cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Venue

መድረሻ ባይኖር ፣ መጓዝ ብርቅ ነበር! : መራመድ ባልከፋ ፣ መድረሻም ባልጠፋ ነገ ላይ ለመድረስ ፣ ሰው ባያጣ ተስፋ ።

Show more
Advertising posts
2 182
Subscribers
-224 hours
+237 days
+6330 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
« ኡራዝ ቪ» [አብዱልሀኪም ሰፋ] : ሁለት ወደ ኋላ: አንድ ወደፊት! : በስተመጨረሻ ነገ 7/9/2016 ይጀመራል! መልካም ንባብ ይሁንላችሁ! : @Venuee13 @Venuee13
2390Loading...
02
Media files
4387Loading...
03
~ስለተሰረቁ መስከረሞቻችን እንማልዳለን (እምላችሁ ስለዚህ ስለውዴታዬ ጉራማይሌ መፅሀፍን የሚሰጠኝ የለም?እጀግ የሚወዱት ነገር እጅ ለመግባት ለምን ይህን ያህል ዘመን እንደሚያስጠብቅ አይገባኝም) ነጃት ነኝ። @Venuee13
4385Loading...
04
እናንተ ምነው ቀኑ እሁድ መሆኑን ደበቃችሁ?
4560Loading...
05
ዛሬ ቅዳሜ ነው አሉ😳 ቀኑ ይሄደዋል ቢስሚላህ.... እኔ እፅፍ በነበረበት ወቅት የመጀመሪያው አስተያየት ቃላቶችሽ ከባድ ናቸው ነበር... እኔ ደግሞ በንግግር የምጠቀማቸውን አማርኛዎች(ሁሉም ከእናቴ የተወረሱ) ነው ምጠቀመው... እናላቼሁ አሁን ሳውራ ምን አልሽ ብለው ያስቆሙኝን ቃል ልንገራችሁ ቃሉ ... «ለደለደ» ወይም «ለድልዷል» የሚል ነው... ይህን ቃል ትርጉሙን እናውቃለን ብላችሁ ገላግሉኝ እስቲ😂 ነጃት ነኝ። @Venuee13
5141Loading...
06
Media files
7086Loading...
07
በቅርብ ቀን በመድረክ ላይ እንገናኛለን! እስከዛ ድረስ ባላችሁ የሶሻል ሚድያ አካውንቶች በማስተዋወቅ እንድትቆዩኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ!🙏 . @huluezih @huluezih
6131Loading...
08
« ሙትቻ ላሉህ ሰዎች እራስህን ለማስረዳት አትሞክር። ለሞትክባቸው ሰዎች የምታባክነው ጊዜ አይኑርህ። ውበትህ ግለፅ ሲወጣ የመጣ ሁሉ ውበትህን አይቶ ላይሆን ይችላልናበ አመዳምነት ዘመንህ ላይ ውበትህ የታያቸውን ጠበቅ አድርገህ ያዝ። ቆንጆ መሆንሽን ከሚያደንቁት የበለጠ የሚያስጠላብሽን ሊያስውቡልሽ የሚጣጣሩትን አትዘንጊ። ቁስልሽን በሰው አትከልዪ። የሚመክሩሽ ሁሉም ከጥቃት አይጠብቁሽም። ጥንቃቄ የብልሆች መንገድ ነው። በጣም ነፃነት በሚሰማሽ ሰው በኩል ስስ ነሽና አትራቆቺ። ዋጋ የምትከፍዪላቸው ከጌታሽ መንገድ እንዳያስቱሽ አስተውዩ! የምወድሽዋ ልብሽን በቀደር አረጋጊ! የምወድህዋ እራስህ ካልወደቅክ አይጥሉህምና በጌታህ ታግዘህ ፅና። መንገዱ ምን እንዳለው አይታወቅምና ሰላም ለልባችሁ! » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
6758Loading...
09
« የራሴ አላረግህ ነገር ነውር ነህ፣ አልርቅህ ነገር ርቄ አልርቅህም። አላመሰግንብህ ነገር ስህተቴ ነህ። አልመኝህ ነገር የተከለከልከኝ ነህ። እንዴት ያለ ቻይነት አምላኬ ቢያስታጥቀኝ ሞከረኝ? ምናል ለአይንህ ጌታዬ ብርሀን ባይሰጠው? ምናል ሰይጣኔ ለሩሄ አንተን እንድጠላ ጥላቻ ሹክ አላለውም? ፍቅሬም፣ ትዝታዬም ሁሉም ወንጀል! » [አብዱልሀኪም ሰፋ] እስከ 7/9/16 ድረስ በደንብ ተብሰልሰሉበት! : @Venuee13 @Venuee13
62311Loading...
10
-1- : @Venuee13 @Venuee13
84117Loading...
11
« ቁርዓንን ማን ሲቀራው መስማት ይበልጥ ደስ ይልሀል ብባል ቀድሜ የምጠራው የእሳቸውን ቂርዓት ነው። የመካው ድምፅ፣ ባለ ወርቃማው ድምፅ ባለቤት ሸይኽ አብዱልባሲጥ አብዱሰመድ። ከየትኛውም ቃሪ የእሳቸው ቂርዓት ይማርከኛል። የእሳቸውን ቂርዓት ማድመጥ ስለምወድ ይሆናል እየተጣደፈ የሚቀራ ቃሪ ለመስማት ብዙ አልመቻችም። ቁርዓን ተረጋግቶ ሲቀራ ይበልጥ ይማርከኛል። ግብፅ አንድ ከሚገርመኝ ነገሯ የሚገራርሙ ቃሪዎች አፍርታለች። ብዙ ቃሪዎች የእሳቸው የአቀራር ዘይቤን ተከትለው ለመቅራት ቢሞክሩም ሊስተካከሏቸው ግን አልቻሉም። መተናነሳቸው፣ በድምፆቻቸው ውስጥ የቁርዓኑን ትርጉም ለመግለፅ የሚሄዱበት ርቀት ይገርመኛል። እንዲሁ ድምፅን ማሳመር አይደለም። በጥልቀት ስናዳምጠው በድምፆቻቸው ከፍታና ዝቅታ ውስጥ የሚመላለስ ትርጉም አለ። ስለ ሸይኽ አብዱልባሲጥ አብዱሰመድ የሆነ ቀን ስለ ታሪካቸው በደምብ ለምስራት እሞክራለሁ። እጅግ ስለምወዳቸው ስለምወዳችሁም ልጋብዛችሁ ለእናንተም። » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
9696Loading...
12
በቀን ብዙ ሰው አገኛለሁ ፡ ታክሲ ውስጥ ፡ መንገድ ላይ ፡ በጣም ብዙ ደግሞ ስራ ቦታ... ብዙ ታሪኮችን ሰምቻለሁ... አይቻለሁም ብዙ ባህሪዎችን... እና እስቲ ስንፍናዬን የሚገፍ ነገር በሉኝና የሆነ የሆነ ቀን ላጋራችሁ🌼 አሁንም ነጃት ነኝ ለማለትዩ : @Venuee13
7791Loading...
13
ሐሳቤን ዘርዝሬ ማስረዳት እየከበደኝ ነው መሰለኝ... አሁን አንድ ቪዲዮ ማየቴ ሁሌ የማስበውን ነገር አስታወሰኝ። ቀጠሮ ላለው ሑሌ ቀድሞ መገኘት(ተመሳሳይ ሰው ጋር)... እንደሚያረፍድ እያወቃችሁ ፡ አይ በቃ አሁን ቀስ ብዬ እሄዳለሁ ብላችሁ እያሰባችሁ እንኳ መዘግየት ልባችሁን የሚከብደው ከሆነና ሑሌ ጠባቂ ከሆናችሁ... ክብራችሁን ነጥቃችሁ ለነጣቂ እየሰጣችሁ ነው ማለት ይቻላል? ነጃት ነኝ። @Venuee13
7811Loading...
14
ደግ የልብ ምርኩዝ የሚሆን ሰው አያሳጣችሁ! መልካሙን ተመኘሁ! ሰላም ለልባችሁ! 🙏🙏🙏 : @Venuee13 @Venuee13
9246Loading...
15
« በሩቁ በምንሰነዝራቸው መልካም ቃላት ሰበብ ሰዎች ሲያከብሩን፣ እንደ አዋቂ ሲያስቡን ልንኮራ አይገባም። ሲጀመር መኩራትም ፈፅሞ የለብንም። በቃ ለመልካም ጥርጣሬያቸው አላህን እናመስግን። ምክራችንን የሰሙ ሁሉ ከእኛ ያነሰ እውቀት አላቸው ማለት አይደለም። ንግግሮቻችንን የናቁ ሁሉ ከእኛ የተሻሉ ስለሆኑ አይደለም። ነፍስያን መግራት ግድ ይላል። ልባችን ካልተደነቅንም ሆነ ካልተከበርን ሊከፋው አይገባም። ጭብጫና አድናቆት ለልብ ቀለብ የሚሆን ዚክር አይደለም። ጭብጨባ ሁሉ ጀነት አያደርስም። አድናቆትም ሁሉ ከቂያም ጭንቀት አይገላግልም። አንዳንድ ሰዎች አለን ከሩቁ ማር የምንመስል፣ ጠልቀው ቀርበው ሲያውቁን ግን መራራ የሆንን። ከሩቁ አዋቂ መስለን ሲቀርቡን ሲጠጉን ለቃቅሞ ከማውራት የዘለለ የተጨበጠ እወቀት የሌለን ሰዎች አለን። ለሰዎች የሆነን መልካም ነገር ማስታወስ የልቅና ምልክት አይደለም። የተለየ የዓሊም ደረጃንም አያጎናፅፍም። አጓጉል አንኮፈስ። እጅግ በጣም የሚበልጡን፣ ከጉያቸው ተናንሰን ልንማርባቸው የሚገቡ መዓት የሚያዳምጡን ሰዎች አሉ። ግዴላችሁም ቀስ፣ ሰከን፣ ረጋ እንበል! ሰዎችን ስናደንቅም ሆነ ስናከብር ሰው መሆናቸውን ልንዘነጋ አይገባም። ሰዎች ካሰብነው በታች ሊወርዱ፣ ከገመትነው በላይ ከፍ ሊሉ፣ ከጎደልናቸው በላይ ሊሞሉ፣ ከሞላናቸው በላይ ሊጎድሉ፣ ካስቀመጥናቸው ቦታ ላይገኙ ይችላሉ። ስናደንቅም ስንደነቅም፣ ስናከብርም ስንከበርም አደብ አንጣ። ብቻ ልቤ እንዲህ ይለኛል። » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
9157Loading...
16
ዴንማርክ ውስጥ የሚገኝ አንድ ላይብረሪ(ቤተ መፅሀፍት) አለ። በዚህ ቤተ መፅሀፍት ውስጥ ለ30 ደቂቃ ያህል መፅሀፍ ወስዶ ከማንበብ ሰዎችን ተውሶ የህይወት ታሪካቸውን ማዳመጥ ይቻላል። በነገራችን ላይ ፓስፖርት ያለኝ ሰው ነኝ።(ለማንኛውም ብዬ ነው 😂😂😂 ) እናም ሳስበው እኔ ዴንማርክ ከሄድኩ ይሄን ላይብረሪ የማዘወትርበት ይመስለኛል። የሰው ታሪክ ተፅፎ ከማንበብ በህይወት እያለ እራሱ ሲነግረኝ ይበልጥ ደስ ይለኛል። ምን ታስባላችሁ እኛ ሀገር እንዲህ አይነት ቤተ መፅሀፍት ቢኖር? እስቲ በዛውም ሰዎች የነገሯችሁ የማይረሳችሁ የህይወት ተሞክሮ ካለ አካፍሉን። እዚህ ወይም @Venuee13bot ላይ ሹክ በሉን። 👇👇👇👇👇
8071Loading...
17
« ሰዎች ሆይ ለአንዳንድ የህይወት ግራ መጋባቶቻችን ምላሽ ፍለጋ ስንዳክር በስነ ምግባራችሁ ማርኩን። ያኔ ያልገባንን በቀናነት እንጠይቃችኋለን። አንዳንዴ በህይወት ውስጥ እንዲህ ነው ሁሉም መንገድ ልክ ይመስላል። አላህ ትክክለኛውን መንገድ ያሳየን፣ ወደ ትክክለኛው መንገድም የሚያመላክቱትን አያሳጣን። » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
7956Loading...
18
« አንቱ ሰው በህይወቴ ውስጥ ማድረግ ካሉብኝ ነገሮች አንዱን ንገሩኝ? » « አሳምር የኔ ልጅ! » « እንዴት? » « የኔ ልጅ ጌታህ የስራህ ማማር እንጂ የስራህን መብዛት አይመለከትም። ከታይታ መራቁ ውበቱ ነውና ስትሰጥ አስውበህ ስጥ። ፍቅርህን ለማሳመር ስታፈቅር ፍቅርን ከጌታህ ተዋስ። የኔ ልጅ ፍጥረተ ዓለሙ የጌታህ ምርጥ አሳማሪነትን የሚመሰክር ነው። እንኳን ለሚገዙት ቀርቶ ለሚያምፁት ባርያዎቹ ሁሉንም ነገር አሳምሮ በሚሰጠው ጌታዬ እያመንክ እንደምን ማሳመር ላይ ልትሰንፍ ትችላለህ? የኔ ልጅ አሳምር ጌታህ አሳማሪዎችን ይወዳል። » « አንቱ ሰው እወዶታለሁ! » « አሳማሪው ጌታዬ ልብህን ያሳምርልህ! » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
7177Loading...
19
« እኔ ምልህ መርሳትን ግን ለምንድን ነው በሽታ የምንለው? » « ለምን ጠየቅሺኝ? » « ማስታወስ በሽታ መሆን የነበረበት አይመስልህም? » « እንዴት? » « ቆይ ሰው በረሳው ነገር ነው ወይስ በሚያስታውሰው ነገር ነው ይበልጥ የሚሰቃየው? » [አብዱልሀኪም ሰፋ] እስከ 7/9/16 ድረስ እያሰባችሁበት! : @Venuee13 @Venuee13
6665Loading...
20
« እኔ ምልህ መርሳትን ግን ለምንድን ነው በሽታ የምንለው? » « ለምን ጠየቅሺኝ? » « ማስታወስ በሽታ መሆን የነበረበት አይመስልህም? » « እንዴት? » « ቆይ ሰው በረሳው ነገር ነው ወይስ በሚያስታውሰው ነገር ነው ይበልጥ የሚሰቃየው? » [አብዱልሀኪም ሰፋ] እስከ 7/9/16 ድረስ እያሰባችሁበት! : @Venuee13 @Venuee13
10Loading...
21
እዚህ ጥያቄ ስር የሰጣችሁትን መልስና ምኞታቼሁን ሳይ ምንም ምንም በቃ «በዚህ ስብስብ ውስጥ ስላስገኘኸኝ አልሐምዱሊላህ» ብቻ🥺 ኸይር የሆነ ምኞታችሁ ሁሉ ይሙላልኝ ፡ የሑለት አገር ክብረትን ተሸለሙ ቢስሚላሂ። (ነጃት ሐሰን) : @venuee13
7820Loading...
22
ምን ድረስ ወይም ምን ያኽል ሐብታም መሆን ትፈልጋላችሁ? : @Venuee13
8291Loading...
23
ከሰው ጉዞ ተቃራኒ ባለ መንገድ ታክሲ ውስጥ መግባት... ያው እስኪሞላ መከራ ነው። በመሐሉ ሶፍት ማስቲካ የሚሸጡ ኩታራዎች ይጎበኙታል። ደግሞ ልጃቸውን በጀርባቸው ያደረጉ(ልትመራው ኮ ነው) እናቶች እጃቸውን ይዘረጋሉ... መከበር መጦር የነበረባቸው ትልልቅ አዛውንቶችም አፍ አውጥተው ይጠይቃሉ። ታዲያ አንድ ትልቅ ሰው ምን አሉ ዛሬ «አረጀሁ ለስራ አቅም አጣሁ... ታዲያ ምን ያደርጋል እኔ ባረጅ እሱ አያረጅ... አብሮ ቢያረጅ ምን ነበር?» አሉ ወደሆዳቸው እየጠቆሙ... እኔን 😑 (ነጃት ሐሰን) : @Venuee13
7994Loading...
24
Media files
7860Loading...
25
ብዙ ነገር ወድጄ ብዙ ነገር ሰልችቶኝ ያውቃል። እንማውራት አሰልቺ ነገር ግን አጋጥሞኝ ያውቅ አይመስለኝም። (ነጃት ሐሰን) : @Venuee13
7946Loading...
26
የመጀመርያው ረዘም ያለ ፅሁፌ የነበረው #ቅንፍ ይህን ይመስል ነበር። እንዴት ነው ቁም ነገር አገኛችሁ? ከ6ዓመታት በፊት ፅፈፀው በነበረው በቅርብ አመታት ውስጥ በምፅፋቸው ውስጥ የአፃፃፍ እና የሀሳብ ምርጫዎቼ ላይ ያስተዋላችሁት ነገር አለ? እስቲ ልክ ልኬን እዚህ ኮሜንት ስር ወይም @Venuee13bot ላይ ንገሩኝ።
8310Loading...
27
" አ… አው ዶክተር አው…" መርበትበት ጀመረ። እናቱን ከሞት መመለስ ባይችል እንኳ ከአደጋው በፊት ሲያሰቃያት የነበረውን ህመም ለማወቅ ጓጉቷል። " ይኸውልህ ቢኒ ይህ ሚሞሪ ነፍሳቸውን ይማረውና ወይዘሮ ሳሚያ ናቸው የሰጡኝ " " ም…ምን " አንዳች የማወቅ ጉጉት ውስጡን እየሞቀው። " ይህ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና አድርገንላቸው ከነቁ በኋላ ስልኬን አውጥቼ ድምፃቸውን እንድቀዳ ነገሩኝ " ብሎ ሳይጨርስ አይኖቹ እንባ አቀረሩ። ቢንያሚን የእናቱን የመጨረሻ ንግግር ለመስማት ጉጉቱ ሊገለው ነው መጠበቅ አልቻለም። " በቃ …ምንም ልልህ አልችልም ሁሉንም በዚህ ታገኛለህ ምናልባት የምትፈልገው ነገር ካለ ልታገኘኝ ትችላለህ። አይዞን እንግዲህ በርታ በል! " ብሎ ሚሞሪውን አስረክቦት ተሰናብቶት ወጣ። ቢንያሚን ሚሞሪውን በእጁ እያየ መርበትበት ጀመረ። ሰውነቱ ይንቀጠቀጣል፣ በድን አካሉ ነፍስ ሲዘራ ይታወቀዋል። የእናቱ የመጨረሻ መልዕክት ምን እንደሆነ ለማወቅ ተጣደፈ። ሚሞሪውን ስልኩ ላይ ከቶ የጆሮ ማዳመጫ ጆሮው ላይ ሰክቶ ያዳምጥ ጀመር። በደከመ ነገር ግን ውስጡ ፍቅርና ብርታት የተሞላ የእናቱን ድምፅ መስማት ጀመረ። ሁለመናውን ነዘረው። የእናቱን ንግግር ሲሰማ ሳያስበው የደስታም የሀዘንም ስሜት ተደበላልቆበት እንባውን ዘረገፈው። በተለይ ንግግራቸውን ሲጀምሩ " ልጆቼ…" የሚለው ንግግራቸው የሰመርን በህይወት አለመኖር ሹክ እያለው ከእንባው ጋር አንዳች ስሜት ወረረው ወደ ውጭም ወደ ውስጥም አነባ። ሳግ እየተናነቀው ማድመጡን ቀጠለ። " ልጆቼ የእኔ ውዶች አይቼ የማልጠግባቹ አጠገቤ ሆናችሁ የምትናፍቁኝ አበቦቼ ይህን የመጨረሻ ንግግሬን ስትሰሙ በህይወት አልኖርም። እኔን በማጣታቹ የነገ ህይወታችሁ እንዳይጠለሽ ነገን በተስፋና በደስታ እንድትኖሩልኝ ነው የመዳኔ ተስፋ መመንመኑን ስረዳ ነው ይህን መልዕክት የተውኩላችሁ። ዛሬ ደስተኛ ነኝ መልዕክቴ እናንተ ጋር ደርሷል አልሀምዱሊላህ። ለምን ገደልከኝ ለምን ይህን በሽታ ሰጠኸኝ ብዬ አላህን አልወቅሰውም። ከህመሜ በላይ እናንተን ወርቅ የሆኑ ልጆች ሰጥቶኝ እንኳ በወጉ ምስጋናዬን አላደረስኩም። የኔ ውድ በህይወት እያለው ጥሩ ሰው ሆነህ ስኬታማ እንድትሆንልኝ ነበር ምኞቴ በህይወት የለችም ብለህ ምኞቴን እንዳትነፍገኝ። ልጆቼ የእናንተ የነገ ህይወት ከመስተካከል ውጪ ምንም የምፈልገው ነገር የለም ። እህትህን አደራ እኔን ማጣቷን ለደቂቃም እንዲታወሳት እንዳታረግ…" ቢኒያሚን አቅም አነሰው ድምፅ አውጥቶ ማልቀስ ጀመረ። የአደራ እህቱ ከሱ ጋር የለችም። " ልጆቼ አላህ አናንተን ስለሰጠኝ ሳመሰግነው ኖርያለው። እኔን ከናንተ ነጠቀ ብላችሁ እንዳታማርሩት! እኔ የቤተሰቦቼ አደራ ነበርኩ። እነሱ ስላልቻሉ ወደ ራሱ መለሰኝ፣ እናንተ ደሞ የኔ አደራዎች ናችሁ ከኔ በላይ አደራዬን ለሚጠብቅልኝ ለአላህ የናንተን ነገር አደራ ብዬዋለው። አደራ ልጆቼ የአደራዬን ጠባቂ ድንበር እንዳታልፉት። ልጆቼ ነፍስን እንዳትበድሉ ምህረት እየለመናቹ ይቅርታን እንዳትነፍጉ። ልጆቼ ይቺን ዓለም ለቅቄ ብሄድም በናንተ ጥሩ ስራ ህያው እሆናለው፣ በመልካምነታቹ እመነዳለው፣ ክፉ ብትሆኑ እወቀሳለው፣ የሰራሁት ወንጀል ይበቃኛል የናንተ ህይወት መበላሸት መንስኤ ሆኜ ወንጀሌን ከማብዛት ታደጉኝ… " ቢንያሚን ይንሰቀሰቅ ጀመር። የእናቱን አደራ ጠባቂ መውቀሱ አንገበገበው። እየተንሰቀሰቀ የመጨረሻ ደቂቃ የእናቱን ንግግር ማድመጡን ቀጠለ። " ልጆቼ እናንተ ማለት አንድ የተከፈተ ቅንፍ ናችሁ። በተከፈተው ቅንፍ መሀል ያሻችሁን ማስፈር ትችላላችሁ ጥሩም ይሁን በጎ። ወደዚች ምድር ስትመጡ ይህ ቅንፍ ይከፈታል። በዛ መሀል ስራቹ ሁሉ ይመዘገባል። ወደ ማይቀረው ሞት ስትሄዱ ደሞ መዝገባቹ በቅንፍ ይዘጋል። በተከፈተው ቅንፍ መሀል ጥሩ ነገር ብታጎድሉ ህይወትን ትቀጥፋችሁ፣ ነገን ትሸረሽራላችሁ። አደራ በሰው ስቀይ ከሚመጣ ደስታ ተቆጠቡልኝ። ሰው የራበውን ልብ አይዞህ ማለት እንዳትረሱ። የተከፈተውን የህይወቴን ቅንፍ በሰራሁት ስራ የቻልኩትን ሞልቼ ይዘጋል። በናንተ የህይወት ጉዞ በመልካም ስራችሁ አድምቁልኝ። ልጆቼ በተስፋ ድልድይ ሁሉም ይታለፋል። እኔም ነገ ጥሩ ሰው ትሆናላችሁ ብዬ በተስፋ ባለሁበት ፈገግ እላለው። ይህንን አደራዬን እንዳትረሱ! አደራ ጠባቂዬንም ሌት ተቀን ከማመስገን እንዳትቦዝኑ እወዳችኋለሁ። " ቢንያሚን እስኪወጣለት አነባ ተስፋ ያጣው ህይወቱ በእናቱ የአደራ ቃል ዳግም ተነሳሳ። በአይነ ህሊናው ወይዘሮ ሸምስያ ታወሱት። በዚህ ሰዓት ሰው የራባቸው ከሳቸው ውጪ አጣ። የእናቱን ናፍቆት በወይዘሮ ሸምስያ እናትነት ውስጥ ሊፈልገው ወሰነ። በእናቱ የአደራ ቃል ከጌታውም ከራሱ ጋር ሊታረቅ ለራሱ ቃል ገባ። ነገን በተስፋ ሊኖር እናቱ እንዳለችው በተስፋ ድልድይ ሁሉንም ለማለፍ ተስፋ ሰነ። ( በህይወት ውስጥ ብዙ የተጀመሩ ነገር ግን ያልተቋጩ ነገሮች አሉ። የተስፋ ድልድይ ሁሉንም ያሻግራል። ተሻግራችሁ የሀሽሽ ነጋዴዎችን ሴራ ድረሱበት። ተፈፀመ የሚባል ነገር የለም ህይወት ትቀጥላለች። እኔ ግን አበቃሁ ከዚህ በላይ አልቀጥልም ) April 2018 : @Venuee13 @Venuee13
8011Loading...
28
* ቅንፍ * አብዱልሀኪም ሰፋ ( ክፍል አስራ አንድ ) : የብርሀን ፀዳል የቀኑን ፍካት አድምቆታል። ድብቅ ነገር ሁሉ ግልፅ ይሆን ይመስል ሁሉም ባለጥለት ነጭ ነጠላውን ተከናንቦ አስረቅራቂና ሙሾ በሚመስል የቁጭት እንባ ያነባል። ከዚህ በፊት ስለመኖራቸው ፍንጭ ያልነበራቸው ሰዎች በጠቅላላ እየተንጋጉ ዋይታውን እያቀለጡት ነው። የዚህ ሁሉ ነገር ትርጉም ግራ የገባው አንድ ልጅ የተከናነበውን ጋቢ በእምባው ረጥቦ፣ ፍም ከመሰሉ ዓይኖቹ ያለ ማቋረጥ የእንባ ዘለላዎች እንደ ጅረት ያለማቋረጥ ይፈሳሉ። ለቀስተኛው ሁሉ በየተራ እየተንጋጋ የማፅናኛ ቃሉን እየወረወረ ከፊቱ እያነባ ይሄዳል። ለማንም ምንም ምላሽ ከመስጠት የተቆጠበው የውስጡን እልህ በእምባዉ ከመግለፅ ዉጪ ምንም ድፍረት አላገኘም። ገና በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገኝ በጣም ያልቀላ በተለምዶ የቀይ ዳማ የሚመስል ክብ ፊት ያለው ተጫዋች ልጅ ነው። የሚያውቁት ሁሉ በማራኪው ፈገግታውና በጨዋታ አዋቂነቱ ይወዱታል። ዛሬ ግን ያ ጨዋታውና ፈገግታው ከፊቱ የለም ጨዋታ አዋቂ አንደበቶቹ ተለጉመዋል። እነዝያ ጣፋጭ አንደበቶች ሳቅ ተርበው ሀዘናቸውን በእምባ ጎርፍ እየገለፁ ነው። ቢንያሚን በምድር ላይ አሉኝ ብሎ የሚላቸው አንዳቸውም የሉም። ሁሉም ሄደዋል። ብቸኛ ጓደኛውም እርዳታውን እየፈለገ ተስፋ እንዳደረገበት ተስፋውን ሊነጥቀው ላይመለስ ሄዷል። ምድር የሲኦል ያህል ቀፈፈችው፣ ስለመፈጠሩ ተቆጨ፣ ተስፋ መቁረጥ ዙረያውን ከቦ " ለምን ትኖራለህ ? መኖርህ ምን ይፈይዳል ? ለማን ብለህ ልትኖር ነው ? " እያለ ህሊናው ይወቅሰዋል። በተቀመጠበት ዊልቸር ላይ ሆኖ የቁጭት እንባውን ያወርዳል። በሆስፒታል ውስጥ የሳሚ ግድያ ዜና ከተሰማ በኋላ ወይዘሮ ሸምስያ በገዛ ልጃቸው ላይ እንዲያ መሆናቸው ትውስ እያለው ለራሱ ይሁን ለሳቸው ሳያውቀው እምባው ይወርዳል። ሰው በሚያስፈልገው ሰዓት አጠገቡ ያልተገኙ ሁሉ በመገናኛ ብዙሀን በሰሙት አየመጡ የአዞ እንባቸውን እያወረዱ ወሬ ማጣፈጫ ቃላት ለማግኘት በማስተዛዘን ሰበበ ጆሮዋቸውን ደቅነው ተጥደዋል። ቢንያሚን የሀዘን በትር ዙርያውን መቶት ይንገበገባል። በአንድ ጊዜ እህት፣ እናት እና ጓደኛ አጥቶዋል። የፀሀይዋ ድምቀት ለሱ ጨለማ ነው፣ የብርሀኑ ወጋገን " ተመልከት ማንም የለህም ብቸኛ ነህ እኮ " የሚል እየመሰለው ያጣውን እንዲያስተውል የተላከ መልዕክተኛ ይመስለዋል። የሚያምር ነገር ሁሉ የሚቀፍ ሆኖበታል። በዚ መሀል አንድ የማያውቀው ስልክ ተደወለ። ለጊዜው ሀዘኑ እንጂ ምንም አይታወሰውም። ስልኩን በትክክክል ማውራት ከብዶት አጠገቡ ለሚገኝ አንድ ሰው ሰጥቶ " ምን እንደሚፈልግ ጠይቀው " አለ በጣም በዛለ ድምፅ። ስልኩን ተቀብሎት ከደዋዩ ጋር ሰላምታ ተለዋውጠው ቢንያሚን አለመሆኑን ገልፆ አድራሻ ከተለዋወጡ በኋላ ስልኩ ተዘጋ። : : ወይዘሮ ሸምስያ ሀዘን ቁርፍድ አርጓቸው እያነቡት ያለው እንባ ፊታቸው ላይ ጥቁር ሰንበር ሰርቶ ፊታቸው በጥቁር ጅራፍ የተመታ እስኪመስል ጠቁሮ ሞጌያቸው ወጥቷል። አንድም ቀን እንደ እናት በወጉ ሳይጦሩ እድሜ ዘመናቸውን በሙሉ የለፉላቸው ልጆቻቸው እርባና ቢስ ሆነው የሀዘን ሽመል አስታቅፈዋቸዋል። " ክበር ክበር አሉ በምን ሆኜ ልክበር የትካዜ ሾተል ገብቶ በኔ መንደር " እያሉ የሀዘን ማሞቅያቸውን የሚደሰኩሩ፣ በነገርም እየወጉ የሚያለቅሱትን እየሰሙ እንባቸውን ማውጣት ከበዳቸው። የእርጅና ዘመናቸው በሀዘን ማጌጡ አንገሸገሻቸው። ሁሌም ከዛሬ ነገ ይሻላል ብለው የናፈቁት ነገ እንደናፈቃቸው ሳይሆን በእድሜ ዘመናቸው ያላዩትን መዓት ይዞ ከትላንት ብሶ ተቀበላቸው። እህል በአፋቸው አይዞርም፣ ከንፈራቸው ደርቆ ነጭ ሆኗል። የአይናቸው እንባ ከምንጩ የደረቀ ይመስላል። " እንዳንተ አይነት ልጅ ከሚሰጠኝ ምናል መሀን በነበርኩ …" ብለው ያሉት እንደ እሳት ያንገበግባቸዋል። እናት ሆነው ይህን ያህል በልጃቸው መጨከናቸው የእግር እሳት ሆኖባቸዋል። የእናትነት አንጀታቸው ተቆርጦ ወጥቶ ልጃቸው ላይ መጨከናቸው እናት ባልሆንኩ ሲሉ እራሳቸውን እንዲረግሙ አስገድዷቸዋል። ልጆቻቸው በህይወት ኖረው ባይጠቅሟቸውም በመኖራቸው ብቻ ደስተኛ ነበሩ። ዛሬ ግን ያ የለም ብቸኛ ናቸው። አይተው የሚደሰቱበት ነገር አንዳችም ነገር የላቸውም። የእርጅና ዘመናቸው በቁጭትና በፀፀት ከማሳለፍ ውጪ ዞር ብሎ የሚያያቸው አንድም የኔ ሚሉት የለም። ፈጣሪም ላይ ተስፋ ለማድረግ አቅም የላቸውም። ብቸኝነታቸውን ገፎ ሀዘናቸውን የሚጋራ እራሱ ፈጣሪ ካልላከላቸው በቀር ሁሉም ከንፈር ከመምጠት ውጪ አንዳችም ነገር አያደርግላቸውም። : : መርማሪ ፖሊሶቹ ግራ ተጋብተዋል። የእነሱን እያንዳንዱን ድርጊት ቀድሞ መረጃ ደርሷቸው መረጃ የሚያጠፉትን የሀሽሽ አከፋፋዮች ሚስጥር እንቆቅልሽ ሆኖባቸዋል። ከመርማሪ ፖሊሶቹ መሀል፣ ከበላይ ባለስልጣናት የተለያዩ ሰዎች እጅ እንዳለበት ቢተማመኑም እነማን እንደሆኑ ግን አልታወቁም። ጀሚል እየታከመበት ባለበት ሆስፒታል ተገድሏል። ጀሚል የሚታከምበት ክፍል ይገቡ የነበሩት ዶክተሮች፣ ነርሶችና እሱን ለመጠበቅ የተመደቡ ሰዎች ተጠርጥረዋል። ወይዘሮ ሸምስያ ሆስፒታሉን ድብልቅልቁን አውጥተው በግድ ተይዘው ከወጡ በኋላ እንዳይገቡ ታግደው ከሆስፒታሉ ከተባረሩ በኋላ ነበር ግድያው የተፈፀመው። የጀሚል ሬሳ እየተመረመረ ነው ነገር ግን በሰውነቱ ላይ ምንም አይነት አሻራ አልተገኘም። በተቀመጡት የደህንነት ካሜራ ላይም አንድም የተለየ እንቅስቃሴ ወይም ምስል አልተገኘም። ይህን ሁሉ ጠባቂ ተቀምጦ ስለ ወንጀሉ አንድም ፍንጭ ማጣታቸው ለመርማሪ ፖሊሶቹ ትልቅ እራስ ምታት ሆኗል። ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ቢያውሉም ምንም ፍንጭ አላገኙም። በፖሊሶቹ መሀከል መተማመን ጠፍቷል። የህብረተሰቡ ጫና አይሏል። " እንዴት ይህ ሁሉ ጊዜ ተመሳሳይ ወንጀል ሲፈፀም እንዴት አላወቃችሁም? " የሚለውን ጥያቄ መመለስ ተስኗቸዋል። ወንጀሉ የተጠናና በደንብ ታቅዶበት እንደተፈፀመ ግልፅ ነው። ነገር ግን ሰሙን አውቀው ወርቁን ግን ማግኘት ከብዷቸዋል። የሀሽሽ አከፋፋዮቹ ድብቅ ሴራ ከነሱ በስተጀርባ ያሉት ሰዎች ማንነት ማወቅ ለፖሊሶቹ ስውር ቅኔ ሆኗል። : : ቢንያሚን በተቀመጠበት ዊልቸር ላይ በሀዘን አላፊ አግዳሚውን ይቃኛል። በትንሽዬ የአጥር ሽቦ በታጠረችው ቤቱ ያለውን ትርምስ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆኖ ይመለከታል። ከሀዘንተኛው መሀል አንድ ሰው ወደ እሱ እየቀረበ ሲመጣ ተመለከተ። ቀልቡን ሰብስቦ የአይኖቹን እንባ ጠራርጎ በደከመ ፈገግታ ተቀበለው። የእናቱን ህመም መንስኤ የሚነግረው ብቸኛ ሰው ነው። እናቱ ወይዘሮ ሳሚያ እራሳቸውን ስተው በነበረበት ወቅት ሆስፒታል ውስጥ ሲያክማቸው የነበረው ዶክተር ነበር። " ቢኒ ስለተፈጠረው ነገር በጣም አዝናለው አይዞህ ፈጣሪ ብርታቱን ይስጥህ… " " አ…አመሰግናለው ዶክተር " አለ እንባው እየቀደመው። " ቢኒ ስለ እናትህ ብዙ ነገር መጠየቅ እንደምትፈልግ አቃለው ያኔ ሆስፒታል ውስጥ መድሀኒት እንድትገዛ ከነገርኩህ በኋላ እናወራለን ብዬህ ነበር … "
6612Loading...
29
እነሆ የማይደክመው ነገር አለመድከም ሁኖል🤭
6381Loading...
30
#ከሰዎች_ውስጥ : @Venuee13 @Venuee13
7227Loading...
31
#3_ቀናት ይህ ከዚህ ቀደም ያስነበብኳችሁ ፅሁፍ ነው። ወጥ በሆነ መንገድ ለማንበብ እንዲመች አንድ ላይ ብታደርገው የሚል ጥያቄ ቀርቦልኝ ነበር። እናም አሁንም ምላሽ ልስጥበት። በአንድ ላይ PDF አድርጌ ስላዘጋጀሁት አውርዳችሁ ማንበብና ከሌሎች መፅሀፎቻችሁ ጋር ልታስቀምጡት ትችላላችሁ። ይህ ወጥ በሆነ መንገድ የተዘጋጀ 6ኛው PDF ነው። በድጋሚ መልካም ንባብ። [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
7515Loading...
32
#3_ቀናት ይህ ከዚህ ቀደም ያስነበብኳችሁ ፅሁፍ ነው። ወጥ በሆነ መንገድ ለማንበብ እንዲመች አንድ ላይ ብታደርገው የሚል ጥያቄ ቀርቦልኝ ነበር። እናም አሁንም ምላሽ ልስጥበት። በአንድ ላይ PDF አድርጌ ስላዘጋጀሁት አውርዳችሁ ማንበብና ከሌሎች መፅሀፎቻችሁ ጋር ልታስቀምጡት ትችላላችሁ። ይህ ወጥ በሆነ መንገድ የተዘጋጀ 6ኛው PDF ነው። በድጋሚ መልካም ንባብ። [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
10Loading...
33
ስትስቂ አይተው ስታወሪ ሰምተው እጅግ ተገረሙ ደግሞ አጉረመረሙ የማነች? የማነች? ከእንግዲህ የኔ ነች! ብለው ተዛዛቱ ……ብታይ ብዛቱ የተባባሉቱ ኮስተር! ኮምጨጭ ዝም… ረጭ ኩምሽሽ ቁጭት ተስፋን ቅጭት ………እልህ ንቀት ስድብ ውድቀት ግርርፍ ጥድፍ ልብን ንድድፍ ምርርዝ ስርዝ ከብርን ድልዝ እንደማያገኙሽ ሲያውቁ እየሞቱ ራቁ። እኔን ውሽቅ በልብሽ ድብቅ በፍቅርሽ ቅብብጥ ሲመኙሽ ድንግጥ ህ……… ሳትበድዪኝ ይቅርታ ስለተመኙሽ መሀርታ እየጠየቅሺኝ እያፈቀርሺኝ አተለቅሺኝ ተለቅኩ በክብርሽ ደመቅኩ ስላገኘሁሽ ረባሁ በነፍስ በዛሁ። (አብዱልሀኪም ሰፋ) : @Venuee13 @Venuee13
68210Loading...
34
* ቅንፍ * አብዱልሀኪም ሰፋ ( ክፍል አስር) : ቢንያሚን በተዘጋጀለት ዊልቸር ደግፈው ካስቀመጡት በኋላ በነርሶቹ ድጋፍ እናቱ ወደ ሚገኙበት ክፍል እያመራ ነው። ልክ እንደሱ የመኪና አደጋ ደርሶበት ተጎድቶ በመታከም ላይ ካለ ሰው ጋር አይን ለአይን ተጋጩ። ይህንን መልክ ከዚህ በፊት ያውቀዋል አዲስ አልሆነበትም ነገር ግን የት እንደተመለከተው እና የት እንደሚያውቀው ማስታወስ ተስኖታል። ይህንን እያብሰለሰለ አናቱ ወይዘሮ ሳሚያ ወደ ሚታከሙበት ክፍል ገቡ። ወይዘሮ ሳሚያ የኦክስጅን መተንፈሻ ተገጥሞላቸው በነጩ አልጋ ላይ እንደ በድን ሬሳ ተዘርረዋል። ቢንያሚን እናቱን ሲመለከት እንባ በአይኑ ሞላ አንዳች ነገር ሰውነቱን ወረረው። በምድር ላይ አለችኝና ቀረችኝ ብሎ የሚላት እናቱ ከሟች ተሽላ በህይወት ካሉት አንሳ ከሞት ጋር ነፃ ፍልሚያ እየገጠች ነው። ቢንያሚን ወደ እናቱ ጠጋ ብሎ በእምባ በራሰ ፊቱ ተግጥቶ ሳማቸው። የቁጭት እንባውን ያወርዳል። " እማ አንቺም እንደሌሎቹ አትጨክኚብኝማ… እማ እየፈራው ነው… ብቸኝነቴ የቁም እሳት ሆኖ እያንገበገበኝ ነው እማ ግን ይህን ያህል ፈጣሪን ምን ብንበድለው ነው? እማ አቤት አትዩኝም እንዴ…? እማ ድምፅሽ ናፈቀኝ! ና የኔ ውድ… አትዪኝም እ…? " እንባውን መቆጣጠር አቃተው ናፍቆቱ ወደ እልህና ንዴት ተቀየረ። የእናቱ ዝምታ እንደ አውሬ አስፈራው። ሳግ እየተናነቀው " እማ እማዬ…" እያለ የተኛውን የእናቱን ትከሻ ይዞ መነቅነቅ ጀመረ። " እማዬ… " አልጋው እስኪርገፈገፍ ድረስ መነቅነቅ ጀመረ። እንባውና እልሁ እየጨመረ ትንፋሹ ይቆራረጥ ጀመር። ነርሶቹ ተደናግጠው በዶክተሩ ትዕዛዝ የተቀመጠበትን ዊልቸር ገፍተው ተረባርበው አስወጡት። ወይዘሮ ሳሚያ የልብ ምታቸው ጨመረ። በተከደነ አይናቸው የስንብት የሚመስል እንባ አወረዱ። ቢንያሚን የሚሆነው አሳጥቶታል። ዶክተሩ እንዲረጋጋና ሌሎች ህሙማንን እያወከ መሆኑን ነግሮ አደብ እንዲያረግ አስጠነቀቀው። ቢንያሚን ፊቱን ያጠበውን እንባ እየጠረገ እያለ ያ የት እንደሚያውቀው ግራ የገባው መልክ በድጋሚ ሲመለከተው ታወሰው። ከግር ጥፍሩ እስከ እራስ ፀጉሩ ድረስ በሸቀ። እንደሱ ጉዳት ደርሶበት የተመለከተው ጀሚል ነበር። ከዚህ በፊት ምንም አይነት ግኑኝነት አልነበራቸውም። አንዲት ቀን ምናልባት ሽራፊ ሰከንዶች በማይሞላ ሁኔታ ላይ ነበር የተመለከተው። ነገር ግን ልክ እንደ ዛሬ ሆኖ ያስታውሰዋል። ቢንያሚን እናቱን ወይዘሮ ሳሚያ እራሳቸውን ስተው ወድቀው አቅፎ ወደ ሆስፒታል ለመሄድ ወደ አስፋልቱ ወጥቶ የሚሄዱትን መኪናዎች እርዳታ እየጠየቀ እያለ ጀሚል ደሞ ወደ ሀሽሽ አከፋፋዮች ጋር እየሄደ እያለ በድንገት ከሆስፒታል ተደውሎለት በሀሳብ ሰምጦ ወዴት እንደሚሄዱ ግራ የተጋባው ሹፌር ወደ ዳር መኪናውን ሲያስቆመው ቢንያሚን እርዳታ ሊሰጣቸው የቆመ መስሎት ሲሄድ ወድያው ጀሚል ከሀሳብ ሰመመኑ ተመልሶ ሹፌሩን " አፍጥነው ንዳው " አያለ እንዳይቆም ሲከላከል በነበረበት ቅፅበት ነበር የተመለከተው። ጀሚል የሚሄድበት ቦታ ስለመድረሱ እንጂ ማን ይኑር ማን ምን ይፈልግ የሚያውቀው ነገር አልነበረም። ቢንያሚን በዛች ቅፅበት የተመለከተውን ላፍታ እንኳ አልዘነጋም። " ለዚህ ሁሉ ጥፋት ተጠያቂው እሱ ነው። ምናልባት የዛን ቀን መኪናው እንደቆመ እርዳታ አድርጎ ቢሆን ኖሮ ይሄ ሁሉ እልቂት ባልተፈጠረ ነበር። እኔም አንድ እህቴን ባልተነጠቅኩ ነበር " እያለ በንዴት ለራሱ ይናገራል። አይኖቹ ፍም መስለዋል። ይህን ሰው ህይወቱን ቢቀማው እንኳ አያስደስተውም፣ እድሜ ልኩን ቢቀጣው አይወጣለትም። ሲመለከተው ደሙ ይፈላል። አሁን ወደ ውጭ ማልቀስ አልቻለም እንደ ወንድ ልጅ ወደ ውስጥ ያነባል። ጥላቻ፣ በቀል፣ እልህና ንዴት ዙርያውን ከበው ሁለመናውን ተቆጣጠሩት። አሁን ባለበት ሁኔታ ምንም የማድረግ አቅም ስላልነበረው ሁሉንም ዋጥ አርጎ ዝም አለ። : : ወይዘሮ ሸምስያ አንድ ዜና ከሰሙ ቡኋላ ወደ ሆስፒታሉ መጥተው ድብልቅልቁን አወጡት። ጀሚልን እየተመለከቱ… " አንተ አረመኔ ምን ብበድልና ብትጠላኝ ነው ተባባሪህ ያረግከኝ አንተ አውሬ! " " ኧረ አንቺ ሴትዮ ምንሼ ነው ምትቀውጪው? " " ዝም በል አንተ ማትረባ አንድ ቀን ሳላርፍ ሁሌም እህ እንዳልኩ ይህም ሳይበቃህ እንደዚ ጉድ ታረገኛለህ…?! " " ም…ምንሼ ነው ረጋ ብለሽ አናግሪኝ እንጂ…" " አልረጋጋም …! አልረጋጋም! አንተ ከይሲ አልረጋጋም! " እያሉ እንባቸው ያወርዱታል። " ቂል አርገህ ገመናህን እንድደብቅ ታረገኛለህ? " " አረ ሴትዮ እንዳታስበዪኝ! " እምባቸውን መቆጣጠር ተስኗቸው ሳግ ይተናነቃቸዋል። የደረቡትን ነብራማ ፎጣ አውልቀው በመቀነታቸው የደበቁትን 25000 ብር አውጥተው ፊቱ ላይ ወረወሩት። " እንካ በደም ያመጣኸው ኮተትህን… እናትነቴን ተጠቅመህ አሞኘኸኝ ለልጄ ፍትህ እንጂ ሌላ ነገር ጠየቅኩህ ንገረኝ እስቲ?! " : : መርማሪ ፖሊሶቹ እየተካሄደ ስላለው ወንጀል የተለያዩ መረጃዎችን አግኝተዋል። በጀሚል ቤት ውስጥ የተገኘው 200 ግራም የሚመዝነው ሀሺሽ ዋነኛ የወንጀሉ ተዋናዮች እንዳልተያዙ ጠቋሚ ነው። የመገናኛ ብዙሀን የአደጋው አድራሾች ከምን ደረሱ የሚለው ጥያቄያቸው አላቆመም። አድማጭ ተመልካቹም መጠየቁን አጠናክሮ ቀጥሎበታል። እስካሁን የደረሱበትን ዝርዝር ሁኔታ እንዲያሳውቋቸው ውትወታቸው ጨምሯል። ይበልጥ ጥያቄውን ያባባሰው የአንድ ግድያ ዜና ከተሰማ በኋላ ነበር። ሁሉም ትክክለኛውን መረጃ እንዲሰጧቸው አጥብቀው እየሞገቱ ነው። መርማሪ ፖሊሶቹ መረጃቸውን አጠናክረው እንደሚያሳውቋቸው ገልፀዋል። : : የሀሽሽ አከፋፋዮቹ ውጥረት ውስጥ ገብተዋል። እስከ ዛሬ ስለሚያከፋፍሉት ሀሽሽ ማንም ሰው አንዳችም ፍንጭ አልነበረውም። ከተከሰተው አደጋ በኋላ አደጋው የመገናኛ ብዙሀንን ቀልብ ከሳበ ሰነባብቷል። የአደጋው ዋና ተጠርጣሪ ጀሚል ነው። ይህም ከነሱ ሀሽሽ ደንበኛ መካከል አንዱ ነው። በተቀጣጠሩበት ወቅት ካረፈደ ደንበኝነቱን እንደሚያጣና በድጋሚ አገልግሎቱን ለማግኘት 35000 ብር ማስያዝ እንዳለበት ነበር ለመጨረሻ ጊዜ የተነጋገሩት። ጀሚል ምናልባት አደጋውን ባያደርስና ምንም ነገር ባይፈጠር ኖሮ መረጃ ይወጣብናል የሚለው ስጋት ባላሳሰባቸው ነበር። አሁን ግን ጀሚል ሆስፒታል ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሎ ጠባቂዎች ተመድበውለት እየተጠበቀ ይገኛል። የመረጃውን ምንጭ ማድረቅ ይፈልጋሉ። ብቸኛ የመረጃ ምንጭ ደሞ በአሁን ሰዓት ጀሚል ብቻ ነው። በጀሚል አማካኝነት ጥቆማ ደርሷቸው ፖሊሶች ከደረሱበት ስራቸው አደጋ ላይ ነው። የመረጃ ምንጩን ለማድረቅ የጀሚል በህይወት አለመኖር ግዴት ነው። ይህን ለማድረግ የሆስፒታሉ ሙሉ መረጃ አላቸው። ወደ ጀሚል ክፍል ማን እንደሚገባ ጠንቅቀው ያውቃሉ። በመረጃቸው መሰረት ጀሚልን ለመግደል ሰው ተመድቧል። ሳይቀደሙ መቅደም ብቻ ነው። : : በመገናኛ ብዙሀን ተከሽኖ የቀረበው የፖሊሶቹ መረጃ አነጋጋሪ ሆኗል። " በትላንትናው እለት በከተማችን አዲስ አበባ አንድ የግድያ ወንጀል ተፈፅሟል። በትላንትናው እለት የተገደሉት አቶ ሳሙኤል ሀይሉ የተባሉ ግለሰብ በግድያ ወንጀል ተጠርጥረው በጊዜያዊ ፖሊስ ማረፍያ ቤት እንዳሉ ነው የተገደሉት። እስካሁን ድረስ ስለገዳዮቹ ምንም አይነት ፍንጭ አልተገለፀም። በተጨማሪም በከተማችን ውስጥ የሀሽሽ ንግድ እየተካሄደ እንደሚገኝ መረጃ አግኝተናል ሲሉ ፖሊሶች አስታውቀዋል። በቅርቡ በመዲናችን አዲስ አበበ በሳር ቤት ገብርኤል አካባቢ የመኪና አደጋ በማድረስ የተጠረጠረው ጀሚል ጃቢር በተባለ ግለሰብ ቤት በተደረገ ፍተሻ
6910Loading...
35
200 ግራም የሚመዝን ሀሽሽ መገኘቱ ታውቋል። መርማሪ ፖሊሶቹ እንዳስታወቁት በትላንትናው እለት የተገደሉት አቶ ሳሙኤል ሀይሉ የተባሉ ግለሰብ የጀሚል ጃቢር ወንድም በመግደል ሰበብ እንደተጠረጠሩ ገልፀው ከዚህ ግድያ ጀርባ የግለሰቡ እጅ ሊኖርበት እንደሚችል ጨምረው አስታውቀዋል። " : : " አንተ አረመኔ ጠበቃ ጓደኛ አለኝ ያልከው ገዳይ ነበር አደል ኧረ ው…ይ…" እያሉ ጩኸታቸውን ለቀቁት " ባክሽ አታካብጂ የወንድሜን ገዳይ አልነበር የምትትፈልጊው ዋጋውን አሰጠሁት! " " ወይኔ ወይኔ … ው…ኧረ ው…" ጩኸታቸው እየባሰ መጣ። ዶክተሮች፣ ነርሶችና እሱን ጥበቃ የተመደቡት ፖሊሶች ግር ብለው ገቡ። ወይዘሮ ሸምስያን ለማረጋጋት ሞክረው ሲያቅታቸው ከክፍሉ ጎትተው ይዘው መሄድ ጀመሩ። አየተውራጩ " ምናል እንዳንተ አይነት ነፍሰ ገዳይ ልጅ ከሚሰጠኝ ምናል መሀን በነበርኩ… " እያሉ መጮሀቸውን ሳያቆሙ በእምባ ታጅበው የግዳቸውን ይዘው አስወጧቸው። ሆስፒታል ውስጥ ያለው ሰው በሙሉ ተረብሿል። ሁኔታቸው ያሳዘነውም ያበሳጨውም አልጠፋም። በማረፍያ እድሜያቸው በልጆቻቸው እንዲህ መባከናቸው ያንገበገበው ሁሉም የምፀት እንባውን ያወርዳል። ( እረፍት አልባ ማረፍያ እስኪያገኝ እንደ ዛለ ይቀጥላል) April 2018 : @Venuee13 @Venuee13
6700Loading...
36
ያ ደግ ሰው ፡ «ቃልህ ግን ያምር ነበር - እንደ ፈሪ ወታደር ያለቦታህ እያፈሰስኸው ትጨርሰዋለህ እንጂ! ደሞ ትክክለኛዋ ሚስትህ ስትመጣ ምን ትላታለህ? ቀድመህ ቃልህን በትነኸው ተመልሰህ ልትሰበስበው ነውን?» አለው። ገፅ 42🌼💔 @Venuee13
6381Loading...
37
* ቅንፍ * አብዱልሀኪም ሰፋ ( ክፍል ዘጠኝ) : ወይዘሮ ሸምሲያ እየተጣደፉ ወደቤት እየሄዱ ነው። ጠበቃ ጓደኛውን አናግረው የልጃቸው ደም ከንቱ እንዳይቀር ፍትህ ለማግኘት ቋምጠዋል። ሰፈር እንደደረሱ ወደ ተማም ሱቅ አቀኑ። ልጃቸው አድርጊ እንዳላቸው ማድረግ ጀመሩ ። ወይዘሮ ሸምስዬ መሆናቸውን እንዳወቀ ተማም ፈገገ " እትዬ ሸምስያ እንዴት ኖት? " " አልሀምዱሊላህ ተምዬ ደህና ነህ? " " ወይ እትዬ ሸምስያ…" አለ በግርምት " አሁን ምን ልስጦት… እኔ ምለው እትዬ እንደው በአላህ እንዳይቀየሙኝ ድጋሚ ሆስፒታል ለመምጣት እኮ አልመች አለኝ… ይኸው ሱቅ የሚቆም ሰው የለም ግን እንደው እንዴት ነው እየተሻለው ነው? " " እስቲ ተወኝ …እንደው አላህ እሱን ያትርፍልኝ እንጂ እከሌ ጠየቀው እከሌ አልጠየቀውም የምል ይመስልሀል? " " አይ በፍፁም! " " እራስህን አታስጨንቅ ይልቅ አሁን የመጣሁት ጀሚሌ አንተ ጋ ስልክ አለ ከፍቶ ይስጥሽ ብሎኝ ነው እንደው ከሆስፒታል እየበረርኩ የመጣሁት… " " የትኛው ስልክ? " " እኔ ምን አውቄ ምንም የለም እንዴ አንተ ጋ? " " አሀ… አሀ የኔ ነገር እቃ ሲወደድ እኮ የማስታውሰው ነገርም ጠፋኝ ቆይ አንዴ… " " በል ፍጠን ቤት ቶሎ መድረስ አለብኝ። " ተማም በተባለው መሰረት ስልኩን ከፍቶ ለወይዘሮ ሸምስያ ሰጣቸው ስልኩን ከተቀበሉት ቡሀላ ወደ ቤት ገሰገሱ። ጀሚል ይህን ስልክ እጅግ በጣም አጣብቂኝ ውስጥ አልያም አደጋ ላይ ከሆነ ብቻ ነው የሚጠቀምበት። ታማኝ ወዳጆቹ ናቸው ልክ እንደሱ ይህን የሚጠቀሙት። ይህንን ስልክ ሁል ጊዜ ክፍት ሆኖ አይቀመጥም። እርዳታ የፈለገ ሰው ይደውላል ስልኩን የያዘው ሰው በቀን ቢያንስ ለተወሰኑ ሰዓታት አንዴ ክፍት ያደርገዋል። ስልኩ ሲከፈት የአሳውቁኝ መልዕክት ስለሚገባ ማን እንደደወለ በቀላሉ ይለያል። የደውለው ሰው ስልኩ በ10 ደቂቃ ውስጥ መልሶ ካልተደወለለት የተደወለለት ሰው አደጋ ላይ መሆኑን ተረድቶ በድጋሚ ደውሎ በሌሎች መሰሎቹ እርዳታ እንዲደረግለት ያደርጋል። : : ቢንያሚን በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆኖ የእናቱን መዳን ይጠባበቃል። የደረሰበት ጉዳት ለአፍታ ትዝ አይለውም ያጣውንና የሚያጣውን እያሰበ የመኖሩ ትርጉም ግራ ገብቶታል። የእናቱን ህመም በውል እንኳ አልተረዳም ወይዘሮ ሰብለ በሚስጥር ሸሽገውት ልጅነቱን ተጠቅመው ጭንቀት ብቻ መሆኑን አሳምነውት ወደ ማይቀረው አለም ሄደዋል ። " ወይኔ እማዬ …ምን አጥፍተን ይሆን?… አምላኬ ይቺን አለም በቅጡ ያልተረዳችን ህፃን የነጠቅከኝ ብቸኛ ሁን ያልከኝ ምን ብበድል ነው?… የመኖሬን ትርጉም የሳቄን ፍሬ መና ያስቀረኸው ምን ልታረገኝ ነው? ህ…እ …ይህን ሁሉ እንዳይ ነው? ወይ አትገለኝ ወይ አታኖረኝ ከሙታን በታች ያደረግከኝ ምን እንድሆን ነው? እኔ እናት ፣ አባት፣ እህትና ወንድም አያስፈልገኝም? መኖሬ ካልጠቀመ መሄዴም አይጎዳም! " እያለ ከአይኖቹ የእምባ ጎርፍ እያወረደ በልቡ ከአምላኩ ጋር ይሟገታ። የሚንከባከቡት ነርሶች መምጣት ሲጀምሩ ከሀሳቡ ተመለሰ ነርሶቹ የሚቀየርለትን ፋሻ ከቀየሩለት ቡሀላ ሊሄዱ ሲሉ " ይቅርታ አንዴ ዶክተርን ማናገር ፈልጌ ነበር? " " ምነው ችግር አለ ምናልባት የምትፈልገው ነገር ካለ …" " አይ ምንም የለም ዶክተሩን ማናገር ፈልጌ ነው እናቴን ማየት እፈልጋለው…" " እሺ አሁን ይመጣል " ብለው ዶክተሩን ለመጥራት ነርሶቹ ወጡ። ዶክተሩ ቢንያሚን የተኛበት ክፍል ገብቶ በቅድሚያ ስለ ጤንነቱ አንዳንድ ነገር ከጠየቀው በኋላ ለምን እንደፈለገው ጠየቀው " ዶክተር እናቴን ማየት እፈልጋለው? " " ይኸውልህ ቢንያሚን እናትህን ታያቸዋለህ ምንም ችግር የለም ነገር ግን እንዳየኸው አንተም በደንብ ሊሻልህ ይገባል እናትህ እስካሁን አልነቁም የቻልነውን ሁሉ እያደረግን ነው። " " ዶክተር ሰማኸኝ እናቴን ማየት እፈልጋለው እኔ ገና ለገና አልተሻለኝም ብዬ በእናቴ ናፍቆት መሰቃየት አልፈልግም የእናቴን እስትንፋስ መስማት እፈልጋለው! " " ይኸውልህ ቢኒ…" ብሎ ሳይጨርሰው ንዴትና እልህ ተደበላልቆበት " እናቴ ጋር ትወስደኛለህ አትወስደኝም!? " " እኔ አልወስድህም አላልኩም… " " እና አሁኑኑ ውሰደኛ…! " " እያልኩህ ያለውት ትንሽ ማገገም አለብህ ነው የምለው ቆመህ እንኳ በትክክል መራመድ መቻል አለብህ… " " ይኸው " ብሎ ለመነሳት ሲሞክር ከተቀመጠበት የአልጋ ጠርዝ ወደ መሬት ወደቀ ሁሉም በድንጋጤ ተረባርበው አነሱት። " ይኽን ነው የምልህ ቢኒ ገና አንተ እራሱ አልጠነከርክም… " " መራመድ አደል የቀረኝ ይኸው " ብሎ በድጋሚ ሊነሳ ሞከረ አቃተው። እልህ እና ንዴት ተጨማምሮ እምባውን ዘረገፈው … " ዶክተር እናቴ በህይወት እንዳለች ማየት እፈልጋለው ! ዶክተር ከህመሜ በላይ እኮ እሷ በህይወት አለች የለችም የሚለው ጭንቀት ሊገለኝ ነው እናቴ ጋ ውሰደኝ !!! " ንዴቱ እየጨመረ መጣ። " ቆይ ማን ስለሆንክ ነው ይምትከለክለኝ!? " " እኔ የመከልከል ስልጣን የለኝም አንተ ግን ተረጋጋ… " " አንድ ነገር ልንገርህ እናቴን ሳላያት ብትሞት ግን አንተም በህይወት አትኖርም ! " አለ ቢንያሚን ንዴቱና እልሁ ተቀላቅለው ሳግ እፍን እያደረገው። ዶክተሩ ሁሉም ነገር ከቁጥጥሩ ውጪ ሆነበት ያለው አማራጭ መፍቀድ ብቻ ሆነ። " አስቸጋሪ ሰው ነህ ቢኒ እናትህን አታይም ያልኩህ ከዚህ ሁኔታ እንድታገግም ነበር። ድርቅ አልክ አሁን ለትንሽ ደቂቃዎች ማየት ትችላለህ ነገር ግን ማልቀስም ሆነ ሌላ ነገር ማድረግ ፈፅሞ የተከለከለ ነው። አሁን እግሮቹ ስላልጠነከሩ ዊልቸር አምጡለትና አስገቡት እዛው እጠብቃቹኋለው። " ብሎ ዶክተሩ ተሰናብቶ ሄደ። ቢንያሚን የተስፋ ጭላንጭል ወገግ ያለለት ይመስል ፈገግ ብሎ እንባውን መጥረግ ጀመረ ። : : ወይዘሮ ሸምስያ መርማሪ ፖሊሶቹ ሳይደርሱ ቀድመው ደርሰዋል። እየተጣደፉ ኮመዲኖ ስር አለ የተባለውን ብር መፈለግ ጀመሩ። እንዳላቸው ከኮመዲኖው ግርጌ ሁለት ባለ 10 አና አንድ ባለ 5 ሺህ ብር በጥቁር ፌስታል ተጠቅልሎ ቁጭ ባሏል። ሰርተን ለፍተን ያመጣነው ነው ብሎ ስላላቸው የትም እንዳይባክን ሁነኛ ቦታ ለመደበቅ አሰቡ። ለጊዜው ከራሳቸው በላይ የሚያምኑት ስላልነበረ ብሩን አንስትው መቀነታቸው ላይ ከተው እላዩ ላይ ነብራማ ወፈር ያለ በብርድ ሰዓት የሚለበስ ፎጣ ደረቡበት። ከእናትነታቸው ተደማምሮ የደረቡት ፎጣ አግዝፏቸዋል ። የኮርኒሱ ጣራ ስር አለ ያላቸውን ለመፈለግ ወደ ቆጡ ሊወጡ ሲሉ መርማሪ ፖሊሶቹ ከተፍ አሉ። ቤቱን ሊፈትሹ እንደመጡና እንዲተባበሯቸው ጠየቋቸው ። ሰዉነታቸው ይንቀጠቀጣል። እንዳለውም ህይወቴን አደጋ ላይ ይጥለዋል ያላቸው እቃ ከተገኘ የልጃቸውን ህይወት በገዛ ፍቃዳቸው እንደሰውት ቆጥረው ፀፀቱ በድጋሚ ሌላ ጠባሳ ሊጨምርባቸው ነው። ደብቂ ስላላቸው እቃ ምንም አይነት ነገር አያውቁም። መርማሪ ፖሊሶቹ ቤቱን አብጠርጥረው እየፈተሹት ነው። በዚ መሀል ጀሚል ይደወልልሻል ብሎ ያላቸው ስልክ ጠራ። ፍትህ የተጠማው ልባቸው የነበረውን ጭንቀት ረስቶ የሀሴት ጮቤ ረግጦ የተደወለውን ስልክ ለማንሳት ከቤቱ ወጣ ብለው ማናገር ጀመሩ። የደወለላቸው ሰው ጀሚል አለመሆኑን ተረድቷል። ነገር ግን ሁሉንም ነገር ጀሚል እንዳመቻቸ ደግሞ ገብቶታል። የተፈጠረውን ሁሉ በእምባ እያደመቁ ተረኩለት። ዝም ብሎ ያዳምጣል። በመሀል ግን
5760Loading...
38
" ማን ነበር ስሙን ያሉኝ? " " ሳሙኤል ሀይሉ " " የት ፖሊስ ጣቢያ ነው ያለው? " " እ…እዚህ ሆስፒታሉ አቅራቢያ ያለው ፖሊስ ጣቢያ ነው…" " ምን ይባላል የፖሊስ ጣቢያው ስም? " " ምን አውቄ ብለህ ነው… አንዱን ስለው አንዱን ውክብ ብዬ እንደው ስሙን እንኳ መያዝ አቃተኝ…" " በቃ ችግር የለም እርሶ ይረጋጉ ደንበኛ ጠበቃ ስላለ በቅርቡ የሚፈልጉትን ያገኛሉ… " " እንደው አላህ ይባርክህ የእጅህን አትጣው…" እያሉ ምርቃታቸውን ሳይጨርሱ ስልኩ ተዘጋ። " አልሀምዱሊላህ ምን ይሳንሀል " አሉ ወይዘሮ ሸምሲያ። ወድያው ቤት ውስጥ እየፈተሹ ያሉ ፖሊሶች ትዝ ብለዋቸው እየተርበተበቱ ገቡ። ነገር ግን እስካሁን አንድም ያገኙት መረጃ አልነበረም። ወይዘሮ ሸምስያ ሰውነታቸው ይንቀጠቀጣል ላብ እያጠመቃቸው ነው ቀስ ብለው አይናቸውን ሰረቅ አርገው ወደ ቆጡ ጣራ ተመለከቱ ይህን እንቅስቃሴያቸውን ሲከታተል የነበረ አንድ መርማሪ ፖሊስ ትኩረቱን በሙሉ ጣራው ላይ አድርጎ ወጥተው እንዲፈትሹ ትዕዛዝ አስተላለፈ። የጣራውን ኮርኒስ መሀል ለመሀል ቀደዱት። ብዙ አዋራና የአይጦች አይነምድር ተቀላቅሎ ወረደ ከዛ መሀል ግን አንድ ዱቄት የመሰለ 200 ግራም የሚመዝን ሀሽሽ ተገኘ። የወይዘሮ ሸምስያ ልብ ለሁለት ስንጥቅ አለች። መርማሪ ፖሊሶቹ ጥርጣሬያቸውን ከፍ የሚያደርግላቸውን መረጃ አግኝተዋል። ከመኪና አደጋው ጀርባ ሌላ ትልቅ ወንጀል እየተካሄደና እየተፈፀመ እንዳለ በቂ መረጃ አግኝተዋል። አሁን የዚህን ወንጀል ዋነኛ አቀንቃኞችን ለመያዝ ሀይላቸውን አጠናክረው ቀጥለውበታል ። ( ቀዳዳ እኮ መስፋት አይጀምር እንጂ አይቆምም ይቀጥላል) April 2018 : @Venuee13 @Venuee13
6930Loading...
39
" እስከዛሬ ድረስ እኔና ወንድሜ ሰርተን ያጠራቀምነው ነው" " ምን ሰርታቹ ነው ይህን ያህል? " " እስር ቤት እንድበሰብስ ነው የምትፈልጊው? " " ኧረ አላህም አያደርገውም… " " ያልኩሽን አርጊ ይህን ብር…" "…ይህን ብር ቢያዩ ሰረቀ እንጂ ሰርቶ ነው አይሉም ሌላው ደሞ እነ ተማም ሱቅ ያስቀመጥኩት ስልክ አለ ከፍተህ ስጠኝ በይውና ተቀበዪው በሱ ስልክ ይደወልልሻል የማውቀው ጓደኛዬ ነው ጠበቃ ነው ሁሉንም ነገር አስረጂው ምንም ሳትደብቂ ንገሪው አንድ መፍትሄ ላይ እንደርሳለን። " " እሺ እንግዲህ አላህ ያውቃል… " " በይ አሁን እንዳታስፎግሪ አሁን በሙድ ንኪው " ወይዘሮ ሸምሲያ ጠበቃ ጓደኛ አለኝ የሚለው ንግግሩ ቀልባቸውን ገዝቶት የብሩንና ደብቂው ስለተባሉት እቃ ትኩረታቸው አጥተው በፍጥነት ሆስፒታሉን ለቀው ወደ ቤት በጥድፍያ መሄድ ጀመሩ ። ( ለጉድ የፈጠረው ጉዱ መች ያልቃል) April 2018 : @Venuee13 @Venuee13
4960Loading...
Photo unavailableShow in Telegram
« ኡራዝ ቪ» [አብዱልሀኪም ሰፋ] : ሁለት ወደ ኋላ: አንድ ወደፊት! : በስተመጨረሻ ነገ 7/9/2016 ይጀመራል! መልካም ንባብ ይሁንላችሁ! : @Venuee13 @Venuee13
Show all...
👍 11 5🔥 3
👍 3👎 2
~ስለተሰረቁ መስከረሞቻችን እንማልዳለን (እምላችሁ ስለዚህ ስለውዴታዬ ጉራማይሌ መፅሀፍን የሚሰጠኝ የለም?እጀግ የሚወዱት ነገር እጅ ለመግባት ለምን ይህን ያህል ዘመን እንደሚያስጠብቅ አይገባኝም) ነጃት ነኝ። @Venuee13
Show all...
3🔥 1🥰 1
እናንተ ምነው ቀኑ እሁድ መሆኑን ደበቃችሁ?
Show all...
😁 7🥰 2
ዛሬ ቅዳሜ ነው አሉ😳 ቀኑ ይሄደዋል ቢስሚላህ.... እኔ እፅፍ በነበረበት ወቅት የመጀመሪያው አስተያየት ቃላቶችሽ ከባድ ናቸው ነበር... እኔ ደግሞ በንግግር የምጠቀማቸውን አማርኛዎች(ሁሉም ከእናቴ የተወረሱ) ነው ምጠቀመው... እናላቼሁ አሁን ሳውራ ምን አልሽ ብለው ያስቆሙኝን ቃል ልንገራችሁ ቃሉ ... «ለደለደ» ወይም «ለድልዷል» የሚል ነው... ይህን ቃል ትርጉሙን እናውቃለን ብላችሁ ገላግሉኝ እስቲ😂 ነጃት ነኝ። @Venuee13
Show all...
🤔 7😁 4👍 2👏 1
❤‍🔥 6👍 1😢 1
Photo unavailableShow in Telegram
በቅርብ ቀን በመድረክ ላይ እንገናኛለን! እስከዛ ድረስ ባላችሁ የሶሻል ሚድያ አካውንቶች በማስተዋወቅ እንድትቆዩኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ!🙏 . @huluezih @huluezih
Show all...
👍 10 3🤔 1
« ሙትቻ ላሉህ ሰዎች እራስህን ለማስረዳት አትሞክር። ለሞትክባቸው ሰዎች የምታባክነው ጊዜ አይኑርህ። ውበትህ ግለፅ ሲወጣ የመጣ ሁሉ ውበትህን አይቶ ላይሆን ይችላልናበ አመዳምነት ዘመንህ ላይ ውበትህ የታያቸውን ጠበቅ አድርገህ ያዝ። ቆንጆ መሆንሽን ከሚያደንቁት የበለጠ የሚያስጠላብሽን ሊያስውቡልሽ የሚጣጣሩትን አትዘንጊ። ቁስልሽን በሰው አትከልዪ። የሚመክሩሽ ሁሉም ከጥቃት አይጠብቁሽም። ጥንቃቄ የብልሆች መንገድ ነው። በጣም ነፃነት በሚሰማሽ ሰው በኩል ስስ ነሽና አትራቆቺ። ዋጋ የምትከፍዪላቸው ከጌታሽ መንገድ እንዳያስቱሽ አስተውዩ! የምወድሽዋ ልብሽን በቀደር አረጋጊ! የምወድህዋ እራስህ ካልወደቅክ አይጥሉህምና በጌታህ ታግዘህ ፅና። መንገዱ ምን እንዳለው አይታወቅምና ሰላም ለልባችሁ! » [አብዱልሀኪም ሰፋ] : @Venuee13 @Venuee13
Show all...
👍 10 8🙏 3🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
« የራሴ አላረግህ ነገር ነውር ነህ፣ አልርቅህ ነገር ርቄ አልርቅህም። አላመሰግንብህ ነገር ስህተቴ ነህ። አልመኝህ ነገር የተከለከልከኝ ነህ። እንዴት ያለ ቻይነት አምላኬ ቢያስታጥቀኝ ሞከረኝ? ምናል ለአይንህ ጌታዬ ብርሀን ባይሰጠው? ምናል ሰይጣኔ ለሩሄ አንተን እንድጠላ ጥላቻ ሹክ አላለውም? ፍቅሬም፣ ትዝታዬም ሁሉም ወንጀል! » [አብዱልሀኪም ሰፋ] እስከ 7/9/16 ድረስ በደንብ ተብሰልሰሉበት! : @Venuee13 @Venuee13
Show all...
😢 9💔 7
Show all...
💔 18👍 2😢 2