en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

Open in Telegram

💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።

Show more
8 754
Subscribers
-524 hours
-367 days
-7330 days
Posts Archive
የጥሩ ሚስት ሥነ-ምግባራት (አደቦች) መካከል በጥቂቱ፦ አል-ገዛሊይ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦ • በቤቷ ውስጥ የምትረጋ፣ በስራዋ ላይ የምትበረታ፣ (ሰዎችን ለማየት ወይም ለመታየት) ወደ ውጭ መውጣትና ማየት የማታበዛ መሆንዋ ነው ። • ከጎረቤቶቿ ጋር ንግግሯ አነስተኛ የሆነ፣ አስፈላጊ ሁኔታ ካላስገደዳት በቀር ወደ እነሱ ዘንድ የማትገባ መሆንዋ። • ባሏ በሌለበት ክብሩን የምትጠብቅ፣ በጉዳዮቿ ሁሉ እርሱን ማስደሰትን የምትፈልግ፣ በራሷ ክብረ ንፅሀና ሆነ በገንዘቡ ላይ ክህደት የማትፈጽም መሆንዋ ። • ያለ እርሱ ፈቃድ ከቤቷ የማትወጣ፣ በፈቃዱም ብትወጣ እንኳን ባልተጋነነ (ትኩረት በማይስብ) አለባበስ ተሸፋፍና የምትወጣ፣ ከዋና ዋና መንገዶችና ገበያዎች ይልቅ ሰው የማይበዛባቸውን ቦታዎች የምትመርጥ፣ ባዳ ሰው ድምጿን እንዳይሰማ ወይም በማንነቷ እንዳያውቃት እጅግ የምትጠነቀቅ መሆንዋ። • ለሃጃዎቿ ስትል የባሏን ጓደኛ የማትቀርብ፣ ይልቁንም ያውቀኛል ወይም አውቀዋለሁ ብላ ከምትጠረጥረው ሰው የምትርቅ መሆንዋ። • ዋነኛ ጭንቀቷና ትኩረቷ ጉዳዮቿን ማስተካከልና ቤቷን ማስተዳደር የሆነ። •(በዒባዳዋ) በሶላቷና በጾሟ ላይ ትኩረት የምታደርግ። • የባሏ ጓደኛ ደጃፍ ላይ ቆሞ ፍቃድ በጠየቀ ጊዜ ባሏ ከሌለ፣ ለራሷና ለባሏ ካላት ክብርና ጥንቃቄ የተነሳ ጥያቄ የማታበዛና  ተራ ወሬ የማታወራ መሆንዋ። • አላህ ባስገኘው የባሏ ሲሳይ ላይ የምትብቃቃ (ረክታ የምትኖር) መሆንዋ። • የባሏን መብት ከራሷም ሆነ ከሌሎች ዘመዶቿ መብት ሁሉ የምታስቀድም ። • ንፅህናዋን የጠበቀች፣ በፈለገው ጊዜ ሁሉ ባሏ እንዲደሰትባት በሁሉም ሁኔታዎች ዝግጁ የሆነች። • ለልጆቿ አዛኝ የሆነች፣ ክብራቸውንና ምስጢራቸውን የምትጠብቅ። • ልጆቿን ከመሳደብና ባሏን ከመነታረክ  ምላሷን የጠበቀች መሆንዋ ነው። 📚— ኢሕያእ ዑሉም አድ-ዲን (2/59) [1]

VID_20261029_145606_814.mp4.m4a1.24 MB

👈 من معالم المنهج السلفي • قال العلامة عبد الله بن عبد الرحيم البخاري حفظه الله تعالى ورعاه : من معالم وسمات هذا المنهج أو هذه الدعوة السلفية : • أولا : تحقيق العبودية لله جل وعلا. • ثانيا : تحقيق تجريد الإتباع لرسول الله ﷺ . • ثالثا : لزوم فهم السلف الصالح رضي الله عنهم للأدلة الشرعية، وعدم الخروج عن ذلك . • رابعا : الحذر والتحذير من البدعة والمبتدعة. • خامسا : الوسطية بين الغلو والجفاء . • سادسا : الثبات على الحق . • سابعا : الحرص على الإجتماع والإئتلاف على الحق وبالحق . • ثامنا : نبذ الفرقة والإختلاف . • تاسعا : الحرص على تحصيل العلم النافع، ونشره بين الناس ودعوتهم إليه مع الصبر على الأذى فيه . • عاشرا : العمل بالعلم .
ما هي السلفية )(49 - 50).

እህቶቼ ከሚዲያ ሰፍር አላህ ያውጣችሁ ዲናችሁንም በቤታችሁ ለመማር ያብቃችሁ

وصية_الامام_ابن_قدامة_لأحد_اخوانه.mp32.29 MB

[ተቀርቶ የተጠናቀቀ ماهي السلفية ሙሉ ደርስ ] ➲የኪታቡ pdf➶ t.me/ibnumohammedyimer/1319 t.me/ibnumohammedyimer/1319 ➲ክፍል ⓵ t.me/ibnumohammedyimer/1332 t.me/ibnumohammedyimer/1332 ➲ክፍል ⓶ t.me/ibnumohammedyimer/1353 t.me/ibnumohammedyimer/1353 ➲ክፍል ⓷ t.me/ibnumohammedyimer/1373 t.me/ibnumohammedyimer/1373 ➲ክፍል  ⓸ t.me/ibnumohammedyimer/1388 t.me/ibnumohammedyimer/1388 ➲ክፍል ⓹ t.me/ibnumohammedyimer/1416 t.me/ibnumohammedyimer/1416 ➲ክፍል  ⓺ t.me/ibnumohammedyimer/1439 t.me/ibnumohammedyimer/1439 ➲ክፍል  ⓻ t.me/ibnumohammedyimer/1456 t.me/ibnumohammedyimer/1456 ➲ክፍል ⓼ t.me/ibnumohammedyimer/1478 t.me/ibnumohammedyimer/1478 ➲ክፍል ⓽ t.me/ibnumohammedyimer/1478 t.me/ibnumohammedyimer/1494 ➲ክፍል ⓾ t.me/ibnumohammedyimer/1509 t.me/ibnumohammedyimer/1509 ➲ክፍል⓵⓵ t.me/ibnumohammedyimer/1530 t.me/ibnumohammedyimer/1530 ➲ክፍል ⓵⓶ t.me/ibnumohammedyimer/1542 t.me/ibnumohammedyimer/1542 ➲ክፍል ⓵⓷ t.me/ibnumohammedyimer/1594 ht.me/ibnumohammedyimer/1594 ➲ክፍል ⓵⓸ t.me/ibnumohammedyimer/1628 t.me/ibnumohammedyimer/1628 ➲ክፍል ⓵⓹ t.me/ibnumohammedyimer/1640 t.me/ibnumohammedyimer/1640 ➲ክፍል ⓵⓺ t.me/ibnumohammedyimer/1663 t.me/ibnumohammedyimer/1663 ➲ክፍል⓵⓻ t.me/ibnumohammedyimer/1679 t.me/ibnumohammedyimer/1679 ➲ክፍል ⓵⓼ t.me/ibnumohammedyimer/1690 t.me/ibnumohammedyimer/1690 ➲ክፍል ⓵⓽ t.me/ibnumohammedyimer/1724 t.me/ibnumohammedyimer/1724 📍ሼር በማድረግ የኸይር ተካፋይ ይሁኑ!

قَالَ الْإِمَامُ أَحْمَدُ بْنُ حَنْبَلٍ رَحِمَهُ اللَّهُ : المَرْأَةُ الصَّالِحَةُ كَنْزٌ مِنْ كُنُوزِ الدُّنْيَا. يَعِفُّ ال
قَالَ الْإِمَامُ أَحْمَدُ بْنُ حَنْبَلٍ رَحِمَهُ اللَّهُ : المَرْأَةُ الصَّالِحَةُ كَنْزٌ مِنْ كُنُوزِ الدُّنْيَا. يَعِفُّ اللهُ بِهَا الرَّجُلَ، وَيُثَبِّتُهُ عَلَى الطَّاعَةِ. 📕【 الآدَابُ الشَّرْعِيَّةُ     ( ١ / ٤٤٨)  】

