💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
Open in Telegram
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Show more8 767
Subscribers
-724 hours
-307 days
-7430 days
Posts Archive
فضل
: سبحان الله والحمدلله ولا إله إلا الله والله أكبرفضيلة الشيخ: #عبدالرزاق_البدر حفظه الله
⭕️👉አትራፊ እና ከሳሪ በመባል ሰው ለሁለት ይካፈላል!
አትራፊዉ፦ እነዚያ ያመኑ መልካም ስራዎችን የሰሩ በሀቅ (በእዉነት) በትግስት (በሶብር) ላይ የተመካከሩ ሲቀሩ ከዚህ ውጭ ያለው ሁላ በርግጥም ከሳሪ ዉስጥ ነዉ።
== t.me/https_Asselfya
- قَال صلَّى الله عليهِ وسلَّم:
سَبَقَ المُفَرِّدُونَ!
قالُوا: وَما المُفَرِّدُونَ يا رَسولَ اللهِ؟
قالَ: الذَّاكِرُونَ اللَّهَ كَثِيرًا، وَالذَّاكِرَاتُ.
- صَحيحُ مُسلِم
اَلسَّلَامُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللهِ وَبَرَكاتُهُ
🛑👉አድስ ማስታወቂያ
~
የኢብኑ ተይሚያ መርከዝ የአሻራ መጣያ ግሩፕ ረመዷንን አስመልክቶ ሙሀደራ እና ግሩፑም አስመልክቶ አንዳድ ነገሮች ፕሮግራም ተዘጋጅቷል !
√ ለዛሬ ቅዳሜ ምሽት↳ በሳዑድ 9:00 ስአት !
↳በኢትዮ 3:00 ስአት !
«በኢብኑ ተይሚያ መርከዝ የአሻራ መጣያ ግሩፕ ላይ ይጠብቁን ..!»
~
🎙በአቡ አብዲላሀ እና በአቡ አዩብ حفظهم الله
ላይቨ የሚሰራጭበት አድራሻ
↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/Merkez_Ibnu_Teymya2
https://t.me/Merkez_Ibnu_Teymya2🎙በዑስታዝ አብዱናስር መኑር
👉ርዕስ:- ተቅዋ
ጀ
መ
ረ
=
https://t.me/wru_ms_officialgroup?videochat
.
ሁለተኛው ፕሮግራም
ተ
ጀ
መ
ረ
🎙 الشيخ رشاد الورد الحبيشي
ሼይኽ ረሻድ አል-ሁበይሺይ ከሳዑዲ
ሼር ይደረግ 👇👇
የቀጥታ ስርጭት ሊንክ
https://t.me/sefinetunuh?livestream
https://t.me/sefinetunuh?livestream
Repost from አህሉ-ተውሂድ ኢስላሚክ ሴንተር - ሀርቡ
.
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ፕሮግራም
ተ
ጀ
መ
ረ
🎙الشيخ أول بن أحمد الخميسي
< ሼይኽ አወል አህመድ አል-ከሚሲይ>
ሼር ይደረግ 👇👇
https://t.me/sefinetunuh?livestream
https://t.me/sefinetunuh?livestream
⭕️👉ከረመዷን በፊት ልብን ማስተካከል
!!
. ~~~~
ረመዷን የሙእሚን የአኼራ ስንቅ የሚሠነቅበት ለረዠሙ ጉዞ ቀለብ የሚያዝበት (የሚሸመትበት )ወር ነዉ።~ይህ ታላቅ ወር ረመዷን ሸህሩ መغፊራ የአላህ ዉዴታ የሚገኝበት ይህን የተከበረ ወር ለመቀበል እሚደረጉ ዝግጅቶች ዉስጥ አንዱ ልብን ቀድሞ ማስተካከል ነዉ። ~አላህ ሱብሀነሁ ተአላ ከሙእሚኖች የሚፈልገዉ ትልቁ ስፍራ ልብ ነዉ እሚያየዉም እሱ ነዉ። በሁሉም አጋጣሚ ላይ ልቦች ከተስተካከሉ በሁሉም የኢባዳ አጋጣሚዎች ላይ የምናገኘዉ ድርሻ የላቀ ይሆናል።ልቦች ከተበላሹ መልፋቱ ፦መድከሙ፦ወጭ ማዉጣቱ ጥቅም አይኖረዉም። ሀጅ ካደረጉት ሠዎች ዉስጥ ይበልጥ በሀጁ ተጠቃሚ የሚሆነዉ በሀጁ ልቡ የተስተካከለለት ሠዉ ነዉ።ከፆመኛች ዉስጥ ፆም ጠቅሞታል የሚባለዉ ጾም ልቡን ያስተካከለዉ ሠዉ ነዉ። ቁርአንም፦ከዚክሩም፦ ከዱአውም ሠዎች ከማድረግ አንፃር የተለያየ ኢባዳዎችን ያደርጋሉ።ነገር ግን ከለፊዎች ሁሉ ተጠቃሚዉ በሠራዉ ስራ ልቡን ያስተካከለ ሰዉ ነዉ። ~ረመዷንን ልባችንን አስተካክለን ከተቀበል ነዉ ረመዷን ላይ የምንዘራዉ ዘር ፍሬ ያፈራል።ይፀናል።ለቀጣይ አመት ሙሉ ይጠቅመናል። የአላህ መልእክተኛ ከረመዷን እስከ ረመዷን ፦ከጁሙአ እስከ ጁሙአ ፦አምስት ወቅት ሰላት፦ መሀል ላይ የተሠራዉን ወንጀል ያሠርዛል። ይቅር ያስብላል ብለዋል። ረመዷኑ ያማረለት ሰዉ ያመት ወንጀሉ ይሠረዝለታል ።ስለዚህ ረመዷን አመታዊ የምግብ ለዉጥ ፦ያለባበስ ለዉጥ እምናደርግበት ጊዜ ሳይሆን. አመታዊ የልብ እድሳት ስራ እምንሠራበት ወር ሊሆን ይገባል።ይህ ይሳካ ዘንድ ልብን የማስተካከል አንገብጋቢነት ቀድመን ልናዉቅ ይገባል። ረመዷንን የምንቀበለዉ ፦በጀለብያ ፦በሽርጥ፦በፉስታን ፦በኩፍያ ፦በጥምጣም ፦በቤት አስቤዛ ሳይሆን አስቀድመን የአኼራ ዘር የምንዘራበትን ልባችንን በማፅዳት ፦በማስተካከል ሊሆን ይገባል። ልብን ሳያስተካክሉ በደመ ነፍስ በነሻጣ መልካምን ስራ መስራት ትርፉ ድካም ብቻ የሚሆነዉ።መልሰዉ ያበላሹታል ሠዎችን በመስደብ ፦የሠዉ ስም በማጥፋት ፦የሠዉ ስጋ በመብላት፦በመሠል ነገሮች ልብ ሳይስተካከል የተሠራ ስራ መልሶ ይበላሻል።የቂያም ቀን ጀነት የምንገባዉ የጀነት ደረጃዎች ላይ የምንወጣዉ ልብ ሲይስተካከል ነዉ። يَوْمَ لَا يَنفَعُ مَالٌۭ وَلَا بَنُونَ ~ገንዘብም ልጆችም በማይጠቅሙበት ቀን፡፡ إِلَّا مَنْ أَتَى ٱللَّهَ بِقَلْبٍۢ سَلِيمٍۢ ~ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ ገንዘብም ሆነ ልጅ የማይጠቅምበት ቀን ነዉ.የቂያም ቀን.. ማለት ልቡ ንፁህ ላልሆነ ሰዉ ነዉ።ልቡ ንፁህ የሆነለት ሠዉ ልብ ለተስተካከለለት ሰዉ ልጁም ገንዘቡም ዱአም ዚክርም መልካም ነገር ስልጣኑም ይጠቅመዋል። መሪዉ ስለተስተካከለ እሱን ተከትለዉ የሄዱ በሱስር ያሉ ነገሮች ሁሉ ለአኼራዉ የሚጠቅሙ ይሆናሉ።የንፁህ ልብ ባለቤት የቂያም ቀን ይድናል የሚባለዉ ልብ ፦ከሽርክ ሲፀዳ፦ በድን ላይ በአላህ ጉዳይ ላይ አኼራ ላይ ከጥርጣሬ ሲፀዳ ነዉ።ከምቀኝነት ፦ከኩራት ለሠዎች ሸር ከማሠብ ሲፀዳ ነዉ።ለአላህ ባሮች ኸይር ሲያስቡ እህቶቸ ወንድሞቼ ናቸዉ ብለዉ ሸርን ሲጠሉላቸዉ መልካምን ሲወዱላቸዉ ቅን ሲሆኑ ልብ ንፁህ ሆኗል ይባላል።የሠዉ ልጅ ልብ ከሠዉነት አካላቶች ይበልጥ ስስና ጥንቃቄ የሚያስፈልገዉ እሱ ነዉ።በጥሩዉም በመጥፎዉም ተጽእኖ ዉስጥ ይወድቃል ።ጥሩ ነገሮችም ልብ ላይ ተፅኖ ይፈጥራሉ በቀላሉ መጥፎ ነገሮችም ቶል ተጽእኖ ያሳድሩበታል አይናችንን ሳስተን ከምንብቀዉ በላይ ዉጫችንን ከምንጠብቀዉ በላይ የልባችን ዉስጡ እንዳይበላሸ አላህ እሚጠላዉ ነገር እንዳይገባበት ጥንቃቄ ልናደርግለት ይገባል። =http://t.me/https_Asselfya
በረመዳን ተጠቃሚ ከሚያደርጉን ነገሮች ውስጥ!ማብዛት ነው። ከዚክሮች ሁሉ በላጩ ደሞ ቁርአን ነው። ስለዚህ ከሌሎች ወራት በበለጠ በዚህ ወር ውስጥ ለቁርአን ሰፊ ቦታና ትኩረት እንስጥ።እናብበው ፣እናዳምጠው፣እናቅራውእንቅራው፣እናስተንትነው እንፈዘው፣ የተጅዊድ አህካሞችንም በመማር በማዳመጥ አቀራራችንን እናስተካክል። የተፍሲር ካሴቶችን (አሽሪጣዎችን) በማዳመጥ ትርጉሙን ለመረዳት እንሞክር። ቢያንስ አጫጭር ሱራዎችን እንኳን ትርጉሙን ለማወቅ እንሞክር። 🔹ቢያንስ ቁርአንን ካከተምክ ስንት አመት ሁኖሃል? ምሳሌ ካከተምክ 5 አመት ሁኖሃል እንበል አምስት አመት ሙሉ ስትቀራው ምን ያህል ትርጉሙን ተረድተሀዋል? እስኪ እራስህን ጠይቀው? እንዳው እንበልና በብዛት ሶላቶች ላይ እምንቀራቸው አጫጭር ሱራዎችን እንኳን ትርጉማቸውን እናውቅ ይሁን?? ‹‹ሊኢላፊ ቁረይሽ›› ‹‹አረአይተለዚ ››ኢና አእጦይና ››ማለት ምን ማለት ነው? «ቁል አኡዙ ቢረቢል ፈለቅ »ማለት ምን ማለት ነው? ? ሁሌ ፈርድም ላይ ሱናም ላይ በብዛት እኒህን ሱራዎች እንቀራቸዋለን። ግን ትርጉማቸውን አናውቅም ። ለምን ?? ‹‹የሚገርመው አለማወቃችን ሳይሆን ለማወቅ አለ መሻታችን ነው።›› ቱርጉሙን ካላወቅን ማስተንተን አንችልም። ካላስተነተነው ደሞ ልንለወጥበት ልንገሰፅበት አንችልም። ስለዚህ« إنما العلم باتعلم››‹ እውቀት የሚገኘው በመማር ነው። » ተብሏልና የእውቀት ሁሉ መጀመሪያና ቁንጮ የሆነውን ቁረአንን እንማር እንወቅ ። ወላሁ አዕለም منقل =http://t.me/https_Asselfya~~~~~~ ~ .[²] ዚክር
አቢ ሁረይራ አላህ መልካም ስራዉን ይወደድለትና የልብ ወዳጄ (صلى الله عليه وسلم) #በሶስት ነገር አደራ ብለውኛል።~በየወሩ ሶስት ቀን እንድፃም ~ሁለት ረከአ የዱሀ ሶላትን እንድሰግድና ~ከመተኛቴ በፊት ዊትርን እንድሰግድ ~
እንዴት እንሐፍዛለን?» ኡስታዝ አብዱ ረዛቅ ገብቷል ግቡና ተከታተሉ!
👇👇
https://t.me/fewaidabdurazaq?livestream
ናፈቀኝ ሀገሬ ጓራና ተራራዉ ጋራ ሸንተረሩ ...!ያደግንበት ሀገር ያ የገጠር ምድሩ ተራራዎች ወንዞች መልከ መልካም ምድሩ ቦርቀን ያደግነዉ በጨፌ በባህሩ ቡቃያዉ አብቦ በዉበት ሲያበሩ አበቦች አፍርተዉ እሸት ሲያጓመሩ ድንቅ ዉበት ነበረዉ ያ የገጠር ምድሩ ሀገሬን እያሠብኩ ልቤ መዋተቱ ዛሬ ነገ እያልኩኝ ገደለኝ ናፍቆቱ ~
🔖
~~~~
« ¹»
መጀመሪያ ረመዳንን በአግባቡ ለመጠቀም ቆራጥ መሆን ይኖርብናል። ይህ ረመዳን ብዙዎች ተመኝተውት ያጡት ለኛ የተሰጠ ትልቅ ኒእማ መሆኑን አውቀን ልንጠቀምበት ይገባል። ስንትና ስንት አሉ አምና እኛው ጋር የፆሙ እኛው ጋር ተራዊህ የሰገዱ ዘንድሮ ረመዳንን ያላገኙ ። የእኛም ድርሻ የዘንድሮው ብቻ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ በአግባቡ እንጠቀምበት ።የቀጣይ ረመዳን ላላገኝ እችላለሁ ብለን እንሰብ። የዘንድሮውን እራሱ ላንጨርሰው እንችላለን ።ስለዚህ ያለንባትን ሰአት ሳስተን ቆጥበን እንጠቀምባት። ወላሂ ነው የምላችሁ ረመዳንን ማግኘት ትልቅ የሆነ ኒዕማ ነው። ያጣው ሰው እንጂ አያውቀውም። የሚገርመው ግን ረመዳንን ከሌላው ወር የተሻለ አድርጎ የማያየው ብዙ አለ። ምላሱ ያልፆመ ፣አይኑ ያልፆመ ፣ጆሮው ያልፆመ ብዙ አለ። ረመዳን ከሌላው ወር የሚለየው ባለ መብላትና ባለ መጠጣት ብቻ የሚመስለው ብዙ አለ።ምናልባት የረመዳንን አዳብ ባለማወቅ ሊሆን ይችላልና እናስታውሳቸው እንምከራቸው ። በቀጥታ መምከር የማይቻል ከሆነ ስለ ረመዳን አዳብ የሚያወሩ ሙሀደራዎችን ፣ፁሁፎችን በመላላክ በረመዳን መጠቀምም ማስጠቀምም እንችላለን። በረመዳን ለመጠቀም ከሚረዳን ነገር አንዱ ፆም የተደነገገበትን አላማ ማወቅ ነው። እሱም አላህን እንድንፈራ ነው ።«لعلكم تتقون» ብሎናልና።የተደነገገበት አላማ አላህን ለመፍራት መሆኑን ስናውቅ እንፈረዋለን ማለት ነው። ስንፈራው ደሞ እንገዛዋለን።ስንፈራው ምላሳችንን እንጠብቃለን። ስንፈራው ጆሮያችንን እንጠብቃለን ማለት ነው።ስለዚህ የተፈለገበት አላማ ላይ ስናውለው ተጠቃሚዎች እንሆናለን።
∆አላህ ከረመዳን ተጠቃሚዎች ያድርገን።
منقل
= t.me/https_Asselfya
ረመዳንን በአግባቡ ለመጠቀም!
🪷ሀይእ !
ሀያእ ማለት መንገድ ላይ አገት ደፍቶ መሄድ ብቻ አይደለም ሀያእ ከምንሰራቸው መጥፎ ስራዎች በገሀድም ሆነ በድብቅ አላህንም መፍራት ማፈርም ጭምር ይይዛል ሀያእ የኢማን ቀንዘል ነው።
ኢማን በልብ ብቻ ማመን አይደለም ተግባርም ጭምር ይጠይቃል የታዘዝነ መታዘዝ የተከለከልነው መከልከል ይይዛል ሀያእ ከአላህም ሆነ ከሰዎች ከምንሰራቸው መጥፎ ነገሮችን መታቀብም ጭምር ይይዛል።"
✍እሙ ሒባ
ኪታቡ አስ_ሲያም ከዑምደቱል አህካም
~
𝐏𝐝𝐟 ፦ t.me/https_Asselefya1/18115
ክፍል ① t.me/https_Asselefya1/18116
ክፍል ② t.me/https_Asselefya1/18183
ክፍል ③ t.me/https_Asselefya1/18213
ክፍል ④ t.me/https_Asselefya1/18234
ክፍል ⑤ t.me/https_Asselefya1/18296
🎙𝐔𝐬𝐞𝐭𝐚𝐳 𝐌𝐮𝐡𝐚𝐦𝐦𝐞𝐝 𝐒𝐢𝐫𝐚𝐣𝐞 ʰᵃᶠⁱᶻʰᵘˡˡᵃʰ
