ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Открыть в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 15 949 подписчиков, занимая 5 311 место в категории Религия и духовность и 2 239 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 15 949 подписчиков.

Согласно последним данным от 22 октября, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 412, а за последние 24 часа — 1, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 25.65%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 10.94% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 4 091 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 1 745 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 28.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 23 октября, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Религия и духовность.

15 949
Подписчики
+124 часа
+1607 дней
+41230 дней
Архив постов
ጥቅምት 29 | አርፍደን ጻፍንላቹህ ታላቁ ገዳማችን አሰቦት ደብረ ወገግንና ደብረ ኪሩብን ለመሠረቱት ለአባታችን ለአቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ በዓለ ዕረፍት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡ ✤✤ #አቡነ_ሳሙኤል-ዘደብረ_ወገግ፡፡ ፠ በታላቁ አባት አቡነ ተክለሃይማኖት ‹እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፥ ጣዖታትን የሚሰብር፣ የሚያጠፋ፣ አጋንንትን በጸሎቱ የሚያርቅ፣ ሕዝብን ከኀጢአት በሽታ የሚያድን፣ ፈጣሪውን የሚያስደስት ደግ ልጅ› ተብሎ በተነገረለት ትንቢታዊ ብሥራት ከደጋግና ከበቁ አባታቸው እንድርያስና ከእናታቸው አርሶንያ ሐምሌ 10 ቀን 1248 ዓ.ም. በቡልጋ (በኢቲሳ ደብረ ጽላልሽ ገዳም) ተወለዱ፤ ሲወለዱም መልካቸው በአራት ልዩ ልዩ ሕብረ መልክ እየተለዋወጠ አንድ ጊዜ እንደ በረዶ፣ አንድ ጊዜ እንደ እሳት፣ አንድ ጊዜ እንደ ልምላሜና ቢጫ ሆነው ታይተዋል፡፡ ፠ስማቸውን ሳሙኤል ብለው የሰየሟቸውና ክርስትናም ያነሷቸው፤ ኋላም መዓርገ ምንኵስናን በደብረ ሊባኖስ የሰጧቸው አቡነ ተክለሃይማኖት ናቸው፡፡ ፠ ብዙ ጻድቃንን (አቡነ ተክለሃይማኖትን፣ ታዴዎስ ዘደብረ ድኁኃን፣ ሮማኖስ ዘደብረ ዋምን፣ አቡነ አኖሬዎስ ዕንቈ ባሕርይ ዘመረግድ ወመስተጋድል ወምግባር ንጹሕን) በሥጋ የሚዛመዱ ናቸው፡፡ ፠ ሃይማኖቱ የቀና ደግ ጻድቅ ንጉሥ ዳዊት በነገሠ ጊዜ አባታችን ሳሙኤል ዘወገግን አገኘውና አባቱ ዓምደ ጽዮን ለሠራው ክፉ ሥራ ‹‹መማጸኛ እንዲሆነኝ በእንድርያስ መቃብር ላይ ቤተክርስቲያን ሥራልኝ›› ብሎ ለመነውና የሩፋኤልን ቤተ ክርስቲያን ሠራለት፡፡ የእንድርያስንም አጽም ከመቅደሱ ስር አኖረው፡፡ ንጉሡም በዚያ በእንደግብጦን አውራጃ ሁሉ ላይ ፓትርያርክ አድርጎ ሾመው፡፡ ፠፠ አቡነ ተክለሃይማኖት ትንቢት እንደተናገሩላቸው አቡነ ሳሙኤል፤ * በሰዎች፣ በባሕርና በዛፍ ላይ እያደሩ ይመለኩ የነበሩ በጣም ብዙ አጋንንትን አጠፏቸው፡፡ * ጠንቋዮችንም በውስጣቸው ካደረባቸው ሰይጣን እያላቀቁ የእግዚአብሔር አገልጋይ ያደርጓቸውና ያመነኩሷቸው ነበር፡፡ * ወንጌልን ዞረው በማስተማር ሐዋርያትን መሰሉ፥ * ከዓላውያን ጋር ለመዋጋት ሰውነታቸውን ለሞት በመስጠት ሰማዕታትን መሰሉ፥ * በጾም በጸሎት በስግደት በተጋድሎ ቅዱሳን ጻድቃንን መሰሉ፥ * ይህን ኀላፊና ጠፊ ዓለም ንቀው በመተው ባሕታውያንን መሰሉ፥ * በደልንና ኃጢአትን በማስተሠረይ ካህናትን መሰሉ፥ * በጽሕናና በቅድስና መላእክትን መሰሉ፤ * ብዙ አስደናቂ ተአምራትንም በማድረግም ይታወቃሉ፤ ከእነዚህም ጥቂቶቹ በትእምርተ መስቀል አድርገው እንደሙሴ ባሕርን ለሁለት ከፍለዋል፣ እንደ ኢያሱ በጸሎታቸው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ ሳሙኤል ተጋድሏቸውን ፈጽመው ከጌታችን ታላቅ ቃኪዳን ተቀብለው በዚህች ዕለት (በጥቅምት 29) በኦጋዴን ዘርዘር በተባለ ቦታ በሰላም አርፈዋል፤ ከ7 ወራት በኋላ ሠምረ ክርስቶስ የተባለ ልጃቸው ሥጋቸውን አፍልሶ በደብረ ወገግ በክብር አሳርፎታል፡፡ ፠ አቡነ ሳሙኤል የአሰቦት ደብረ ወገግን (ምዕራብ ሐረርጌ) ና ደብረ ኪሩብ (አፋር) ገዳምን ያቀኑ፥ ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑና፤ የመሠረቱት ገዳም የምሥጢርና የብዙ ስውራን መኖሪያ የኾነላቸው፥ ምስራቅ ኢትዮጵያን እስከ ሞቃድሾ ድረስ በወንጌል ያረሱ፥ አረማውያንን ያጠመቁ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ፠ ከአቡነ ተክለሃይማኖት በኋላ ከተሾሙት 12ቱ ንቡራነ ዕድ አንዱ ናቸው፤ ሃገረ ስብከታቸውም ሐረርና ሱማሌ ነው፡፡ የአቡነ ሳሙኤል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡ ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘፍቅዳቲሁ ራብዕ፤ ውእቱ ልኩእ ዲበ ረቀ ሰማይ ሳብዕ፡፡ ሊቀ ካህናት ሳሙኤል ዘደብተራ ሐዲ ምሥዋዕ፤ አስተስሪ ኀጣውእየ በደመ ነቢብ በግዕ፤ ለቤዛ ሙታን ዘሞተ በግፍዕ፡፡ (ሳሙኤል ሆይ ቊጥሩ ዐራት ለኾነ በሰባተኛው የሰማይ ብራና(ወረቀት) ለተጻፈ ስም አጠራርህ ሰላምታ ይገባል፤ የሐዲስ መሠዊያ አገልጋይ፥ የካህናት አለቃ ሳሙኤል ሆይ፤ ለሰዎች ቤዛ ለመኾን በግፍ በሞተ በነባቢ ክርስቶስ ደም ኀጢአቴን አስተሥርይ፡፡) /ታሪኩን ለዘገበልን ወንድማችን አምላከ አቡነ ሳሙኤል በረድኤት ፥ በበረከት ፥ በጤና ይጠብቅልን፡፡/ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

ሥርዓተ ማኀሌት ዘወርኀ ጽጌ ‹‹ዘላይ ወዘታች››ቤት ፫ኛ ዙር ዓመተ ፤፭ኛ ሳምንት፣ ጥቅምት ፳፱ በዓለ ወልድ

ወረብ | ብፁአን አበዊነ አረጋዊ .. | በደብረሰላም ሊቃውንት ዝማሜ ※ጥቅምት14፤2013 ዓ.ም በዓለ አቡነ አረጋዊ ወገብረክርሰቶስ ወሙሴ ብእሴ በዩቲዩብ ገጻችን ላይ ይመልከቱ https://youtu.be/3o4wj7Qqcaw

※ጥቅምት14፤2013 ዓ.ም | በዓለ አቡነ አረጋዊ ወገብረክርሰቶስ ወሙሴ ብእሴ ከፎቶ ማሕደራችን
+6
※ጥቅምት14፤2013 ዓ.ም | በዓለ አቡነ አረጋዊ ወገብረክርሰቶስ ወሙሴ ብእሴ ከፎቶ ማሕደራችን

---------- ዝማሜ | ዘእምደብረ ደናግል |በፍኖተ ሕይወት | በሕፃናት ክፍል| ※ጥቅምት14፤2013 ዓ.ም | በዓለ አቡነ አረጋዊ ወገብረክርሰቶስ ወሙሴ ብእሴ በዩቲዩብ ገጻችን ላይ ይመልከቱ https://youtu.be/8TaHMwbZ-KQ

※ጥቅምት14፤2013 ዓ.ም | በዓለ አቡነ አረጋዊ ወገብረክርሰቶስ ወሙሴ ብእሴ ከፎቶ ማሕደራችን
+5
※ጥቅምት14፤2013 ዓ.ም | በዓለ አቡነ አረጋዊ ወገብረክርሰቶስ ወሙሴ ብእሴ ከፎቶ ማሕደራችን

ሥርዓተ ማኀሌት ዘወርኀ ጽጌ ‹‹ዘላይ ወዘታች››ቤት ፫ኛ ዙር ዓመተ ፤፭ኛ ሳምንት፣ ጥቅምት ፳፱ በዓለ ወልድ ሙሉውን ሥርዓተ ማኀሌት ለማግኝት ወደ facebook ገጻችን (like page) 👇 ይሂዱ
ሥርዓተ ማኀሌት ዘወርኀ ጽጌ ‹‹ዘላይ ወዘታች››ቤት ፫ኛ ዙር ዓመተ ፤፭ኛ ሳምንት፣ ጥቅምት ፳፱ በዓለ ወልድ ሙሉውን ሥርዓተ ማኀሌት ለማግኝት ወደ facebook ገጻችን (like page) 👇 ይሂዱ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool

———— ወረብ | #ትምስል እምኪ | በ ዲ/ን ፍቅረሥላሴ እና ፀጋዬ | ከማኀሌተ ጽጌ በየቲዩብ ገጻችን ላይ ያምልከቱ https://youtu.be/_COmSOCC9hY ከማኀሌተ ጽጌ 2013 በቀጨኔ ደብረሰላም መድኀኔዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ -------------

ታላቁ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ #ገብርኤል #ቤተክርስቲያን፤
ታላቁ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ #ገብርኤል #ቤተክርስቲያን፤

ማኀደረ ሰላምነ ቅድስት #ደብረሰላም ✤ታላቁ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን፤ (ስብስብ 3)፤ # የ116 ዓመታት ዕድሜ ያለው ጥንታዊ የኢያሱ ደብር፡፡ ‹‹በወርቅ ወበዕንቊ ሥርጉት ደ
ማኀደረ ሰላምነ ቅድስት #ደብረሰላም ✤ታላቁ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን፤ (ስብስብ 3)፤ # የ116 ዓመታት ዕድሜ ያለው ጥንታዊ የኢያሱ ደብር፡፡ ‹‹በወርቅ ወበዕንቊ ሥርጉት ደብረ ሰላም፤ ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ›› ለዛቲ ቤት ሣረራ ኢያሱ ቀዲሙ ለዛቲ ቤት፤ ወፈጸመታ ንግሥት ዘውዲቱ፡፡ (ይህችን ደብረ ሰላምን በመጀመሪያ አቤቶ ኢያሱ /አልጋ ወራሽ ልጅ ኢያሱ/ (ክፍለ ያዕቆብ) በሐምሌ 26 ቀን 1903 ዓ.ም. መሠረታት፤ ንግሥት ዘውዲቱ አሁን ያለውን ሕንፃው ቤ.ክ ጥቅምት 27 ቀን 1913 ዓ.ም አስፈጸመች፡፡) ስለ ታላቁ ደብር ብዙ ነገር ባወራን ደስ ባለን ነበር ….. የሰላም አምላክ የፍቅር ጌታ ያደረባት ደብረ ሰላም ብዙ ነገሮች አሏት፤ የብዙ ሊቃውንት መፍለቂያ፤ የላይ ቤት አቋቋም፣ የተክሌ ዝማሜና የሸዋና የራሱ የደብሩ ቀለም እንደ ወንዝ የሚፈስባት፤ ታሪካዊ ቅርሶችን የያዘ ቤተ መዘክር (Museum)ና ቤተ መጻሕፍት የሚገኙበት፤ ደብሩን አገልግለው ወደ ሌላ ደብር የሚዛወሩ ካህናት ኹሌም በዓይናቸው የደብሩ ፍቅር ውልብ የሚልባቸው፤ ምዕመናኑ በአጸዱና በግርማ ሞገሱ ኹሌም የሚደነቁበት፤ ስዕለት ሰሚ ታቦታት ያሉበት፤ 4ት የሚጠጉ ፈዋሽ ጠበሎች የሚገኙበት፡፡ ጽዶቹ ሳይቀሩ #በ72 አርድዕት ቅዱሳን አምሳያ የተተከሉበት፤ በቀድሞ ዘመን መዐዛ ቅዳሴ የተሰኘው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ቅዳሴ በወርኃ ጽጌ የሚቀድስበት፤ 3 ጳጳሳትን ያፈራ፣ ……. ደብር ነው፡፡ ✣ ለደብረ ሰላም ይደልዋ ስብሐት፤ እስመ በውስቴታ ኀደረ መድኀኔዓለም (በደብረ ሰላም በውስጧ መድኀኔዓለም ስላደረ ምስጋና ይገባታል፡፡) በዓሉ በዚሁ ደብር በታላቅ ድምቀት ይከብራል፡፡ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool

#በምዕራብ ወለጋ እና በጉራፈርዳ እንዲሁም በቤንሻንጉል በግፍ #የተገደሉ ዜጐች አስመልክቶ ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ በከፊል ---------- ፟አላስፈላጊ በሆነ ምክንያት በግፍ ለተገደሉትና ሕይ
#በምዕራብ ወለጋ እና በጉራፈርዳ እንዲሁም በቤንሻንጉል በግፍ #የተገደሉ ዜጐች አስመልክቶ ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ በከፊል ---------- ፟አላስፈላጊ በሆነ ምክንያት በግፍ ለተገደሉትና ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን በቤተ ክርስቲያናችን ስም ልባዊ ሐዘናችንን እየገለጽን ዳግሞ እንዲህ ዓይነት ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እንዳይፈጸም መንግሥት ለዜጐች አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግ ወንጀለኞችንም ለፍርድ እንዲያቀርብ እያሳሰብን መላው ኢትዮጵያውያን ልጆቻችንም በቀጣይ ለጋራ ሰላምና አንድነት እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ የሞቱ ወገኖቻችንን ነፍስ ይማርልን፡፡፟ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ፤ ይቀድስ፤ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!! አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ---------- በሞት የተለዩንን ወገኖቻችንን እግዚአብሄር በእቅፉ ያኑርልን አሜን! https://t.me/medihanaelem