ለባለትዳሮች ብቻ… 💍 |•| የባልና ሚስት የሀላል ፍቅር ጨዋታ በግጥም ባል: አንቺ የኔ ፍቅር የህይወት ጨረቃ ልቤ ይከፋዋል ሳጣሽ ለደቂቃ ሴቶች ብዙ ናቸው አንቺ ግን ልዩ ነሽ ህይወቴን አድሻት ካጠገቤ ሁነሽ ሚስት: አንተ የኔ ፍቅር የህይወት ነፀብራቅ ፍቅርህ ምግቤ ነው ከጎኔ አትራቅ ወንዶች ብዙ ናቸው አንተ ግን ልዩ ነህ ፍቅርህን መግበኝ ካጠገቤ ሁነህ ባል: የትዳር አጋሬ የልጆቼ እናት ደስታዬ አለሜ የሀላል ሚስቴ ናት ጌታዬ ይመስገን እሷን አድሎኛል ውዴን የመሰለ ከቶ የት ይገኛል ሚስት: የልጆቼ አባት የትጋዳሬ አጋር ተስፋዬ ብሩህ እስካለሁ ካንተ ጋር መኖርህ መኖሬ መጥፋትህ መጥፋቴ ሳጣህ ቅር ይለኛል አትጥፋ ከፊቴ ባል: የሽቶ መኣዛ የቴምር ጭማቂ ሁቢ ማር ወለላ ሁሌም ተናፋቂ ጣፈጭ ነገር ሁሉ አንቺን ይመስሉኛል ብቻ ምን ልበልሽ… ቃላቶች ያጥሩኛል! ሚስት: የዐይኔ ማረፊያ የህይወቴ ፀደይ የፊትህ ብርሃን ይበልጣል ከፀሐይ የረህማን ፅጦታ የጀሊሉ ኒዕማ አንጀቴ ይርሳል ድምፅህን ስሰማ ባል: ሚስቱን የሚመታ የትዳር አጋሩን የፍቅር አይደለም ሳስበው ነገሩን ውዷ ባለቤቴ ክብርሽ ይከበር አንቺን የመታው ቀን እጄ ይሰበር ሚስት: እኔ እንክት ልበል እኔ ልሰባበር እሾህ አይውጋብኝ እንኳንስ መሰበር የፍቅር አርበኛ ፊትአውራሪ ጀግና አንተ መውድድ እንጂ ዱላ መች ታውቅና ባል: አኔ እዚህ ጎራ አንቺ ወዲያ ማዶ ልቤ አረረልሽ በፍቅርሽ ማገዶ የልቤ በረዶ መዳኒቴ ነሽ ውዷ ባለቤቴ ሁቢ እንዴት ነሽ? ሚስት: ፈረስ አይጋልበው በበቅሎ አይደረስ በርሬ አንዳልመጣ ያለህበት ድረስ ውዱ ባለቤቴ ፍቅርህ ለበለበኝ አሁንስ ከብዶኛል በዱኣህ አስበኝ ታሳቢነቱ በሩቅ ተነፋፍቀው ላሉ የትዳር ጥንዶች ስለሆነ…ላጤዎች ሳታነቡ እለፉት ¡

👉ፈለጋችሁበት ግቡና ተከተ ታሉ ❶ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን t.me/SheikhMuhammedZainAdam?livestream ➋ሸይኽ አወል አህመድ t.me/SheihkAbuAmarAwolIbnuAhmed?livestream=c5d0f3c25dab45753f ❸ሸይኽ አቡ ሀኒፋ t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris ➍ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር https://t.me/IbnuMunewor ❺ ኡስታዝ አቡ ሙስሊም t.me/AbumuslimAlarsi

👉ከሰዎች እይታ በራቅሽ ቁጥር ወደ አላህ እየቀረብሽ ነው የምትሄጅው!! ~

🔖የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦    “ከሰዎች ሁሉ እጅግ ከባድ ቅጣት ያለባቸው ሁለት አይነት ሰዎች ናቸው። ባሏን ያመፀች ሴት እና ሰዎች እርሱን(በሐቅ) እየጠሉት ኢማም ሆኖ ያሰገደ።”
📚[ሰሒሁ አትቲርሚዚ (359)]
t.me/https_Asselfya

ዑመር ብኑል ኸጣብ የደካሞች ጋሻ! ~ አገሩ ወዲያ ነው - ከመካ በረሃ ክንዱ የሚፋጀው - የሚያሰኘው ውሃ! . ዑመር ብኑል ኸጣብ ከመስለማቸውም በፊት በሃይለኝነታቸው በአይበገሬነታቸው የሚታወቁ ነበሩ። አቡ ጀህልም እንዲሁ ነበር። አቡ ጀህል ስሙ ዐምር ብኑ ሂሻም ብኒል ሙጊራ አልመኽዙሚይ ይባላል። ነብዩ ﷺ የነዚህን ሁለት ሰዎች መስለም በእጅጉ ይፈልጉ ነበር። ይህም የሆነው በጊዜው እንግዳ ለሆነው ኢስላም ክብርና አይደፈሬነትን ይሰጣል በሚል መነሻ ነበር። ለዚህም ነበር የአላህ መልእክተኛ ﷺ “አምላኬ ሆይ! ኢስላምን ከነዚህ ሁለት ሰዎች አንተ ዘንድ በተወደደው አስከብረው'' ማለታቸው። በአቡ ጀህል ወይም በዑመር ብኑል ኸጣብ! ከሁለቱ እሱ ዘንድ የተወደደው ዑመር ሆነ፡፡ [ቲርሚዚይ፡ 3681] ኢብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “ዑመር እስከሚሰልም ድረስ ከዕባ አካባቢ መስገድ አንችልም ነበር፡፡ ዑመር ሲሰልም ግን ቁረይሾችን ተፋለማቸው፡፡ ከዚያም ከዕባ ዘንድ ሰገደ፡፡ ከሱም ጋር ሰገድን።” “ዑመር ብኑል ኸጣብ ከሰለመ ጀምሮ የተከበርን ሆነናል፡፡” [ቡኻሪይ፡ 3684] ኡሙ ዐብዲላህ ቢንት አቢ ሐስማህ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ትላለች:- “ወላሂ ወደ ሐበሻ ምድር ልንሰደድ እየተዘጋጀን ነበር፡፡ ባለቤቴ ዓሚር የሆነ ጉዳያችንን ሊፈፅም ወጥቶ ሳለ ዑመር መጣና ቆመ፡፡ በሺርኩ ላይ እንዳለ ነው፡፡ ከሱ ፈተናና ስቃይ ይደርስብን ነበር፡፡ ከዚያም፡ * “የምርም መጓዛችሁ ነው ኡሙ ዐብዲላህ?” አለኝ፡፡ - “አዎ ወላሂ! አላህ መውጫ እስከሚያደርግልን ድረስ ከአላህ ሀገሮች ወደ አንዱ እንወጣለን፡፡ አስቸገራችሁን አሰቃያችሁን!” አልኩት፡፡ * “አላህ አብሯችሁ ይሁን” አለ፡፡ ቀድሜ አይቸው የማላውቀው መቆርቆር አየሁበት፡፡ ከዚያም ተመልሶ ሄደ፡፡ ሳስበው መውጣታችን በርግጥም አሳዝኖታል፡፡ ባለቤቴ ዓሚር የሄደበትን ጉዳያችንን ፈፅሞ ሲመጣ፡ - “የአብደላህ አባት ሆይ! እንዲያው ዑመርን ቅድም ብታየው፣ ለኛ መቆርቆሩንና ማዘኑን” አልኩት፡፡ * “ይሰልማል ብለሽ ከጀልሽ እንዴ?” አለኝ፡፡ - “አዎ” አልኩት፡፡ * “የኸጣብ አህያ ሳይሰልም ያ ያየሽው ሰውዬ አይሰልምም!” አለኝ፡፡ “በኢስላም ላይ የሚያደርሰውን ጭካኔና ድርቅና በማየት ተስፋ ቆርጦ ነው።” ዐብዱላህ ብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “ዑመር ሲሰልም ቀድሞ በክህደት የተቀመጠባቸውን ስብሰባዎች አንድም ሳያስቀር መስለሙን ሊያውጅባቸው ለነብዩ ﷺ ቃል ገብቶ ነበር፡፡ እናም በሰለመ ጊዜ፡ - 'ከቁረይሽ እጅግ ወሬ አራጋቢ የሆነው ማነው?' ሲል ጠየቀ፡፡ * 'ጀሚል ብኑ መዕመር ነው' አሉት፡፡ ቀጥታ ወደሱ ሄደ፡፡ ምን እንደሚሰራ ለማየት ከስር ከስሩ ተከትየው ሄድኩኝ፡፡ በጊዜው የማየውን ሁሉ በደንብ የማስተውል ልጅ ነበርኩ፡፡ ጀሚል ጋ መጣና፡ - 'ጀሚል ሆይ! መስለሜን አወቅክ ወይ? ወደ ሙሐመድ ሃይማኖት ገባሁ'ኮ!' አለው፡፡ ወላሂ ከዚያ በኋላ ጀሚል ለዑመር አልመለሰም፡፡ ቀጥታ ኩታውን እየጎተተ ወጣ፡፡ ዑመር ተከተለው፡፡ እኔም ዑመርን ተከተልኩት፡፡ ጀሚል ከመስጂዱ በር ቆመና ድምፁን በጣም ከፍ አድርጎ ጮኸ፡- * 'የቁረይሽ ህዝብ ሆይ! አዋጅ! የኸጣብ ልጅ አፈንግጧል' አለ፡፡ በከዕባ ዙሪያ ተሰብስበው ነበር፡፡ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ከኋላው እየተከተለ፡ - “ዋሸ! ባይሆን እኔ በርግጥም ሰልሜያለሁ፡፡ ከአላህ ውጭ በሐቅ የሚመለክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ እንደሆነ መስክሬያለሁ” አለ። ዑመርን ሮጠው ከበቡት። ሲታገላቸው ሲታገሉት እኩለ ቀን ሆነ፡፡ ዑመር አቃተውና ቁጭ አለ፡፡ በራሱ ላይ ወጡበት፡፡ እሱ ይህኔ * “የታያችሁን ሁሉ አድርጉ፡፡ በአላህ እምላለሁ! በርግጠኝነት ሶስት መቶ ወንዶች ብንሆን መካን ወይ እንተውላችኋለን፣ ወይ ትተውልናላችሁ!” አላቸው። ከሁለት አንዳችን ይወጣል እያላቸው ነው። በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ አንድ የቁረይሽ ሽማግሌ መጣ፡፡ የተቀለመ ሙሉ ልብስ ለብሷል፣ ቀሚስ ጋር፡፡ ቀጥታ ካጠገባቸው ቆመና፡ - “ምን እየሆናችሁ ነው?” አላቸው፡፡ * “ዑመር አፈንግጦ ነው” አሉት፡፡ - “ቢሆንስ?! እረፉ! አንድ ሰው ለራሱ የሆነ ነገር መረጠ፡፡ ታዲያ ምንድን ነው የምትፈልጉት? ይህን ሰውዬ እንዲህ ስታደርጉት የዐዲይ ጎሳዎች ዝም የሚሉ መሰላችሁ? ከሰውየው ዞር በሉ!” አላቸው፡፡ ከዚያም በአላህ ይሁንብኝ ልክ ከላዩ ላይ እንደተገፈፈ ልብስ ሆኑ! (ባንዴ ለቀቁት)፡፡ አባቴ ወደ መዲና ከተሰደደ በኋላ: * “አባዬ ሆይ! ያኔ መካ የሰለምክ እለት እነዚያን ሲታገሉህ የነበሩትን ሰዎች የተቆጣቸው ሰውዬ ማነው?” አልኩት፡፡ - “ያማ አልዓስ ብኑ ዋኢል አሰህሚ ነው የኔ ልጅ” አለኝ፡፡ (አልዓስ ብኑ ዋኢል አሰህሚ ማለት የብልሁ ፖለቲከኛ የዐምር ብኑል ዓስ አባት ነው።) = (ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 1/2006) የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ወረፋን አለመጠበቅ ~ ወረፋ በሚጠበቅበት የትኛውም ቦታ ላይ የቀደሙ ሰዎች እያሉ በጉልበትም ይሁን በመሸወድ ቀድሞ መግባት ነውረኛ ተግባር ነው። የታክሲ፣ የውሃ፣ የክፍያ ቦታዎች፣ ሃኪም ቤቶች፣ የተለያዩ መስሪያ ቤቶች፣ ... ከኛ የቀደሙ ተገልጋዮች እያሉ በየትኛውም ጤነኛ ባልሆነ መንገድ ቀድሞ ተጠቃሚ መሆን አላህን ለሚፈራ ሰው ሞኝነት እንጂ ብልጠት አይደለም። ይልቁንም ነፍሰ ጡር እና ልጅ የያዙ እናቶችን፣ ህመምተኞችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ አዛውንቶችን ማስቀደም አጅር ያለው ተግባር ነው። = የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor