💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
الذهاب إلى القناة على Telegram
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
إظهار المزيد8 814
المشتركون
-724 ساعات
-177 أيام
-8330 أيام
أرشيف المشاركات
ጥያቄ ? 📮📮
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።
📝 ጥያቄ
አል አቅሷ መስጂድን የገነባው ነብይ ማን ነው ?
🔖አንድ ሴት ሰለፍይ ወይም ሷሊህ ደግ ናት ማለት ወንጀል የማትሰራ የማትሳሳት ጥቡቅ ናት ማለት አይደለም። ነገር ግን፦
~ሲያስታውሷት ትነቃለች
~ሲመክሯት ትቀበላለች
~ከስህተቷ ትመለሳለች
~ለወንጀሏ እስቲግፋር ትጠይቃለች።
~
t.me/https_Asselfya
Repost from ስለ ቀልባችን
➔ ዛሬ ላይ እጅግ በርካታ ሴቶች እንደ ቀላል ነገር የሚመለከቱት፣ ነገር ግን በአላህና በመልእክተኛው ዘንድ እጅግ የከበደና አስከፊ ከሆኑ ወንጀሎች ተርታ የተመደበ አንድ አጥፊ ድርጊት አለ፤ እርሱም አንዲት ሴት ሽቶ ተቀብታ አጅነቢይ (ባዕድ) ወንዶች ባሉበት መውጣቷ ነው።
ይህንን አስመልክቶ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንድህ ይላሉ፦
❝ማንኛዋም ሴት ሽቶ ተቀብታ፤ ሽታዋን ያሸቱ ዘንድ በሰዎች (በአጅነቢይ ወንዶች) አጠገብ ካለፈች፤ እርሷ ዝሙተኛ ናት!❞ [አቡ ዳዉድ፣ ቲርሚዚይ እና ነሳኢይ]
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሽቶ ተቀብታ የወጣችን ሴት «ዝሙተኛ ናት» በማለት የጠሯት ዝም ብለው አይደለም። ሽቶ የአንድን ወንድ የስሜት ህዋሳት የሚቀሰቅስ፣ ልቡን የሚያሸፍት እና አይኑን ወደ እርሷ እንዲያነጣጥር የሚያደርግ ገዳይ መርዝ ነው። እርሷ በወጣችበት መንገድ ሁሉ የወንዶችን ስሜት በማነሳሳት የዓይን ዝሙት፣ የልብ ዝሙትና የሀሳብ ዝሙት እንዲፈጽሙ በር ከፋች ትሆናለች፤ በዚህም ሳቢያ በፈጸሙት ወንጀል ሁሉ ሙሉ ተካፋይ ትሆናለች።አደጋው በዚህ ብቻ አያበቃም! ይልቁንም ወደ አላህ ቤት መስጂድ ለመስገድ ስትሄድ እንኳ ሽቶ ከተቀባች ሶላቷ ተቀባይነት እንደሌለው በሌላ ሐድስ ተነግሯል።
ልብ በይ! ወደ አላህ ቤት፣ ለዒባዳ እና ለሶላት ለመሄድ ሽቶ መቀባት እንዲህ የሚያስጠይቅና ሶላትን ውድቅ የሚያደርግ ከሆነ፤ ለገበያ፣ ለትምህርት ቤት፣ ለቢሮ፣ ለመንገድ እና ለሰርግ ድግሶች ሽቶ ተቀብቶ በአጅነቢይ ወንዶች ፊት መዘዋወር ቅጣቱ ምን ያህል የከፋ ይሆን?!
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
Repost from 📱[ انتبه أنت مراقب ] 📲
"ከሀራም ግንኙነቶች መራቅ የንቃት፣ የብስለት፣ ለአላህ ትዕዛዝ የመታዘዝ እንዲሁም የነቢዩን ﷺ ፈለግ የመከተል ውጤት እንጂ—አንዳንዶች እንደሚያስቡት—የኋላ ቀርነት ወይም የዘመናዊነት እጥረት አይደለም..
الآدابُ الْمُهِمَّةُ لِنِسَاءِ الْأُمَّةِ
🏝 አዲስ ደርስ ለሴቶች
【 ክፍል ሀያ አንድ ②① 】
https://t.me/misbahulhu
«ነገሩ የአላህ ተውፊቅ (ስኬት/እርዳታ) ጉዳይ
መሆኑን ለማረጋገጥ፤ ዚክርን ተመልከት። ከዒባዳዎች (የመታዘዝ ሥራዎች) ሁሉ በጣም ቀላሉ ነው፤ ነገር ግን ለእርሱ የሚወፈቀው (የሚታደለው) ጥቂት ሰው ብቻ ነው!»
ኢብኑ ዑሠይሚን👉 ሚስት የቤት መልካም አስተዳዳሪ እና ምስጥር ጠባቂ_ናት
ነብዩ ﷺ "የምትታዘዝ፣ ራሷን የምትጠብቅ፣ የባሏን ሀብት እና ክብር የምትጠብቅ" ሴት ጥሩ ሴት ናት ብለዋል
ቤቷን በንጽህና፣ በፍቅር እና በሰላም ማስተዳደር የትልቁ ሃላፊነቷ ነው።
Repost from "ዳሩል -ዒልም የእዉቀት ማዕዲ !
👉ሴት ልጁ ወይም እህቱ አልያም ሚስቱ በየትኛዉም ባህበራዊ ሚዲያ ላይ እንደፈለገች እሆነች ዝም የሚል ወንድም ደዩስ ብቻ ሳይሆን ጅል ሞኝ ነዉ። አንዳንዶቹማ ጭራሽ ያበረታቷቸዋል። ቆይ አንተ ሚስትህ ማንም ጋር ሚዲያ ወጥታ ከማንምጋ ስትገለፍጥ እንደት አስቻለህ!?በቁምህ ሙተሀል። እህቶች ደግሞ እባካችሁ በተለይ ትንሽ አዉቀናል ቀርተናል የምትሉ እናስተምራለን በሚል ስበብ ሚዲያ ላይ አትርከሱ። ማስተማር ካለብሽ ስንት እህቶች አሉ አንደል ሚያቀራቸዉ ሲያጡ ወንዶች ጋር ሂደዉ የሚቀሩ!? አሉ ደግሞ የሚያቀራቸዉ ሲያጡ አቂዳቸዉ ከተንሻፈፈ መንጋዎችጋ ሂደዉ የሚተራመሱ፣ እዉቀት ካለሽ ሚዲያ ከምትወጭ ለምን እነሱን ሰብስበሽ በራስሽ አታስሞጥሊም። ታዉ እህቶች የሚቆጫችሁን ነገር አታድርጉ። በሚጠቅማችሁ ነገር ላይ ብቻ ትኩረት አድርጉ
ከሱና እህታችሁ ሐያት....✍
🔖 አዲስ የቂርአት ፕሮግራም!
➖➖➖➖➖➖
👉የኪታቡ ርዕስ
➫➫➫➫➫➫
🌐 «ما هي السلفية
➡️ (ክፍል አስራ ሶስት )
🎙በኡስታዝ አቡ አብዲላህ ተውፊቅ
t.me/ibnumohammedyimer
t.me/ibnumohammedyimer
📚 የኪታብን Pdf ለማገኘት ⤵
t.me/ibnumohammedyimer/1319
ሞትን አብዝቶ ማስታወስ እጅግ የተወደደ (
ሙስተሐብ) የሆነ ተግባርና የነቢዩﷺ ምክር ነው፤ ዓላማውም ልብን ማነቃቃትና ወደ አላህ (ሱ.ወ) ያለንን ቅርበት ማሳደግ ነው።🔖«አላህ ለአንድ ወንድ ከሚሰጣቸው
ፀጋዎች መካከል አንዱ የምትወደው
ሚስት መሰጠቱ ነው።».
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ሪያዶች ስራ ፈልጉስኪ ባረከላሁፊኩም ሸሪኻም ስራ ከተገኘ ኢቃማ አላቸው
@Locked_10
@Umu_Khalid_1
⬆️አናግሩን በጀመኣችሁም ከተገኘ ተባበሩን
