en
Feedback
የጥበብ ማዕድ

የጥበብ ማዕድ

Open in Telegram

ዝም ብለህ ተቀላቀል!

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel የጥበብ ማዕድ

Channel የጥበብ ማዕድ (@yetbebmead_ab) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 15 974 subscribers, ranking 5 411 in the Religion & Spirituality category and 2 116 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 15 974 subscribers.

According to the latest data from 25 June, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 604 over the last 30 days and by -23 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 2.64%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 2.10% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 419 views. Within the first day, a publication typically gains 334 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 10.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
ዝም ብለህ ተቀላቀል!

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 26 June, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

15 974
Subscribers
-2324 hours
+1447 days
+60430 days
Posts Archive
የአክስቴን ቤት ከረጅም ጊዜ በኋላ ትናንትና ሄድኩኝ ። ቤታቸው ስገባ አላመኑኝም ። በተለይ አክስቴና ልጇ ( ቃልኪዳን ) እግሬ በራቸውን እንደረገጠ ነው መጥተው ጥምጥም ያሉብኝ ። ሰላም ከተባባልን በኋላ ቤቱ ሞቅ ሞቅ አለ ። በተለይ የአክስቴ ፊት ሎተሪ እንደወጣለት እድለኛ ተፍነክንካለች ። ልጇ ቃልኪዳን የ ስድስት ዓመት ህፃን ናት ። ማንም ሰው እነሱ ቤት እንደማይመጣ ያወኩት ደስታቸውን ካየሁ በኋላ ነው ። " እና አክስቴ ኑሮ እንዴት ነው " ? አልኩ ድምፄን ከፍ አድርጌ ( ማዕድ ቤት ናት ) " እግዚአብሔር ይመስገን " አለች " ቃልዬ ደሞ አድጋልሻለች " አልኩ እቅፌ ውስጥ ያለችውን ቃልን እያየሁ .. "አዎን !! ይመስገን እ..... ግን " ብላ ዝም አለች " ግን ምን ? አክስቴ ? " አልኩ ግርምት ይሁን ድንጋጤ በማላውቀው ስሜት ፊቴን ቅጭም አርጌ ። " አይይይ!! ብሩኬ ልጄ እኮ በዘመዶቿ ናፍቆት እየከሳች ነው ። አንተም ይሀው እዚ ቤት ከመጣህ ዛሬ ድፍን ሶስት አመቱ ። ልጄ ሰው ያስፈልጋታል አንተም ይህ ስሜት ይገባሃል ብየ ነበረ ግን አንተም ያው ነህ ። " አለችኝ ንግግሯ ምክር ይሁን ዘለፋ ባላውቅም ግን ልቤን ነው የነካችው ። የልጇን ፊት አየሁ ፤ እውነትም ሰው ናፍቋታል ። እኔ ሃሳቤ ደርሼ በቶሎ ለመመለስ ነበረ ። ግን የቃልዬን ደስታ እንዴት ላጨልመው ? አንድ ሰው ሎተሪ ደርሶት ከተደሰተ በኋላ ይቅርታ ተሳስተን ነው ባለ ዕድሉ ሌላ ሰው ነው ሲባል የሚሰማው ስሜት አለ አይደል ። የኔም በቶሎ መመለስ ለቃልዬ እንደሱ መስሎ ታየኝ ። " ቃልዬ ምን ልግዛልሽ " ? አልኳት አቅፌ ፀጉሯን እያሻሸሁ " ልትሄድ ነው እንዴ " ? አለች በሚጣፍጥ አንደበቷ " አረ !! አልሄድም ለምን እንደዚ አልሽ" ? አልኳት " የ ማሚ ጓደኛ መስከለም አዚ መጥታ ልትሄድ ሽትል ነው ብል ምትሸጠኝ " አለች " ልሂድ ወይስ እዚ ልቆይ" ? አልኳት " እኛ ጋ አብለህ ኑል የትም አትሂድ " ብላ ጥብቅ አርጋ አቀፈችኝ ። እሺ ለዚች ትንሺዬ ልጅ ምን ልበል ? ነገ እመጣለሁ ብዬ በውሸት ተስፋ ሆዷን ልሙላ ? ስራ ምሰራው ከሰኞ - ቅዳሜ ነው ያለኝ የእረፍት ቀን እሁድ ነው እሱም አብዛኛውን እሁድ ማሳልፈው በስብሰባ ነው ስለዚህ አይመቸኝም ብዬ ግልፁን ላውራ ? ከራሴ ጋ ሙግት ገጠምኩ ። በመጨረሻም አንድ ነገር ወሰንኩ !! እንደምንም ብዬ አሁድ እሁድ ለመምጣት ለራሴ ቃል ገባሁ ። ✍ Henok

መብራት የጠፋ ለት የቤተሰቦችህ ልብ በርቶ ታገኘዋለህ።

ደስታዋ ማደጓን ማሳየት ነበረ!      የተሻለ ያገኘች ቀን ፍጥነቷ ራሱ ልቧ ምን ያህል እንደፈካ ይገልጽ ነበር።      በዚህ የተነሳ ማጣትን ረገምኩት ሁሌ ፊቷ ላይ ደስታን ስላሳጣኝ!!!

እንድታወራቸው ፈቀዱልህ ማለት ያደረካቸውን ረሱልህ ማለት አይደለም!!! እንደውም መንቀሳቀስህን የሚጠብቅ ፈንጂ ላይ እንደቆምክ ቁጠረው!!!

በ እናት ሆድ ውስጥ ጥጋብ ነው ርሀብ የለም::በ እናት ሆድ ውስጥ ሙቀት ነው ብርድ የለም። ከሁሉም በላይ ግን በ እናት ሆድ ውስጥ ጣዕር የለም ። መስራትም የለም። በምቾት መንፈላሰስ እና በለስላሳ ውሀ ውስጥ መንሳፈፍ ነው። ይህ ሁሉ ድሎት በተወለድንበት ቅፅበት ይለወጣል። ወተንፈስ ግድ ይላል ርሐብን ለማስታገስ መጥባት እንጀምራለን። ይበርደናል ሙቀት ለማግኘት ከሌላው እንጠጋለን ለመኖር አለበለዚያ መኖር የለም መታፈን በርሀብ አለንጋ መቆላትና በብርድ ቆርፍዶ መሞት። የፍርሐታችን ሁሉ መነሻ ይሆናል በእናታችን ማህፀን የምናውቀው መኖር ብቻ ነው። መወለድ አለመኖርን አመልካች ነው ። 📖 አለመኖር !

" ሜሉዬ" አልኩኝ ( ፊቷን አንገቴ ውስጥ ቀብራ ጥብቅ ! አድርጋ አቅፋኛለኝ ) " እእእእእ " አለች ( በእንቅልፍ ሰመመን ውስጥ ሁና ) " ነገ በጠዋቱ ቁርስ እንድትሰሪልኝ እሺ " አልኳት " እእ
" ሜሉዬ" አልኩኝ ( ፊቷን አንገቴ ውስጥ ቀብራ ጥብቅ ! አድርጋ አቅፋኛለኝ ) " እእእእእ " አለች ( በእንቅልፍ ሰመመን ውስጥ ሁና ) " ነገ በጠዋቱ ቁርስ እንድትሰሪልኝ እሺ " አልኳት " እእእእእእእ " አለች እእእ ብለሻል አዎ ! አልሰማሁም እንዳትይ " ኡፍፍፍፍፍፍፍ !!! እሺሺሺ" አለች ተናዳ😡 እኔም ስልክ ማፍጠጤን ትቼ በሃሳብ ባቡር ተሳፈርኩ ። ለካ ብዙ ከማውራት " እእእእእእእ" ብሎ ማለፍ ይቻላል ። እንዴት ነው " እእእእእእእ " መልስ ሚሆነው ? እንዴት ነው በ " እእእእእእእ" መግባባት ሚቻለው ? እእእእእእእ ራሱ ምንኛ ነው ? እኔና ሜሉ ግን በ እእእእእእ ተግባባን ። እኔ ብዙ አወራለሁ እሷ እእእእእ ትላለች ። በአላዋቂነት ብዙ ከማውራት በአዋቂነት እእእእእእእ ማለት ብዙ ያግባባል ። ብዙ ከማወራ ብዙ ባስብ ይሻላል ። የበዛ ወሬ ውሸትን ይወልዳል ውሸት ደግሞ ውዱን የሰውን ልጅ ርካሽ ያደርጋል ። " እእእእእእእ" ✍ Henok

ቤተሰብ ይህ ሁሉ የቤተሰብ ቁጥር ይዘን ተመልካችም እያለ ስለምን የወደዱትን ፣ ያነበቡትን ሐሳብ አስተያየት ለምን አትሰጡበትም እንዲሁም ማበረታቻ ይሆን ዘንድ ለምን #like አያደርጉትም?! ካልወደዱትም እንደዛው…

. . አንቺ ጋር ስጣላ... መንግስትን ተሳደብ ፣ ተሳደብ ይለኛል ከሰደብኩት ደሞ ፣ አስሮ ይገርፈኛል ከገረፈኝ ደሞ... ለጊዜውም ቢሆን ፣ አንቺን ያስረሳኛል! ከረሳሁሽ ደሞ... አጣኋትኝ ብዬ  ፣ አላስብም ቅንጣት ተሳድቦ መገረፍ.... ሳይሻል አይቀርም፣ አፍቅሮ ከማጣት፡፡ (በላይ በቀለ ወያ)

አንዳንድ ሰው ሐሳብና ችግሩ ሸክም ሆኖበት እንኳን ለሰው ደስታ ይደክማል።

ውድቀት መነሻው ራስን ካለመግዛት ነው።

ጥበቡ ወርቅዬ say's
ካንቺ ባላገኝ የልጅ ፍሬ አልቀይርሽም በሠው እኔ ሚዛን ደፋቶአል ፍቅሬ አሂሂ ካንቺ ባላገኝ የልጅ ፍሬ አልቀይርሽም በሠው እኔ ሚዛን ደፋቶአል ፍቅሬ አሂሂ......🥹❤️‍🔥
 የምር ግን እንደዚህ አይነት ወንድ አለ?🥺 ቆይ አንችስ ፍቅረኛሽ መውለድ ባይችል አብረሽው ለመኖር ምን ያህል ዝግጁ ነሽ? ፍቅር ማለት እስከዚህ ድረስ ነው እድሜ ልክሽን የተመኘሽውን እናትነትሽን እንኳን ልትተይለት የምትችይው ትልቁ መስዋትነት የሚጠይቅ ነገር ነው ። ብዙ sacrifice ለመክፈል ዝግጁ ካልሆናቹ በቃ አትፈቃቀሩ መጨረሻው ቁስል ነው 🥺💔

ደስታዋ እኮ የልጇ ደስታና ስኬት ነው።        እናቶች በምድርም በሰማይም ክፉ አይንካቸው!

መብራት ሐይል ጊቢ ውስጥ ጀነሬተር አየሁ እንዴት ነው ነገሩ?🤔

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ዒድ ሙባረክ!

ከሌለህ የሚፈልጉህ ባንክ ቤት ብቻ ናቸው እሱንም አካውንት ከሌለህ እንድታወጣላቸው!        #ለፈገግታ

፡ "ማፍቀር ማለት በጨለማ ሰማይ ላይ ከፈሰሱት ኅልቆመሳፍርት ከዋክብት፤ አንዷን መርጦ እንደ ጨረቃ ማግዘፍ ነው፡፡" (ከዕለታት ግማሽ ቀን) ፡

የዘመኑ አስር ብሮች እንደ ሰዉ ሆድ የባሳቸው ናቸው።