en
Feedback
ሁሌ መረጃ.com/hule merja

ሁሌ መረጃ.com/hule merja

Open in Telegram

የሰው ልጅ መረጃ የማግኘት መብቱ መገደብ የለበትም...እኛም ይህንን ፍላጎት ለመሙላት እዚ አለን፡፡ሁሌ መረጃ ሁሌ እውነት

Show more
600
Subscribers
+124 hours
+67 days
+830 days
Posts Archive
alljobson.com - ስራ እድሎች ከቤተሰብ ጋር ምን አዲስ ስራ እድሎች እንደሚገኙ ታውቀዋለህ? NGO, ባንክ፣ ኢምባሲ እና በቴክኖሎጂ አገልግሎት ላይ ያሉ ስራዎች፣ አዳዲስ ደረጃ ለተማሪዎች፣ ፓ
alljobson.com - ስራ እድሎች ከቤተሰብ ጋር ምን አዲስ ስራ እድሎች እንደሚገኙ ታውቀዋለህ? NGO, ባንክ፣ ኢምባሲ እና በቴክኖሎጂ አገልግሎት ላይ ያሉ ስራዎች፣ አዳዲስ ደረጃ ለተማሪዎች፣ ፓርት ታይም ያሉ ስራዎች። በፍጥነት መረጃ ይቀበሉ። 📱 ስራ ለማግኘት ዝግጅትህ እንደ ምን ነው? ለስራ ፍላጎት, የተለያዩ እድሎች, ግንኙነት፣ እኛ አሁን እንሂድ! 🔍 Перейти 🚀 #ad 📢 🎯 የቴሌግራም ማስታወቂያ በ1 ደቂቃ

እኔ ተጠቃሚ ስለሆንሁ በዚህ ቻናል ያሉ መረጃዎች በሙሉ ተፈጻሚነት እንዳሉ ማረጋገጥ ተከናወናል። ከመለኪያ ማስተላለፊያ ጀምሮ እስከ ቅርጸ ነገር ድረስ በርካታ ስለሆነ እንደ እውነት ተግባራዊ ነው። ቻ
እኔ ተጠቃሚ ስለሆንሁ በዚህ ቻናል ያሉ መረጃዎች በሙሉ ተፈጻሚነት እንዳሉ ማረጋገጥ ተከናወናል። ከመለኪያ ማስተላለፊያ ጀምሮ እስከ ቅርጸ ነገር ድረስ በርካታ ስለሆነ እንደ እውነት ተግባራዊ ነው። ቻናሉ በሚያቀርበው ክርፕቶ ዜና በጣም እንቅስቃሴ አለውFree internet and Safaricom. የሚከተሉት አካላት አይነት ያላቸውን መረጃዎች ለመያዝ ይሞክሩ። #ad 📢 🎯 የቴሌግራም ማስታወቂያ በ1 ደቂቃ.

በቱሉ ካፒ ወርቅ ማዕድን ፕሮጀክት ላይ የነበረው የስራ እንቅስቃሴ መታገዱ ታወቀ በለንደን የአክሲዮን ገበያ የተመዘገበው የማዕድን ኩባንያ "ከፊ ጎልድ ኤንድ ኮፐር" በኦሮሚያ ክልል በሚገኘው ዋናው የቱሉ ካፒ የወርቅ ማዕድን ፕሮጀክት ላይ እየተከናወኑ የነበሩትን ሁሉንም የልማት ስራዎች ማገዱን አስታወቀ። እገዳው የተጣለው ከሶስት ቀናት በፊት በፀጥታ አካላት እና በአካባቢው ማህበረሰብ መካከል ተፈጥሯል በተባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት የሰዉ የህይወት ማለፉን ተከትሎ ነው። በወቅቱ በተፈጠረው ግጭት የኩባንያው ሰራተኛ ህይወት ማለፉ ተረጋግጧል። ኩባንያው ከህብረተሰቡ ተወካዮች፣ ከክልል የስራ ሃላፊዎች እና ከጸጥታ አካላት ጋር በመነጋገር የደህንነት ሁኔታውን ለመገምገም እና ቀጣይ ስራዎችን በሰላም ለመጀመር የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እስኪፈጠር ድረስ የመስክ ስራዎች ሙሉ በሙሉ እንደተቋረጡ ገልጿል። Via Capital Newspaper

