cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

°•°ቢስሚከ ነህያ °•°

🦋አዋቂ ወይም ተማሪ አለያ አድማጭ ሁን አራተኛን ግን አትሁን ትጠፋለህና (ነብዩ ሙሐመድ ሰዐወ) @HAYAttuna JOIN አጭርና አስተማሪ ፅሁፎችን በ @HAYAttuna ክሮስ ለመስራት ሀሳብ ለመስጥት በ @Muuheee

Show more
Advertising posts
584
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Repost from "ኡማ ቲቪ " Tv
መሲ ከተባለች ውጭ ከምትኖር እህቴ በውስጥ የደረሰኝ መልዕክት ነው 🙏 እዴት ነህ ወንድሜ እኔ እደምታውቀው በጣም ብዙ ፈተና አልፊያለው በተለይ ይሄን ሁለት አመት ከጤናየ እስከ ስራየ ያልሄድኩበት ያልወሰድኩት መድሀኒት የለም ከሩቅያ ጀምሮ ሁለት ሶስቴ ሞክሪያለው በክፍያ ግን ከሁለት ወር ወዲህ ትልቅ የሚባል ለውጥ አይቻለው በምን አትለኝም ካለኝ ላይ ለ 4 ሙስሊሞች ጤፍ ገዛው የድብቅ ሰደቃ ከዛ በኃላ አልሀምዱዲላ በጣም ለውጥ አለኝ ይሄን የምልህ እንደኔ የተጨነቁ የታመሙ እስቲ ትንሽየ ሰደቃ ያርጉና ይሞክሩት ሸር አርገው ገጽህ ላይ ©copy
Show all...
ሥራ ለሌላችሁ፣ ማሻሻል ለምትፈልጉ፣ አዳዲስ ዕውቀቶችን ማግኘት ለምትሹ‼ ====================================== (በዚህ ወቅትም ሥራ አጣሁ የሚል ሰው አለ? በትዕግስት ይነበብ!) • (OpenAI ChatGPT፣ MS Bing Chat፣ Alphabet - Google Bard፣ Anthropic - Claude፣ xAI Grok) * (ይህ ጽሑፍ በቀጥታ ዲናዊ ሳይሆን ዱንያዊ (አካዳሚክ ነክ) ነው።) || ✍ ሁላችንም እንደምናውቀው በአሁኑ ወቅት የሥራ አጥ መጠን በዝቷል። የባለፈ አመቱና የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ውጤት ለብዙዎቻችን አነጋጋሪ ሆነ እንጂ አልፈው ወደ ዩኒቨርስቲው ገብተው ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎችም እጣ ፈንታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ከሆኑ አመታት በፊት ሩቅ ሳንሄድ ያውም በኛ እድሜ አንድ ሰው ድግሪ ካለው ተለምኖ ነበር የሚቀጠረው። በወቅቱ ዲፕሎማ ያለው ሁሉ በሙያው ይቀጠር ነበር። ቀስ በቀስ ዲፕሎማ እየቀረ የዲግሪም ተፈላጊነት እየቀነሰ መጣ። አሁን አሁን ደግሞ ማስተር ያለው ጭምር ሥራ እያፈላለገ ነው። ፕሮፌሰርና ልምድ ያለው ማስተርስ ካልሆነ በስተቀር የቅጥር ነገር እንደምታዩት ነው። ያን ያክል ሁሉ አመት ዩኒቨርስቲ ውስጥ በአሳይመንት፣ በፕሮጀክትና በፈተና ሲጠገረር የነበረ ተማሪ ገና ሊመረቅ ሱፉን ሲለብስ ደስታው ግማሽ ይሆናል። ሱፉን ካወለቀ በኋላ የት እንደሚቀጠር ሲያስበው፤ ዳግም ቤተሰቡ ጋር ሂዶ መቀመጥን ሲያስበው ይጨንቀዋል። «ሥራ አገኘህ?» የሚለው የዘመድ አዝማዱና ጓደኛው ጥያቄ ያማርረዋል። የሚያሳዝነው ደግሞ እንደምንም ተብሎ ቅጥር ሲገኝ (ያንኑም ባልተማሩት ፊልድ)፤ በአለቃ መሳቀቁን ተውትና የደመወዙ አለመበርከት። የወር ደመወዝ ወጣ ብለህ ስትደሰት፤ የተበደርከውን ሳትከፍል ያልቃል። አሁንም ለቀጣዩ ወር ተስፋ እንዳደረግክ በዚህ ዑደት ህይዎት ከእጅ ወደ አፍ ሆና ትቀጥላለች። ጭራሽ ልጆችን የምታስተምር፣ የቤት ኪራይና መሰል የቤተሰብ ወጪ ካለብህ'ማ ተወው። ልጆቼ ከአለባበሳቸውና ከሚማሩበት ት/ቤት ጀምሮ ከሌሎች እንዳያንሱ ብለህ ትጥራለህ። ግን… ስለ ችግሩ ይህቺን ታክል ካነሳሁ፤ ሌላውን ሁላችሁም በየቤታችሁ ስለምታውቁት ልተወው። መንግስት ቅጥር ማቆሙን ባለፈ አሳውቋል። 12ኛ ክፍል ላይ ደርሶ የማያልፈውን ተማሪ ብዛት እያዬን ነው። ተሳክቶላቸው ያለፉትም ከተመረቁ በኋላ የሚቀጠሩበት ቦታ አጥተው የሚሆኑትን እያዬን ነው። ይሄን ይሄን ስንመለከት፤ ከታች የሚማረው የአንደኛ ደረጃና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ከላይ እየሆነ ስላለው ነገር አልሰማ ይሆን እንደ? ያስብላል። ወደ መፍትሄው ልምጣ፦ ከላይ ካሉት የቱንም ያክል ተማሪ አላለፈም ቢባል፣ የቱንም ያክል ተማሪ ሥራ አጣ ቢባል ጆሮ ሳትሰጡ ዝም ብላችሁ ተማሩ። ባይሆን ላይ ስትደርሱ ምን መማር እንዳለባችሁ እወቁ። ወደ ጥቆማዬ ስሄድ፦ መጀመሪያ በአይቲ፣ በኮምፒዩተር ሳይንስ፣ በሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ፣ በኢንፎርሜሽን ሳይንስ፣ በኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግና ከነዚህ ጋር ተያያዥ በሆኑ መስኮች የተመረቃችሁና በፊልዳችሁ ያልተቀጠራችሁ፣ የተቀጠራችሁበት ደመወዝ አርኪ ላልሆነላችሁ፣ ጭራሽ ሥራ ላልያዛችሁ… የምላችሁ ነገር ቢኖር፤ ሥራና በቂ ደመወዝ ያጣችሁት የፊልዱን ስም ብቻ ይዛችሁ ብቃቱን (ስኪሉን) ሳትይቁ ቀርታችሁ ስለሆነ ፈጥናችሁ በራሳችሁ ስኪሉን ያዙና ሥራ በቆንጆ ደመወዝ የት እንደሚገኝ ጠይቁኝ። ከነዚህና ተያያዥ ፊልዶች ውጭ በሆነና በአሁኑ ወቅት ተፈላጊ ባልሆነ መስክ የተመረቃችሁና እየተማራችሁ ያላችሁ ደግሞ፤ ብትቀጠሩም ባትቀጠሩም ወደነዚህና ተያያዥ መስኮች ሺፍት አድርጉ። ①) መጀመሪያ ስኪሉን የት እንማር፣ እንደት እናግኝ፣ እንደት እንፍጠን? * √ ስኪሉ የሌላችሁ የነዚህ የቴክ ፊልዶች ተመራቂዎችና የሌሎች ፊልዶች ተመራቂዎች በአሁኑ ወቅት ለሥራ ብቁ የሚያደርጋችሁን መስክ መማር ከፈለጋችሁ፤ ወደ ኢንተርኔት ጎራ በሉ። ግን ኢንተርኔት ላይ ብዙ ነገር ስላለ ወደየትኛው ለሚለው ደግሞ ሜንቶር ቢኖራችሁ ጥሩ ነው። አቅጣጫውን የሚያመላክታችሁ ጠቋሚ አካል ማለቴ ነው። የቴክ ፊልዶቹ ባክግራውንድ ያላችሁ በራሳችሁ ብትማሩ ጥሩ ነው። ምክንያቱም ቲወሪ ፓርቱን ስለምታውቁት ሰርች እያደረጉ ማንበብና ፕራክቲስ በማድረግ ስኪሉን መያዝ ስለምትችሉ። ሌሎቻችሁ ግን ትንሽ ቻሌንጅ እንዳያደርጋችሁ የምትማሩበት ተቋም ቢኖር ጥሩ ነው። ችግሩ እነዚህን መስኮች የሚያስተምር ተቋም የለም። ግን እንግሊዝኛ ቋንቋ የምታውቁ ከሆነ የዚህ መስክ ዘርፎች ብዙ ቢሆኑም አንዱን መርጣችሁ ስኪሉን ብትቀስሙ በቀላሉ ትረዱታላችሁ። ደስ የሚለው ነገር ደግሞ በነዚህ መስኮች ኢንተርኔት ላይ በቂ ሪሶርስ አለ። በጣም አክቲቭ የሆነ ኮሚኒቲም አለ። ግን እንደ ጀማሪ በቀላሉ ከምን ተነስታችሁ ወደ ምን መሄድ እንዳለባችሁ የሚጠቁሟችሁ ቡት ካምፖች ነበሩ። እንደ አለመታደል ሆኖ እኛ ሃገር ግን በብዛት የሉም። የማውቃቸውን ወደዚህ መስክ ዓይናችሁን ከምትገልጡበት መስክ አስጀምረው መሠረት ያሲዟችኋል የምላቸውን ሁለት ቡት ካምፖች ግን ሳልጠቁማችሁ አላልፍም። 1) Evangadi Tech ይሰኛል። አሜሪካ ነው ያሉት። ግን በተለይ እዛው አሜሪካ ያላችሁ ብትማሩባቸው ትጠቀማላችሁ። ለሌሎቻችሁ ደግሞ የነፃ ስኮላርሺፕ አላቸው። ግን ለ30 ሰው ስለሆነ በዛ ቢባል 10 ሰው ብቻ ቢደርሰው ነው። ሃገር ውስጥ ያላችሁት ግን የክፍያውን አትችሉትም ብዬ ነው። አጠቃላይ 1,800$ ዶላር ስለሆነ በኛ በብላክ ብታባዙት ወደ 200 ሺህ ብር ይሆንባችኋል። ድረ ገፃቸው፦ evangadi.com የቴሌግራም አካውንት ያላቸው አይመስለኝም። 2) እዚሁ ሃገር ውስጥ ያለ Mizan Institute of Technology (MiT) የሚባል ቡትካምፕ አለ። የነዚህ ክፍያ ሃገር ውስጥ ካላችሁት ጋር የሚሄድ ይመስለኛል። ኮርሱ ለ9 ወር ነው፤ ክፍያው በየወሩ 5 ሺህ ብር ነው። አቅሙ ያላችሁ ብትማሩ ብዙ አመት ሊፈጅባችሁ የሚችለውን ነገር በአጭር አቅጣጫ መያዝ ትችላላችሁ። ድረ ገፃቸው፦ mizantechinstitute.com ተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም አካውንታቸው ላይ ታገኛላችሁ። t.me/MizanInstituteOfTechnology አሁን ላይ በምዝገባ ላይ ስለሆኑ ሳይሞላባችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ። ሁለቱም ተቋማት የሚያስተምሩት ፉል ስታክ ዌብ ዴቨሎፕመንት ሲሆን ሁለቱም በኦንላይን ነው የሚያስተምሩት። ስለዚህ ከግል ሥራችሁ ጋር ሳይጋጭ ቦታ ሳይገድባችሁ እንደፈለጋችሁ መማር ትችላላችሁ። የእንግሊዝኛ ዕውቀቱ ያላችሁና አቅጣጫውን የምታውቁ ግን፤ በራሳችሁ አንብቡና ቶሎ ወደ ሥራው ግቡ። በነዚህ መስኮች ላይ ዕውቀቱ ኖሯችሁ በበፊቱ አድካሚ በሆነው መንገድ እየለፋችሁ ያላችሁ ካላችሁ ደግሞ፤ ምናልባት ካላወቃችሁ ከላይ መግቢያዬ ላይ የዘረዘርኳቸውን ቻትቦቶች ተጠቀሙ። እጅግ በጣም ሥራችሁን ያቃልሉላችኋል። በብዙ እጥፍ ፍጥነታችሁን ይጨምሩታል። ባይሆን የተሳሳተ ምላሽ እንዳላቸውም እወቁ። እያንዳንዳቸውም የራሳቸው ጠንካራና ደካማ ጎን ስላላቸው ማንን ለምን ጉዳይ መጠቀም እንዳለባችሁ ለዪ። ምንም ግንዛቤው በሌላችሁ ነገር ላይ አታዋሯቸው፤ የተሳሳተ ነገር ሲመልስሏችሁ ትክክል ነው ወይንስ አይደለም ብላችሁ የምትለዩበት ግንዛቤ ሊኖራችሁ ይገባል። ያንን መለየት ከቻላችሁ ላይፋችሁን ያቀሉታል።
Show all...
የምታገኙባቸው ሊንኮች፦ 1) ChatGPT → chat.openai.com 2) Bing Chat with GPT-4 → የሞባል አፕ አላቸው። https://play.google.com/store/apps/details?id=com.microsoft.bing 3) Google Bard → bard.google.com 4) Claude → claude.ai 5) Grok → grok.x.ai (Testing phase) ከፊሎችን በብሮውዘሮች ኤክስቴንሽን መልክና በቴሌግራም ቦት መልክ ታገኟቸዋላችሁ።
Show all...
ቻትጂፒቲ አሁን ላይ በኢትዮጵያ ስልክ ቁጥር መክፈት ስለሚቻል አካውንቱ ክፈቱና ያለ ቪፒኤን ተጠቀሙበት። የቢንግን ቻት በራሳቸው በኢጅ ብሮውዘር ማግኘት ትችላላችሁ። የቻትጂፒቲን GPT-4 ሞደል ኢንተግሬት አድርገውት ነው። ከቢንግ ሰርች ኢንጂን ጋር ስለተያያዘም፤ ከቻትጂፒቲ በላይ ከ2021 ወዲህ ያሉ የቅርብ ጊዜ መረጃዎችንም ያካትታል። በተጨማሪም DALL·E 3 ጋር ስላላያያዙት ኢሜጅ ጀነሬት ማድረግ ይችላል። የጎግል ባርድንም በቪፒኤን መጠቀም ትችላላችሁ። ከጎግል ሰርች ኢንጂን ጋር መያያዙም ዳታውን የተገደበ አያደርገውም። አዳዲስ መረጃዎችን ያካትታል ክላውድንም እንደዛው፤ ግሮክ ግን ገና እየተጀመረ ስለሆነ ለጊዜው እኛ ሃገር የለም። ለወደፊቱ ግን ከትዊተር (ኤክስ) ጋር ስላጣመሩት በ2024 ከቶፕ ሦስቱ ቻትቦቶች መካከል ይመደባል ተብሎ ይጠበቃል። የኦፕን ኤአይን GPT-3&4 ሞደል ኢንተግሬት ያደረጉ በርካታ የኤይ ቱሎችንም ስለምታገኙ፤ ከፊሉ ለሪሰርች፣ ከፊሉ ለኮዲንግ… እንደየፍላጎታችሁ መጠቀም ትችላላችሁ። በርግጥ ራሱ ኦፕንኤአይም GPT-4 Turbo አዲስ ሞደል እስከ አፕሪል 2023 ድረስ ያሉ fixed dataset (curated and pre-processed) የያዘ አስተዋውቋል። ግን አመቱ ሲጨምር ይሄም ወደ ኋላ ይቀራል። ለዛም ነው እነ ባርድና ቢይንግ ቻት የራሳቸው ብሮውዘር ስላላቸው እንዲሁም የወደፊቱ ግሮክ ኤክስ ስላለው አዳዲስ መረጃ ማካተት የሚችሉበት መንገድ መኖሩ የሚጠቅማቸው። • ②) ስኪሉን ከያዝን በኋላ የት እንሥራ? ስኪሉን ከያዛችሁ በኋላ ሃገራችን አሁን ካለችበት እድገት አንፃር የናንተን ስኪልን የሚመጥን መቀጠሪያ ቦታ ላታገኙ ትችላላችሁ። ግን ደግሞ ስኪሉ በደንብ የገባው ሰው በርካታ ፕሮብለሞች ያሉት በእንደዚህ አይነቱ ባላደጉ ሃገራት ውስጥ ነውና ያንን ችግር የሚፈታ መፍትሄ በዕውቀትህ ታግዘህ ካመጣህ መንግስት ራሱና ጠካቶችህ ሳይቀሩ ይቀበሉሃል። ይሄን ማድረግ ካልተቻለ ደግሞ ከያዝከው ስኪል ጋር የሚሄድ ቆንጆ ፕሮፋይል ታዘጋጅና ወደ LinkedIn,Turing እና UpWork አካውንት ከፍተህ ጎራ በል። ያኔ ራስህን ለሥራ ክፍት መሆንህ አሳውቅ፤ ከአራቱም የዓለም አቅጣጫ በዶላርና በዩሮ የሚከፍልህ ይመጣልሃል። ያንን በኢትዮ ብር እየመነዘርክ ፈተና ብለህ መኖር ነው። ጭራሽ የተወሰኑ ልምዶችን ስታካብት ስትፈልግ Freelancer ሆነህ፣ ስትፈልግ ሪሞትሊ ተቀጥረህ ትሠራለህ። ቋሚ ሠራተኛ እንዳይቀጥሩ እንዲሠራላቸው የሚፈልጉት ነገር ጊዚያዊ ነገር የሚሆንባቸው አሉ። እነርሱ እንዲህ አይነት ሥራ የሚሠራልን ብለው የሥራ ማስታወቂያ ሲለቁ ከአንተ የሚጠበቀው አለሁ ማለት ብቻ ነው። የማገናኘቱን ሥራ ፕላትፎርሞቹ በራሳቸው ይሠሩልሃል። እና ሥራ ማለት ይህ አይደል? ወይንስ ሥራ ማለት ለአንተ በአንድ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ መታዘዝ ነው? ያንኑም ላልረባ ደመወዝ! ያንኑም አለቃህ እንዳያባርርህ ሁሌ ተሳቀህ! ካባረረህ ደግሞ አስበው ድጋሜ ሌላ ቅጥር እስክታገኝ ድረስ የምትሆነውን! በተለይ ቤተሰብ አስተዳዳሪ ከሆንክ! ሌላ ሥራ እስኪገኝ ያጠራቀምኩትን ገንዘብ እጠቀማለሁ እንዳትል እንኳ፤ ያ የማይረባ ደመወዝ እንኳን የሚጠራቀም ሊተርፈው እዳህንም ጨርሶ አልከፈለ! እኔ በእንደዚህ አይነት መልኩ በአጭር ጊዜ የተቀሩ በአካል ጭምር የማውቃቸው ወንድሞች አሉ። አውቃለሁ! ብዙዎቻችሁ መረጃው ስለሌላችሁ ነው። ይሄው ነግሪያችኋለሁ፤ ዛሬ ነገ ሳትሉ ስኪሉን ያዙና ጎራ በሉ። ስኪሉ ኖሯችሁ ይሄን የማታውቁ ካላችሁ ደግሞ ተጠቀሙበት። ግን አብዛሃኛው ስኪሉ ያለው ሰው እነዚህን ነገሮች ጠንቅቆ ያውቃል። ሌላ ጊዜ ደግሞ በሌሎች ነጥቦች ጎራ ለማለት እሞክራለሁ። ጊዜ ካገኘሁ ደግሞ እኔም በነዚህ መስኮች ላይ አንዳንድ የነፃ ሰርቪሶችን ላካፍላችሁ እሞክራለሁ። የበርካታ ወንድምና እህቶችን ህይዎት ሊቀይር ስለሚችል መልዕክቱን ከተጋራችሁት ለሌሎችም ሼር አድርጉት። እስከዛው መዓኩም ሰላሙ-ል'ሏህ! || t.me/MuradTadesse ummalife.com/MuradTadesse
Show all...
01:01
Video unavailableShow in Telegram
አላህን ለመገናኘት ዝግጁ ነህ?
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ለአላህ ስንል እንተባበራት‼ ይህቺ እህታችን እነዚህን ሁሉ ልጆቿን ይዛ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ትገኛለች። ያው እንደ ብዙዎች ቤቷ ተፈርሶባት ነበር። ግን እርሷ ሰለምቴ ስለነበረች አሁን ላይ ለልጆቿ መኖሪያም ሆነ ምግብ ማግኘት ከብዷታል። ሰለምቴ ናት። ቤተሰቦቿ እምነቷን ከቀየረች እንደሚንከባከቧት ነግረዋታል። እርሷ ግን እምነቴን አልለቅም ብላ እስካሁን የዱንያን ችግር ከነዚህ ጨቅላ ልጆቿ ጋር በመጋፈጥ ላይ ትገኛለችና አነሰ በዛ ሳትሉ ሁላችሁም የአቅማችሁን አላህ ከሰጣችሁ ላይ ሰድቁ። የንግድ ባንክ አካውንት፦ 1000574738017  ስልክ፦0902448980 (ባለፈ አካውንቷ ሞባይል ባንኪንግ አልተከፈተም ነበር። ዛሬ ስለተከፈተ በሞባይል ባንኪንግ በማስተላለፍ መሰደቅ ትችላላችሁ።)
Show all...
👍 5
አስቂኝ ክስተት ፈገግ በሉበት‼️ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ✍የመን ውስጥ ዘማር የተባለ ቦታ ላይ አንድ መስጂድ ውስጥ የተከሰተ በጣም አስቂኝ ክስተት ነው አንብበው ሳይጨርሱ በሳቅ ሟቋረጥ ግን አይቻልም¡ || ይህ ክስተት እዚያው መስጂዱ ውስጥ ሶ'ፈል አወል (የመጀመሪያው ሰፍ) ላይ ቆሞ ሲሰግድ የነበረ አንድ ሰጋጅ ነው የሚያስተላልፍልን... * እናም ይህ ሰው እንዲህ ይለናል:- «አንድ ሰው ይሞትና ተሰግዶበት ተቀበረ ከዚያም ከኢሻ ሶላት በኋላ ነእሹ (ጀናዛ መሸከሚያው) ሊመልሱት ይዘውት ወደ መስጂድ ሲመጡ ሰአት ሄዶ ስለነበር መስጂዱ ተዘግቷል። ስለዚህ ኻዲሞች ለፈጅር ሶላት ሲመጡ እንዲያነሱት በሚል ጀናዛ መሸከሚያው ከመስጂዱ በር ከደረጃ ላይ ያስቀምጡታል። : ነገር ግን ሌሊት 9:30 ሰአት አካባቢ አንድ ሰውዬ ወደ መስጂድ ሲመጣ መስጂዱ ዝግ ሆኖ እና በረንዳው ተከፍቶ አገኘው የተወሰነ ቢጠብቅም መስጂዱን የሚከፍተው አጣ  ብርዱ በጣም ሲበረታበት ዞር ብሎ ሲያይ ጀናዛ መሸከሚያው ከአጠገቡ አገኘ በውስጡም ብርድልብስ ነገር አለ። : እና ይህ ሰው አገኘሁ ብሎ ጀናዛ መሸከሚያው ውስጥ ብርድ-ልብሱን ለብሶ ለጥ ብሎ እንቅልፉን ተኛ አባቴ! በብርድ ደንዝዞ የነበረው ሰውነቱ ትንሽ ምቾት ሲያገኝ ነፍሱንም አያውቅ ለጥ ብሎ ተኝቶልሀል... ሃሃሃ! ትንሽ እንደቆየ የመስጂዱ ኻዲም መጥቶ መሲጂዱ ሊከፍት ሲል በረንዳ ላይ ከነእሹ (ጀናዛ መሸከሚያው) ላይ የተኛ ሰውዬ ይመለከታል ከፈጅር በኋላ ሊሰገድበት ያመጡት ጀናዛ መሰለው... : ከኋላውም ሌሎች ሰዎች መጥቶ ግማሹ ሽንት ቤት ሌላው ውዱእ ሊያደርግ ይሄዳሉ ይህ በረንዳ ላይ ተኝቶ የሚያዩት ሰውዬ (ጀናዛ) ደግሞ ሁሉም ቀድመውኝ የመጡ ሰዎች ሊሰገድበት ያመጡት ጀናዛ ነው ብሎ ያስባል በውስጡ... (ያዝ እንግዲህ¡) በዚያ ላይ ፈጅር ነው ሰው ከእንቅልፉ ተነስቶ እየመጣ ነው ያለው ገና በደንብ ያልነቃ ህዝብ ነው። ሊሰገድበት የመጣ ጀናዛ ይሆናል በማለት ተጋግዘው ወደ መስጂድ ኢማሙ ጋር ወደ ሚህራብ አስገቡት። ሃሃ! : ብ ር ድ የቀጠቀጠው ሰውዬ ሲሸከሙት አያውቅ ተኝቷል¡ ህእ! ሰዎቹም የማን ይሁን ብለው አይጠይቁ ገና ከእንቅልፋቸው በደንብ አልነቁም እና ተሸክመው መስጂድ ውስጥ አስገቡት። ፈጅር አዛን ብሎ ለመስገድ ወደ 50 የሚሆኑ ሰዎች ተሰበሰቡ። ይህንን ታሪክ የሚያስተላልፍልን ሰው እኔም ከሰጋጆቹ አንዱ ነኝ የመጀመሪያው ሶፍ ላይ ነበርኩ ይላል። ከፈርድ በኋላ ልንሰግድበት ጀናዛው ከፊት ተደርጎ የፈጅር ሶላት እየሰገድን ነው። እህእ! : ልክ ለሁለተኛው ረከአ ስንነሳ ጂናዛው ሲንቀሳቀስ አየሁ እንዴዴዴ አይኔ ነው ወይስ ምንድ ነው¿ ብዬ አይኔን አበስኩ ጨፍኜም ገለጥኩ መንቀሳቀሱን ግን አልተወም በቃ እንቅልፍ አለቀቀኝም ይሆናል ብዬ አሰብኩ። ነገር ግን ነእሹ በደንብ መንቀሳቀስ ጀመረ ያኔ መረባበሽና መፍራት ጀመርኩ። ይህ የተኛው ሰውዬ ከብርድ ልብሱ ውስጥ ድንገት አንገቱ  አውጥቶ ሰገዳችሁ? ብሎ ጠየቀ። : ያኔ! ሁሉም ሰጋጆች ደንግጦ መተረማመስና መሮጥ ጀመሩ  እኔም አጠገቤ ከነበረው በር ወጥቼ በባዶ እግሬ ሮጥኩኝ ወደ 1 ኪ.ሜ ያክል የሚርቀውን ቤቴን በትንሽ ደቂቃዎች ደረስኩ ደግሞ ባዶ እግሬ መሆኔም የማውቀው ነገር የለም። ኢማሙ (አሰጋጁም) ሲያየው ደንግጦ መሬት ላይ ይወድቋል ሌሎች ሰዎች ግማሹ ከግድግዳ ጋር ይጋጫል ሌላው ደግሞ ልክ እንደኔው በባዶ እግሩ ይሮጣል መስጂድ ውስጥ አንድ ሰው አልቀረም። : አሁንም ሌላኛው በጣጣጣም የሚያስቀው ክስተት ተከሰተ ያ ከሬሳ መሸከሚያ(ከነእሹ) ላይ ተኝቶ የነበረው ሰውዬ ሲነሳ ሰዎች ሲሸሹ ሲሮጡ ሲያይ ከኋላቸው ተከትሎ መሮጥ ጀመረ። እናንተ ምን ሆናችሁ ነው ? ቂያማ ቆሞ ነው እንዴ? እያለ ከኋላ ኋላቸው መሮጥ ጀመረ። ሃሃሃ! : ሰዎቹ ደግሞ ወደ ኋላቸው ሲዞሩ ይህ ሰውዬ እየተከተላቸው  መሆኑ ያያሉ ያኔ ይብስባቸዋል ባለ በሌለ ሀይላቸው ይሮጣሉ። በዚህ መልኩ ሁሉም  ሰላታቸውን አቋርጠው ሮጡ...» ይለናል ቦታው ላይ የነበረ አንዱ ሰጋጅ። t.me//HAYAttuna
Show all...
°•°ቢስሚከ ነህያ °•°

🦋አዋቂ ወይም ተማሪ አለያ አድማጭ ሁን አራተኛን ግን አትሁን ትጠፋለህና (ነብዩ ሙሐመድ ሰዐወ) @HAYAttuna JOIN አጭርና አስተማሪ ፅሁፎችን በ @HAYAttuna ክሮስ ለመስራት ሀሳብ ለመስጥት በ @Muuheee

ፎቶ ①: ወራሪዋ እስራኤል በጋዛ ከተማ ንጹሐን ነዋሪዎች ላይ ህፃናት፣ ሴቶችና አረጋውያን፣ ት/ቤትና ሆስፒታል፣ መጠለያ ካምፕና የእምነት ተቋም ሳትለይ እየፈጸመችው ያለ ያላባራ የቦምብ ማዕበል ፎቶ ②: ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ ወራሪዋ የምድር ጦር ጋዛ ላይ ስለጀመረች የተገደሉባት 11 ወታደሮች √ አሸባሪዋ አሜሪካ በምትሰጣት ዘመናዊ የጦር መሳሪያ በአየር ቦምብ በማዝነብ እንጂ እንደ ጀግና ፊት ለፊት ገጥሞ በማሸነፍ'ማ የለችበትም። ልብ ከየት ተገኝቶ! ጦርነቱ ከተጀመረ 26ኛውን ቀን ይዟል። ወራሪዋ በተለመደው የአሜሪካና አጋሮቿ እገዛ በ1967 በ6 ቀን አሸንፊያለሁ ብላ ስትጎረር ነበር። ግን የአንድት መንደር ታጣቂ ሐማስ የተባለ ቡድን ብቻውን ይሄው አንድ ወር ገደማ ቀጥ አድርጎ ይዟታል። ያውም እርሱ ከአላህ ውጭ ማንም ደጋፊ የለውም። እርሷ ግን የዓለማችን ቁጥር አንድ ጦረኛ በሆነችው አሜሪካና ኃያላን በሚባሉት የአውሮፓ ሃገራት ያላሰለሰ ድጋፍ እየተደረገላት ነው። ጉራ ብቻ መሆኗን ዓለም ታዝቧል። እነዚህ አጋሮቿ ባይኖሩ ኖሮ ደግሞ በ26 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ሐማስ እስራኤልን ተቆጣጥሮ ሊያስገብራት ይችላል። ከዚህ በተጨማሪ ከዐረብ ሃገራት በባሰ መልኩ ሌሎች ሰብዓዊነት ከተሰማቸው ሃገራት ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ክስረት አጋጥሟታል። እንደ ኮሎምቢያ፣ ቺሊና ቦይሊቪያ ያሉ ሃገራት አምባሳደሯን ከማባረር ጀምሮ ከርሷ ጋር ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እስከማቋረጥ ደርሰዋል። ከባለፈው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጀምሮ በርካታ የአውሮፓ ሃገራትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከዷት መሆኑን የሚያሳይ አቋም አንጸባርቀዋል። ኢንሻ አላህ ቀስ በቀስ ከዓለም የተነጠለች ብቸኛ ተገፊ መሆኗ አይቀርም። ጋዛዊያን ግን እንኳን የጦር መሳሪያ ምግብና ውሃ እንኳ እንዳያገኙ ተደርገው ይሄው በፅናት እያሳለፉ ነው።
Show all...
ሰሞኑን የፈለስጢን ጉዳይ ብቻ ነው ጭንቅላቴ ዉስጥ ያለው ። ሀሳቤን ሙሉ በሙሉ ይዞ ያለው። በዚህ ጉዳይ የተያዘ ጭንቅላት ስለሌላ ነገር መናገር እንዴት ይቻለዋል? ፈለስጢን፤ ያች ትንሿ ቁራጭ ጨርቅ የምታህለው ጋዛ ዓለም ሁሉ ብቻዋን ለወራሪ ትቷት ከአየር፣ ከየብስ፣ ከባህር እሳት ይዘንብባት ከጀመረ 3ኛ ሳምንቷን ይዛለች። ተዓምር ነው መቸስ ፅናቷ። በነቢዩ ሶ.ዐ.ወ.  አንደበት "ላ የዱሩሁም መን ኸዘለሁም" "ባትረዷቸዉና ብቻቸዉን ብትተዉዋቸ እንኳ የሚሸነፉ አይደሉም ።" የተባለላቸው የዚያ የተቀደሰው ምድር ሐቅን የያዙ ጥቂት አማኞች እነኚህ ናቸው መሰል።
Show all...