cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሁሌ መረጃ.com/hule merja

የሰው ልጅ መረጃ የማግኘት መብቱ መገደብ የለበትም...እኛም ይህንን ፍላጎት ለመሙላት እዚ አለን፡፡ሁሌ መረጃ ሁሌ እውነት

Show more
Advertising posts
656Subscribers
+124 hours
+67 days
+1430 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViewsSharesViews dynamics
01
Media files
60Loading...
02
Media files
640Loading...
03
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 22 ሰዎች በወባ በሽታ ህይወታቸውን አተዋል ተባለ። ወቅቱ የወባ ስርጭት ከፍተኛ የሚሆንበት በመሆኑ በክልሉ 22 ሰዎች በወባ በሽታ ህይወታቸውን ማጣታቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ናፍቆት ብርሀኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በአሁኑ ወቅት በሳምንት እስከ 7 ሺ የሚሆኑ ሰዎች በወባ በሽታ እየተያዙ እንደሚገኙ ተናግረዋል ፡፡ ችግሩን ለመቅረፍም የአካባቢው ማህበረሰብ እንዴት እራሱን ከወባ በሽታ መከላከል እንደሚችል የተለያዩ ትምህርቶችን እየሰጡ እንደሚገኙ አንስተዋል፡፡ በአከባቢው ላይ ውሀ ያቆሩ ቦታዎችን የማፋሰስ ስራ እና ማህበረሰቡ አጎበር እንዲጠቀም የማድረግ ስራዎችን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ ሰዎች የትኩሳት ስሜት ሲሰማቸው በተለይም ህፃናት እና ነፍሰጡሮች እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲያስተውሉ  ወደ ጤና ተቋም ሄደው ተገቢውን የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ እያደረን እንገኛለን ሲሉ ምክትል ሀላፊው ተናግረዋል፡፡
650Loading...
04
Media files
1090Loading...
05
ኢትዮጵያና ኮንጎ ብራዛቪል የአየር ትራንስፖርት ስምምነት ተፈራረሙ ኢትዮጵያና ኮንጎ ብራዛቪል ዛሬ ሚያዚያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም የሁለትዮሽ የአየር ትራንስፖርት ስምምነት እዚህ አዲስ አበባ የተፈራረሙ ሲሆን ቀደም ሲል ሁለቱ ሀገራት እ.ኤ.አ. ሜይ 5/ 2017 በአጭር ፊርማ የተፈረመውን ስምምነት የአፍሪካ አየር መንገዶች በአፍሪካ አየር ክልል ላይ ያለምንም ገደብ የበረራ አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችላቸው እና በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ ህብረት አነሳሽነት እየተተገበረ ባለው በያሙሱኩረ ውሳኔ (Yamoussoukro Decision) መሰረት በማሻሻል በአጭር ፊርማ በሙሉ ለማጠናቀቅ ያስቻለ ነው፡፡ ዛሬ የተከናወነው ስምምነት የአንዱ ተዋዋይ ሀገር ተወካይ አየር መንገድ የሌላውን ተዋዋይ አገር አየር ክልል አቋርጦ የመብረር መብት (Over Flights)፣ በበረራ ላይ ያለ የአንዱ ወገን ተወካይ አየር መንገድ አውሮፕላን በበረራ ላይ ችግር ሲገጥመው ወይም ነዳጅ ለመሙላት በሌላኛው ወገን አየር ማረፊያ የማረፍ መብት (Technical Landing)፣ መንገደኛ ወይም ጭነት ካንድ ተዋዋይ ወገን በማንሳት ወደ ሌላኛው ተዋዋይ ወገን አየር ማረፊያ ወስዶ የማራገፍ መብት (3rd freedom traffic rights) የሚያስችል ነው። በተጨማሪም መንገደኛ ወይም ጭነት ከሌላኛው ተዋዋይ ወገን አየር ማረፊያ በማንሳት ወደ ሀገር የመመለስ መብት(4th freedom traffic rights)፣ እና በአፍሪካ አገራት ውስጥ በ5ኛ የትራፊክ መብት በመጠቀም መንገደኛ እና ጭነት ከሌላኛው ተዋዋይ ወገን አየር ማረፊያ አንስቶ ወደ ሌላ 3ኛ አገር አየር ማረፊያ የማራገፍ/አንስቶ የመመለስ መብት መብት (5th freedom traffic rights) የሚያሰጥ ነው። በመሆኑ የስምምነቱ በሙሉ ፊርማ መጠናቀቅ ሀገራችን ከኮንጎ ሪፐብሊክ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክር፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቱሪዝም፣ ንግድና ኢንቨስትመንት የሚያበረታታ፣ የበረራ ተደራሽነት የሚያሳድግና ለአየር መንገዳችን ተጨማሪ የገበያ ዕድል የሚፈጥር፣ እና የውጭ ምንዛሬን በማዳንም ሆነ በማስገኘት ረገድ አዎንታዊ አስተዋፅኦ የሚያበረክት በመሆኑ ለሀገራችን የሚያገኘው ጥቅም ከፍተኛ ነው፡፡ ስምምነቱን በኢትዮጵያ በኩል የፈረሙት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚንስትር ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ ሲሆኑ የኮንጎ ብራዛቪል የትራንስፖርት: ሲቪል አቪዬሽንና የመርቻንት ኔቪ ሚኒስትር ሚስተር ኦነሬ ሳይ ደግሞ ሀገራቸውን በመወከል ፈርመዋል። በአሁኑ ሰዓት አየር መንገዳችን ወደ ኮንጎ ብራዛቪል በሳምንት ሰባት (07) በረራ የሚያደርግ ሲሆን የስምምነቱ በሙሉ ፊርማ መጠናቀቅ የበረራ ምልልሱ ላይ ለውጥ የሚያመጣ ባይሆንም ተፈጻሚነቱን ግን ከፍ ያደርጋል፡፡ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ስምምነቶች የቱሪዝም፣ ንግድና ኢንቨስትመንት የሚያስድ ከመሆኑም በላይ ከአገራት ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክር፣ ለአየር መንገዶች ተጨማሪ የገበያ ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ ለአገር የሚያበረክቱት አስተዋፅዎም ላቅ ያለ ነው። በዚሁ አግባብ ባጠቃላይ አገራችን ኢትዮጵያ ከ111 አገሮች ጋር የአየር አገልግሎት ስምምነቶችን በአጭርና በሙሉ ፊርማ ደረጃ ተፈራርማለች፡፡ በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ79 አገራት በረራ እያደረገ ያለ ሲሆን 135 መዳረሻዎችም አሉት፡፡
1340Loading...
06
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ቦይንግ በወንጀል እንዲከሰስ ጠየቁ! በኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ከአምስት ዓመት በፊት ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ለአደጋው መንስዔ የሆነው የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ላይ የወንጀል ክስ እንዲመሠረት የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤትን ጠየቁ።የመንገደኞቹ ቤተሰቦች በዋሽንግተን ከአሜሪካ የፍትህ ባለሥልጣናት ጋር ሚያዝያ 16/ 2016 ዓ.ም በተነጋገሩበት ወቅት የአሜሪካው ኩባንያ ቦይንግ ለፍርድ እንዲቀርብ ጠይቀዋል። የተጎጂዎች ቤተሰቦች እና ተወካይ ጠበቆቻቸው ኩባንያው የሚያመርታቸውን አውሮፕላን ምርቶች ደኅንነት እና ጥራት ለማስጠበቅ ከሦስት ዓመት በፊት ከአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ጋር የገባውን የቁጥጥር መርሃ ግብር ጥሷል ብለዋል። የ157 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈው ከኢትዮጵያው አደጋ በተጨማሪ ለ189 ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት በሆነው የኢንዶኔዥያ አየር መንገድ አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ቦይንግ በወንጀል እንዲጠየቅ ለፍትህ መሥሪያ ቤቱ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል። በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው አሰቃቂ በተባለው በቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን አደጋዎች የ346 ሰዎች ሕይወት አልፏል።በሁለቱ አውሮፕላን አደጋዎች ሕይወታቸውን ያጡ ቤተሰቦች በቅርቡ ንብረትነቱ የአሜሪካ አላስካ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በበረራ ላይ ሳለ መስኮቱ መገንጠሉ ጋር ተያይዞ አሁንም የደኅንነት እና የጥራት ችግር እንዳለበት የሚያሳይ ነው ብለዋል። የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤት በአውሮፕላንን አምራቹ ላይ ካደረገው የረዥም ጊዜ ምርመራ በኋላ ቦይንግ ለ737 ማክስ አውሮፕላኑ ፍቃድ ለማግኘት ሲል ሆን ብሎ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ተቆጣጣሪዎችን እንዳሳሰተ ደርሸበታለሁ በሚል “አሜሪካን ለማጭበርበር በማሴር” በሚል ከሦስት ዓመት በፊት ክስ መስርቶበት ነበር። ቦይንግ ቺካጎ በነበረው የፍርድ ሂደት በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ካሳ ለመክፈል ተስማምቶ በምላሹም የአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት ለአውሮፕላን አምራቹ ከ737 ማክስ ዲዛይን ጉድለት ጋር በተያያዘ በማጭበርበር ሴራ በወንጀል እንዳይከሰስ ከለላ ሰጥቶት ነበር። የአውሮፕላን አምራቹ በአደጋው ለሞቱት ሰዎች ኃላፊነቱን እንደሚወስድ እና ተጠያቂነቱን ተቀብሎ ለአሜሪካ መንግሥት፣ አደጋ ለደረሰባቸው አየር መንገዶች እና ለተጎጂዎች የሚሆን 2.5 ቢሊዮን ዶላር የቅጣት ካሳ ለመክፈል ተስማምቷል።
1520Loading...
07
የሜክሲኮ የምግብ አቅራቢ የአይጥ መረቅን ከ50 ዓመታት በላይ ለደንበኞቹ ሲያቀርብ መቆየቱን አስታወቀ በሜክሲኮ ሜርካዶ ሪፐብሊካ ደ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ በሚሰኘው ገበያ ውስጥ በርካታ ነገሮችን ፈልጎ ማግኘት ይቻላል፣ ነገር ግን ከሁሉም በላይ ልዩ የሆነው የአይጥ ስጋን በመሸጥ የሚታወቅ የቆየ የምግብ አቅራቢ ድርጅት ታዋቂ ነው። ለበርካታ የዓለም ህዝብ የአይጥ ስጋ በፍፁም የማይለመድ እና ነውር ቢሆንም በሜክሲኮ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ ክልል ውስጥ ግን ለየት ያለ ጣዕሙ እና ለመድኃኒትነት ይውላል በሚል ለረጅም ዓመታት ጥቅም ላይ ውሏል። ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአይጥ ሥጋ የሚሸጡባቸው ሱቆች እና አከፋፋዮች ከአካባቢው ገበያ እየጠፉ ይገኛል። በሜርካዶ ሪፑብሊካ ደ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ ውስጥ ግን አንዱ አከፋፋይ አሁንም ሁለቱንም ማለትን ጥሬ የአይጦች ስጋ እና የአይጥ መረቅ ከተለያዩ አትክልቶች እና ቅመማ ቅመም ጋር አዋህዶ መሸጡን ቀጥሏል። እያንዳንዱ የአይጥ መረቅ አንድ ሙሉ ሳህን የሚይዘው  በ100 የሜክሲከ ፔሶ ወይም በ5.80 የአሜሪካን ዶላር ዋጋ ተቆርጦለታል።በሜርካዶ ሪፑብሊካ የመጨረሻው የአይጥ ስጋ ሻጭ ሆሴ ሬሜዲዮስ ሄርናንዴዝ "ካሚሎ" በመባልም የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየችው ወላጅ እናቱ ይህንኑ ንግድ ወርሷል። በአንድ ወቅት በገበያው ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ የአይጥ ስጋ ሻጮች እንደነበሩ ያስታውሳል፣ ነገር ግን ሁሉም ጡረታ ወጥተዋል አልያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አሁን ላይ በገበያው ውስጥ ብቸማ አቅራቢ ሆኖ ቀጥሏል። ስራው እየተቀዛቀዘ በርካቶች ከዘርፉ ቢወጡን በቅርብ ጊዜ ውስጥ የቤተሰብን ንግድ ለመተው እቅድ የለኝም ሲል ይናገራል። ይህው የቤተሰቡ ንግድ ለ52 ዓመታት ዘልቋል። በተቻለም መጠን ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ ለማድረግ የአቅሜን ያህል መስራቴን እቀጥላለሁ ሲል ይደመጣል። ካሚሎ የሚያቀርበውን የአይጥ ሾርባ ለማዘጋጀት  በሳን ሉዊስ ፖቶሲ ዙሪያ ካሉ የከተማ አካባቢ እና በዙሪያው ክሚገኙ ገጠራማ ስፍራዎች ተይዘው ይመጣሉ። የአይጥ ሥጋ በተለይ የደም ማነስ፣ የስኳር በሽታ ወይም ካንሰር ላለባቸው ሰዎች ጠቃሚ ሲሆን የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን ለማጠናከር እና የምግብ ፍላጎትን ለመጨመር ይረዳል ተብሎ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ይታመናል። በሜርካዶ ሪፑብሊካ ደ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ ውስጥ በሚገኘው ካሚሎ ሁለቱንም የአይጥ መረቅ በ100 ፔሶ የሚሸጥ ሲሆን ጥሬ አይጥ ገዝተው ቤት ይዘው ለሚሄዱ በ90 ዋጋ ይቀርባል።የስጋውን ጣዕም በትክክል ለማሟላት በአትክልቶችና ቅመማ ቅመሞች ለማብሰል ይመክራል ሲሉ የሬስቶራንቱ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
1390Loading...
08
Media files
1530Loading...
09
Media files
1510Loading...
10
እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ ቤት እና ስቱዲዮ ጥገና ሊደረግለት ነው። እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ ቤት እና ስቱዲዮ የጥገና ስራ ለማከናወን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ከ ቢዋይ ኤምቲ ኮንትራክተር እና ዳሎል አማካሪ ድርጅት መካከል የተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች በተገኙበት በ15/08/2016 ዓ.ም የስራ ርክክብ ተደርጓል። በፕሮግራሙ ላይ መልእክታቸውን ያስተላለፉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው  ቅርሱ የነበረውን አሻራና ይዘት በጠበቀ መልኩ  የቅርስ ጥገና መርሆዎችን በተከተለ መንገድ በጥንቃቄ መከናወን እንዳለበት ገልፀው፡፡የጥገና ስራው በተያዘለት የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ጥራቱን ጠብቆ መጠገንና ለሃገር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ መሆን እንደሚኖርበት አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም ስራ ተቋራጩ ይህን ታሪካዊ ቅርስ ጥገና ማድረግ በመቻላቸው እድለኛ እንደሆኑ ገልጸው ስራውን በተፈለገው ጊዜና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ አከናውነው እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል፡፡
1620Loading...
11
ከኢትዮጵያ ከ 350 በላይ ስደተኞች ወደ አሜሪካ ማቅናታቸውን አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይኦኤም አስታወቀ በተያዘዉ 2016 ዓመት ሰኔ ወር 4ሺ6 መቶ 8 ስደተኞች ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አይ ኦ ኤም አስታውቋል። አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ለብስራት ሬድዮ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ድርጅቱ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመነጋገር እና በመተባበር በኢትዮጵያ የሚገኙ የሶስተኛ ሀገር ስደተኛ ዜጎች ወደ አደጉ ሀገራት የማሸገር ስራ ይሰራሉ፡፡ አይኦኤም በመልሶ ማቋቋሚያ ስር  ውስጥ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደ አሜሪካ እንዲደርሱ ለማድረግ ተከታታይ የቻርተር በረራ እንቅስቃሴዎችን እና እንዲሁም በንግድ አየር መንገዶች ላይ የቡድን ምዝገባዎችን ያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ድጋፍ ያለው የዩናይትድ ስቴትስን የ2024 የስደተኞች መጤ ግብ ለማሳካት የስደተኞችን መልሶ የማቋቋም ስራ እያሰፋ ይገኛል።ዩናይትድ ስቴትስ በ2024 ከ4ሺ500 በላይ ስደተኞችን ከኢትዮጵያ ለመቀበል ቃል መግባቱን አይኦኤም አስታውቋል፡፡ ባለፉት አስርት አመታት ውስጥ ብቻ አይኦኤም ከ1.19 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን እና ሌሎች ስጋት ያለባቸውን በአለም ዙሪያ ካሉ 166 አካባቢዎች የመቋቋሚያ እንቅስቃሴዎችን አዘጋጅቶ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል።በ2023 አይኦኤም 5ሺ3 መቶ4 ስደተኞችን ኢትዮጵያ አስፍሯል። ከእነዚህ ውስጥ 1ሺ1መቶ 94ቱ ወደ አሜሪካ አቅንተዋል።
1850Loading...
12
በኢትዮጵያ በገዳይነቱ የተመዘገበው የ 'ካላዛር' በሽታን ለማከም የሚውል መድኃኒት በሰዎች ላይ መሞከር ተጀመረ የካላዛር ሕሙማንን ለማከም ለ17 ቀናት የሚሰጠውን የመርፌና የእንክብል መድኃኒት ሙሉ ለሙሉ በእንክብል ብቻ ለመተካት የሚያስችለው መድኃኒት፣ የዕድሜ ክልላቸው ከ18 እስከ 44 በሚደርሱ 52 ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያን ላይ ሙከራው ተጀመረ። በምርምሩ 15 የጤና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ሲሆን፣ ፈውስ ትኩረት ለተነፈጉ በሽታዎች ኢኒሺዬቲቭ ወይንም ዲ ኤን ዲ የጤና ምርምር የተባለ ተቋም እና አጋሮቹ ለዚህ በሽታ የሚያደርጉት የመድሃኒት ፍለጋ ምእራፍ ሁለት የክሊኒካል ሙከራ ደረጃ መሸጋገሩ ተጠቁሟል። በአፍሪካ አሁን እየተሰጠ የሚገኘው የካላዛር ህክምና ለ17 ቀናት የሚወሰድ ከፍተኛ ህመም የሚፈጥር ክትባት ሲሆን በኢትዮጵያ በምርምር ላይ የሚገኘው አዲሱ የ “LXE408” በአፍ  የሚወሰድ መድሀኒት አሁን ከሚሰጠው ህክምና የበለጠ ፈዋሽና እንደሚሆን ይጠበቃል ተብሏል። በኢትዮጵያ በዓመት ከ2 እስከ 3 ሺ ሰዎች በካላዛር በሽታ ይያዛሉ ሲባል በበሽታው ተይዘው ሕክምና ካላገኙት ውስጥ 95 በመቶ ያህሉ እንደሚሞቱ ተጠቁሟል። Sheger
1540Loading...
13
Media files
1380Loading...
14
ከሰሞኑ በቤተክርስቲያን ዉስጥ ሲተኩስ የታየዉን የፌዴራል ፖሊስ አባል ተከትሎ ኮሚሽኑ ከመተዳደሪያ ህግና አሠራር ውጭ ነዉ ሲል ኮነነ 👉🏼 የፖሊስ አባሉም ይህንን ተግባር እንደፈፀመ ወዲያውኑ በቁጥጥር ሥር ዉሏል ተብሏል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በማህበራዊ የትስስር ገጹ ላይ ካሰራጨዉ መግለጫ እንደተመለከተነው ፖሊስ ከየትኛውም ሃይማኖት፣ ብሄር እና ፖለቲካ  ወገንተኝነት የፀዳ እና ብዛህነትን እሴቱ ያደረገ ሕዝባዊ ተቋም መሆኑን ገልጿል። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሃይማኖቶች ብዛህነትን የሚያከብርና የሚያስከብር በእኩልነት ለሁሉም ሙያዊ አገልግሎት የእየሰጠ ያለ ተቋም ሆኖ ሳለ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አዲስ የፖሊስ አባላትን ለመመልመል ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ የተላከ የፖሊስ አባል ምክትል ሳጂን ታመነ ዱባለ ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ኬቾ ወዜ ቅዱስ ባለወልድ ቤተክርስቲያን  በመገኘት የደንብ ልብሱን እንደለበሰ ሃይማኖታዊ መዝሙር በመዘመር እና በሕዝብ ፊት ጥይት እየተኮሰ በማህበራዊ ሚዲያ ሰሞኑን የሚሰራጨው ቪዲዮ ከተቋሙ መተዳደሪያ ህግና አሠራር ውጭ እንደሆነ መግለጫው ወቅሷል። አባሉም ይህንን ተግባር እንደፈፀመ ወዲያውኑ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ   በቁጥጥር ሥር አውሎት የፈፀመው ድርጊት በተቋሙ ሕገ ደንብ መሠረት በሕግ አግባብ እያጣራ እንደሚገኝ መግለጫው አመላክቷል።
1570Loading...
15
በጅቡቲ የባሕር ጠረፍ ላይ በጀልባ መገልበጥ የሞቱ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ብዛት 21 መድረሱን ተነግሯል። ትላንት በስቲያ ምሽት ከየመን የባህር ዳርቻ ልዩ ስሙ አራ ከሚባል ስፍራ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ ጅቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ጎዶሪያ በሚባል አካባቢ በደረሰባት የመገልበጥ አደጋ  ሕይወታቸው  ያለፈ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 21 መድረሱን  ዓለማቀፉን የፍልሰት ድርጅት (አይ ኦ ኤም) ገልጿል። ከጀልባዋ 77 ተሳፋሪዎች መካከል፣ 23ቱ ፍልሰተኞች እስከ ትናንት ምሽት ድረስ የደረሱበት እንዳልታወቀ ዘገባው ጠቅሷል። ከአደጋው የተረፉት 33 ፍልሰተኞችና በአደጋው የሞቱት ፍልሰተኞች ኹሉም ኢትዮጵያዊያን እንደኾኑ በጅቡቲ የድርጅቱ ሃላፊዎች አረጋግጠዋል ተብሏል። ትላንት በስቲያ ምሽት ከየመን የባህር ዳርቻ ልዩ ስሙ አራ ከሚባል ስፍራ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ ጅቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ጎዶሪያ በሚባል አካባቢ በደረሰባት የመገልበጥ አደጋ ነበር የኢትዮጵያውያኑ ሕይወት ያለፈው፡፡ ከ2 ሳምንት በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በደረሰ አደጋ የ38 ፍልሰተኛ ዜጎቻችን ሕይወት ማለፉ የሚታወስ ነው።
1490Loading...
16
በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ሊባኖስ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ። አደጋው ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም እየተጓዘ የነበረ የቤት አውቶሞቢል ከኮሶበር ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ከነበር የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ጋር ቀሲም በተባለ ልዩ ቦታ በመጋጨቱ የደረሰ ነው። በአደጋው የአራት ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፈ በ14 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት፤ በስምንት ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። የደብረ ሊባኖስ ወረዳ ትራፊክ ደህንነት አስተባባሪ ረዳት ኢንስፔክተር ኃይለማርያም ደባሌ÷ የአደጋው መንስኤ በፍጥነት ማሽከርከር እና ቅድሚያ አለመሰጠት መሆኑን መናገራቸዉን ከወረደዉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
1570Loading...
17
ከየመን ወደ ጂቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ በደረሰባት የመገልበጥ አደጋ 16 ኢትዮጵያውያን ሕይወታቸው አለፈ *** ትላንት ምሽት ከየመን የባህር ዳርቻ ልዩ ስሙ አራ ከሚባል ስፍራ 77 ኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ ጅቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ጎዶሪያ በሚባል አካባቢ በደረሰባት የመገልበጥ አደጋ የ16 ኢትዮጵያውያን ሕይወት አልፏል፡፡ በጀልባ መገልበጥ አደጋው የ16 ኢትዮጵያውያን ሕይወት ሲጠፋ አብረው የተሳፈሩ 28 ዜጎችን እስካሁን ማግኘት አለመቻሉ ተጠቅሷል፡፡ በደረሰው አደጋ ህይወታቸውን ካጡ ሰዎች መካከል 5ቱ ሕፃናት መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን፤ 1 ሴትን ጨምሮ 33 ፍልሰተኞች በሕይወት ተርፈው ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመልክቷል።  ኤምባሲው በደረሰው አሳዛኝ ክስተት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልፆ፤ ከጅቡቲ ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገራት የሚደረገው ህገ ወጥ ጉዞ እጅግ አደገኛ ከመሆኑም በላይ በየጊዜው የዜጎቻችንን ሕይወት እያሳጠ እንደሚገኝ አስገንዝቧል።  ዜጎች በህገ ወጥ ደላሎች የሀሰት ስብከት በመታለል ውድ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው በዚህ አደገኛ የጉዞ መስመር ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ ያሳሰበው ኤምባሲው፤ የፍትህ አካላትም ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን ከገጠራማ የአገሪቱ አካባቢዎች ዜጎችን በመመልመል ለስደት በሚዳርጓቸው ግለሰቦች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪውን አስተላልፏል። ከ2 ሳምንት በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በደረሰ አደጋ የ38 ፍልሰተኛ ዜጎቻችን ሕይወት ማለፉ የሚታወስ ነው።
1620Loading...
18
Media files
1520Loading...
19
ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ መሆኑ ተሰማ ሕወሓት ከአራት ዓመት በፊት “ሕገ–ወጥ ነው” ያለውን ገዥውን ፓርቲ ብልፅግና ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድሮች እያደረገ መሆኑ ተሰምቷል። ከኹለት ዓመት ደም አፋሳሽ ጦርነት በኋላ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት የፈረመው ሕወሓት፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በሊቀመንበርነት የሚመሩትን ብልፅግናን በመቀላቀል በሀገራዊ ጉዳዮች አብሮ ለመስራት መስማማቱን ቢገልፅም፣ ፓርቲውን ለመቀላቀል ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡን ዋዜማ ከተለያዩ ምንጮች ያሰባሰብኩት መረጃ ያመለክታል ስትል ዘግባለች። ከብልፅግና በፊት የነበረው ኢሕአዴግ እኩል የሥራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ውክልና ያላቸው አራት ንዑስ ፓርቲዎች ጥምረት ሲሆን፤ ብልፅግና ግን አንድ ወጥ ፓርቲ ነው። የብልፅግና የፓርቲ ውክልና በህዝብ ብዛት የሚወሰን እንጂ እንደ ኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች እኩል ውክልና አይኖራቸውም። አሁን እየተደረገ ባለው ድርድር ሕወሓት የብልፅግና ፓርቲ ሕገ-ደንብ ተሻሽሎ በፓርቲ ውስጥ አባል ድርጅቶች እኩል የማዕከላዊ ኮሚቴና የሥራ አስፈፃሚ ውክልና እንዲኖራቸው ይፈልጋል። ብልፅግና ግን ሕወሓት የተናጠል ህልውናውን አክስሞ ብልፅግናን እንዲቀላቀልና ውክልናውም በትግራይ ህዝብ ቁጥር ልክ የሚወሰን መሆኑን ይገልፃል። የሕወሓት ሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል በአዲስ አበባ ተገኝተው ይህን ድርድር የጀመሩት ሲሆን፤ ከሁለት ሳምንት በኋላ የብልፅግና ምክትል ሊቀመንበር አደም ፋራህ ወደ መቀሌ ተጉዘው በጉዳዩ ላይ በስፋት መነጋገራቸው ተገልጿል። በሕወኋት በኩል ብልፅግናን መቀላቀል “ስህተት ነው …አስፈላጊም አይደለም” ብለው የሚያምኑ አመራሮች ቢኖሩም፤ "ውህደቱ ለትግራይ ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት ጠቀሜታ አለው፣ በተለይም የትግራይን ፀጥታና ደህንነት ለመስጠበቅ ከብልፅግና ጋር አብሮ መቆም አስፈላጊ ነው ብለው የሚያምኑ መኖራቸውንም ዘገባው አመላክቷል።
1540Loading...
20
#ሊዝ #አዲስአበባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ መሬትን በሊዝ ለማስተላለፍ 2ኛ ዙር ጨረታ አውጥቷል። መሬትን በሊዝ የማስተላለፍ ተግባር ለአራት ዓመታት ከተቋረጠ በኋላ ግንቦት 5 ቀን 2015 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል፡፡ 2ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታም ረቡዕ ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም መውጣቱን አዲስ ልሳን ጋዜጣ መረጃውን አጋርቷል። በከተማዋ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ መረጃ መሠረት፣ በ2ኛው ዙር ጨረታ 243 መሬት (ቦታ) የተዘጋጀ ሲሆን፣ እነዚህ ቦታዎችም በአስር ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ናቸው፡፡ በአራዳ ክ/ከተማ (ፒያሳ) በዓድዋ ድል መታሰቢያ አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ ፦ - በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ - በኮልፌ ቀራንዮ፣ - በአራዳ፣ - በአቃቂ ቃሊቲ፣ - በየካ፣ - በቦሌ፣ - በአዲስ ከተማ፣ - በቂርቆስ፣ - በጉለሌ እና በልደታ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎች በ2ኛው ዙር ጨረታ በሊዝ ሊተላለፉ እንደቀረቡ ታውቋል። ከዚህ ቀደም አልሚዎች ተጫርተው አሸናፊ ከሆኑ በኋላ በሚተላለፉ የተለያዩ ቦታዎች ላይ “የይገባኛል” ጥያቄዎች ይነሱባቸው እንደነበር ነበር። አሁን ለመተላለፍ የተዘጋጁ ቦታዎች ግን ከሶስተኛ ወገን ጥያቄ ነፃ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ገልጿል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ሚያዝያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አካባቢ ኤም.ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው በከተማዋ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በ9 ተከታታይ የስራ ቀናት በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዳራሽ የሚከፈት ሆኖ፣ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለፃል ተብሏል፡፡ ተጫራቾች ቦታውን በአካል ቀርበው ለመመልከት ከፈለጉ በ16/8/16 ዓ.ም እና በ18/8/16 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡00 እና ከሰዓት በ8 ሰዓት ለጨረታ የተዘጋጁ ቦታዎች የሚገኙበት ከፍለ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽህፈት ቤት ድረስ በመቅረብ ለዚህ ስራ በሚመደቡ አስጎብኚዎች አማካኝነት መመልከት እንደሚችሉ ከአዲስ አበባ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮና / ከአዲስ ልሳን ጋዜጣ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
1540Loading...
21
በኩባ ኮንዶም እንደ ሁለገብ እቃዎች ይቆጠራሉ። • ለዓሣ ማጥመድ፣ ለፀጉር ማሰሪያ እና ለወይን ጠጅ ሥራ ያገለግላሉ።
1480Loading...
22
የመስተንግዶ ባለሙያዎች የአለባበስ ኮድ መመሪያ እንዲፀድቅ ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት መላኩ ተነገረ በሆቴሎች የሚሠሩ ሴት የመስተንግዶ ባለሙያዎች ከሀገሪቱ ባሕል ውጪ የሆነውን አለባበሳቸውን ለማስተካከል የሚያስችል የአለባበስ ኮድ መመሪያ ዝግጅቱ ተጠናቅቆ ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት መላኩ የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ። አሁን ላይ የመስተንግዶ ባለሙያዎች በተለይም ሴቶች በአንዳንድ ሆቴሎች አማካኝነት ሥነ-ሥርዓቱን ያልጠበቀ አለባበስ እንዲለብሱ ይገደዳሉ የተባለ ሲሆን መመሪያው ፀድቆ ሥራ ላይ ሲውል በሆቴሎች የሚሠሩ የመስተንግዶ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ ዓለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የአለባበስ ኮድ እንዲከተሉ ይደረጋል ተብሏል። መመሪያው በከተማዋ ካቢኔ በቅርቡ ፀድቆ ተግባራዊ እንደሚደረግ ሲገለፅ ሕጉ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣትም ጭምር ያለው በመሆኑ መመሪያውን በሚተላለፉ ላይ ቅጣት እንደሚጣል የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሣው (ዶ/ር) መግለፃቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
1690Loading...
23
የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተማሪዎች የአገልግሎት ክፍያ የሚከፍሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ በሰኔ ወር 2016 የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተፈታኝ ተማሪዎች የአገልግሎት ክፍያ የሚከፍሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። በዚህም መሠረት ተፈታኝ ተማሪዎች እያንዳንዳቸው የአገልግሎት ክፍያ 500.00 (አምስት መቶ) ብር ብቻ የሚከፍሉ መሆኑን፤ ሚኒስቴሩ ለሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ ገልጿል። በዚህም ተፈታኞች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000553176097 በመጠቀም እስከ ነገ ማክሰኞ ሚያዚያ 15/2016 ድረስ ለትምህርት ሚኒስቴር ገቢ እንዲያደርጉ አሳስቧል። ተፈታኞች የከፈሉበትን ደረሰኝ ኮፒ በኢሜይል አድራሻ [email protected] እና [email protected] መላክ እንደሚናርባቸውም ተገልጿል።
1550Loading...
24
የአማራ ክልል መንግሥት ለሕዝቡ ጥሪ አቀረበ የሕወሓት ታጣቂ ቡድን የሰላም አማራጮችን ወደ ጎን በመተው የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ የራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረም እና ዛታ አካባቢዎችን በወረራ ይዟል:: ይህንን ተከትሎ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ የአማራ ሕዝብ ዛሬም እንደትላንቱ ከሀሰት ፕሮፓጋንዳ እና ከሰርጎ ገቦች ራሱን እና አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አስተላልፏል:: ሕዝቡ ከክልሉ መንግሥት እና በየአካባቢው ከሚገኙ አስተዳደሮች ጋር የጠበቀ ቁርኝት በመፍጠር ጠላቶቹ የከፈቱበትን ጥቃት ለመመከት በሚደረገው ጥረት የድርሻውን እንዲወጣ ነው ጥሪ ያደረገው:: የክልሉ መንግሥት ከአማራ ሕዝብ በተጨማሪ ለፌደራል መንግሥት እና ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ጥሪ አቅርቧል፤ ለፌደራል መንግሥት ባስተላለፈው ጥሪ የሕወሓት ታጣቂ ቡድን በወረራ ከያዛቸው ቦታዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቆ እንዲወጣ እና ሕዝቡን ከጥፋት መታደግ እና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት መታደግ እንደሚገባ ጠቁሟል:: ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ደግሞ ሕወሓት በክልሉ ሕዝብ ላይ የፈጸመውን ወረራ በጥብቅ እንዲያወግዝ እና ከክልሉ ሕዝብ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል:: ሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም (አሚኮ በኩር)
1450Loading...
25
ዓለም ብርሃን ትምህርት ቤት የቀድሞ አስተማሪዎችን በማመስገን 50 ኛ ዓመቱን ሊያከብር ነው በአዲስ አበባ በተለምዶ ማዕከላዊ ወይም ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ  ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ዓንጋፋው የመጀመሪያ ደረጃ ትምርት ቤት የዓለም ብርሃን የተመሰረተበትን  50 ዓመት ለማክበር በቀድሞ ተማሪዎቹ ኮሚቴ አዋቅሮ ዝግጅት የጀመረ ሲሆን በዓሉ በመጪው ግንቦት መጨረሻ ባሉት ቀናት ይከበራል ተብሏል። በዓሉ አብሮ የተማሩ ነገር ግን  የተጠፋፉ የድሮ ተማሪዎች ከማገናኘት ባሻገር የፎቶ አውደ ርዕይ የሚኖረው ሲሆን  በቀጣይ ስለሚሰሩ የበጎ ምግባር ስራዎች ላይ ወይይት ይደረግበታል። ትምህርት ቤቱ 50ኛ ዓመቱን ሲያከብር ትምህርት ቤቱን ላይበረሪ በማደስ ፣ አሁን እየተማሩ ካሉ ተማሪዎች ውስጥ አቅም የሌላቸውን በደብተር፣ መማሪያ መፅሀፍ እና ዩኒፎርምና ሌሎች ለትምህርት የሚያስፈልጉ ቁሶችን በመርዳት እንደሆነ የቀድሞ ተማሪዎች ኮሚቴ ትናንት በነበረው ስብሰባ ገልፇል። በበአሉ ላይ የቀድሞ አስተማሪዎች የሚመሰገኑበት ፕሮግራም የሚከናወን ሲሆን በትምህርት ቤቱ የተማሩ የቀድሞ ተማሪዎች ጥሪ የሚደርግላቸው ሲሆን በአሉን ለመታደም ሲመጡ ተማሪዎች የሚያግዝ መፅሀፍ ወይም ሌላ የትምህርት መርጃ ይዘው እንዲመጡ ይደረጋል ተብሏል። ኮሜቴው ለዚህ ስራ እንዲያግዘው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር የከፈተ ሲሆን ይሄን ዓላማ የሚደግፉ የቀድሞ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች 1000623474837 በተጠቀሰው የንግድ ባንክ ቁጥር የአቅማቸውን ገንዘብ ገቢ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል። የቀድሞ ተማሪዎች ሀሳባቸውን የሚጋሩበት የቴሌግራም ቻናል እና  https://t.me/all12Tr የፌስ ቡክ ፔጅ https://www.facebook.com/profile.php?id=61558763457711 እንደተከፈተም ኮሚቴው ገልፇል።
1370Loading...
26
የአልማዝ ትክክለኛነትን ለማረጋገጥ አንዱ መንገድ በላዩ ላይ መተንፈስ ነው። • እርጥበት ያለው ውሃ በሐሰተኛው ላይ ይታያል። አልማዝ ከሆነ ግን አይታይም።
1390Loading...
27
ቀሲስ በላይ መኮንን ከሰሞኑ "ተሳትፈዉበታል" በተባለው የማጭበርበር ድርጊት የተነሳ የአፍሪካ ህብረት የዉጪ ምንዛሬ የሚያስቀምጥበትን የባንክ ሂሳብ ከኢትዮጵያ ዉጪ ለማድረግ እንዳሰበ ተሰማ 👉🏼 ህብረቱ ለሶስተኛ ጊዜ በሀሰተኛ ሰነድ ልጭበረበር ነበር ያለ ሲሆን "ታማኝ" በተባሉ ሰዎች የተፈጸመው ሙከራ ወደፊት "በባለስልጣናት ላለመሞከሩ ማረጋገጫ ስለሌለኝ ነዉም" ብሏል ከሰሞኑ ቀሲስ በላይ መኮንን በሀተኛ ሰነድ 6 ሚሊዮን 50 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ገንዘብ ለማዘዋወር ሞክረዋል መባላቸውን ዳጉ ጆርናል ተከታታይ መረጃዎችን አድርሷል። ይህንኑ ተከትሎ ቀሲስ በላይ የተጠረጠሩበት ድርጊት መነጋገሪያ ሆኖ የቆየ ሲሆን ዘ ሪፖርተር ደግሞ አዲስ መረጃ አጋርቷል። ቀሲስ በላይ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ዉስጥ በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በመገኘት ሀሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከህብረቱ የሂሳብ ቁጥር ለግንባታ እና ሌሎች ስራዎች ክፍያ በሚል 6 ሚሊዮን 50 ሺህ ዶላር ለማዘዋወር ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ዉለዋል። ስማቸዉ ያልተጠቀሰ የዘ ሪፖርተር ምንጭ ታድያ ይህንን ድርጊት ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት የዉጪ ምንዛሬ የሚያስቀምጥበትን የባንክ ሂሳብ ከኢትዮጵያ ዉጪ ለማድረግ እንዳሰበ ተናግረዋል። ህብረቱ ለሶስተኛ ጊዜ በተጭበረበረ ሰነድ ከባንክ ሂሳቡ ሊወጣ የነበረ ገንዘብን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ያስታወቀ ቢሆንም "እምነትና እዉቅና" ባላቸዉ ሰዎች የተፈጸመዉ ተግባር ወደፊት በባለስልጣናት ለላመሞከሩ መተማመኛ የለኝም በማለቱ መሆኑን ዘገባው አመላክቷል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ዉስጥ ያለዉ ቅርንጫፉ ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት የተከፈተ ሲሆን በዋነኛነት የአፍሪካ ሒሳቦችን በተለይ ለማስተዳደር ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮም የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከልን ጨምሮ የተቋሙ ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሪ ክምችት ያላቸዉ አካውንቶችን በማካተት ቁጥጥር ያደርጋል። ቀሲስ በላይ በወቅቱ ሀሰተኛ የህብረቱ ማህተም ያረፈባቸዉን ወረቀቶች በመያዝ ለግንባታ እና የማሽነሪዎች አቅርቦት በሚል ክፍያዉን መጠየቃቸውን ሪፖርተር ዘግቧል። ክፍያዉ ከመፈጸሙ በፊት ወደ ህብረቱ የስልክ ጥሪ ያደረጉት የባንኩ ሰራኞች የክፍያዉን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ሲሞክሩ የህብረቱ የፋይናንስ ክፍል የማያዉቀዉ መሆኑን እና ክፍያዉ እንዲታገድ ህብረቱ መጠየቁ መረጃዉ ይደርሳቸዋል። ህብረቱ ይህንን ተከትሎም ግለሰቡ እንዲያዙለት ጠይቆ ቀሲስ በላይ በህብረቱ ጠባቂዎች በቁጥጥር ስር ዉለዉ በፌዴራል ፖሊስ ተላልፈው መሰጠታቸዉ ይታወሳል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የፋይናንሺያል አስተዳደር ዲቪዥን ኃላፊ ማዳሊስቶ ሙኡሶ ሎሌም ወዲያውኑ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል እና የትራፊክ አደጋ ምርመራ ክፍል ደብዳቤ ጽፈዋል ብሏል ዘገባዉ። ኃላፊዉ የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ ከአፍሪካ ህብረት ሒሳብ ወደ አራት ግለሰቦች ሒሳብ እንዲዘዋወር የጠየቁ ሰነዶች ሁሉም ፎርጂድ ናቸው ብለዋል በጻፉት ደብዳቤ። ከዚህ ክስተት በኋላ የህብረቱ እና የባንኩ  ሰራተኞች ለፖሊስ ቃላቸዉን መስጠታቸው በዘገባዉ ተጠቅሷል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ እንደተናገሩት "በመሠረቱ ጥሬ ገንዘብ በውጭ ምንዛሪ ብቻ ሊሰጥ አይችልም ። ለማጭበርበር የሞከረዉም ግለሰብ መጥቶ መጠኑን በጥሬ ገንዘብ ሲጠይቅ ይህን እንኳን አያውቅም ነበር ማለታቸዉን ነዉ። አክለዉም " ግለሰቡ እዚህ አገር የዶላር አካውንት ከሌለው ገንዘቡ ቢተላለፍም እንኳ የትም ሊደርስ አይችልም።  አጭበርባሪዎች በየቀኑ ወደ ባንካችን ይመጣሉ።  ባንክ ስለምንሰራ የተለመደ ነው።  እኛ ግን ሁልጊዜ ከመሳካታቸው በፊት እናጣራለን።  ለፍርድም እየወሰድናቸው ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞቹን ሒሳቦች የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት።  ያንንን እያደረግን ነው።  የአፍሪካ ህብረትም እስካሁን ድረስ ቀጥተኛ ቅሬታ አላቀረበብንም" ሲሉ አቶ አቤ ተናግረዋል። "ማጭበርበር ሲያጋጥም ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው" ያሉት ስማቸው ያልተጠቀሱት የዜና ወኪሉ የአፍሪካ ህብረት ምንጭ" አሁን ማጭበርበሩ በተከበሩ ሰዎች እየተሞከረ ስለሆነ ተጨንቀናል" ብለዋል። ይህ ድርጊት  "ባለስልጣናት አንድ ቀን ተመሳሳይ ነገር ላለማድረጋቸዉ ምንም አይነት ዋስትና የለንም" ያሉም ሲሆን  "እምነት እያጣን ነው" ብለዋል። ባለስልጣኑ አክለዉም በዚህ የተነሳ "ኢትዮጵያ ውስጥ ለደሞዝ አነስተኛ መጠን ያለው ፎሬክስ(የዉጪ ምንዛሪ ) ለመያዝ ወስነናል ፤ የድርጅቱን ገንዘብ ከኢትዮጵያ ውጭ ማቆየት እንድናስብ ያስገድደናል" ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የአፍሪካ ህብረት ባለስልጣን መናገራቸውን ተናግረዋል። Via The Reporter
1580Loading...
28
29 ሺሕ ዜጎች ከራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መፈናቀላቸውን ተገለጸ ከሰሞኑ በትግራይ እና አማራ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ባገረሸው ግጭት ምክንያት፤ 29 ሺሕ ዜጎች ከራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (ኦቻ) አስታውቋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (ኦቻ) ትናንት ሚያዝያ 11/2016 ባወጣው ሪፖርት፤ በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉት ዜጎች በቆቦ፣ ሰሜን ወሎ እና ሰቆጣ ከተማ በሚገኙ መጠለያዎች ላይ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልጿል፡፡ ከተፈናቀሉት 29 ሺሕ ዜጎች ውስጥ 70 በመቶዎቹ ሕጻናት እና ሴቶች ሲሆኑ፤ ቀሪዎቹ አዛውንቶች እና ታዳጊዎች ናቸው ያለው ሪፖርቱ፤ ከአጠቃላይ ተፈናቃዮች ውስጥ 23 ሺሕ የሚሆኑት ቆቦ ቀሪዎቹ 5 ሺሕ 980 የሚሆኑት ደግሞ ሰቆጣ ከተማ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልጿል። በአካባቢው ያለው ሁኔታ አሁንም ያልተረጋጋ በመሆኑ ተጨማሪ ዜጎች ሊፈናቀሉ ይችላሉ ያለው ጽ/ቤቱ፤ አሁን ላይ ለተፈናቃሉ ዜጎች ውሃ፣ ምግብ እና ሌሎች ሕይወት ማቆያ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። ነገር ግን ለተፈናቃዮቹ የሚቀርበው የምግብ እና ውሃ እጥረት አሳሳቢ መሆኑን በመግለጽ፤ ተፈናቃዮቹ አፋጣኝ የነፍስ አድን እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አመላክቷል። በተጨማሪም ለጋሽ አገራትና አጋር ተቋማት የሚያደርጉት ድጋፍ ውስን በመሆኑ፤ አሁን ላይ በአካባቢው ያለው ማህበረሰብ ለተጎዱ ተፈናቃዮች የሚችለውን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል። ኦቻ ለተፈናቃዮቹ በተለይም መጠለያ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችና የሕክምና አገልግሎት በአፋጣኝ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ያሳሰበ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚሽን ሰራተኞች ጉዳዩን ለመከታተል ሚያዚያ 11 ቀን 2016 ወደ ስፍራው ማቅናታቸውንም ገልጿል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት የትግራይ እና አማራ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ በሚያነሱባቸው የራያ አካባቢ ዳግም ግጭት መቀስቀሱ የሚታወስ ሲሆን፤ በዚህም ግጭት የህወሃት ታጣቂዎች ወደ ራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መምጣታቸውን ተከትሎ፤ የአካባቢው ነዋሪዎች ቤታቸውን ጥለው ለመሰደድ መገደዳቸው ተገልጿል፡፡ የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎም፤ የአማራ ክልል መንግሥት "ህወሕት ለአራተኛ ጊዜ ወረራ ፈጽሞብኛል" ሲል ወቅሷል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ፤ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ "ክሥተቱ በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ወይም በህወሓት አልያም በትግራይ እና በአማራ ክልሎች መካከል የተፈጠረ ግጭት አይደለም" ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የፌደራሉ መንግሥት በበኩሉ የይገባኛል ጥያቄ በሚነሣባቸው በእነዚህ አካባቢዎች ባለው ወቅታዊ ሁኔታ፤ ሁሉም ወገኖች ለፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት እንዲገዙና ከተንኳሽ ተግባራት እንዲቆጠቡ የጠየቀ ሲሆን፤ ሁሉም ወገኖች ካለፈው ግጭት ትምህርት መውሰድ እንዳለባቸው አሳስቧል።
1750Loading...
29
በሶማሊላንድ ወደ የመን ለመሻገር ሲሞክሩ የነበሩ 170 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መያዛቸው ተነገረ በራስ ገዟ ሶማሊላንድ ወደ የመን ለመሸጋገር ሲሞክሩ የነበሩ 170 ኢትዮጵያዊያን ህገወጥ ስደተኞች በሶማሊላንድ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የራስ ገዟ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል። ስደተኞቹ መረጋጋት ወደ ሌለባት ሀገር የመን ለመጓዝ በ Snaag eion የባህር ዳርቻ በሚገኝ ትልቅ ጀልባ ላይ ተሳፍረው ሳሉ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ከነዚህ ስደተኞች መሃከል ሴቶችም ይገኙበታል ተብሏል። @TikvahethMagazine
1720Loading...
30
በ“ጫካ” የምትገኙ ኢትዮጵያውያን፤ ከላኳችሁ እና ከሚከፍሏችሁ ይልቅ ኢትዮጵያ ትበልጣለች- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “በጫካ፣ በአንዳንድ ስፍራ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን፤ ከላካችሁ ኃይል ይልቅ ኢትዮጵያ ትበልጣለች፤ ከሚከፍሏችሁ ይልቅ ኢትዮጵያ ትበልጣለች” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ተገኝተው ለመግስታቸው በተደረገ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ነው ይህን የተናገሩት። በንግግራቸውም “ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ሰላምና ብልጽግና በጋራ እንድንቆም ከከፋፋይ፣ ከሰፈርተኝነት፣ ከመንደር እሳቤ ወጥታችሁ አብራችሁን ቁሙ” ብለዋል። የባህል፣ የቋንቋ እና የማንነት መገለጫዎች በተፈጥሮ የተለያዩ በመሆናቸው ይህንን መደፍጠጥ አይቻልም ያሉት ተቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ነገር ግን የኛ የቋንቋ፣ የባህል እና የአቀማመጥ ልዩነት ኢትዮጵያን የሚበትን መሆን የለበትም” ሲሉ ተደምጠዋል። በመድረኩ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በማለት እንደገለጹት “አንድነት ኃይል ነው” የሚለውን አባባል በተግባር ያሳየው የጉራጌ ሕዝብ፤ “ሊከፋፍሉን፣ ሊለዩን፣ ሊያባሉን ለሚፈልጉ፤ በየዕለቱ ገንዘባቸውንና እውቀታቸውን ለሚያጠፉ ሁሉ” ትምህርት መሆን አለበት። የማትለምንና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ በጋራ እንድናሻግር፤ “የሳታችሁ ወንድሞቻችን ልቦና እንዲሰጣችሁ እኔና የወልቂጤ ሕዝብ በጋራ መልዕክት እናስተላልፋለን”ም ብለዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት አመለካከት አለ ያሉት ዐቢይ አህመድ፤ አንደኛው ኢትዮጵያ ትፈርሳለች፣ ትበታታናለች የሚል ሲሆን “እኛ ደግሞ ኢትዮጵያ ትበለጽጋለች፤ የአፍሪካ የነጻነት፣ የኢኮኖሚ፣ የሰላምና የአንድነት ምሳሌ ትሆናለች እንላለን” ሲሉ ገልጸዋል። ሃሳቦቹ በቀላሉ አይታረቁም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የጉራጌ ሕዝቦች መርካቶን ነጻ እንዳወጣችሁ፤ ዛሬ አዲስ አበባን ከሽንት፣ ከቆሻሻ፣ ከአልባብሌ እሳቤ፣ እጅግ ኋላ ቀር ከሆነ የኑሮ ዘዬ አላቀን ወደእውነተኛ የብልጽግና ምልክት ለማሻገር የምናደርገውን ሂደት” እንድትደግፉ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
1460Loading...
31
ሰሞኑን በአሜሪካ ፊላዲልፊያ ወንጀል ተጠርጥሮ በመንታ ወንድሙ ፖሊስ በካቴና ታስሮ ወደ ጣቢያ የሄደው ሰው ያሳየው ፈገግታ ማህበራዊ ሚዲያውን አስገርሟል።
1500Loading...
32
በቋሚ ፈገግታው ምክንያት ኩካካ በጣም ደስተኛ እንስሳ እንደሆነ ይታወቃል።
1530Loading...
33
የቡድን ሰባት ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፤ በኢትዮጵያ ያሉ “ውጥረቶች” እንደሚያሳስቧቸው ገለጹ የቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች ይታያሉ ያሏቸው፤ “የማያቋርጡ እና ኃይለኛ ውጥረቶች” እንደሚያሳስቧቸው ገለጹ። በኢንዱስትሪ የበለጸጉት ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ይፈጸማሉ የሚባሉ “የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እና በደሎች ሪፖርቶች”፣ “ብርቱ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ” እና “የምግብ ዋስትና እጦት መስፋፋት” እንዳሰጋቸውም አስታውቀዋል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በኢትዮጵያ ጉዳይ ስጋታቸውን ያንጸባረቁት፤ በጣልያኗ ካፕሪ ደሴት ያካሄዱትን ስብሰባ ሲያጠናቅቁ ዛሬ አርብ ምሽት ባወጡት መግለጫ ነው። ሚኒስትሮቹ በዚሁ መግለጫቸው፤ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል በተፈረመው ግጭት የማቆም ስምምነት አተገባበር ረገድ የተወሰዱ እርምጃዎችን በበጎ እንደሚቀበሉ ገልጸዋል። በሰብዓዊ መብቶች እና በሲቪል ሰዎች ጥበቃ፣ ውጥረቶችን ለመፍታት በሚደረግ ፖለቲካዊ ውይይት፣ በዕርቅ፣ በብሔራዊ ውይይት፣ የሽግግር ፍትህ እና በግጭት ወቅት ወንጀል የፈጸሙ ተጠያቂ ለማድረግ ተጨማሪ እና ዘላቂ እርምጃዎች ተግባራዊ እንዲደረጉ አበረታተዋል። በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በመካሄድ ላይ በሚገኙ ግጭቶች የሚሳተፉ ወገኖች፤ በንግግር ሰላም ለማውረድ ተመሳሳይ ቁርጠኝነት እንዲኖራቸው ጥሪ አቅርበዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
1750Loading...
34
Media files
1710Loading...
35
ራይድ እና ቪዛ የትራንስፖርት ክፍያን ለማቀላጠፍ ተጣመሩ፡፡ በኢትዮጵያ ቀዳሚው የጥሪ-ትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ራይድ እና ታዋቂው ዓለም አቀፍ የድጂታል ከፍያ ተቋም ቪዛ ጎብኚዎች፣ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች እና የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት የትራንስፖርት ክፍያቸውን በራይድ መተግበሪያ አማካኝነት ለመፈጸም የሚያስችለውን ጥምረት በዛሬው ዕለት አበሰሩ። ይህ ጥምረት ጎብኚዎች፣ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች እና ዲያስፖራዎች የቪዛ ካርዳቸውን ብቻ በመጠቀም የመጓጓዣ ክፍያቸውን እንዲያከናውኑ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ አማራጭ የማቅረቡ ጥረት ጅምር ነው፡፡ በዚህም መንገደኞች ስለ ገንዘብ እና ምንዛሪ ሳይጨነቁ በኢትዮጵያ አርኪ ቆይታ እንዲኖራቸው ያግዛል። የራይድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳምራዊት ፍቅሩ “ለጎብኚዎች፣ በኢትዮጵያ ለሚኖሩ የውጭ አገር ሰዎች እና ለዲያስፖራ አባላት ይህንን አስተማማኝ እና ቀልጣፋ የክፍያ አማራጭ ለማቅረብ ከቪዛ ጋር መጣመራችን አርክቶናል'' ብለዋል። አያይዘውም “ትብብሩ የኤፌዲሪ መንግስት በቅርቡ ካስጀመረው የድጂታል ኢትዮጵያ 2025' ትልም ጋር በጥብቅ ከመተሳሰሩ በተጨማሪ፤ የራይድን መተግበሪያ ለመጠቀም በጎብኚዎች በኩል የታየውን ፍላጎት በብቃት ለማስተናገድ ያለንን ተነሳሽነት ያመላክታል" ሲሉ አክለዋል። በኢትዮጵያ የቪዛ ዳይሬክተሩ አቶ ያሬድ በበኩላቸው “ቪዛ የተቀላጠፈ እና አስተማማኝ የድጂታል ክፍያን ለሁሉም እና በሁሉም ቦታ ለማዳረስ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል። “ከራይድ ጋር የተጀመረው ጥምረት በዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ዘንድ አስተማማኝነቱ የተመሰከረለትን የቪዛ ክፍያ ሥርዓት በማቅረብ የኢትዮጵያን የጉዞ እና ቱሪዝም ዘርፍ ለመደገፍ ተቋማቸው ያነገበውን ቁርጠኝነት እንደሚያመላክት" ጠቅሰዋል። ራይድ በቀልጣፋ የሞባይል መተግበሪያ እና በ8294 የጥሪ ማዕከል አማካኝነት በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መንገደኞችን ከአገልግሎት ሰጪዎች ጋር የሚያገናኝ ፈር ቀዳጅ የጥሪ-ትራንስፖርት ድርጅት ነው። ራይድ ከተመሰረተበት ከ2006 ዓ.ም አንስቶ የአፍሪካዊያንን የዕለት ተዕለት ኑሮ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማሳለጥ ያለመ ተዓማኒ፣ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እየተጋ ይገኛል። በኢትዮጵያ በሦስት ከተሞች የሚንቀሳቀስ ሲሆን፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቋሚ ደንበኞችን በብቃት ያገለግላል። እንዲሁም በዛሬዉ እለት ከራይድ ጋር ጥምረቱን  ያደረገዉ  ቪዛ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ደንበኞቹ፣ ለንግድ እና የገንዘብ ተቋማት እና ለመንግታዊ ድርጅቶች የድጂታል ከፍያንየሚያከናውን ዓለም አቀፋዊ ተቋም ነው። ቀዳሚ ተልዕኮውም ግለስቦች፣ የንግድ ድርጅቶች እና ኢኮኖሚዎች ኦይበልጥ እንዲጎለብቱ እና እንዲሳለጡ ማስቻል ነው። ቪዛ በዓለም ዙሪያ ከ 200 በላይ ሀገራት የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች አሉት። ድጂታል ኢትዮጵያ “የአራተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት ዋነኛ መገለጫ የሆነውን የድጂታል ትራንስፎርሜሽን በይፋ ተቀላቅሎ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ጀምራለች፡፡ ለዚህም ይረዳ ዘንድ በኢፌዲሪ መንግስት አስተባባሪነት “ድጂታል ኢትዮጵያ 2025” የተሰኘ መርሐ ግብር ተቀርፆ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ፈጣን እና የተሳለጠ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊለውጥን ለመተግበር የድጂታል ቴክኖሎጂን ያማከለ ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂ ተነድፏል። የድጂታል መታወቂያ፣ የድጂታልክፍያ እና የሳይበር ደህንነት ውጥኖች የዚህ ስትራቴጂ ቁልፍ ነጥቦች ናቸው። ለዚህም የዲጂታል ክፍያን ቀልጣፋ ለማድረግ አቢሲኒያ እና እናት ባንክ አንድ ላይ በመሆን እንደሚሰሩ አብስረዋል።
1600Loading...
36
Media files
1600Loading...
37
አውስትራሊያዊው ሰው በ24 ሰዓታት ውስጥ 120 መጠጥ ቤቶችን ገብተው 20 ሊትር መጠጥ በመጠጣታቸው ጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ ላይ ተመዘገቡ ዳቪድ ክላርክሰን የተባሉት ሰው ከሳምንት በፊት በገቡበት መጠጥ ቤት ቢያንስ በአማካኝ 125 ሚሊ ሊትር መጠጥ የጠጡ ሲሆን በአጠቃላይ በ 24 ሰዓታት ውስጥ 20 ሊትር የተለያየ የአልኮል መጠጥ ጠጥተዋል።
1750Loading...
38
⚡️ለፖርሽ መኪና ከዚህ የተሻለ ማስታወቂያ የለም ያስብላል ሰሞኑ በዱባይ የጎርፍ መጥለቅለቅ የፖርሽ ታይካን ከተዋጠችበት ስትወጣ የሚያሳየው ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ብዙ ታይቷል።
1780Loading...
39
የዉጪ ባለሃብቶች ከማዳበሪያ እና ከነዳጅ በስተቀር በሁሉም የንግድ ኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ እንዲሳተፉ ተፈቀደ! መሰረታቸውን በዉጪ ያደረጉ ባለሃብቶች በችርቻሮ እና በጅምላ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ፍቃድ መሰጠቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሸን እና የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጋራ አስታውቀዋል። ከጅምላ ንግድ ጋር ተያይዞ ከማዳበሪያና ከነዳጅ ጅምላ ንግድ በስተቀር በሁሉም አይነት የጅምላ ንግድ መስኮች መሰማራት ይችላሉ ተብሏል በዚህም በጥሬ ቡና፣ በቅባት እህሎች፣ ጫት፣ ጥራጥሬ፣ ቆዳ እና ሌጦ፣ የደን ውጤቶች እና የቁም እንስሳት የመላከ የወጪ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ነዉ የተፈቀደው ። ከዚህ ቀደም ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ ተከልለው የቆዩ የወጪ፣ የገቢ፣ የጅምላ እና የችርቻሮ ንግድ ዘርፎች አሁን ደግሞ ለውጭ ባለሃብቶች ከፍት እንዲሆኑ መደረጉ ነዉ ለማወቅ የተቻለው። Via Capital
1610Loading...
40
ሊቅ አዕላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን መጠኑ ከፍተኛ የኾነ ገንዘብ ወደ ግል ሒሳባቸው ሊያስገቡ ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ ተባለ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ የኾኑት ሊቅ አዕላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን በጸጥታ አካላት ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዋዜማ ከታማኝ ምንጮች ሰምታለች። ምክትል ሥራ አስኪያጁ ትላንት ማክሰኞ ሚያዚያ 9 ቀን በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ አፍሪካ ኅብረት ዋና መስሪያ ቤት አካባቢ በሚገኝ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ መጠኑ ከፍተኛ የኾነ ገንዘብ ወደ ግል ሒሳባቸው ሊያስገቡ ሲሉ መሆኑን ምንጮች ለዋዜማ ተናግረዋል። ሊቀ አዕላፍ በላይ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ልደታ ወደሚገኘው አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውን ዋዜማ ተናግረዋል። ሊቀ አዕላፍ በላይ ከዓመታት በፊት ከቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ልዩነት ከፈጠሩ በኋላ፣ በእርቅ ወደ ቤተክህነት ተመልሰው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ኾነው እንደተሾሙ ይታወሳል። Via ዋዜማ
1681Loading...
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 22 ሰዎች በወባ በሽታ ህይወታቸውን አተዋል ተባለ። ወቅቱ የወባ ስርጭት ከፍተኛ የሚሆንበት በመሆኑ በክልሉ 22 ሰዎች በወባ በሽታ ህይወታቸውን ማጣታቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ናፍቆት ብርሀኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በአሁኑ ወቅት በሳምንት እስከ 7 ሺ የሚሆኑ ሰዎች በወባ በሽታ እየተያዙ እንደሚገኙ ተናግረዋል ፡፡ ችግሩን ለመቅረፍም የአካባቢው ማህበረሰብ እንዴት እራሱን ከወባ በሽታ መከላከል እንደሚችል የተለያዩ ትምህርቶችን እየሰጡ እንደሚገኙ አንስተዋል፡፡ በአከባቢው ላይ ውሀ ያቆሩ ቦታዎችን የማፋሰስ ስራ እና ማህበረሰቡ አጎበር እንዲጠቀም የማድረግ ስራዎችን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ ሰዎች የትኩሳት ስሜት ሲሰማቸው በተለይም ህፃናት እና ነፍሰጡሮች እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲያስተውሉ  ወደ ጤና ተቋም ሄደው ተገቢውን የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ እያደረን እንገኛለን ሲሉ ምክትል ሀላፊው ተናግረዋል፡፡
Show all...
ኢትዮጵያና ኮንጎ ብራዛቪል የአየር ትራንስፖርት ስምምነት ተፈራረሙ ኢትዮጵያና ኮንጎ ብራዛቪል ዛሬ ሚያዚያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም የሁለትዮሽ የአየር ትራንስፖርት ስምምነት እዚህ አዲስ አበባ የተፈራረሙ ሲሆን ቀደም ሲል ሁለቱ ሀገራት እ.ኤ.አ. ሜይ 5/ 2017 በአጭር ፊርማ የተፈረመውን ስምምነት የአፍሪካ አየር መንገዶች በአፍሪካ አየር ክልል ላይ ያለምንም ገደብ የበረራ አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችላቸው እና በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ ህብረት አነሳሽነት እየተተገበረ ባለው በያሙሱኩረ ውሳኔ (Yamoussoukro Decision) መሰረት በማሻሻል በአጭር ፊርማ በሙሉ ለማጠናቀቅ ያስቻለ ነው፡፡ ዛሬ የተከናወነው ስምምነት የአንዱ ተዋዋይ ሀገር ተወካይ አየር መንገድ የሌላውን ተዋዋይ አገር አየር ክልል አቋርጦ የመብረር መብት (Over Flights)፣ በበረራ ላይ ያለ የአንዱ ወገን ተወካይ አየር መንገድ አውሮፕላን በበረራ ላይ ችግር ሲገጥመው ወይም ነዳጅ ለመሙላት በሌላኛው ወገን አየር ማረፊያ የማረፍ መብት (Technical Landing)፣ መንገደኛ ወይም ጭነት ካንድ ተዋዋይ ወገን በማንሳት ወደ ሌላኛው ተዋዋይ ወገን አየር ማረፊያ ወስዶ የማራገፍ መብት (3rd freedom traffic rights) የሚያስችል ነው። በተጨማሪም መንገደኛ ወይም ጭነት ከሌላኛው ተዋዋይ ወገን አየር ማረፊያ በማንሳት ወደ ሀገር የመመለስ መብት(4th freedom traffic rights)፣ እና በአፍሪካ አገራት ውስጥ በ5ኛ የትራፊክ መብት በመጠቀም መንገደኛ እና ጭነት ከሌላኛው ተዋዋይ ወገን አየር ማረፊያ አንስቶ ወደ ሌላ 3ኛ አገር አየር ማረፊያ የማራገፍ/አንስቶ የመመለስ መብት መብት (5th freedom traffic rights) የሚያሰጥ ነው። በመሆኑ የስምምነቱ በሙሉ ፊርማ መጠናቀቅ ሀገራችን ከኮንጎ ሪፐብሊክ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክር፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቱሪዝም፣ ንግድና ኢንቨስትመንት የሚያበረታታ፣ የበረራ ተደራሽነት የሚያሳድግና ለአየር መንገዳችን ተጨማሪ የገበያ ዕድል የሚፈጥር፣ እና የውጭ ምንዛሬን በማዳንም ሆነ በማስገኘት ረገድ አዎንታዊ አስተዋፅኦ የሚያበረክት በመሆኑ ለሀገራችን የሚያገኘው ጥቅም ከፍተኛ ነው፡፡ ስምምነቱን በኢትዮጵያ በኩል የፈረሙት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚንስትር ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ ሲሆኑ የኮንጎ ብራዛቪል የትራንስፖርት: ሲቪል አቪዬሽንና የመርቻንት ኔቪ ሚኒስትር ሚስተር ኦነሬ ሳይ ደግሞ ሀገራቸውን በመወከል ፈርመዋል። በአሁኑ ሰዓት አየር መንገዳችን ወደ ኮንጎ ብራዛቪል በሳምንት ሰባት (07) በረራ የሚያደርግ ሲሆን የስምምነቱ በሙሉ ፊርማ መጠናቀቅ የበረራ ምልልሱ ላይ ለውጥ የሚያመጣ ባይሆንም ተፈጻሚነቱን ግን ከፍ ያደርጋል፡፡ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ስምምነቶች የቱሪዝም፣ ንግድና ኢንቨስትመንት የሚያስድ ከመሆኑም በላይ ከአገራት ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክር፣ ለአየር መንገዶች ተጨማሪ የገበያ ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ ለአገር የሚያበረክቱት አስተዋፅዎም ላቅ ያለ ነው። በዚሁ አግባብ ባጠቃላይ አገራችን ኢትዮጵያ ከ111 አገሮች ጋር የአየር አገልግሎት ስምምነቶችን በአጭርና በሙሉ ፊርማ ደረጃ ተፈራርማለች፡፡ በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ79 አገራት በረራ እያደረገ ያለ ሲሆን 135 መዳረሻዎችም አሉት፡፡
Show all...
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ቦይንግ በወንጀል እንዲከሰስ ጠየቁ! በኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ከአምስት ዓመት በፊት ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ለአደጋው መንስዔ የሆነው የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ላይ የወንጀል ክስ እንዲመሠረት የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤትን ጠየቁ።የመንገደኞቹ ቤተሰቦች በዋሽንግተን ከአሜሪካ የፍትህ ባለሥልጣናት ጋር ሚያዝያ 16/ 2016 ዓ.ም በተነጋገሩበት ወቅት የአሜሪካው ኩባንያ ቦይንግ ለፍርድ እንዲቀርብ ጠይቀዋል። የተጎጂዎች ቤተሰቦች እና ተወካይ ጠበቆቻቸው ኩባንያው የሚያመርታቸውን አውሮፕላን ምርቶች ደኅንነት እና ጥራት ለማስጠበቅ ከሦስት ዓመት በፊት ከአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ጋር የገባውን የቁጥጥር መርሃ ግብር ጥሷል ብለዋል። የ157 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈው ከኢትዮጵያው አደጋ በተጨማሪ ለ189 ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት በሆነው የኢንዶኔዥያ አየር መንገድ አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ቦይንግ በወንጀል እንዲጠየቅ ለፍትህ መሥሪያ ቤቱ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል። በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው አሰቃቂ በተባለው በቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን አደጋዎች የ346 ሰዎች ሕይወት አልፏል።በሁለቱ አውሮፕላን አደጋዎች ሕይወታቸውን ያጡ ቤተሰቦች በቅርቡ ንብረትነቱ የአሜሪካ አላስካ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በበረራ ላይ ሳለ መስኮቱ መገንጠሉ ጋር ተያይዞ አሁንም የደኅንነት እና የጥራት ችግር እንዳለበት የሚያሳይ ነው ብለዋል። የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤት በአውሮፕላንን አምራቹ ላይ ካደረገው የረዥም ጊዜ ምርመራ በኋላ ቦይንግ ለ737 ማክስ አውሮፕላኑ ፍቃድ ለማግኘት ሲል ሆን ብሎ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ተቆጣጣሪዎችን እንዳሳሰተ ደርሸበታለሁ በሚል “አሜሪካን ለማጭበርበር በማሴር” በሚል ከሦስት ዓመት በፊት ክስ መስርቶበት ነበር። ቦይንግ ቺካጎ በነበረው የፍርድ ሂደት በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ካሳ ለመክፈል ተስማምቶ በምላሹም የአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት ለአውሮፕላን አምራቹ ከ737 ማክስ ዲዛይን ጉድለት ጋር በተያያዘ በማጭበርበር ሴራ በወንጀል እንዳይከሰስ ከለላ ሰጥቶት ነበር። የአውሮፕላን አምራቹ በአደጋው ለሞቱት ሰዎች ኃላፊነቱን እንደሚወስድ እና ተጠያቂነቱን ተቀብሎ ለአሜሪካ መንግሥት፣ አደጋ ለደረሰባቸው አየር መንገዶች እና ለተጎጂዎች የሚሆን 2.5 ቢሊዮን ዶላር የቅጣት ካሳ ለመክፈል ተስማምቷል።
Show all...
👍 1