አካዳሚክ አቅምዎን ይክፈቱ በ ለኢትዮጵያዊ ተማሪዎች የጥናት ቁሳቁሶች፣ ማስታወሻዎች እና ኪዊዞች 📚; አሁን ትምህርትዎን ያሳድጉ! #ad 📢 InsideAd.
አካዳሚክ አቅምዎን ይክፈቱ በ ለኢትዮጵያዊ ተማሪዎች የጥናት ቁሳቁሶች፣ ማስታወሻዎች እና ኪዊዞች 📚; አሁን ትምህርትዎን ያሳድጉ! #ad 📢 InsideAd.

አስተማሪ ታሪክ ታሪክ የሚነጋገር እና የዓለምን ምስጢሮች የሚያሳይ ቦታ ነው። እንደ አሳዛኝ ፍላጎት፣ አስደናቂ ዝርዝሮች፣ ታሪካዊ ግንዛቤ ትዕዛዝ ይፈልጋሉ? ተምሩ ታሪክን በቀላሉ፣ ግልጽ እና አስደና
አስተማሪ ታሪክ ታሪክ የሚነጋገር እና የዓለምን ምስጢሮች የሚያሳይ ቦታ ነው። እንደ አሳዛኝ ፍላጎት፣ አስደናቂ ዝርዝሮች፣ ታሪካዊ ግንዛቤ ትዕዛዝ ይፈልጋሉ? ተምሩ ታሪክን በቀላሉ፣ ግልጽ እና አስደናቂ መልኩ! 📜 አስተማሪነት, አሳዛኝ ትንታኔዎች, የማይረሳ ታሪክ ትናንትና። 🔍 ተጫወት 🌟 #ad 📢 🎯 የቴሌግራም ማስታወቂያ በ1 ደቂቃ

የ12ኛ ክፍል ፈተና ዝርዝር ጊዜ ይወዳድር ይችላሉ - የወቅቱን ትኬት አግኝ ኤክስፕሼ ዘጉር ይኖረዋል! ይህ ልክ ዛሬ ብቻ ነው! #ad 📢 🎯 የቴሌግራም ማስታወቂያ በ1 ደቂቃ

አዲሱን ፒዲኤፍ መፅሐፍ የገና እያየሃል? ከሚጠበቁ የስነ-ልቦና፣ ኳይኗው የትምህርት ወይም የምርጫ መጽሐፍት የሚገኙበት ሹክቱስ pdf መፅሐፍት ነው። በአነስተኛ ጊዜ ማንበብ ለሚፈልጉ እና አዲስ መጽሐ
አዲሱን ፒዲኤፍ መፅሐፍ የገና እያየሃል? ከሚጠበቁ የስነ-ልቦና፣ ኳይኗው የትምህርት ወይም የምርጫ መጽሐፍት የሚገኙበት ሹክቱስ pdf መፅሐፍት ነው። በአነስተኛ ጊዜ ማንበብ ለሚፈልጉ እና አዲስ መጽሐፍ ማግኘት ለምትወዱ መድረሻዎ ነው። ዛሬ ይጎብኙ እንዳታንቀሳቀስ! #ad 📢 🎯 የቴሌግራም ማስታወቂያ በ1 ደቂቃ

ምስጢራችንን አውጥተን ከተናገርን በኋላ የምንጸጸተው ለምንድን ነው? ​«ለነገሩ ይህን ሁሉ ምን አናገረኝ?» ንግግሩ ባበቃ ማታ፣ ከአእምሮአችን ጋር የምናደርገው ትግል ይጀምራል። «በጣም የግል ነገሬን አወራሁ እንዴ? ስለ እኔ አሁን ምን ያስብ ይሆን? ራሴን አጋለጥኩ ማለት ነው?» ​የስነ-ልቦና ባለሙያዎች «ኦቨርሼሪንግ»  ወይም ከልክ በላይ መናገር የሚሉት ክስተት፣ አንድ ሰው ለአንድ አጋጣሚ ወይም የቅርብነት ደረጃ ካልተመጠነ ሁኔታ በላይ የግል ምስጢሩንና ስሜቱን አውጥቶ ሲናገር ነው። ይህ ከአዲስ የስራ ባልደረባ ጋር በሚደረግ ጨዋታ፣ በመጀመሪያው የፍቅር ቀጠሮ፣ ከቀላል አውቃቂዎች ጋር በሚደረግ ሰላምታ ወይም በሶሻል ሚዲያ ልጥፎች ላይ ሊከሰት ይችላል። ​ስለ ስሜታችን እና ስለ ህይወት ልምዳችን ማውራት በራሱ መጥፎ ነገር አይደለም። እንዲያውም ራሳችንንና ምስጢራችንን ማጋራት እምነትን ለመገንባት እና ግንኙነቶችን ለማጠናከር ይረዳል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት የግል መረጃዎችን መጋራት ሰዎች ወደ መቀራረብ እንዲመጡ ያደርጋል። ነገር ግን ዋናው ቁልፍ ነገር የምናጋራው የውይይት ጥልቀትና ግልጽነት ከግንኙነቱ ደረጃ ጋር የሚመጥን መሆኑ ነው። ​ያልተመጠነ ግልጽነት ምንጭ፦ ለምን የልክ በላይ እንናገራለን? ​ከልክ በላይ መናገር ብዙውን ጊዜ ከመሰረታዊ የሰው ልጅ ፍላጎት ይመነጫል፦ ከሰዎች ጋር የመቀራረብና የመገናኘት ፍላጎት። ብቸኝነት የሚሰማቸው፣ በትክክል እንዳልተረዱ ወይም ትኩረት እንዳላገኙ የሚያስቡ ሰዎች ውስጣቸውን ለሌላ ሰው አውጥተው የመናገር ከፍተኛ ፍላጎት ሊኖራቸው ይችላል። በተጨማሪም አእምሮን የሚረብሹ አሳሳቢ ሀሳቦች ሲበዙብን፣ የውስጥ ጫናን ለመቀነስ ሲባል ብቻ በቀላሉ ማውራት እንጀምራለን። ​ታሪካችንን ማውራታችን ለአጭር ጊዜ እፎይታን ሊሰጠን ይችላል። የሆነን ነገር አውጥተን እንናገራለን፣ ትኩረት እናገኛለን፣ እንዲሁም የመረዳት ምላሽን እንጠብቃለን። በመሆኑም የልክ በላይ መናገር አእምሮ ራሱን ከተጫነው ስሜታዊ ጫና ነፃ ለማውጣት የሚጠቀምበት መንገድ (Emotional self-regulation) ሊሆን ይችላል። ​ነገር ግን ዋናው ችግር፦ እምነትን በኃይል ወይም በአንድ ጀመር ማስገደድ አይቻልም። ​የልክ በላይ መናገር አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው ገና በደንብ የማናውቃቸው ሰዎች ዘንድ ነው። ለምሳሌ አዲስ የስራ ባልደረባ፣ በግብዣ ላይ ያገኘነው አዲስ ሰው፣ ወይም ገና ማወቅ የጀመርነው ሰው ሊሆን ይችላል። ከእነዚህ ሰዎች ጋር በፍጥነት