en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Open in Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 16 047 subscribers, ranking 5 283 in the Religion & Spirituality category and 2 238 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 16 047 subscribers.

According to the latest data from 26 October, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 518 over the last 30 days and by 5 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 25.13%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 10.43% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 4 033 views. Within the first day, a publication typically gains 1 674 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 29.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 27 October, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

16 047
Subscribers
+524 hours
+1057 days
+51830 days
Posts Archive
እንኳን ለኪዳነ ምሕረት ክብረ በዓል (ቃል ኪዳን ለተቀበለችበት) በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡ (ድንግል ሆይ ቃል ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ የሲኦል እሳት ባሰጠመን ነበር፡፡) ፠ የካቲት ፲፮ ቀንም በጎልጎ
+6
እንኳን ለኪዳነ ምሕረት ክብረ በዓል (ቃል ኪዳን ለተቀበለችበት) በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡ (ድንግል ሆይ ቃል ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ የሲኦል እሳት ባሰጠመን ነበር፡፡) ፠ የካቲት ፲፮ ቀንም በጎልጎታ ቦታ ቆማ ወደ ልጇ እንዲህ ብላ ለመነች፡፡ ፠ጸሎትና ልመናዬን ስማኝ ቃሌንም አድምጥ እኔ እናትህ አገልጋይህ የምለምንህን ይህ ነው፡፡ ፨ መታሰቢያዬን ለሚያደርጉ፣ ፨ አብያተ ክርስቲያኔን ለሚሠሩ፣ ወይም ፨ ለታረዙ ለሚያለብሱ፣ ለተራቡ ለሚያጠግቡ፣ የተጠማውንም ለሚያጠጡ (በስሜ ለድሆችና ለችግረኞች ቀዝቃዛ ውኃ ለሚሰጡ)፣ ፨ የታመመውንም የሚጎበኝ፣ ያዘነውንም የሚያረጋጉ፣ የተከዘውንም ደስ የሚያሰኙ ወይም ፨ ምስጋናዬን ለሚጽፉ፣ ልጆቹንም በስሜ ለሚሰይም፣ ፨ በበዓሌም ቀን በማኅሌት ለሚያመሰግን አቤቱ በዓይን ያልታየውን በጆሮ ያልተሰማውን በጎ ዋጋ ስጣቸው፡፡ ፨ በአማላጅነቴም የሚተማመኑትን ሁሉ ከሲዖል ነፃ አድርጋቸው ከአንተ ጋር የደረሰብኝን ረሃብና ጥማቱን መከራውን ሁሉ አስብ አለችው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንዳልሽው ይሁንልሽ የሰጠሁሽን ቃልኪዳን እንዳይታበይ በራሴ በባሕርይ አባቴ በአብ በባሕርይ ሕይወቴ በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጣት፡፡ #ሥርዐተ_ማኅሌት_ዘየካቲት_16፤ #በዓለ_ኪዳነ_ምሕረት፡፡ የሚቆመው ቁመት፤ የ3ት ዐበይት አድባራት አብነት ነው፡፡ እነዚህም፤ 1ኛ) የደ/መድኀኒት ዐቢየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት አብነት 2ኛ) የደ/ኀይል ወደብረ ጥበብ በዓታ አብነት 3ኛ) የደፈጫ ኪዳነ ምሕረት አብነት ናቸው፡፡ ስለዚህ ደብራችሁ የላይ ቤት ከኾነ ‹‹ዘዐቢየ እግዚእ›› የሚለውን፤ የታች ቤት ከኾነ ‹‹ዘበዓታ›› የሚለውን እንድትጠቀሙ እናሳስባልን፡፡ ፠፠ ወረቦቹን፣ አንገርጋሪንና እስመ ለዓለምን በድምፅ ከፈለጉ በቴሌግራም ገጻችን https://t.me/medihanaelem ያገኛሉ፡፡

እንኳን ለኪዳነ ምሕረት ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤ በአዲስ አበባ የኪዳነ ምሕረት ክብረ በዓል የሚከበርባቸው ገዳማትና አድባራት፤ (፠ …….. በአዲስ አበባ ያልዘገብናቸው ሌሎችም ካሉ ከተቻለ ከነፎቷቸው አሳውቁን፡፡) ፠ እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪደነ ምሕረት ፠ ደብረ …. ሥዕል ቤት ኪዳነ ምሕረት (በዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ግቢ ውስጥ የምትገኝ ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን) ፠ ጉራራ ምሥራቀ ፀሐይ ኪዳነ ምሕረት ቤ/ክ (ከፈረንሳይ ሌጋሲዮን አልፎ) ፠ አየር ጤና አንቀጸ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት፤ ፈለገ ሕይወት ኪዳነ ምሕረት (ኮልፌ ቀራንዮ፥ ወረዳ 5) ፠ ጉለሌ(ሸጎሌ) ቅድስት ኪዳነ ምሕረት፤ ፠ ቀበና ቤዛዊተ ዓለም ቅድስት ኪዳነ ምሕረት፤ ፠ ኮተቤ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ፠ ደብረ ወርቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት (ነፋስ ስልክ ላፍቶ) ፠ ቤዛ ብዙኃን ኪዳነ ምሕረት (ጎፋ ሠፈር) ፠ አዲስ አምባ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት (ነፋስ ስልክ ላፍቶ ፥ ቅዱስ ዮሴፍ አካባቢ) ፠ ጃቲ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት (አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ) ፠ ቦሌ ሰሚት ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ፠ አያት ጌቴ ሴማኒ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ፠ ቀራንዮ መድኀኔ ዓለም (በድርብነት ይከበራል) ፠ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ (በድርብነት ይከበራል) ፠ ደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ (በድርብነት ይከበራል) ፠ ቦሌ (ገርጂ) ደብረ ገነት ቅዱ ጊዮርጊስና ቅዱስ ገብርኤል (በድርብነት ይከበራል) ፠ ኤረር ጎሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል (በድርብነት ይከበራል) ፠ ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል (በድርብነት ይከበራል) ፠ መርካቶ ደብረ ኀይል ቅዱስ ራጕኤል (በድርብነት ይከበራል) በፎቶ ላይ የምትመለከታቸው አብያተ ክርስቲያን፤ 1ኛ) #አዲስ አበባ እንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳም፡፡ ይህች ገዳም ታሪኳ ከታላቁ ገዳማችን ዋልድባ (ገዳመ ዋሊ) ለ2ኛ ጊዜ መሥፋፋት (መመሥረት ጋር) የተያያዘ ታሪክ ያላት ናት፡፡ ይኸውም የሸዋ አባቶች ወደ ዋልድባ በ485 ዓ.ም. በንጉሥ አልአሜዳ ዘመነ መንግሥት ባቀኑ ጊዜ የተሰባሰቡባት ቦታ ናት፡፡ እነዚህም አበው ከመኖሪያ ቀዬቸው (ቡልጋ/ምንጃር/) ሲሆንሁለት ታቦታትን (ታቦተ ኪዳነ ምሕረት ዘምሕረት አምባና ታቦተ መድኀኔ ዓለምን ዘዐብየ ገዳምን) ይዘው ነበር፤ በዚህች በተቀደች ቦታ ይዘዋት በመጡት ታቦተ ኪዳነ ምሕረት ገዳመ ሐመረ ኖኅን መሥረተዋል፡፡ የመድኀኔዓለም ታቦትን ደግሞ በታላቁ ገዳም በዋልድባ አኑረዋል፡፡ ይህች ሐመረ ኖኅ፤ *በ500 ዓ.ም በአባ ሊባኖስ ዘመጣዕ የአንድነት ገዳም ሆና ተስፋፍታ ተቋቋመች፡፡ *በ9ኛ መቶ ክ/ዘመን ዮዲት ጉዲት የአክሱም ጽዮንን ቤተ መቅደስ ለማቃጠል ስትነሳ ንጉሡ አንበሣ ውድም ታቦተ ጽዮንን በምሥጢር በማስያዝ ወደ ሸዋ መጥተው በእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነምሕረት ገዳም ታቦተ ጽዮንን አሳድረው ወደ ዝዋይ ደሴት ሲሄዱ ለገዳሟ ንዋየ ቅድሰት ስጦታ አበርክተዋል ጸበሏን ተጠምቀው ቦታውን መርቀው ሄደዋል፡፡ *በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከንጉሥ ላሊበላ ጋር ወደ ዝቋላ አምባ ሲመጡ በዚህች ገዳም በእንግድነት አድረው በጸበሏ ተጠምቀው ቦታውን ባርከዋል፡፡ * አፄ ዘርዐ ያዕቆብም ወደዚህች ገዳም መጥተው አቀማመጧንና የጸበሏን ፈዋሽነት ተመልክተዋል ‹‹ዳሯ እሳት መሐሏ ገነት ይሁን›› ብለው ብዙ ስጦታ አበርክተዋል፡፡ * አፄ ልብነ ድንግልም ወደ ገዳሟ መጥተው ተማኅጽኖ አድርገው በጸበሏ ተጠምቀው ታቦተ ልደታንና ብዙ ንዋየ ቅድሳት ሰጥተው ሄደዋል፡፡ * በንግሥት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት ይህች ገዳም ሐመረ ኖኅ ኪዳነምሕረት ገዳም ተብላ ተሰይማለች፡፡ **ይህች ቦታ ከታላቁ ገዳም ከዋልድባ ጋር አሁንም ግንኙነቷ እንደጠነከረ ነው፤ ከዋልድባ ያሉ አባቶች በተለያየ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ በዋነኛነት የሚያርፉባት ጥንተ ርስታቸውም ናት፡፡ **ይህች ቦታ በርካት ቅዱሳን በኪደተ እግር የረገጧት እንደመኾኗ፤ ጸበሏ የአጋንንት ድል መንሻ፤ የብዙ መነኰሳት መጠጊያ፤ የሕሙማን መፈወሻ፤ … በመሆኗ በአዲስ አበባ የእመቤታችንን ቃል ኪዳን ለማግኘት ብዙውን ጊዜ ለሱባኤ ከሚመረጡ ቦታዎችም አንዷ ናት፡፡ 2ኛ) #ደብረ_መድኀኒት_ዐቢየ_እግዚእ_ኪዳነ ምሕረት፤ * በሃገራችን ኢትዮጵያ የመጻሕፍተ ብሉያት አንድምታ ትርጓሜ ዋና ማስመስከሪያ መካነ አእምሮ (University) የኾነች፤ * ታላቁ ጻድቅ አቡነ ዐቢየ እግዚእ በኪደተ እግር የረገጧት፤ * በአቋቋም በኩልም የላይ ቤት አብነት የኾነች፤ * የታላላቅ ሊቃውንት መፍለቂያና ታላላቅ ሊቃውንት ወንበር ዘርግተው፥ ጕባኤ አስፋፍተው ያስተማሩባትና በማስተማር ላይ ያሉባት ቦታ ናት፡፡ የምትገኘውም ጎንደር ከተማ ነው፡፡ 3ኛ) #ኢየሩሳሌም_ደብረ_ገነት_ኪዳነ_ምሕረት፡፡ ሕንፃ ግንባታዋ፤ በዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ተጀምራ በዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ የተጠናቀቀች፡፡ 4ኛ) አዲስ አበባ #ስዕል_ቤት_ኪዳነ_ምሕረት፤ በታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ግቢ ውስጥ የምትገኝ፡፡ በዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ የተሠራች፡፡ 5ኛ) #ራማ_ኪዳነ_ምሕረት፡፡ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#ዐርብ_የካቲት_13፤ #ከ፲፪-፪ ሰዓት #የሕይወት_ፈተና_ምንጮች_ክፍል_፲፩፡፡ #የማጠቃለያ_ትምህርት Shareee, Like … እንዳያመልጥዎ በጕባኤው ላይ ይገኙ፡፡ ፠ ለምን እንፈተናለን፤ ፠ ፈተናዎ
+1
#ዐርብ_የካቲት_13፤ #ከ፲፪-፪ ሰዓት #የሕይወት_ፈተና_ምንጮች_ክፍል_፲፩፡፡ #የማጠቃለያ_ትምህርት Shareee, Like … እንዳያመልጥዎ በጕባኤው ላይ ይገኙ፡፡ ፠ ለምን እንፈተናለን፤ ፠ ፈተናዎች ለምንና እንዴት ይመጣሉ፤ ፠ ፈተናዎችን እንዴት አድርገን ድል እናድርጋቸው፤ …. ፠ ……እንዳያመልጣችሁ፤ በሌሎችም ርዕሶች ዙሪያ በብዙ ጕባኤያት ላይ ያልተዳሰሱ ርዕሶች የሚዳሰሱበት ጕባኤ ስለሆነ እንዳያመልጣችሁ፤ #ደግመን_እንላለን_ይህ_ትምህርት_በፍጹም_እንዳያመልጣችሁ!!!!! ለተከታታይ ሳምንታት፤ ትምህርቱ ተከታታይነት ስላለው መቅረትና ማርፈድ አይመከርም!!፡፡ (፻፷፩ኛ ሳምንት የዐርብ ጕባኤ) #ዐርብ_የካቲት_፲፫፤ #ከ፲፪-፪ ሰዓት አሁንም በድጋሚ እንላለን ለሕይወታችን ወሳኝና በብዙ የትምህርት ጕባኤያት ላይ የማይዳሰሱ ትምህርቶች ስለሆኑ እንዳያመልጣችሁ!!!! የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት፡፡ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#የዐቢይ_ጾም_ሳምንታት_ስያሜዎች ከፍኖተ ሕይወት ሰሌዳ መጽሔት የተወሰደ ፩ኛ)የመጀመሪያው እሑድ(ሳምንት)፥ #ዘወረደ (#ሙሴኒ፣ #ጾመ_ሕርቃል) ይባላል፡፡ በመጽሐፉ መጀመሪያ አምላክ ከሰማይ መውረዱን
+1
#የዐቢይ_ጾም_ሳምንታት_ስያሜዎች ከፍኖተ ሕይወት ሰሌዳ መጽሔት የተወሰደ ፩ኛ)የመጀመሪያው እሑድ(ሳምንት)፥ #ዘወረደ (#ሙሴኒ፣ #ጾመ_ሕርቃል) ይባላል፡፡ በመጽሐፉ መጀመሪያ አምላክ ከሰማይ መውረዱን፣ ሰው መሆኑንና መስቀሉን ስለሚያወሳ ነው፡፡ ፪ኛ. የሁለተኛው እሑድ፥ #ቅድስት ይባላል፤ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ስለሚያወሳ ነው ፫ኛ. የሦስተኛው እሑድ፥ #ምኲራብ ይባላል፤ በዚህ ሰንበት ጌታ በመዋዕለ ትምህርቱ በምኲራብ ገብቶ ማስተማሩ ይነገራል፡፡ ፬ኛ. ዐራተኛው እሑድ፥ #መፃጉዕ ይባላል፤ ድውያንን መፈወሱን፣ ዕውራንን ማብራቱን፣ የሚያነሣ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡ ፭. አምስተኛው እሑድ፥ #ደብረ ዘይት ይባላል፡፡ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሁኖ ያስተማረው ትምህርት፥ የዳግም ምጽአትን ነገር የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡ ፮. ስድስተኛው እሑድ፥ #ገብርኄር ይባላል፡፡ የጌታውን ብር ተቀብሎ ያተረፈበት፣ በጌታውም ፊት ምስጋናን ያገኘው ሰው ታሪክ ይዘመርበታል፡፡ ፯. ሰባተኛው እሑድ፥ #ኒቆዲሞስ ይባላል፡፡ በሌሊት ወደ ጌታ እየመጣ ይማር የነበረውን የኒቆዲሞስን ታሪክ የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡ ፰. ስምንተኛው እሑድ፥ #ሆሣዕና ነው፡፡ ጌታ በአሕያ ውርንጭላ ሆኖ ሆሣዕና በአርያም እየተባለ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት ዕለት መታሰቢያ ነው፡፡  ከሠርክ ሆሣዕና እስከ ትንሣኤ ያለው ሰባት ቀን #ሕማማት ይባላል፡፡- የጌታን መከራና ስቃይ እንዲሁም ሞት የምናስታውስበት ሳምንት ነው ፡፡ #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#የዐቢይ_ጾም_ሌሎች_መጠሪ_ስያሜዎች ፩. #ዐቢይ_ጾም ይባላል፤ ፪. ጾመ ሁዳዴ ይባላል፤ ፫. #የካሣ_ጾም ይባላል፤ ፬. የድል ጾም ይባላል፤ ፭. #የመሸጋገሪያ_ጾም ይባላል፤ ፮. ጾመ አስተምህሮ ይባ
#የዐቢይ_ጾም_ሌሎች_መጠሪ_ስያሜዎች ፩. #ዐቢይ_ጾም ይባላል፤ ፪. ጾመ ሁዳዴ ይባላል፤ ፫. #የካሣ_ጾም ይባላል፤ ፬. የድል ጾም ይባላል፤ ፭. #የመሸጋገሪያ_ጾም ይባላል፤ ፮. ጾመ አስተምህሮ ይባላል፤ ፯. #የቀድሶተ_ገዳም ጾም፤ ፰. የመዘጋጃ ጾም ይባላል፤ ፱. #የሥራ_መጀመሪያ ጾም፤ ፲. ጾመ አርብዓ ይባላል፡፡ #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

እንኳን ለዐቢይ ጾም አደረሳችሁሁ፡ የ2012ዓ.ም. (አበቅቴ 6፤ መጥቅዕ 24 ነው) *ጾመ ነነዌ፤ የካቲት 2 (February 10) ሰኞ ውሏል፡፡ #ዐቢይ ጾም = 14 ተውሳክ + 2ቀናት(የጾመ ነነዌ) = 16፤ #የካቲት_16_ (February 24)ሰኞ_ይገባል፡፡ *ደብረ ዘይት = 11 ተውሳክ + 2ቀናት(የጾመ ነነዌ) = 13፤ መጋቢት 13 (March 22) እሑድ ይከበራል፡፡ #ሆሳዕና = 2 ተውሳክ + 2ቀናት(የጾመ ነነዌ) = 4፤ ሚያዝያ 4 (April 12) እሑድ ይከበራል፡፡ *ስቅለት = 7 ተውሳክ + 2ቀናት(የጾመ ነነዌ) = 9፤ ሚያዝያ 9 (April 17) ዐርብ ይውላል፡፡ #ትንሣኤ = 9 ተውሳክ + 2ቀናት(የጾመ ነነዌ) = 11፤ ሚያዝያ 11 (April 19) እሑድ ይከበራል፡፡ *ርክበ ካሕናት = 3 ተውሳክ + 2ቀናት(የጾመ ነነዌ) = 5፤ ግንቦት 5 (ረቡዕ ይውላል፡፡ #ዕርገት = 18 ተውሳክ + 2ቀናት(የጾመ ነነዌ) = 20፤ ግንቦት 20 (May 13) ኀሙስ ይውላል፡፡ *ጰራቅሊጦስ = 28 ተውሳክ + 2ቀናት(የጾመ ነነዌ) = 30፤ ግንቦት 30 (June 7) እሑድ ይከበራል፡፡ #ጾመ ሐዋርያት = 29 ተውሳክ + 2ቀናት(የጾመ ነነዌ) = 1(በ30 ተገድፎ)፤ ሰኔ 1 (june 8) ሰኞ ይገባል፡፡ *ጾመ ድኅነት = 1 ተውሳክ + 2ቀናት(የጾመ ነነዌ) = 3፤ ሰኔ 3 (June 10) ረቡዕ ይገባል፡፡ #ለቡ_!!፥ (N.B)፥ ልዩ ዓዋጅ፥ ልዩ መስታወሻ፤ ፠ ሁልጊዜም፤ ጾመ ነነዌ፥ ዐቢይ ጾምና ጾመ ሐዋርያት የሚጀምሩት በሰኞ ነው፡፡ ፠ ሁልጊዜም፤ በዓለ ደብረ ዘይት፥ ሆሳዕና፥ ትንሣኤና ጰራቅሊጦስ የሚከበሩት በእሑድ ቀን ነው፡፡ ፠ ሁልጊዜም፤ በዓለ ዕርገት የሚከበረው ኀሙስ ነው፡፡ ፠ ሁልጊዜም፤ ስቅለት የሚውለው ዐርብ ነው፡፡ ፠ ሁልጊዜም፤ ርክበ ካሕናት የሚውለውና ጾመ ድኅነት የሚጀመረው ረቡዕ ነው፡፡ ፠ እንደ አምናው የዐቢይ ጾም የየሳምንታቱን ማብራሪያና የየሰንበታቱን መዝሙርና ምንባባት የምናቀርብ መሆኑን እንዲሁም ‹‹ከሰይጣን ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ /ተዋስኦተ ጳውሊ ምስለ ሰይጣን/፡፡›› የሚለውን ደግሞ ከክፍል 1 ጀምሮ ሰኞና ዐርብ የምናቀርብ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ #በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ #በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

#የማንቂያ_ደውል #የማንቂያ_ደውል #የማንቂያ_ደውል #የማንቂያ_ደውል #የማንቂያ_ደውል (በደቡብ ሸዋ፣ በድሬደዋና በደቡብ ኢትዮጵያ እንገናኝ) Sharereeeeee ‹‹#የእግዚአብሔር_ድምፅ_ከተማይቱን
+3
#የማንቂያ_ደውል #የማንቂያ_ደውል #የማንቂያ_ደውል #የማንቂያ_ደውል #የማንቂያ_ደውል (በደቡብ ሸዋ፣ በድሬደዋና በደቡብ ኢትዮጵያ እንገናኝ) Sharereeeeee ‹‹#የእግዚአብሔር_ድምፅ_ከተማይቱን_ይጠራታል_ስምህን_መፍራት_ጥበብ_ነው_፡፡›› /ትንቢተ ሚክያስ 6፥9/ ፠ ኀሙስ የካቲት 12፤ በድሬደዋ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል፡፡ ፠ የካቲት 13፤ በናዝሬት (አዳማ) ቅድስት ማርያም፡፡ ፠ ከየካቲት 13-15፤ በሐዋሳ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም፡፡ #ይቀጥላል ~ ጎንደር ፥ ጂጂጋ ፥ አርባምንጭ ፥ ጂንካ ፥ ቡታጅራ ፥ ደሴ ፥ ባሕርዳር ፥ አሶሳ ፥ አዳማ ፥ ጋምቤላ፥ ሆሳዕና ..... ፠፠፠ የአቤልን የግፍ ሞት፤ የዘካርያስን በግፍ መገደል የተበቀለ የአባቶቻችን አምላክ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በቤተ ክርስቲያናችንና በምዕመኗ ላይ የደረሰውን ግፍ፣ ቅትለት (ግድያ)፣ ማስፈራሪያ፣ ዛቻ፣ ሥልጣንን ተገን በማድረግ የሚሠራ ደባ፣ ሙስና፣ ……. እርሱ ይበቀልልን፤ እርሱ ፍርዱን ይስጥ፡፡ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

/ከትናንቱ የቀጠለ……/ #ክፍል_፬.፬ #ለየካቲት_12_የሰማዕታት_ቀን_መዳረሻ፥ #ለየካቲት_23_የአድዋ_ድል_መነሻ፥ #ለሚያዝያ_27_የድል_ቀን_ማስታወሻ_ ፠ ‹‹ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ፡፡
+9
/ከትናንቱ የቀጠለ……/ #ክፍል_፬.፬ #ለየካቲት_12_የሰማዕታት_ቀን_መዳረሻ፥ #ለየካቲት_23_የአድዋ_ድል_መነሻ፥ #ለሚያዝያ_27_የድል_ቀን_ማስታወሻ_ ፠ ‹‹ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ፡፡ (#በአባቶችሽ_ፈንታ_ልጆች_ተወለዱልሽ) ፠ የዘንድሮ የካቲት 12/2012 ዓ.ም. በዓል በአባቶቻችን እግር ሥር የተተኩ ሕፃናትና ወጣቶች (የአርበኞች ትምህርት ቤት፣ የኢትዮጵያ ስካውት ማኅበር፣ ብሉ በርድ ትምህርት ቤት፣ ሒል ሣድ ትምህርት ቤት፣ ድራማና ዝማሬና ሽለላ ልክ በወቅቱ ያለ አስመስለው አቡነ ጴጥሮስንም አስመስለው የሚያቀርቡ ማኅበራትና ሌሎችም ተሳትፈዋል፡፡) በዕለቱም ከተጻፉ ጥቅሶች መካከል ጥቂቶቹ፤ #ሀገሬ_እኔ_ብለህ_የምትኖርባት_እኛ_ብለህ_የምትሞትላት_ጣፋጭ_ቅኔ_ናት፡፡ ፠ ለዘለዓለማዊ የሰው ልጅ ሞቱ ነፍሱ ከሥጋው መለየቱ ሳይሆን ነጻነትን አለማወቁ ነው፡፡ #ከሰብዐዊነት_ዘር_ይበልጣልን? ፠ እኛ የሞትነው መወለድ ግብሯ የሆነውን ኢትዮጵያን ልንወልድ ነው፡፡ #ኢትዮጵያ_በክፋት_የነካትን_የምታቃጥል_እሳት_ናት፡፡ ፠ አገሩን በሰላም ወጋግራ አቁሞ ለማለፍ ሰው ከአባቱ ገዳይ ጋር በቅርታ ይፋቀራል፡፡ #ኢትዮጵያን_የምታክል_ሃገር_እንዴት_ለባርነት_እናስረክባለን፡፡ ፠ ለራስህ ከርስ ብለህ ለመጪው ትውልድ ባርነትንና ምድራዊ ገሃነምን እንደምን ታወርሰዋለህ!!፡፡

/ከትናንቱ የቀጠለ……/ #ክፍል_፬.፫ #ለየካቲት_12_የሰማዕታት_ቀን_መዳረሻ፥ #ለየካቲት_23_የአድዋ_ድል_መነሻ፥ #ለሚያዝያ_27_የድል_ቀን_ማስታወሻ_ ፠ የዘንድሮ የካቲት 12/2012 ዓ.ም. በዓ
+3
/ከትናንቱ የቀጠለ……/ #ክፍል_፬.፫ #ለየካቲት_12_የሰማዕታት_ቀን_መዳረሻ፥ #ለየካቲት_23_የአድዋ_ድል_መነሻ፥ #ለሚያዝያ_27_የድል_ቀን_ማስታወሻ_ ፠ የዘንድሮ የካቲት 12/2012 ዓ.ም. በዓል የአባቶቻችንና የእናቶቻችን አርበኞች ሰማዕታት ውሎ በከፊል፡፡

/ከትናንቱ የቀጠለ……/ #ክፍል_፬.፪ #ለየካቲት_12_የሰማዕታት_ቀን_መዳረሻ፥ #ለየካቲት_23_የአድዋ_ድል_መነሻ፥ #ለሚያዝያ_27_የድል_ቀን_ማስታወሻ_ (የዘንድሮ የካቲት 12/2012 ዓ.ም. በዓልና ጸሎተ ፍትሐት በ6ኪሎና በ4 ኪሎ ሥላሴ ምን እንደሚመስል ፎቶውን ይመልከቱ፡፡) ‹‹#የአካፋው_ሚካኤል››፤ #የካቲት_12/1929ዓ.ም. (#የሰማዕታት_ቀን) (#30_ #ሺህ_ኢትዮጵያውያን_ሰማዕታት_) ፠ ዐጤ ኀይለ ሥላሴ ወደ ሃገራቸው ከተመለሱ በኋላ በ6 ኪሎ ለሰማዕታቱ ሐውልት ቆመ መጀመሪያ የተሠራው አነስተኛ በመሆኑ ኋላ አሁን ያለው ትልቅ ተደርጎ ተሠርቷል፡፡ ፠ ቀኑ እንዳይረሳም #ቤተ_ሳይዳ ተብሎ ይጠራ የነበረው ሐኪም ቤት #የካቲት_12_ሆስፒታል ተባለ፡፡ ፠ በጀግንነት ለተዋጉት አርበኞች በ1934ዓ.ም. በአዲስ አበባ ‹‹የአርበኞት ትምህርት ቤት›› ተሠራ፡፡ ፠ በ1923 ዓ.ም. ተመሥርቶ የነበረውና በእቴጌ መነን ይጠራ የነበረው ትምህርት ቤትም ቆይቶ የካቲት 12 ትምህርት ቤት በመባል ተሠየመ፡፡ ፠ ከ8 ዓመት በኋላም (ጥቅምት 23 በ1937 ዓ.ም.) የሰማዕታቱ ዐፅም ተሰብስቦና ፈልሶ በ4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በክብር እንዲያርፍና መቃብር ቤት እንዲሠራለት ተደረገ፡፡ (በነገራችን ላይ የዛሬን አያድርገውና /በስመ ታዋቂና ባለሀብት እየተባለ ሆነ እንጂ/ የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ጀግኖች አርበኞች የሚቀበሩበት ቤተ ክርስቲያን ነበር)፡፡ በሐውልቱ ላይ ያለው ጽሑፍና ግጥም እንዲህ ይነበባል፤ #‹‹ዝንቱ ውእቱ ምዕራፈ አዕጽምቲሆሙ ለብዙኃን ኢትዮጵያውያን እለ ተቀትሉ በግፍዕ በእደዊሆሙ ለሕዝበ ኢጣሊያ ፋሽስታውያን አመ ፲ወ፪ ለየካቲት በ፲ወ፱፻፳ወ፱ ዓ.ም.፤ ወተቀትሎቶሙኒ ኮኑ በውግረተ አእባን ወበአብትር፥ በመክርይ ወበመስኤ፥ በመሕፄ ወበዕፀው፥ በመብረቀ ሐፂን ወበፀዓዕ፥ ወበውዕየተ እሳት ውስተ ቤቶሙ፡፡ ወበራብዕ ዓመት እምዘኮነ ዝንቱ ነገረ ግፍዕ ተመይጠ እግዚእነ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እም ሀገረ ብሪታንያ በግርማ መዊዕ፤ ወአቲዎ ብሔሮሙ ሠረዎሙ ለጸላእትነ ወአቀመ ትእምርተ ግዕዛንነ፡፡ ወእምድኅረዝ አዘዞሙ ለኅሩያኒሁ ከመ ያስተጋብኡ አዕጽምቲሆሙ ለእሉ እለ ተቀትሉ በግፍዕ ወያንብርዎሙ ውስተ ዝንቱ መካን ቅዱስ ዘሕኑፅ ለዝክረ ነገር ወለዝክረ ስሙ፤ ወኮነ በዓለ ፍልሰቶሙ ወተጋብኦቶሙ ለእሙንቱ አዕጽምተ ምውታን በ፲ወ፬ ዓመተ በዓለ ንግሡ ለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትየጵያ አመ ፳ወ፫ ለጥቅምት በዕለተ ኀሙስ በ፲ወ፱፻፴ወ፯ዓ.ም.፡፡›› ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

‹‹#የአካፋው_ሚካኤል››፤ #የካቲት_12/1929ዓ.ም. (#የሰማዕታት_ቀን) (#30_ #ሺህ_ኢትዮጵያውያን_ሰማዕታት_) ፠ ውለታን የማትረሳ ቤተ ክርስቲያናችን እነዚህን ሰማዕታት በአዲስ አበባ 6 ኪሎ
+3
‹‹#የአካፋው_ሚካኤል››፤ #የካቲት_12/1929ዓ.ም. (#የሰማዕታት_ቀን) (#30_ #ሺህ_ኢትዮጵያውያን_ሰማዕታት_) ፠ ውለታን የማትረሳ ቤተ ክርስቲያናችን እነዚህን ሰማዕታት በአዲስ አበባ 6 ኪሎ መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ቀድሞም ይከበራል፤ ከ2ት ዓመት ወዲህ ደግሞ ከአዲስ አበባ ዩነቨርሲቲ የተገኘው የቅዱስ ሚካኤልም አብሮ ወጥቶ ይከበራል፡፡

ዝክረ ቅዱስ ያሬድ ዘየካቲት እንደተለመደው በተለያዩ መርሐ ግብሮች የሚዘከር በመሆኑ እንዳያመልጥዎ፡፡ ቀንና ሰዓቱ፤ ረቡዕ የካቲት 11 በ12 ሰዓት ፠ ቅዱስ ያሬድን ያልዘከረ ምኑን ካህን ኾነ? ፠ ቅ
+1
ዝክረ ቅዱስ ያሬድ ዘየካቲት እንደተለመደው በተለያዩ መርሐ ግብሮች የሚዘከር በመሆኑ እንዳያመልጥዎ፡፡ ቀንና ሰዓቱ፤ ረቡዕ የካቲት 11 በ12 ሰዓት ፠ ቅዱስ ያሬድን ያልዘከረ ምኑን ካህን ኾነ? ፠ ቅዱስ ያሬድን ያልዘከረ ሰንበት ተማሪ ምኑን ሰንበት ተማሪ ኾነ? ፠ ቅዱስ ያሬድን ያልዘከረ ክርስቲያን ምኑን ክርስቲያን ኾነ? ፠ ቅዱስ ያሬድን ያልዘከረ ኢትዮጵያዊ ምኑን ኢትዮጵያዊ ኾነ? የፍኖተ ሕይወት ሰ/ትቤት

#ሰበር_ዜና_ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ራሱን “የኦሮምያ ቤተ ክህነት” አደራጅ አድርጎ የነበረው ቡድን ሦስት አመራሮች ክህነታቸው እንዲያዝ እና ከማንኛውም መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲታገዱ፣ በየአካባቢው የከፈቷቸው ጽሕፈት ቤቶች እንዲዘጉ እና በሕግ እንዲጠየቁ ውሳኔ አስተላለፈ። ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem

/ከትናንቱ የቀጠለ……/ #ክፍል_፬ #ለየካቲት_12_የሰማዕታት_ቀን_መዳረሻ፥ #ለየካቲት_23_የአድዋ_ድል_መነሻ፥ #ለሚያዝያ_27_የድል_ቀን_ማስታወሻ_ #የካቲት_12 (#30_ #ሺህ_ኢትዮጵያውያን_ሰማዕታት_) (‹‹#የአካፋው_ሚካኤል››፤) ለሁለተኛ ጊዜ ሃገራችንን ልተወር በመጣችው የጣሊያን የጦር ሹም የነበረው ግራዚያኒን ለመግደል ጀግኖቹ አብርሃም ደቦጭና ሞገስ አስገዶም በጣሉት አደጋ ግራዚያኒ በመቁሰሉና አመራሮቹ በመሞታቸው የተቆጣው የጣሊያን ጦር በአዲስ አባባ በየካቲት 12/1929ዓ.ም. ለቅ/ሚካኤል ወርኋዊ በዓል በየቤተ ክርስቲያኑ የተገኙትን (ሔሮድስ ምጽዋት አደርጋለሁ ብሎ እንደሰበሰበው ጣሊያንም ለምጽዋት የተሰበሰቡትን ኢትዮጵያውያን ጨምሮ)ና በየቤቱ በመግባት 30 ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን በአሰቃቂ ሁኔታ በአካፋ ጭምር እንደ ቅጠል አረገፏቸው፤ 30ሺህ ሰማዕታት በመባልም ይታወቃሉ፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላም የደብረ ሊባኖስ ገዳም መነኰሳትን አርበኞችን ደብቃችኋል በሚል በተቀደሰው ስፍራ ተረሸኑ፡፡ በዚህም ምክንያት ጣሊያን ይህን አሰቃቂ ግፍ በአካፋ ጭምር ስትሠራና የሰማዕታቱን የከበረ አካል በአካፋ በመሰብሰቧ ‹‹#የአካፋው_ሚካኤል_›› በሚል መጠሪያ ይጠራል፡፡ በተለይም በ6 ኪሎ በመንበረ ልዑል ቅ/ማርቆስ የቅ/ሚካኤል ታቦተ ሕግ ወጥቶ በልዩ ሁኔታ ይከበራል፡፡ (እናት ቤ/ክ መቼውንም ቢሆን የሃገርና የቤ/ክ ባለውለታዎችን አትዘነጋምና!!!!) (እናቶቻችንና አባቶቻችን እንደነገሩን ከ6 ኪሎ የደብራችን አጥቢያ ምዕመን በቅርብ ርቀት የሚገኙ በመሆኑ፤ አያቶቻችን የተሠዉ እናዳሉና ግማሾቹም ይህንን ዜና ሲሰሙ ወደ 6 ኪሎ እየሄዱ ሳለ ሲሰሙ ከመንገድ የተመለሱ እንዳሉም ልብ ይሏል፡፡) ዐጤ ኀይለ ሥላሴም ወደ ሃገራቸው ከተመለሱ በኋላ በ6 ኪሎ ለሰማዕታቱ ሐውልት ቆመ መጀመሪያ የተሠራው አነስተኛ በመሆኑ ኋላ አሁን ያለው ትልቅ ተደርጎ ተሠርቷል፡፡ ቀኑ እንዳይረሳም #ቤተ_ሳይዳ ተብሎ ይጠራ የነበረው የካቲት 12 ሆስፒታል ተባለ፡፡ ቆይቶ ደግሞ በእቴጌ መነን ይጠራ የነበረው ትምህርት ቤትም የካቲት 12 ትምህርት ቤት በመባል ተሠየመ፡፡ ከ8 ዓመት በኋላም የሰማዕታቱንም ዐፅም ሰብስበውና አፍልሰው በ4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በክብር እንዲያርፍና መቃብር ቤት እንዲሠራለት ተደረገ፡፡ በሐውልቱ ላይ ያለው ጽሑፍና ግጥም እንዲህ ይነበባል፤ #‹‹ዝንቱ ውእቱ ምዕራፈ አዕጽምቲሆሙ ለብዙኃን ኢትዮጵያውያን እለ ተቀትሉ በግፍዕ በእደዊሆሙ ለሕዝበ ኢጣሊያ ፋሽስታውያን አመ ፲ወ፪ ለየካቲት በ፲ወ፱፻፳ወ፱ ዓ.ም.፤ ወተቀትሎቶሙኒ ኮኑ በውግረተ አእባን ወበአብትር፥ በመክርይ ወበመስኤ፥ በመሕፄ ወበዕፀው፥ በመብረቀ ሐፂን ወበፀዓዕ፥ ወበውዕየተ እሳት ውስተ ቤቶሙ፡፡ ወበራብዕ ዓመት እምዘኮነ ዝንቱ ነገረ ግፍዕ ተመይጠ እግዚእነ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እም ሀገረ ብሪታንያ በግርማ መዊዕ፤ ወአቲዎ ብሔሮሙ ሠረዎሙ ለጸላእትነ ወአቀመ ትእምርተ ግዕዛንነ፡፡ ወእምድኅረዝ አዘዞሙ ለኅሩያኒሁ ከመ ያስተጋብኡ አዕጽምቲሆሙ ለእሉ እለ ተቀትሉ በግፍዕ ወያንብርዎሙ ውስተ ዝንቱ መካን ቅዱስ ዘሕኑፅ ለዝክረ ነገር ወለዝክረ ስሙ፤ ወኮነ በዓለ ፍልሰቶሙ ወተጋብኦቶሙ ለእሙንቱ አዕጽምተ ምውታን በ፲ወ፬ ዓመተ በዓለ ንግሡ ለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትየጵያ አመ ፳ወ፫ ለጥቅምት በዕለተ ኀሙስ በ፲ወ፱፻፴ወ፯ዓ.ም.፡፡›› #ራስን ካንገት ላይ ቈራርጦ እየጣለ፤ በችንካር ቸንክሮ ሰው እየገደለ፤ ሰውን ከነቤቱ አብሮ እያቃጠለ፤ ማነው እንደ ፋሽስት በሰው ግፍ የዋለ?፡፡ ሥጋችንን ገድለው ሳይቀብሩ እየጣሉ፤ ስማችንን ገድለው ሊቀብሩት ከጀሉ፡፡ በዚህ ያልነበሩ ሐሰት እንዳይሉ፤ እሊህ አስከሬኖች ይመሰክራሉ፡፡ ይህን ታላቅ ስቃይ መከራና ግፍ፤ ሲያስታውስ ይኖራል የታሪክ መጽሐፍ፡፡ አትርሱት አንርሳው ያስታውሰው ዘራችን፤ ኢጣሊያ መሆኗን መርዛም ጠላታችን፡፡ እናንት አእጽምቶች ዕድለኞች ናችሁ፤ በኃይለ ሥላሴ ትንሣኤ አገኛችሁ፡፡ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem