ስለ ቢዝነስ ማስታወሻ
Open in Telegram
ስለ ቢዝነስ ማስታወሻ በነፃ ስለ business ግንዛቤ ለማግኘት ትክክለኛ ቦታ 👉https://t.me/businessIdea_7 የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ፡፡ የቢዝነስ መረጃዎች እና አነቃቂ ሃሳቦችን በቀላሉ ታገኛላችሁ፡፡ https://t.me/+KoGdFzHO8eA3YWE0
Show more341
Subscribers
No data24 hours
+37 days
+1630 days
Data loading in progress...
Similar Channels
Tags Cloud
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Incoming and Outgoing Mentions
---
---
---
---
---
---
Attracting Subscribers
October '24
October '24
+21
in 0 channels
September '24
+17
in 0 channels
Get PRO
August '24
+28
in 0 channels
Get PRO
July '24
+24
in 0 channels
Get PRO
June '24
+22
in 0 channels
Get PRO
May '24
+25
in 0 channels
Get PRO
April '24
+28
in 0 channels
Get PRO
March '24
+27
in 0 channels
Get PRO
February '24
+46
in 0 channels
Get PRO
January '24
+27
in 0 channels
Get PRO
December '23
+286
in 1 channels
| Date | Subscriber Growth | Mentions | Channels | |
| 14 October | +2 | |||
| 13 October | +2 | |||
| 12 October | 0 | |||
| 11 October | 0 | |||
| 10 October | +4 | |||
| 09 October | 0 | |||
| 08 October | +5 | |||
| 07 October | 0 | |||
| 06 October | 0 | |||
| 05 October | 0 | |||
| 04 October | +8 | |||
| 03 October | 0 | |||
| 02 October | 0 | |||
| 01 October | 0 |
Channel Posts
የቢዝነስ ቡዳ የበላቸው ብዙ አሉ ......
እንደማንኛውም ስራ ልክ እንደ ፖለቲካው ሁሉ በቢዝነስ ዓለምም ስህተት ትሰራለህ ። ስህተትም ባይሰሩም ብዙ የቢዝነስ ሰዎቻችን ከነ ምርጥ ሃሳቦቻቸው ጋር ቡዳ በልቶአቸው የተሰነካከሉ አሉ ።
ቡዳ የሚለውን ቃሉን ነው ለመግባቢያ የወሰድኩት እንጂ ምንድን ነው ብትሉኝ ላብራራላችሁ አልችልም ።
ብቻ ግን የቢዝነስ ቡዳ ከበላቸው ሰዎቻችን መሓል ገብረየስ ቤኛ ፣ ኤርሚያስ አመልጋ ፣ ብርሃነ መዋ እና ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ ፣ የሚገኙበት ይመስሉኛል ወይንም ናቸው ።
| 2 | ካፒታል ማርኬት ምንድን ነው ? የሚለውን ለመረዳት ቀለል ለማድረግ ስራ ፈጣሪዎች የስራ ሃሳባቸውን ለመተግበር የሚያስችላቸውን ካፒታል ለማሰባሰብ የሚረዳቸው መገበያያ ቦታ እንደማለት ነው።
ወይንም ቁጠባና እንቪስትመንትን ማገናኛ ገመድ ልንለውም እንችላለን ። ይህ አባባል ይበልጥ የሴኩሪቲ ማርኬት የሚለውን ይገልፀዋል ።
በሴኩሪቲ ገበያ ቁጠባን ወደ ኢኮኖሚው ለማስገባት እና የቁጠባን ገንዘብ ለማንቀሳቀስ ቻናልን በመፍጠር ረገድ ጉልህ ሚና አለው security market ። (mobilize and channelise saving)።
የኢንቨስተሮችን የእለት ገንዘብ ( Liquidity) በመፍታት የፋይናንስ ሲስተሙ ጠንካራ እንዲሆን ያደርጋል ።
እንደሚታወቀው በአንድ አገር አሪፍ የፋይናንስ ሲስተም እንዲኖር ከሚያስችሉት ውስጥ የውጭ ምንዛሬ ደንብ ( Regulations) ፣ የባንኮች አገልግሎት ፣ የውጭ ምንዛሬ ክምችት አስተዳደር ፣ የብድር ቁጥጥር፣ የፊሲካል እና ገንዘብ ፖሊሲ እንዲሁም የ የዕለት ገንዘብ አስተዳደር (liquidity management ወሳኞች ናቸው ።
አንዳንዶች ይህ የካፒታል ማርኬት የሚባለው ነገር ለድሃው ምን ይፈይዳል ? ሃብታምን ወይንም ያለውን ነው የሚጠቅመው የሚል ይዘት ያለው ሃሳቦችን ያንሸራሽራሉ ።
ለአገር ኢኮኖሚ የሚያመጣውን አዎንታዊ ሄደት ካለማጤን ጠቄሜታውን ካለመገንዘብ የመጣ ይሆን ወይንስ ከርዕዮተ ዓለም በመነሳት ይህ እንደሚባል አላውቅም ።
ይሁንና ካፒታል ማርኬት ከሌለ ታድያ ምን ይኑር የሚለው ጥያቄን ሊመልሱ ይገባል ። አሁን ዓለም ከካፒታል ማርኬት ወደ ዲጅታል ማርኬት እየተሻገረ ነው ያለው ።
ወደ ዲጅታል ማርኬት እንጓዝ ከሆነም እሰየው ። ይህ የዲጂታል ማርኬት ምክር ግን አሁን ባለው የሃሳብ ገበያ ላይ ለመጀመር ማሰብ በራሱ አድካሚ ነው የሚሆነው ። | 338 |
| 3 | ስህተትን የመቀበል ፀጋ!
"ሠው ስህተት ይሰራል...ስህተቱ ሠውን ይሰራዋል"
ሁሉም ሰው ስህተት ይሠራል፣ ነገር ግን ጥቂቶች ብቻ መሳሳታቸውን ያምናሉ.... ጥቂቶች ድፍረቱን አግኝተው፣ መሳሳታቸውን አምነው ከስህተቱ በመማር ያሻሻላሉ።
ብዙዎቻችን ነገሮች ሲበላሹ ሃላፊነቱን ለመውሰድ እናመነታለን፣ ሰበብ እንደረድራለን አሊያም በሌሎች እናማካኛለን።
ነገር ግን ስህቱቱ ከሚኖረው መዘዝ ይልቅ የምናገኘውን ትምህርት ማየት ብንችል እና ፍጹም አለመሆናችንን አምነን ስህተቱን መቀበል ከቻልን ያኔ ስህተቱ እኛን ይሰራናል።
ስህተትን መቀበል ደካማ ወይም ዝቅተኛ አያደርገንም ይልቁንስ ልናሳካው ያሰብነውን ጉዳይ በተሻለ መንገድ፣ በደመቀ ጥበብ እንደአዲስ እንድንሞክር ሁለተኛ እድል ይሰጠናል እንጂ።
#ጥበብ_እና_ማስተዋል_ለሰው_ልጆች_ሁሉ!
ሣሙኤል ተክለየሱስ | 313 |
| 4 | ሥራን የሚሠራን ሰው አትረብሹ!
ሀገራችን የኧንተርፕሪነር እጥረት አለባት።
የብዙ ሰው ሥራ በሂደት ላይ ያለ እና Work in Progress የሚባል ዓይነት ነው። ሙከራዎች ይበረታታሉ። ሙከራዎች እየተስተካከሉ ወደ ፍጽምና እስኪደርሱ መትጋት ያስፈልጋል። ሙከራዎች እንዲሳኩና ውጤታማ እንዲሆኑ መደገፍ ደግሞ የሁላችን ኃላፊነት ነው።
አንድ ሰው ስንት ጊዜ ይሞክር?
ቶማስ ኤዲሰን ምን አስተማረን? 1,000 ጊዜ ወይንስ 10,000 ጊዜ መሞከር፣ መሞከር፣ መሞከር! መሞከር ይበረታታል።
መሞከር፣ ጽናት፣ አለመድከም የትጉሃን ባህሪይ ነው።
የአንድ ሰው መደናቀፍ ለብዙ ሰዎች መውደቅ ምክንያት ይሆናልና ሰውን አታደናቅፉ! ደግፉ! አበረታቱ እንጂ አታዳክሙ።
ሠራተኞች በርቱ! ሞክሩ! ትጉ!
ቅኖች ደግሞ ሠራተኞችን ደግፉ! አበረታቱ! ከጥቃት ተከላከሉ!
መልካም ጊዜ! | 508 |
| 5 | እኔ በበኩሌ ልብስ የለበሱ አሻንጉሊቶች አስወልቆ መግዛት ሰልባጅ መግዛት ይመስለኛል ።
ሶስት ጓደኛሞች ለአንደኟዋ ጓደኛቸው ልብስ ለማግዛት ከ 22 ከጎላጎል ሞል ወደ ቦሌ 17 -17 በሚወስደው መንገድ ያሉትን ቡቲክ ቤት እያሰሱ ነበር ።
እየጠየቁ እያዩ እየለኩ ዋጋ እየተከራከሩ የተሻለ ደግሞ እናገኛለን ብለው ሲያስቡ የሚቀጥለው ቤት እየጠየቁ መጨረሻ አካባቢ ደረሱ ።
አሁን ሄደው ሄደው ደክሟቸዋል ። አንደኛዋ ባክሽ ላይ ያየነው ወይን ጠጁ ቶፕ ያምራል እሱን እንግዛ ተባብለው በመመለስ ቤቱን ቢፈልጉት አጡት ።
ቤቶቹ ተመሳሳይ ስለነበሩ ለማግኘት አልቻሉም ። ሁሉም እጃቸውን የዘረጉ አሻንጉሊት በራቸው ላይ ተደርድሯል ። መስታዎቱ የቤቱ እቃ አደራደር አንድ አይነት ነበሩ ። አንዳቸው ከአንዳቸው የሚለዩበት የጎላ ምልክት አልነበራቸውም ።
ስራን በልዩነት መስራት በጣም ጠቃሚ ነገር ነው ።
ሰው ጠይቆ ከወጣ በኋላ ሊመለስ ሲፈልገው ለምን ሱቅዎትን ያጣዋል ? ሌላ ጊዜ ቆይቶ ቢመጣማ ጨርሶ ሊያገኘው አይችልም። በዚህ ሁኔታ እንዴት ደንበኛ ያፈራሉ ?
ቢዝነስን unique features አድርጎ መስራት ያስፈልጋል ። ደንበኞችዎ እርስዎን ከሌላው በምን ይለይዎታል ?
ከእርስዎ ከተወዳዳሪዎችዎ ለይተው እንዴት ይምጡ ?
ለስራዎ ለራስዎ Value prepositions ወይ ልዪ እሴትን ያክሉበት ። | 437 |
| 6 | "ገዢ ብቻ ይደውል" ሌላ የለህም😁
መደብሬ ላይ ከገዢ እኩል/በላይ ለጠያቂ ክብር አለኝ። የትህትናዬን ጥግ የማሳየው ለጠያቂ ነው። ገዢማ አይቶ ወስኖና አምኖበት አንደኛውኑ ሊገዛ መጥቷል። ጠያቂ ግን ለማወቅ አስቦ ነው የሚመጣው። ጎበዝ ነጋዴ በቂ መረጃ በመስጠትና ከቻለ ደግሞ ወደ ገዢ እርከን ከፍ በማድረግ ሀሳብ ያስለውጣል።
ብዙዎች የመጣ ሰው ሁሉ እንዲገዛቸው በመፈለግ ጠያቂዎችን ያንጓጥጣሉ፣ ፊት ይነሳሉ። በቂ መረጃ አይሰጡም። አለፍ ሲልም ያመነጫጭቃሉ። ይህ ችግር ከመንግስት መስሪያ ቤቶች አልፎ በግል ድርጅቶችም ይስተዋላል። እንዴት ሰው ገበያው ላይ ይቀልዳል🤔
ይህ ፈፅሞ አግባብ ነው ብዬ አላምንም።
ሰዎች ስለ ምርቶቻችን ወይም አገልግሎታቸው ለማወቅ ሲፈልጉ የምንይዝበት አግባብ በደንብ መታረም አለበት።
ጠያቂ ስለ ምርታችን/አገልግሎታችን ማወቅ ሲፈልግ በትዕግስት እስኪገባው ድረስ ማስረዳት፣ የተሳሳቱ አመለካከቶች ካሉት ለመፋቅ መሞከር፣ ምርቱ ወይም አገልግሎቱ ነፃ ሙከራ ካለው ማስሞከር አስፈላጊ ነው።
እስከማስታውሰው ቆሎዬን ለመጠየቅ ለሚመጡ ሰዎች ፊት ለፊታቸው ከፍቼ የማቅመስ ልምድ አለኝ። በጣም ይደሰታሉ። አብዛኛው ኧረ በፍፁም አትክፈት ይላል። የከፈትኩለት ሩብ ቆሎ ይሆናል። ግለሰቡ ቋሚ ደንበኛዬ ከሆነ ግን የዚህን ብዙ እጥፍ እየሸጥኩለት አተርፍበታለሁ።
በዚህ ረገድ ቻይናዎች የሚስተካከላቸው ያለ አይመስለኝም። Alibaba ላይ ገብተህ የምትፈልገውን ምርት/ማሽን መግዛት ብትፈልግ እስከጥግ መረጃ ይሰጡሀል። ለመመለስ አይሰለቹም። ባልጠበከው መልኩ Advance ሀሳቦችን ይሰጡሀል። ከነሱ ጋር ተያያዥ ምርት ያልሆነና ፍላጎቱ ካለህ እስከቻሉት ለማገናኘት ጥረት የደርጋሉ። አንተማ አትገዛም፣ ዝም ብለህ ልታለፋኝ ነው አይሉም።
ከ ዜሮ ወለል ተነስተው እስክትግባቡ ያስረዳሉ። የፅሁፍ፣ የምስልና የቪድዬ አስረጅዎችን ይሰጡሀል። ስትጠፋ ለምን ጠፋህ? ምን ግልፅ ያልሆነ ነገር አለ? ሀሳብና አስተያየት ስጠን? የመሳሰሉ መልዕክቶችን እያከታተሉ ይሰዳሉ።
Let me know if you have any questions.
if any question pls contact with me at any time.
feel free to share your thoughts with me.
እያሉ ልብህን ያባቡታል😁
እኛ ሀገር ግን በአካል የሚነግደው ቀርቶ በ online የሚነግደው ሰውዬ/ሴትዮ "ገዢ ከሆንክ ብቻ ደውል" ብሎ ማስታወቂያውን ይዘጋል። አንዳንዱ ነጋዴ ከቤትህ ስትወጣ ከፈጣሪ ተመርተህ እሱ ጋር ልትገዛ የወጣህ ይመስለዋል😁
አሰብኩና አንድ አባባል አመጣሁ
"የዛሬ ጠያቂ የነገ ገዢ ነው" ተንከባከበው! ከተመቸሀው ይገዛሀል ወይም ለሌላ ለሚገዛ ማስታወቂያ ይሆንሀል! ካልሆነ ግን ስትራብ ይገባሀል!
➦የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ፡፡ የቢዝነስ መረጃዎች እና አነቃቂ ሃሳቦችን በቀላሉ ታገኛላችሁ፡፡ https://t.me/+KoGdFzHO8eA3YWE0 | 1 113 |
| 7 | "ስኬታማ ሰዎች እንዴት ያስባሉ?"
1. በትልቁ ማሰብ፡ ስኬት የሚለካው በጅማሬው ሳይሆን ፀንተን በተጓዝንበት ርቀት ልክ ነው። በትልቅ ማሰብ፣ ነገርግን በትንሹ መጀመር፣ አናም ደግሞ ውጥኑ እስኪሳካ መፅናት የስኬታማነት ቁልፍ ነው።
2. እንቅፋት ሳይሆን እድሎች፡ ተግዳሮቶችን እንደ እንቅፋት ሳይሆን እንደ አጋጣሚዎች መመልከት መቻል፤ የነቃ አስተሳሰብን ካጎለበትን ተግዳሮቶችን (Challenges) እንደችግር ሳይሆን መፍትሄዎችን በማፍለቅ የጋራ ጥቅምን (Mutual Benefits) መፍጥር የምንችልበትን አጋጣሚ ይፈጥርልናል።
3. እራስ ላይ ኢንቨስት ማድረግ፡ ቀጣይነት ባለው መልኩ በእውቀት እና ክህሎት እራስን ማነፅ፤ ለስኬታማነት አስተዋፅዖ የሚያደርጉ ዕውቀትና ክህሎቶችን እራሳችን ላይ ኢንቨስት ማድረግ ከቻልን ሁሌም በመሻሻል ውስጥ እንሆናለን።
4. ከምቾት ቀጠና መውጣት፡ የምንፈልገውን ለማግኘት የማንፈልገውን መስራት የግድ ነው፤ በአደባባይ ለመሸለም በጓዳ መልፋት አይቀሬ ነው።
5. አሁን መጀመር፡ ጊዜ በጣም ውድ የሆነው ሀብት ነው። ያሰብነውን ለመጀመር ዛሬ ከነገ በእጅጉ የተሻለ ነው እና ትኩረታችን የነገውን ስኬት በዛሬ መጀመር ውስጥ እናድርገው።
#ጥበብ_እና_ማስተዋል_ለሰው_ልጆች_ሁሉ!
ሣሙኤል ተክለየሱስ
(የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ እና የቢዝነስ አማካሪ)
====================
©️Sammy 𝐊. Tekle™ | 347 |
| 8 | በየቀኑ ጠንክሮ ሰርቶ የዕለት ገቢ ማግኘት (Actively) ወይንስ ስማርት ሆኖ ኢንቨስት አድርጎ በኋላ ላይ (passively ) የተሻለ ገቢ ማግኘት ?
The parable of the pipeline story የሚል መፅሓፍ ካነበብኩት ቆየሁ ።
በዛ መፅሓፍ ላይ ከተጠቀሱት ሁለት ሰዎች ገፀባህርያት ማለትም ቀኑን ሙሉ ታታሪ ሆኖ ውሃ በጀዲካን ለመንደሩ ሰዎች በመቅዳት ስራ ስለሚተዳደር ጠንካራው ሰራተኛ ብሩኖ ስለሚባለው እንዲሁም በተመሳሳይ ውሃ በመቅዳት ስራ ላይ የተሰማራው አባመላ ወይንም ስራ ፈጣሪው ፓብሎ ስለሚባሉ ሰዎች ታሪክ እጅግ አጭሩን ሃሳቡን ልነገራችሁ ወደድኩ ።
የመፅሓፉን ርዕስ ወደ አማርኛ ስንመልሰው " የ ቧንቧው መስመር ታሪክ ልንለው እንችላለን ። ፀሃፊው ደግሞ በርክ ሄጅስ ይባላል ።
በመፅሓፉ ውስጥ ብሩኖ በጠዋት እየተነሳ ለመንደሩ ሰዎች በ ውሃ በመያዣ ጀዲካን እየተሸከመ የሚያመጣ ሰው ነው ። ፖብሎ ደግሞ ከብሩኖ ጋር በተመሰሳሳይ እየሰራ ቢሆንም በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ ገቢውንም መጨመር እንደማይችል ገብቶት አስተማማኝ ለማድረግ በማሰብ በረጅም ጊዜ ቧንቧ ስለመዘርጋት የሚያስብ ሰው ሆነ ። ኢንተርፕርነርነትን !!
ሃሳቡን ለቡርኖ ቢያማክርም ቡርኖ በእለት የሚያገኘው ገንዘብ በቂዬ ነው ቧንቧ ስዘረጋ ስውል እዚህ የማገኘው ገቢ ይቀንስብኛል ብሎ ስላመነ ሊቀበለው አልቻለም ።
ፓብሎ ግን በከፊል በጀዲካን እየቀዳ ከፊል ጊዜውን ጉልበቱን እና ገንዘቡን ቧንቧ መዘርጋቱ ላይ አዋለው ።
ብሩኖ በተቃራኒው በየዕለቱ የሚያገኘውን ገንዘብ መዝናናት መብላት መጠጣት ላይ ያውለው ነበር ።
ከአመታት በኋላ የቧንቧው ስራ ተጠናቀቀና ለመንደሩ ሰዎች አስተማማኝ የውሃ አቅርቦትን ማግኘት ስለቻሉ ቋታቸው በቀላሉ ይሞላ ነበር ። ፓብሎም የእርሱ መኖር ሳያስፈልግ ያልተቋረጠ ውሃ ሃያ አራት ሰዓትን ማቅረብ ቻለ ።
አሁን ፓብሎ ለገንዘብ አይሰራም ገንዘብ ግን ለእርሱ እንዲሰራ አድርጓል ።
እኛስ ከወዴትኛው ነን በየቀኑ ጀዲካን ከሚሸከመው አስተሳሰብ ወይንስ ቧንቧን መዘርጋትን ከሚያስበው ?
መልካም ሰኞ ይሁን ።
አገራችንን ሰላም ያድርግልን ። | 408 |
| 9 | የባንክ ሰራተኞች ተደላድለው የስራ ዋስትና ምቾት ውስጥ እንዳሉ ሆነው ይሰማቸው ይሆን ? ።
የሚከተለው ፅሁፍ በዋናነት እነርሱን ይመልከት እንጂ ሌሎቻችንም ነው ። የስራ አጥነት ቁጥር እየተቀረፈ ሳይሆን እየተወሳሰበ ቁጥሩም እየጨመረ እንደሚሄድ ብዙ ማሳያዎችን ማንሳት ይቻላል ።
እስቲ ባንኮችን እንያቸው ።
እንደ ኤውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 ዓ.ም በኢትዮጵያ ያሉት የባንክ ቅርንጫፍ ቁጥር 8250 ነበር ።
የ 2023 ሪፖርትን ስላላገኘሁት እንጂ በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መመሰረት ባንኮች ያላቸውን የቅርንጫፍ ቁጥሮች በየዓመቱ በ25 ይሁን በ30 በመቶ ማሳደግ እንዳለባቸው ስለሚያስገድድ ቁጥሩ ከተጠቀሰውም በላይ ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል ።
የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢ ያሉትም በትክክል ስራ ላይ ስለመሆናቸው እርግጠኛ በመሆን መግለፁ ካልቸገረ በቀር ቅርንጫፎቹ የሰው ኃይል ቅጥር የሚያስፈልጋቸው ናቸው ወይንም ነበሩ ።
አንድ የባንክ ቅርንጫፍ ለመክፈት ከ 7.5 ሚሊየን ብር እስከ 16 ሚሊየን ብር እንደ የደረጃው በጀት ይፈልጋል ።
ይህንን ወጪ ሸፍነው የባንክን ቢዝነስ ለማስቀጠል ለባንኮች ፈታኝ መሆኑ ደግሞ አይቀሬ ነው ።ለዚህም የ2022/2023 በጀት ዓመት የባንኮችን operating cost ሪፖርት በማየት መገመት ይቻላል ። በያዝነውም በጀት ዓመትም አዲስ ቅርንጫፍ እየከፈቱ ያሉት አዳዲሶቹ እንጂ ነባሮቹ እየተቸገሩበት ያለ መሆኑን እየተሰማ ነው ።
የ Unitary bank system ን የሚከለክለው ብሔራዊ ባንክ የ branch banking ፖሊሲው አንዱ ምክንያት ባንኮች የስራ አጥን ቁጥር እንዲቀንሱ ከቴክኖሎጂ ይልቅ የሰው ኃይልን እንዲጠቀሙ ማድረግን ታሳቢ አድርጎ ይመስላል ወይንም ነው ። ሌላኛው የፋይናንስ አካታችነትን ወይንም ተደራሽነትን ለመጨመርም የሚል ነው ። እንደ እድል ሆኖ በአንድ ህንፃ ላይ አምስት እና ስድስት ባንኮች ከመኖራቸውም በላይ በአንድ አካባቢ በጥቂት ርቀት ውስጥ የአንድ ባንክ ቅርንጫፎች መብዛት ብቻ ሆነ እንጂ ።
ይህ ግን ቴክኖሎጂ በተሻለ ወጪ፣ ጊዜና ጥራት እየተካው መሄዱ አይቀርም ።
ዛሬ ባንኮች ውስጥ የሚቀመጠው የሰው ኃይል ቁጥር እየቀነሰ ስለመሆኑ ብዙ መስኮቶች ክፍት ሆነው በሁለት እና ሶስት ሰው ብቻ የሚሰሩ Activities መሆናቸውን እያየን ነው ።
ቨርቹዋል ባንኪንግ የጀመሩ ባንኮችን በተጨማሪነትም መጥቀስ ይቻላል ። ሞባይል ባንኪንግ ጨምሮ እየተተገበሩ ያሉት የ Fin-tech ሲስተምስ የባንክ አገልግሎትን እያቀላጠፉት ይገኛሉ ። በዚህ ምክንያት ባንኮች ተጨማሪ የሰው ኃይል ሊቀጥሩ ይቅርና ያለውንም ይዘው መጓዝ አያስፈልጋቸውም ።
በቅርብ ጊዜ ካስተዋልናቸው ነገሮች አንዱ የATM ማሽን አስፈላጊነት እየቀነሰ መሆኑን ልብ ይሏል ። ሞባይል ባንኪንግ እየተካው ስለሆነ ።
እየመጣ ያለው የ AI ቴክኖሎጂ እድገት ደግሞ ብዙውን ሰው ይሰራው የነበረውን ስራ በተሻለ ቅልጥፍና እና ፍጥነት የሚሰራው መሆኑ እየታየ ነው ። ትንሽ የሚባለውን ሪፖርት ማዘጋጀትን ጨምሮ ሰፊ የሆነው ስራ ሁሉ ይሰራዋል ።
ባንክ ውስጥ እየሰራችሁ ያላችሁ ሰራተኞች በሚቀጥሉት ጥቂት አመታት ውስጥ ኢንደስትሪው የሚፈልገው የሰው ኃይል ቁጥር በሁኔታዎች አስገዳጅነት ትርጉም ባለው መልኩ መቀነሱ አይቀርም ። እንደ ሃገር ይህንን ተገንዝቦ ከወዲሁ strategy እየተዘጋጀ ስለመሆኑ ደግሞ እርግጠኛ መሆን አይቻልም ።
እናስ ?
እናማ ራስን ማዳን ራስን ማዘጋጀት የግል ስልታዊ እቅድን ማሰብ ያስፈልጋል ። ልክ ሁኔታዎች ሲደርሱ ከመጋፈጥ ከመደናገጥ አስቀድሞ ማቀድ ። | 527 |
| 10 | ብራንድ ማለት መለያ ነው - በቃ!
ብራንድ ማለት የጥራት መለያ ማለት የሚመስላቸው አሉ። ግን ብራንድ ማለት እንደዚያ አይደለም። ጥራት ያላቸው ብራንዶች አሉ። ታዋቂና ዝነኛ ብራንዶችም አሉ።
ብራንድ ሁሉ ታዋቂ አይደለም። ታዋቂ የሆኑ ብራንዶች ግን አሉ።
ከሰውም፣ ከምርትም፣ ከቦታም ታዋቂ የሆኑ ብራንዶች አሉ።
ለብራንድ ታዋቂ መሆን አንዱ መንገድ ቀዳሚነት ነው።
ለታሸገ ውሃ "ሃይላንድ" ፣ ለዱቄት ሳሙና "ኦሞ" ፣ ለማራቶን ሩጫ "አበበ ቢቂላ" ፣ ለበረኛ "ጊላ" ፣ ለእንግሊዝኛ ዜና አንባቢ "ልዑልሰገድ ኩምሳ" ፣ ለልጆች አጫዋች "አባባ ተስፋዬ" ፣ ለገጣሚ "ጸጋዬ ገብረ መድህን" ፣ ለአፍሪካ አባት "አጼ ኃይለ ሥላሴ" ፣ ለ ጨረቃ ረጋጭ "ኒል አርምስትሮንግ" ፣ ለ ጠፈርተኛ "ዩሪ ጋጋሪ" ፣ ... በቀዳሚነታቸው ታዋቂ የሆኑ ናቸው።
ለታዋቂ ብራንድነት ግን መንገዱ ቀዳሚነት ብቻ አይደለም። ሌሎችም መንገዶች አሉ።
ታድያ ለቀዳሚነት ያለህበት ዘርፍ ከተያዘብህ ግን ሌላ ንዑስ ዘርፍ መፈለግና አዲስ ከፍቶ ቀዳሚ መሆን ሌላው መንገድ ነው።
ለምሳሌ በሴት ጠፈርተኝነት ታዋቂዋ "ቫሌንቲና ቴሬሽኮቫ" ናት። ከዩሪ ጋጋሪ ቀጥሎ የመጡት ሌሎች ጠፈረተኞች ዝና ሳይናኝና ስማቸው ሳይታወቅ የቫሌንቲና መታወቅ አዲስ በሆነው የሴቶች ዘርፍ መምጣቷ ነው።
በሀገራችን በቢራ ዘርፍ ቀዳሚው ማን ነው? በአልኮል ነጻ ቢራ ዘርፍ ግን "ሐረር ሶፊ" መሆኑ የማያጠራጥር ነው።
ለቦታም፣ ለሰውም፣ ለኩባንያም፣ ለምርትም ብራንድ አለው። ብራንድ ማለት ስም ብቻ አይደለም። ብራንድ ማለት ምልክት(ሎጎ) ብቻ አይደለም። ስምና ሎጎ ግን አንድን ቦታ ይሁን ኩባንያ፣ ሰው ይሁን ምርት ከሌላው በቀላሉ ለመለየት የሚያስችሉ የብራንድ አካላት ናቸው።
የአዲስ አበባ የብራንድ መገለጫ ምንድን ነው?
ስለቦታ ብራንዲንግ ሌላ ጊዜ እናወጋለን።
እስኪ ለሚከተሉት ስሞች የብራንድ መገለጫ ይሆናሉ የምትሉትን ጥቀሱ።
ሀ) ሀገራት
፩) ቻይና
፪) ሕንድ
፫) ብራዚል
፬) ኢትዮጵያ
፭) አሜሪካ
፮) ታይላንድ
፯) ስዊዘርላንድ
ለ) ከተሞች
፩) ጆሃንስበርግ
፪) ዱባይ
፫) አዲስ አበባ
፬) ጎንደር
፭) ሐዋሳ
፮) ድሬዳዋ
፯) ወላይታ ሶዶ
ሐ) ሰዎች
፩) Fitsum Atnafwork Kidanemariam
፪) Eyob Mihreteab Amlesom
፫) Fidel Gebremedhin
፬) Abayneh Tegegne
፭) Yordanos Goushe
፮) Kefe Hailu
፯) Bejai Nerash Naiker
"ብራንድ ማለት አንተ በሌለህበት ሰዎች ስላንተ 'እንዲህ ነው' ብለው የሚናገሩት ነው።"
~ ጄፍ ቤዞስ | 447 |
| 11 | የጠራ የቢዝነስ ሃሳብ እንዲኖረኝ ያደረገኝን አሰራርን እንዴት ነበር ያውኩት ? ትዝ ይስለኝን ለመፃፍ ምክክር እስቲ ..
መጀመሪያ የምወደው (passionate ) የምሆንበት ነገር ምንድን ነው ብዬ ያሰብኩበት ይመስለኛል ። ከዚያም በመረጥኩት ስራ ላይ ያለኝን እውቀት ማዳበር ስለነበረብኝ ያንን በከፊል አደርጌ ቀሪውን እየሰራሁ በመውደቅ በመነሳት ልማር አቀድኩኝ ።
ከዕለታት አንድ ቀን ደግሞ business model canvas (BMC ) ወይንም business model Generation የሚል ምርጥ ዕውቀት ያለበትን ዘዴ ጋር በድንገት ተዋወኩኝ ።
ይህ የ አንድ ገፅ ቢዝነስ ፕላን አዘገጃጀት የሚያስረዳውን እውቀት ከስር መሰረቱ ለማወቅ የሚያስችለኝን በቂ ሊባል የሚችል ኦን ላይን ኮርስ ወሰድኩ ።
እጅግ በጣም ሲያጥር ዘጠኙ ቤቶች የቢዝነስ ፕላን ይህን ይመስላል ።
√ ደንበኛን መለየት የሚያስችል ቴክኒክ ወይንም customer segmentation አንደኛው ቤት ነው ።
√ ሁለተኛው ክፍል ሰለ ልዮ እሴት ወይ value
proposition ያለበት ምርት እና አገልግሎት ዲዛይን
ስለማድረግ የሚያወራው ክፍል ነው ። problem እና
satisfaction መለየት ምሰሶዎቹ ናቸው ።
√ ከደንበኞች ጋር መገናኛ መስመር መዘርጋትን ወይንም
channels ሶስተኛው ነው ። ደንበኞችዎትን እንዴት
ያገኝዋችዋል ? የሚለውን መመለስ ቀላል ነገር አይደለም ።
√ የደንበኞች ግንኙነትን ማጠንከርን ወይንም customer
relationship አራተኛው ነበር ።
√ አምስተኛ የገቢ ማግኛ መስመር /Revenue streams
መለየትና ማወቅ ነው ። ይህ ቀላል ይመስላችሁ ይሆናል
ነገር ግን እንደሚታሰበው አይደለም ። በትክክል
ስለምትሸጡት ነገር ማወቅ. ይጠይቃል ። ሁላችን
በምናውቀው እንዱን በምሳሌ እንውሰድ ። Apple
የሚሸጠው ስልክ ብቻ የሚመስለን ብዙ ነው ። ነገር ግን
ምቾት፣ ሴኩሪቲ status ጨምሮ ፕሮፌሽናሊዝምን
ጭምር ብዙ ነገሮችንም ነው ።
√ ስድስተኛው ቢዝነሳችን ላይ የምናውለው ቁልፍ ሃብቶች
ምን ምን እንደሆኑ ለይቶ ማወቅን ወይንም key
resources የሚመለከት ነው ።
√ ሰባተኛው ቤት ቢዝነሳችንን ስንጀምር ምን ምን ቁልፍ
ተግባራትን መስራት እንደሚጠበቅብን በየቅደም
ተከተላቸው ዘርዝሮ በመፃፍ ማወቅ እና መተገበር ነው ።
ይህ በእንግሊዝኛው Key Activities ይባላል ። ይህንን
ፅፈን አቅደን በየደረጃው ካልፈፀምነው የምንሰራውን እና
ያልሰራነውን እንዴት ልናውቅ እንችላለን ?
√ ስምንተኛው ቁልፍ የሆኑ አጋሮችን መለየት ወይንም
Key partnerships ማወቅ ነው ። ለስኬታችን አብረን
የምንሰራውን አጋሮቻችን ለይቶ ማወቅ አብሮ
ለመስራትም ማቀድ እና መተግበር ግድ ይላል ።
√ ዘጠነኛው የወጪ መዋቅሮችን ማወቅ / Cost
structure እና ለዚህም ስልታዊ እቅድን አቅዶ በዝርዝር
መፈፀም ነው ። እነዚህ የሚታወቁ ዘጠኝ ብሎኮች
በዓለም አቀፍ ደረጃ ዝነኛ የአንድ ገፅ ፕላን መጠቀሚያ
ናቸው ። ጎግሉት ።
ቀጣዩ የሚቀረኝ ደግሞ የቢዝነስ ሃሳቤን ገምግሜ በ minimum viable product (MVP) የሙከራ ስርጭት ማስጀመር ይሆናል ማለት ነው ።
በመጨረሻም የስርጭት ሙከራዬ ሲሳካ invincible company ለመፍጠር ሂደቱን አቀጥላለሁ ።
ይህ ሁሉ ስራ የሚሰራው wheel and steering በሚባለው ዘዴም ጭምር ነው ። እያዩ እያረሙ እያስተካከሉ መጓዝ በሚለው ። የሮኬት ሞዴሉ ለጀማሪ ቢዝነስ አያዋጣም ።
ባብዛሁ አፉ በሉኝ ። ቅዳሜ አይደል መልካሙን ሁሉ ተመኘሁ ። | 404 |
| 12 | አምስት ፐርሰንት ብቻ ስኬታማ ይሆናሉ !
ምን ስላደረጉ ነው የተሳካላቸው ?
ዘጠና አምስት በመቶዎቹ ደግሞ አልተሳካላቸውም !
ምን ስላደረጉ ወይንም ስላላደረጉ ነው ያልተሳካላቸው ?
የየትኞቹን መስማት ትሻላችሁ ?
የሌላውን አላውቅም ።እኔ ግን ዘጠና አምስቱ ፐርሰንት ውስጥ ስላለሁ ከራሴ ስኬት አልባነት ብማር እመርጣለሁ ።
እኔ ቢዝነስ ስራ ስጀምር የጠራ ሃሳብ አልነበረኝም ። የስራ ሃሳቤንም አልገመገምኩትም ። clear thought and Idea evaluation አላደረኩም .አንድ በሉ ።
እኔ ጥሩ ቲም አልገነባሁም ። ታለንትድ ከሆኑት ጋር ለመስራት ሞክሬ ነበር ። እነርሱ ግን የተሻለ ሲያገኙ ሊታገሱኝ እና አብረን ፍሬውን እስክናይ ሊቆዩ የሚችሉ አልነበሩም ። ትልቅ ቲም መገንባት እና ታለንትድ ቲም መገንባት ልዩነቱን ያስተዋልኩት ከውድቀቴ ነበር ። ሁለት አላችሁ
እኔ ጥሩ የስራ አጋር አልመረጥኩም ነበር ።ክህሎትን compromize የሚያደርጉ አልነበሩም ። ይህ ሶስተኛዬ ነው ።
እኔ ስለ ካሽ ፍሎው ምንነት ምንም አላውቅም ነበር ። ገንዘብ እንዳገኘሁ ስራ ላይ አወጣለሁ ። መቼ እና በስንት መጠን መመለስ አለበት የሚባለውን ጥቅምና ጉዳት አላውቅም ነበር ። ይህ አራተኛ መሆኑም አይደል ?
እነዚህን እነዚህ የመሳሰሉት እኔጋ እንዳልነበሩ አስተዋልኩ። ከዚያም አምስቱ ፐርሰንቶች ጋ ሄድኩ እዚያ ግን ነበሩ ። ልብ አልኳቸው ።
አሁን አነፃፀርኩ እናም ስራዬን በአዲሰ መንፈስ ልጀምር ነው ።
አሁንም በጉዞዬ እማራለሁ ። ቢዝነስ እንደዛ ነው ። ትሰራለህ ትወድቃለህ ትነሳለህ ትጓዛለህ ትከስራለህ ታተርፋለህ ትማራለህ ..... ወይንስ
ስለ ጡረታ ማሰብ ይሻል ይሆን ? | 1 007 |
| 13 | እርጥብ የብዙሓን ምሳ !
ኮተቤ ላም በረት ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ ላይ ከጓደኞቼ ጋር ሆኜ ቆሜያለሁ ።
ሶስት ከሳ ከሳ ያሉ ወጣቶች ቀረቡን ። በከሲታ ሰውነታቸው ላይ ልጥፍ ያለች ሸሚዝ እና ቀጭን ከረባት አንጥልጥለዋል ።
የ እንትን ባንክ ጊዚያዊ ሰራተኞች ነን ። ቋሚ እንድትደረጉ ከፈለጋችሁ ባስከፈታችሁት ቡክ ብዛት ነው ስለተባልን እባካችሁ ተባበሩን አሉን ።
ብዙ የባንክ ቡክ በየባንኩ መክፈት ለክፉም ለደጉም ጥሩ አይደለም ። ቤታቸው ሲፈተሽ ይህን ያህል ቡክ በእጃቸው ተገኘ እየተባለ ብዙ ሰው ሲወነጀል አልሰማችሁም እንዴ አልናቸው ።
በመከፋት ስሜት ሆነው አልፈውን ሄዱና አንዲት መንገድ ዳር ካለች እርጥብ የሚባል ምግብ መሸጫ ጋ ቆመው መመካከር ጀመሩ ።
እርጥብ የሚባለው ከድንች ከሚጥሚጣ (በርበሬ) የሚሰራ በዳቦ ወይንም ከዳቦ ጋር የሚቀርብ የወቅቱ ዝነኛ ምግብ ነው ። በተለይ ዩኒቨርስቲ እና ሃይ ስኩል አካባቢ ወጣቶች ይወዱታል ። እንደ ቺፕስ ሆኖ ረጥቦ የሚሰራ ነው ። non -cafe ለሆኑ ወጣት ተማሪዎች በዋጋውም በጣዕሙም ተመራጭ ነው ።
በአማካኝ ስልሳ ብር ሲሸጥ እንቁላል እና ሽንኩርት ከገባበት ደግሞ ስፔሻል ተብሎ አንዳንድ ቦታ መቶ ብር አካባቢ ይሸጣል ።
በቀን ሙያተኞች እና የዕለት ገቢ ባላቸው ( በነገራችን ላይ እነዚህ የከተማችን መካከለኛ ገቢ ያላቸው የሚባሉ ናቸው ) የሚወሰድ ምግብ ነው ። ሆድ ያዝ ያደርጋል ይሉታል ።
አነስተኛ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኛ ግን ዋጋው የሚቻል አይደለም ።
እነዚያ የባንክ ጊዚያዊ ሰራተኞች ነን ያሉን ሁለት እርጥብ ለሶስት ለመብላት መዋጮው ላይ ሲወያዩ በሬ ለመግዛት ምክር የሚያደርጉ ይመስል ነበር ።
አንጀቴን በሉት !
ልክፈልላችሁ ለማለትም ሞራል የሚባል ነገር አለና ተሳቀኩ !
ብቻ ጥቂት ኪሴ የነበረ ገንዘብ ሰጥቻቸው ቡክ ክፈቱበት ብዬ ወደፊት ሄድኩ ።
አዕምሮዬን ያዘኝ " ስንት ሰው ነው የስልሳ ብር እርጥብ ለመብላት በከተማችን እየተጨነቀ ያለው ? " | 448 |
| 14 | የዳታን ጥቅም አለማወቅ በየቀኑ ገንዘብ እየቀደዱ እንደመጣል ይቆጠራል ።
Data ወደ information ሲቀየር እውቀት ይሆናል ። እውቅትን በሚገባ መተንተን እና በስራ ላይ ማዋል ወይንም መጠቀም ስንጀምር ወድ ሃብት ይቀየራል ።
በአጠገባችን እና በእጃችን ዴታ ከሌለን መረጃን ማዳበር ማውጣት አንችልም ። ከዴታ የምናወጣው መረጃን ደግሞ በሚገባው ተንትነን በስራ ላይ ካላዋልነው ሃብት አይፈጠርም ።
እውነተኛ ዘላቂ ሃብት ያለእውቀት ፣ እውቀትም ያለ ትክክለኛ መረጃ ፣ መረጃም ያለ ዴታ አይኖርም ።
በኢትዮጵያ እንደ ዴታ የተቀለደበት ኃብት ያለ አይመስልም ። በሚገባ Abuse ተደርጓል እየተደረገም ነው ። እሱም በተራው እየቀለደብንም እንዲሁም የቀለድንበትንም ያህል በደንብ አድርጎ እየተጫወተብን ይገኛል ።
የዘመናችን አነጋጋሪው Artificial intelligence ዋናው ስራው ይህንን ዴታ ለሰው ልጅ እንዲጠቅም ሰብስቦ እና Analyse አድርጎ ወደ ሃብት መቀየር መቻል ነው ።
ወደድንም ጠላንም ዓለም እየተቀየረ ብቻ ሳይሆን ወሳኝ በሆነ መልኩ ተቀይሯል ። ይህንን ማመን ተገቢ ነው ወይንም ተገቢ ይመስለኛል ።
አሁን አሁን ግሎባላይዜሽን ተፅዕኖ የሚባል ነገር ቀርቷል የሚለው ሃሳብን የሚገዙት በዝተዋል ። ያለው የ ቴክኖሎጂና የሳይንስ ተፅዕኖ ነው ።
መጭው አምስት እና አስር ዓመት ከዚህ ቀደም ስናከናውነው የነበረውን ዓይነት የዕውቀት ሞዴል ይዘን የትም እንደማንደርስ መረዳት የሚያስፈልግበት ዘመን ላይ ነን ።
ለዚህም ነው ሰሞኑን Davos ላይ በነበረው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ስብሰባ የዓለማችን ትልቁ ስጋት Misinformations and Disinformation ሲል ስጋቱን ያስቀመጠው ።
➦የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ፡፡ የቢዝነስ መረጃዎች እና አነቃቂ ሃሳቦችን በቀላሉ ታገኛላችሁ፡፡ https://t.me/+KoGdFzHO8eA3YWE0 | 477 |
| 15 | በሰው ኃብት እና ገንዘብ ስራን መስራት ይቻላል ።
ይህ መቼም እንዴት ሊሆን ይችላል ብሎ የሚጠይቅ አይጠፋም ።
በርግጥ የሰው ኃብትና ገንዘብን ተጠቅሞ መስራት የሚቻልበት ብዙ መንገዶች ቢኖሩም ማሰብን ግን በዋናነት ይጠይቃል ። (critical thinking)
ማስብ መቻልን እንደቀላል የሚያዩ ሰዎች በሰው ኃብት እና ገንዘብ እንዴት መስራት እንደሚቻል ምስጢሩን ሊደርሱበት አይችሉም ።
ማሰብ ከባድ ስራ ነው ። አለማሰብ ዋጋ ሲያስከፍል ማሰብ ግን ዋጋ አ...ያ...ስ...ከ..ፍ....ል....ም ! ። ቢያስከፍልም Rewardu የትየለሌ ነው ።
አንድ ጊዜ ከአንድ የምህንድስና ሙያ ባለቤት ከሆነና በዘርፉ ረጅም አመት ልምድ ካለው ሰው ጋራ መስራት ስለሚችለው ስራ እያወራን ሳለ ይህ ርዕስ ተነሳ ።
የተለያየ የስራ ሃሳቦችን ስንጥል ስናነሳ ሳለ ለእያንዳንዱ ለሚነሱት የስራ ሃሳቦች ሊሳካ የማይችልበትን ምክንያቶችን ሁሉ በሚገባ ያስቀምጥልኝ ነበር ።
የሚላቸው ነገሮች ስህተት ኖሮበት አልነበረም ። ግን የሚሳካበትን መንገድ መሻትን እንዳያስብ አዕምሮውን ዘግቶት ነበር ።
ካቀረብኩለት አንዱ ሃሳብ በሰው ገንዘብ እና ሃብት መስራት የሚለውን አንዱ ነውና በስራ አጋጣሚ የማውቃቸው በውጭ አገር የሚኖሩ ሰዎች በአዲስ አበባ ከተማ G+9 ፈርኒሽድ የሆነ አፓርትማ ሆኖ ከታች ሁለት ወለሎች ለኮሜርሻል ስራ የሚውሉ እጅግ ውብ ሆነው የተጠናቀቀ ህንፃን የሚያስተዳድርላቸው ይፈልጉ ነበር ።
የእነርሱ ሃሳብ የሚፈልጉት ሰው ንብረቱን በታማኝነት አስተዳድሮላቸው በዓመት የተወሰነ ክፍያ ለእነርሱ እንዲከፍልና ከዚያ ከሚስማሙበት በላይ የሚያገኘውን ገቢውን maximize በማድረግ እንዲጠቀም ነበር ።
ግንባታው የነበረበት ቦታ አሪፍ ከመሆኑም በላይ ግንባታዎቹ የተጠናቀቁበት ማቴሪያል እንዲሁ ምርጥ ስለነበረ ለውጭ ዜጎች ጭምር በቀላሉ የሚከራዩ ጭምር በመሆናቸው ከኤምባሲዎች ጋር ግንኙነት ፈጥሮ ሴኩሪቲው ሃይ በማድረግ ጥሩ ስራ ሊሰራበት የሚችል አቅም ያለው ቢዝነስ ነበር ።
በክርክራችን መደምደምያ ላይ እንዲህ ያለ Risk መውሰድ አልፈልግም ወይንም የምወደው ስራ አይደለም አለኝ ። ይህ የምወደው ስራ አይደለም ብሎ የመለሰልኝ መልስ ብቻ አሳመነኝ ። ይሁንና የመስሪያ ካፒታል አጣሁ ለሚለኝ ጥያቄው ከብዙ አማራጮች ውስጥ አንድ ምላሽ የሚሆን ሞዴል ያገኘ መሰለኝ ። በሰው ንብረት እና ገንዘብ ስለመስራት።
በነገራችን ላይ ይህ ስራ wealth management ወይንም Asset managment ይባላል ። በዓለም አቀፍ 103 ትሪሊየን ዳላር ያህል ንብረቶች በ wealth management ስር ሲሆኑ ከ 1 እስከ 3% የሚሆን ንፁህ ገቢ ይገኝበታል ። | 453 |
| 16 | ቢዝነስ ውስጥ የሚፈፀሙት አስሩ ስህተቶች !
Passionate ያልሆንበትን የቢዝነስ መስክ መምረጥ አለመቻል ።
ስለምንሰራው ቢዝነስ በቂ እውቀት ሳይኖረን መጀመር
አንድ ገፅ እንኳን የተፃፈ እቅድ ያለመኖር ( BMC)
ካፒታልን በዘፈቀደ ንግድ ፈቃድ ላይ ማስመዝገብ እና ቢዝነስን Run ለማድረግ መሞከር
ተወዳዳሪነትን ግምት አለመስጠት ።
ትክክለኛ ያልሆነ የቢዝነስን አጋር መምረጥ
ፕሮዳክትንና ደንበኛን ትኩረት መንፈግ
የባለሙያን ምክር አለመጠቀም ።
የካሽ ፍሎው ምንነትን አለማወቅ እና ፋይናንስን ማኔጅ ማድረግ አለመቻል ።
የንግድ እና ታክስ ህጎችን ለመገንዘብ አለመቻል ወይንም ትኩረት መንፈግ ...(ignorance) ናቸው ።
➦https://t.me/businessIdea_7 | 433 |
| 17 | ዕውቀት (knowledge) ምንድ ነው ?
=================================
“እውቀት በወጣትነትህ ጌጥ፣ በጉልምስናህ ጊዜ የገቢ ምንጭ፣ በእርጅናህ ጊዜ ደግሞ ምርኩዝህ ነው” የሚለን ታላቁ የፍልስፍና አባት አርስቶትል ዕውቀትን በሶስት ይከፋፍለዋል፡፡
የመጀመሪያው የዕውቀት ምድብ:-
1. Technical knowledge/ ቴክኒካል የምንለው ዕውቀት ሲሆን የዚህን የእውቀት አይነትና ጥቅም ሲያብራራም “በአለም ላይ ካሉ ፍጥረታት ሁሉ አምራች የሆነው የሰው ልጅ ብቻ ነው፤ ይህንን ምርታማነት ደግሞ ከተፈጥሮ ስለማያገኝ ከቀደሙት አባቶቹ የሚያገኘው የቴክኒክ ዕውቀት ያስፈልገዋል” ይላል፡፡ ሁለተኛው የዕውቀት ምድብ :-
2. ስነምግባራዊና ፖለቲካዊ እውቀት (ethical and political knowledge) እንደሆነ ገልፆ፣ ይህ የሰው ልጅ ህይወት በሞራል ህግጋት ሊገራ የሚገባው እንደሆነ ያስረዳል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የራስ ወዳድነትና የበላይነት ስሜቶች በማህበረሰቡ ውስጥ ገነው በመውጣት ማህበራዊ ቀውስን እንደሚፈጥሩ ያስረዳል፡፡ (ይህን ዕውነታ የተረዳው የሳይንሱ ሊቅ አልበርት አንስታይንም “እውቀት በጨመረ ቁጥር ራስ ወዳድነት (ego) ይቀንሳል፤ እውቀት በቀነሰ ቁጥር ደግሞ ራስ ወዳድነት ይጨምራል” ማለቱን ማስታወስ ተገቢ ነው) አርስቶትል ገለጻውን ሲቀጥል የሰው ልጅ ፖለቲካዊ እንስሳ (political animal) በመሆኑ ይህንኑ በብቃትና በብስለት ይከውን ዘንድ እነዚህ እውቀቶች እንደሚያስፈልጉት ይጠቅሳል፡፡ ሶስተኛው የዕውቀት አይነት:_
3. ንድፈሃሳባዊ እውቀት (theoretical knowledge) ሲሆን በዚህ ስርም በአዕምሮ የሚደረስባቸውና የማይደረስባቸው ጉዳዮች ይጠቃለሉበታል፡፡ ከነዚህም ውስጥ የዲበ አካል (metaphysics) የፍልስፍናና የሒሳብ ዕውቀቶች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ባለንበት የግሎባላይዞሽን አለም ዕውቀት በየአዳዲስ የቴክኖሎጂ ግኝቶች ውስጥ ለራሱ አካል ሰጥቶ (embedded) የሚታይ ግዙፍ አዕምሮአዊ ንብረት (intellectual asset) ከመሆኑም ባሻገር የሃገራትን ኢኮኖሚ እስከመሸከም የደረሰ ተፅዕኖ ያለው ሃብት እንደሆነ የዕውቀት ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ ከሌሎቹ ሃብቶች በተለየ የዕውቀት ሃብት ቢለገስ የማይቀንስ፣ ቢሰራበት የማይደበዝዝ፣ ውጤቱም ሁሌ አትራፊ እንደሆነ የሚያስረዱት ሊቃውንቱ ይህንን ሃብት በቅጡ ለማስተዳደርም የዕውቀት ማኔጅመንት (knowledge management (KM)) የተባለ የጥናት ዘርፍ እስከመመስረት ደርሰዋል፡፡
በመሆኑም እንደ ህንድና ቻይናን በመሳሰሉት ሃገራት ዕውቀትን ለሃገራቸው እድገትና ብልፅግና እንደዋነኛ ሃብት ከመቁጠርም ባለፈ ለምዕራባውያን በመሸጥና በአዳዲስ የፈጠራ ብቃቶቻቸው በመገዳደር በኢኮኖሚ ፉክክሩ ውስጥ ወሳኙን ቦታ ለመያዝ ችለዋል።
ስለ ቢዝነስ ማስታወሻ በነፃ ስለ business ግንዛቤ ለማግኘት ትክክለኛ ቦታ 👉https://t.me/businessIdea_7
የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ፡፡ የቢዝነስ መረጃዎች እና አነቃቂ ሃሳቦችን በቀላሉ ታገኛላችሁ፡፡ https://t.me/+KoGdFzHO8eA3YWE0 | 415 |
| 18 | ካፒታል ማርኬት ምንድን ነው ? የሚለውን ለመረዳት ቀለል ለማድረግ ስራ ፈጣሪዎች የስራ ሃሳባቸውን ለመተግበር የሚያስችላቸውን ካፒታል ለማሰባሰብ የሚረዳቸው መገበያያ ቦታ እንደማለት ነው።
ወይንም ቁጠባና እንቪስትመንትን ማገናኛ ገመድ ልንለውም እንችላለን ። ይህ አባባል ይበልጥ የሴኩሪቲ ማርኬት የሚለውን ይገልፀዋል ።
በሴኩሪቲ ገበያ ቁጠባን ወደ ኢኮኖሚው ለማስገባት እና የቁጠባን ገንዘብ ለማንቀሳቀስ ቻናልን በመፍጠር ረገድ ጉልህ ሚና አለው security market ። (mobilize and channelise saving)።
የኢንቨስተሮችን የእለት ገንዘብ ( Liquidity) በመፍታት የፋይናንስ ሲስተሙ ጠንካራ እንዲሆን ያደርጋል ።
እንደሚታወቀው በአንድ አገር አሪፍ የፋይናንስ ሲስተም እንዲኖር ከሚያስችሉት ውስጥ የውጭ ምንዛሬ ደንብ ( Regulations) ፣ የባንኮች አገልግሎት ፣ የውጭ ምንዛሬ ክምችት አስተዳደር ፣ የብድር ቁጥጥር፣ የፊሲካል እና ገንዘብ ፖሊሲ እንዲሁም የ የዕለት ገንዘብ አስተዳደር (liquidity management ወሳኞች ናቸው ።
አንዳንዶች ይህ የካፒታል ማርኬት የሚባለው ነገር ለድሃው ምን ይፈይዳል ? ሃብታምን ወይንም ያለውን ነው የሚጠቅመው የሚል ይዘት ያለው ሃሳቦችን ያንሸራሽራሉ ።
ለአገር ኢኮኖሚ የሚያመጣውን አዎንታዊ ሄደት ካለማጤን ጠቄሜታውን ካለመገንዘብ የመጣ ይሆን ወይንስ ከርዕዮተ ዓለም በመነሳት ይህ እንደሚባል አላውቅም ።
ይሁንና ካፒታል ማርኬት ከሌለ ታድያ ምን ይኑር የሚለው ጥያቄን ሊመልሱ ይገባል ። አሁን ዓለም ከካፒታል ማርኬት ወደ ዲጅታል ማርኬት እየተሻገረ ነው ያለው ።
ወደ ዲጅታል ማርኬት እንጓዝ ከሆነም እሰየው ። ይህ የዲጂታል ማርኬት ምክር ግን አሁን ባለው የሃሳብ ገበያ ላይ ለመጀመር ማሰብ በራሱ አድካሚ ነው የሚሆነው ።
በኢትዮጵያ ውስጥ የካፒታል ማርኬት እድልና እንቅፋቶችን ሰሞኑን ለማየት እንሞክራለን ። | 420 |
| 19 | ነጻ አውጪያችን ቴክኖሎጂ ነው!
ዛሬ አንድ በአውሮፓ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በAI ዘርፍ የPh D ትምህርቱን በማጠናቀቅ ላይ ካለ ወዳጄ ጋር በስልክ ስንወያይ ነበር።
አሁን የዶክትሬት ዲግሪውን ለማጠናቀቅ ጥቂት ጊዜያት ብቻ ቀርተውታል። ምርምሩን ያደረገው በAI ዘርፍ በተለይም በAI ቋንቋን መተርጎምና ማንበብ ላይ ነው።
በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በትግርኛ የተጻፉ ጽሁፎችን ማንበብ እና መተርጎም የሚችል ቴክኖሎጂን እያበለጸገ ነው። ይህ ቴክኖሎጂ በሌሎች የውጭ ቋንቋዎች ያለ ቢሆንም፣ በሀገራችን ቋንቋዎች ግን የለም ብሎኛል።
እንግዲህ አስቡት! ይህ የቴክኖሎጂ አፕሊኬሽን ሥራ ላይ ሲውል የቋንቋ ላይ ጭቅጭቅ ውሃ ሊበላው ነው። በፈለገው ቋንቋ ይጻፍ ወይም ይነገር በቃል ይሁን በጽሁፍ እዚያው በዚያው ይተረጎምልሃል። ያንተም እንደዚያው ለሌላው ይተረጎማል።
ይህ ቴክኖሎጂ ሥራ ላይ ሲውል መጽሓፍትን ያነብና ወደ ኦዲዮ ቡክ ይለውጠዋል። ይህም በጉዞ ላይ መጽሓፍን መስማት ለሚወዱ፣ ለዐይነ ስውራን እና ለቋንቋ ትርጉም ጥቅም ላይ ይውላል።
አሁን ይህ ወዳጄ ሥራውን በገንዘብ የሚደግፍ የቢዝነስ አጋር ይፈልጋል። ፍላጎት ያላችሁ በውስጥ ልታናግሩኝና የበለጠ መረጃ መስጠት እችላለሁ።
ዘመኑ እየተለወጠ ነው።
ዳይ ነቅነቅ በል።
ተባበር! | 436 |
| 20 | በኢኮኖሚ ማደግ ትፈልጋለህ?
በኢኮኖሚ ማደግ ከፈለግህ የሚከተሉትን ሳትታክት ከውን!
፩) የምትፈታውን ችግር ፈልግና ሥራ ጀምር። ገቢ የማያስገኝ ችግር ፈቺነት ብዙ አያስጉዝህምና ገቢ የሚያስገኝ መፍትሔ ፈልግ።
፪) መፍትሔህን ለገበያ አስተዋውቅ። ያመጣኸውን መፍትሔ ማን ይፈልገዋል? ፈላጊዎችህን ካወቅህ እነርሱ የሚጉኘበት ቦታ ሂድና መፍትሔህን አስተዋውቅ።
ልብ በል ጧፍ የሚሸጠው ቤተ ክርስቲያን ደጃፍ እንጂ መስጊድ በር ላይ አይደለም። ጀለቢያም መስጊድ በር ላይ እንጂ ቸርች በር ላይ ጠያቂ አያገኝም።
ትክክለኛ ቦታህን መርጠህ መፍትሔህን አስተዋውቅ።
፫) ቶሎ ወደ ሽያጭ ግባ። የሙከራ ሽያጭ የቢዝነስህን ተፈላጊነት ማረጋገጫ ነው።
ሽያጭ የቢዝነስ ዋና ሥራ ነው። No sales no business.
በምርምር ጊዜ አትፍጅ። መሸጥ ከቻልህ ቢንጎ!
እየሠራህ፣ እየሸጥህ ተመራመር።
በትንሹም ቢሆን ሃሳብህ፣ አገልግሎትህ መሸጡን ፈትሽ፣ ሞክር፣ አስተካክል።
፬) ትኩረትህን ቢዝነስህ ላይ አድርግ። ልብህ አይወላውል፣ ዐይንህን አትንቀል።
ቢዝነስ ትኩረት ይፈልጋል። የሽያጭ ገቢህን ለካ። እየለካህም መሻሻል ያለበትን አሻሽል።
፭) ሁሌም ወጪህ ከገቢህ ያነሰ ይሁን። በተከታታይ ከገቢህ በላይ እያወጣህ ማደግ አትችልምና ወጪህ ከገቢህ እንዳይበልጥ ተጠንቀቅ!
፮) ትርፋማ ስለሆንክ አትኩራራ።
ቢዝነስ ሁሌም በውድድር ላይ ነው። ቢዝነስ የማራቶን ሩጫ ዓይነት ነው። ውድድሩ ረዥም ጊዜ ይወስዳልና ገና በግማሽ ላይ ስለመራህ አትኩራራ። ይልቅስ ሁሌም ተወዳዳሪዎችህን እየቃኘህ በትጋት ተጓዝ።
፯) የደንበኛህን ፍላጎት ቀድመህ ተገኝ።
ደንበኞችህ ከሚጠይቁት በላይ ለመስጠት ተጣጣር። ለደንበኛ በቂ ነው አትበል። ደንበኞችህን አስደምም።
➦https://t.me/businessIdea_7 | 415 |
