ ሱና አቋም፦ ሑሰይን የወጡበትን አቋም ከቀየሩ በኋላ ነው የተገደሉት። ይሄ ደግሞ ግልፅ በደል ነው። የሑሰይንን “ወይ ወደ መካ ልመለስ፣ ወይ የዚድ ዘንድ ሄጄ ቃል ልግባ ወይ ደግሞ ከሙስሊሙ ሰራዊት ጋር ልዝመት ተውኝ” ማለታቸውን እምቢ ብሎ ሰራዊት ያዘመተው ዑበይዱላህ ብኑ ዚያድ፣ ጭፍጨፋውን ያካሄዱትና አስከሬናቸው ላይ ነውረኛ ተግባር የፈፀሙት አካላት ሁሉ ወንጀለኞች ናቸው። እውነታው ይህ ከሆነ ከመካ የወጡበትን መነሻ ብቻ በመውሰድ የመጨረሻ ውሳኔያቸውን ገሸሽ አድርጎ በአመፀኝነት መክሰስ ልክ አይደለም። የተገደሉትም በግፍ ነው። ይሄኛው የአህለ ሱና አቋም ነው። ለዚያም ነው ኢብኑ ተይሚያ “ሑሰይንን የገደለ፣ ወይም በግድያው ላይ የተባበረ፣ ወይም ግድያውን የወደደ የአላህ፣ የመላእክትና የሰዎች ሁሉ እርግማን በሱ ላይ ይሁንበት” ማለታቸው። [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 4/487] Ibnu Munewor = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Show all...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

በሑሰይን ጉዳይ ላይ የታዩ ሶስት የተለያዩ አቋሞች ~ የሑሰይን ግድያ በሙስሊሙ ኡማ ላይ ትልቅ ጠባሳ ጥሏል። ጉዳዩን ግን ከስሜት ነፃ ሆኖ መያዝ ያስፈልጋል። በምንይዘው አቋም ላይ ስሜታዊነት ጣልቃ እንዳይገባ መጠንቀቅ አለብን። ልክ እንደ ሑሰይን ነብያትን ጨምሮ በርካታ ታላላቆች በአሰቃቂ ሁኔታ በግፍ ተገድለዋል። ነብዩላህ የሕያና ዘከርያ በሰው እጅ ነው የሞቱት። ኸሊፋዎቹ ዑመር፣ ዑሥማንና ዐሊይም በሰው እጅ ነው የተገደሉት። እነዚህ ሁሉም ከሑሰይን የሚበልጡ ከመሆናቸው ጋር ሞታቸውን ለፍርደ ገምድል ውሳኔ እንደማንጠቀመው ሁሉ የሑሰይንን ክስተትም የሶሐባ ጠላቶች አጀንዳ ማስፈፀሚያ እንዳንሆን በጥንቃቄ ልንይዘው ይገባል። የሑሰይን ውሳኔ ሁለት የተለያዩ ገፆች አሉት። የመጀመሪያው ገፅ ከመካ የተነሱበት ክፍል ነው። ሁለተኛው ደግሞ የሞቱበት አቋም ነው። የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ እንዳንደርስ ሁለቱን ነጣጥሎ ማየት ይገባል። [ሀ]፦ ከመካ የወጡበት አቋም ሑሰይን ሰው ናቸው። እንደ ሰው ኢጅቲሃዳቸው ሊስት ወይም ሊያገኝ ይችላል። ከመካ ተነስተው ወደ ኩፋ ለመሄድ የወሰኑበት ግላዊ እይታቸው ልክ አልነበረም። ልክ ቀደም ብለው ከዐሊይ ጋር ጦርነት ውስጥ የገቡት ታላላቆች እይታቸው ስህተት እንደሆነው ማለት ነው። በወሕይ የሚመሩ አልነበሩምና ስህተታቸው የሚደንቅ አይደለም። ይሄ የሑሰይን ውሳኔ ልክ እንዳልነበር ለመረዳት የሚከተሉትን ነጥቦች ማንሳት ይቻላል፦ 1. ሶሐቦች የሑሰይን መውጣት ልክ እንዳልሆነ ጠቁመዋል። ኢብኑ ዐባስ፣ ኢብኑ ዑመር፣ ኢብኑ ዙበይር፣ ጃቢር ብኑ ዐብዲላህ፣ ዐብዱላህ ብኑ ዐምር ብኒል ዓስ፣ ሙሰዊር ብኑ መኽረማ፣ ዐብዱላህ ብኑ ሙጢዕ፣ አቡ ዋቂድ አለይሢይ፣ ሰዒድ ብኑ ሙሰዪብ፣ ወዘተ ሑሰይን እንዲመለሱ ወትውተው ነበር። * ኢብኑ ዐባስ:- “እነዚህ ሰዎች አሚራቸውን ገድ ለው፣ አገሩን ተቆጣጥረው ከሆነ የጠሩህ ሂድ። ያለበለዚያ አሚሩ በህይወት እያለ፣ እየተቆጣጠራቸው፣ ሹማምንቱ ገቢ እየሰበሰቡ ከሆነ የጠሩህ ሰዎቹ ለሁከትና ለጦርነት ነው የጠሩህ።” ሑሰይን አልታጠፉም። በዚህን ጊዜ ኢብኑ ዐባስ እንዲህ አሉ፦ “ከመሄድ የማትመለስ ከሆነ ሴቶችና ልጆችን አትውሰድ። ወላሂ! እኔ ዑሥማን ሴቶቹና ልጆቹ እያዩ እንደተገደለው ሴቶችህና ልጆችህ እየተመለከቱ እንዳትገደል እፈራለሁ።” ይህም አልሆነም። በዚህን ጊዜ “ከሱ ውጭ አምላክ በሌለው እምላለሁ! ፀጉርህን አናትህን ጨምድጄ ይዤህ ከዚያ ሰው ተሰብስቦ ስታይ ትታዘዘኛለህ ብዬ ባስብ አደርገው ነበር” አሉ። * ኢብኑ ዑመርም እንዲህ ብለዋል፦ “ሑሰይን ብኑ ዐሊይ አሸንፎን ነው የወጣው። በአባቱና በወንድሙ ላይ በደረሰው በቂ ትምህርት እንዳየ እምላለሁ። እድሜ ልኩን እንዳይንቀሳቀስ የሚያደርገው፣ እንዲሁም ሙስሊሞች ከገቡበት እንዲገባ የሚያደርገው በቂ ፈተናና ክህደትን (ከኩፋ ሰዎች) አይቷል። ምክንያቱም የሙስሊሙ አንድነት ይሻላልና።” * አቡ ሰዒድ አልኹድሪ፦ “ሑሰይን አሸንፎኝ ነው የወጣው። ‘በነፍስህ ላይ አላህን ፍራ! ቤትህን ያዝ። በመሪህ ላይ አትውጣ’ ብየው ነበር” ብለዋል። [አጦበቃቱል ኩብራ፣ ኢብኑ ሰዕድ፡ 6/425] ወንድማቸው ሙሐመድ ኢብኑል ሐነፊያ ራሱ ሑሰይን እንዳይወጡ ለማድረግ ጥረው ነበር። የሑሰይን መውጣት ልክ ቢሆን ኖሮ እነዚህ ሁሉ ሶሐቢዮች ሊከለክሏቸው ቀርቶ ከጎናቸው ይሰለፉ ነበር። 2. ከጥቂቶች በስተቀር ሶሐቦች እንዳለ ለየዚድ ቃል ገብተዋል። ሑሰይን ራሳቸው ኋላ ላይ ወደ የዚድ በመሄድ ቃል ለመግባት ጠይቀው ነበር። “የዚድ ከሃዲ ነው፣ ቃል ኪዳን የለውም” የሚል ካለ እነዚያ ሁሉ ሶሐቦች ለከሃዲ ነው ቃል የገቡት እያለ ነው። ሑሰይንም “ለየዚድ ቃል ልግባ” ሲሉ ለከሃዲ ቃል ሊገቡ እየጠየቁ ነበር ማለቱ ነው። የሑሰይንን የመጀመሪያ ውሳኔ ልክ ለማድረግ በማሰብ የዚያን ሁሉ ሶሐባና ታላላቆች ውሳኔ ስህተት ነበር ማለት ፈፅሞ የሚያስኬድ አይደለም። ባይሆን ስህተታቸው በዐሊይና በሙዓዊያ ዘመን በሶሐቦች መካከል እንደደረሱት ግጭቶች ከኢጅቲሃድ የመነጨ ነበር ቢባል ነገሩ ይቀላል። ከነዚህ ነጥቦች በመነሳት የሑሰይን የመጀመሪያ ተግባር ስህተት እንደነበር መረዳት ይቻላል። ይሁን እንጂ ልንዘነጋው የማይገባ ነገር ቢኖር ሑሰይን በዚህ አቋም ላይ አይደለም የሞቱት። ቀጣዩን ነጥብ እንመልከት። [ለ]፦ የሑሰይን የመጨረሻ አቋም ሑሰይን መጨረሻ ላይ ሶስት ምርጫዎችን አቅርበው እንደነበር ይታወሳል። ወደ መካ መመለስ፣ ወደ ሙስሊሞች የጦር ግንባር መጓዝ፣ ወይም ደግሞ ወደ ሻም በመሄድ ለየዚድ ቃል ኪዳን መግባት። ይሄ ሃሳብ ተደጋግሞ ቢነሳም በዑበይዱላህ ብኑ ዚያድ ግትርነት ሳይሳካ ቀርቷል። የሆነ ሆኖ ይሄ የከሸፈ ድርድር ሑሰይን ከመካ የተነሱበትን አቋም እንደቀየሩ ያሳያል። ስለዚህ የሞቱት በወጡበት አቋም ላይ አይደለም ማለት ነው። ከሑሰይን ግድያ ጋር በተያያዘ ሶስት የተራራቁ አቋሞች ተንፀባርቀዋል። 1. የናሲባ አቋም፦ ናሲባ ማለት ለነብዩ ﷺ ቤተሰቦች ጥላቻን የደቀኑ ጭፍራዎች ናቸው። እነዚህ አካላት የሑሰይን ግድ ያ ልክ ነው ባይ ናቸው። ምክንያታቸው ሑሰይን የሙስሊሞችን ህብረት ሊከፋፍል የተነሳ አማፂ ነው የሚል ነው። ማጠናከሪያም “በአንድ ሰው ላይ ውሳኔያችሁ ከተስማማ በኋላ ህብረታችሁን ሊበትን የሚመጣን ሰው ማንም ቢሆን ግደሉት” የሚለውን ሐዲሦ ያጣቅሳሉ። [ሙስሊም፡ 1852] ሑሰይን የሙስሊሞችን ህብረት ሊከፋፍል በመነሳቱና ነብዩ ﷺ በዚህ መልኩ የተነሳን አካል “ማንም ቢሆን ግደሉት” እስካሉ ድረስ ግድያው ተገቢ ነው ይላሉ። እነዚህ አካላት የሑሰይን የመጨረሻ ጥያቄዎች ላይ አይናቸውን የሚጨፍኑ ናቸው። 2. የሺዐ አቋም፦ እነዚህ ደግሞ ሑሰይን ሊታዘዟቸው የሚገባ ኢማም ነበሩ። ስለሆነም ኺላፋው (መሪነቱ) ለሳቸው መሰጠት ነበረበት የሚሉ ናቸው። በዚህ አቋማቸው ላይ የማይጋራቸውን ሑሰይንን በመጥላት ይወነጅላሉ። ሰዎችን ስሜት ውስጥ የሚከቱ ልጓም አልባ ሃሰተኛ ዘገባዎችን በገፍ ይለቃሉ። ዘገባዎች ውስጥ ጤነኛና ሃሰተኛ እንዳለ የማያውቁ አላዋቂዎች የአህለ ሱና ዑለማዎች በሑሰይን ጉዳይ ከግፈኞች ጎን እንደቆሙ አድርገው ይወነጅላሉ። ይሄ የሺዐዎችና የአንዳንድ ጥራዝ ነጠቆች መታወቂያ ነው። ሊሰመርበት የሚገባ ነገር ቢኖር ሑሰይን ኸሊፋ አልነበሩም። ከኤሺያ እስከ አፍሪካ ከተንጣለለው የሙስሊሙ አለም ውስጥ ኩፋ ላይ ከታየው ውጭ ለሳቸው ቃል የገባ #አካባቢ የለም። መቼስ በተግባር ሳይገኝ የነብዩ ﷺ ቤተሰብ በመሆናቸው ብቻው ኸሊፋ ሆነው ነበር አይባል ነገር። “የዚድ አመፀኛ ስለነበር በሱ ላይ መውጣት ተገቢ ነው” ይላሉ። እንደማጠናከሪያም ሑሰይንን ገድሏል፣ ወደ መካና መዲና ጦር ልኮ ጥፋት ፈፅሟል ይላሉ። ይሄ የታሪካዊ ክስተቶችን ቅደም ተከተል ማደባለቅ ነው። ምክንያቱም ሑሰይን በየዚድ ላይ ሲወጡ እነዚህ ጥፋቶች በጊዜው አልነበሩምና። ሁሉም ኋላ የተፈፀሙ ክስተቶች ናቸው። ኋላ የመጡ ጉዳዮችን ቀድሞ ለተፈፀመ ክስተት ማመሀኛ (Justification) አድርጎ ማቅረብ ከፍትህ የራቀ ሙግት ነው።
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
↪️ ክፍል 1
↪️ ክፍል 2
↪️ ክፍል 3
↪️ ክፍል 4
↪️ ክፍል 5
↪️ ክፍል 6
↪️ ክፍል 7
↪️ ክፍል 8
↪️ ክፍል 9
↪️ ክፍል 10
↪️ ክፍል 11
➡️ SadatKemal Abu Meryem
"ጅን አውድቅና ፈውሱ" pdf ከሩቃ ሸርኢያ ጋር የተያያዙ ፈትዋዎችን ለሚፈልግ!! ⬇️▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬⬇️ ከሸይኽ ሷሊህ ብን ፈውዛን ብን ዓብዲላህ አል`ፈውዛን ሃፊዞሁሏህ ፈታዋ ተወስዶ በአማረኛ የትርጉም ፅሑፍ የተዘጋጀ ። ▪️በቻልነው ሁሉ ለሌሎች እንዲደርስ የበኩላችንን እናበርክት:: 👇┈┈┈•••✿❒👇❒✿•••┈┈┈👇 https://t.me/alruqyehsheriyeh https://t.me/alruqyehsheriyeh
Show all...
ብሩን በባንክ አስቀምጦ ያለበትን የሰው እዳ የማይከፍል ሰው የሚገርም ፍጡር ነው። ገንዘቡን የአራጣ ተቋም እየተጠቀመበት ባለ ሐቁን መበደል መዘዙ የከፋ ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል :- يُغْفَرُ لِلشَّهِيدِ كُلُّ ذَنْبٍ، إِلَّا الدَّيْنَ "ለሸሂድ ሁሉም ወንጀሉ ይማርለታል፣ እዳ ሲቀር!" [ሙስሊም፡ 1886] ህይወትን አሳልፎ ለሰጠው ሸሂድ እንዲህ ከተባለ ለኛ ብጤው ምን ይባላል?! Ibnu Munewor = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Show all...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

10:55
Video unavailableShow in Telegram
ይሄንን የሺዓዎች ጉድ ተመልከቱ ጉድ ብላቹህ አታበቁም ቡዙ አይነት ውዱእ አደራረግ አለ እያለ ሲያስተምር በዛውም ትስቃላቹህ። t.me/abumuazhusenedris
Show all...
መንገድ ዳር ሎሚ፣ጎመን እየቸረቸረች ያለችዋ ሴት ፣ጫማ እየጠረገ ያለው ወጣት ኢማን ፣ ተቅዋ ካለው የአላህ ወልይ ነው ! የወልይን ማዓና አንሻፈው ለሚተረጉሙት አድርሱላቸው። 🎙 በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላህ https://t.me/Darutewhide
Show all...
❝የሙሴ ጽላት ከኢሰራኤል #ተሰርቆ መጥቶ በአክሱም አለና የተቀደሰች መሬት ናት❞ ይሉሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (ወንጌል) የሚለው መስረቅ (ስርቆት) ሃጢያት (ወንጀል) እንደሆነ ያስተምራል። “እንግዲህ አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርምን? አትስረቅ ብለህ የምትሰብክ #ትሰርቃለህን?” — ሮሜ 2፥21 “አትስረቅ።” — ዘጸአት 20፥15 “አትስረቅ።” — ዘዳግም 5፥19 “... አትስረቅ፥ ፥” — ማቴዎስ 19፥18 “...አትስረቅ፥ ።” — ማርቆስ 10፥19 ነገር ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ኦርጂናሉን የሙሴን ታቦት ሰርቄ አምጥቼ አክሱም ፅዮን አስቀምጬዋለሁ ብላ ህዝቡን ታሳስታለች። አክሱም የሙሴ ጽላት ከእሰራኤል ሃገር #ተሰርቆ መጥቶ አለና አክሱም የተቀደሰች መሬት ናት ይሉሃል። ✅የተሰረቀ ነገር ለቅድስና እንዴት ያገለግላልን? ✅እውነት ጽላቱ ኢትዮጵያ ካለ ኢስራኤል ንብረቷን አስመልሳ ትልቅ የቱሪስት ገቢ ታገኘበት ነበርኮ። ✅ደግሞስ ከ 10ቱ ትዕዛዛት አንዱ #አትስረቅ አይደል ሚለው? ታቦት ከእስራኤል ተሰርቆ ኢትዮጵያ ይገኛል ማለት ከመጽሐፉ ጋ አያጋጫችሁም? ታቦቱ መቼ? እና እንዴት? እንደተሰረቀ እንደሚከተለው ተዘግቧል። የተሰረቀው የቃልኪዳኑ ታቦት‼ የቃልኪዳኑ የሙሴ ታቦት የት ነው ሚገኘው? የቃል ኪዳኑ ታቦት በቀዳማዊ ምኒልክ በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት ተሰርቆ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በአክሱም ይገኛል ትላለች ቤተክርስቲያን ማለትም በአፈታሪክ፣ በተረተረት። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ በተቃራኒው ታቦቱ ወደ ባቢሎን #ተሰርቆ እንደተወሰደ ይነግረናል፡፡ በጣም የሚገረም ነው፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እንኳን መስማማት አልቻሉም፡፡ “እግዚአብሔርን የሚያገለግሉበትን ንዋየ ቅድሳቱን ጥቃቅኑን እና ታላቁን ዕቃ ሁሉ የግዚአብሔር ማደሪያ ታቦትንም ከቤተ መንግሥት እቃ ቤትም ያለውን ሳጥኑንም ሁሉ ማርከው ወደ ባቢሎን ወሰዱ። (እዝራ ካልዕ1:54) “ቅዱሱን ታቦት የእሥራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ባሰራው ቤት ውስጥ አኑሩት ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም” (2ዜና ምዕራፍ 35 ቁጥር 3 ) ኢዮስያስ ለሰሎሞን #አሥራ #ስድስተኛ ንጉስ ነበር ። ከእዮሲያ በኋላ የነገሰው ሴዴቂያስ ነበር የባቢሎን ምርኮ ከኢዮስያስ ዘመን በኃላ ተጀምሮ በሴዴቅያስ ዘመን ተፈጽሟል። በባቢሎን የምርኮ ዘመን የነበረው ነቢይ ኤርምያስ ነበር። (ኤር 1:1-5) የሀገራችን ጭፍን የተረትና የውሸት ንጉሶች በሰሎሞን ጊዜ ታቦቱ ተሰርቆ መጥቷል ሲሉ መጽሐፍ ቅዱስ ግን ወደባቢሎን ተማርኳል ይላል። ታዲያ ከዚህ በላይ ምን ቅዠት አለ? ሰለሞን በእስራኤል ሶስተኛ ንጉስ ሲሆን ሴዴቂያስ ደግሞ ለሰለሞን 21ኛ ንጉስ ነበር፡፡ የኦርቶዶክስ የውሸት ክምር ሀሰታዊ መረጃ ውድቅ ይሆናል፡፡ ታቦት በሰለሞን ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል ካላችሁ መረጃ ስትባሉ ለምን ወገቤን ትላላችሁ? ለምንስ በቀጥታ አትመልሱም? ለምን መረጃ መስጠት ይሳናችኀል፡፡ ውሸት ለካ እንዲህ ያሳፍራል፡፡ ለማንኛውም ወደ ኢትዮጰያ ምንም ዓይነት ታቦት አልመጣም፡፡ ምንም እንኳን የሀሰት ወሬቸውን አግጦ ብናየውም ታቦቱ በልጅ ሰለሞን ዘመን ወደ አክሱም ሊመጣ አይችልም፡ ምክንያቱም ከሰለሞን በኋላ ንጉስ በነበረው ኢዮሲያ በእሱ ዘመን ወደ ባቢሎን የተወሰደው ዘመን ተማርኮ ስለነበር፡፡ የባቢሎን ምርኮ ከኢዮስያስ ዘመን በኃላ ተጀምሮ በሴዴቅያስ ዘመን ተፈጽሟል። ሴዴቂያስ ለሰለሞን 21ኛ ንጉስ ነው፡፡ ታዲያ የሙሴ የቃል ኪዳን ታቦት በ21ኛው ንጉስ በሴዴቂያስ ጊዜ ከነበር በሰለሞን ጊዜ ወደ ኢትዮጰያ ተሰርቆ መጥቷል የሚለው የቅዠት ነው ማለት ነው፡፡ በሰለሞንና በሰዴቄያስ መካከል የነበረው የዓመታት ልዩነት ደግሞ ሶስት መቶ ሃምሳ ዓመት ነበር፡፡ ይህ ደግሞ የዚህን ተረት አፈር ከድሜ ያበላዋል፡፡ ወደጥያቄያችን ስንመለስ‼ ✅የተሰረቀ ነገር ለቅድስና እንዴት ያገለግላልን? ✅እውነት ታቦቱ ( ጽላቱ) ኢትዮጵያ ካለ ኢስራኤል ንብረቷን አስመልሳ ትልቅ የቱሪስት ገቢ ታገኘበት ነበርኮ። ✅ደግሞስ ከ 10ቱ ትዕዛዛት አንዱ #አትስረቅ አይደል የሚለው? ✅እውነት ታቦቱ ተሰርቆ ሀገራችን አለብንልንኳ የተሰረቀው 1 ታቦት ሆኖ ሳለ ይህ ሁሉ 44 ታቦት ከየት መጣ? ✅ታቦት ከእስራኤል ተሰርቆ ኢትዮጵያ ይገኛል ማለት ከመጽሐፉ ጋ አያጋጫችሁም? ምንጭ:- ትግራይ ሙስሊም ሚዲያ
Show all...
ሑሰይን በከርበላእ አሳዛኙ ፍፃሜ ~ ሑሰይን ከርበላእ የተሰኘ ቦታ ደረሱ። የቦታውን ስም ሲጠይቁ “ከርበላእ” አሏቸው። “ከርቡን ወበላእ” አሉ፣ ጭንቀትና መከራ! በሰዕድ ብኑ አቢ ወቃስ ልጅ ዑመር የሚመራ 4 ሺ ጦር ከቦታው ደረሰ። ሑሰይንን ወደ ኩፋ ዑበይዱላእ ብኑ ዚያድ ዘንድ እንዲሄዱ አናገራቸው። ወደ ኩፋ እንዳይሄዱ ወይም ከመንገድ እንዲመለሱ በተደጋጋሚ ቢጠየቁ ፈቃደኛ ያልሆኑት ሑሰይን ጉዳዩ ከባድ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ሲያስተውሉ መለሳለስ አሳዩ። ለዑመር ሶስት ምርጫ አቀረቡ። 1ኛ፦ ወደ መካ እንድመለስ ተወኝ 2ኛ፦ ወይም ከሙስሊሞች የጦር ግንባሮች ውስጥ ወደ አንዱ ልሂድ 3ኛ፦ ወይ ደግሞ ወደ ሻም ልሂድና ለየዚድ ቃል ኪዳን ልግባ። ዑመር ተስማማ። የተስፋ ጭላንጭል የታየ መሰለ። “አንተ ወደ የዚድ ላክ። እኔ ደግሞ ወደ ዑበይዱላህ ብኑ ዚያድ ልላክ። የሚሆነውን እንይ” አላቸው። ምን ዋጋ አለው? ሑሰይን ወደ የዚድ መልእክት ሳይልኩ ቀሩ። ዑመር የራሱን ድርሻ ተወጣ። ወደ ዑበይዱላህ ብኑ ዚያድ ላከ። ዑበይዱላህ ብኑ ዚያድ የቀረቡለትን ምርጫዎች ተቀበለ። ሑሰይን ከሶስቱ ምርጫዎች ያሻቸውን እንዲመርጡ ተስማማ። አፍታም ሳይቆይ ግን ውሳኔው ተቀየረ። ሸሚር ብኑ ዚልጀውሸን የተሰኘ ክፉ አማካሪ ጣልቃ ገብቶ “በጭራሽ! ላንተ ፍርድ እጅ መስጠት አለበት” አለው። እሱም ይህን ሲሰማ አጉል ነፍሲያ ያዘውና “ልክ ነው። በኔ ፍርድ ስር መሆን አለበት” ብሎ ተነሳ። ራሱን ሸሚርን ወደ ዑመር ሄዶ ጉዳዩን እንዲያስፈፅም፣ ዑመር ብኑ ሰዕድ ካልተስማማ የጦሩን አመራር ከሱ እንዲወስድ ነግሮ ላከው። የተስፋው ጭላንጭል ተዘጋ። ሑሰይን ውሳኔው ደረሳቸው። “በጭራሽ ወላህ! ፈፅሞ ለዑበይዱላህ ብኑ ዚያድ ፍርድ እጅ አልሰጥም” አሉ። የኩፋው ጦር 5ሺ ደርሷል። ከሑሰይን ጋር ያለው 72 ፈረሰኛ ብቻ ነው። ፊት ለፊት ተፋጠጡ። ፍፁም በማይመጣጠኑበት ሁኔታ “ሁለቱ ጦር ተፋጠጡ” ማለት ስሜት ይሰጥ ይሆን? ብቻ የሆነው ይሄው ነበር። ሑሰይን ከፊታቸው የተሰለፈውን የሸሚርን ጦር መገሰፅ ያዙ። “የኔን አምሳያ መዋጋት ለናንተ ይበጃል ወይ? እኔኮ የነብያችሁ የልጅ ልጅ ነኝ! ከኔ ውጭኮ ምድር ላይ ሌላ የነብይ የልጅ ልጅ የለም። በርግጥም የአላህ መልእክተኛ ﷺ እኔንና ወንድሜን ‘እነዚህ የጀነት ወጣቶች አይነታዎች ናቸው' ብለዋል” አሉ። ደጋግመው ገሰፁ። ዑበይዱላህ ብኑ ዚያድን ትተው ከሳቸው ጎን እንዲሰለፉ አሳሰቡ። ሰላሳ ሰዎች አካባቢ ወደሳቸው ተቀላቀሉ። ከነሱ ውስጥ አንዱ አንድ ሺ ጦር ይዞ ወደ ኩፋ እንዳይሄዱ ሊያግዳቸው ሲሞክር የነበረው ሑር ብኑ የዚድ ነው። እንዴት ከኛ ጋር መጥተህ ወደ ሑሰይን ትሄዳለህ ቢሉት “ወዮላችሁ! ወላሂ እኔ ነፍሴን ከእሳትና ከጀነት ነው እያስመረጥኳት ያለሁት። ብቆራረጥ፣ ብቃጠል እንኳ በጀነቴ ላይ ሌላን አልመርጥም!” አላቸው። ከዚህ በኋላ ሑሰይን የዙህርና የዐስር ሶላቶችን ሰገዱ። የሚደንቀው ግን የዑበይዱላህ ብኑ ዚያድ ጦር ጭምር ሑሰይንን ተከትሎ ነበር የሰገደው። ግራ የገባ ነገር። መግባባቱ ግን ፈፅሞ ሊገኝ አልቻለም። በዚሁ ሁኔታ ላይ መግሪብ ደረሰ። የዑበይዱላህ ብኑ ዚያድ ጦር ፈረሰኞች ወደ ሑሰይን ገስግሰው መጡ። “ምን ፈለጋችሁ?” “ወይ ለዑበይዱላህ ብኑ ዚያድ ፍርድ ይደር፤ ካልሆነ ይዋጋ።” ሑሰይን “ይቺን ሌሊት ጊዜ ስጡን፣ ለጌታዬ ልስገድ” አሉ። ሌሊቱን በሶላት፣ በኢስቲግፋር፣ በዱዓእ አሳለፉ። እለተ ጁሙዐ! ሌሊቱ ለንጋቱ ቦታው ሲለቅ ጦርነቱ ተቀሰቀሰ። የሑሰይን ጭፍራዎች ይህንን የማይመጣጠን ጦርነት መቋቋም እንደማይችሉ ያውቁታል። ስለዚህ ብቸኛ ምርጫቸው ከሑሰይን ፊት መሞት ብቻ ሆነ። እስከ ደም ጠብታ እየታገሉ አንድ ባንድ ወደቁ። ሁሉም አለቁ። ሑሰይን ረዲየላሁ ዐንሁ በጊዜው ታሞ ከነበረ ልጃቸው ዐሊይ (ዘይኑል ዓቢዲን) ጋር ብቻቸውን ቀሩ። ምነው የደረሰው እልቂት በዚህ በበቃ! ፍልሚያው አልቆመም። ግና ማንም ሑሰይንን መጠጋት አልደፈረም። ማናቸውም ሑሰይንን ረዲየላሁ ዐንሁ በመግደል ራሳቸውን ፈተና ላይ መጣል አልፈለጉም። ሙሉ ቀን በዚህ ሁኔታ አለፈ። የጦሩ መሪ፣ የዑበይዱላህ ብኑ ዚያድ ክፉ መካሪ ሸሚር ብኑ ዚልጀውሸን መጥቶ “ከባችሁ ግደሉት” ብሎ አምባረቀባቸው። ከበባ አደረጉ። ሑሰይን ብኑ ዐሊይ ሰይፋቸውን ይዘው አንበሳ ሆነው መሀላቸው መንጎባለል ይዘዋል። ሊቀርቧቸው ከሞከሩት ውስጥ የተወሰኑትን ጣሉ። ግና “ካንድ አንበሳ ሁለት ኮሳሳ” ነው ነገሩ። ብዛት ጀግንነትን ይረታ። ሸሚር አሁንም ጮኸ! “ወዮላችሁ! ምንድን ነው የምትጠብቁት? ተቀደሙ!” አለ። በቃ! አሳዛኙ ፍፃሜ እውን ሆነ! ምድር ላይ ብቸኛው የነብዩ ﷺ የልጅ ልጅ ሑሰይን ብኑ ዐሊይ ወደቁ! ይሄም አልበቃ! ጭንቅላታቸውን ቆርጠው ወደ ዑበይዱላህ ብኑ ዚያድ ወሰዱ። ዑበይዱላህ ብኑ ዚያድ ጭንቅላታቸው ከፊቱ ሲቀርብለት በያዘው እንጨት አፋቸውን እየነካካ፣ ወደ ውስጥ እየከተተ "ጥርሱ ያምር ኖራል ለካ" አለ። አነስ ብኑ ማሊክ ረዲየላሁ ዐንሁ በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉት፦ “ወላሂ! የአላህ መልእክተኛ ﷺ ይህንን በእንጨትህ የምትነካበትን ቦታ ሲስሙት አይቻለሁ” አሉ። በዚህ አሰቃቂ ጦርነት ሑሰይንን ጨምሮ ስድስት የዐሊይ ልጆች፣ ሁለት የሑሰይን ልጆች፣ ሶስት የሐሰን ልጆች፣ ሁለት የዐብደላህ ብኑ ጀዕፈር ልጆች፣ ቀደም ብሎ ኩፋ ላይ የተገደለውን ሙስሊም ብኑ ዐቂልን ጨምሮ አራት የዐቂል ልጆች አለቁ። ሑሰይን ወደ ኩፋ እንዳይሄዱ የወተወቱ ሶሐቦች የፈሩት ደረሰ። ቀድመው ያለቀሱበት፣ የወተወቱበት አስፈሪው፣ አስጨናቂው ጉዳይ ይሄው ልብን በሚያደማ፣ ቅስምን በሚሰብር አሳዛኝ ሁኔታ ተደመደመ። ኢብራሂም አነኸዒይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ “እኔ ከሑሰይን ገዳዮች ውስጥ ሆኜ ጀነት ብገባ ነብዩ ﷺ ፊቴን እንዳያዩኝ በፊታቸው ማለፍ አፍር ነበር።” [አልሙዕጀሙል ከቢር፡ ቁ. 2829] ርእሳችን አልተቋጨም። Ibnu Munewor = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Show all...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور