en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)

የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)

Open in Telegram

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።

Show more
2 791
Subscribers
No data24 hours
+87 days
+1730 days
Posts Archive
ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ_ጽንሰቱ
መስከረም ሃያ ስድስት በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ገብርኤልን ወደ በራክዩ ልጅ ዘካርያስ ልኮት መጥምቁ ዮሐንስ ከእርሱ ስለ መወለዱ አበሠረው። ስሙ የተመሰገነ እግዚአብሔር ልጅን ይሰጠው ዘንድ አስቀድሞ ሁል ጊዜ በመጸለይ ወደ እግዚአብሔር ይማልድ ነበር። ልጅ ያልወለደውን እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ምድርን ምሉዋት ያለውን በረከት ያጣ ነው በማለት እስራኤል ይገዳደሩት ነበርና። ልመናውንም ሰማ በቤተ መቅደስም ቁሞ ዕጣንን ሲያሳርግ መልአኩን ላከለት በከበረ ወንጌልም እንደተባለ መንገዱን ይጠርግ ዘንድ በንጉሥ ክርስቶስ ፊት እንደሚሔድ የተነገረለት ታላቅ ነቢይ ዮሐንስ ከእርሱ መወለዱን አበሠረው። ዘካርያስም የሰውነቱን መድከም የመውለጃውም ዘመን እንዳለፈና ፈጽሞ እንዳረጀ የሚስቱም እንዲሁ ዘመኗ እንዳለፈና ፈጽማ እንዳረጀች መካንም እንደሆነች ያውቃልና ስለዚህ ይህ ነገር እንዴት ይሆንልኛል እኔ ያረጀሁ ሽማግሌ ነኝ ሚስቴም እንዲሁ ዘመኗ አልፎ መካን ሁናለች ብሎ የእግዚአብሔርን መልአክ ተከራከረው። መልአኩም እኔ ይህን ልነግርህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወዳንተ ተልኬ ነበር ልትጠራጠር ባልተገባህም ነበር አሁንም ይህ በጊዜው እስቲፈጸም ዲዳ ሁነህ መናገር ይሳንሃል ብሎ ገሠጸው። ዘካርያስም የወልደ እግዚአብሔርን መንገድ የሚጠርግ ዮሐንስ እስከሚወለድበት ጊዜ ድረስ ዲዳ ሆነ። በሚገረዝበትም ቀን የሕፃኑን አባት ዘካርያስን የሕፃኑን ስም ምን ብለው እንደሚሰይሙት ጠየቁት እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ በዚያም ጊዜ አንደበቱ ተፈትቶ እግዚአብሔርን አመሰገነው። ስለ ልጁ ዮሐንስም እርሱ የልዑል ነቢይ እንዲባል መንገዱንም ይጠርግ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ። የቅዱሳኑ ረድኤት በረከት በሁላችንም ላይ ይደር!!

📢የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ 📜የሥራ ዘርፍ ዝርዝሮች:- 1. 💻የጽሕፈትና ጠቅላላ አገልግሎት ባለሙያ 2. 📚የቤተመጻሕፍት ባለሙያ ዝርዝሩን በመመልከት በሰንበት ት/ብቱ ጽ/ቤት ወይንም ከላይ በተጠቀ
+1
📢የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ 📜የሥራ ዘርፍ ዝርዝሮች:- 1. 💻የጽሕፈትና ጠቅላላ አገልግሎት ባለሙያ 2. 📚የቤተመጻሕፍት ባለሙያ ዝርዝሩን በመመልከት በሰንበት ት/ብቱ ጽ/ቤት ወይንም ከላይ በተጠቀሱት የቴልግራም አድራሻዎች በአስቸኳይ እንድታመለክቱ እናሳስባለን።

‹‹እነሆ ክረምት ዐለፈ፤ ዝናቡም ዐልፎ ሔደ፡፡ አበባ በምድር ላይ ታየ፤ የመከርም ጊዜ ደረሰ፡፡ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ፡፡ በለሱ ጐመራ፤ ወይኖችም አበቡ፤ መዓዛቸውንም ሰጡ …›› /መኃ.፪፥
‹‹እነሆ ክረምት ዐለፈ፤ ዝናቡም ዐልፎ ሔደ፡፡ አበባ በምድር ላይ ታየ፤ የመከርም ጊዜ ደረሰ፡፡ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ፡፡ በለሱ ጐመራ፤ ወይኖችም አበቡ፤ መዓዛቸውንም ሰጡ …›› /መኃ.፪፥፲፩-፲፫/
በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።  የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

አቤቱ ኀይልኽን እዘዝ፤አቤቱ ይህንም ለእኛ የሠራኸውን አጽናው። በኢየሩሳሌም ስላለው መቅደስኽ ነገሥታት እጅ መንሻን ለአንተ ያመጣሉ። --መዝ ፷፰፥፳፰-፳፱ በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳ
አቤቱ ኀይልኽን እዘዝ፤አቤቱ ይህንም ለእኛ የሠራኸውን አጽናው። በኢየሩሳሌም ስላለው መቅደስኽ ነገሥታት እጅ መንሻን ለአንተ ያመጣሉ። --መዝ ፷፰፥፳፰-፳፱
በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።  የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

"ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ እንሆ መልካም ነው እንሆም ያማረ ነው።" መዝ.132÷1 ውድ የባለትዳር አባላት እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ የጉባዔያችን ቀን ደረሶ ነገ በ24/01/19 ዓ/ም ከቀኑ
"ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ እንሆ መልካም ነው እንሆም ያማረ ነው።" መዝ.132÷1 ውድ የባለትዳር አባላት እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ የጉባዔያችን ቀን ደረሶ ነገ በ24/01/19 ዓ/ም ከቀኑ 5:00 ሰዓት ጀምሮ ወርሃዊ ልዩ ጉባዔያችን ላይ ልንገናኝ ነው በመሆኑም የጉባዔያችንን ሰዓት አክብረን እንድንገናኝ በአምላከ ቅዱስ ሚካኤል ስም በድጋሚ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን በሰላም ያገናኘን።

ብርሃን ለጻድቃን፥ደስታም ለልበ ቅኖች ወጣ። ፤ጻድቃን፥በእግዚአብሔር ደስ ይበላችኹ፥ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ። --መዝ ፺፮፥፲፩-፲፪ በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/
ብርሃን ለጻድቃን፥ደስታም ለልበ ቅኖች ወጣ። ፤ጻድቃን፥በእግዚአብሔር ደስ ይበላችኹ፥ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ። --መዝ ፺፮፥፲፩-፲፪
በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።  የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል በምኵራብም ትገረፋላችሁ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ። አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ
እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል በምኵራብም ትገረፋላችሁ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ። አስቀድሞም ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበክ ዘንድ ይገባል። ሲጐትቱአችሁና አሳልፈው ሲሰጡአችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁ፥ ዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና። ወንድምም ወንድሙን አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ። ይገድሉአቸውማል፤ በሁሉም ዘንድ ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። --ማር ፲፫፥፱-፲፫
በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።  የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የሐዘን መግለጫ የሰንበት ት/ቤታችን ሥራ አመራር ሰብሳቢ የሆነው የመ/ር ኢ/ር ዳዊት አበበ ወላጅ እናት እንዲሁም የእህታችን ሊዲያ አሰፋ አያት አርፈዋል። ሥርዓተ ቀብራቸው ነገ መስከረም 22/2019 ዓ.ም በለቡ ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ከቀኑ 5:30-6:00 ሰዓት የሚፈጸም በመሆኑ በቀብሩ ላይ መገኘት የምትችሉ ተገኝተን እንዲሁም በመኖሪያ ቤታቸው 43 ቀበሌ አካባቢ በመገኘት እንድናጽናናቸው ይሁን።  የእናታችንን ነፍስ  ይማርልን ። ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com

"...ማርያም ድንግል ምክሆን ለደናግል ፡፡ ይእቲኬ ቤተ ምስኣል ፡፡ ዘአስተዐፀቡ ታቀልል ፡፡ ለኵሉ ፍጥረት ትተነብል ፡፡ በአክናፈ መላዕክት ትትኬለል ፡፡ ይእቲ ተዐቢ እምኪሩቤል ፡፡ ወትፈደፍድ እ
"...ማርያም ድንግል ምክሆን ለደናግል ፡፡ ይእቲኬ ቤተ ምስኣል ፡፡ ዘአስተዐፀቡ ታቀልል ፡፡ ለኵሉ ፍጥረት ትተነብል ፡፡ በአክናፈ መላዕክት ትትኬለል ፡፡ ይእቲ ተዐቢ እምኪሩቤል ፡፡ ወትፈደፍድ እምሱራፌል ፡፡ መንክር ወመድምም ዕበያ ወክብራ ለድንግል ፡፡ ጽሕፍት ውስተ ወንጌል ፡፡ ወዲበ ርእሳኒ አክሊል በትዕምርተ መስቀል ” ቅዱስ ያሬድ          ትርጉሙ “…የደናግል መመኪያ የኾነች እመቤታችን ድንግል ማርያም የተጨነቁበትን ነገር ኹሉ ታቀላለች ፡፡ ለኹሉ ፍጥረት ትማየምተመሰገን። በመላእክት አክናፍ ተከባ የምትኖር የምተመሰገን። አምላካችንን የምንለምንባት የጸሎታችን ማሰረጊያ ናት ፡፡ እርሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች ፡፡ ከሱራፌልም ትልቃለች ፡፡ በወንጌል ውስጥ የተገለጸች በራሷ ላይም በትዕምርተ መስቀል የብርሃን ዘውድ የደፋች የድንግል ክብሯ ፈጽሞ እጅግ ድንቅ ነው ፡፡…” ቅዱስ ያሬድ
ከእመቤታችን፣ ከቅዱስ መስቀሉ፣ ሃይማኖትን ካቀኑ አርዮስን ካወገዙ ከሠለስቱ ምዕት፣ በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን ሁሉ በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።  የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

መስከረም 21 #ብዙኃን_ማርያም በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም ፳፩ ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው፡፡ ጉባዔ_ኒቅያ በ325ዓ.ም አርዮስ የሚባል መናፍቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አርዮስ ክህደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአርዮስ ክህደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!›› የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአርዮስ ክህደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡ በዚህም መሠረት ከሚያዝያ 21 ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 21 ቀን ድረስ 2348 (ሁለት ሺሕ ሦስት መቶ ዐርባ ስምንት) ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል፡፡ ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር ፱ ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን "ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ" ባላቸው ጊዜም ከ (2348) መካከል (318) ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው "ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው" ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም "ሃይማኖት እንደ 318 ቱ ሊቃውንት ይኹን" ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት 318ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው /ዘፍ.፲፬፥፲፬/፡፡ 318ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮስን አውግዘው በመለየት "ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን" የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር ፱ ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም ፳፩ ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት "#ብዙኃን_ማርያም" እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡ 2. ዕፀ መስቀል በሌላ በኩል መስከረም ፳፩ ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ታሪኩም በአጭሩ የሚከተለው ነው፤ ዐፄ ዳዊት መንፈሳዊና ደግ ንጉሥ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ቸነፈር ተከሥቶ ሕዝቡ ስለ ተሰቃየባቸው እጅግ አዘኑ፤ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ባሕታዊ መጥተው "የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አስመጥተህ በአገርህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠርተህ ብታስቀምጥ ረሃቡ፣ ቸነፈሩ ኹሉ ይታገሥልሃል" አሏቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም ከብዙ ገጸ በረከት (ስጦታ) ጋር "የጌታችንን መስቀል ላኩልኝ" የሚል መልእክት አስይዘው መልእክተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱ፡፡ መልእክተኞቹም በታዘዙት መሠረት መስቀሉን ይዘው መምጣታቸውን ዐፄ ዳዊት ሲሰሙ "ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት" ብለው መስቀሉን ለመቀበል ጉዞ ጀመሩ፡፡ ዐፄ ዳዊት ስናር (ሱዳን) ደርሰው ከመልእክተኞቹ ጋር ተገናኝተው መስቀሉን በክብር አጅበው ወደ መካከል ኢትዮጵያ ለማስገባት ሲነሡም ከበቅሏቸው ወድቀው ጥቅምት ፱ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በዚህም ሠራዊታቸው ተደናግጠው የጌታችንን መስቀል እዚያው ትተው የዐፄ ዳዊትን አስከሬን ይዘው ተመለሱ፡፡ መስቀሉ በስናር ከቆየ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ ሲነግሡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ አምጥተው ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ለማስቀመጥ ቢያስቡም ምቹ ቦታ ግን ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው ምቹ ቦታ ሲፈልጉ መስቀሉን በኤረር ተራራ፣ በደብረ ብርሃን፣ በመናገሻ ማርያም ዓምባ፣ በእንጦጦ ጋራ ብዙ ጊዜ አስቀምጠውት ቆይተዋል፡፡ መስቀሉ በእንጦጦ ጋራ ሳለ እግዚአብሔር አምላክ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" የሚል ቃል ለንጉሡ በራእይ ነገራቸው፡፡ መስቀሉን ወደ ወሎ ሀገረ ስብከት እንዲወስዱትም አዘዛቸው፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው በእግዚአብሔር መሪነት መስቀሉን ይዘው ወሎ ሲደርሱም ጌታችን ወደ አምባሰል እያመለከተ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" ይላቸው ነበር፤ ንጉሡ መስቀሉን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ መስቀለኛው የግሸን ተራራን አገኙ፤ በዚያም ቤተ ክርስቲያን አሠርተው በ፲፬፻፵፮ (1446) ዓ.ም የጌታችንን መስቀል በክብር አስቀምጠውታል፡፡ ከዚህ በኋላ ንጉሡ ‹‹መካከሏ ገነት፤ ዳሯ እሳት ይኹን! የበረረ ወፍ፣ የሠገረ ቆቅ አይታደንባት! በድንገት ሰው የገደለ፣ ቋንጃ የቈረጠ ወንጀለኛ አይያዝባት!›› ብለው ዐዋጅ ነግረዋል፡፡ የእመቤታችን ጽላትም አብሮ በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ ስለዚህም መስከረም ፳፩ ቀን በየዓመቱ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ ከበዓሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን። ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው። https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

"ወንድሞች ሆይ መጠራታችሁን ተመልከቱ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኛዎች የሆኑ ብዙዎች ኀያላን የሆኑ ብዙዎች ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም።" 1ኛ ቆሮ. 1÷26
"ወንድሞች ሆይ መጠራታችሁን ተመልከቱ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኛዎች የሆኑ ብዙዎች ኀያላን የሆኑ ብዙዎች ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም።"  1ኛ ቆሮ. 1÷26

እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው።ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን
እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው።ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል።የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤.. --ዮሐ ፲፥፩-፬
በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።  የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

«ቶማስም። ጌታ ሆይ፥ ወዴት እንደምትሄድ አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን ማወቅ እንችላለን? አለው። ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም አለው።» --ዮ
«ቶማስም። ጌታ ሆይ፥ ወዴት እንደምትሄድ አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን ማወቅ እንችላለን? አለው። ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም አለው።» --ዮሐንስ 14፥5-6
በዚህች ዕለት ከሚታሰቡ ቅዱሳን በረከት ያሳትፈን! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ።  የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

#ነገረ_መስቀል ክፍል-5 (የመጨረሻው ክፍል) ጌታ በመስቀል ላይ ሳለ የተናራቸው ሰባቱ የመስቀል ቃላቶች እኒህ ናቸው ፡፡ ሀ- "ወይቤ እግዚእ ኢየሱስ አባ ሥረይ ሎሙ እስመ በዘኢየምሩ ይገብሩ ፡፡" ሉቃ = 23 ፥ 34 ፡፡ ለ- "ነዋ ወልድኪ ፡፡ ወነያ እምከ" -የሐ = 19 ፥ 25 ፡፡ ሐ- "አማን እብለከ እመን ፈድፋደ ከመ ዮም ትሄሉ ምስሌየ በውስተ ገነት ፡፡" ሉቃ = 23 ፥ 43 ፡፡ መ- "ጸማዕኩ ፡፡"የሐ = 19 ፥ 28 ፡፡ ሠ- "ኤሎሄ ኤሎሄ ኤልማስ ላማ ሰበቅታኒ" ማቴ = 27 ፥ 46 ፡፡ ረ- "አባ ውስተ እዴከ አመኀፅን ነፍስየ" ፡፡ሉቃ = 23 ፥ 46 ፡፡ ሰ- "ተፈጸመ ኵሉ ፡፡" ዮሐ = 19 ፥ 30 ፡፡ የዓለም ቤዛ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተናገራቸውን እነዚህ ቃላት፣ በልባችን ሰሌዳ ላይ ተጽፈው ሊኖሩ ይገባል። በአጠቃላይ የመስቀል በዓልን ስናከብር የምናገኛቸው ትምህርቶች ብዙ ቢሆኑም የተወሰኑትን ለመዳሰስ #በአረጋዊ_ኪራኮስ ----ምንም ብናውቅ አረጋውያንን እንጠይቅ ፡፡ ---ወይም ከቀደሙን ለመማር መዘጋጀት ---ኹሉም ነገር ቢኖረንም ለመጠየቅ አንፈር አንፍራ ፡፡ ---ዕውቀት በአባቶች ዘንድ እንጂ በሥልጣን ኀይል ላይ አይደለም ---ነባር ታሪክን ከአበው መጠየቅ በራስ መተማመንን ያስገኛል ፡፡ #በእንጨቶቹ_መደመር ---በኑሯችን ብቻ ሳይኾን እያለፍንም ለሌሎች ብርሃን እንኹን ፡፡ ---ልዩ ልዩ መኾናችን ለአንድነታችን አስፈላጊነትን ያሳያል ፡፡ ---የአስተሳሰረን ማንነት እንዳለን ያመለክታል ፡፡ #መዓዛ_ጢስ ከሩቅ የሚሸት መልካም ስም ሊኖረን ይገባል ፡፡ ---በእሳት በተመሰለ የመንፈስ ቅዱስ ፍቅር ለመቃጠል መዘጋጀት ---በውስጣችን የያዝነው ለብዙዎች ሊተርፍ የሚችል በጎነት አለን ---በአለን ችሎታ ኹሉ ለተቸገሩ ሰዎች የመነሣሣት አቅጣጫን እናሳይ #ቁፋሮ ----በራሳችን ራሳችን መቈፈር መጀመር አለብን ፡፡ ---ምንድነው ያለን ጸጋ (ተውህቦ) ብለን እንጠይቅ ፡፡ ---የምንሰማውን ኹሉ እውነት ብለን አንቀበል ፡፡ እንመርምር ፡፡ ---ውስጣችን የተቀበረ ጠቃሚ ችሎታ እንዳለን መገንዘብ #ስታገኝ የመስቀሉን ችንካሮች ነው ለልጇ ቆስጠንጢኖስ መላኳ ---ከምናገኘው ነገር ኹሉ ለሌሎችም መካፈል እንደሚገባ፡፡ #በመስቀሉ_እንማራለን መስቀል ተመርኵዘን ወንጌል ተጫምተን ሃይማኖትን ሰበክን በክርስቶስ አምነን ማን ያሸንፈናል እኛ ክርስቲያንን ክርስቶስ አለልን! ምንጭ ፦ ከኢትዮጵያውያን አበው ሊቃውንት ትምህርት የተወሰደ! አዘጋጅ፦ ሊቀ ጉባኤ ታረቀኝ (የቅኔና የትርጓሜ መምህር፤ የደብራችን ስብከተ ወንጌል ኃላፊ) #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር #ወለወላዲቱ_ድንግል #ወለመስቀሉ_ክቡር #አሜን!

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

#ነገረ_መስቀል ክፍል-4 ሰላም በስምምነት አብሮ ተከባብሮ ተቻችሎ መኖር ማለት ነው ፡፡ እንዲህ ያለው ሕይወት ደግሞ ፍጹም የዕረፍት ስሜትን የሰጣል ፡፡ ሰው እንዲህ ሲኾን ልክ እንደ ክረምት ወራት
#ነገረ_መስቀል ክፍል-4 ሰላም በስምምነት አብሮ ተከባብሮ ተቻችሎ መኖር ማለት ነው ፡፡ እንዲህ ያለው ሕይወት ደግሞ ፍጹም የዕረፍት ስሜትን የሰጣል ፡፡ ሰው እንዲህ ሲኾን ልክ እንደ ክረምት ወራት በራሱ ሕይወት ውስጥ የዘርእ የአበባ ወርኅ ያልፍና “ ወፍሬሁሰ ለመንፈስ ቅዱስ ተፋቅሮ ፍሥሓ ሰላም ትእግሥት ምጽዋት ኂሩት ሃይማኖት የውሃት ኢዘምዎት ይላል ፡፡” ከተባሉት ከዘጠኙ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬያት ታላቁን ፍሬ ሰላምን ያፈራል ገላ = 5 ፥ 22 ፡፡ በእርግጥ ነቢዩ ኢሳይያስ በ9 ፥ 6 ላይ እንደሚነግረን የሰላም አለቃ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፡፡ እርሱን ሰላም እንያዝ ፡፡ ምድር ክብሩን የምትናገርለትን ፤ ሰማይ የምትመሠክርለትን አይሁድ በጎልጎታ በቀበሩት መስቀል ላይ ተሰቅሎ የአዳነን የሰላምን አለቃ ለመከተል እንድንችል ፡፡ ለዚኽም ነው ቅዱስ ያሬድ “ ትነግር ምድር ፡፡ ወይዜኑ ሰማይ ፡፡ እስመ ተረክበ ዕፀ መስቀል ክቡር በጎልጎታ ዘደፈኑ አይሁድ ፡፡ ይኩን ሰላም ወዛኅን በዲበ ምድር ” ሲል የዘመረልን ፡፡ #የሰላሙ_ንጉሥ_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ለሀገራችን_ሰላም_ያድለን! ክፍል-5 ይቀጥላል! ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። የቴሌግራም ቻናል https://t.me/finotebirhan12 የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12 የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1 የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc