en
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Open in Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 15 373 subscribers, ranking 5 571 in the Religion & Spirituality category and 2 195 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 15 373 subscribers.

According to the latest data from 05 July, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 30 over the last 30 days and by -4 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 22.23%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 9.08% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 3 418 views. Within the first day, a publication typically gains 1 397 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 20.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 06 July, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

15 373
Subscribers
-424 hours
-197 days
+3030 days
Posts Archive
‹‹#ያገለገለህነሰው_ሞት_ቸል_አትበል፡፡›› ሲራክ 38÷26 ( እያዘንን ጻፍንላቹ ) ደብራችንን ለ54 ዓመታት ያገለግሉትነ መሪጌታ ይሁኔ ፈቃዱ አጭር የሕይወት ታሪክ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡ #መሪጌታ ይሁኔ ፈቃዱ (አጋፋሪ) #ትውልድ ፣ዕድገት እና ት/ት አጋፋሪ ይሁኔ ፍቃዱ ከአባታቸው መሪጌታ ፍቃዱ ተሰማ እና ከእናታቸው ከ ወ/ሮ ለምለም ወርቁ በ 1933 ዓ.ም በጎንደር ክፍለ ሃገር በ ደራ ወረዳ ልዩ ስሙ ደብረ ሲና ማርያም በሚባል ቦታ ተወለዱ መሪጌታ ይሁኔ ፍቃዱ እድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ ከ አስኳላው ትምህርታቸው ጎን ለጎን ከ አባታቸው ከ መሪጌታ ፍቃዱ ከ ቁጥር እስከ ዳዊት ተምረዋል በዲቁና ሃገራቸው ያገለግሉ ነበር:: ከዛም በመቀጠል በደብረ ሲና ማርያም ፀዋአቶ ዜማ ተምረው ካጠናቀቁ በኃላ ወደ ምዕራብ ጎጃም አዊ ዞን ጋጋስታ ጊዮርጊስ በመሄደ ከ መምህር ቢንያም ቅኔን ከነ አገባቡ እና ከነጓዙ ተምረዋል ፡፡ አጋፋሪ ይሁኔ ፍቃዱ በ1954ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከመንፈሳዊው ትምህርታቸው ጎን ለጎን በአስኳላው ትምህርት በመዝለቅ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ በሂሳብ ትምህርት (አካውንቲንግ) ዲፕሎማቸውን ይዘዋል ፡፡ ትምህርት እና #አገልግሎት አጋፋሪ ይሁኔ ፍቃዱ ወደ አዲስ አበባ ከመጡበት ከ1954 ዓ.ም ጀምሮ ማረፊያቸውን በ ታላቁ ደብር ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በማድረግ አቋቋም ከመምህር ገብረ ማርያም ጠንቅቀው በመማር ከዛም ደብራችን እስከ ህልፈተ ሕይወታቸው ቀን ድረስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ካላቸው የቃለ እግዚአብሔር ፍቅር በቀና አገልግሎት ለ54 ዓመታት በጽናት ሲያገለግሉ ኖረዋል ፡፡ አጋፋሪ ይሁኔ ፍቃዱ ከመንፈሳዊው አገልግሎታቸው በተጨማሪ በተማሩበት የቀለም ት/ት በመንግስት ልዩ ካቢኔ እንዲሁም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በሚኒሊክ ሆስፒታል በዋና ገንዘብ ያዥነት ለበርካታ አመታት በቅንነት እና በታማኝነት ሲያገለግሉ ቆይተው እድሜያቸው ለጡረታ ሲደርስ በክብር ተሸኝተዋል ፡፡ አጋፋሪ ይሁኔ ልዩ በሆነው ድምጻቸው እና የቀጨኔ ደብረሳለም የአቋቋም ይት ባህልን ጠንቅቆ በማወቅ እናም ከሰንበት ት/ቤታችን ጋር በመሆን በድምጽ ተቀርጾ እንዲቀር በማድርቅ፤ በልዩ የዜማ እና የድምጽ ፀጋቸው፤ እናወቃቸዋለን ፤ እናስታውሳቸዋልነ ፡፡ #ሕይወት አጋፋሪ ይሁኔ ከትዳር አጋራቸው 2 ወንድ እና 1 ሴት ልጅ አፍርተው 1 የልጅ ልጅ አይተዋል አጋፋሪ ይሁኔ ቅን ታማኝ እና ልዩ የቃለ እግዚአብሔር ፍቅር ያደረባቸው ከሰው ሁሉ ጋር በፍቅር እና በስምምነት የሚኖሩ ትልቅ ትንሽ ሳይሉ ሁሉን በፍቅር የሚያዩ የትህትና አባት ነበሩ :: #ኅልፈት ለጥቂት ቀናት ብቻ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ምክንያት ቃለ እግዚአብሔርን ከ አፋቸው ሳይነጥሉ በ80 ዓመታቸው አርፈዋል ሥርዓተ ግብዐተ መሬታቸው ለ 54 ዓመታት ባገለገሉበት እና ብዙ ደቀ መዛሙርትን ባፈሩበት በታላቁ ደብር በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም እና ደብረ ትጉኃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በወርኃ ሰኔ ቀን 24 2012 ዓ.ም ተፈጸመ፡፡ ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጆቻቸው እንዲሁም ለዘመናት በአንድ መቅደስ ውስጥ አብረው ሲያገለግሉ ለኖሩት ሊቃውንት እግዚአብሔር መጽናናቱን ያድልንን፡፡ በረከታቸው ይደርብን አጭር ሺድዮ ይመልከቱ https://youtu.be/8ZwyVQwEzUg

‹ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት #ሐምሌ 7/2012 ዓ.ም በሐመረ ኖህ ቅድስት ኪዳነምሕረት ገዳም #በሥርዐተ_ተክሊል ጋብቻህን የፈጸምከው የሰ/ት/ቤታች አባል ወንድማችን #እንዳልካቸው_አወቀ ከእህታችን #መስታዎት_ይርጋለም ጋር የፈጸምከው ጋብቻ፤ የአብርሃምንና የሣራን፤ የይሰሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ ፤ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ÷ ያጣምራቹ ÷ ያዋህዳችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ ፤ ቅዱስ #ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኀላ ይከተላቹ፡፡ <<ጌታን እንዲወዱና በአካልም ይሁን በመንፈስ በባሎቻቸው ደስ እንደሰኙ ለእህቶች ንገራቸው፡፡ ልክ እደዚሁ ጌታ ቤተ-ክርስቲያንን እደወደደ ሚስቶቻቸውን እንዲወዱ ለወንድሞች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንገራቸው፡፡>> ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበስ ለፓሊካርፐስ በላከው መልእክቱ፡፡ <ከተጋባቸሁ በኋላ ባልና ሚስተ አንድ አካል ናችሁ፡፡ እንጂ ሁለት ስላይደላችሁ በፍጹም ልባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፈቀሩ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ወንድ ወይም ሌላ ሴት አትፈልጉ ይልቁንም በተቻላችሁ መጠን አንዳችሁ ሌላውን ደስ አሰኙ ፤ በመረዳዳትና በፍጹም ፍቅር ኑሯችሁን ሁሉ አሳምሩ፡፡>> ኢትዮጵያዊው ፈላስፈ ቅዱስ አጼ ዘርአያዕቆብ፡፡

‹ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡›› ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት በሐምሌ 5/2012 ዓ.ም በቀ/ደ/ሰላም መድኃኔዓለም ቤ/ክ #በሥርዐተ_ተክሊል ጋብቻህን የፈጸምከው የሰ/ት/ቤታች አባል እና #ሰብሳቢ_ዲያቆን_ታምራት_ሙሉነህ እና፤ የሰ/ት/ቤታችን አባል የሆንሽው #ሮማን_ለማ፤ የፈጸማቹሁት ጋብቻ፤ የአብርሃምንና የሣራን፣ የይስሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ÷ ያጣምራቹ ÷ ያዋህዳችሁ፤ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ ፤ ቅዱስ ገብርኤል ከፊት ይምራችሁ ከኃላ ይከተላችሁ፡፡ <<ጌታን እንዲወዱና በአካልም ይሁን በመንፈስ በባሎቻቸው ደስ እንደሰኙ ለእህቶች ንገራቸው፡፡ ልክ እደዚሁ ጌታ ቤተ ክርስቲያንን እደወደደ ሚስቶቻቸውን እንዲወዱ ለወንድሞች በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ንገራቸው፡፡>> ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ለፓሊካርፐስ በላከው መልእክቱ፡፡ <ከተጋባቸሁ በኋላ ባልና ሚስት አንድ አካል ናችሁ፡፡ እንጂ ሁለት ስላይደላችሁ በፍጹም ልባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፈቀሩ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ሌላ ወንድ ወይም ሌላ ሴት አትፈልጉ ይልቁንም በተቻላችሁ መጠን አንዳችሁ ሌላውን ደስ አሰኙ ፤ በመረዳዳትና በፍጹም ፍቅር ኑሯችሁን ሁሉ አሳምሩ፡፡>> ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ቅዱስ አጼ ዘርአያዕቆብ፡፡