en
Feedback
ኮኬት

ኮኬት

Open in Telegram

ስለ ዶሮ እርባታ እና እንቁላል መረጃ ለማግኘት በዚህ Link ወደ channalachn ይቀላቀሉ። https://t.me/joinchat/Skco_yn435jyGhWv "መረጃ (Information) ማለት ገንዘብ ማለት ነው...."

Show more
2 144
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
በሀገራችን በብዛት የሚገኙ የእንቁላል ጣይ ዝርያ #ዲካልብ ዋይት_፡- የእጣልያን ዝርያ ነዉ 1. ረዘም ያለ ጀርባ እና እግር አላቸዉ 2. ነጭ ቀለም አላቸዉ 3. በብዛት ነጭ ቅርፊት ያላቸዉ እንቁላል
በሀገራችን በብዛት የሚገኙ የእንቁላል ጣይ ዝርያ #ዲካልብ ዋይት_፡- የእጣልያን ዝርያ ነዉ 1. ረዘም ያለ ጀርባ እና እግር አላቸዉ 2. ነጭ ቀለም አላቸዉ 3. በብዛት ነጭ ቅርፊት ያላቸዉ እንቁላል ይጥላሉ 4.ሞቃት አከባቢ የመኖር አቅም አላቸዉ 5. በ22 ሳሚንት ዕድሜ እንቁላል መጣል ይጀምራሉ 6. ከ280---320 እንቁላል በዓመት በአማካይ ይጥላሉ 7. 2ኪግ. ወንድ፣ 1.5ኪግ. ሴት በአማካይ ይመዝናሉ #ቦቨን_ብራዉን፡- የሆላንድ ዝርያ ነዉ 1. ረዘም ያለ ጀርባ እና እግር አላቸዉ 2. ቀይ ቡኒ ቀለም አላቸዉ 3. በብዛት ቀይ ቡኒ ቀለም ቅርፊት ያላቸዉ እንቁላል ይጥላሉ 4. ሞቃት አከባቢ የመኖር አቅም አላቸዉ 5. በ22 ሳሚንት ዕድሜ እንቁላል መጣል ይጀምራሉ 6. ከ280 -300 እንቁላል በዓመት በአማካይ ይጥላሉ 7. ኪግ. ወንድ፣ 2ኪግ. ሴት በአማካይ ይመዝና

"የኢትዮጽያ ወተት ላም እርባታ Ethioapian Dairy farming" https://t.me/+ckwmrjSK6282Yjdk ስለ ወተት ላም እንድሁም አጠቃላይ ስለ ከብት ዕርባታ ከባለሙያዎች የምክር አ
"የኢትዮጽያ ወተት ላም እርባታ Ethioapian Dairy farming" https://t.me/+ckwmrjSK6282Yjdk ስለ ወተት ላም እንድሁም አጠቃላይ ስለ ከብት ዕርባታ ከባለሙያዎች የምክር አገልግሎት ለማገናኘት ይህን Telegram Group ተቀላቀሉ https://t.me/+ckwmrjSK6282Yjdk

ዶሮዎቼ ትልልቅ እንቁላል እንዲጥሉ ምን ላድርግ? -------------------------------------------------------- የዶሮዎች እንቁላል ትልቀት በክብደት የሚለካ በመሆኑ ምክንያት በአብዛኛው አለም ሃገሮች መሸጫ ካርቶን ክብደት የማያነሳ ተደርጎ የሚሰራው፡፡ የእንቁላል ክብደት በተለያየ ደረጃዎች የሚቀመጡ ሲሆን ይህም • 1.አነስተኛ መጠን=53ግራም • 2.መካከለኛ መጠን=63ግራም • 3.ከፍተኛ(ትልቁ) መጠን=73ግራም የእንቁላል መጠን በተለያዩ ምክንያቶች ከፍ እና ዝቅ ሊል ሲችል ዋነኛ ምክንያት 1.ዝርያ የተለያዩ የዶሮ ዝርያዎች የተለጠያዩ መጠን ያለውን እንቁላል ይጥላሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል የሳሶ ሴት ዶሮ ከቦቫንስ ወይንም ሎማን ብራውን በአማካይ ከፍ ያለ እንቁላል ሊጥሉ ይችላሉ፡፡ይህም ማለት አነስተኛ መጠን ያላቸው ዶሮዎች ሁሉ አነስተኛ እንቁላል ይጥላሉ ማለትም አይደለም፡፡ ተመሳሳይ ዝርያ ዶሮዎች በራሳቸው ትልቅ እና ትንሽ እንቁላል ሊጥሉ ይችላሉ፡፡ 2.እድሜ እንቁላል የዶሮዎች እድሜ በሄደ ቁጥር በመጠንም በክብደትም እየጨመረ ይሄድና በተለምዶ በሃገራችን ነጋዴዎች የደረበ እንቁላል የሚባለው ስያሜ ይይዛል፡፡ ዶሮዎች የመጀመሪያዎቹ ከ8-10 የምርት ሣምንታት በአማካኝ 53ግራም የሚጥሉ ሲሆን ከ30ሣምንት እድሜየቸው በዋላ ከ60 ግራም በአማካይ ይጥላሉ፡፡ በ90 ሳምንታቸው 20% ያህሉ ጃቦ(jumbo) ከ70 ግራም በላይ እስኪደርሱ ድረስ በየሳምንቱ 0.1 ግራም ክብደት እየጨመረ ይሄዳል፡፡ 3.ምግብ የመኖ ምጥን አሰራር እና ጥራት የዶሮዎችን ምርት እና መጠን በሚገባ ይወሰናል፡፡ በተለየ መልኩ ፕሮቲን (ገንቢ ንጥረ ነገር)፣ ካልሺየም፤አሚኖ አሲድ ለእንቁላል ምርት የተለየ ሚና አላቸው፡፡ 4.የቄብ ዶሮዎች ክብደት ቄብ ዶሮዎች የመጀመሪያ ምርታቸው ወቅት አናሳ መጠን ያላቸው እንቁላሎች ይጥላሉ ፡፡ በዚህም እድሚያቸው ከፍተኛ ክብደት ያላቸው ዶሮዎች ትልቅ እንቁላል የመጣል እድል አላቸው በዚያው ልክ ለማህፀን መገልበጥ ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላል፡፡ 4. በሽታ እና ድባቴ በአካባቢ አየር መለወጥ፣ መረበሽ እና ድባቴ ዶሮዎች በእጅጉ ይጎዳቸዋል፡፡በዚህም ምክንያት በመጠንም በአይነቱም በጣም አነስተኛ (fart egg) እና ከመካከለኛ መለስተኛ እንቁላል ይጥላሉ፡፡ ታዲያ ዶሮዎች ትልቅ እንቁላል እንዲጥሉ ምን ላድርግ ? ይህንን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት ኢትዩጵያ ውስጥ ያለው ነባራዊ የእንቁላል ሽያጭ በእንቁላል መጠን እና ክብደት ሳይሆን በፍሬ ወይንም በቁጥር ነው፡፡ ይህ መሆኑ ሁለት ግለሰቦች ተመሳሳይ የእንቁላል ቁጥር ግን ደግሞ የኪሎ ልዩነት ያለውን በተመሳሳይ ዋጋ እንዲሸጡ ይገደዳሉ፡፡ ፍሬሽ(ትኩስ) እንቁላል በክብደቱ ከፍተኛ ሲሆን ከሳምንት እና ከዛ በላይ የቆየ እንቁላል የውሃ መጠኑ ስለሚቀንስ አነስተኛ ክብደት ይኖረዋል ሆኖም ግን ገበያ ላይ የዋጋ ለውጥ አይኖረውም፡፡ ስለሆነም አርቢዎች ትልልቅ እንቁላል መጣሉ ፋይዳው ብዙም አይሆንም፡፡ ይልቁንም ትልልቅ እንቁላል የአልቡሚን እና ዬልክ (አስኮል) መጠኑ ትልቅ ስለሆነ በዚሁ ልክ ከፍተኛ የመኖ እና የውሃ ፍጆታ ይኖራቸዋል፡፡ በአማካይ ከ75 ግራም በላይ እንቁላል የምትጥል ዶሮ ሁለት እጥፍ 150 ግራም መኖ ትመገባለች፡፡ ይህም በአንፃራዊነት ከ120ግራም በላይ ተመግባ የምትጥለው እንቁላል የገበያ ዋጋ (market price) ልዩነት ስለማያመጣ ከትርፍ ኪሳራ ሊያመዝን ይችላል፡፡ ዶሮዎቻችን አነስተኛ እንቁላሎችን በጣሉ ቁርጥ የምርት መጠናቸው የመጨመር ዝንባሌ አለው፡፡

ስለ ዶሮ እርባታ እና እንቁላል መረጃ ለማግኘት በዚህ Link ወደ channalachn ይቀላቀሉ። https://t.me/joinchat/Skco_yn435jyGhWv "መረጃ (Information) ማለት ገንዘብ ማለት ነው...."

የተሻሻለ ዶሮ ርባታ ሥራ ሥልጠና ስለ ዶሮ እርባታ እና እንቁላል መረጃ ለማግኘት በዚህ Link ወደ channalachn ይቀላቀሉ። https://t.me/joinchat/Skco_yn435jyGhWv "መረጃ (Information) ማለት ገንዘብ ማለት ነው...."

ስለ ዶሮ እርባታ እና እንቁላል መረጃ ለማግኘት በዚህ Link ወደ channalachn ይቀላቀሉ። https://t.me/joinchat/Skco_yn435jyGhWv "መረጃ (Information) ማለት ገንዘብ ማለት ነው...."

ስለ ዶሮ እርባታ እና እንቁላል መረጃ ለማግኘት በዚህ Link ወደ channalachn ይቀላቀሉ። https://t.me/joinchat/Skco_yn435jyGhWv "መረጃ (Information) ማለት ገንዘብ ማለት ነው...."

የዶሮ እርባታ Document. ስለ ዶሮ እርባታ እና እንቁላል መረጃ ለማግኘት በዚህ Link ወደ channalachn ይቀላቀሉ። https://t.me/joinchat/Skco_yn435jyGhWv "መረጃ (Information) ማለት ገንዘብ ማለት ነው...."

የዶሮ እርባታ Document....... 👇👇👇👇👇👇👇

ከማንኛውም ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ለእርባታ ግዢ ከመፈፀማቹ በፌት ልብ ልትሉ የሚገባቹ እና ልትታለሉ የምትችሉበት ነገር ቢኖር በምትገዟቸው ዶሮዎች በእድሜያቸው የሚኖረው የክብደት መጠን እንደ ዝርያቸው የሚለያይ ቢሆንም በእድሜያቸው ሊኖራቸው የሚገባውን ክብደት ሠ ማሟላት መቻላቸውን ማረጋገጥ ይኖርባችኋል። ከ 10-15% በማይበልጥ ልዩነት ውስጥ የሚኖራቸው ክብደት ተቀባይነት ቢኖረውም በጣም የተጋነነ ልዩነት የሚኖረው ከሆነ ዶሮዎቹ # በቂ እንክብካቤ # በቂ የተመጣጠነ መኖ አላገኙም ወይም የተባላቹት እድሜ ትክክለኛ አደለም ማለት ነው። ለምሳሌ አንድ በጥሩ እንክብካቤ የተያዘች የ2 ወር ቦቫንስ ብራውን ለመግዛት ካሰባቹ ፤ በ 2 ወር =8 ሳምንት =60 ቀን ሊኖር የሚገባት የክብደት መጠን 685 gram - 750 gram ውስጥ ከሆነ በጣም አሪፍ ነው ፤ ነገር ግን የ 8 ሳምንት ተብላቹ ክብደታቸው ከ 490gram በታች ከሆነ  በርግጠኝነት የምነግራችሁ በእንክብካቤ አላደጉም ወይም የ 45 ቀን ( 6 ሳምንት ) ዶሮዎች ናቸው።ይህ ማለት ለ ሁለት ሳምንት የሚሆን የመኖና ተጓዳኝ ወጪዎች እንዲሁም እኛ ካሰብነው የምርት እቅድ በ 2 ሳምንት እንድንዘገይይ እንገደዳለን ማለት ነው። 🐓🐓 🐓🐓          

ከማንኛውም ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ለእርባታ ግዢ ከመፈፀማቹ በፌት ልብ ልትሉ የሚገባቹ እና ልትታለሉ የምትችሉበት ነገር ቢኖር በምትገዟቸው ዶሮዎች በእድሜያቸው የሚኖረው የክብደት መጠን እንደ ዝርያቸው የሚለያይ ቢሆንም በእድሜያቸው ሊኖራቸው የሚገባውን ክብደት ሠ ማሟላት መቻላቸውን ማረጋገጥ ይኖርባችኋል። ከ 10-15% በማይበልጥ ልዩነት ውስጥ የሚኖራቸው ክብደት ተቀባይነት ቢኖረውም በጣም የተጋነነ ልዩነት የሚኖረው ከሆነ ዶሮዎቹ # በቂ እንክብካቤ # በቂ የተመጣጠነ መኖ አላገኙም ወይም የተባላቹት እድሜ ትክክለኛ አደለም ማለት ነው። ለምሳሌ አንድ በጥሩ እንክብካቤ የተያዘች የ2 ወር ቦቫንስ ብራውን ለመግዛት ካሰባቹ ፤ በ 2 ወር =8 ሳምንት =60 ቀን ሊኖር የሚገባት የክብደት መጠን 685 gram - 750 gram ውስጥ ከሆነ በጣም አሪፍ ነው ፤ ነገር ግን የ 8 ሳምንት ተብላቹ ክብደታቸው ከ 490gram በታች ከሆነ  በርግጠኝነት የምነግራችሁ በእንክብካቤ አላደጉም ወይም የ 45 ቀን ( 6 ሳምንት ) ዶሮዎች ናቸው።ይህ ማለት ለ ሁለት ሳምንት የሚሆን የመኖና ተጓዳኝ ወጪዎች እንዲሁም እኛ ካሰብነው የምርት እቅድ በ 2 ሳምንት እንድንዘገይይ እንገደዳለን ማለት ነው። 🐓🐓የምንሰጣቸው አገልግሎቶች 🐓🐓           👇👇👇👇👇👇                                🤔ለህሊናችን እንጂ ለሆዳችን አንገዛ በቃ..🤔 🐓ስልጠና ና የማማከርና አገልግሎት እንሰጣለን 🐓የዶሮ እርባታ ጉብኝት አናደርጋለን 🐓የህክምና አገልግሎት እንሰጣለን አድራሻ:- (Addis Ababa) 09 39 77 06 77 /09 84 98 32 81....ዶ/ር ቸርነት ቡናሬ https://t.me/c/1968653562/1

ቢዝነስ ለመስራት ስናስብ ልብ ልንላቸዉ የሚገቡ ጉዳዮች ብዙ ሰዉ የራሱ ቢዝነስ እንዲኖረዉ ከዚያም አልፎ በቂ ሃብት አፍርቶ የራሱ ጌታ መሆን ይፈልጋል። ይህንን ህልም ለማሳካት ግን ሊከፈሉ የሚገቡ መስዋእትነቶች ስለሚኖሩ ለዚህ አቅዶና ተዘጋጅቶ ወደሃብት የሚደረገዉን ጉዞ መጀመር ውጤታማ የመሆን እድላችንን ያሰፋዋል። ስራዉ የሚጠይቀዉን መስዋትነት ለመክፈል ቀበቶም ሆነ መቀነትን ጠበቅ ማድረግ ያስፈልጋል። ለምሳሌ፡ ስራዉን ለማሳካት በቀን/በሳምንት ለረጅም ሰአታት መስራት ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ይሄኔ ከቤተሰብ/ልጆች ጋር የምናሳልፈዉ ጊዜ ሊያንስ ነዉ። ለዚህ ተዘጋጅተናል? ቤተሰቦቻችንስ በዚህ ሂደት ዉስጥ ምን ያህል ሊያግዙን ተዘጋጅተዋል? ምን ያህል ገንዝብ ነዉ ቢዝነሱ ላይ የምናፈሰዉ? አያድርገዉና ቢዝነሱ ባይሳካ ቤተሰቤን ማስተዳደር እችላለሁ? ደንበኛ ለመሳብ ቢዝነሱን ያለመታከት ማስተዋወቅ፣ የቢዝነስ ኔትወርክ መዘርጋት ያስፈልጋል። “አይ እኔ እንዲህ አይነት ነገር አይሆንልኝም፣ የሰዉ አይን እፈራለሁ!” ብለን ስራዉን ለሌላ ሰጥተን እንቀራለን ወይንስ ራሳችንን ቀይረን አዲስ ሰዉ እንሆናለን? ልንሸጥ የምንፈልገዉ ነገር ቢኖር ጊዜ ና ጥሪታችንን እንዳለ እዛ ላይ ከማፍሰሳችን አስቀድሞ በቂ ፈላጊ እንዳለዉ ማጥናት ያስፈልጋል። እኔ እና ሁለት እኛ ቢሮ ያሉ ጓደኞቼ ስለምንወደዉ ብቻ ሌሎች ሰዎችም ይወዱታል ፤ ገንዘባቸዉን ከፍለዉም ይገዙታል ማለት አይደለም። ኪሳራን እና አጉል ድካምን ለመቀነስ የገብያ ጥናት ጠቃሚ ነዉ፡፡ ከቤተሰብ እና ጓደኛ ዉጪ ያሉ ለመሸጥ የምናስበዉን እቃ ወይንም የምንሰጠዉን አገልግሎት ሊፈልጉ ይችላሉ ብለን የምናስባቸዉን ሰዎች ቀርበን መጠየቅ ተገቢ ነዉ፡፡ ሊሰራ ስለሚታሰበዉ ቢዝነስ ማጥናት፣ እቅድ ማዉጣት፣ ገንዘብ ማዘጋጀት፣ ወዘተ…. ያስፈልጋል።፡በስሜት ሌላ ሰዉ ሲያደርገዉ ስላየን ብቻ የቤተሰቦቻችንን ቤት በባንክ አስይዝን ንግድ ዉስጥ ልግባ ማለት አላስፈላጊ ስህተት ዉስጥ ሊከተን ይችላል፡፡ አሊያም ደግሞ የምናስበዉን ያህል ዉጤታማ ሳንሆን እንቀራለን፡፡ ሆኖም ስናቅድ እድሜያችን ይግፋ ማለት አይደለም፡፡ አንዴ ያቀድነዉ ለእድሜ ልክ ያገለግላል ማለትም አይደለም። ስለደንበኞቻችን፣ ስለተፎካካሪዎቻችን እና ስለቢዝነሱ ተጨማሪ መረጃ ሲኖረን እቅዳችንን እያስተካከልን እንሄዳለን። ሃሳብ ተግባር ላይ ካልዋለ ግን ከህልምነት አያልፍም፡፡ ብዙዎች በሃሳብ በመዋለል እና በወሬ ወርቃማ ጊዜያቸዉን ያባክናሉ፡፡ በስኬት ጎዳና ለመጓዝ ማሰብ፣ ማቀድ፣ መስራት! ከአላዋቂ ሳሚ ተጠንቀቁ! ልትሰራ ስለምታስበዉ ነገር ካንተ የተሻለ እዉቀት ወይም ልምድ ካለዉ ሰዉ ካልሆነ ምክር አትጠይቅ፡፡ አይሆንም ከባድ ነዉ ብለዉ ያስፈራሩሃል አሊያም በጭፍኑ ያዋጣል ብለዉ ያከስሩሃል፡፡ https://t.me/businessnote7 ልንሰራ በምናስበዉ የንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ሰዉ ፈልገን ከነሱ አቅም የፈቀደዉን ሁሉ መማር ጠቃሚ ነዉ፡፡ ይህ ማለት ግን የኮንስትራክሸን ስራ ላይ መሰማራት የሚፈልግ ሰዉ የግድ ደረጃ አንድ ኮንትራክተር እስኪያገኝ መጠበቅ አለበት ማለት አይደለም፡፡ በቅርቡ ከሚያገኘዉ (አዲስ ነገር ሊያስተምረዉ ከሚችለዉ) ጀምሮ በሂደት ከፍ እያለ መሄድ የተሻለ አማራጭ ነዉ፡፡ ብዙ ሰዉ ስራ መቀጠር የሚፈልገዉ ደሞዝ ለማግኘት ነው፡፡ በነጻም ሆነ በአነስተኛ ክፍያ ሰርታችሁ ለወደፊት የቢዝነስ ህልማችሁ ሊጠቅማችሁ የሚችል ልምድ፣ እዉቀት እና ኮኔክሽን (ጓደኛ ልበለዉ?) የምታገኙበት አጋጣሚ ስታገኙ ተጠቀሙበት፡፡ ለጊዜዉ መቶ ወይም ሺህ ብር በደሞዝ መልክ ልታጡ ብትችሉም ለሚሊዮን ብሮች የሚሆን ጠንካራ መሰረት ትጥላላችሁ፡፡ ከፈቀደ እና አጋጣሚዉን ካገኛችሁ እዉቀትና ችሎታችሁን ማሳደግ የምትችሉበት ስልጠና ብትካፈሉ፣ መጽሃፍ ብታነቡ ለቢዝነሱ የሚኖራችሁን ዝግጁነት ይሳድገዋል፡፡ የምትማሩት ግን ዲፕሎማ ወይንም ዲግሪ አለዉ ለመባል ወይም አንድ ጓደኛችሁ ስለተመዘገበ ለመመሳሰል እንዳይሆን! ያለ የሌለንን ገንዘብ እና አቅም ቢዝነሱ ላይ ከማፍሰሳችን በፊት በትንሹ መሞከር ይመከራል። ይህ አካሄድ የሚሰራዉን ጨምሮ፣ የተበላሸዉን አስተካክሎ ለመሄድ እድል ይሰጠናል፡፡ ብንወድቅም እንነሳለን። ጎረቤት የሚሰራዉን እንዳለ ለመድገም አትሞክር፡፡ ቪዲዮ ቤት ሲከፍቱ ቪዲዮ ቤት፣ ዲሽ ቤት ሲከፍቱ ዲሽ ቤት ብዙ ጊዜ አይሰራም፡፡ ሰዉ ምን ይፈልጋል? እኔስ ያንን ፍላጎት እንዴት ማሟላት እችላለሁ ብሎ ማሰብ አስፈላጊ ነዉ፡፡ በተቃራኒዉ ደግሞ ሰዎች ያንተን ቢዝነስ ሊኮርጁ እንደሚችሉ አዉቀህ በቀጣይነት ከሌሎች ተሽለህ መገኘት የምትችልበትን መንገድ ማዘጋጀት ይገባሃል፡፡ https://t.me/businessnote7 ጥሩ የገንዘብ አያያዝ ባህል አዳብር፡፡ ይሄ ባህል ቢዝነስህን ለመጀመር ገንዘብ እንድታጠራቅም ይረዳሃል፡፡ ቢዝነስህን ከጀመርክ በኋላ ደግሞ ከብክነት ይታደግሃል፡፡ ከወንድምህ ጋር እንኳ ብትሰራ በዘፈቀደ አትንቀሳቀስ፡፡ አንብበህ፣ ጠይቀህ፣ ወይንም ተምረህ ገንዘብህን በስርአት ጠብቅ፡፡ ጠንካራ የሂሳብ አያያዝ ሰርአት የሌለዉ የንግድ ስራ ወጪና ገቢዉን በተገቢዉ መንገድ ሊያውቅ አይችልም፡፡ ወጪና ገቢዉን በደንብ የማያዉቅ ቢዝነስ ደግሞ አይኑን ጨፍኖ በርካታ ጉድጓዶች ባሉበት ሜዳ ከሚጓዝ ሰዉ ብዙም አይለይም፡፡ የስራ ማስኬጃ ና የግል ወጪዎችን መለየት አንዱና ቀላሉ ርምጃ ነዉ፡፡ ስራዉን በተሳካ መንገድ ለማካሄድ ከሚያስፈልገዉ ዉጪ ያሉ ወጪዎችን መቀነስ ይገባል፡፡ የሚሽከረከር ወንበር፣ የሚያምር ላፕቶፕ፣ ቦሌ መሃል ያለ ቢሮ፣ ላያስፈልግ ይችላል፡፡ በመጨረሻም የገንዘብ አያያዝ ሰርአት ሲባል የግድ በኮምፒዉተር የታገዘ ማለት አይደለም፡፡ አስፈላጊዉን መረጃ እስከያዘ ድረስ የወረቀት መዝገብም የሚፈለገዉን አገልግሎት መስጠት ይችላል፡፡ https://t.me/businessnote7

የእንቁላል ጉዞ ሴት ዶሮ አንድ እንቁላል እጆት ላይ ከመስጠቷ/ከመጣሏ በፊት፤ የእንቁላሉን ምስረታ ሂደትን ለማወቅ ይፈልጉ? አንድ እንቁላል በተለያዩ የዶሮ የመራቢያ ክፍሎች በሚያደርገው ጉዞ አማካኝነት ይሠራል። እነርሱም፤ 👉ኦቫሪ 👉ኦቪደክት [ኢንፈንዲቡለም፤ ማግነም፤ እና ኢስትመስ] 👉ማህፀን 👉ክሎአካ ናቸው። ዶሮዎች አንድ የሚሰራ ኦቫሪ (ovary) ብቻ አላቸው። እሱም የግራው ኦቫሪ ሲሆን የተለያየ መጠን እና እድገት ላይ ያሉ ፎሊክሎችን (follicle) ይዟል። እያንዳንዱ የፎሊክሎች ((follicle)እድግት ሲጠናቀቅ፤ አስኳል ወይም ቪቴልየስ ይባላል። አስኳሉ ከኦቫሪ [ovary] ወደ ኦቪደክት [oviduct] በኢንፈድቡለም [Infundibulum] እርዳታ ጉዞውን ይጀምራል። የኦቪደክት [oviduct] የመጀመሪያው ክፍል ኢንፈንዲቡለም ሲባል፣ አስኳሉ ለ15 ደቂቃ ያህል የሚቆይበት ክፍል ነው። የወንድ ዘር ያለው እንቁላል [የዳበረ እንቁላል] የምናገኝበት ሚስጢር ለዚህ ነው። ማሳሰቢያ፦ ሴት ዶሮ ምንም አይነት ግንኙነት ከወንዱ ዶሮ ጋር ባታደርግም ወይም የወንድ ዶሮ በአቅራቢያ ባይገኝ፤ የወንዱ የዘር ፍሬ በሰቷ ዶሮ ኦቪደክት ውስጥ ለአራት ሳምንታት ያህል መቆየት እንደሚችል ጥናቶች ያስነብባሉ። የሚቀጥለው የኦቪደክት ክፍል ማግነም [Magnum] ሲሆን እንቁላሉ ለሦስት ሰዓታት ያህል በዚህ ይቆያል። የእንቁላሉ ነጭ ክፍል የሚመሠረተው በእዚሁ ነው። እንቁላሉ በማለፍ ወደ ኢስትመስ [Isthmus] ጉዞውን በመቀጠል ለአንድ ሰዓት ያህል በዚህ ክፍል ይቆያል። በቆይታውም በዙሪያው በሁለት ሽፋኖች [membranes] ይጠረዛል። ቀጥሎ የሚመጣው የ24 ሰዓት ጊዜ በማህፀን ቆይታ፤ ቅርፊቱ በዚህ ክፍል ውስጥ ይመሰረታል። የመጨረሻው የእንቁላሉ መዳረሻ ክሎአካ [cloaca] ሲባል፤ በአርጊኒን ቫሶቶሲን [Arginine Vasotocin] ሆርሞን አማካኝነት የማሕፀን መኮማተር በማነሳሳት ሚስኪኗ ዶሮ እንቁላል ለመጣል ትገደዳለች። እንግዲህ፤ ለምን ዶሮ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ትጥላለች ለምትሉ፦ አንድ እንቁላል ለመሰራታ የሚፈጀው ጊዜ ዶሮን በቀን ከአንድ እንቁላል በላይ እንዳታመርት ይገድባታል። ዶ/ር አሮን አለማየሁ

https://www.youtube.com/watch?v=pV1Ak-E-fFA መቄዶንያንን ቢንያም ቢመሰርተውም ሀላፊነቱ ግን የህዝብ ነው new challenge መቄዶንያንን tv subscribers https:
https://www.youtube.com/watch?v=pV1Ak-E-fFA መቄዶንያንን ቢንያም ቢመሰርተውም  ሀላፊነቱ ግን የህዝብ ነው  new  challenge መቄዶንያንን tv subscribers https://www.youtube.com/watch?v=ohJ-rGmjOO8 የ አንድ ሚሊዬን ቻሌንጅ ከ መቄዶንያ | Mekedonia Tv

👇👇ከባለሞያ አንፃር የተሰማኝን ለማካፈል ያክል 👇👇 እንቁላል ለተጠቃሚዎች በስምንት ብር መቅረቡ እጅግ የሚበረታታ ተግባር ነው፤ አቶ ፋሩቅ ጀማል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ይህን ሀሳብ ሁሉም ማህበረሰብ ይደግፈዋል ነገር ግን በጀርባው የተጋረጠውን ችግር ማጤን ያሰፈልጋል ። በስምንት ብር እንቁላል የሚያስረክብውን አርቢ ማህበረሰብ እና በኩንታል አራት ሺህ ብር መኖ የሚሸጠውን ማህበረሰብ አቀራርቦ ማነጋገር ያሰፈልጋል ። እንቁላል አምራች ማህበረሰብ የዶሮ መኖ በጥራትና በተመጣጣኝ ወጪ ዋጋ ከቀረበለት ከስምንት ብር በታችም ለሸጥ ይችላል ። እንቁላል እና መኖ አምራች ማህበረሰብ ማህበረሰብን አቀራርቦ ማነጋገር ካልተቻላ ሁለቱም ማህረሰቦች መጨረሻቸው ኪሳራ ነው ከዛም ማህበረሰቡ የእንቁላል ምርት አቅርቦት እስከማጣት ደረጃ ሊደርሰ ይችላል እስቲ ሀሳብ ስጡበት .......

ምክር ቢጤ ... . ... ደላሎችና ኦንላይን ነጋዴዎች ፌስቡክ ላይ የሚሸጡትን ያስተዋውቃሉ ... ፌስቡክ አካውንታቸውን እንደሱቃቸው የአካውንት ስማቸው ደግሞ ብራንድ ስማቸው ይሆናል ... . የሚገር
ምክር ቢጤ ... . ... ደላሎችና ኦንላይን ነጋዴዎች ፌስቡክ ላይ የሚሸጡትን ያስተዋውቃሉ ... ፌስቡክ አካውንታቸውን እንደሱቃቸው የአካውንት ስማቸው ደግሞ ብራንድ ስማቸው ይሆናል ... . የሚገርመው ግን በርካቶቹ አስታዋዋቂዎች ከህዝቡ ጋር ሲናቆሩ ቦተሊካ ሲፈተፍቱ በከረሙበት አካውንት መሸቀል ያምራቸዋል ... ገበያቸውን እይታቸውን በሚደግፉት ላይ ብቻ እያጠበቡት መሆኑን ማስተዋል ነበረባቸው ... . ሌላው ደሞ ለመያዝ የሚያስቸግረው ስማቸው ነው ... እገሌ አበሉ የእንትና ወዳጅ፣ ፉላኒት ኢብን ፉላን ዲኗን አፍቃሪ ከመሳሰሉት ጀምሮ ህፃን ልጅ በነካካው ኪቦርድ የተፃፉ የሚመስሉ ስሞችን ይዘው ነው ሽቀላ የሚመጡት ... . ... የፌስቡክ ስማቸው መፈለጊያ ('ፈ' ይጥበቅ) ብራንዳቸው ነው ... ብራንድ ስም ደሞ አፍ ላይ የቀለለ በቀላሉ የሚታወስ መሆን አለበት የነዚህ እንኳን ሊታወስ ሊያነቡት ይከብዳል ... የብራንድ ስም ሁለት ወይም ሶስት የድምፅ ፊደሎችን የያዘ ቢሆን ይመረጣል ... ቢቻል ደሞ የትኛውንም ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች በቀላሉ የሚይዙትና የተገደበ ከስተመር እስካላሰቡበት እምነትና ቦተሊካን ያላማከለ መሆን አለበት ... . ... እና ደላሎችና ነጋዴዎች አስቡበት ለማለት ኖ! . ... አንባቢ ሆይ ከላይ የፃፍኩት ሳይንስ አይደለም! ስለ ቢዝነስ ማስታወሻ የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ፡፡ የቢዝነስ መረጃዎች እና አነቃቂ ሃሳቦችን በቀላሉ ታገኛላችሁ፡፡ https://t.me/+TRYVuizgfJUp52kJ

ሺላጂት (Shilajit) ዶሮዎች እንቁላል እንዲጥሉ እና ጤንነታቸው እንዲጠበቅ!!! ይህ ሺላጂት Shilajit, ተለጣፊ ጥቁር ንጥረ ነገር በዋነኝነት በሂማሊያ ተራሮች ውስጥ ይገኛል። የተፈጠረው ለብዙ ምዕተ ዓመታት በቀስታ የእፅዋት መበስበስ መክንያት ነው። ከ3000 ዓመታት በላይ በAyurveda ጽሑፎች ውስጥ ተጠቅሷል። የሺላጂት ዋና አካል የሆነው (Fluvic Acid) ፉልቪክ አሲድ (antioxidant) አንቲኦክሲዳንት ነው። በቅርብ በተደረገ ጥናቶች ይህ (Fluvic Acid) ፉልቪክ አሲድ ለእንቁላል ጣይ እና ለስጋ ዶሮዎች በርካታ ጥቅሞችን ይዞ ተገኝተዋል። ከሚሰጣቸው ጥቅሞች በጥናት ከተረጋገጡት መካከል 1. የተሰጣቸው መኖ በተሻለ ሁኔታ በሰውነታቸው እንዲጠቀሙት ያደርጋል። 2. የእንቁላል መጠን ይጨምራል። 3. ዶሮዎች የሚያብረቀርቅ ላባ እንዲኖራቸው ያደርጋል። 4. የዶሮዎች አንጀትን ከጎጂ ተህዋሲያን ይከላከላል። 5. የዶሮዎች የመታመም እድላቸውን በእጅጉ ይቀንሳል። 6. የዶሮዎች ክብደትን ይጨምራል። ይህንን በርካታ ጥቅም ያለውን ንጥረ ነገር በርካሽ መገኘቱም በአለማችን የሚገኙ ዶሮ አርቢዎች ዘንድ ተፈላጊ እንዲሆን አድርጓታል። ሀገራችን ላይ ያለን ዶሮ አርቢዎችስ መቼ እንጠቀመው ይሆን????? ዶ/ር ሳላሀዲን አሊ

Dairy farming *Animal husbandry *Milk processing *Technology exchange 》Learn about animal production and development! https://t.me/+ckwmrjSK6282Yjdk

በዶሮ እርባታ እና በስጋ አቅርቦት ዘርፍ ላይ ተሰማርተዋል ? እንግዲያውስ አስደሳች ዜና ይዘንልዎ መጥተናል!! ከጥቅምት 15-17 ለ 12ተኛ ጊዜ በሚዘጋጀው አመታዊ የዶሮ እርባታ እና ስጋ አቅርቦት
በዶሮ እርባታ እና በስጋ አቅርቦት ዘርፍ ላይ ተሰማርተዋል ? እንግዲያውስ አስደሳች ዜና ይዘንልዎ መጥተናል!! ከጥቅምት 15-17 ለ 12ተኛ ጊዜ በሚዘጋጀው አመታዊ የዶሮ እርባታ እና ስጋ አቅርቦት አውደ ርዕይ እና ጉባኤ ላይ ይሳተፉ!! በዘርፉ የካበተ ልምድ ካላቸው ሙያተኞች ጋር ለመገናኘት እንዲሁም የሙያ መስኩን አንድ እርምጃ ከፍ ለማድረግ የሚያግዙን ጠቃሚ መረጃዎች ለመሸመት ልዩ አጋጣሚ ይሆንልዎታል!! በእንስሳት መኖ፣ በእንስሳት ጤና፣ በዶሮ እርባታ፣ በወተት፡ በስጋ እንዲሁም በንብ እና በአሳ ሃብት ልማት ላይ ያተኮሩ ከ17 ሀገራት የተወጣጡ ከ100 በላይ ዓለምዓቀፍ የቴክኖሎጂ እና ግብዓት አቅራቢዎች እንዲሁም ገናና የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች በአንድ ጣራ ስር ተሰብስብው ይጠብቁዎታል። ታዲያ እርሶስ በየትኛው ዘርፍ ሊሳተፉ አስበዋል? ከጥቅምት 15-17 ሚሊኒየም አዳራሸ እንዳይቅሩ!! በዚህ ትልቅ አውደ ርዕይ እና ጉባኤ ላይ ንግድና ምርቶን ለማስትዋወቅ https://bit.ly/applystandalec በመጠቀም ይመዝገቡ ለበለጠ መረጃ 092930864/63 ይደውሉ በድህረ ገፃችን www.ethiopoultryexpo.com/ www.africanlivestock.net/ አዘጋጅ - ፕራና ኢቨንትስ

በአይነቱ ለየት ያለ የ3ቀን የዘመናዊ ወተት ከብት እርባታ ስልጠና በምቹ ስፍራ ------------------------------------------------------------ ከጥቅምት 1-3 የስልጠ
በአይነቱ ለየት ያለ የ3ቀን የዘመናዊ ወተት ከብት እርባታ ስልጠና በምቹ ስፍራ ------------------------------------------------------------ ከጥቅምት 1-3 የስልጠና ቦታ፡ አዲስ አበባ ጉርድ ሾላ በኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ግቢ ውስጥ የስልጠና ዋጋ፡ 2500 ብር  ( የምዝገባ፣ የስልጠና፣ የሰርተፍኬት፣ የስልጠኛ ማኑዋል እና ውሃ) ለመመዝገብ ማስፈጠርያውን ይጫኑ፡https://forms.gle/zqZ8acwFbGyt8tUy6 ለተጨማሪ መረጃ ስልክ፡011304747/0116677008       0919074407/0919076607 ይደውሉ