en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Open in Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 16 052 subscribers, ranking 5 274 in the Religion & Spirituality category and 2 238 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 16 052 subscribers.

According to the latest data from 30 October, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 511 over the last 30 days and by 3 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 23.32%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 10.33% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 3 742 views. Within the first day, a publication typically gains 1 658 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 29.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 31 October, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

16 052
Subscribers
+324 hours
+1077 days
+51130 days
Posts Archive
ኦ ፍጡነ ረድኤት … ብለው ኢትዮጵያውያን በእምነት ኾነው ሲጠሩት፤ ከዐይን ጥቅሻና ከዐውሎ ነፋስ ይልቅ ፈጥኖ የደረሰላቸው የሊቀ ሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓሉ ነው፡፡ #ኮከበ ክብር፥ *ሊቀ ሰማዕታት፥ *መክብበ ሰማዕታት፥ *የፋርስና የቤሩት ኮከብ፥ *የልዳ ፀሐይ፥ *የኢትዮጵያ ገበዝ፥ *ባለ ፀዓዳ ፈረስ፥ *፸ ነገሥታትን ድል ያደረገ፥ *በሕይወቱ ክርስትናን ያስፋፋ፥ *፫ት ጊዜ ሞቶ ፫ት ጊዜ የተነሣ፥ *፯ት አክሊላትን የተቀናጀ፤ *እመቤታችንን በጣም ስለሚወድ ስሙ ከስሟ፥ ዝክሩ ከዝክሯ ጋር፥ ፍልሰቱ ከፍልሰቷ ጋር እንዲኾን ያደረገችለት፤ የካቲት 23 ከዋይዜማው ጀምሮ በተለይም በአ.አ መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ. የሚቆመውን ሙሉውን ሥርዐተ ማኅሌት አቅርበንላችኋል፡፡ ሥርዐተ ማኅሌቱን ሌሎችም እንዲደርሳቸው ከዚህ በታች የሰፈረውን ገጻችንን LIKE LIKE እንዲያደርጉ ያስተዋውቁ፤ INVITE INVITE INVITE ያድርጉ፡፡ (የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት) (የቅድመ ዓድዋን ታሪክና የዓድዋን ታሪክ ነገ ይጠብቁ)፡፡

ወላዲተ አምላክ ማርያም፡፡ በፎቶ የምትመለከቱት የዛሬ ወር በጥር 21 በአንዲት እኅትና ቤተሰቧ የተሠራችውን የእመቤታችን ሕንፃ ቤ.ክ ምረቃ ላይ የሰ/ት/ቤት አባላቶቻችን ሲያገለግሉ የሚያሳይ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያኗ ስም #መጠቆሚያ_ማርያም ስትባል፡፡ የምትገኝበት ቦታ ጊንጪ ጃልዳ፥ ጮሜ ተኮማ የ1 ሰዐት የእግር መንገድ ተጕዞ፡፡ የተመሠረተችው በ1942ዓ.ም.፡፡ ‹‹#እንነሳና_እንስራ_አሉ_እጃቸውንም_ለበጎ_ነገር_አበረቱ፡፡›› ነህ. 2፥18 (ልዩ ማሳሰቢያ፤ እንደ መድኀኔ ዓለም ፈቃድ ሰንበት ትምህርት ቤታችን በዚህች ደብር ላይ ሕንፃውን ካሠራችው እኅትና ቤተሰቦቿ ጋር በመሆን በርካታ አገልግሎቶችን ለማከናወን ስላሰበ፤ አገልግሎቱ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ የሰ/ት/ቤቱን ጽቤት ማነጋገር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡)

ምሴተ ጥበብ ዘዓድዋ፤ የማይቀርበት መርሐ ግብር፡፡ በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰ/ት/ቤት፡፡ ዐርብ የካቲት 22/2011ዓ.ም. ከ11፡30 ጀምሮ፡፡

20 ቀን ቀረው፤#ፍኖተ_ሕይወት_/#የሕይወት_ጕዞ/፤ #መጋቢት_15/2011ዓ.ም.፡፡ ወደ #ኵሉ_ወይን_ቅድስት_አርሴማ፡፡ **በብዙሃን ዘንድ ዜናው ያልተሰማው፤ 3ት ትላልቅና ሌሎችም ክፍሎች ያሉት፤ ብዙ ንዋያተ ቅድሳት የተገኙበትና በቁፋሮ የተገኘው ጥንታዊ ዋሻ ይጎበኛል፤ **ምክረ አበው በሊቃውንት መምህራን፣ ዝማሬ በዘማርያን ይቀርባል፡፡ **ከሰ/ትቤታችን ምሥረታ ጀምሮ የነበሩና አሁንም ያሉ አባላት በአንድነት የሚሳተፉበት ዐቢይ ጕዞ፡፡ **ለበለጠ መረጃ፤ 0977 30 17 18

ዛሬ የሊቀ መልአኩ ወርኀዊ የበዓል ውሎ በታላቁ ደብራችን ይህንን ይመስላል፡፡

፨፨የፌስቡክ/Facebook/ ((Add Friend)) ገጻችን ስለሞላ፤ የሚከተለውን የ‹‹LIKE›› ገጽ አድራሻችንን <<LIKE>> ያድርጉ ለሌላውም ያስተዋውቁ፡፡ (የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት) ወይም https://www.facebook.com/%E1%8B%A8%E1%89%80%E1%8C%A8%E1%8A%94-%E1%8B%B0%E1%89%A5%E1%88%A8-%E1%88%B0%E1%88%8B%E1%88%9D-%E1%88%98%E1%8B%B5%E1%8A%80%E1%8A%94%E1%8B%93%E1%88%88%E1%88%9D%E1%8A%93-%E1%8B%B0%E1%89%A5%E1%88%A8-%E1%89%B5%E1%8C%89%E1%88%83%E1%8A%95-%E1%89%85%E1%8B%B1%E1%88%B5-%E1%8C%88%E1%89%A5%E1%88%AD%E1%8A%A4%E1%88%8D-%E1%89%A4%E1%89%B0-%E1%8A%AD%E1%88%AD%E1%88%B5%E1%89%B2%E1%8B%AB%E1%8A%95-%E1%8D%8D%E1%8A%96%E1%89%B0-%E1%88%95%E1%8B%AD%E1%8B%88%E1%89%B5-%E1%88%B0%E1%8A%95%E1%89%A0%E1%89%B5-%E1%89%B5%E1%88%9D%E1%88%85%E1%88%AD%E1%89%B5-%E1%89%A4%E1%89%B5-1620932764891482/ ፨፨#በቴሌግራምም_ሊያገኙን_ከፈለጉ (የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት) ወይም https://t.me/medihanaelem

#ከሰይጣን_ጋር_የተደረገ_ቃለ_ምልልስ (ተዋስኦተ ጳውሊ ምስለ ሰይጣን)፤#ክፍል#፰_ #ዲያብሎስ_የሚፈራቸውና_የማይፈራቸው_ሰዎች አባ ጳውሊ፤ በውኑ ከአዳም ልጆች የምትፈራው አለን አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ ከአዳም ልጆች የምፈራቸውም የማልፈራቸውም አሉ አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ የምትፈራቸውና የማትፈራቸው እነማን እንደሆኑ ሳትዋሽ እውነቱን ትነግረኝ ዘንድ በአምላኬ ስም አምልሐለሁ አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ አስቀድሜ ሁሉን ነገርኩህ፡፡ #ስለ_እግዚአብሔር_ፍቅር_ብሎ_ሥጋውን_ለመከራ_የሚሰጠውን_ሰው_እፈራለሁ፡፡ ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ብሎ ሥጋውን ለመከራ የማይሰጠውንና ከመከራ የሚሸሽውን አልፈራውም አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ ዳግመኛ አሁን ከነገርከኝ ሌላ ማንን ትፈራለህ? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ #የቅዱሳንን ዐፅምና ዐፅማቸውን የሚጠብቁ #መላእክትን እፈራለሁ፡፡ ስለ ክርስቶስ ብለው መከራውን በመታገሥ ስለተጋደሉት ተጋድሎ ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ክብር ተዘጋጅቶላቸዋልና፤ ቃል ኪዳንም ተቀብለዋልና፡፡ በቦታቸው እንዳንኖር መላእክት ይከለክሉናል፤ ያባርሩናል፡፡ ኃይላችንም ይደክማል፡፡ #እኛም በዚያ ቦታ የኃጢአት ፍርፋሪ እናገኝ ዘንድ ዘወትር ተግተን እንዋጋለን አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ የተናገርከው እውነት ነው፡፡ በእውነት የቅዱሳንን ምግባርና ትሩፋት ስታዩ በእጅጉ የሚያስፈራችሁና የሚያስደነግጣችሁ አይደለምን? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ አዎ #ፍቅር፥ ቅን ኅሊናና ንጹሕ ልብን፥ ትሕትናን፥ ጾምን፥ ጸሎትን፥ ለመልካም ሥራ መትጋትን ስናይ እንፈራለን፡፡ ይበልጥኑም የድንግል ማርያም ልጅ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማራቸውን #ጸሎት #አቡነ ዘበሰማያትን እንፈራለን አለ፡፡ አባ ጳውሊ፤ የማርያም ልጅ የምትለው ማንን ነው? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ አንተን የፈጠረ እርሱ ነው አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ በእውነት እርሱን ትፈራለህን? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ ከአንተ የተነሳ ወዮልኝ ስሙን እየጠራህ አታቃጥለኝ፡፡ እንዴት አልፈራውም! እነሆ ኃይሌን አድክሟል፤ ብዙ ነፍሳትን አድኗል፤ ከእጄም ማርኳልና አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ ከነገርከኝ በዚህ ዓለም የምትፈሩት ሌላ አለን? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ አዎን አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ እነማን ናቸው? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ #የእርሱ ማደሪያ የሆኑና ደስ የሚያሰኙት ቅዱሳን ናቸው፡፡ ዳግመኛም #እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን ሁሉ እንፈራለን፡፡ ዳግመኛም በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው የተናገሯትን #ጸሎተ ሃይማኖትን እንፈራለን፡፡ በውሃ ምንጭ፣ በባድማ፣ በመቃብር ቤት፣ በወንዝ ስንዘዋወር ወይም እኛ ባለንበት ቦታ ሁሉ #የጸሎተ ሃይማኖትን ጸሎት ስንሰማ እንደነግጣለን፡፡ ዳግመኛም አንዱ ወንድሙን እኔ በድያለሁና #ይቅር በለኝ የሚለውን የይቅርታ ቃል ስንሰማ ደንግጠን ከአጠገቡ እንርቃለን፡፡ ዳግመኛም ቅዱስ #መስቀልና የክርስቶስ #ሥጋና ደም፥ #ንጹሕ ጸሎት ካለበት ቦታ መቅረብ አይቻለንም እንሸሻለን አለው፡፡ (ማቴ.፮፥፲፬፤ ፲፰፥፴፭) #የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችንን ሕዝቡን (በካህናት አንጻር)፤ ነገሥታት፥ መኳንንትና መሳፍንትን በምን እንደሚፈትናቸው… ክፍል ፱.… ይቀጥላል ከነገ ወዲያ ይጠብቁን/ /#ዋልድባ_ዋሊ_ገጽ/

#ከሰይጣን_ጋር_የተደረገ_ቃለ_ምልልስ (ተዋስኦተ ጳውሊ ምስለ ሰይጣን)፤#ክፍል#፯_ #ለሰው በሚፈልገው ሰይጣናት ተመስለው በምትሐት እንደሚገለጹ፤ የሰይጣናት አሳሳች መሆናቸው ለጥቂት ደጋጎች እንጂ (በመጨረሻ በሥራቸው) እንጂ ለሁሉ እንደማይታወቁ፤ በገዳም የሚኖሩትን በምን እንደሚዋጋቸውና እንደሚያሸነፉት፤ ከሰው ልጆች የሚፈራቸውና የማይፈራቸውን/ አባ ጳውሊ፤ ለሰው በምትሐት የምትታዩት በስንት አምሳል ነው? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ ለማሳት እኛ በምንፈልገው መልክ እርያ፥ እባብ፥ ሴት፥ ወንድ፥ ወጣት፥ ሽማግሌ፥ ቀበሮ፥ ጦጣ፥ ዝንጀሮ መስለን መታየት እንችላለን፡፡ ከእኛ እያንዳንዳችን በድንግል ማርያምና በልጇ አምሳል፤ በብርሃን መልአክና በቀደሙ ቅዱሳንና ቀድሞ በሞቱ ሰዎች አምሳልም ቢሆን ሰው በሚፈልገው ሁሉ እንታያለን አለው፡፡ (ሙት ሳቢ የሚባሉትን ልብ ይለዋል)፤ "ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና፡፡ እንግዲህ አገልጋዮቹ ደግሞ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ቢለውጡ ታላቅ ነገር አይደለም፤ ፍጻሜያቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል፡፡" /፪ቆሮ.፲፩፥፲፬/ አባ ጳውሊ፤ እናንተ አሳቾች እንደሆናችሁ ለሰው በምን ትታወቃላችሁ? መጨረሻችሁስ እንዴት ነው? አለው፡፡ ሰይጣን፤ ለጥቂት ደጋጎች ነው እንጂ ለሁሉ አንታወቅም፡፡ በመጨረሻ ሥራችን ግን እንታወቃለን አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ ሥራህ ሁሉ ክፉ እንደሆነ ከአንተ ተረዳሁ አለው፡፡ ሰይጣን፤ እንደ አንተ ንጹሕ የሆነ ሁሉ በክፉ ሽታዬ ያውቀኛል፡፡ ኃጥአን ግን በሽታዬ ለይተው ሊያውቁኝ አይችሉም አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ #አንተ ከክብርህ የተዋረድክ #እንደ አንተ ንጹሕ የሆነ በማለት በውዳሴ ከንቱና በትምክሕት ወጥመድ ጠልፈህ ልትጥለኝ ትፈልጋለህን? እግዚአብሔር የተመኘኸውን አይስጥህ ያሰብኸውንም አይፈጽምልህ፡፡ እኔስ ኃጢአተኛ ነኝ እንጂ ንጹሕና ጻድቅ አይደለሁም፡፡ ዕለተ ሞቴን አስባለሁ፡፡ በፊቴ የእግዚአብሔር ፍርድ አለ አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ አንተ የተረገምክ! ዳግመኛም ስለምጠይቅህ ነገር ምንም ከእኔ እንዳትሰውረኝ በስሙ አምልሐለሁ አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ ከአንተ የተነሳ ወዮልኝ፡፡ እነሆ ከዚህ በፊት ተሰምቶ በማይታወቅ መከራ ተፈተንኩ፡፡ አንተ ክፉ ሽማግሌ በእኔ ላይ ከወዴት እንደሠለጠንክ አላወቅሁም አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ እንዴት አድርገህ ነው በገዳም ከሚኖሩት ጋር የምትዋጋው አለው፡፡ ዲያብሎስም ከአንተ የተነሳ ወዮልኝ በጠላቶቼ መካከል ሰውን የማጠምድበትን ሥራዬን ትገልጥብኝ ዘንድ ትወዳለህን አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ ሥራህን ብቻ የምገልጥ አይደለሁም ለሰው ጥቅም የሌለው የጥበብህንም ፍጻሜ ነው እንጅ አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ አስቀድመን መነኰሳትን የምንዋጋቸው በገዳሙ ቆይታ ላላቸውና በእድሜ በማዕረግ ለሚበልጧቸው ለአበ ማኅበሩ እሺ በጀ ብለው እንዳይታዘዙ፥ ምክራቸውን፣ ተግሣጻቸውን እንዳይቀበሉና እንዳይሰሙ፤ እኔ የምነግራቸውና የማሳስባቸውን ለአበው እንዳይነግሩ በማድረግ ነው፡፡ ዳግመኛም ጥርጣሬንና መሸበርን የልብ ድንጋጤን በላያቸው እናመጣባቸዋለን፡፡ በሐሰተኛ ሕልም እናስታቸዋለን፡፡ በዚህ ባያምኑና ቢያቸንፉን ብዙ የምኞት ፈተናን እናመጣባቸዋለን፡፡ ወርቅና ብር መውደድን የላመ የጣመ መብላት መጠጣትን እናመጣባቸዋለን፡፡ የማይጠቅም ዙረትን እንዲያበዙ እናደርጋቸዋለን፡፡ ሰውን የሚያጣሉና ነገር አመላላሾች እንዲሆኑ የአበውን ምክር እንዳይሰሙ ልቡናቸውን እናደነድነዋለን፡፡ በዚህ አኗኗራቸው በአንድ ቦታ እንዳይጸኑ በየጊዜው ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ እንዲዛወሩና ሥራን እንዳይወዱ ፤ ሌላ የደከመበትን እንዲመገቡ በአፋቸው እኛ ዓለምን ንቀናል እንዲሉ፤ ዓለም ግን ከደስታዋና ከፍላጎቷ ሁሉ ጋር በእነርሱ ላይ በዝታ እንድትታይና መንፈሳዊ ዕውቀትን ትዕግሥትን መረጋጋትን እንዲያጡ እናደርጋቸዋለን፡፡ ሰይጣን፤ ከገዳማቸው በወጡ ጊዜ በነፍሳቸው ለገዳሙ አባት ሊገዙ ከገቡባት ከገዳማቸው ልቡናቸውን እናርቀዋለን፡፡ እኛ የዚህችን ዓለም ሥራ ስለምናሳምርላቸው በስም መነኮሳት ሲባሉ በገዳም መኖራቸውን ፈጽመው ይጠላሉ፡፡ በዚህ ፈትነናቸው ካቸነፉን ሌላ የሚፈተኑበት ምክንያት እናመጣባቸዋለን፡፡ ሌላው በሚሠራው ሥራ በመቅናትና በቂም አንዱ ለአንዱም መልካም ሥራ እንዳይሠራ እንቅፋት እንዲሆነው በማድረግ እንዋጋቸዋለን፡፡ በገዳሙ ውስጥ በሚሰሩት ሥራ ውዳሴ ከንቱን አብዝተው እንዲፈልጉና ራሳቸውን ከወንድሞቻቸው ከፍ እንዲያደርጉ፣ ከራሳቸው ሥራ በቀር የሌላውን እንዲነቅፉ እንዋጋቸዋለን፡፡ ኃላፊውን ዓለም መመኘትንና ሥጋዊ ትምክሕትን ዘወትር በልቡናቸው እናሳድርባቸዋለን፡፡ በዚህ ሁሉ የኃጢአት ወጥመድ ካቸነፉንም ተስፋ እንዲቆርጡ ክፉ ሐሳብን በእነርሱ ላይ ለማምጣት ዘወትር እንበረታለን፡፡ ከዚህ ሁሉ ጋር ዳግመኛ በላያቸው ላይ ጊንጡን እባቡን ቅማሉንና ቁንጫውን ትኋኑን የሚያሰቃዩአቸውን ሁሉ አራዊት እናስነሣባቸዋለን፡፡ ከምግባቸው ዘመሚቱን ትሉን ክፉውን ነገር ሁሉ እናስገባባቸዋለን፡፡ የእጅ ሥራ አዝመራቸውንና እንስሶቻቸውን በአራዊትና በአይጥ በአዕዋፍ በበሽታ በተቻለን ሁሉ እናጠፋባቸዋለን አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ በዚህ በምትዋጋቸው መከራ ምን ትጠቀማለህ? እነርሱስ በምን ያቸንፉሃል አለው፡፡ ዲያብሎስም ፈጣሪያቸውን እንዳያመሰግኑ ተስፋ እንዲቆርጡና የዘለዓለም ሕይወትንም እንድናሳጣቸው ነው እንጂ የምንጠቀመው ጥቅም የለንም፡፡ ዲያብሎስ፤ በምን ያቸንፉሃል ስለምትለኝም ፤ በፍቅር፥ በመታዘዝና በትዕግሥት፤ በጾምና በጸሎት፤ ከቂም በቀል ንጹሕ በሆነ ልቡና፤ ባለመለያየት ወንድሞቻቸውን ፈጽሞ በመውደድ፤ ከዚህ ሁሉ ጋር ትሕትና ከመንፈሳዊ ሥራቸው ሁሉ ትበልጣለችና በፍጹም ሃይማኖት ትሕትናን ቢይዙ ያቸንፉናል፡፡ በመጨረሻም የክርስቶስን ሥጋና ደም በመቀበላቸው ያርቁናል ፤ ያቸንፉናል፡፡ #የክርስቶስ ሥጋና ደም የእኛን መርዝ ያጠፋል፡፡ እሾሃችንንም ይነቅላል ፤ ያቃጥላልና አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ ከእናንተ የተነሳ ለሰው ወዮለት አለ፡፡ የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጀመሪያ በራችሁን ይዝጋ ፤ ወጥመዳችሁን ያጥፋ ኃይላችሁም ያድክም አለው፡፡ ያን ጊዜ የተረገመ ዲያብሎስ አንተ ክፉ ሽማግሌ ከእንግዲህ ወዲህ ምንም ነገር አልነግርህም፡፡ ከአሁን በኋላ ከአንተ ዘንድ ወጥቼ እሄዳለሁ ብሎ ጮኸ፡፡ አባ ጳውሊ፤ ከዚህ የሚበዛ ብዙ የምጠይቅህ አለኝና አንተ ርኩስ የክፉ ሥራ ምሥጢርህን ጨርሰህ ሳትነግረኝ ከእኔ ትሔድ ዘንድ ሥልጣን የለህም፡፡ #ዲያብሎስ የሚፈራቸውና የማይፈራቸው ሰዎች፤ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን በምን እንደሚፈትናቸው… ክፍል ፰.… ይቀጥላል ከነገ ወዲያ ይጠብቁን/ /#ዋልድባ_ዋሊ_ገጽ/

#አዋጅ_አዋጅ፤ #የምሥራች_የምሥራች፡፡ በ1 ወር ውስጥ 3 ዓይነ ሥውራን ዓይናቸው በርቷል (1ዱ ከጅማ አካባቢ የመጣ ነው)፤ መንቀሳቀስ የማይችል 1ድ ሰው ከበሽታው ተፈውሷል፡፡ ሲቈፈር መስቀል ተገኝቷል፡ በታላቁ ደብራችን በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ስር የነበሩት 4ት ጠበሎችን ወደ 8 ከፍ የሚያደርጉ ተጨመሪ #4ት_ጠበሎች_ፈለቁ፡፡ ከቀጨኔ ወደ 19 ቀበሌ መሻገርያ ድልድዩ አጠገብ በታች በኩል ቀድሞም እንደ ጠበል የሚያገለግል ምንጭ ነበር፡፡ ታኅሣሥ 13/2011ዓ.ም. ግን በሦስት አቅጣጫ በብዛት መመንጨት ጀምሯል፤ አንዲት ዓይነ ሰሥውር እኅትንም ፈውሷል፡፡ (እንዚህ የኪዳነ ምሕረት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስና የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጠበሎች ናቸው፡፡) ከ1 ሳምንት በፊት የካቲት 3 ዕለት ደግሞ የእመቤታችን ማርያም ጠበል አዲስ ፈልቋል፡፡ **ቅዳሜ የካቲት 16/2011ዓ.ም. ይባረካል፡፡ (ቦታው ከሽሮ ሜዳ የቋስቋም ታቦት ማደሪያ ወደ ቀጨኔ መሻገሪያ 19 ድልድይ ጋር፡፡ ወይም ከቀጨኔ ከመስ (አዲስ ብርሐን ት/ቤት) ወደ 19 ቀበሌ መሻገሪያ ድልድይ ጋር) (ለማስታወስ ያክል፤ በደብራችን ሥር የሚገኙ የቀደሙት ጥንታውያን ጠበሎች፤ *የቅዱስ እግዚአብሔር አብ ጠበል(ከግቢ ውጭ) *የዮርዳኖስ ጠበል(ከግቢ ውጭ) *የቅዱስ ገብርኤል ጠበል (ከግቢ ውጭ) *የመድኀኔ ዓለም ጠበል (ግቢ ውስጥ)