en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

Open in Telegram

💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።

Show more
8 745
Subscribers
-824 hours
-447 days
-10430 days
Posts Archive
✅ በመስጠት ውስጥ ሁሌም  እረፍት አለ ። የሚወጣው ሁሉ ከኛ  ነውና የሚቀልልን ሸክምና ደስታ የሚሰጥ ስሜት እናገኛለን። መስጠትን ሁሌም ከመኖር ጋር አናያይዘው ምናለኝና ምን እሰጣለሁ አንበል እኛ ካለን በቂ ነውና ። ~ለጨነቀው ሰው መልካም ቃልን በመናገር ማረጋጋት መስጠት ነው ። ያዘነንም ማፅናናት መስጠት ነው ። መንገድ  መሻገር ያቃተውን ደካማ ማሻገርም መስጠት ነው። የሚፈልገውን ቦታ መጠቆምም መስጠት ነው ። ~ ለመስጠት ቀና ልቦና ብቻ ነው የሚያስፈልገው ይሄ አይጠቅምም አለማለት እና  የቻልነውን መስጠት ነው ያለብን ። ይሄ ሁሉ የምናደርገው እኛ ሰው በመሆናችን ነው  ይሄ ደሞ ገንዘብ ከመስጠትም በላይ  እራስን ለሌላው ማካፈል ነው ። ያ ያደረግንለት ሰው በእኛ ቀናነት ሲደሰት መዋልና ስለመልካምነት ሲናገር መስማት  ይሄም ለካ ሰውን መርዳት ነው ብሎ ያን ለመተግበር  ልቡን ሲያስገዛ እንደማየት ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ ? ~ከዚህ በላይ መስጠትስ ምንድነው ?  ገንዘብ ስለሌለን መስጠት አንችልም አንበል  ። ለምትወዳቸው ጊዜህን ስጣቸው! ለተጨነቁ ጆሮህን ስጥና አድምጣቸው! ግራ ለገባቸው ሀሳብህን አካፍላቸው! አንድ  በውሃ  ጥም  ዝሎ ሊወድቅ የደረሰን ሰው ገንዘብ ብታሸክመው  ህይወቱን አታድንለትም ። ገንዘብ የለኝምና መስጠት አልችልም ብለህ ብትተወውም  ይሞታል  ።ግን ያለህን አስበህ   ከጓዳህ ካለው ውሃሀ  አንድ ኩባያ ብታጠጣው  ህይወቱን ታተርፍለታለህ ስለዚህ የሚሰጠው ብር ብቻ አይደለም ። ለመስጠት የገንዘብና የቁስ ባለቤት መሆን ሳይሆን የሚጠበቅብን  ቀና ህሊና እና ሰጪ ልብ  መስጠትን አለማማረጥ  የቻልነውን ሰጪ መሆን እንዳለብን  የሚቀበል  ማንነት  ነው የሚያስፈልገን አላህ  ከሁሉም የነዚህ ባለቤት ያርገን ።~እናማ ስጥ ይጨመርሀል ~ስጥ ይሰጥሀል ~ስጥ ይመነዳሀል። ~ t.me/https_Asselfya

✅ ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ነው፡፡ አላህን ፈሪዎች ብቻ ሲቀሩ፡፡ ~መልካም ቆዩልኝ..!

~አንዳንዴ ..... ~ስጠፋ ፈላጊ ~ስዘናጋ አጠናካሪ ~እንቅራ... እንሞጣጠል ... የትነሸ የትጠፋሸ . የሚሉ ከስጋ ዝምድና በላይ የአላህ ገመድ ብቻ ያስተሳሰረን ዉድና ዉብ የሱና እህቶች ስላሉኝ
~አንዳንዴ ..... ~ስጠፋ ፈላጊ ~ስዘናጋ አጠናካሪ ~እንቅራ... እንሞጣጠል ... የትነሸ የትጠፋሸ . የሚሉ ከስጋ ዝምድና በላይ የአላህ ገመድ ብቻ ያስተሳሰረን ዉድና ዉብ የሱና እህቶች ስላሉኝ አልሀምዱሊላህ። ~

~እውነተኛ ጓደኛ… በህይወት ውስጥ ሁሉም ሰው የሚመኛው ነገር ቢኖር ጥሩና እውነተኛ የህይወት ዘመን ጎደኛ ነው።   እውነተኛ ጓደኛ ፦ # በህይወት ውጣ ወረድ ከእኛ ጋር የሚሆኑ፤ #  ጥሩ ያልሆነ ነገር ሲያዩ እኛን ለመመለስ በሚቻልበት ሁኔታ የሚመክሩን፤ # በእኛ ደስታ ከእኛ በላይ የሚደሰቱ፤ #  የውስጣችንን እና የከበደንን የምንነግራቸው፤ # ለእኛ የሚጠቅም እነሱ የሚያውቁት ነገርግን እኛ የማናውቀው ነገር የሚያሳዩን... እንዲህ የመሳሰሉት ባህሪና ስብዕና አላቸው። እንዲህ አይነት ጎደኛ ማግኛት የሚከብድ ነገር ቢሆንም እኛ ግን ለሌሎች እንዲህ አይነት ጎደኛ መሆን አለብን ብዬ አስባለሁ። እውነተኛ ጓደኛ የሀሩሩ ዘመን ጥላ እና የደስታክ ደግሞ ካባ ናቸው። t.me/https_Asselfya

✅ ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸዉና እንዲህ ብለዋል :- " ልብህን ሶስት ቦታ ላይ ፈልገው , ➀}}ቁዓን ስትሰማ ⓶}}አላህ በሚወሳበት ቦታ ⓷}}አንተና አላህ ብቻ በምትሆኑበት ጊዜ በእነዚህ ቦታዎች ላይ ካላገኘኸው አላህ ልብ እንዲሰጥህ ጠይቀው ምክንያቱም ልብ የለህምና " 📕(አል ፈዋኢድ (148)    ~    t.me/https_Asselfya

🔍አብደላህ ኢብኑ መስኡድ እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል። ✅ ሙስሊምን መስደብ ፊስቅ (አመፅ ነው)። 📚(ቡኻሪ ዘግቦታል)። t.me/https_Asselfya

﴿ وَاذْكُر رَّبَّكَ إِذَا نَسِيتَ وَقُلْ عَسَىٰ أَن يَهْدِيَنِ رَبِّي لِأَقْرَبَ مِنْ هَٰذَا رَشَدًا ﴾ - «سُبْحَانَ اللهِ» - «الحَمْدُ للهِ» - «لَا إلَهَ إلَّا اللهُ» - «اللهُ أكْبَرُ» - «سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ» - «سُبْحَانَ اللهِ العَظِيمِ» - «لَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إلَّا بِاللهِ» - «أسْتَغْفِرُ اللهَ وَأتُوبُ إلَيْهِ» - «لَا إلَهَ إلَّا أَنْتَ سُبْحَانَكَ إنِّي كُنْتُ مِنَ الظَّالِمِينَ» ~~

~እቅድ የነደፍሽ ለት ከሆነ ይሆናል ካልሆነም የራሡ ጉዳይ ብለሽ መንገድን አትጀምሪ። ምንም ቢፈጠር በአላህ ፍቃድ አሳካዋለሁ በሚል ወኔ እና ተስፋ ጉዞሽን ጀምሪ! የሆነ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር ልቅር
~እቅድ የነደፍሽ ለት ከሆነ ይሆናል ካልሆነም የራሡ ጉዳይ ብለሽ መንገድን አትጀምሪ። ምንም ቢፈጠር በአላህ ፍቃድ አሳካዋለሁ በሚል ወኔ እና ተስፋ ጉዞሽን ጀምሪ! የሆነ  ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር ልቅር ልሂድ እያልሽ የምታንገራግሪ  ልፍስፍስ አትሁኚ! ይልቁንስ  የፈተና መብዛት የማይገነድሳት ፅኑ ሁኚ . . አትርሺ ሙዕሚን ሊወዘወዝ ይችላል ግን በፍፁም አይገነደስም።

~ዑመር ኢብኑል ኸጧብ (ረዲየ‘ሏሁ ዓንሁ) እንዲህ አሉ:- «የአንድን ሰው ምንነት ማወቅ ከፈለግክ ሶላትና ፆሙን ሳይሆን እውነተኝነቱንና ታማኝነቱን ተመልከት»። ~~

ከተፈበረከ ቅርብ አመታትን ባስቆጠረው በለተሞ ጀማዓ የተሸወዳችሁ ካላችሁ ሀቁ በበለጠ ይበየንላችሁ ዘንድ  በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላህ ከመረጃ ጋር በራሳቸው ምስል ፣ በራሳቸው ድምፅ እንዲሁም በራሳቸው ፁሁፍ አያይዞ በተከታታይ ያቀረባቸውን ፅሁፎች አንብቡ። የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች ..!! ክፍል - 1 ⬇️ t.me/IbnuMunewor/5350 ክፍል -2 ⬇️ t.me/IbnuMunewor/5352?single ክፍል -3 ⬇️ t.me/IbnuMunewor/5362 ክፍል - 4 ⬇️ t.me/IbnuMunewor/5370

ሐይቅ መርከዝ አስሱና የግንባታ ማዕከል وتعاونوا على البر واتقوى ولا تعاونوا على الإثم والعدوان https://t.me/merkezassunah
ሐይቅ መርከዝ አስሱና የግንባታ ማዕከል وتعاونوا على البر واتقوى ولا تعاونوا على الإثم والعدوان https://t.me/merkezassunah

🔖ለሱብሂ ሰላት ባለቤቶች እንቅልፋሞች የማያገኙት ምርኮ አላቸው ! ~የሱብሂ ፈርዱ ብቻ ቀኑን ሙሉ የአላህ ጥበቃን ያሰጣል. ~ሱናዋ ደግሞ ዱንያና ውስጧ ካለው ነገር ሁሉ የተሻለች ምርጥ የተባለች ና
🔖ለሱብሂ ሰላት ባለቤቶች እንቅልፋሞች     የማያገኙት ምርኮ አላቸው ! ~የሱብሂ ፈርዱ ብቻ ቀኑን ሙሉ       የአላህ ጥበቃን ያሰጣል. ~ሱናዋ ደግሞ ዱንያና ውስጧ ካለው      ነገር ሁሉ የተሻለች ምርጥ የተባለች ናት. ~የፈጅር ሰላት ቁርአንን ደግሞ እነዚያ      ምርጥ የሆኑት መላኢኮች የሚሳተፉበት      ነው። ~

~ተጋበዙልኝ🥀 ﴿أَمَّن يُجِيبُ الْمُضْطَرَّ إِذَا دَعَاهُ﴾.

~ፈገግግ በሉ ፈገግታ ሱና ነው! እኛ ሴቶችኮ ብልህ ነን ስንል በምክንያት ነው ህዕ! ~
~ፈገግግ በሉ ፈገግታ ሱና ነው! እኛ ሴቶችኮ ብልህ ነን ስንል በምክንያት ነው ህዕ! ~

⭕️👉 ከአላህ ጋር ያለህን ግንኙነት አሳምርና ከዛም ጉዳዮችህ አላህ እንዴት እንደሚያገራቸው ሁኔታህ እንዴት እንደሚያስተካክልልህ ቁጭ ብለህ የአላህ ተዓምር ተመልከት ~ካንተ ሚጠበቀው በመንገዱ ቀጥ ብለህ መጓዝ ብቻ ነው። { فَٱسۡتَقِمۡ كَمَاۤ أُمِرۡتَ [سُورَةُ هُودٍ: ١١٢] 👉ልክ እንደታዘዝከው ቀጥ በል وَمَن یَتَّقِ ٱللَّهَ یَجۡعَل لَّهُۥ مَخۡرَجࣰا } [سُورَةُ الطَّلَاقِ: ٢] ⭕️👉አላህንም የሚፈራ ሰው ለእሱ  ከሁሉም ጭንቀትና መከራ መውጫን ያደርግለታል፡፡ t.me/https_Asselfya

ረዠም ፅሀፍ አልወድም ብላችሁ እንዳያልፋችሁ ...የስንፍና አዋጅ ..