cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሁሌ መረጃ.com/hule merja

የሰው ልጅ መረጃ የማግኘት መብቱ መገደብ የለበትም...እኛም ይህንን ፍላጎት ለመሙላት እዚ አለን፡፡ሁሌ መረጃ ሁሌ እውነት

Show more
Advertising posts
657Subscribers
+124 hours
+67 days
+1430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ኢትዮጵያና ኮንጎ ብራዛቪል የአየር ትራንስፖርት ስምምነት ተፈራረሙ ኢትዮጵያና ኮንጎ ብራዛቪል ዛሬ ሚያዚያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም የሁለትዮሽ የአየር ትራንስፖርት ስምምነት እዚህ አዲስ አበባ የተፈራረሙ ሲሆን ቀደም ሲል ሁለቱ ሀገራት እ.ኤ.አ. ሜይ 5/ 2017 በአጭር ፊርማ የተፈረመውን ስምምነት የአፍሪካ አየር መንገዶች በአፍሪካ አየር ክልል ላይ ያለምንም ገደብ የበረራ አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችላቸው እና በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ ህብረት አነሳሽነት እየተተገበረ ባለው በያሙሱኩረ ውሳኔ (Yamoussoukro Decision) መሰረት በማሻሻል በአጭር ፊርማ በሙሉ ለማጠናቀቅ ያስቻለ ነው፡፡ ዛሬ የተከናወነው ስምምነት የአንዱ ተዋዋይ ሀገር ተወካይ አየር መንገድ የሌላውን ተዋዋይ አገር አየር ክልል አቋርጦ የመብረር መብት (Over Flights)፣ በበረራ ላይ ያለ የአንዱ ወገን ተወካይ አየር መንገድ አውሮፕላን በበረራ ላይ ችግር ሲገጥመው ወይም ነዳጅ ለመሙላት በሌላኛው ወገን አየር ማረፊያ የማረፍ መብት (Technical Landing)፣ መንገደኛ ወይም ጭነት ካንድ ተዋዋይ ወገን በማንሳት ወደ ሌላኛው ተዋዋይ ወገን አየር ማረፊያ ወስዶ የማራገፍ መብት (3rd freedom traffic rights) የሚያስችል ነው። በተጨማሪም መንገደኛ ወይም ጭነት ከሌላኛው ተዋዋይ ወገን አየር ማረፊያ በማንሳት ወደ ሀገር የመመለስ መብት(4th freedom traffic rights)፣ እና በአፍሪካ አገራት ውስጥ በ5ኛ የትራፊክ መብት በመጠቀም መንገደኛ እና ጭነት ከሌላኛው ተዋዋይ ወገን አየር ማረፊያ አንስቶ ወደ ሌላ 3ኛ አገር አየር ማረፊያ የማራገፍ/አንስቶ የመመለስ መብት መብት (5th freedom traffic rights) የሚያሰጥ ነው። በመሆኑ የስምምነቱ በሙሉ ፊርማ መጠናቀቅ ሀገራችን ከኮንጎ ሪፐብሊክ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክር፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቱሪዝም፣ ንግድና ኢንቨስትመንት የሚያበረታታ፣ የበረራ ተደራሽነት የሚያሳድግና ለአየር መንገዳችን ተጨማሪ የገበያ ዕድል የሚፈጥር፣ እና የውጭ ምንዛሬን በማዳንም ሆነ በማስገኘት ረገድ አዎንታዊ አስተዋፅኦ የሚያበረክት በመሆኑ ለሀገራችን የሚያገኘው ጥቅም ከፍተኛ ነው፡፡ ስምምነቱን በኢትዮጵያ በኩል የፈረሙት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚንስትር ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ ሲሆኑ የኮንጎ ብራዛቪል የትራንስፖርት: ሲቪል አቪዬሽንና የመርቻንት ኔቪ ሚኒስትር ሚስተር ኦነሬ ሳይ ደግሞ ሀገራቸውን በመወከል ፈርመዋል። በአሁኑ ሰዓት አየር መንገዳችን ወደ ኮንጎ ብራዛቪል በሳምንት ሰባት (07) በረራ የሚያደርግ ሲሆን የስምምነቱ በሙሉ ፊርማ መጠናቀቅ የበረራ ምልልሱ ላይ ለውጥ የሚያመጣ ባይሆንም ተፈጻሚነቱን ግን ከፍ ያደርጋል፡፡ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ስምምነቶች የቱሪዝም፣ ንግድና ኢንቨስትመንት የሚያስድ ከመሆኑም በላይ ከአገራት ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክር፣ ለአየር መንገዶች ተጨማሪ የገበያ ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ ለአገር የሚያበረክቱት አስተዋፅዎም ላቅ ያለ ነው። በዚሁ አግባብ ባጠቃላይ አገራችን ኢትዮጵያ ከ111 አገሮች ጋር የአየር አገልግሎት ስምምነቶችን በአጭርና በሙሉ ፊርማ ደረጃ ተፈራርማለች፡፡ በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ79 አገራት በረራ እያደረገ ያለ ሲሆን 135 መዳረሻዎችም አሉት፡፡
Show all...
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ቦይንግ በወንጀል እንዲከሰስ ጠየቁ! በኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ከአምስት ዓመት በፊት ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ለአደጋው መንስዔ የሆነው የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ላይ የወንጀል ክስ እንዲመሠረት የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤትን ጠየቁ።የመንገደኞቹ ቤተሰቦች በዋሽንግተን ከአሜሪካ የፍትህ ባለሥልጣናት ጋር ሚያዝያ 16/ 2016 ዓ.ም በተነጋገሩበት ወቅት የአሜሪካው ኩባንያ ቦይንግ ለፍርድ እንዲቀርብ ጠይቀዋል። የተጎጂዎች ቤተሰቦች እና ተወካይ ጠበቆቻቸው ኩባንያው የሚያመርታቸውን አውሮፕላን ምርቶች ደኅንነት እና ጥራት ለማስጠበቅ ከሦስት ዓመት በፊት ከአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ጋር የገባውን የቁጥጥር መርሃ ግብር ጥሷል ብለዋል። የ157 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈው ከኢትዮጵያው አደጋ በተጨማሪ ለ189 ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት በሆነው የኢንዶኔዥያ አየር መንገድ አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ቦይንግ በወንጀል እንዲጠየቅ ለፍትህ መሥሪያ ቤቱ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል። በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው አሰቃቂ በተባለው በቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን አደጋዎች የ346 ሰዎች ሕይወት አልፏል።በሁለቱ አውሮፕላን አደጋዎች ሕይወታቸውን ያጡ ቤተሰቦች በቅርቡ ንብረትነቱ የአሜሪካ አላስካ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በበረራ ላይ ሳለ መስኮቱ መገንጠሉ ጋር ተያይዞ አሁንም የደኅንነት እና የጥራት ችግር እንዳለበት የሚያሳይ ነው ብለዋል። የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤት በአውሮፕላንን አምራቹ ላይ ካደረገው የረዥም ጊዜ ምርመራ በኋላ ቦይንግ ለ737 ማክስ አውሮፕላኑ ፍቃድ ለማግኘት ሲል ሆን ብሎ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ተቆጣጣሪዎችን እንዳሳሰተ ደርሸበታለሁ በሚል “አሜሪካን ለማጭበርበር በማሴር” በሚል ከሦስት ዓመት በፊት ክስ መስርቶበት ነበር። ቦይንግ ቺካጎ በነበረው የፍርድ ሂደት በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ካሳ ለመክፈል ተስማምቶ በምላሹም የአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት ለአውሮፕላን አምራቹ ከ737 ማክስ ዲዛይን ጉድለት ጋር በተያያዘ በማጭበርበር ሴራ በወንጀል እንዳይከሰስ ከለላ ሰጥቶት ነበር። የአውሮፕላን አምራቹ በአደጋው ለሞቱት ሰዎች ኃላፊነቱን እንደሚወስድ እና ተጠያቂነቱን ተቀብሎ ለአሜሪካ መንግሥት፣ አደጋ ለደረሰባቸው አየር መንገዶች እና ለተጎጂዎች የሚሆን 2.5 ቢሊዮን ዶላር የቅጣት ካሳ ለመክፈል ተስማምቷል።
Show all...
የሜክሲኮ የምግብ አቅራቢ የአይጥ መረቅን ከ50 ዓመታት በላይ ለደንበኞቹ ሲያቀርብ መቆየቱን አስታወቀ በሜክሲኮ ሜርካዶ ሪፐብሊካ ደ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ በሚሰኘው ገበያ ውስጥ በርካታ ነገሮችን ፈልጎ ማግኘት ይቻላል፣ ነገር ግን ከሁሉም በላይ ልዩ የሆነው የአይጥ ስጋን በመሸጥ የሚታወቅ የቆየ የምግብ አቅራቢ ድርጅት ታዋቂ ነው። ለበርካታ የዓለም ህዝብ የአይጥ ስጋ በፍፁም የማይለመድ እና ነውር ቢሆንም በሜክሲኮ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ ክልል ውስጥ ግን ለየት ያለ ጣዕሙ እና ለመድኃኒትነት ይውላል በሚል ለረጅም ዓመታት ጥቅም ላይ ውሏል። ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአይጥ ሥጋ የሚሸጡባቸው ሱቆች እና አከፋፋዮች ከአካባቢው ገበያ እየጠፉ ይገኛል። በሜርካዶ ሪፑብሊካ ደ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ ውስጥ ግን አንዱ አከፋፋይ አሁንም ሁለቱንም ማለትን ጥሬ የአይጦች ስጋ እና የአይጥ መረቅ ከተለያዩ አትክልቶች እና ቅመማ ቅመም ጋር አዋህዶ መሸጡን ቀጥሏል። እያንዳንዱ የአይጥ መረቅ አንድ ሙሉ ሳህን የሚይዘው  በ100 የሜክሲከ ፔሶ ወይም በ5.80 የአሜሪካን ዶላር ዋጋ ተቆርጦለታል።በሜርካዶ ሪፑብሊካ የመጨረሻው የአይጥ ስጋ ሻጭ ሆሴ ሬሜዲዮስ ሄርናንዴዝ "ካሚሎ" በመባልም የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየችው ወላጅ እናቱ ይህንኑ ንግድ ወርሷል። በአንድ ወቅት በገበያው ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ የአይጥ ስጋ ሻጮች እንደነበሩ ያስታውሳል፣ ነገር ግን ሁሉም ጡረታ ወጥተዋል አልያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አሁን ላይ በገበያው ውስጥ ብቸማ አቅራቢ ሆኖ ቀጥሏል። ስራው እየተቀዛቀዘ በርካቶች ከዘርፉ ቢወጡን በቅርብ ጊዜ ውስጥ የቤተሰብን ንግድ ለመተው እቅድ የለኝም ሲል ይናገራል። ይህው የቤተሰቡ ንግድ ለ52 ዓመታት ዘልቋል። በተቻለም መጠን ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ ለማድረግ የአቅሜን ያህል መስራቴን እቀጥላለሁ ሲል ይደመጣል። ካሚሎ የሚያቀርበውን የአይጥ ሾርባ ለማዘጋጀት  በሳን ሉዊስ ፖቶሲ ዙሪያ ካሉ የከተማ አካባቢ እና በዙሪያው ክሚገኙ ገጠራማ ስፍራዎች ተይዘው ይመጣሉ። የአይጥ ሥጋ በተለይ የደም ማነስ፣ የስኳር በሽታ ወይም ካንሰር ላለባቸው ሰዎች ጠቃሚ ሲሆን የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን ለማጠናከር እና የምግብ ፍላጎትን ለመጨመር ይረዳል ተብሎ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ይታመናል። በሜርካዶ ሪፑብሊካ ደ ሳን ሉዊስ ፖቶሲ ውስጥ በሚገኘው ካሚሎ ሁለቱንም የአይጥ መረቅ በ100 ፔሶ የሚሸጥ ሲሆን ጥሬ አይጥ ገዝተው ቤት ይዘው ለሚሄዱ በ90 ዋጋ ይቀርባል።የስጋውን ጣዕም በትክክል ለማሟላት በአትክልቶችና ቅመማ ቅመሞች ለማብሰል ይመክራል ሲሉ የሬስቶራንቱ ባለሙያዎች ይናገራሉ። በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ ቤት እና ስቱዲዮ ጥገና ሊደረግለት ነው። እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ ቤት እና ስቱዲዮ የጥገና ስራ ለማከናወን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ከ ቢዋይ ኤምቲ ኮንትራክተር እና ዳሎል አማካሪ ድርጅት መካከል የተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች በተገኙበት በ15/08/2016 ዓ.ም የስራ ርክክብ ተደርጓል። በፕሮግራሙ ላይ መልእክታቸውን ያስተላለፉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው  ቅርሱ የነበረውን አሻራና ይዘት በጠበቀ መልኩ  የቅርስ ጥገና መርሆዎችን በተከተለ መንገድ በጥንቃቄ መከናወን እንዳለበት ገልፀው፡፡የጥገና ስራው በተያዘለት የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ጥራቱን ጠብቆ መጠገንና ለሃገር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ መሆን እንደሚኖርበት አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም ስራ ተቋራጩ ይህን ታሪካዊ ቅርስ ጥገና ማድረግ በመቻላቸው እድለኛ እንደሆኑ ገልጸው ስራውን በተፈለገው ጊዜና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ አከናውነው እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል፡፡
Show all...
ከኢትዮጵያ ከ 350 በላይ ስደተኞች ወደ አሜሪካ ማቅናታቸውን አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይኦኤም አስታወቀ በተያዘዉ 2016 ዓመት ሰኔ ወር 4ሺ6 መቶ 8 ስደተኞች ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አይ ኦ ኤም አስታውቋል። አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ለብስራት ሬድዮ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ድርጅቱ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመነጋገር እና በመተባበር በኢትዮጵያ የሚገኙ የሶስተኛ ሀገር ስደተኛ ዜጎች ወደ አደጉ ሀገራት የማሸገር ስራ ይሰራሉ፡፡ አይኦኤም በመልሶ ማቋቋሚያ ስር  ውስጥ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደ አሜሪካ እንዲደርሱ ለማድረግ ተከታታይ የቻርተር በረራ እንቅስቃሴዎችን እና እንዲሁም በንግድ አየር መንገዶች ላይ የቡድን ምዝገባዎችን ያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ድጋፍ ያለው የዩናይትድ ስቴትስን የ2024 የስደተኞች መጤ ግብ ለማሳካት የስደተኞችን መልሶ የማቋቋም ስራ እያሰፋ ይገኛል።ዩናይትድ ስቴትስ በ2024 ከ4ሺ500 በላይ ስደተኞችን ከኢትዮጵያ ለመቀበል ቃል መግባቱን አይኦኤም አስታውቋል፡፡ ባለፉት አስርት አመታት ውስጥ ብቻ አይኦኤም ከ1.19 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን እና ሌሎች ስጋት ያለባቸውን በአለም ዙሪያ ካሉ 166 አካባቢዎች የመቋቋሚያ እንቅስቃሴዎችን አዘጋጅቶ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል።በ2023 አይኦኤም 5ሺ3 መቶ4 ስደተኞችን ኢትዮጵያ አስፍሯል። ከእነዚህ ውስጥ 1ሺ1መቶ 94ቱ ወደ አሜሪካ አቅንተዋል።
Show all...
በኢትዮጵያ በገዳይነቱ የተመዘገበው የ 'ካላዛር' በሽታን ለማከም የሚውል መድኃኒት በሰዎች ላይ መሞከር ተጀመረ የካላዛር ሕሙማንን ለማከም ለ17 ቀናት የሚሰጠውን የመርፌና የእንክብል መድኃኒት ሙሉ ለሙሉ በእንክብል ብቻ ለመተካት የሚያስችለው መድኃኒት፣ የዕድሜ ክልላቸው ከ18 እስከ 44 በሚደርሱ 52 ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያን ላይ ሙከራው ተጀመረ። በምርምሩ 15 የጤና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ሲሆን፣ ፈውስ ትኩረት ለተነፈጉ በሽታዎች ኢኒሺዬቲቭ ወይንም ዲ ኤን ዲ የጤና ምርምር የተባለ ተቋም እና አጋሮቹ ለዚህ በሽታ የሚያደርጉት የመድሃኒት ፍለጋ ምእራፍ ሁለት የክሊኒካል ሙከራ ደረጃ መሸጋገሩ ተጠቁሟል። በአፍሪካ አሁን እየተሰጠ የሚገኘው የካላዛር ህክምና ለ17 ቀናት የሚወሰድ ከፍተኛ ህመም የሚፈጥር ክትባት ሲሆን በኢትዮጵያ በምርምር ላይ የሚገኘው አዲሱ የ “LXE408” በአፍ  የሚወሰድ መድሀኒት አሁን ከሚሰጠው ህክምና የበለጠ ፈዋሽና እንደሚሆን ይጠበቃል ተብሏል። በኢትዮጵያ በዓመት ከ2 እስከ 3 ሺ ሰዎች በካላዛር በሽታ ይያዛሉ ሲባል በበሽታው ተይዘው ሕክምና ካላገኙት ውስጥ 95 በመቶ ያህሉ እንደሚሞቱ ተጠቁሟል። Sheger
Show all...