ልዩ ቁጥጥርና ጥልቅ ግንኙነት ለመፍጠር ስንል፣ ሳናውቀው ማለፍ ያለብንን በርካታ የደረጃ ደረጃዎች ዘልለን እንልፋቸዋለን። ​ስለዚህ የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ታሪካችንን ከመናገራችን በፊት ጥቂት ሰከን ብለን ራሳችንን እንድንጠይቅ ይመክራሉ፦ «በእርግጥ ይህንን ሰው አምነዋለሁ ወይንስ በግልጽነቴ እምነትን ለመገንባት እየሞከርኩ ነው?» ​ምክንያቱም እምነት በጊዜ ሂደትና በደረጃ የሚያድግ ነገር ነው። ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሰዎች የግል መረጃቸውን ለሌሎች የሚያካፍሉበት ፍጥነት ይለያያል። አንድ ሰው ብዙ ነገሩን ዘረዝሮ ሲናገር ሌላኛው ወገን ግን መጠነኛና የተገደበ ሆኖ ከተገኘ፣ ይህ አለመመጣጠን በኋላ ላይ ከፍተኛ የሀፍረትና የጸጸት ስሜትን ይፈጥራል። ​ከተናገርን በኋላ የምንጸጸተውና የምንፈራው ለምንድን ነው? ​የመሸማቀቅና የሀፍረት ስሜቱ የሚመጣው አብዛኛውን ጊዜ ውይይቱ ካበቃ በኋላ ነው። ምናልባት አዳማጩ የጠበቅነውን ያህል አልተገበረም፤ ተጨማሪ ጥያቄ አላቀረበም፣ ግራ በመጋባት ተመለከተን ወይም የውይይቱን ርዕስ በፍጥነት ቀየረው። በዚያን ጊዜ «በጣም አብዛኛሁት ማለት ነው» የሚል ስሜት ወዲያውኑ ይፈጠራል። በመቀጠል «ኦቨርቲንኪንግ»  ወይም ከመጠን በላይ ማሰብ ይጀምራል፦ ንግግሩን በአእምሯችን እንደገና እንጫወተዋለን፣ እያንዳንዱን ዓረፍተ ነገር እንመርምራለን፣ እና ምን ዓይነት ምስል ጥለን እንዳለፍን ለማወቅ እንጨነቃለን። ​ስለ ራስ-ግልጽነት የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ ሰዎች ከመናገራቸው በፊት ሊያስከትል የሚችለውን ውጤት በበቂ ሁኔታ ካላሰቡበት በኋላ ላይ ውሳኔያቸውን ሊጸጸቱ ይችላሉ። ለምሳሌ በአንድ የጥናት ግኝት ላይ ከታቀፉት ሰዎች መካከል 21 በመቶ ያህሉ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያወጡትን ልጥፍ (Post) በኋላ ላይ እንደተጸጸቱበት ተናግረዋል። ​ነገር ግን የልክ በላይ መናገር ሁልጊዜ ውርደት አይደለም ​እንደዚያም ሆኖ፣ እያንዳንዱ የግል አስተያየት ወይም ስሜት ስህተት ነው ማለት አይደለም። አንዳንዴ ሌላው ሰው ሁኔታውን ምን ያህል እንደተመለከተው እኛ ራሳችን አጋንን አድርገን እናስባለን። ለእኛ ሙሉ በሙሉ ስሜታዊ መጋለጥ ወይም ስህተት መስሎ የታየን ነገር፣ ለሌላው ሰው አየር ላይ በኖ የጠፋ ተራ ነገር ሊሆን ይችላል። ​በተጨማሪም ግልጽ መሆን በእርግጥም ግንኙነቶችን ያጠናክራል። ለምሳሌ በመልእክት መላኪያ መተግበሪያዎች (Messengers) በሚጠቀሙ ሰዎች ላይ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው፣ በጓደኛሞች መካከል ያለው የራስ-ግልጽነት እና የማህበራዊ ደጋፊነት ቀጥተኛ ግንኙነት አለው። ​ስለሆነም ዋናው ውሳኔ ሰጪ ጥያቄ «በጣም ብዙ ተናገርኩ እንዴ?» የሚለው ሳይሆን «ላወራሁት ሰው፣ ለነበረን ጊዜ እና ለነበረን የግንኙነት ደረጃ ተስማሚ ነበር ወይ?» የሚለው ነው። ​የልክ በላይ መናገርን ለመግታት የሚረዱ 5 መፈተሻ ጥያቄዎች ​ወደፊት ራስዎን ለመግታትና ሚዛን ለመጠበቅ ከፈለጉ፣ ወዲያውኑ ጭምት ወይም ዝጉርፉ መሆን አይጠበቅብዎትም። ከመናገርዎ በፊት እነዚህን አጫጭር የውስጥ መፈተሻዎች ማድረግ በቂ ነው፦ ​ይህን ነገር አሁን ለምን መናገር እፈልጋለሁ? መቀራረብ ለመፍጠር፣ ምክር ለማግኘት ወይንስ የውስጥ ጫናን ለመቀነስ? ​ይህንን ሰው በእርግጥ ምን ያህል አውቀዋለሁ? እስካሁን በመካከላችን አስተማማኝ እምነት ገንብተናል? ​ነገ ጠዋት በዚህ ንግግሬ አሁንም ምቾት ይሰማኛል? ይህ ጥያቄ በተለይ በጣም ለግል አሳሳቢ ጉዳዮች ከፍተኛ እርዳታ ይሰጣል። ​ሌላኛው ሰው በተመሳሳይ መጠን ያወራልኛል? የውይይቱ የእርስ በአዳማጩ ምላሽ የንግግሩ ደረጃ ተስማሚ  መሆኑን የሚያሳይ ትልቅ ጠቋሚ ነው። ​ይህን ነገር የግድ አሁን መናገር አለብኝ? አንዳንድ ጊዜ ለጥቂት ሰከንዶች ያህል ታግሶ ማሰብ ትልቅ ልዩነት ያመጣል። ​ከተናገሩ በኋላ ቢጸጸቱ ምን ማድረግ አለብዎት? ​በመጀመሪያ፦ አይደንግጡ። አንድ ጊዜ የልክ በላይ መናገርዎ የግድ ግንኙነቱን ያበላሸዋል ማለት አይደለም። በእርግጥ ያልተመቸዎት ከሆነ፣ ሁኔታውን በግልጽ ማንሳት ይችላሉ፦ «ቀለል አድርጌ ሳስበው፣ አሁን ትንሽ አብዝቼ ያወራሁ ይመስለኛል» በማለት በሳቅ ማለፍ ይቻላል። ይህ ዓይነቱ ግልጽነት ብቻውን የነበረውን ውጥረት ያቃልለዋል። ​ጉዳዩ የውስጥ ጫናን የመቀነስ ጉዳይ ከሆነ ደግሞ ሌላ መንገድ መጠቀም ይቻላል፦ ማስታወሻ (መጻፍ፣ በእግር መራመድ፣ ሀሳቦችን በወረቀት ላይ ማስፈር ወይም በጣም ለምናምነው የቅርብ ሰው ብቻ ማካፈል። ምንጭ:  ብሊክ ጋዜጣ

የለመኑ ዙፋን መዋቅር ከገንዘብ ገበያ መምርም ወይ የርቅ ማዕከላችን ስለ ቢተኮች ትዕዛዝ መረዳት ይቻላል። ወደ ዚህ በገፅ ዙፋን የሚያስታወክ ወይም አግኙ መዋቅር አይልኩም። ዛሬ ይወቁ! 👉 ይገናኙ
የለመኑ ዙፋን መዋቅር ከገንዘብ ገበያ መምርም ወይ የርቅ ማዕከላችን ስለ ቢተኮች ትዕዛዝ መረዳት ይቻላል። ወደ ዚህ በገፅ ዙፋን የሚያስታወክ ወይም አግኙ መዋቅር አይልኩም። ዛሬ ይወቁ! 👉 ይገናኙ #ad 📢 🎯 የቴሌግራም ማስታወቂያ በ1 ደቂቃ